uk
Feedback

Не попадись на ботовода! Telemetrio знаходить і позначає такі канали мітками 👉 Хочеш бачити мітку, оформляй підписку

ወደ ኢየሱስ ደረት

ወደ ኢየሱስ ደረት

Відкрити в Telegram

Romans 8÷1 There is therefore now no condemnation to them which are in Christ Jesus, who walk not after the flesh, but after the Spirit.

Показати більше
Країна не вказанаКатегорія не вказана
276
Підписники
-124 години
-27 днів
-630 днів
Архів дописів
ለመጨረሻ ጊዜ ለብቻችሁን በፀሎት ከጌታ ጋር የተገናኛችሁት ቀኑ መች ነበር
Anonymous voting

አንድ ነገር አነበብኩ እና በጣም ስለገረመኝ share ባደርግላችው ብዬ ነው እንዲህ ይላል....
አንዳንዴ ትላልቅ መፈሳዊ Encounteroch ወደ ህይወታቹ ለማስተናገድ የኔ የምትሏቸውን ነገሮች ከህይወታቹ መሸኘት ሊኖርባቹ ይችላል፤ ያዕቆብ ትዝ ይላቹ ከሆነ ለአንድ ቀንም እንኳን ተለይቷቸው መኖር የማይችላቸውን ሚስቶቹን እና ልጆቹን ጨክኖ የያቦቅ ወንዝን ካሳገር በኃላ ነበር እግዚአብሔር ብቻውን አግኝቶት ታሪኩን የቀየረለት፤ የተወደዳቹ ምናልባት በእናንተ እና በእግዚአብሔር መካከል የገቡ ልባቹን በየቀኑ የያዙ ጉዳዮች ብቻቹን ሊያገኛቹ ለሚፈልገው ለእግዚአብሔር መሰናክል ሆነውበትስ ቢሆኑ ብላቹ አስባቹ አታውቁም ? እኛ ትልቅ ቁም ነገር ያየዘ ጉዳይ ለሰው መንገር ስንፈልግ ያ ሰው ተረጋግቶና ብቻውን ሲሆን ጠብቀን  ልንነግረው እንደምንፈልግ  ልክ እንደዛ እግዚአብሔር እናንተ ብቻቹን ስትሆኑለት ብቻ ጠብቆ ሊነግራቹ የሚፈልገው ትልቅ ጉዳይ እንዳለው ማስተዋል ይኖርባቿል። ብቻቹን ሁኑለት፤ ብቻቹን ይፈልጋቿል !

አስር_ጊዜ_ባይህ_10_gize_bayih_ዮሴፍ_አስቻለው_Yosef_Aschalew256k.mp35.96 MB

ትልቅ መልዕክት ነው ክርስትናችን ቃላት ሳይቀላለፅ እና ሳይደረደር ይታወቅልን በኢየሱስ ስም🙌 አንድ መፅሀፍ ቅዱስ ላይ የሚገርመኝ ክፍል አለ ማቴ 26÷73 በዚህ ክፍል ጴጥሮስ በክህደት ውስጥ ሆኖ ሳለ(ቁ73)አንድ ነገር ተፈጠረ እንዲህም ተባለ አንተ ከኢየሱስ ጋር ቆይተሀል! ብለው አሉት ምክንያቱም ኢየሱስ ሲያስተምር ሰምተውታል እና ጴጥሮስ ከኢየሱስ ጋር ነበር እንደ ኢየሱስ ነበር የሚናገረው እና እንዲታወቅበት አልፈለገም ነበር ነገር ግን ከማን ጋር እንደቆየ አነጋገሩ አስታወቀበት ይገርማል ይህን ያክል የቆየንበት የሰነበትንበት የከረምንበት ይህወታችንን ይወስናል እየቆየን ያለነው በአለም ነው ወይስ ኢየሱስ ጋር ማንነት ይፈተሽ 🙏 ከላይ ያለውን ሀሳብ ሳነብ ገረመኝ እና ይህ ህይወት ያስፈልገናል....... መድረክ ወተን ሳንሰብክ ህይወታችን ይስበክልን ሳንዘምር ህይወታችን ይዘምርልን ሳንፈልግ እንኳን ኢየሱስ ኢየሱስ የምል ጠረን......

ክርስትና በምላስ ብቻ የሚነገር ሳይሆን በሕይወት የሚታይ ነው። ሰዎች ቃላችንን ከመስማታቸው በፊት ሕይወታችንን ያነባሉ። ፍቅርን እየተናገርን ጥላቻን ከኖርን፣ ትሕትናን እየሰበክን በኩራት ከተመላለስን፣ ስለ ይቅርታ እየተናገርን ይቅር ማለት ካልቻልን ቃላችን ኃይል ያጣል። እውነተኛ ክርስትና የሚገለጠው በምንናገረው ሳይሆን በምንኖረው ነው። በጨለማ ውስጥ ብርሃን መሆን፣ በጥላቻ መካከል ፍቅርን ማሳየት፣ በተሰበሩ ልቦች አጠገብ መቆም፣ የተበደሉን ይቅር ማለት እና ለሌሎች በጎ ማድረግ ነው። ኢየሱስ ሰዎችን ወደ ራሱ የሳበው በቃላቱ ብቻ ሳይሆን በኑሮው ነበር። ስለዚህ እኛም ክርስቶስን በአንደበታችን ብቻ ሳይሆን በሕይወታችን እንመስክር። ምክንያቱም አንዳንድ ሰዎች የሚያነቡት ብቸኛው ወንጌል የእኛ ሕይወት ሊሆን ይችላል። አፍ ብቻ ሳይሆን ህይወታችንም ይናገር🙏

ውሎዬን ለጌታዬ ደስታ እስኪ ዛሬ ለራሳችን challeng እንስጥ ቀን ይውጣልን እና እግ/ር እንደሚወደው እንዋል! በምናደርገው ነገር ሁሉ፦ ➡እግ/ር ይከብር ይሁን ? ➡ይወደው ይሁን? እያልን የእግ/ር ደስታ እያስቀደምን የስጋችንን ደስታ ትተን እራሳችንን እየጠየቅን እንዋል እስቲ በዚህ ውስጥ ያለው ሰላም እና ርካታ ሚወራ እና ሚገለፅ አደለም እስቲ ዛሬ ኖረን ምናወራ ሰዎች እንሁን መልካም ጌታን የማስደሰት ውሎ ይሁንላችሁ 🙌

እግዚጨብሔር ይመስገን🙏

‎#ወደ_እግዚአብሔር_ማደግ! ‎ ‎➣ ወደ እግዚአብሔር ማደግ ማለት የእግዚአብሔርን መልክና ባሕርይ በሕይወታችን ውስጥ እየገለጥን መሄድ ማለት ነው። ‎➣ የዕድገታችን መጨረሻው ክርስቶስን መምሰል ነው። ‎👉 ማደግ በሕይወት የመኖራችን ማሳያ/ ምልክት ነው ‎👉 ወደ እግ/ር ማደግ ለክርስቲያን አማራጩ ሳይሆን ግደታው ነው፣ ‎👉 ወደ ማን እያደግን እንደሆነ እድገታችን ያስታውቃል፣ ‎ ‎❌ ብዙዎቻችን ማደግ እንፈልጋለን ግን ለመንፈሳዊ ዕድገት የምረዱ ነገሮችን ለማድረግ አንፈልግም‼️ ‎ ‎ወደ እግዚአብሔር ለማደግ መሠረታዊ መንገዶች ‎ ‎1. በቃሉ መመገብ (የዕውቀት ዕድገት) ‎ ‎➭ መንፈሳዊ ዕድገት የሚጀምረው እግዚአብሔርን በማወቅ ነው። ‎➭ ቃሉን ሳናነብና ሳናጠና የእግዚአብሔርን ፈቃድ ማወቅ አንችልም። ‎👉 "ጌታ ቸር መሆኑን ቀምሳችሁ እንደ ሆነ፥ ለመዳን በእርሱ እንድታድጉ አሁን እንደ ተወለዱ ሕፃናት ተንኮል የሌለበትን የቃልን ወተት ተመኙ።" (1ኛ ጴጥሮስ 2:2-3) ‎➣ ቃሉን ሁልጊዜ በመመገብ መኖር ወደ ጌታ እንድናድግ አቅም ይሆናል። ‎ ‎2. የጸሎት ሕይወት (የግንኙነት ዕድገት) ‎ ‎✔️ ጸሎት ከፈጣሪ ጋር የምንገናኝበት ድልድይ ነው። ✔️ ማደግ የሚፈልግ ሰው ከእግዚአብሔር ጋር ምስጢር መለዋወጥና በፊቱ መቆየት አለበት። ‎"ሳታቋርጡ ጸልዩ፤ በሁሉ አመስግኑ፤ ይህ የእግዚአብሔር ፈቃድ በክርስቶስ ኢየሱስ ወደ እናንተ ነውና።" (1ኛ ተሰሎንቄ 5:17-18) ‎➣ የማያቋርጥ የጸሎት ሕይወት ‎ ‎3. በመንፈስ ቅዱስ መመራት (የኃይል ዕድገት) ‎ ‎ክርስቲያናዊ ሕይወት በራስ ጥረት ብቻ የሚኖር አይደለም። መንፈስ ቅዱስ በውስጣችን እንዲሠራና እንዲመራን መፍቀድ አለብን። "ነገር ግን እላለሁ፥ በመንፈስ ተመላለሱ፥ የሥጋንም ምኞት ከቶ አትፈጽሙ።" (ገላትያ 5:16) ‎ ‎4. በቅድስና መመላለስ (የባሕርይ ዕድገት) ‎ ‎እግዚአብሔር ቅዱስ ስለሆነ፣ ወደ እርሱ የሚጠጋ ሰው ራሱን ከዓለም ቆሻሻና ከኃጢአት መጠበቅ አለበት። "እኔ ቅዱስ ነኝና ቅዱሳን ሁኑ ተብሎ ተጽፎአልና።" (1ኛ ጴጥሮስ 1:16) .................ይቀጥላል (tesfa s)

.             ሀብተ ሰማይ ዘማሪት ሀና ተክሌ|Live Worship sʜᴀʀᴇ◈sʜᴀʀᴇ◈sʜᴀʀᴇ ማርከን ዜማ @Markenzema_bot በዚህ ቻናል የማይደመጥ መዝሙር የለም ብቻ ምን አለፋችሁ join ይበሉ  👇 https://t.me/+S2wsmZMSQp3vcGxp https://t.me/+S2wsmZMSQp3vcGxp

እንፀልይ🙏 ቅዱስ እግዚአብሔር ሆይ አንድ ነገር እንፀልያለን በክርስትና ጉዞ ላይ የመንፈስ ቅዱስ ሀይል በድካማችን ምክንያት ርቆናል አባት ሆይ፤ ብዙ ነገር እየመጣብን መንፈሳዊ አቅማችንን እየገደለው ነው እርዳን እባክህ 🙌ጌታ ሆይ መንፈስ ቅዱስን ተቀብለናል ነገር ግን ሀይሉ ከእኛ ርቋል በዚህም ምክንያት እየጠፋን ነው ጉዞ ከብዶናል አባታችን ሆይ እንፀልያለን ፂዮናችንን ሳንደርስ ድካም ተጫጭኖናል ስለዚህ መጎብኘትን እንሻለን፤ ጌታ ሆይ ሀይልህ ያስፈልገናል ሀይላችንን አድስልን፤ክብርህ ሀይልህ አብዛልን ጌታ ሆይ ከላይ ከፀባኦት ሀይልህን አፍስስብን እንደገና መንፈስ ቅዱስ በውስጣችን ሳይበርድ እና ሳይቀዘቅዝ  በኢየሱስ ስም ይስራብን ሲሰራም ይታወቀን ከአሁን ሰአት ጀምሮ እግሮቻችን ዙረት የሚያበዙ ሳይሆኑ የሚበረከኩ፤ እጆቼ ለቃልህ አይኖቼም ለቃልህ የፈጠኑ ይሁኑ እራሴን ላንተ አሳልፌ ሰጠው ሀይልህ በስልጣን ይገለጥብኝ ...ስለሰማኸን እናመሰግናለን ስለምትመልስልንም እናመሰግናለን ውድ በሆነው እና በምትወደው በልጅህ በኢየሱ ስም          አሜን🙌

"ቆይቼ ልጥና ደጅህን ደጋግሜ ላንኳኳ በርህን ብትወድ በሀይለኛው ንፋስህ ብትወድ በነበልባል እሳትህ ብትወድ ዝም ባለው ፀጥታህ ብትወድ በትንሿ ኮሽታ ብቻ አንተ ና አንተ ብቻ ና"😭 ህሊና ካሳሁን ፍለጋ        sʜᴀʀᴇ◈sʜᴀʀᴇ◈sʜᴀʀᴇ                  Video Watch        ማርከን ዜማ @Markenzema_bot                       በዚህ ቻናል የማይደመጥ መዝሙር የለም ብቻ ምን አለፋችሁ join ይበሉ                            👇                          https://t.me/+S2wsmZMSQp3vcGxp                          https://t.me/+S2wsmZMSQp3vcGxp

የእግዚአብሔር ምሕረት ካለፈው ስህተትህና ከበደልህ በላይ የሚሰፋ፣ ተስፋ በቆረጥክበትና ራስህን በኮነንክበት ቅጽበት እንኳ በታላቅ ርኅራሄ የሚቀበልህ ሕያው እቅፍ ነው፤ እርሱ አንተን ይቅር ለማለትና አዲስ ሕይወት ለመስጠት ፍጹም እንድትሆን አይጠብቅም፣ ይልቁንም በቅንነትና በሰበረ ልብ ወደ እርሱ ስትቀርብ ኃጢአትህን ከምሥራቅ እስከ ምዕራብ አርቆ በምሕረቱ ያጥብሃል። ስለዚህ በሕይወትህ ውስጥ ምንም ያህል ብትደናቀፍና የሕሊና ወቀሳ ቢከብድህ እንኳ፣ የእርሱ ይቅርታ ካንተ ውድቀት ሁልጊዜ እንደሚበልጥ አስተውለህ፣ ሳትፈራና ሳታቅማማ ወደ ጸጋው ዙፋን በመቅረብ ሸክምህን በእርሱ ላይ ማሳረፍና ልብህን በሰላም መሙላት ብቸኛ አማራጭ ነው።🙌

የኢየሱስ ክርስቶስ መልካምነት ስብራታችንንና ውድቀታችንን በፍፁም ርኅራሄና ያለ ምንም ቅድመ-ሁኔታ የሚጠግን፣ ማንም በሌለበት የብቸኝነትና የጭንቀት ማዕበል ውስጥ "አትፍሩ እኔ ከእናንተ ጋር ነኝ" እያለ ልባችንን በሰላም የሚሞላ ሕያው የፍቅር መግለጫ ነው። እርሱ ፍጹም መሆናችንን ሳይጠብቅ በደካማነታችን የመጣ፣ በሕይወቱ ትልቅ ዋጋ ከፍሎ ያዳነንና ሸክማችንን ሁሉ በቅንነት የምናሳርፍበት ታማኝ እረኛችን በመሆኑ፤ በሕይወታችን ውስጥ ምንም ዓይነት ከባድ ፈተና ቢገጥመን እንኳ በእርሱ የማይለወጥ መልካምነት ላይ ተደግፈን፣ ጭንቀታችንን ለእርሱ ሰጥተን በፍቅሩ እረፍት እናገኛለን። ወንድሞቼ እና እህቶቼ ጊዜ ወደማይለውጠው በደዚህ ጌታ ደረት እንድንጠጋ መንፈስ ቅዱስ ይርዳን🙏

ለቤተክርስትያን በረከት እንጂ መርገም አንሁን! በውሎዬ አንድ ነገር አስተዋልኩ ምንድነው እሱ በእግ/ር ቤት ውስጥ ለምንድን ነው የእግዚአብሄር የመለኮቱ ክብር እንደጥንቱ በሀይል ማይገለጠው? ብዬ ሳስብ ነበር።በተለያየ angle አምልኮ አለን ግን የእግ/ር መንፈስ ክብሩ የለንም የደረቀን አገልግሎት ስጋ ሞቅ ሚልበትን አገልግሎት እያገለገልን ነው።ትውልድ ሆይ ልንነቃ ያስፈልጋል ለምን ድነው ብዬ እራሴን ስጠይቅ እንዲ ተሰማኝ እግዚአብሄር በባህሪው ቅዱስ ነው የሚገኘውም በተቀደሰ ስፍራ ነው፤ስለዚህ እኛ አገልጋዮች ያልተሰራን ህይወት፤ያልተገታ አደበትን ድርጊት ይዘን ስላለን የእግ/ር ክብር በእኛ መሀከል ኢ ካቦድ ሆኑዋል፤የእግ/ርን ማደሪያ/መገኛውን በተለያዩ ነገር ሞላነው ለዚህም ሀይል ከዳር ሆነ፤የቅድስና ህይወት የለንም ግን ስለቅድስና እንዘምራለን እንሰብካለን ብቻ ብዙ ብዙ ነገር ስለዚህ ስለዚህ የአንደበት ክርስትና ሳይሆን በህይወት ነሚገለጥ በተግባር የሚታይ ክርስትና ሊኖረን ይገባል ዛሬም እግ/ር በገዛቤቱ ማደርን መገኘትን መመለክን ይፈልጋል። ስለዚህ እንመለስ፤ በእኛ ሀጥናት መርገም ምክንያት ጥሩ ህይወት ከእግ/ር ጋር ላላቸው ሰዎች እና ለቤተክርስቲያን መርገም እንዳንሆን፤ እግ/ር ደሞ ክብሩን አያስነካም፤ስለዚህ እግ/ር ዝም ስላለን ዝም እንዳንል በቸልተኝነት እንዳንኖር ፤እግ/ር እንድንመለስ ይነግረናል በቁጣ ሳይመጣብን ቶሎ ንስሀ እንግባ🧎‍➡️ እኔ ለቤተክርስቲያን መርገም እንዳልሆን ጌታሆይ ቀድሰኝ አሜን🙌 እራሳችንን እንመልከት🧎‍♀

እንታደግ ክርስትናን መሠረት በማድረግ፣ ራስን ከዚህ ዓለም ኃጢአት፣ ክፋትና ፈተናዎች ጠብቆ ማቆየት (ቅድስናን መኖር) ጥልቅ መንፈሳዊ ጉዞ ነው። መጽሐፍ ቅዱስ በሮሜ 12፥2 ላይ “የእግዚአብሔር ፈቃድ እርሱም በጎና ደስ የሚያሰኝ ፍጹምም የሆነው ምን እንደ ሆነ ፈትናችሁ ታውቁ ዘንድ በልባችሁ መታደስ ተለወጡ እንጂ ይህን ዓለም አትምሰሉ” በማለት ይመክረናል። ​ራስን ከዓለም ኃጢአት ለመታደግና በመንፈሳዊ ሕይወት ለመጽናት የሚረዱ ዋና ዋና መጽሐፍ ቅዱሳዊና ክርስቲያናዊ ምክሮችን እንደሚከተለው በዝርዝር ማየት ይቻላል፦ ​1. የልብ መታደስና የሀሳብ ቁጥጥር ​ኃጢአት የሚጀምረው ከውስጥ፣ ከሰው ሀሳብና ፍላጎት ነው። ስለዚህ መከላከያው መጀመር ያለበት ልብንና አእምሮን በመጠበቅ ነው። ​በእግዚአብሔር ቃል መሞላት፦ መዝሙረኛው “በአንተ ላይ ኃጢአትን እንዳልሠራ፥ ቃልህን በልቤ ሰወርሁ” (መዝሙር 119፥11) ይላል። የአምላክን ቃል ዘወትር ማጥናት፣ ማስተንተንና በልብ ማኖር ለፈተናዎች ፈጣን ጋሻ ይሆናል። ​አእምሮን በጥሩ ነገር መሙላት፦ ሐዋርያው ጳውሎስ እንዳለው እውነተኛ፣ ንጹህ፣ ፍቅር ያለበትና መልካም ወሬ ያለውን ነገር ማሰብ (ፊልጵስዩስ 4፥8)። የዓለምን አስከፊና መርዛማ የሆኑ ምስሎች፣ ቃላትና አስተሳሰቦች ወደ አእምሯችን እንዳይገቡ በር መዝጋት ያስፈልጋል። ​2. ጸሎትና ንቁ ሆኖ መጠበቅ (ትጋት) ​ፈተናዎች በድንገትና ባልታሰበ መንገድ ሊመጡ ይችላሉ። ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ “ወደ ፈተና እንዳትገቡ ትጉና ጸልዩ” (ማቴዎስ 26፥41) ብሏል። ​የዘወትር ግንኙነት፦ ጸሎት ከፈጣሪ ጋር የምንገናኝበትና መንፈሳዊ ኃይል የምናገኝበት መንገድ ነው። በራሳችን ብርታት ኃጢአትን ማሸነፍ አንችልም፤ የጸጋው ረዳትነት ግን ያበረታናል። ​ራስን መመርመር፦ በየቀኑ መጨረሻ ላይ “ዛሬ በሃሳቤ፣ በንግግሬና በተግባሬ እግዚአብሔርን የሚያሳዝን ምን አደረግኩ?” ብሎ ራስን መጠየቅና ንስሐ መግባት። ​3. ከፈተናዎችና ከክፉ አጋጣሚዎች መሸሽ ​አንዳንድ ጊዜ ኃጢአትን ፊት ለፊት ተጋፍጦ ማሸነፍ ሳይሆን ከመነሻው መሸሽ መጽሐፍ ቅዱሳዊ ጥበብ ነው። ​የዮሴፍ ምሳሌ፦ የጶጢፋራ ሚስት በፈተነችው ጊዜ ዮሴፍ ተከራክሮ ለማሸነፍ አልሞከረም፤ ልብሱን ጥሎ ሸሸ (ዘፍጥረት 39)። ​ክፉ ጓደኝነትን ማስወገድ፦ “ክፉ ባልንጀርነት መልካሙን አመል ያጠፋል” (1 ቆሮንቶስ 15፥33)። ወደ ኃጢአትና ወደ ዓለማዊ ሕይወት የሚጎትቱንን ወዳጅነቶችና አካባቢዎችን በቆራጥነት መለየት ያስፈልጋል። ​4. የእግዚአብሔርን ሙሉ የጦር ዕቃ መልበስ ​ሐዋርያው ጳውሎስ በኤፌሶን 6፥11-18 ላይ የገለጸውን መንፈሳዊ የጦር ዕቃ ዘወትር መልበስ ከክፉው መከላከያ ነው። ​የእውነት መታጠቂያ እና የጽድቅ ጥሩር። ​የእምነት ጋሻ፦ የክፉውን የእሳት ፍላጾች ሁሉ ለማጥፋት የሚረዳ። ​የመዳን ራስ ቁር እና የመንፈስ ሰይፍ (እሱም የእግዚአብሔር ቃል ነው)። ​5. በቤተክርስቲያንና በቅዱሳን ኅብረት ውስጥ መኖር ​ብቸኝነት ለፈተና ያጋልጣል። አንድ የከሰል ፍም ከሌሎቹ ፍሞች ሲለይ በፍጥነት እንደሚጠፋ ሁሉ፣ አንድ ክርስቲያንም ከኅብረት ሲወጣ ይቀዘቅዛል። ​መንፈሳዊ ጓደኞች፦ አብረው የሚጸልዩ፣ በመንፈሳዊ ሕይወት የሚገስጹና የሚያበረታቱ ጓደኞችን መያዝ። ​የምስጢራተ ቤተክርስቲያን ተካፋይ መሆን፦ ንስሐ መግባት፣ ቅዱስ ቁርባን መቀበልና በጉባኤያት መገኘት መንፈሳዊ ኃይልንና ጥንካሬን ይሰጣል። ​6. ዓላማንና ዘላለማዊነትን ማሰብ መተው ​ይህ ዓለምና ምኞቱ ሁሉ አላፊ መሆኑን ማሰብ ራስን ለመጠበቅ ትልቅ ጉልበት ነው። ​“ዓለሙም ምኞቱም ያልፋሉ፤ የእግዚአብሔርን ፈቃድ የሚያደርግ ግን ለዘላለም ይኖራል” (1 ዮሐንስ 2፥17)። ​እኛ የዚህ ዓለም መጻተኞችና እንግዶች መሆናችንን ማወቅ (1 ጴጥሮስ 2፥11)። ዋናው ግባችንና ቤታችን ሰማያዊው መንግሥት መሆኑን ስንረዳ፣ የዓለም ኃጢአትና ጊዜያዊ ደስታ ክብደታቸውን ያጣሉ። "ጌታ ይርዳን" ✍Lukas

እንዘምር ለጌታ🎤🎸🎹🎧🎤 ☑️ይብዛልኝ መታዘዜ ዘማሪ በረከት ለማ ግራና ቀኜን ላንተ ትጉ አድርገው ቀንሳለ ልሩጥህ መንግስትህን ላስፋው ደጆቼ ተከፍተው ብርሃኔም በርቶ የመንግስትህ ጉዳይ ያጥምደኝ በዝቶ ይብዛልኝ መታዘዜ ይብዛልኝ ላንተ መሮጤ ይብዛልኝ የመንግስትህ ጉዳይ ይክበደኝ ከሌላው በላይ ኢያኤል ያቺ ሴት ግራዋም ቀኙዎም ታዛዥ በድንኳን ከሚኖሩ ከሴቶች ይልቅ የተለየች ውሀ ለለመነ ወተት ሰጪ በከበረ ዳካ ሲሳራን የዘረረችው በእግሯ ስር አጋድማ ግራዋን ለካስማ ቀኝ እጇን ለመዶሻ በጥበብ የተሞላች ጠላትን የዘረረች የሆነች ታታሪ ለመንግስትህ ሰሪ የሆነች ሰራተኛ ለስራህ የማትተኛ ግራና ቀኜን ላንተ ታታሪ አድርገው ቀንሳለ ልሩጥህ መንግስትህን ላስፋው ደጆቼ ተከፍተው ብርሃኔም በርቶ የመንግስትህ ጉዳይ ያጥምደኝ በዝቶ ይብዛልኝ መታዘዜ ይብዛልኝ ላንተ መሮጤ ይብዛልኝ የመንግስትህ ጉዳይ ይክበደኝ ከሌላው በላይ በችግር በመከራ በፅናት ወንጌል ሰባኪ በድንጋይ ተወግሮ ማልዶ ለወንጌል ዘማች ግርፋት ደዌ ማያስቆመው በእፉኝት መነደፍ ዕለት ዕለት ሚያሳስበው የመንግስትህ መስፋት ሁልጊዜ ደስ የሚለው ታስሮ እንኳን የማይከፋው እንደ ጳውሎስ የጀገነ እስከ ሞት የቆረጠ የሆነ ሰራተኛ ለወንጌል የማይተኛ የሆነ ታታሪ ለመንግስትህ ሰሪ በዚች አጭር እድሜ መላኬን ዘንግቼ ለራሴ ጉዳይ እንዳይሆን ሩጫዬ ከእናቴ ማህፀን ጀምሮ ከለየኝ የኔ ብሎ እሮጣለሁኝ ከስጋ ከደም አልማከርም *2 ይብዛልኝ መታዘዜ ይብዛልኝ ላንተ መሮጤ ይብዛልኝ የመንግስትህ ጉዳይ ይክበደኝ ከሌላው በላይ sʜᴀʀᴇ◈sʜᴀʀᴇ◈sʜᴀʀᴇ እንዘምር ለጌታ https://t.me/beka_tm ✅ ▷ https://t.me/inzemirlegeta ◁✅ 🔺ይ🀄️ላ🀄️ሉ

Repost from N/a
🤗ሰይጣን ምን አጠፋ ጌታ ተማምኖበት እዮብ ካልታመነ፣ ባህያና ግመል አይኑን ከደቀነ፣ ስሞላ ዘምሮ በጉድለት ከካደ፣ በአለት ተደግፎ ከተንገዳገደ፣ በእየሱስ አንግቶ በአለም ካመሸ፣ ሰይጣን ምን አጠፋ ሰው ከተበላሸ። የምድር ሀብት ከሆነ የአቋሙ መግለጫ፣ ዝናን ካተኮረ ፍለጋው ባብላጫ፣ ስደላው አምልኮ ስከፋው ብሄድ ጥሎ፣ እሱስ ስላለው ነው የሚያመልከው ብሎ፣ ሰይጣን ምን አጠፋ ምግባሩን ስሎ። በዘላለሙ ርስት እምነቱ ካልፀና፣ አላፊውን አንብቦ ብወድቅ በፈተና፣ ስነግሩት ቸል ብሎ ወዶ ከተደፋ፣ እዮብ ካልታመነ ሰይጣን ምን አጠፋ። ✍ አላዘር

ይቅር ‎ ‎አንተን አደብዝዞ ራስን ማሳየቱ ‎የሚገባህን ክብር ለሌላ መስጠቱ ‎ይቅርብኝ አባቴ በማትገኝበት በዛ ውሎ ማደር ‎አንተን ችላ ብሎ ከንቱ ኑሮ መኖር. ‎የዚህ ዓለም ክብር ሀብት እውቀት ዝና ‎ካንተ ጋር ካልሆነ መባከን ነውና ‎ምን ዋጋ አለው ጌታ ሁሉን የኔ ባደርግ ‎አንተ ካልተደሰትክ ካልሆንከኝ ወግ ማረግ. ‎ክብሬ ሞገሴ ውበት ማንነቴ ‎የሕይወቴ ድምቀት የመኖር ምክንያቴ ‎የሳቄ ሚስጥር የደስታዬ ምንጩ ‎ኢየሱስ አንተ ነህ ሕይወቴን ለዋጩ. ‎ሺ አደባባይ አንተ የሌለህበት ‎መንፈስህ እርቆ ባዶ ከሆነበት ‎ምን ያረግልኛል በሰዎች መታወቅ ‎አንተ በሌለህበት በዛ ራስን ማድመቅ. ‎ሁሉ ነገር ሞልቶ አንተን ግን አጥቼ ‎ከቶ አልችልምና ልኖር ተደስቼ ‎ይቅርብኝ ብያለሁ ይቅር ሁሉም ነገር ‎ያለኝ ነገር ሁሉ ይሁን ላንተ ክብር.... (T.s)

ሀይላችን እግዚሐብሄር ነው! 🔺ሰዎች ብዙውን ጊዜ ጥንካሬ ከየት ነው የመጣው?  ሀይልህ/ሽ የቱ ጋር ነው? ማን ነው? ብለው ሲጠይቁን የራሳችንን ጥንካሬ ስናወራ ነው ውድቀታችን ሚጀምረው ። ♦️መጽሐፈ መሣፍንት 16:17-18 ላይ ሶምሶን የኃይሉ ምልክት ፀጉሩ እንደሆነ ተናግሮአል፣ ግን እውነተኛው ኃይሉ ከእግዚአብሔር ነበር። ፀጉሩ ራሱ ኃይል አልነበረውም፤ ከእግዚአብሔር ጋር ያለው የኪዳን ምልክት ነበር። ስለዚህ ሶምሶን የወደቀው ፀጉሩ ብቻ ስለተቆረጠ ሳይሆን ለእግዚአብሔር የተለየ ሕይወትን ስለናቀ ነው። ሰው በውበቱ፣ በገንዘቡ፣ በጥበቡ ወይም በጉልበቱ ሲመካ ውድቀት ይጀምራል። ሶምሶንም የኃይሉ ምንጭ እግዚአብሔር መሆኑን ከመግለጥ ይልቅ በፀጉሩ ምልክት ላይ አተኮረ። ነገር ግን እውነተኛው ኃይል ከእግዚአብሔር ነው። ስለዚህ  ለራሳችን ሆነ ለሌላ ሰው የምንሰጠው ምላሽ ከእግ/ር ያራርቀናል ይልቁን“ኃይሌ እግዚአብሔር ነው” ብለን እንመካ።💪