Sinksar tube(ስንክሳር)
Відкрити в Telegram
እኔ ቅዱስ ነኛና ቅዱሳን ሁኑ 1ጴጥ 1:15
Показати більшеКраїна не вказанаКатегорія не вказана
3 018
Підписники
+4924 години
+1067 днів
+24130 днів
Архів дописів
3 018
🎯 ከዘማሪያን የማንን መዝሙር ማዳመጥ ይፈልጋሉ?
┏•••••••••••••••••••••••••••••••┓
🎤 ሊቀ መዘምራን ቴዎድሮስ ዮሴፍ 🎤
┗•••••••••••••••••••••••••••••••┛
┏•••••••••••••••••••••••••••••••┓
🎤 ሊቀ መዘምራን ይልማ ኃይሉ 🎤
┗•••••••••••••••••••••••••••••••┛
┏•••••••••••••••••••••••••••••••┓
🎤 ሊቀ መዘምራን ኪነጥበብ 🎤
┗•••••••••••••••••••••••••••••••┛
┏•••••••••••••••••••••••••••••••┓
🎤 ዘማሪ አቤል መክብብ 🎤
┗•••••••••••••••••••••••••••••••┛
┏•••••••••••••••••••••••••••••••┓
🎤ዘማሪት ሲስተር ህይወት ተፈራ🎤
┗•••••••••••••••••••••••••••••••┛
┏•••••••••••••••••••••••••••••••┓
🎤ዘማሪ ዲያቆን ሙሉቀን ከበደ🎤
┗•••••••••••••••••••••••••••••••┛
┏•••••••••••••••••••••••••••••••┓
🎤 ቀሲስ ምንዳዬ ብርሃኑ 🎤
┗•••••••••••••••••••••••••••••••┛
┏•••••••••••••••••••••••••••••••┓
🎚 ዘማሪት ፋሲካ ድንቁ 🎚
┗•••••••••••••••••••••••••••••••┛
🎤 የሁሉንም ዘማሪያን መዝሙር ለማግኘት 🔔 👇
🫧🫧🫧🫧🫧🫧🫧🫧🫧🫧🫧🫧🫧🫧
3 018
✞✞✞ ✝በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ ፡፡ አሜን ፡፡ ✝✞✞✞
✞✞✞✝ እንኩዋን ለነቢዩ #ቅዱስ_ዮናስ እና ለእናታችን #ቅድስት_አውፎምያ ዓመታዊ የዕረፍት በዓል በሰላም አደረሳችሁ ✞✞✞✝
✞✞✞ ✝ቅዱስ ዮናስ ነቢይ✝ ✞✞✞=>በቤተ ክርስቲያን አስተምሕሮ ከ12ቱ #ደቂቀ_ነቢያት አንዱ የሆነው #ቅዱስ_ዮናስ ከክርስቶስ ልደት 800 ዓመታት በፊት እንደ ነበረ ይታመናል:: #ሊቃውንት እንዳስተማሩን ደግሞ እናቱ #ቅዱስ_ኤልያስን የመገበችው የሰራፕታዋ መበለት ናት:: ቅዱስ ዮናስ ገና ሕጻን ሳለ በእሥራኤል ምድር ዝናብ ለ3 ዓመታት ከ6 ወራት ተከልክሎ ነበር:: +ይሕንንም ያደረገው ደጉ ነቢይ ኤልያስ ለአምልኮተ እግዚአብሔር ቀንቶ ነው:: በወቅቱ ኤልያስ በሰራፕታ ሳለ ሕጻኑ ዮናስ ታሞ ሞተ:: ልጇ የሞተባት መበለትም ኤልያስን ለመነችው:: ኤልያስም ወደ ፈጣሪው ማልዶ ሕጻኑን ዮናስን ከሞት አስነስቶታል:: ትንሽ ከፍ ባለ ጊዜም ከጉዋደኞቹ (ከነቢያቱ) #አብድዩና #ኤልሳዕ ጋር ሆነው ታላቁን ነቢይ ኤልያስን ተከትለውታል:: +ኤልያስ ካረገ በሁዋላ ሁሉም በየተሰጣቸው አገልግሎት ተሠማርተዋል:: ቅዱስ ዮናስን #እግዚአብሔር "ወደ ነነዌ ሒደሕ ንስሃን ስበክ" አለው:: ዮናስ ግን የፈጣሪውን መሐሪነት ጠንቅቆ ያውቃልና አልሔድም አለ:: (ተመልከቱ የየዋሕነት ብዛት) +እግዚአብሔር እየደጋገመ እንዲሔድ ሲነግረው ነቢዩ "እንዲሕ የሚዘበዝበኝ ከፊቱ ብቀመጥ አይደል" ብሎ ሊኮበልል ወጣ:: ነገር ግን አልቀናውም:: በእርሱ ምክንያት ማዕበል ተነሳ:: ሕዝቡም ሊያልቁ ሆነ:: ከእንቅልፉ የነቃው ዮናስ ከመርከቡ ላሉት አሕዛብ አምልኮተ እግዚአብሔርን ሰብኮላቸው: በእርሱ ጠያቂነት ሐምሌ 15 ቀን ወደ ባሕር ጥለውታል:: +አሣ አንበሪም ተቀብሎታል:: በግዙፉ አሣ ውስጥም ያለ እንቅልፍ በጾም: በጸሎትና በምስጋና 3 ለቀን ቆይቷል:: ሙስና ሳያገኘውም በዚህች ቀን አሣ አንበሪው #ነነዌ ዳር ላይ ተፍቶታል:: ቅዱስ ዮናስ እግዚአብሔር እንዳዘዘው "እስከ ሠሉስ ዕለት ትትገፈታእ ነነዌ ዓባይ ሃገር" /እስከ ሦስት ቀን ድረስ ነነዌ ትገለበጣለች (ዮናስ 3:4)/ ብሎ አሰምቶ ሰበከ:: +የነነዌ ሰዎችም በስብከተ ዮናስ አምነው: ንስሃም ገብተው ድነዋል:: በዚህም ጌታችን በወንጌል ላይ አመስግኗቸዋል:: ቅዱስ ዮናስ መኮብለሉ #በሐዲስ_ኪዳን ለሚደረገው ምስጢረ ትንሳኤ ጥላ (ምሳሌ) ነውና ይደነቃል:: (ማቴ. 12:38) ነቢዩ ግን በተረፈ ሕይወቱ ሕዝቡን ሲያስተምር: ፈጣሪውን ሲያገለግል ኑሮ በመልካም ሽምግልና ዐርፏል::
+"+ ቅድስት አውፎምያ ሰማዕት +"+=>እናታችን #ቅድስት_አውፎምያ (ስሟ አፎምያ አይደለም:: በስሕተት "ው" መካከል ላይ የገባች እንዳይመስልዎ:: እስመ ከመዝ ስማ-ስሟ እንዲሁ ነው የሚጠራው) በ3ኛው መቶ ክ/ዘመን ከነበሩ ወጣት ክርስቲያኖች አንዷ ናት:: ገና ከልጅነቷ ልቧ በፍቅረ ክርስቶስ የተነደፈ ነበር:: +በዚህም ምክንያት ራሷን በጾምና በጸሎት ወስና ትኖር ነበር:: እድሜዋ ገና በአሥራዎቹ ቢሆንም በመንኖ ጥሪት መኖር ምርጫዋ ነበር:: ሊቃውንት አበው ከሰማዕትነቷ ደርበው "ጻድቅት አውፎምያ" እያሉም ይጠሯታል:: +አንድ ቀን ግን መንገድ ወጥታ ነበርና ክርስቲያኖች ሲሰቃዩ ተመለከተች:: ምንም ጥፋት ሳይገኝባቸው ክርስቶስን ስላመለኩ ብቻ ይሙት በቃ ተፈርዶባቸው ሊገደሉ እየተወሰዱ ነበር:: አሕዛብ ግብራቸው የአውሬ ነውና ርሕራሔ የላቸውም:: ሰማዕታቱ ደማቸው በየመንገዱ እየፈሰሰ ጥቁር ሰንሰለት በአንገታቸው: በእጃቸውና በእግራቸው ላይ አድርገው ይጐትቷቸው ነበር:: +ቅድስት አውፎምያ የተደረገውን ሁሉ ተመልክታ አምርራ አለቀሰች:: ፈጠን ብላም ወደ መኮንኑ ቀርባ ገሰጸችው:: "አንተ አእምሮ የጎደለህ! እንዴት ክርስቲያኖችን እንዲህ ታሰቃያለህ? አምላካቸው #ጌታ_ክርስቶስ ታጋሽ ባይሆን ኑሮ በቅጽበት ከገጸ ምድር ባጠፋህ ነበር" አለችው:: +በድፍረቷ የተገረመው መኮንኑ "አንቺስ ማንን ታመልኪያለሽ?" ሲል ጠየቃት:: እርሷም "ሰማይና ምድርን የፈጠረውን: ስለ እኛ ሲል በቀራንዮ አንባ የተሠዋውን #ኢየሱስ ክርስቶስን አመልካለሁ" ስትል መለሰችለት:: በዚያች ሰዓት የመኮንኑ ቁጣ በቅድስቷ ላይ ነደደ:: +ነገር ግን ቁጣውን ከቁም ነገር አልቆጠረችውምና እንዲያሰቃዩዋት አዘዘ:: ወታደሮቹ ሥጋዋን በብዙ አሰቃዩ:: ብላቴናዋ አውፎምያ ግን ጽንዕት ናትና አልቻሏትም:: በመጨረሻ በእሳት ተቃጥላ ትሞት ዘንድ ተፈረደባት:: +እሳቱ ከመሬት ከፍ ባለ ጊዜ ወደ ውስጥ ወረወሯት:: በእሳቱ መካከል ቁማ ለረዥም ጊዜ ጸለየች:: ከዚያም ነፍሷን አሳልፋ ሰጠች:: ምዕመናን በክብር ገንዘው ቀብረዋታል:: =>አምላካችን ከነቢዩና ከሰማዕቷ ወዳጆቹ በረከት ይክፈለን:: =>ሐምሌ 17 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት= 1.ቅዱስ ዮናስ ነቢይ (ከአሣ አንበሪ ሆድ የወጣበት) 2.ቅድስት አውፎምያ (ጻድቅትና ሰማዕት) 3.ቅዱስ ዮስጦስ ሰማዕት (ታላቁ) 4.ቅዱስ ዘካርያስ =>ወርኀዊ በዓላት 1.ቅዱስ እስጢፋኖስ ሊቀ ዲያቆናት (ቀዳሜ ሰማዕት) 2.ቅዱስ ያዕቆብ ሐዋርያ (ወልደ ዘብዴዎስ) 3.ቅዱሳን አበው መክሲሞስና ዱማቴዎስ 4.አባ ገሪማ ዘመደራ 5.አባ ዸላሞን ፈላሢ 6.አባ ለትጹን የዋህ 7.ቅዱስ ኤዺፋንዮስ ሊቅ (ዘደሴተ ቆዽሮስ) =>+"+ በዚያን ጊዜ ከጻፎችና ከፈሪሳውያን አንዳንዶቹ መለሱና:- 'መምሕር ሆይ! ከአንተ ምልክት እንድናይ እንወዳለን' አሉት:: እርሱ ግን መልሶ እንዲህ አላቸው:- 'ክፉና አመንዝራ ትውልድ ምልክት ይሻል:: ከነቢዩም ከዮናስ ምልክት በቀር ምልክት አይሰጠውም:: ዮናስ በአሣ አንበሪ ሆድ ሦስት ቀንና ሦስት ሌሊት እንደ ነበረ እንዲሁ የሰው ልጅ በምድር ልብ ሦስት ቀንና ሦስት ሌሊት ይኖራል:: የነነዌ ሰዎች በፍርድ ቀን ከዚህ ትውልድ ጋር ተነስተው ይፈርዱበታል:: በዮናስ ስብከት ንስሃ ገብተዋልና:: እነሆም ከዮናስ የሚበልጥ ከዚህ አለ:: +"+ (ማቴ. 12:38) <<< ወስብሐት ለእግዚአብሔር >>> 🔵TELEGRAM 🔴 YOUTUBE
3 018
🎯 ከዘማሪያን የማንን መዝሙር ማዳመጥ ይፈልጋሉ?
┏•••••••••••••••••••••••••••••••┓
🎤 ሊቀ መዘምራን ቴዎድሮስ ዮሴፍ 🎤
┗•••••••••••••••••••••••••••••••┛
┏•••••••••••••••••••••••••••••••┓
🎤 ሊቀ መዘምራን ይልማ ኃይሉ 🎤
┗•••••••••••••••••••••••••••••••┛
┏•••••••••••••••••••••••••••••••┓
🎤 ሊቀ መዘምራን ኪነጥበብ 🎤
┗•••••••••••••••••••••••••••••••┛
┏•••••••••••••••••••••••••••••••┓
🎤 ዘማሪ አቤል መክብብ 🎤
┗•••••••••••••••••••••••••••••••┛
┏•••••••••••••••••••••••••••••••┓
🎤ዘማሪት ሲስተር ህይወት ተፈራ🎤
┗•••••••••••••••••••••••••••••••┛
┏•••••••••••••••••••••••••••••••┓
🎤ዘማሪ ዲያቆን ሙሉቀን ከበደ🎤
┗•••••••••••••••••••••••••••••••┛
┏•••••••••••••••••••••••••••••••┓
🎤 ቀሲስ ምንዳዬ ብርሃኑ 🎤
┗•••••••••••••••••••••••••••••••┛
┏•••••••••••••••••••••••••••••••┓
🎚 ዘማሪት ፋሲካ ድንቁ 🎚
┗•••••••••••••••••••••••••••••••┛
🎤 የሁሉንም ዘማሪያን መዝሙር ለማግኘት 🔔 👇
🫧🫧🫧🫧🫧🫧🫧🫧🫧🫧🫧🫧🫧🫧
3 018
📖 ስለ ምልጃ በሃያ ክፍል የተጠየቁ ጥያቄዎች እና በጽሑፍ የተመለሱ (የተላለፉ) ትምህርቶች በእነዚህ ሊንኮች ይገኛል👇
📖 አማላጅ ማለት ምን ማለት ነው❓
📖 ማማለድ ምንድን ነው❓
📖 አማላጅ የምንለው ማንን ነው❓
📖 የቅዱሳን አማላጅነት ለምን አስፈለገ❓
📖 የቅዱሳን አማላጅነት በብሉይ ኪዳን እና በአዲስ ኪዳን❓
📖 የቅዱሳን መላእክት አገልግሎቶች ምን ምን ናቸው❓
📖 የቅዱሳን መላእክት አማላጅነት እንዴት ይገለጻል❓
📖 የእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም አማላጅነት እና ተራዳኢነት ስንል ምን ማለታችን ነው❓
📖 ክርስቶስ አማላጅ ነው? አምላክ ነውና ወደ ማን ይማልዳል❓
ይ🀄️ላ🀄️ሉ 👇
🤗https://t.me/addlist/sZA2UFcsVPplMjI0
3 018
💠የንስሐ ◇የሽብሻቦ ◇ወረብ ◇የቅዱሳን እንዲሁም የመላእክት መዝሙር የምትፈልጉ ከሆነ አሁኑኑ JOIN በሉት ይሄ ቻናል ምርጥ ምርጥ መዝሙሮችን በጥራትና በፍጥነት ያሳያል። 𝐉𝐨𝐢𝐧👇👇👇
https://t.me/addlist/sZA2UFcsVPplMjI0
3 018
አንድ አምላክ በሚሆን በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም አሜን
ሐምሌ 16- ‹‹ወንጌሉ ዘወርቅ›› የተባለ ታላቁ አባት አቡነ ዮሐንስ ዕረፍታቸው ነው፡፡ አባታችን ሀገራቸው ሮም ሲሆን ወላጆቻቸውም ደጋግ ባለጸጋ የሆኑ ክርስቲያኖች ስለነበሩ ለመምህር ሰጥተው መጻሕፍትን እየተማሩ እንዲያድጉ አደረጓቸው፡፡ በኋላም ገበታው የወርቅ የሆነ ወንጌልን ያሠራላቸው ዘንድ አባታቸውን ለመኑትና አሠራላቸው፡፡ ያንንም ወንጌል ዕለት ዕለት ያነቡት ነበር፡፡ ኢየሩሳሌም ሲሄድ ወላጆቻቸው ቤት የሚያርፍ አንድን መነኩሴ እንዲወስዳቸው ለመኑትና ወደ ገዳሙ በስውር ይዟቸው ሄደ፡፡ የገዳሙ አበ ምኔትም ዮሐንስን አመነኮሷቸው፡፡
ከዚህም በኋላ ሥጋቸው አልቆ አጥንታቸው እስኪታይ ድረስ በታላቅ ተጋድሎ ኖሩ፡፡ አበ ምኔቱም ድካማቸውን እንዲቀንሱ ይመክሯቸው ነበር፡፡ እግዚአብሔርም በራእይ ወደ አባታቸው ቤት እንዲሄዱ አመላከታቸውና ለአበ ምኔቱ ነግረው ወደ ባለጸጋው አባታቸው ዘንድ ሄዱ፡፡ በመንገድ ላይም አንድ ነዳይ አገኙና ልብሳቸውን ቀይረውት የነዳዩን ልብስ ለብሰው ሄደው በአባታቸው ደጅ ማንም ሳያውቃቸው ለማኝ መስለው ተቀመጡ፡፡ በአባታቸው ደጅም በጾም በጸሎት እየተጋደሉ የአባታቸው ባሪያዎች የሚጥሉትን ፍርፋሪ እየተመገቡ 7 ዓመት ተቀመጡ፡፡
እናታቸውም ከቤት በወጡ ጊዜ ሽታቸው እየከረፋቸው ትጨነቅ ነበር፡፡ ዕረፍታቸውም በቀረበ ጊዜ የታዘዘ መልአክ ለአቡነ ዮሐንስ ተገልጦላቸው የዕረፍታቸውን ጊዜ ነገራቸው፡፡ ወዲያውም ወደ እናታቸውም ሰው ልከው ስትመጣላቸው ልጇ መሆናቸውን ሳይነግሯት በሚሞቱ ሰዓት በዚያች በለበሷት እራፍ የነዳይ ጨርቅ ብቻ ጠቅልለው እንዲቀብሯቸው ነገሯት፡፡ ‹‹በሞትኩም ጊዜ ይህን መጽሐፍ በአስክሬኔ ላይ አንብቡልኝ›› ብለው የወርቅ ወንጌላቸውን ጠቅልለው ሰጧት፡፡ አባታቸውም በመጣ ጊዜ ያንን የወርቅ ወንጌል ባየ ጊዜ ልጁ እንደሆነ ዐወቀና መሪር ዕንባን አለቀሰ፡፡ ሁሉም አብረው ተላቀሱ፡፡ የሮም ከተማ ሽማግሌዎችና ሕዝቡም ተሰበሰቡ፡፡ አቡነ ዮሐንስም ሰባት ቀን ሲሆናቸው ሐምሌ 16 ቀን ዐረፉ፡፡ እናታቸውም ባማሩና በተዋቡ ንጹሕ ጨርቆች እንዲገነዙ ስታደርግ ወዲያው ታመመች ነገር ግን አባታቸው በእራፊ ጨርቃቸው እንዲገንዟቸው ያዘዟቸውን አስታውሰው ቀድሞ በለበሱት እራፊ ጭርቅ ሲገንዟቸው ተመልሳ ዳነች፡፡ የአቡነ ዮሐንስ ረድኤት በረከታቸው ይደርብን በጸሎታቸው ይማረን!
+++
ዳግመኛም በዚህ ዕለት ኢትዮጵያዊው ጻድቅ ዕድሜ ልካቸውን እናትና አባታቸውን እንኳን ባለመናገር ዘረኝነትን ከሀገራችን ያጠፉ ታለቁ አባት አባታችን አቡነ ዳንኤል ዘቦረና ዕረፍታቸው ።
አቡነ ዳንኤል ዘቦረና፦ እኚህ ጻድቅ አባት አንድ ትልቅ ግብር አላቸው፤ ይኸውም ዕድሜ ልካቸውን እናትና አባታቸውን እንኳን ባለመናገር ዘረኝነትን ከሀገራችን ያጠፋ ታላቅ ጻድቅ አባት ናቸው። ግድ ብለው አጥብቀው ሲይዟቸው "እናቴ አክሱም አለች፤ አባቴም ልጇ ነው" በማለት ዘረኝነትን በዘመናቸው አጥፍተዋል።
ቦረና ሳይንት ባለው ገዳማቸው ውስጥ የሚገኘውን ባለ፡ሦስት ዓምድ ገድላቸውን ደርቡሾች ከጠባቂው በትንሽ ገንዘብ ገዝተው ወስደውታል። እርሱም በመቅሰፍት ተመቶ ሞቷል። ጻድቁ በሀገራችን ከ 250 በላይ አብያተ ክርስቲናትን አሠርተዋል። መካነ መቃብራቸው በጋስጫ ይገኛል"።
3 018
ዐሥራ ኹለት ክንፍ የተሰጣቸው ታላቁ ኢትዮጵያዊ ጻድቅ አቡነ ሐዋርያ ክርስቶስ ሐምሌ 16 ቀን ልደታቸው ነው፡፡
አቡነ ሐዋርያ ክርስቶስ፡- አቡነ ሐዋርያ ክርስቶስ የትውልድ ሀገራቸው ሸዋ መርሐ ቤቴ ነው፡፡ እንደ እነ ኤልያስና ሄኖክ ተሰውረዋል እንጂ በምድር ላይ ሞትን አልቀመሱም፣ ገና ወደፊት መጥተው በሰማዕትነት ይሞታሉ፡፡ ልደታቸው ሐምሌ 16 ቀን ነው፡፡ የነበሩበት ዘመንም በጻድቁ ንጉሥ በዐፄ ገብረ ማርያም ሐርበይ ዘመን ነው፡፡ ጻድቁን መልአኩ ከሚያገለግሉበት ከወሎ የህላ ሚካኤል ወደ ደብረ በንኮል ገዳም ወስዷቸው እንዲመነኩሱ አድርጓቸዋል፡፡ የቆረቆሩት ‹‹አቡነ ሐዋርያ ክርስቶስ ገዳም›› ወሎ መሐል ተከዜ ውስጥ ይገኛል፡፡ የበዛው ገድላቸው በዝርዝር ተጽፎ አይገኝም፡፡ ተከዜ በረሃ ላይ እጅግ አስደናቂ ትልቅ የአንድነት ገዳም አላቸው፡፡ 12 ክንፍ የተሰጣቸው ታላቁ ጻድቅ አቡነ ሐዋርያ ክርስቶስ በዛሬዋ ዕለት ነው የተሠወሩት፡፡ ረድኤት በረከታቸው ይደርብን፣ በጸሎታቸው ይማረን፡፡
3 018
3 018
3 018
✝✝††† እንኳን ለታላቁ ሊቅና አፈ በረከት ቅዱስ ኤፍሬም ሶርያዊ ዓመታዊ የዕረፍት በዓል በሰላም አደረሳችሁ፣ አደረሰን። †††
†††✝ በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን! †††✝
††† ✝ቅዱስ ማሪ ኤፍሬም ሶርያዊ ✝†††††† እንደ ቤተ ክርስቲያናችን ትውፊት ቅዱስ ኤፍሬም የተወለደው ንጽቢን በምትባል የሶርያ ግዛት ውስጥ በ298 / 306 ዓ/ም ነው:: ወላጆቹ በክርስቶስ የማያምኑ አላውያን ነበሩ:: (ምንም አንዳንድ ምንጮች ክርስቲያኖች ነበሩ ቢሉም) ቅዱሱ ተወልዶ ባደገባት ንጽቢን ጵጵስናን የተሾመ ቅዱስ ያዕቆብ የሚባል ታላቅ ሰው ነበር:: የሰማዕትነት: የሐዋርያነት: የጻድቅነትና የሊቅነት ግብር ያለው አባት ነው:: ታዲያ ቅዱስ ኤፍሬም ይሔ አባት ሁሌ ሲያስተምር ይሰማው ነበርና በስብከቱ ተማርኮ ደቀ መዝሙሩ ለመሆን በቃ:: ቅዱስ ኤፍሬም በቅዱስ ያዕቆብ እጅ ከተጠመቀ በኋላ ሙሉ የወጣትነት ጊዜውን ያሳለፈው በትምሕርት ነው:: የሚገርመው መምሕሩ ቅዱስ ያዕቆብ ዘንጽቢን እመቤታችን ድንግል ማርያምን በፍጹም ልቡ የሚወድና ጠርቷት የማይጠግብ አባት ነውና ለልጁ ለቅዱስ ኤፍሬም ይሕንኑ አጥብቆ አስተምሮታል:: ቅዱስ ኤፍሬም ክርስትናን ሲመረምር የእመቤታችን ፍቅር ይበዛለት ጀመር:: ምክንያቱም እመ ብርሃንን ሳይወዱ ክርስትና የለምና:: እንደ እርሱ የሚወዳት የለም እስኪባል ድረስ ያገለግላት: ይገዛላትም ገባ:: እንዲህ እንደ ዛሬ የድንግል ማርያም ምስጋና በአንደበት እንጂ በመጽሐፍ አይገኝም ነበር:: እርሱ ግን ከወንጌለ ሉቃስ በስድስተኛው ወርን (ይዌድስዋን) እና ጸሎተ ማርያምን(ታዐብዮን) አውጥቶ በየዕለቱ በዕድሜዋ ልክ ስልሳ አራት ስልሳ አራት ጊዜ ያመሰግናት ነበር:: በእንዲህ ያለ ግብር እያለ አርዮስ በመካዱ እርሱን ለማውገዝና ሥርዓተ ቤተ ክርስቲያንን ለማጽናት በ317 (325) ዓ.ም ሦስት መቶ አሥራ ስምንቱ ሊቃውንት በኒቅያ ሲሰበሰቡ አንዱ መምሕረ ኤፍሬም ቅዱስ ያዕቆብ ነበር:: በዚህ ምክንያት ቅዱስ ኤፍሬም ከሊቃውንቱ ትምሕርትና በረከትን አግኝቷል:: ከጉባዔ መልስ መንገድ ላይ በራዕይ የብርሃን ምሰሶ አይቶ "ጌታ ሆይ! ምንድን ነው?" ብሎ ቢጠይቅ "ይሕማ ታላቁ ቅዱስ ባስልዮስ ነው::" አለው:: እርሱም መምሕሩን ቅዱስ ያዕቆብን ተሰናብቶ ወደ ቅዱስ ባስልዮስ (ቂሣርያ) ወረደ:: ተገናኝተውም በአንድ ሌሊት ቋንቋ ተገልጦላቸው ሲጨዋወቱ አድረዋል:: በቦታው ብዙ ተአምራት ተደርጓል:: ቅዱስ ኤፍሬም ከታላቁ ባስልዮስ ከተማረ በኋላ ሃገረ ስብከት ተሰጥቶት ያስተምር ጀመር:: ሁል ጊዜ ታዲያ ጸሎቱ ይሔው ነበር:: "እመቤቴ ሆይ! ምስጋናሽ እንደ ሰማይ ከዋክብት: እንደ ባሕር አሽዋ በዝቶልኝ: እንደ እንጀራ ተመግቤው: እንደ ውኃ ጠጥቼው: እንደ ልብስም ተጐናጽፌው" እያለ ይመኝ ነበር:: አፍጣኒተ ረድኤት: ፈጻሚተ ፈቃድ እመ ብርሃንም በገሃድ ተገልጻ የልቡን ፈቃድ ፈጸመችለት:: ዛሬ ጸጋ በረከት የምናገኝበትን ውዳሴ ማርያምን ደረሰላት:: ሲደርስላትም እርሷ አእላፍ መላእክትን: ጻድቃን ሰማዕታትን አስከትላ ወርዳ: በፊቱም ተቀምጣ ሲሆን እርሱ ደግሞ ባጭር ታጥቆ: በፊቷ ቆሞ: በመንፈስ ቅዱስም ተቃኝቶ ነው:: ውዳሴዋን በሰባት ቀናት ከደረሰላት በኋላ በብርሃን መስቀል ባርካው: ሊቀ ሊቃውንትም እንዲሆን ምሥጢር ገልጣለት ዐረገች:: ከዚህ በኋላ በምሥጢር ባሕር ውስጥ ዋኝቶ አሥራ አራት ሺህ ድርሰቶችንም ደርሷል:: ዛሬ ሶርያ ውስጥ የምንሰማውን ዜማም የደረሰው ይህ ቅዱስ ነው:: እንዲያውም አንድ ቀን የምሥጢር ማዕበል ቢያማታው "አሃዝ እግዚኦ መዋግደ ጸጋከ" ብሎ ጸልዩዋል:: (የጸጋህን ማዕበል ያዝልኝ) እንደ ማለት ነው:: ቅዱስ ኤፍሬም ሶርያዊ በመጨረሻ ሕይወቱ ተክሪት በምትባል ሃገር ኤጲስ ቆጶስ ሆኖ ተሹሟል:: በጣፋጭ ስብከቱ ብዙዎችን ካለማመን መልሷል:: የምዕመናንንም ሕይወት አጣፍጧል:: ለመናፍቃንና ለአርዮሳውያን ግን የማይጋፉት ግድግዳ ሆኖባቸው ኑሯል:: በዘመኑም ብዙ ተጋድሎ አፍርቷል:: ተአምራትንም ሠርቷል:: በተወለደ በስልሳ ሰባት ዓመቱ በ365 (373) ዓ.ም ዐርፎ ተቀብሯል:: ††† ቅዱሱ ለሶርያ ብቻ ሳይሆን እመቤታችንን ለምንወድ የዓለም ክርስቲያኖች ሁሉ ሞገሳችን ሆኗል:: ስለዚህም እንዲህ እያልን እንጠራዋለን:- 1.ቅዱስ ኤፍሬም 2.ማሪ ኤፍሬም 3.አፈ በረከት ኤፍሬም 4.ሊቀ ሊቃውንት ኤፍሬም 5.ጥዑመ ልሳን ኤፍሬም 6.አበ ምዕመናን ኤፍሬም 7.ርቱዐ ሃይማኖት ኤፍሬም . . . አባታችን አንተ ነህ:: ††† ጽንዕት በድንግልና: ሥርጉት በቅድስና እመቤታችን ለቅዱስ ኤፍሬም የሰጠሽውን ጸጋውን: ክብሩን: አእምሮውን: ለብዎውን በልቡናችን ሳይብን: አሳድሪብን . . . አሜን::
†††✝ ጴጥሮስ ወጳውሎስ ✝†††††† ዳግመኛ በዚህ ቀን ብርሃናተ ዓለም ጴጥሮስ ወጳውሎስ ይታሠባሉ:: ቅዱሳኑ ሶርያ አካባቢ ውስጥ ወደምትገኝ አንዲት ሃገር ገብተው ሕዝቡን ከንጉሣቸው ጰራግሞስ ጋር አሳምነው አጥምቀዋል:: ነገር ግን እነርሱ ሲወጡ ሰይጣን አስቶት አጥፊ ሰው ወደ መሆን ተመልሶ ንጉሡ ሐዋርያትን አሰቃይቷቸዋል:: ስለ ቅዱሳኑ ግን ፈረሶቹ ሰግደው: በሰው አንደበት ቅድስናቸውን መስክረዋል:: በመጨረሻም ንጉሡን ከነ ሕዝቡና ሠራዊቱ በዓየር ላይ ሰቅለው ንስሐ ሰጥተውታል:: በእነዚህ ተአምራትም ሁሉም አምነው ለከተማዋና ለሕዝቡ ድኅነት ተደርጓል:: ††† ✝ከአባቶቻችን አበው ሐዋርያት በረከት ይክፈለን::✝ ††† ሐምሌ 15 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት 1.ቅዱስ ማሪ ኤፍሬም ሶርያዊ (አፈ በረከት) 2.ብርሃናተ ዓለም ቅዱሳን ሐዋርያት ጴጥሮስ ወጳውሎስ 3.አባ ሓርዮንና ደቀ መዛሙርቱ (ሰማዕታት) 4.አባ ፍሬምናጦስ መስተጋድል ††† ወርኀዊ በዓላት 1.ቅዱስ ቂርቆስና እናቱ ኢየሉጣ 2.ቅዱስ ሚናስ (ማር ሚና) ሰማዕት 3.ቅድስት እንባ መሪና 4.ቅድስት ክርስጢና ††† "ለምኑ ይሰጣችሁማል:: ፈልጉ ታገኙማላችሁ:: መዝጊያ አንኳኩ ይከፈትላችሁማል:: የሚለምነው ሁሉ ይቀበላልና:: የሚፈልገውም ያገኛል:: መዝጊያንም ለሚያንኳኳ ይከፈትለታል::" ††† (ማቴ. ፯፥፯) ††† "የጻድቅ አፍ ጥበብን ያስተምራል:: አንደበቱም ፍርድን ይናገራል:: የአምላኩ ሕግ በልቡ ውስጥ ነው:: በእርምጃውም አይሰናከልም::" ††† (መዝ. ፴፯፥፴) 🔵TELEGRAM 🔴 YOUTUBE
