ፍኖተ-አማራ ሚዲያ (Finote Amhara Media)
Открыть в Telegram
የተመሠረተው የአማራን ሕዝብ ለማንቃት፣ ለማደራጀት እና ለማስተባበር ነው። የአማራ ሕዝብን ✅ ፖለቲካዊ ✅ ማህበራዊ ✅ ኢኮኖሚያዊ ታሪካዊ ጥያቄዎችን ለማሰማት እና የአማራን ሕዝብ በማንቃት ሰፊውን ሕዝብ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ይሰራል። ወደዱም ጠሉም የኃላ ታሪካችን በእኛ እጅ ይፃፋል። አማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ ( አፋብን)
Больше4 379
Подписчики
-924 часа
+2477 дней
+1 42930 дней
Архив постов
የጥንቃቄ መረጃ
እጅግ አስደንጋጭ መረጃ
በደቡብ ክልል የተከሰተው ገዳዩ የሁሞሮጅክ ፌቨር በሽታ በመከላከያ ውስጥ ወታደሮችን እየገደለ መሆኑን ከሰራዊቱ የተገኘ ሚስጢራዊ መረጃ ያመለክታል።
የመረጃ ምንጫችን እንዳረጋገጠው በሽታው ወደ መከላከያው ሊገባ የቻለው ለእረፍት ቤተሰቡን ለመጠየቅ ወደ ጅንካ አምርቶ የነበረ አንድ የመከላከያ መኮነን ጂንካ በቆየበት ወቅት የቅርብ ቤተሰቡን ለማሳከም ወደ ጅንካ ሆስፒታል አቅንቶ ነበር።በሽታው ከሆስፒታሉ ሰራተኞች ወደ መከላከያ አባሉ ሳይተላለፍ እንዳልቀረ የመረጃ ምንጫችን ጠቁሞናል።
የመከላከያ አባሉ ከእረፍት ከተመለሰ በኋላ ከፍተኛ ትኩሳት እና በአፍ እና በአፍንጫው ደም ፈሶች እንደነበርና ከበርካታ ሰራዊት ጋር ተነካክቶ ስለነበር እርሱን ጨምሮ በርካታ የሰራዊቱ አክላት ለሞት ተዳርገዋል።
አገዛዙ ሰራዊቱ ይበተናል በሚል ስጋት በሚስጢር ቢይዘውም በየቀኑ የሚሞቱት እና የሚታመሙት ቁጥር ከፍተኛ ደረጃ ደርሷል።
ከሊቅ እስከ ደቂቅ የተሳተፈበት የህዝብ መድረክ በታሪካዊቷ ማጀቴ ከተማ ተካሔደ!
የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል ደቡብ አማራ ቀጠና አሳምነው ዕዝ ዓፄ ዘርዓ ያዕቆብ ፩ኛ ኮር በታሪካዊቷ ማጀቴ ከታማ ከሊቅ እክከ ደቂቅ የዕዙ አመራሮችና የዓፄ ዘራዓ ያዕቆብ ፩ኛ ኮር ከፍተኛ አመራሮች በተገኙበት የህዝብ መድረክ ተካሔዷል።
ይህ በእንዲህ እንዳለ በተለያዩ የአማራ ክፍሎች የአብይ አህመድ እና የእሱ ደናቁርቶቹ ናለትም የብአዴን ካድሪዎች በአንድም በሌላም ያልሰሩት ያግፍና የጥፋት አይነት የለም። እንዳለመታደል ሆኖ አማራ ከምድረ ገፅ እንዲጠፋ አሁን ሳይሆን የተጀመረው ከ1960ቹ ጀመሮ ነበር ይላል የዓፄ ዘርዓ ያዕቆብ አንደኛ ኮር ዋና ፖለቲካ ዘርፍ ኃላፊ አርበኛ ፋኖ ያሬድ አስናቀ ። ሆኖም ማጀቴ በተደጋጋሚ ከአጎራባች የኦሮሞ ልዩ ዞን በእየ ቀኑ ትንኮሳዎች እየተነሱ ማህበረሰባችን አላግባብ ሲንገላታ የቆየ መሆኑ የሚታወቅ ሃቅ ነው።
በመድረኩም አርበኛ ፋኖ ያሬድ አስናቀ የዓፄ ዘርዓ ያዕቆብ አንደኛ ኮር ዋና ፖለቲካ ዘርፍ ኃላፊ፤አበበ ፀጋዬ የአሳምነው ዕዝ የሃብት አሰባሳቢ መምሪ፤ ደረሰ ታደስ የአሳምነው ዕዝ አደርጃጅት መምሪያ እንዲሁም ተስፋማሪያም ታፈሰ የደቡብ አማራ ቀጠና አሳምነው ዕዝ ዋና ፖለቲካ ዘርፍ መምሪያ በተገኙበት ለማህበረሰቡ ሰፋያ ያለ የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል ያለው ቁመናን በተመልከተ ከአመራሮቹ ግንዛቤ በመስጠት ህዝቡም አንኳር አንኳር የሚባሉ ነጥቦችን በተለይም የህዘብ አደረጃጀት ከብአዴን ጀመሮ የሚመጣው መንግስት እንዲሁም አማራ ጠሉ ብልፅግና በእራሱ ለአሰራር በሚመቸው መንገድ ይመርጥ ስለነበር እኛ እንድሉን ሰጣችሁን የሚሆነን የምናምንበት የእራሳችን መሪዎች በእናንተ በልጆቻችን እንድንመርጥ ሃሳባችንን በነፃነት እንድንግልፅ ስላደረጋችሁን ከምንም በላይ ለአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል ለድርጅታችሁንና ለእናንተ ክብርና ምስጋ ይገባል በርቱ አማራ ማለት ለዚህች ውድ ሃገር ዋልታና ማገር ነው አንድነታችሁ ለአገዛዙ የውድቀት ምዕራፍ ነው በማለት ከማህበረሰቡ አንኳር ነጥቦች ተነስተዋል።
በመጨረሻም ከአራት ስዓት በላይ በወሰደው የህዝብ መድረክ የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል አሁን ላይ ኃይሉን በደንብ አዘምኖ ወደ ፊት በመግስገስ ላይ ስላለ በተለይም ማህበረሰቡ እራሱን ማደራጀት አለብት ያ ማለት ህዝብ ማለት ፋኖ ነው ፋኖ ማለትም ደግሞ ህዝብ ነው ስለዚህ ከትግሉ ጎን ለጎን የማህበረሰብ አደረጃጅት መፍጠር ለህብረተሰቡ ወቁቱን ያማከለነ ነው ስለዚህ በዚህም የቀበሌ መዋቅር አደረጃጅት በመፍጠርና የተመረጡት አመራሮች ለማህበረሰቡ በታማኝና በሃቀኝነት ለመስረታ የሙስሊም እና የኦርቶዶክስ አባቶች ቃለ መሀላ በመፈፀም አደረጃጀት ተሰርቷል።
መረጃዎን ያደረሰን የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል ደቡብ አማራ ቀጠና አሳምነው ዕዝ የዓፄ ዘርዓ ያዕቆብ 1ኛ ኮር ህዝብ ግንኙነት ኃላፊ አማረ ታዘዘ ነው
ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን
አፋብኃ ደቡብ አማራ ቀጠና አሳምነው ዕዝ የህዝብ ግንኙነት ዜና ክፍል።
ህዳር 07/ዐ3/2018 ዓ.ም
[16/11, 4:40 pm] 7ለ70 ብርጌድ: ከሊቅ እስከ ደቂቅ የተሳተፈበት የህዝብ መድረክ በታሪካዊቷ ማጀቴ ከተማ ተካሔደ!
የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል ደቡብ አማራ ቀጠና አሳምነው ዕዝ ዓፄ ዘርዓ ያዕቆብ ፩ኛ ኮር በታሪካዊቷ ማጀቴ ከታማ ከሊቅ እክከ ደቂቅ የዕዙ አመራሮችና የዓፄ ዘራዓ ያዕቆብ ፩ኛ ኮር ከፍተኛ አመራሮች በተገኙበት የህዝብ መድረክ ተካሔዷል።
ይህ በእንዲህ እንዳለ በተለያዩ የአማራ ክፍሎች የአብይ አህመድ እና የእሱ ደናቁርቶቹ ናለትም የብአዴን ካድሪዎች በአንድም በሌላም ያልሰሩት ያግፍና የጥፋት አይነት የለም። እንዳለመታደል ሆኖ አማራ ከምድረ ገፅ እንዲጠፋ አሁን ሳይሆን የተጀመረው ከ1960ቹ ጀመሮ ነበር ይላል የዓፄ ዘርዓ ያዕቆብ አንደኛ ኮር ዋና ፖለቲካ ዘርፍ ኃላፊ አርበኛ ፋኖ ያሬድ አስናቀ ። ሆኖም ማጀቴ በተደጋጋሚ ከአጎራባች የኦሮሞ ልዩ ዞን በእየ ቀኑ ትንኮሳዎች እየተነሱ ማህበረሰባችን አላግባብ ሲንገላታ የቆየ መሆኑ የሚታወቅ ሃቅ ነው።
በመድረኩም አርበኛ ፋኖ ያሬድ አስናቀ የዓፄ ዘርዓ ያዕቆብ አንደኛ ኮር ዋና ፖለቲካ ዘርፍ ኃላፊ፤አበበ ፀጋዬ የአሳምነው ዕዝ የሃብት አሰባሳቢ መምሪ፤ ደረሰ ታደስ የአሳምነው ዕዝ አደርጃጅት መምሪያ እንዲሁም ተስፋማሪያም ታፈሰ የደቡብ አማራ ቀጠና አሳምነው ዕዝ ዋና ፖለቲካ ዘርፍ መምሪያ በተገኙበት ለማህበረሰቡ ሰፋያ ያለ የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል ያለው ቁመናን በተመልከተ ከአመራሮቹ ግንዛቤ በመስጠት ህዝቡም አንኳር አንኳር የሚባሉ ነጥቦችን በተለይም የህዘብ አደረጃጀት ከብአዴን ጀመሮ የሚመጣው መንግስት እንዲሁም አማራ ጠሉ ብልፅግና በእራሱ ለአሰራር በሚመቸው መንገድ ይመርጥ ስለነበር እኛ እንድሉን ሰጣችሁን የሚሆነን የምናምንበት የእራሳችን መሪዎች በእናንተ በልጆቻችን እንድንመርጥ ሃሳባችንን በነፃነት እንድንግልፅ ስላደረጋችሁን ከምንም በላይ ለአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል ለድርጅታችሁንና ለእናንተ ክብርና ምስጋ ይገባል በርቱ አማራ ማለት ለዚህች ውድ ሃገር ዋልታና ማገር ነው አንድነታችሁ ለአገዛዙ የውድቀት ምዕራፍ ነው በማለት ከማህበረሰቡ አንኳር ነጥቦች ተነስተዋል።
በመጨረሻም ከአራት ስዓት በላይ በወሰደው የህዝብ መድረክ የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል አሁን ላይ ኃይሉን በደንብ አዘምኖ ወደ ፊት በመግስገስ ላይ ስላለ በተለይም ማህበረሰቡ እራሱን ማደራጀት አለብት ያ ማለት ህዝብ ማለት ፋኖ ነው ፋኖ ማለትም ደግሞ ህዝብ ነው ስለዚህ ከትግሉ ጎን ለጎን የማህበረሰብ አደረጃጅት መፍጠር ለህብረተሰቡ ወቁቱን ያማከለነ ነው ስለዚህ በዚህም የቀበሌ መዋቅር አደረጃጅት በመፍጠርና የተመረጡት አመራሮች ለማህበረሰቡ በታማኝና በሃቀኝነት ለመስረታ የሙስሊም እና የኦርቶዶክስ አባቶች ቃለ መሀላ በመፈፀም አደረጃጀት ተሰርቷል።
መረጃዎን ያደረሰን የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል ደቡብ አማራ ቀጠና አሳምነው ዕዝ የዓፄ ዘርዓ ያዕቆብ 1ኛ ኮር ህዝብ ግንኙነት ኃላፊ አማረ ታዘዘ ነው
ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን
አፋብኃ ደቡብ አማራ ቀጠና አሳምነው ዕዝ የህዝብ ግንኙነት ዜና ክፍል።
ህዳር 07/ዐ3/2018 ዓ.ም
#የሚሊሻው_ልጅ_የአባቱን_ትጥቅ_ከቤት_ከተኛበት_አንስቶ_ወደ_ፋኖ_ተቀላቀለ!!
የ14 አመቱ ብላቴናው ግዛው ማርየ አዘነው የተባለው ታዳጊ ልጅ የአገዛዙ ቅጥረኛ ሚሊሻ የሆነው አባቱ እንደተኛ ትጥቁን በማንሳት ፅሀይ መውጫ ልዩ ቦታው ተንበኮ አካባቢ የምስራቅ አማራ ኮር 1 አሳምነው ክፍለጦርን ተቀላቀለ::
የልጁ ቁርጠኝነት ያስደነቀው የምስራቅ አማራ ኮር 1 ምክትል ወታደራዊ አዛዠ እና የአሳምነው ክፍለ ጦር ሀላፊ አርበኛ ጌታሁን ሲሳይ (ግጠም አለኝ) ለልጁ ማበረታቻ እንዲሆን ሁለት እግራ ስናይቶ ክላሽ ሸልሞታል ሲል የኮሩ ህዝብ ግንኙነት ኃላፊ አርበኛ ንጉስ አበራ አስታወቀ::
🔥#የቪአይፒ_ጥበቃወች_ወደ_ፋኖ_ተቀላቀሉ‼️
ህዳር 07/2018 ዓ.ም
1፦እስቲበል አሞኘ
2፦አበባው ሁኔ 102ኛ ኮር 3ኛ ሻለቃን ከእነ ሙሉ ትጥቃቸው 06 ካዝና ከእነ ተተኳሹ በመያዝ ፋኖን ተቀላቅለዋል።
በአመራሮች በኩል አቀባበል የተደረገላቸው ሲሆን በጊዜው የትጥቅ ችግር ስለነበረብን መሳሪያ ይዘን ለመውጣት ነበር የገባነው አሁን ላይ እቃድችን አሳክተናል ከዚህ በሗላ ህዝባችን ለመካስ ተዘጋጅተናል በማለት ሀሳባቸውን ተናግረዋል።
©ፋኖ ሐብታሙ የሱፍ
07/ዐ3/2018 ዓ.ም
➳➳ጥብቅ ማስጠንቀቂያ ለደብረ ኤልያስ ወረዳ ማሕበረሰብ በሙሉ➳➳❗
በሁለንተናዊ ቁመናው በታላቅ የሰብአዊነት ልዕልና የሚገኘውና የትክክልኛ ሰብአዊነት መገለጫዎችን የተጎናጸፈው ታላቁ የአማራ ማሕበረሰብ ከግማሽ ምዕት ዓመታት ወዲህ አስከፊ የሕልውና ቅርቃር ውስጥ ገብቶ በሆነ አጋጣሚ መንበረ መንግስቱን በተቆናጠጡ የእፉኝት ልጆች ከፍተኛ ግፍና በደልን እያስተናገደ ይገኛል።
በቅርቡም የኦሮሙማው ኦሕዴድ ሥርዓት በሕዝባችን ላይ ይፋዊ የሞት አዋጅ አውጆ አያሌ ሰብአዊና ቁሳዊ ውደመቶችን ማድረስ ከጀመረ ዓመታት እየተቆጠሩ ነው።
ይህን የጅምላ ጭፍጨፋም በሁለንተናዊ ዘርፍ በመደገፍም ውልደ አምሐራ የሆኑ በእላቂ ጨርቅ፣በድቃቂ ሳንቲምና በርካሽ የስልጣን ፍርፋሪ ለአራጆቻችን በማደርና ለገዳዩ ሥርዓት ዓይንና ጆሮ በመሆን ሕዝቡን እያስጨፈጨፈ የሚገኘው ከሰብአዊነት ከፍታ ወርዶ የሕዝባችንን የመታረጃ ቢላዋ የሚስል፤ ለሰይጣናዊው የብልጽግና ሥርዓት የደም ግብር ይሆኑ ዘንድ ንጹሐን አማራውያንን አመቻችቶ የሚሰጥ ሆዳም የአማራ ባንዳ ቀዳሚው ነው።
ከነዚህም መካከል ከሕጻን እስከ አረጋዊያን ያሉ አያሌ ንጹሐንን በዘግናኝ ሁኔታ የጨፈጨፈውና ያስጨፈጨፈው በርካቶችን ያለ መኖርያ ቤት ያስቀረው፣ የበርካቶችን ንብረትም የዘረፈውና ያዘረፈው ከተማዋን የምድር ሲኦል ያደረጋት በደብረ ኤልያስ ከተማ የተወሸቀው የብልጽግና ስብስብ ይገኝበታል።
ይህ ስብስብ በቆየባቸው ወራት በርካቶችን ለከፋ እልቂት፣ዘረፋና እንግልት የዳረገ ሲሆን ይህንንም የሚያስፈጽመው የብልጽግና አመራር ተብየው በሚሰጠው ግልጽ ትዕዛዝ በጸጥታ መዋቅሩ አስፈጻሚነት ነው።
ከሰሞኑም አዲስ የስቃይ ስልት በመቀየስ ማሕበረሰቡን ለመበዝበዝና ለከፋ እንግልት ለመዳረግ በሰላም አስከባሪ ስም ያደራጃቸውን የሌባ ስብስቦችና ነፍሰ ገዳዮችን ቀጠናውን የሚያስተዳድረውን የበረኸኛው ቀስተ ደመና ሻለቃ ፋኖዎችን ዩኒፎርም በማልበስ እገታና ዘረፋ መጀመሩን ደርሰንበታል።
በዚህ ስራ ሊከወናወኑ ከታሰቡ ተግባራት መካከልም አድማ ብተና ፖሊስና ሚሊሻን የፋኖን ዩኒፎርም በማልበስ፦
➠ በየቦታው በማሰማራት ማሕበረሰቡን መዝረፍ፣ ማገት፣ ሴቶችን መድፈርና ንጹሐንን መግደል፤
➠ የቀበሌ አመራሮችን፣ ተጽዕኖ ፈጣሪ ግለሰቦችንና የፋኖ ቤተሰቦችን ይዞ ለጨፍጫፊው ሥርዓት ማስረከብ፤
➠ አረመኔው የዓብይ ሠራዊት በንጹሐንና በንብረት ላይ ለሚፈጽመው በከባድ መሳርያ የታገዘ ጭፍጨፋና ውድመት ሁኔታዎችን ማመቻቸትና መረጃዎችን ማቀበል
➠ በየመንገዱ እየቆሙ ፋኖ የማያውቃቸው ኬላዎችን በመዘርጋት ለገበያ የሚወጣ የሚወርደውን ሕዝባችንን መዝረፍና ሌሎችንም የፋኖን ስብዕና የማይወክሉ አሳፋሪና አሰቃቂ ተግባራትን በመፈጸም የተሰማራለትን የዘረፋ ተግባርና አማራን የማሰቃየት ተግባሩን በመፈጸም እግረ መንገዱንም ፋኖንና ሕብረተሰቡን ይነጥልልኛል ያለውን የጅል ፖለቲካ ለመስራት በእንቅስቃሴ ላይ ይገኛል።
በመሆኑም በደብረ ወረዳ የሚገኘው የተከበረው ሕዝባችን ይህንን የጠላትን ሰይጣናዊ እቅድ ተረድቶ በየትኛውም ሁኔታ ራሱን እንዲጠብቅ ስንል በጥብቅ እናሳስባለን።
በተጨማሪም ከበረኸኛው ቀስተ ደመና ሻለቃ እውቅናና ፈቃድ ውጭ የትም ቦታ ላይ የሚንቀሳቀስና የትኛውንም አይነት ግዳጅ የሚፈጽም አባል የሌለ መሆኑን ተረድታችሁ ከላይ የተጠቀሱ እኩይ ተግባራትን የሚፈጽምን አካል ለሻለቃው መረጃ በመስጠት እንድትተባበሩን ስንል እናሳስባለን።
ህዳር 07/2018 ዓ.ም
ድል ለአማራ ፋኖ!
ፋኖ ዘመን ባሳዝነው
የ206ኛ ኮር 14ኛ ክፍለ ጦር የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ
ደፈጣ ዜና
አማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል ደቡብ አማራ ቀጠና አሳምነው ዕዝ ከሰም ኮር ነበልባል ክፍለ ጦር።
ህዳር 7/03/2018 ዓ ም የብልፅግና ወንበር አስጠባቂ የመቶ አራተኛ ክፍለ ጦር ቀይ ቦኔት ለባሽ ፋራ ኮማንዶ አባል ከምንጃር ሸንኮራ ወደ በረኸት ወረዳ እሬሽን አድርሶ ሲመለስ በነበልባል ክፍለ ጦር በጀነራል ተፈራ ማሞ ብርጌድ በሸማቂው በናደው ሻለቃ ፋኖ አባላቶች አሮጌ ምንጃር ተብሎ በሚጠራው አካባቢ በደፈጣ በወሰዱበት መብረቃዊ የቦንብና የጨበጣ ጥቃት ከፍተኛ የሆነ የሰውና የንብረት ኪሳራ አድርሰውበታል።
በዚህ ጥቃት የተደናገጠው የብልፅግና ጉጂሌ በእጁ ላይ የሚገኘውን ተቀላል እስከ ከባድ መሳሪያ ቢጠቀምም ሸማቂዎቹ በብረሀን ፍጥነት ከተሳፈረበት ከአስሩ መኪና ሁለቱን ከነሰራዊቱ ከጥቅም ውጪ በማረግ በሰላም ወደ ቀጣናቸው ተመልሰዋል።
ድል ለአ.ፋ .ብ. ኃ
ክብርና ሞገስ ለትግሉ ሰማዕታት
ድላችን በተባበረ ክንዳችን
አንድነት ሀይል ነው
ከነበልባል ክፍለ ጦር ሚዲያ ክፍል
አፋብኃ ምዕራብ አማራ ቀጠና ቴዎድሮስ ዕዝ 3ኛ ጎጃም አገው ምድር ክ/ጦር ቀኝ አዝማች ስሜነህ ደስታ ብርጌድ
ሕዳር 7/3/2018 ዓ/ም የህዝብ ደም በቁም ያቃዣቸው እና ተስፋ የቆረጡት የአገዛዙ ታላላኪ ባንዳ የሆኑት ሚሊሻ፣አድማ እና ሆድ አደር የወረዳ ካድሬዎች የግለሰቦችን ንብረት ዘርፈዋል።
ከእንጅባራ ወደ ምርክታ የተንቀሳቀሰው የአገዛዙ ቅጥረኛ ተልኮ አስፈፃሚ ሚሊሻ እና አድማ ብተና የአከና ጅፊ ቀበሌ ኗሪ የሆኑትን የአቶ የኔው ፈጠነን 20 የቀንድ ከብት እና ሙሉ የቤት ቁሳቁሶችን ወደ እንጅባራ ጭኗል።
የቀኝ አዝማች ስሜነህ ደስታ ብርጌድ
ህ/ግንኙነት
በአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል ( አፋብኃ ) የቴዎድሮስ ዕዝ የ105ኛ ኮር የ66ኛ ክፍለጦር ምስረታ ተጠናቋል ‼️
በአፋብኃ ቴዎድሮስ ዕዝ የመልሶ ማደራጀት እና የመዋቅር ማሻሻል ተግባራት መካከል አንዱ የሆነው የኮር አደረጃጀት እና የክፍለጦር መልሶ ማደራጀት ይገኝበታል ።
በዚህ ክፍለጦሩን በአምስት ውህድ ሻለቃ የተዋቀረ ሲሆን ለቀጣይ የህልውና ትግል ዝግጁ መሆናቸውን የክፍለጦሩ ፣ የሻለቃ አመራሮች እና አባላት አረጋግጠዋል ።
ክፋት ለማንም ፣በጎነት ለሁሉም!!
አዲስ ትውልድ ፣አዲስ አስተሳሰብ፣ አዲስ ተስፋ !!
⛔️አሩሲ አቦምሳ ሐይፋ ዳገት!‼️
======
"ወዲያው ከዋናው መንገድ ራቅ ብለው ወደ ጫካ ይዘዋቸው እንደገቡ ተከታታይ የሩምታ ተኩስ ሰምተናል። ምናልባት የተወሰኑትን ሳይጨፈጭፏቸው አይቀርም።
አውቶብሱ በታጣቂዎች መንገድ ተዘግቶበት ቆመ። ወዲያው ታጣቂዎች ወደ አውቶብሱ ገብተው በኦሮሞኛ ሁሉም ተሳፋሪ እንዲወርድ አዘዙ ። ጭምብል አለባበሳቸው መሣሪያ አያያዛቸው አልባሳት አለባበሳቸው ከቴሌቪዥን የምናያቸውን የአልሸባብ ታጣቂዎች ይመስላሉ።
ወዲያው አማራ ኦርቶዶክስ የሆናችሁ በዚህ በቀኝ በኩል ተሰለፉ አሉ። ኦሮሞ የሆናችሁ በግራ ተሰለፉ አሉ።
ወዲያው ቆጠራ አድርገው ኦሮሞዎች ወደ አውቶብስ ገብታችሁ ጉዞ ቀጥሉ አሉ። እኛ ጉዞ እንደጀመርን 31 አማራ ኦርቶዶክሶችን ከሐይፋ ዳገት ወደ ጫካ ይዘዋቸው ገቡ።
.. ወዲያው ከዋናው መንገድ ራቅ ብለው ወደ ጫካ ይዘዋቸው እንደገቡ ተከታታይ የሩምታ ተኩስ ሰምተናል። ምናልባት የተወሰኑትን ሳይጨፈጭፏቸው አይቀርም።
እኔ ኦሮሞ ነኝ ብዬ በግራ በኩል ተሰልፌ ወደ አቦምሳ ገባሁ።
እስከአሁን ልቤ ሐይፋ ዳገት ታግተው ከተወሰዱት ዘመዶቼ ጋር ነው። እነማን ተጨፍጭፈዋል! እነማን ተረፈዋል! ሰቀቀን ላይ ነኝ።
ሰው ላይ የተተኮሰ ጥይትና አየር ላይ የተተኮሰ ጥይት ድምፁ ይለያያል። በእርግጠኝነት የሩምታ ተኩሱ አየር ላይ አይደለም።
በሰው ገላ ላይ ነው ያረፈው። ምነው ዕዛው በቀኝ ተሰልፌ አማራ ኦርቶዶክስ ነኝ ብዬ መከራውን ብቀበል እላለሁ።"
ኅዳር 6/2018 ዓ.ም ከናዝሬት ወደ አቦምሳ ሲጓዙ ሐይፋ የተባለ ቦታ 31 አማራ ኦርቶዶክሶች ታግተው ተወስደዋል። ከዚያ እገታ የተረፈ ሰው ቀጥታ የላከው መልዕክት ነው።
👉ዕገታው ሲፈፀም ዓለሙ ስሜ ጀኔራል ሰለሞን ኢተፋ ኢብራሂም ከድር አቦምሳ ከተማ ሕዝብ ሰብስበው ሠላም ነው በሉ የጠላት ወሬ ነው በሉ የብልጽግና ጉዞ አይቆምም እያሉ ምናባዊ ብልጽግና ይሰብኩ ነበር‼️
@Belete Kassa Mekonnen
ከመቄት ወደ አግሪት በመኪና ተጭኖ ሲቀሳቀስ የነበረ የጥላት ሰራዊት በደፈጣ ተመታ።
አፋብኃ ምስርቅ አማራ ቀጠና ሚኒሊክ ዕዝ የደጋው መብረቅ ኮር አንሻ ክፍለ ጦር ህዳር 6/2018 ዓ/ም አመሻሽ ላይ ባደረገችው ደፈጣ በአንድ ካሶን ተጭኖ ሲቀሳቀስ የነበረ የፋሽስቱ ሰራዊት ዶግ አመድ ተደርጓል።
በደፈጣ ጥቃት የተሰነዘረበት ፋሽስቱ ከአስር በላይ ሙት እና ከ17 በላይ ከባድ ቁስለኛ ማድረግ ተችሏል።ቅሌትና ሽንፈት ተፈጥሯዊ ባህሪው የሆነው የብልፅግና ስርዓት የፋኖን ጎምዛዛ የቅጣት በትር በየ ደቂቃዎች እየተጋታት ይገኛል።
የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል (አፋብኃ)
የደጋው መብረቅ ኮር
"#ጀግና_ይሰዋል_ትግል_ይቀጥላል‼️"
የአርበኛ አለሙ ገብሩ የህይወት እና የትግል ታሪክ!
በአፋብኃ ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ የምስራቅ አማራ ኮር 2 ወታደራዊ ዋና አዛዥ አርበኛ አለሙ ገብሩ የትውልድ ቦታው ራያ ቆቦ ዞብል ነው::
አርበኛ አለሙ ገብሩ እንደ ማንኛውም የአማራ ልጅ ቤተሰቡን በተለያየ ስራ እያገዘ ያደገና በኋላም ለወግ ለማዕረግ በቅቶ አግብቶ የወለደና የሁለት ልጆች አባት የነበረ ነው::
አርበኛ አለሙ ገብሩ እንደ ሌሎች ጓዶቹ ሁሉ ኑሮን ለማሸነፍና የተሻለ ደረጃ ለመድረስ ወደ አረብ ሃገር ሳውዲ አረቢያ በመሄድ ሰርቶ ያለፈለትና ወደ ሃገሩ ተመልሶ ትዳሩን እየመራ ይኖር የነበረ ጀግና ነው::
አርበኛ አለሙ ገብሩ 2013 ዓ.ም በፈነዳው የሰሜኑ ጦርነት ጊዜ የነበረውን ጥሪ በመቀበል የዘመተ ሲሆን በወቅቱ ጠላትን ራስ ምታት በመሆን ከመደበኛው የመንግስት መከላከያ ሰራዊት በላይ ጠላት ጣርማ በር ደርሶ ራያ ላይ በደፈጣ አስቸግሮት የነበረው የዞብል ግንባር ሰራዊት አባልና ግንባር ቀደም አመራር ነበር::
በራያ ዞብል ግንባር ከነበረው የቀድሞው ምስራቅ አማራ ፋኖ ክንፍ ጎን ለጎን ይታገል የነበረው ግዙፍ የወገን ሃይል ህዝባዊ ሰራዊት ግንባር ቀደም አመራር በመሆን በሽምቅ ውጊያ ጠላትን እስከ ራያ አላማጣ ዘልቀው በመግባት ራስ ምታት በመሆን ለተጎናፀፉት ትልቅ ድል ጉልህ ሚና ተጫውቷል::
ከ2013 ዓ.ም ድል በኋላ አርበኛ አለሙ ገብሩና ጓዶቹ ሲመሩት የነበረው ህዝባዊ ሰራዊት ቆቦ ከተማ ላይ የቀድሞውን ምስራቅ አማራ ፋኖ የተቀላቀለ ሲሆን በወቅቱ ብርጌድ የነበረውን ዞብል አምባ ብርጌድ ምክትል አዛዥና የአመራር አባል ሆኖም ታሪካዊውን የበላጎ ምሽግ ደምስሷል::
ከበላጎው ታሪካዊ ድል በኋላም የምስራቅ አማራ ፋኖ የጦር ሰፈር ወደነበረው ራያ ቆቦና አካባቢው በመመለስ ላይቀሬው የህልውና የትጥቅ ትግል ከፍተኛ ዝግጅት ይደረግ ስለነበር ምስራቅ አማራ ፋኖ የአገዛዙ ሹማምንቶችና ከፍተኛ የመከላከያ ጀኔራሎች እንዲሁም የሃይማኖት አባቶች የሃገር ሽማግሌዎችና ተፅዕኖ ፈጣሪ ግለሰቦች በተገኙበት ታላቅ ተሃድሶ አድርጎ ፀረ-ወያኔ ትግሉን ደመደመ::
በመቀጠልም አርበኛ አለሙ ገብሩ የህልውና ትጥቅ ትግሉን አርበኛ ኮማንዶ ሻምበል ዳንኤል አለሙ ሚያዚያ 1/2015 ዓ.ም የህይወት መስዋዕትነት በመክፈል ችቦ ለኩሶ ካስጀመረበት ዕለት ጀምሮ ሰራዊቱን ዳግም በማሰባሰብ በማደራጀትና በማስታጠቅ ብሎም በመምራት በራያ በየጁ በላስታ በአምባሰልና ሌሎች የቤተ-አማራ ቀጠናዎች ብርድና ሃሩሩ ረሃብና ጥማቱ ደጋውና ቆላው ሳይበግረው ደከመኝ ሰለቸኝ ሳይል ለህልውና ትግሉ ከፍተኛ የሚባል አስተዋጽኦ አበርክቷል::
አርበኛ አለሙ ገብሩ በወቅቱ ምስራቅ አማራ ፋኖ በጠላትና በውስጥ ባንዳዎች ገጥሞት የነበረውን የመበተን አደጋ በመቋቋምና እናት ሆና ሌሎች አሃዶችን ዳግም እስከ መውለድና እስከማደራጀት ብሎም ለዛሬ እስከማብቃት የደረሰችውን ዞብል አምባ ክፍለጦር 1ኛ ሻለቃ እየመራ በኋላም ክፍለጦሩን በመምራት በታሪክ የተመዘገበ ደማቅ ገድል ፈፅሟል::
አርበኛ አለሙ ገብሩ ዞብል አምባ ክፍለጦርን እየመራ ትግሉን ትልቅ ደረጃ ካደረሱ ጀግና የአማራ ህዝብ የቁርጥ ቀን ልጆች ተርታ የተሰለፈ ሲሆን ምኒልክ ዕዝ አደረጃጀቱን አዘምኖ ወደ ኮር አደረጃጀት ሲሻገር የምስራቅ አማራ ኮር 2 ወታደራዊ ዋና አዛዥ ሆኖ ትግሉን ከዛሬ በማድረስ የሚጠበቅበትን ተወጥቶ አልፏል::
በመጨረሻም አርበኛ አለሙ ገብሩ ምኒልክ ዕዝ ባወጀውና ከመስከረም 14-30/2018 ዓ.ም በቆየው በዘመቻ አርበኛ አደም አሊ (አባ ናደው) ምስራቅ አማራ ኮር ሁለትን እየመራ በርካታ ወታደራዊ እና ፖለቲካዊ ብሎም ዲፕሎማሲያዊ ድሎችን ተጎናፅፎ ከዘመቻው መገባደድ ማግስት የጠላትን ከባድ የማጥቃት ዘመቻ በመመከት ተኩለሽ ግንባር ከቆቦ ከተማ ቅርብ ርቀት ልዩ ስሙ ጠበለት የተባለ ቦታ ላይ ጥቅምት 7/2018 ዓ.ም በክብር መስዋዕትነትን ተቀብሏል::
በመጨረሻም እኛ የትግል ጓዶቹ አርበኛው ጓዳችን መስዋዕትነት የከፈለበትን አላማ ከግብ እናደርሳለን የህዝባችንን ህልውና እናረጋግጣለን!
©የትግል ጓዶቹ ከትግል ሜዳ‼️
07/ዐ3/2018 ዓ.ም
የአርበኛ ዋሴ ከበደ የህይወት እና የትግል ታሪክ!
"ጀግና ይሰዋል ትግል ይቀጥላል!"
አርበኛ ዋሴ ከበደ የትውልድ ቦታው የራያ ቆቦ አርበት ልዩ ስሙ ቀጋይ አቦ የተባለ ቦታ ነው:: የ1ኛ ደረጃ ትምህርቱን እዛው ተወልዶ ባደገበት አገሩ የተማረ ሲሆን የ2ኛ ደረጃ ትምህርቱንም ቆቦ ሃይስኩል ጨርሶ በኋላም በመምህርነት ተመርቋል::
አርበኛ ዋሴ ከበደ ከሰሜኑ ጦርነት በፊት በመምህርነት ሞያ ሃገሩንና ወገኑን ያገለገለ የነበረ ሲሆን 2013 ዓ.ም በጀመረው የሰሜኑ ጦርነት ምክንያት በነበረው ጥሪ ወደ ማሰልጠኛ ገብቶ ተመርቆ የአማራ ልዩ ሃይልን ተቀላቅሎ ታግሏል::
አርበኛ ዋሴ ከበደ በሰሜኑ ጦርነት የአማራ ልዩ ሃይል የቴዎድሮስ ክፍለጦር አር ፒ ጅ እና ብሬን ተኳሽ ሆኖ የታገለ ሲሆን በወቅቱ በነበረው ከፍተኛ ሴራና አሻጥር በመማረር ነፃ ሆኖ ህዝቡን ለማገልገልና ለመታገል ሲል ከልዩ ሃይሉ በመውጣት በትውልድ አካባቢው ወጣቶችን በማደራጀትና በማስታጠቅ ወደ ሽምቅ ውጊያ በመግባት በርካታ ጀብዶችን ፈፅሟል::
ከጥር 2013 ዓ.ም ድል በኋላም በይፋ ምስራቅ አማራ ፋኖን ተቀላቅሎ የቀድሞው የዞብል አምባ ብርጌድ አባል ሆኖ ሲታገልና ሲያታግል ቆይቷል:: በታሪካዊው የበላጎ ድልም የቀድሞው የዞብል አምባ ብርጌድ አባል ሆኖ ታሪክ ሰርቶ አልፏል::
አርበኛ ዋሴ ከበደ ከሰሜኑ ጦርነት በደቡብ አፍሪካው የፕሪቶሪያ ስምምነትና ድራማ መጠናቀቅ በኋላ ምስራቅ አማራ ፋኖ የአማራን ህዝብ ህልውና በትጥቅ ትግል ለማረጋገጥ ሚያዚያ 1/2015 ዓ.ም በረሃ ከወጣበት ጊዜ ጀምሮ ሰራዊቱን እንደ አዲስ በማሰባሰብ በማደራጀትና በማስታጠቅ ጉልህ ሚና ተጫውቷል::
አርበኛ ዋሴ ከበደ ሰራዊት ከማሰባሰብ ከማደራጀትና ከማስታጠቅ ባሻገር ዞብል አምባ ክፍለጦር 2ኛ ሻለቃ ሻምበል መሪ ዘመቻ እና የሻለቃዋ አመራር ሆኖ በበርካታ ግንባሮች በርካታ ጀብዶችን በመፈፀም ብሎም ቆቦ ከተማ ድረስ ዘልቆ እየገባ ባንዳ ላይ የማያዳግም እርምጃ በመውሰድና በማፅዳትም የሚስተካከለው አልነበረም::
በመቀጠልም አርበኛ ዋሴ ከበደ የዞብል አምባ ክፍለጦር 2ኛ ሻለቃን እየመራ በራያ በየጁ በአምባሰልና በተለያዩ የቤተ-አማራ ግንባሮች በርካታ ድሎችን የተጎናፀፈ ሲሆን መስከረም 26/2016 ዓ.ም ቆቦ ከተማ ሆርማት እና መጋቢት 3/2016 ዓ.ም አምባሰል አካባቢ ሁለት ጊዜ የቆሰለና በፅናት የታገለ ጀግና ነበር::
አርበኛ ዋሴ ከበደ በዞብል አምባ ክፍለጦር ሻለቃ እየመራ ባስመዘገበው ድልና ከፍተኛ አፈፃፃም ምክንያት ወደ ዞብል አምባ ክፍለጦር አመራርነት በኋላም ባለው ከፍተኛ ውጊያን የማንበብና የማዋጋት አቅም የክፍለጦር ዘመቻ ሆኖ የመራ ሲሆን በቅርብ ጊዜም የምስራቅ አማራ ኮር 2 ምክትል ዘመቻ መሪ ሆኖ እስከመመረጥ የደረሰ ጀግና አርበኛ ነበር::
በመጨረሻም አርበኛ ዋሴ ከበደ ምኒልክ ዕዝ ባወጀውና ከመስከረም 14-30/2018 ዓ.ም በቆየው በዘመቻ አርበኛ አደም አሊ (አባ ናደው) የምስራቅ አማራ ኮር ሁለት ምክትል ዘመቻ አመራር ሆኖ በርካታ ወታደራዊ እና ፖለቲካዊ ብሎም ዲፕሎማሲያዊ ድሎችን ተጎናፅፎ ከዘመቻው መገባደድ ማግስት የጠላትን ከባድ የማጥቃት ዘመቻ በመመከት ተኩለሽ ግንባር ከቆቦ ከተማ ቅርብ ርቀት ልዩ ስሙ ጠበለት የተባለ ቦታ ላይ ጥቅምት 7/2018 ዓ.ም በክብር መስዋዕትነትን ተቀብሏል::
በመጨረሻም እኛ የትግል ጓዶቹ አርበኛው ጓዳችን መስዋዕትነት የከፈለበትን አላማ ከግብ እናደርሳለን የህዝባችንን ህልውና እናረጋግጣለን!
ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን!
የትግል ጓዶቹ ከትግሉ ሜዳ!
አፋብኃ ምኒልክ ዕዝ
ህዳር 7/2018 ዓ.ም
