ፍኖተ- አማራ ሚዲያ (Finote- Amhara ) Midea
Открыть в Telegram
የተመሠረተው የአማራን ሕዝብ ለማንቃት፣ ለማደራጀት እና ለማስተባበር ነው። የአማራ ሕዝብን ✅ ፖለቲካዊ ✅ ማህበራዊ ✅ ኢኮኖሚያዊ ታሪካዊ ጥያቄዎችን ለማሰማት እና የአማራን ሕዝብ በማንቃት ሰፊውን ሕዝብ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ይሰራል። ወደዱም ጠሉም የኃላ ታሪካችን በእኛ እጅ ይፃፋል። አማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ ( አፋብን)
Больше3 194
Подписчики
+4524 часа
+967 дней
+45930 дней
Архив постов
+7
ምኒልክ ዕዝ 105ኛ ኮር 47ኛ ክፍለ ጦር አትሮንስ ሻለቃ ለወራቶች ያሰለጠናቸውን ምልምል ፋኖዎች በደማቅ ሁኔታ አስመረቀ::
አማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ (አፋብን) ምኒልክ ዕዝ 105ኛ ኮር 47ኛ ክፍለ ጦር አትሮንስ ሻለቃ ለወራት ያሰለጠናቸውን ሰልጣኞች በድምቀት አስመረቀ::
አትሮንስ ሻለቃ ለአምስት ወራት በብቃትና በጥራት ያሰለጠናቸውን ከ150 በላይ ብቁ ሰልጣኞች አስመርቋል።
ምኒልክ ዕዝ በስሩ ያሉ ኮሮችን ራሳቸውን በሰው ሃይል እንዲያጠናክሩ ባወረደው አቅጣጫ መሰረት 105ኛ ኮር 47ኛ ክፍለ ጦር አትሮንስ ሻለቃ ለወራቶች ያሰለጠኗቸውን ምልምል ፋኖዎች በደማቅ ሁኔታ በማስመረቅ ራሳቸውን በሰው ሃይ እያደራጁ ይገኛሉ::
መዳረሻዉ ድል እና ነፃነት የሆነዉ የአማራ ህዝብ የህልዉና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል!
ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን!
አፋብን ወሎ ቤተ-አማራ ምኒልክ ዕዝ
ሚያዚያ 21/2018 ዓ/ም
#ተጠነክሮ_የቀጠለው_ድርጅት_አቀፍ_ህዝባዊ_መድረክ!
የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ (አፋብን) ባወረደው የስራ መመሪያ መሰረት በሸዋ ጠቅላይ ግዛት የተለያዩ አካባቢዎች የህዝብ መድረኮች ከተለያዩ የማህበረሰብ ክፍሎች ጋር እየተደረገ ይገኛል።
ሚያዚያ 21/2018ዓ.ም
እንደ ድርጅት አፋብን ባስቀመጠው የስራ አቅጣጫ መሰረት "በተደራጀ የፖለቲካ ስራ የአማራ ህዝብ ብሔራዊ ንቃት ይዳብራል፤ ህልውናውም ይረጋገጣል!" በሚል መሪ ቃል የአፋብን ሸዋ ጠቅላይ ግዛት አሳምነው ዕዝ በተቆጣጠራቸው በሁሉም የሸዋ ቀጠናዎች በተለያዩ አጀንዳዎች ላይ እየተካሄደ ባለው የህዝብ መድረክ የተለያዩ የማህበረሰብ ክፍሎች በመሳተፍ ላይ ይገኛሉ።
በዛሬው ዕለት ሚያዚያ 21 ቀን 2018ዓ.ም በሸዋ ጠቅላይ ግዛት መርሀቤቴ አውራጃ በሞረትና ጅሩ ወረዳ በዜናማርቆስ ክላክተር ታላቅ ህዝባዊ መድረክ መካሔዱን የአፋብን ሸዋ ጠቅላይ ግዛት አሳምነው ዕዝ አፄ አምደ ፅዮን ኮር በላከው የግንባር መረጃ ገልጿል።
የአፋበን ሸዋ ጠቅላይ ግዛት አሳምነው ዕዝ አፄ አምደ ፅዮን ኮር የራስ አበበ አረጋይ ክፍለጦር አመራሮች፣ የአርበኞች ጦር ሰራዊት አመራሮች እንዲሁም የዕዙ የፖለቲካ መምሪያ አመራሮች በተገኙበት በጅሩ ቀጠና በዜናማርቆስ ክላስተር ስር ካሉ ቀበሌዎች ከተወጣጡ ነዋሪዎች ጋር ደማቅና ውጤታማ ህዝባዊ መድረክ መካሔዱን ኮሩ ገልጿል።
በክላስተሩ ዙሪያ ካሉ ቀበሌዎች የተወጣጡ የማህበረሰብ ክፍሎች ጋር በተለያዩ አጀንዳዎች ላይ በተደረገው ወቅታዊ ድርጅት አቀፍ ውይይት በትግሉ ሒደትና ተያያዥ ጉዳዮች ዙሪያ በሳል የመድረክ ውይይት የተደረገ ሲሆን፣ ከመድረኩ ተሳታፊዎች ለተነሱ ወቅታዊ የተለያዩ ጥያቄዎች መድረኩን በሚመሩ በየደረጃው በሚገኙ አመራሮች ምላሽና ማብራሪያ ተሰጥቶበታል።
''ክብር ለትግሉ ሰማዕታት''
ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን
የአፋብን ሸዋ ጠቅላይ ግዛት አሳምነው ዕዝ የህዝብ ግንኙነት መምሪያ
ሚያዚያ 21/2018ዓ.ም
+2
አፋብን ምዕ/አማራ ቀጠና ቴዎድሮስ ዕዝ
105ኛ ኮር 44ኛ ክ/ጦር የጓጉሳ ሽኩዳድ ወረዳ ጊዚያዊ መንግሰት 20/8/2018 ሰፊ የሆነ ህዝባዊ መድረክ በመክፈት ህዝቡ ተቃውሞውን አሰምቷል‼️
በመድረኩም፦
➡️ የአማራ የህልውና ትግል ቁመና አና አሁን ያለው የትግሉ ነባራዊ ሁኔታ ከጊዜ ወደ ጊዜ በተሻለ ሁኔታ እንዳለና ወደፊት እየሄደ መሆኑን አርሶ አደሮች ተናግረዋል።
➡️ የአማራ የህልውና ትግል ወደፊት እየሄደ አንደሆነ በመድረኩ የነበሩ አርሶ አደሮች ተናግረዋል አክለውም የአማራን የህልውና ትግል እንደሚደግፉ ተናግረዋል።
➡️ ምርጫን በተመለከተም ሰፊ የሆነ የተቃውሞ ድምጥ ሲያሰሙ ውለዋል።
➡️በምርጫ ህዝብን ማታለል አይቻልም እየሞትን ምርጫ የለም በማለት የጓጉሳ ሽኩዳድ ወረዳ አርሶአደሮች ተናግረዋል።
1.አርሶ አደሩ ፍትህ እንጅ ድሮን አይፈልግም፤
2,ብልጽግና ሴት ልጆቻችን አግቶ አልመለሳቸውም!
3,ለአማራ ገበሬ ትራክተሩ ሳይሆን ታንኩ ቤታችን ደርሷል በማለት ተቃውሞአቸውን አሰምተዋል።
አዲስ ትውል፣አዲስ አስተሳሰብ፣አዲስ ተስፋ!
የጓጉሳ ሸኩዳድ ወረዳ ጊዚያዊ መንግስት ሚዲያና ኮምኒኬሽን ክፍል
21/ዐ8/2018 ዓ.ም
303ኛ ኮር 14ኛ ክፍለ ጦር በጋዝጊብላ ወረዳ መቀመጫ የተሳካ ኦፕሬሽን በማድረግ ድል አስመዘገቡ::
የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ (አፋብን) ወሎ ቤተ-አማራ ምኒልክ ዕዝ 303ኛ አሳምነው ኮር አካል የሆነው 14ኛ ክፍለ ጦር በጋዝጊብላ ወረዳ መቀመጫ አስከተማና ዙሪያው ቅልጥም መስበሪያ ላይ በአገዛዙ ሰራዊትና በብልፅግና ካድሬ ላይ ታላቅ ድል ተጎናፀፈ።
ሚያዚያ 20/2018 ዓ/ም ከረፋዱ 5:00 ሰዓት አካባቢ መነሻውን ከአስከተማ አድርጎ ወደ ላልኪው ለማድረስ የተንቀሳቀሰው የብልፅግና ጦር አምስት ሬሽን የጫኑ መኪናዎችን የክፍለ ጦሩ አንደኛ ሻለቃ ቃኝዎች ቅልጥም መስበሪያ ላይ ደፈጣ በመያዝና በቡድን መሳሪያ በመታገዝ ከፊሉን ሬሽን ከጥቅም ውጭ በማድረግና ሬሽን ያጀቡትን በመደምሰስና ቀሪዎቹ ወደ መጡበት እንዲመለሱ አድርገዋል።
የአንደኛ ሻለቃ ቃኝዎች ላደረጉት የተሳካ ኦፕሬሽን መከታና ደጀን በመሆን በሌላ አቅጣጫ የሦስተኛ ሻለቃ ፋኖዎች ላልኪው ስላሴ አምባ የሚገኘውን የብልፅግና ጦር ላይ ጥቃት በመክፈት እና መፈናፈኛ በማሳጣት ለጠላት ኃይል እገዛና ሽፋን እንዳይሰጡት አድርገዋል።
በተጨማሪም ሚያዚያ 20 ለ21/ 2018 ዓ/ም ሌሊት 8:00 ሰዓት ላይ የክፍለ ጦሩ አንደኛ ሻለቃ ቃኝዎች፣ ከሻምበሎች የተወሰኑ ተጨምረውና የክፍለ ጦሩ አመራሮች ጋር በቅንጅት በደብረወይላ በኩል አድርገው በአስከተማ ቴክኒክና ሙያ በኩል የነበረውን የብልፅግና ሚሊሻና ፖሊስ አባላት ላይ ጥቃት በመፈፀም የነበሩበትን ምሽግ በማስለቀቅና ሁለት ሚሊሻ እስከወዲያኛው በመሸኘት ከሰባት በላይ በማቁሰል ታላቅ ጀብዱ የፈፀሙ ሲሆን የተኩሱን ድምፅ ቀድመው የሰሙት የጋዝጊብላ ወረዳ ብልፅግና ካድሬዎች ሌሊቱን ሻንጣቸውን በመሰብሰብ ወደ ዞኑ መቀመጫ ሰቆጣ ከተማ መኮብለላቸው ታውቋል።
መዳረሻዉ ድል እና ነፃነት የሆነዉ የአማራ ህዝብ የህልዉና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል ሲል የ303ኛ ግዙፉ አሳምነው ኮር ህዝብ ግንኙነት ክፍል መረጃውን አድርሷል።
ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን!
አፋብን ወሎ ቤተ-አማራ ምኒልክ ዕዝ
ሚያዚያ 21/2018 ዓ/ም
ሰበር የቅንደሻ ዜና
አዳኞቹ መራዊ ከተማ ምሽት2:00ሰዓት በመግባት አስደማሚ ሰርጀሪ ሰርተዋል !!
ቴዎድሮስ ዕዝ 102ኛ ኮር 11ኛ ክፍለ ጦር አነፍናፊወች መራዊ ከተማ ዘልቀው በመግባት አስተዳደር ህንፃው አካባቢ በባንዳወቹ ላይ መብረቃዊ ጥቃት ፈፅመዋል ። አዳኞቹ በወሰዱት እርምጃ የስርዓቱ የጀርባ አጥንት አቢቴ ማለደ እና ከወገን ከድቶ ጠላትን ተቀላቅሎ የነበረው ጌታቸው የተባሉ ትልልቅ ባንዳወችን ጨምሮ በቁጥር 07የሆኑት እስከ ወዲያኛው ተሸኝተዋል ።
👇🏻
1ኛ አቢቴ ማለደ
2ኛ ጌታቸው ፈንቴ
3ኛ አንዷለም መዘጋጃ ውስጥ የሚሰራ
4ኛ ፈጠነ
5ኛ አለልኝ
6ኛ ጋሻነህ ብዙ አየሁ(ዘገር)
7ኛ አንተሁነኝ እንቢያለ
☑️ባንዳው አቢቴ ማለደ ማነው ?
አርበኛ ዘመነ ካሴን 2014 ዓ.ም ግንቦት 12ቀን ከነቤተሰቦቹ ያስከበበ በተደጋጋሚ ጊዜ ጠላትን እየመራ የቤተሰቦቹ ሀብት ንብረት እንዲወድም ሲያደርግ የቆየና በ2017ዓም የአርበኛውን ታላቅ ወንድም የገደፋው ካሴን ከብት በጠላት እንዲዘረፍ ያደረገ በጥቅሉ አቢቴ የስርዓቱ ታማኝ አገልጋይ በመሆን የሜጫ ህዝብ ላይ ያልፈፀመው የግፍ አይነት የሌለ ቢሆንም የፋኖ ቤተሰብን ሀብት በመዝረፍ፣ በማፈናቀል ፣በማሳደድ እና ፋኖ ዘራፊ ነው ለማስባል ከባህር ዳር እስከ ቢኮሎ አባይ አጋች ቡድን አሰማርቶ ከሹፌር እስከ ተሳፋሪ ከባለሀብት አስከ አርሶ አደር በማሳገት የሚታወቅ የቀጠናው ጋንግሪን ሆኖ የቆየ ባንዳ ነበር ። አቢቴ ከዘራፊ እስከ ነፍሰ ገዳይ አደራጅቶ ቀጠናውን ሰላም ከመንሳት ባለፈ ከካቢኔ እስከ ኮለኔል እና ጀኔራሎች በጥቅም የተሳሰረ እና የማይረካ በቀልተኛም ነበር ።ታዲያ ላንዴና ለመጨረሻ ጊዜ የሜጫ ምድር እፎይ ይል ዘንድ ካንሰሩ በጀግኖቹ ተነቅሏል ።
☑️ጌታቸው ፈንቴ ከጠላት ተልዕኮ ተቀብሎ ፋኖን ተቀላቅሎ ለጠላት መረጃ ሆኖ የቆየና ወገንን ከድቶ ጠላት ገብቶ ለባንዳነቱም ሀላፊነት ተሰጥቶት መራዊ ከተማ 01ቀበሌ ስራ አስኪያጅ ሆኖ እየሰራ የነበረ።
☑️ ጋሻነህ ብዙአየሁ (ዘገር)ልክ እንደ ጌታቸው ከጠላት ተልዕኮ ተቀብሎ ወገንን ተቀላቅሎ ለጠላት ሲሰራ የቆየና ከወገን ብሬን ይዞ ከድቶ ወደ ጠላት የተቀላቀለ እና ከፋኖ ጋ በነበረበት ወቅት ያጠናቸውን ከተማ የሚኖሩ የፋኖ ቤተሰቦች እየጠቆመ ሲያስጠቃ የቆየ ባንዳ ነበር ። የትግል አሚካላ የእናት ጡት ነካሽ ባንዳን የማፅዳቱ ስራ ተጠናክሮ ይቀጥላል ።
ለዚህ ነው የጊዜ ጉዳይ እንጅ አታመልጡንም የምንላችሁ !!
ቴዎድሮስ ዕዝ 102ኛ ኮር ህዝብ ግንኙነት
የዕዙ ህግና ፍትህ መምሪያ ከሚመለከታቸው ባለ ድርሻ አካላት ጋር ወቅታዊ ውይይት አድርጓል።
ሚያዚያ 21/2018ዓ.ም
የአፋብን ሸዋ ጠቅላይ ግዛት አሳምነው ዕዝ ህግና ፍትህ መምሪያ በሸዋ ጠቅላይ ግዛት ተጉለትና ቡልጋ አውራጃ በስሩ ከሚገኙ የሳሲትና አካባቢው ከሚገኙ የክላስተርና የቀበሌና አመራሮች ጋር በህግና የፍትሕ አሰራር፣በወቅታዊ አጠቃላይ የትግሉ ሂደት ዙሪያ እንዲሁም በሌሎች ተያያዥ ጉዳዮች ላይ ያተኮረ ውይይት አድርጎል።
በመድረኩም መምሪያው ከተቋቋመ ወዲህ በተሰሩ ስራዎች ላይ ያተኮረ የአፈፃፀም ግምገማ በማድረግ ለቀጣይ የስራ አቅጣጫ ያመች ዘንድ በሚመለከታቸው በዘርፉ አመራሮች የሙያ ስልጠና ተሰጥቷል።
በተዘጋጀው መድረክ ላይ በቀጠናው የተመደቡ የፖለቲካ አመራሮች እንዲሁም የህግና የፍትህ አመራሮች እና ከሁሉም ቀበሌ የተወጣጠ የማህበረሰብ ወኪል አመራሮች ተገኝተዋል።
''ክብር ለትግሉ ሰማዕታት''
ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን
የአፋብን ሸዋ ጠቅላይ ግዛት አሳምነው ዕዝ የህዝብ ግንኙነት መምሪያ
ሚያዚያ 21/2018ዓ.ም
102ኛ ኮር 12ኛ ክፍለ ጦር በሰሜን ወሎ ዞን በራያ ቆቦ ወረዳ በጮቢና አዩብ በተለምዶ አዲስ አለም በር አካባቢ በጠላት ላይ ከባድ ማጥቃት በማድረግ ድል አስመዘገብ::
በአብይ አህመድ ዙፍን ጠባቂ ሀይል ላይ ከጧቱ 12 ሰዓት ጀምሮ በ12ኛ ከ/ጦር መካናይዝድ በመታገዝ በአንደኛና በአራተኛ ሻለቃ የሰራዊት አባላት በጥላት ላይ ሰብአዊና ቁሳዊ ኪሳራ አደረሱበት።
በጧት የጀመረው አውደ ውጊያ የ102ኛ ኮር የ12ኛ ክ/ጦር በጮቢ በር አቅራቢያ በነበረው አውደ ውጊያ እንደተለመደው የጥላትን ድሽቃ በወገን ሞርተር ሙሉ በሙሉ በመውደሙ በአገዛዙ በኩል ከፍተኛ ድንጋጤ ተፈጥሯል።
በተጨማሪም በርካታ የእግረኛ ሰራዊት አባላትና ሻንበል መሪውን ጨምሮ ሙትና ቁስለኛ ሳያነሳ እግሬ አውጭኝ በማለት ወደ ንጉስ ጋሌና ወደ ጠዘጠዛ ምሽግ በመሸሽ ተበትኗል።
በመጨረሻም ጠላት በጧት ጀምሮ በድሮን፣ በቢ-ኤም፣በዙ-23፣ በመድፍና በታንክ የተጠናከረ ማጥቃት ቢያደርግም በ12ኛ ክፍለ ጦር የምትመራው የ1ኛ ሻለቃንና የ2ኛ ሻላቃ አይበገሬዎቹን ማቆም ተስኖት ቀጠናውን ለወገን ሀይል አስረክቦ ወጥቷል።
መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልዉና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል!
ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን!
አፋብን ወሎ ቤተ-አማራ ምኒልክ ዕዝ የ102ኛ ኮር ህዝብ ግንኙነት ክፍል
ሚያዚያ 21/2018 ዓ/ም
#አስቸኳይ_የጥንቃቄ_መልዕክት⚠️
⏭የድሮን ቅኝት⚠️
በበርካታ የሸዋ ቀጠናዎች፣በመንዝ ጥርጥራ፣በማፉድ፣በራሳ፣በሳሲት፣ በአልዩ አምባ፣ በአጋምበር፣ በባሽና በአንኮበር ቀጠናዎች
የድሮን ቅኝት እየተደረገ ይገኛል።
✅ከመረጃና ደህንነት መምሪያ🚫
ሰበር ሰበር ሰበር"
የሜጫ አዳኞች ታሪክ ሠርተዋል
ሚያዝያ 21/2018 ዓ.ም
አፋብን ምእራብ አማራ ቀጠና ቴወድሮስ እዝ 102ኛ ኮር 11ኛ ክ/ጦር መራዊ ከተማ ከምሽቱ 2:00 አካባቢ በአነፍናፊ የከተማ አዳኞች እጅግ የተሳካለት ኦፕሬሽን ማድረግ ተችሏል።
የመራዊ ማህበረሰብን በሰቀቀን እና በከፋ መከራ ሲያሰቃዩ የነበሩ የብልፅግና ታማኝ ወንበር አስጠባቂዎች እስከ ወዲያኛው ተሸኝተዋል። በአዳኞቹ በተደረገ ከባድ ኦፕሬሽን
1ኛ. ጌታቸው ፈንቴ የ01 ቀበሌ ስራ አስኪያጅ
2ኛ. አቢቴ ማለደ ከባ/ዳር እስከ መራዊ ከመራዊ እስከ አቸፈር በፋኖ ስም ሰዎችን እያገተ ሲዘርፍ የነበረ እና የመሪያችን አርበኛ ዘመነ ካሴን ቤተሰቦች በድሮን ያስደበደበ 105 በላይ የቀንድ ከብት ለጠላት ነድቶ የሰጠ ግለሰብ እና በብልፅግና የባችማ ቀበሌ እንዲያስተዳድር ሃላፊነት የተሰጠው
3ኛ. አንዷለም የመዘጋጃ ፋይናንስ ሃላፊ የነበረ
4ኛ. ፈጠነ
5ኛ. አለልኝ
6ኛ. ጋሻነህ ብዙአየሁ (ጃሪ)
7ኛ አንተሁነኝ እምቢያለ የተባሉ የብልፅግና ጠበቃዎች ዋጋቸውን አግኝተዋል። የአማራ ህዝብን ለከፋ መከራ አሳልፈው የሰጡ ጥቁር ጣሊያኖች ከሆዳቸው ጋር እንደተጣበቁ እርምጃ ሲወሰድባቸው 7 ክላሽንኮፍ መሳሪያ ተማርኳል። ከዚህ ጋር በተያያዘ በውል ቁጥራቸው የማይታወቅ ሆድ አደሮች ከባድና ቀላል ቁስለኛ መሆናቸውን ማወቅ ተችሏል።
በከፍተኛ የወትሮ ዝግጁነት ላይ የሚገኘው የ11ኛ ክ/ጦር በቀጣይ እንደ ንስር ታድሶ በአስፈሪ ግርማ ሞገስ እየመጣ እንደሆነ እና ጠላትን አፈር ደሜ ለማብላት በተጠንቀቅ ላይ መሆኑን ለማወቅ ተችሏል።
መረጃው፦
የ102ኛ ኮር 11ኛ ክ/ጦር ሕ/ ግንኙነት ነዉ
የችሎት ውሎ መረጃ!
አማራ ማንነታቸው እንደ ወንጀል ተቆጥሮ በሽብር ወንጀል የተከሰሱ የፖለቲካ እና የሕሊና እስረኞች ፍ/ቤት ቀርበዋል።
(1) ~ በእነ ጌታው አዳሙ መዝገብ ፦
ተከሳሾች ጌታው አዳሙ እና አሰፋ እንቁ ከቂሊንጦ ማ/ቤት ሚያዝያ 20/2018 በፌደራል ከፍተኛ ፍ/ቤት ልደታ ምድብ 2ኛ የሕገ መንግስት እና የፀረ ሽብር ወንጀል ችሎት
ቀርበው ነበር።
መዝገቡ የተቀጠረው ይከላከሉ ወይስ አይከላከሉ በሚለው ጉዳይ መዝገቡን መርምሮ ብይን ለመስጠት ነበር።
በዚህም መሰረት ፍ/ቤቱ ጥፋተኛ ናችሁ ተከላከሉ ሲል ብይን ሰጥቷል።
የተከሰሱት በአንቀጽ 29 (2) 'ሀ' ስር ያለውን ድንጋጌ በመተላለፍ ቢሆንም ተሻሽሎ በአንቀጽ 29 (1) 'ሀ' ስር የተደነገገውን በመተላለፍ በሚለው እንዲከላከሉ በማለት ለሰኔ 16/2018 ቀጠሮ ተይዟል።
(2) ~ በእነ ሀብታሙ መሀመድ መዝገብ ፦
በመዝገቡ የተካተቱ 4 (አራት) ሰዎች ከማ/ቤት በችሎት የተገኙ ሲሆን መዝገቡ የተቀጠረው የተከሳሾች የመከላከያ ምስክሮችን ለመስማት በሚል ነበር።
ተከሳሾች የመከላከያ ምስክሮችን ሲያሰሙ ውለዋል ፤ ሂደቱም እስከ ሚያዝያ 22/2018 ድረስ እንደሚቀጥል ታውቋል።
ከመከላከያ ምስክሮች መካከልም ከፋኖ ትግል በመውጣት በተለይም ላለፉት ሶስት ዓመታት በአማራ ሕዝብ ላይ ጦርነት አውጆ ሁሉን አቀፍ ጥቃት እየፈፀመ ለሚገኘው ለኦህዴድ ብልጽግና አገዛዝ እጃቸውን የሰጡት ካፒቴን ማስረሻ ሰጠኝ እና መስፍን ከፈለኝ ይገኙበታል ፤ በእለቱም እንደ እስረኛ በርከት ባሉ አጃቢዎች ተከበው ቀርበው እንደነበር ታውቋል።
(3) ~ በእነ ፈለቀ ታደሰ መዝገብ ፦
ተከሳሾች ፈለቀ ታደሰ (ከቂሊንጦ ማ/ቤት) እና ታደሰ አባቡ (ከአባ ሳሙኤል ማ/ቤት) እንዲሁም ዮሃንስ አንዳርጌ ከውጭ በችሎት ቀርበዋል ፤ አንጻሩ ብሩክ ብናልፍ የተባለው ተከሳሽ ከውጭ አልቀረበም።
በእለቱም ተከሳሽ ፈለቀ ታደሰ በፌደራል ፖሊስ ወንጀል ምርመራ ቢሮ ሜክሲኮ በነበሩበት ወቅት በማንነታቸው የተነሳ ተፈፅሞብናል ያሉትን ከፍተኛ የሆነ የሰብአዊ መብት ጥሰት በተመለከተ ፍ/ቤቱ አጣርቶ እንዲያሳውቅ በሚል ለኢሰመኮ ትዕዛዝ የሰጠ ቢሆንም እስካሁን ድረስ ሪፖርቱ አለመቅረቡን በመጥቀስ ዳግም ትዕዛዝ እንዲሰጥላቸው ብሎም ሪፖርቱ ለተከሳሾች እና ለችሎቱ እንዲሰጥ ጠይቋል።
ታደሰ አባቡ በበኩሉ ከዚህ በፊት በችሎት በቀረበበት ወቅት በአባ ሳሙኤል ከፍተኛ ጥበቃ ማ/ቤት በሚሰሩ ፖሊሶች ከፍተኛ የሆነ የሰብአዊ መብት ጥሰት መፈፀሙን በቃል ሲያቀርብ ችሎቱ አቤቱታህን በጽሁፍ ጨቅርብ ባለው መሰረት ማዘጋጀቱን ገልጾ ይሁን እንጅ ማ/ቤቱ አቤቱታውን ካነበበ በኋላ ማህተም አላደርግም በሚል መከልከሉን አስታውቋል።
ነገር ግን ኮፒውን ይዞ ወደ ፍ/ቤት እንዳይሄድ በሚል ከፍተኛ ፍተሻ የተደረገበት ቢሆንም ኮፒውን ደብቆ ይዞ መቅረቡን በመግለጽ ችሎቱ እንዲቀበለው ጠይቋል።
የፍ/ቤቱ የመሃል ዳኛ ማመልከቻውን ተቀብለው ለማ/ቤቱ ጉዳይ አስፈጻሚ በመስጠት በነገው እለት ማህተም አስመትተህ እንድትቀርብ በማለት አዘዋል።
ተከሳሾች የቀረቡት ፍ/ቤቱ መዝገቡን መርምሮ ብይን ይሰጣል በሚል ነበር።
ዳሩ ግን ዛሬም አልተበየነም።
ተከሳሾች በሰነድ አስተያየት ላይ የስልክ ጠለፋ የተፈፀመብን በፍ/ቤት ትዕዛዝ ስለመሆኑ መረጃው ይቅረብልን በማለት መጠየቃቸውን ተከትሎ ዐቃቤ ሕግ የፍ/ቤቱን ማዘዣ ይዞ እንዲቀርብ በፍ/ቤቱ የታዘዘ ቢሆንም እስካሁን ምላሹን አላመጣም።
ስለሆነም ዐቃቤ ሕግ የጠለፋ ማዘዣውን ለግንቦት 4/2018 ይዞ እንዲቀርብ በሚል ተለዋጭ ቀጠሮ ተሰጥቷል።
(4) ~ በእነ ካሳሁን ሸዋቀና መዝገብ ፦
በመዝገቡ የተከሰሱ 4 (አራት) ሰዎች ማለትም፦
1. ካሳሁን ሸዋቀና፣
2. ተፈራ ጌታቸው፣
3. ታፈረ ቆዬ እና
4. ብዙአየሁ ጌታቸው በእለቱ ችሎት ተገኝተዋል።
አንደኛ ተከሳሽ ክሱ ዋስትና የሚያስከለክል በመሆኑ ክርክር አላደረገም።
በአንጻሩ ሶስቱ ተከሳሾች ግን በቀደመው ችሎት የዋስትና ክርክር ያደረጉ በመሆኑ ብይን ተሰጥቷል።
በመሆኑም ከመካከላቸው ሁለቱ ሲከለከሉ ሶስተኛ ተከሳሽ አቶ ታፈረ ቆዬ ግን በ50 (አምሳ) ሽህ ብር ዋስትና ከእስር ተፈተው ጉዳያቸውን በውጭ ሆነው እንዲከላከሉ ተወስኗል።
በመሆኑም የሰነድ አስተያየት በጠበቃ በኩል ለማቅረብ ለግንቦት 3/2018 ተለዋጭ ቀጠሮ ተሰጥተዋል።
በተያያዘ ከ60 በላይ የሚሆኑ ከጋምቤላ ክልል ተይዘው ወደ ቂሊንጦ ማ/ቤት የመጡ አመራሮችና አባላት በሽብር ወንጀል ተከሰው በተመሳሳይ ችሎት ቀርበው እንደነበርም ለማወቅ ተችሏል።
መረጃው የአውሎግሶን አንድነት ነው።
ሰበር ዜና!!
አፋብን ወሎ ቤተ-አማራ ጀብደኛው ምኒልክ ዕዝ የምስራቅ አማራ 102ኛ ኮር በሰሜን ወሎ ዞን ራያ ቆቦ ወረዳ በቀዩ ጋሪያ፣በአረቋቲና በሮቢት ከተማ ህዝባችንን በማንገላታት የሚታወቀው የአብይ አህመድን ወንበር ጠባቂ ወታደር እርምጃ ወሰደበት።
የአማራ ፋኖ ወሎ ቤተ-አማራ ምኒልክ ዕዝ የምስራቅ አማራ 102ኛ ኮር ዛሬም እንደ ትናንቱ የብልፅግና መራሹ አገዛዝ ላይ አስደናቂ የሆነ መብረቃዊ ጥቃት ፈፀመበት ።
ህዝባችንን በሀይል በመደብደብ ለ7ኛው የአምባገነኑ ብልፅግና ምርጫ የምርጫ ካርድ በአስገዳጅ ሁኔታ ለማስወጣት በቀዩ ጋሪያ፣በአረቋቲና በሮቢት ከተማ ሙከራ ቢያደርግም ልማደኛው የምስራቅ አማራ102ኛ ኮር 12ኛ ክ/ጦር 3ኛ ሻለቃ በአረቋቲ፣ 65ኛ ክ/ጦር በቀዩ ጋሪያ፣ 49ኛ ክ/ጦር በሮቢት ከተማ አቅራቢያ ምሽግና ኬላውን በማስለቀቅ በጥላት ላይ የስነ-ልቦና ስብራት በማድረስ በራያ ቆቦ ዙሪያ ያሉ ቀበሌዎችን ቀጠናውን በማስፋት በቁጥጥር ስር አውሏል።
በተጨማሪም የምስራቅ አማራ102ኛ ኮር አውደ ውጊያ ባደረገባቸው በሁሉም ቀጠናዎች ዘልቆ በመግባት 45 የመከላከያ ሰራዊት አባል 10 የፌደራል ፖሊስ አባል በተከታታይ የሞርተርና የድሽቃ ጥቃት በማድረግ የጌታቸው ረዳን ራሱን ሐራ መሬት እያለ የሚጠራውን የሰራዊት አባል በደጋሜ ደምስሷል።
በዚህ ዘመቻ የነበሩት የምስራቅ አማራ102ኛ ኮር ወታደራዊ አዛዦችና ወታደራ ዘመቻ መሪዎች በሚገርም መናበብና ጦርነቱን እንደተለመደው በተሻለ ብቃት በጥላት ላይ አስደማሚ ገድል መፈፀሙን የ102ኛ ኮር የህዝብ ግንኙነት ገልጿል።
ጠላት ከሰዓት ጀምሮ በድሮን፣ በቢ-ኤም፣በዙ-23፣ በመድፍና በታንክ የተጠናከረ ማጥቃት ቢያደርግም የ102ኛ ኮር አመሻሽ ላይ የ12ኛ ክ/ጦር በሀብተማሪያም መንበሩ የምትመራው የ3ኛ ሻለቃ ዋና አዛዥ የአርበኛ ዝናቤ አማረን ልጆች አይበገሬዎቹን ማቆም ተስኖት ውሏል።
ከሰዓት የጀመረው አውደ ውጊያ በአገዛዙ ላይ ወታደራዊና ፖለቲካዊ የስበት ማዕከሉን በመለየት የምስራቅ አማራ 102ኛ ኮር የ65ኛ ክ/ጦር በአስር አለቃ ሻምበል ተሾመ የምትመራውና የ49ኛ ክ/ጦር በለገሰ ሰማው የምትመራው በጋራ በመሆን የሀይል የበላይነትን በመውሰድ ከላይ የተጠቀሱትን የገጠር ቀበሌዎችንና ከተሞች በቁጥጥር ስር አውሏል።
ከሰዓት የጀመረው ዘመቻ የምስራቅ አማራ102ኛ ኮር የ49ኛ ክ/ጦር በሮቢት ከተማ አቅራቢያ በነበረው አውደ ውጊያ የጥላትን ድሽቃ በወገን ሞርተር ሙሉ በሙሉ በመውደሙ በአገዛዙ በኩል ከፍተኛ ድንጋጤ ተፈጥሯል።
በመጨረሻም የአማራ ፋኖን ጥቃት መቋቋም ያቃተውና ቤተ-ክርስቲያን በማውደም የሚታወቀው አገዛዝ ሆርማት ሆኖ በግምት ባስወነጨፈው መዲፍ በተለምዶ ታችኛው ጎለሻ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ አንድት እናት ከቤቷ ላይ በማረፉ የ3 አመት ልጅ እንዳዘለች ህይወቷን ቀጥፋል።
በአውደ ውጊያው የተገኘ ሞርኮና አጠቃላይ ድሎችን ዘገባውን አጠናቅረን የምንመለስ ይሆናል።
መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልዉና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል!
ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን!
የአፋብን ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ የምስራቅ አማራ102ኛ ኮር ህዝብ ግንኙነት
ሚያዚያ 20/2018ዓ/ም
ብልፅግና ያዝኩት ብሎ ካሰራጨው የኮሎኔል አለሙ ሞላ መረጃ ጋር ተያይዞ መሬት ላይ ያለው ሐቅ!
ኮሎኔል አለሙ ሞላ በቀድሞው ምስራቅ አማራ ፋኖም ይሁን በአሁኑ ምኒልክ ዕዝ ምንም አይነት ሃላፊነት የሌለውና ከ2016 ዓ.ም ክረምት ጀምሮ ትግሉ ላይም ያልነበረ ሲሆን ሃብሩ ወረዳ ጊራና ዙሪያ ልዩ ስሙ ጎራርባ የተባለ ቦታ ላይ ትዳር መስርቶ ወልዶ እየኖረ የነበረ ነው::
መሬት ላይ ያለው እውነታ ኮሎኔሉ ከብልፅግና መከላከያ ሰራዊትም ይሁን ከፋኖ ነፃ ሆኖ የግል ህይወቱን እየኖረ ባለበት ሁኔታ ለፖለቲካና ለፕሮፓጋንዳ ፍጆታ ለማዋል ሲባል ከእውነት የራቀ ነገር ማሰራጨቱ ከብልፅግና አገዛዝ የሚጠበቅና ከተለመደ ህዝብን የማደናገር ተግባር የተለየ አይደለም::
መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልውና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል!
ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን!
አፋብን ወሎ ቤተ-አማራ ምኒልክ ዕዝ
ሚያዚያ 20/2018 ዓ.ም
+1
አፋብን ጎንደር ጠቅላይ ግዛት በላይ ዕዝ 206ኛ ከፍያለው ደሴ ኮር አንበሳው ጋይንት ክፍለ ጦር በምርኮ የተያዙ የመከላከያ ፣የአድማ ብተና፣የፖሊስ እና ሚኒሻ አካላት ተገቢውን የተሀድሶ ስልጠና በመስጠት ተለቀዋል።
መጋቢት 09/2018 ዓ.ም ጋይንት ንፋስ መውጫ ከተማ የተማረኩት አባላቶቹ በቆይታቸው ተገቢውን በክፍለ ጦር የፖለቲካ ዘርፍ ክፍል ፣ በኮሩ የህግ ክፍልና በሌሎች ስራ አስፈጻሚዎች የፖለቲካ የግንዛቤ ተሰጥቷቸው ወደ ማህበረሰቡ እንዲቀላቀሉ ተደርጓል።
አስተያየት እንዲሰጡ የተጠየቁት ምርኮኞቹ በነበራቸው ቆይታ ተገቢውን እንክብካቤ እንደተደረገላቸው በመግለጽ ለማህበረሰቡ ፣ለክፍለ ጦሩ አመራር እና ለመላው አባላቱ ምስጋና አቅርበዋል።
ድል ለአማራ ህዝብ !!!
ድል ለአማራ ፋኖ !!!
አፋብን ጎንደር ጠቅላይ ግዛት በላይ ዕዝ 206ኛ ከፍያለው ደሴ ኮር ቃል አቀባይ ክፍል!!!
