ፍኖተ-አማራ ሚዲያ (Finote Amhara Media)
Открыть в Telegram
የተመሠረተው የአማራን ሕዝብ ለማንቃት፣ ለማደራጀት እና ለማስተባበር ነው። የአማራ ሕዝብን ✅ ፖለቲካዊ ✅ ማህበራዊ ✅ ኢኮኖሚያዊ ታሪካዊ ጥያቄዎችን ለማሰማት እና የአማራን ሕዝብ በማንቃት ሰፊውን ሕዝብ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ይሰራል። ወደዱም ጠሉም የኃላ ታሪካችን በእኛ እጅ ይፃፋል። አማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ ( አፋብን)
Больше4 387
Подписчики
-424 часа
+2487 дней
+1 44230 дней
Архив постов
#ስናይፐር_ይዞ_ፋኖን_ተቀላቅሏል!
የመዋጋት ሞራሉ የላሸቀው የብልፅግና ሰራዊት በየቀኑ እየከዳ ፋኖን በመቀላቀል ላይ ይገኛል።
##ምክትል_አስርአለቃ_መልካሙ_ስማቸው 22ኛ ክፍለጦር ውስጥ የሚገኘው የጠላት ካምፕ የነበረ ሲሆን 01 ስናይፐር በመያዝ የ105ኛ ኮር 66 ክ/ጦር አባይ መተከል ሻለቃን ተቀላቅሏል።
አፋብኃ|ቴዎድሮስ ዕዝ ሕዝብ ግንኙነት መምሪያ
ህዳር 12/2018 ዓም
#ስናይፐር_ይዞ_ፋኖን_ተቀላቅሏል!
የመዋጋት ሞራሉ የላሸቀው የብልፅግና ሰራዊት በየቀኑ እየከዳ ፋኖን በመቀላቀል ላይ ይገኛል።
##ምክትል_አስርአለቃ_መልካሙ_ስማቸው 22ኛ ክፍለጦር ውስጥ የሚገኘው የጠላት ካምፕ የነበረ ሲሆን 01 ስናይፐር በመያዝ የ105ኛ ኮር 66 ክ/ጦር አባይ መተከል ሻለቃን ተቀላቅሏል።
አፋብኃ|ቴዎድሮስ ዕዝ ሕዝብ ግንኙነት መምሪያ
ህዳር 12/2018 ዓም
የአረመኔው ጡት ቆራጭ የብልፅግና መቶ መሪ የደባይ ጮቄ የፋኖ ኃይሎችን ተቀላቀለ
ህዳር 12/2018 ዓ.ም
በአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል/አፋብኃ/ምዕራብ አማራ ቀጠና ቴዎድሮስ ዕዝ 206ኛ ኮር 24ኛ ክ/ጦ ፲ አለቃ #ማስረሻ_አሰማ_መሠሉ የተባለ የአገዛዙ መከላከያ ሰራዊት አባል የነበረ በአማራ ህዝብ ላይ እየደሰሠ ያለውን አረመኔያዊ ሰቆቃ በመረዳት በዛሬው ዕለት ደባይ ጮቄ ሻለቃን ከነ ሙሉ ትጥቁ ቸቀላቅሏል።
፲ አለቃ ማስረሻ አሰማ መሠሉ በመከላከያ ሰራዊት
6ኛዕዝ 52ክ/ጦር 1ኛ ሬጅመንት 2ኛ ሻምበል ውስጥ ጋንታ መሪ የነበረ ሲሆን በዛሬው በመከላከያ ተቋሙ ውስጥ ፋኖ ናችሁ ትግፋላችሁ በሚል በሙሉ የአማራ ተወላጅ መከላከያ ሰራዊት አባላትን ትጥቃቸውን በማውረድ በማሰርና በማሰቃየት ላይ መሆኑን የተናገረ ሲሆን ዛሬ ላይ ከአማራነቴ ማማ ላይ ከምወዳቸው ጓዶቼ ጋር በመቀላቀሌ ደስተኛ ነኝ ሲል ደስታውን በመግለፅ ለቀጣይ ይህንን አረመኔያዊ ስርዓት ከወንድሞቹ ጋር በመሆን ትግሉን እንደሚቀጥል አውስቷል!!!!
አዲስ ትውልድ አዲስ ተስፋአዲስ አስተሳሰብ
Hailemariam Kiber Temesgen
አፋብኃ ምዕ/አማራ ቀጠና ቴዎድሮስ ዕዝ 206ኛ ኮር 24ኛ ክ/ጦር የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ
ያች ጥቁር ቀን‼️
ወፎች ጭጭ ጭጭ ይላሉ የንጋቱ ቅዝቃዜ ያዘለ ንፋስ ይነፍሳል ዉሾች ይጮሀሉ ሰማዩ በብርሃን አና ጨለማ መካከል ደብዘዝ ብሏል አባ ረፍርፍ መቶ ዓለቃ ማናዬ መኮነንን እንደተለመደዉ ቦታዉን ይዞ በንስር እይታ በአራቱም አቅጣጫ ያማትራል ከንጋቱ 11:00 ስዓት ላይ አማራን በምስር ወጥ በሸጡ የእናት ጡት ነካሾች መንገድ መሪነት በጠላት ከበባ ዉስጥ ወደቀ።
አባ ረፍርፍ አየር ወለዱ መቶ ዓለቃ ማናዬ መኮነንን በጠላት ከበባ ዉስጥ መሆኑን ባወቀ ጊዜ አብረዉት የነበሩትን ኮማንዶ የቻለ ገብሬን እና ፋኖ ነብዩን ገዥ ቦታ በማስያዝ እንደ ጉንዳል እየተሰለከለከ በባንዳዉ መሪነት የመጣዉን የጁላ ሰራዊት ረፈረፉት ከ30 ደቂቃ ያላነሰ ዉጊያ ሁለቱን ንስሮች በመያዝ አደረገ በርካታ የጁላ ሰራዊት ታሪክ ሁኖ እንዲቀር አደረገ ማናዬ ከያዘዉ 5 ካዘና 4ቱ ካዘና እስከሚያልቅ ድረስ ከጠላት ጋር ፊት ለፊት ተፋለመ።
በዚህ ጊዜ መቶ ዓለቃን ያበሳጨ፣እንደ አራስ ነብር ያደረገ አንድ ነገር ተከሰተ ከጎኑ ሁኖ ጠላትን ሲወቃዉ የነበረዉ ኮማንዶ የቻለ መሰዋቱን አዬ ያኔ መቶ እንደ አራስ ነብር ሆነ ከትጥቁ የያዘዉን ቦንብ አዉጥቶ ወደ ጠላት እየጣለ ከጠላት ጋር የእጅ በእጅ (የጨበጣ) ዉጊያ አደረገ በርካታዉን የጁላ ሰራዊት ወደ አመድነት ቀየረ ወደ ሌላኛዉ አቅጣጫ በመዞር ዲሽቃ ተኳሹን በቦንብ አጋየዉ ፋኖ ነብዩም በአንድ አቅጣጫ በመሆን ሽፋን እየሰጠዉ ወደ ጠላት ተጠጋ የዲሽቃ ረዳት ተኳሹን እጅ በእጅ ተናነቀዉ ከሩቅ በተተኮሰ ጥይትም ፋኖ ነብዩ ተሰዋ ።
አይበገሬዉ አባ ደፋር መቶ ዓለቃ ማናዬ ከ30 ደቂቃ በላይ ከጠላት ጋር ተናነቀ ብዙ ጠላትንም ታሪክ ሁነዉ እንዲቀሩ አደረገ በመጨረሻም በቀሪዋ አንድ ጥይት እራሱን ሰዋ።
አቸፈር ወንድዬ ሞፈር መቁረጥ ያዉቃል
ካልተለበለበ መቸ የታረቃል‼️
አይኑን በቀጫጭን የተኳኳለዉ
እንደ ነብር ጅራት የሚወራጨዉ
እንዴት ነዉ ማናዬ አቸፈር ያለዉ
የተባለለት አየር ወለዱ መቶ ዓለቃ ማናዬ መኮነንን ‼️
የወንድማችን የ40 ቀን መታሰቢያ ወዳጅ ዘመዶቹ በተገኙበት ተከናዉኗል።
ነፍስህ ከደጋጎች ጎን ትረፍ‼️
ማርበርግ ቫይረስ አርሲ እና ምዕራብ ሀረርጌ
ኦርቶዶክሳውያን ስቃይ የተባባሰባቸው ቦታዎች ከማርበርግ ጋር ስማቸው እየተነሳ ነው፡፡ ባሳለፍነው ወር ምዕራብ ሃረርጌ አሰቦት አካባቢ ሁለት ልጆች ከመታገታቸው በተጨማሪ የገዳሙ ስራ በተግባር ቤት ስራ የሚያግዙ በገዳሙ ዙሪያ የሚኖር ንብ በማነብ ላይ እያሉ ተኩስ ከፈቱባቸው፡፡ በዚህ የተኩስ እሩምታ ምክንያት አንደኛው አረጋዊ መነኩሴ ወዲያው ሲሞቱ ሌላኛው መነኩሴ ከባድ የአካል ጉዳት ደርሶባቸው እስካሁን በህክምና ላይ መሆናቸው የተዘገበው በቅርቡ ነበር፡፡ በምዕራብ ሐረርጌ በጉባ ጉቱ እና አው ጉዲና ወረዳዎች እንዲሁም በጭሮ ወረዳ በረብሱ አካባቢ ደግሞ የስድስት ኦርቶዶክሳዊያን ሕይወት በአሰቃቂ ሁኔታ ተቀጥፏል የሚለው መረጃም የዚህ ሳምንት መረጃ ነበር።
እንደ ምዕራብ ሐረርጌ ፣ምስራቅ ሐረርጌ እና አርሲ ባሉ ቦታዎች ላይ ኦርቶዶክሳዊያን እየኖሩ ያሉት በስጋት ሲሆን ሌሎች ደግሞ በስደት ላይ ናቸው። በሌላ በኩል ማርበርግ ቫይረስ ምዕራብ ሀረርጌ እና ምስራቅ አርሲ እንደተከሰተ ሚዲያዎች እየዘገቡ ቢሆንም በክርስቲያኖች ግድያ እንደለመዱት ክህደት የአካባቢው ባለስልጣናት ውሸት ነው ብለው እያሉ ነው፡፡ ለማንኛውም ለክርስቲያኑም ለሙስሊሙም ለእናንተም ጭምር በሽታው አስከፊ ስለሆነ ግዴላችሁም ትኩረት ስጡት፡፡ በዛው ሰው በማፈናቀል በመግደል የዛለው እጅና አዕምሮ ፋታ ያግኝ፡፡
እኛ ግን አጀንዳችንን አንቀይርም የኦርቶዶክሳውያን ሞት ይቁም፡፡
#በሃገራችን_ኢትዮጵያ_እየተፈጸመ_ያለው_የኦርቶዶክሳውያን_እልቂት_የመንግሥት_መዋቅር_የሚያውቀው_የሚደግፈው_ሽፋን_እየሰጠ_የሚያበረታታው_እንጂ_ባልታወቁ_ኃይሎች_የሚፈጸም_ወንጀል_አይደለም
©ስምዓ ተዋሕዶ
እናት ብቻዋን አይደለችም፤ እናት የአማራ ክልል የትጥቅ እንቅስቃሴ ከተቀሰቀሰ ከሐምሌ 2015 ዓ.ም. ጀምሮ ወሲባዊ ጥቃት ደርሶባቸዋል ተብሎ ከሚታመኑ በሺህዎች ከሚቆጠሩ ሴቶች ውስጥ አንዷ ናት።
ምንም እንኳ እውነተኛው ግጭት ነክ የወሲባዊ ጥቃት መጠን ሪፖርት ባለመደጉ እና ባለመርመሩ በትክክል ባይታወቅም፤ ቢቢሲ ያሰባሰበው መረጃ ከሐምሌ 2015 እስከ ግንቦት 2017 ዓ.ም. ድረስ ከስምንት ዓመት እስከ 65 ዓመት ዕድሜ ያላቸው በሺህዎች የሚቆጠሩ ሰዎች የአስገድዶ መድፈር ጥቃት እንደደረሰባቸው ያመለክታል። ዝርዝር ዘገባውን እዚህ ያንብቡ https://bbc.in/4oRFq4g
© BBC
#የጥንቃቄ_መልክት‼️
የብልፅግና ስርአት ይፋዊ ጦርነት ከጀመሩ ሁለት ድፍን አመት አልፈውታል በመሆኑም በተለያዬ የከተሞች የምትገኙ ወጣቶች ራሳችሁን ንፁህ ነን ብለችሁ የስር አቱን አስከፊ እና ጨፍጫፊነት እያወቃችሁ ከጠላት ጋር በተለያዩ ከተሞች ማለትም በፍኖተ ሰላም አደይ አበባ ግሮሰሪ እና በተለያዩ ፑል ቤት፣መጠጥ ቤት እና የመሳሰሉት በመሰባሰብ የምትንቀሳቀሱ ወጣቶች መንግስት ጥናት በመስራት አፈሳ የጀመረ መሆኑን እየገለፅን ራሳችሁን ከዚህ አረመኔ ስርአት አድኑ።
አዲስ ትውልድ
አዲስ አስተሳሰብ
አዲስ ተስፋ
12/ዐ3/2018 ዓ.ም
⚫️#ሰው በይው ጅብ ብልም ቃላት ያንስብኛል🩸
ሰው በይው ጅብ ብልም ቃላት ያንስብኛል፣
አረመኔ ብልም ቃላት ያንስብኛል፣
እስከ መቼ ድረስ እኔንስ መሮኛል።
ከትናቱም ዛሬየዛሬው አመመኝ፣
ለመስማት አይመች ኧረ ሰቀጠጠኝ፣
እናት እህቶችን በሰይፍ ሲያርድብኝ።
ወለጋ ቢሄዱም በግፍ አረደና አፈናቀለብኝ፣
መተከል ቢሄዱም በግፍ አረደና አፈናቀለብኝ፣
ሸገርም ቢሄዱ በግፍ አረደናአፈናቀለብኝ፣
ከእናቷ ቤት መጦ ከአባቷ ባድማ ምንም ማታውቅ ህፃን ዛሬም አረደብኝ።
የፃዲቁ ስፍራ የፃዲቁም አምላክ ታምርን ስራልኝ፣
ይህን አረመኔ አባይም ሙላና ውሀው ውሰድልኝ።
ፋኖ መከታዬ ፋኖም አለይታዬ ጉድን አየህልኝ፣
አንተ ድረስና ከዚህ ጅብ ገላግለኝ፣
ይህን አረመኔ መግደል ብቻ አይደለም፣
በፃዲቁ ስልህ ሰቅለህም አሳየኝ።
ብርሀኑ ጁላ ነፍስን አይማረው፣
የአማራን ደምስጋ ቀለብህ ያረከው።
የህፃኖች አምላክ አየህ እሂንን ጉድ፣
የእናቶችም አምላክ አየህ እሂንን ጉድ፣
የፃዲቁም አምላክ አየህ እሂንን ጉድ ፣
በደሉም በዛብን ወይፍረድ ውድ ውረድ ።
መታሰቢያነቱ በሰከላ ወረዳ በግፍ ለተደፈረችው፣በግፍ ለታረደችው እና ሰማእቷን ለተቀበለችው ለተማሪ ቃልኪዳን
12/ዐ3/2018 ዓ.ም
ምሥራቅ አርሲ ሮቤ ወረዳ
👉በ 08/03/ በሲቤ መራሮ ቅዱስ ሚካኤል ሀብት ንብረታቸው የተዘረፈባቸው ከብቶቻቸው ሙሉ በሙሉ የተወሰዱባቸው ቤት ውስጥ ያለ አንድም ዕቃ ያልተረፈላቸው፦
፩ ቄስ በቀለ ተክለማርያም
፪ ዱባለ ተክለማርያም
፫ አለሙ ቅጣው
፬ ተስፋዬ ቅጣው
👉09/03/2018 እንደቶ የሚባል ቦታ አጨዳ ላይ እንዳሉ ታግተው የተወሰዱና ደብዛቸው የጠፋ ኦርቶዶክሳውያን
፩ ግርማ ገብሬ
፪ ወ/ሮ መስታወት ንጉሡ(ባለቤት)
፫ ወ/ሮ አበራሽ ታደሰ(እናት)
፬ ወጣት ቡሊ መኩሪያ(ልጅ)
፭ ባሻው ጎሣ
፮ ሰለሞን ተፈሪ
፯ ቡሊ ጎሣ
እነዚህ ኦርቶዶክሳውያን የት እንዳሉ ያልታወቀ ሲሆን ሊገድሏቸውም እንደሚችሉ እየተነገረ ነው።
👉 በወረዳው ላይ ካሉት 33 አቢያተ ክርስቲያናት 31 እጅግ አስጋሪ ሁኔታዎች ላይ ናቸው
👉 በሺዎች የሚቆጠሩ ቤታቸውን ለቀው ተሰደዋል
👉 የኦሮሚያ ቤተ ክህነት አቀንቃኞች ነን የሚሉ ኀይሎች ከአክራሪ እስልምና ጋር ተናበው የቤተ ክርስቲያን አገልጋዮችን እያሳደዱ ይገኛሉ
👉ከ2016ዓ.ም ጀምሮ ካህናትን ጨምሮ ቁጥራቸው ቀላል የማይባል ኦርቶዶክሳውያን ተገድለዋል
"በአማራ ህዝብ በተፈፀሙ የሰብአዊ መብት ጥሰቶች ላይ ገለልተኛ አለም አቀፍ ምርመራ ሊደረግ ይገባል" ሲሉ ዶ/ር ደሳለኝ ጫኔ አሳሰቡ፡፡ ዶ/ር ደሳለኝ ጫኔ በቢቢሲ የቀረበውን ዘገባ በተመለከተ በሰጡት አስተያየት ሪፖርቱን በአማራ ህዝብ ላይ በአሁኑ ወቅት እያጋጠመ ያለውን ከፍተኛ ስቃይ የሚያረጋግጥ መሆኑን ገልፀዋል፡፡
በአረመኒው አብይ አህመድ ጡት ቆራጮች ኃይሎችና በፋኖ መካከል ግጭቱ ከተከሰተ ወዲህ ይህ ቀውስ እየባሰበት መሄዱን የጠቀሱት ዶ/ር ደሳለኝ በሰላማዊ ሰዎች ሞት፣ ስቃይና መፈናቀል አገሪቱ እየተጎዳች መሆኑን አስረድተዋል፡፡ በተራዘመው የእርስ በእርስ ጦርነት ንፁሀን አማሮች የጅምላ ተጠቂ ሲሆኑ ዝም ብሎ መመልከት እንደማይገባ ያሳሰቡት ዶ/ር ደሳለኝ ጨምረውም ‹‹እንደህዝብ ተወካይነቴ ሁሉም ተፋላሚ አካላት በአስቸኳይ ግጭቱን እንዲያቆሙ ጥሪ አቀርባለሁ›› ብለዋል፡፡
እንዲሁም በክልሉ ውስጥ ለተፈፀሙት የሰብአዊ መብት ጥሰቶች በሙሉ በአስቸኳይ ገለልተኛ አለም አቀፍ ምርመራ ተደርጎ አጥፊዎች ተጠያቂ እንዲሆኑም አሳስበዋል፡፡ ዶ/ር ደሳለኝ በመልክእታቸው ማጠቃለያም ‹‹ዘላቂ ሰላም የሚያመጣው የአማራን ህዝብ ህጋዊ ጥያቄዎች እውቅና በመስጠት ተአማኒነት ያለው የፖለቲካ ውይይት ማድረግ ነው፡፡›› ያሉ ሲሆን የአማራ ህዝብ ሰላምና ደህንነት የማግኘት ህጋ መንግስታዊ መብት እንዳለውም ገልፀዋል፡፡
"በአማራ ህዝብ በተፈፀሙ የሰብአዊ መብት ጥሰቶች ላይ ገለልተኛ አለም አቀፍ ምርመራ ሊደረግ ይገባል" ሲሉ ዶ/ር ደሳለኝ ጫኔ አሳሰቡ፡፡ ዶ/ር ደሳለኝ ጫኔ በቢቢሲ የቀረበውን ዘገባ በተመለከተ በሰጡት አስተያየት ሪፖርቱን በአማራ ህዝብ ላይ በአሁኑ ወቅት እያጋጠመ ያለውን ከፍተኛ ስቃይ የሚያረጋግጥ መሆኑን ገልፀዋል፡፡
በአረመኒው አብይ አህመድ ጡት ቆራጮች ኃይሎችና በፋኖ መካከል ግጭቱ ከተከሰተ ወዲህ ይህ ቀውስ እየባሰበት መሄዱን የጠቀሱት ዶ/ር ደሳለኝ በሰላማዊ ሰዎች ሞት፣ ስቃይና መፈናቀል አገሪቱ እየተጎዳች መሆኑን አስረድተዋል፡፡ በተራዘመው የእርስ በእርስ ጦርነት ንፁሀን አማሮች የጅምላ ተጠቂ ሲሆኑ ዝም ብሎ መመልከት እንደማይገባ ያሳሰቡት ዶ/ር ደሳለኝ ጨምረውም ‹‹እንደህዝብ ተወካይነቴ ሁሉም ተፋላሚ አካላት በአስቸኳይ ግጭቱን እንዲያቆሙ ጥሪ አቀርባለሁ›› ብለዋል፡፡
እንዲሁም በክልሉ ውስጥ ለተፈፀሙት የሰብአዊ መብት ጥሰቶች በሙሉ በአስቸኳይ ገለልተኛ አለም አቀፍ ምርመራ ተደርጎ አጥፊዎች ተጠያቂ እንዲሆኑም አሳስበዋል፡፡ ዶ/ር ደሳለኝ በመልክእታቸው ማጠቃለያም ‹‹ዘላቂ ሰላም የሚያመጣው የአማራን ህዝብ ህጋዊ ጥያቄዎች እውቅና በመስጠት ተአማኒነት ያለው የፖለቲካ ውይይት ማድረግ ነው፡፡›› ያሉ ሲሆን የአማራ ህዝብ ሰላምና ደህንነት የማግኘት ህጋ መንግስታዊ መብት እንዳለውም ገልፀዋል፡፡
ሰበር ✊
ጀብደኛው ምኒልክ ዕዝ 💪
የምስራቅ አማራ ኮር 1 ኮር 2 እና የምኒልክ ዕዝ ልዩ ዘመቻ አሃዶች በጥምረት ባደረጉት ተጋድሎ ራያ ግንባር ላይ ትልቅ ድል አስመዘገቡ::
የፋሽስቱ አገዛዝ ብልፅግና ሰራዊት በራያ ቆቦ በጮቢ ግንባር እና ተኩለሽ ግንባር በበርካታ እግረኛ ሰራዊት በቅርቡ ባስገባቸው ቻይና ሰራሽ ኦራል ላይ በተጠመዱ ሶስት 155 mm መድፎች፣ ቢ ኤም፣ ብረት ለበሶች፣ እና ዙ23 ታግዞ ህዳር 9/2018 ዓ.ም ከቀኑ 9:00 ጀምሮ እስከ ህዳር 10/2018 ዓ.ም ምሽት በተጠናቀቀው ተጋድሎ ከባድ ሰብዓዊ ኪሳራ አስተናግዶ ወደ መጣበት ተመልሷል::
በተጋድሎው የምስራቅ አማራ ኮር 1 አሃዶች ሃውጃኖ ክፍለጦር አሳምነው ክፍለጦር 2ኛ እና 5ኛ ሻለቆች እና ከኮር 2 ዲቢና ወርቄ እንዲሁም የዕዙ ልዩ ዘመቻ በጥምረት ባደረጉት ብርቱ ትንቅንቅና ተጋድሎ ጠላት ላይ ከባድ ሰብዓዊ ኪሳራ በማድረስ እና ቀጠናውን በማስከበር ታላቅ ድል ተጎናፅፈዋል::
በተጋድሎው ከባድ ሽንፈት የገጠመው የፋሽስቱ አገዛዝ ሰራዊት የገጠር መንደሮችና ታዳጊ ከተሞች ላይ ከባድ መሳሪያ በማስወንጨፍ በሰው ህይወት ላይ የሞትና የአካል ማጉደል አደጋ ሲያደርስ ቁጥራቸው ቀላል የማይባል እንስሳቶች ተጨፍጨፈዋል ቤትና ንብረትም አውድሟል::
መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልውና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል!
ሕልውናችን በተባበረ ክንዳችን!
አፋብኃ ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ
ህዳር 12/2018 ዓ.ም
ሜጀር ጀነራል ውባንተ አባተ ተወርዋሪ ክፍለ ጦር Vs የአገዛዙ 303ኛ ኮር 77ኛ አራዊት ሰራዊት
ሕዳር 11/2018ዓ.ም ምሽት 03:45
የአቢይ አሕመድ የግል ወታደሮች ከወርሃ መሥከረም እሥከ ሕዳር 11/2018ዓ.ም የሜጀር ጀነራል ውባንተ አባተ ተወርዋሪ ክፍለ ጦርን በተለያዩ ወረዳዎች በተለያዬ ጊዜ ለማፈን ከቀን ደፈጣ እሥከ ሌሊት ደፈጣ፣ ከደፈጣ እሥከ መደበኛ ውጊያ ሙከራ አድርገዋል። ነገር ግን ጥበበኞቹ ውባንታዊያን ፍጹም ተዋጊነትን ከትግል አባታቸው በገቢር የተማሩ ናቸውና የወትሮ ዝግጁነታቸውን ምልዑ አድርገው የአቢይን ጦር ዕቅድ ቅዠት እያደረጉት ይገኛሉ። የጠላት ጦር ደፈጣንም ሆነ መደበኛ ውጊያን በተደጋጋሚ ሞክሮታል የጥቋቁር አናብሥቶቹ ውቤያዊያን ክንድ አሣፍሮ መለሰው እንጅ።
ከ03 ቀናት በፊት ሌሊት ከ250 በላይ የመከላከያ አባላትን የውባንተን ልጆች በደፈጣ ለመምታት ልኳል። ከ300 በላይ የሆነውን ኃይል ደግሞ የኋላ ደጀን አድርጎ ግንዳ ጠመም ላይ አሥቀምጧል። የሜጀር ጀነራል ውባንተ አባተ ተወርዋሪ ክፍለ ጦር ሠራዊት መረጃው ቀድሞ ሥለደረሰው 360° ከተማዋን ከብቦ አድሯል። እሥከ ቀኑ 8:00 ድረሥ ደፈጣ ያዝኩ ያለው የአቢይ ታጣቂ ልበላ ነው ድረሱልኝ ሲል ከላይ ለ303ኛ ኮር ከታች ደግሞ ከአንዳ ቤት እሥከ ግንዳ ጠመም የተሰማራውን የሆድ ዘመዱ መከን ድረሱልኝ አለ። በዚህን ጊዜ ዘረ ውባንተዎቹ ከላይም ቢመጣ ከታች እነሱ መተማመኛቸው የእርሥ በርሥ አንዳዊ የአምሐራነት ትሥሥራቸውና ፍጹም ተዋጊነታቸው ነው። ታዲያ ከበብኩ ያለውን የአቢይ ጦር ደረማምሰውት ሙሉ ከተማውን ተቆጣጥረው ጠላታቸውን ከብበውታል። ደፈጣን በደፈጣ ሳይሆን በመደበኛ አሰላለፍ ብን አደረጉት። ከአንዳ ቤት እሥከ ግንዳ ጠመም ያለው የጠላት ኃይል ደፈጣው በደፈጣ ለከሸበት ኃይል ለመድረሥ ሲሞክሩ ከላይ ከደብረ ታቦር ከተማ ደግሞ ሆድ አደሩና ወዶ ገቡ ፀዳሉ ደሴ በቁጥር 51 የሆድ ዘመዶቹን ወዶ ገቦች እና አማራ በታኞችን(አድማ ብተናዎችን) ይዞ ለመቀላቀል ሞከረ። በሥም መከ የተባለው ቡድን ሥሌት በውባንተ ልጆች የተባበረ አምሐራዊ ክንድ ሲከሽፍ በተመሣሣይ ወዶገቦቹ እነ ፀዳሉ ደሴና አማራ በታኞቹ በአንድ ሻምበል ውቤያዊያን ጦር ሳይዋጋ በሥነልቦና የበታችነት እና የመሸነፍ ብሎም የአልችላቸውም ሥሜት አምልጥ ወደ ደብረ ታቦር ብሏል። በተቃራኒው ዘረ ውባንተዎቹ የአቢይ አሕመድ የግል ቅጥረኞችን በፍጹም አምሐራዊ የማሸነፍ ሥሜት፣ የውጊያ ጥበብ እና በጥቅሉ የጠላትን አቅም በመረዳት ጠላትን ከቁሣዊ እሥከ አካላዊ፣ ከሞራል እሥከ ተቋማዊ ውድመትን እያደረሱበት ይገኛል። የውጊያ ሕግን ጥንቅቅ አድርገው የሚያውቁት ዘረ ውባንተዎች አሸናፊነታቸው በክቡር የነጻነት መሥዋዕትነታቸው ላይ የተመሰረተ ነው።
አምሐሮቹ የሜጀር ጀነራል ውባንተ አባተ ተወርዋሪ ክፍለ ጦር በድጋሜ ከሕዳር 10-11/2018ዓ.ም የመጣውን የአቢይ ታጣቂ በፍጹም ወትሮ ዝግጁነት በ04ቱም ወረዳዎች በንቃት በ340° በንቃት እኛ ዘረ ውባንተ ነን እያለው ይገኛል። ዘረ ውባንተዎቹ የአገዛዙ አራዊት ሰራዊትንም ሆነ ሆድ አደር ቁማርተኞችን ውሥጠ ሰረሰርጌ አካሄድ በንቃት ይከታተላሉ። ሁለገቦች ናቸው፤ በነፍጡም በጭንቅላታቸውም ጠቢባን ናቸው። የውባንተን ልጆች አይበገሬነት እንኳን ወዳጅ ጠላት ራሱ አስረግጦ ምሥክርነትን ይሰጣል። ይህ ተወርዋሪ ክፍለ ጦር መንፈስ ነው እንዴ እሥከማለት ደርሷል።
ይህ ክፍለ ጦር ለአምሐራ ሕዝብ የተሰጠ ዕንቁ ገጸ በረከት ነው። ሰራዊቱ የሚሞትለትንና የሚገድልበትን አላማ አውቆ የሚታገል፣ ከግዛት ዕሳቤ ርቆ አምሐራነት ዕሳቤ ላይ የተቀመጠ፣ ትግሉን በቀጠና ያልወሰነ፣ የነጻነትን ትርጓሜ የተረዳ፣ ለሆድ አደር አምሐሮች ምሕረት የሌለው፣ ለጀግኖች ክብር ያለው፣ የውሥጥና የውጭ ቁማሮችን የለዬ፣ ጀብደኝነታቸው አሥደማሚ፣ ከአባላት እሥከመሪዎቻቸው ፍጹም ተዋጊዎች፣ የግል ንዋያቸውን ለትግሉ የሚያውሉ፣ ብዙ ደሞቻቸውን ለትግሉ የገበሩ፣ ከሥጋ ዝምድና ይልቅ ለአላማ ዝምድና ሕግ የተገዙ፣ ቁጥርንና ፕሮፖጋንዳን የለዩ፣ ወቅታዊ የውሥጥም ሆነ የውጭ ፖለቲካዊ ምልከታን የሚረዱ፣ ተቋምን በደምብ የሚጠብቁና ለተቋማቸው ክብር ያላቸው፣ ለቃላቸው ባለማዕተቦች፣ ላመኑበት እሥከ ቀራኒዮ አደባባይ ተጓዦች፣ወገን መሳይ ጭምብል አጥላቂዎችንም ሆነ መደበኛ የፖለቲካ ቁማርተኞችን ፖለቲካዊ የመሬት መንቀጥቀጥ የሚፈጥሩባቸው፣ የፎቶ ፖለቲካን አምርረው የሚጸዬፉና አውርቶ አደሮችን በሚዛን የሚለዩ፣ ሥራ አሥፈጻሚዎቻቸው የመሪነት ሥነልቦናን የተላበሱ፣ የአሸር ጊንዝበርግ (አሐድ ሀአም)ን አካሔድ በነገደ አሠዘምሐራነት ላይ እየተገበሩ ያሉ፣ ትናንትን ከዛሬ አነጽረው ነገን የሚተነብዩና በጥቅሉ የሜጀር ጀነራል ውባንተ አባተን አላማ በደምብ እየተገበሩ ያሉ የአምሐራ ነጻነት አምዶች ናቸው።
በመጨረሻም አሁናዊው ሩቅ አላሚ ቅርብ አዳሪ ፋሽሥተ ናዚዝሙ የአቢይ አሕመድ አራዊት ሰራዊት በሜጀር ጀነራል ውባንተ አባተ ተወርዋሪ ክፍለ ጦር አይበገሬ ሰራዊት ተምበርክኮና አፍሮ እንደሚመለሥ በምልዑ ልባችን እንተማመናለን።
ዕውቀትን ለአዋቂው
ሱሪን ለታጣቂው
ክብርና ኩራት ነው
ባርነትን አሽቀንጥሮ ነጻነትን ጠባቂው ይባልላቸዋል ዘረ ውባንተዎቹ❗
ውቤያዊያን ትግላቸው በአምሐራነት እሥትንፋሥ የተመላ ነው።
ውባንተነት
አሸናፊነት✊
ኅልውናችን በተባበረ ክንዳችን🔐
ዝንተዓለም ዐምሐራ Forever AMHARA
Hakealew Alebachew
ቋሚ ምሥል፦
✅የሜጀር ጀነራል ውባንተ አባተ ተወርዋሪ ክፍለ ጦር ዋና ወታደራዊ አዛዥ አርበኛ ተመሥገን ውባንተ እና
✅የሜጀር ጀነራል ውባንተ አባተ ተወርዋሪ ክፍለ ጦር ምክትል ወታደራዊ አዛዥ አርበኛ ደርሶ ይሁኔ
ማዳጋስካር በውቅያኖስ የተከበበች ደሴት ናት። 360 ዲግሪ የሚለካ የባህር በር ያላት መሆኗ ለእድገቷ ዋስትና አልሆናትም። ስዊዘርላንድ የባህር በር የላትም። በዓመታዊ ጥቅል ምርት ወይም በነፍስ ወከፍ ገቢ አሊያም በህዝቧ የኑሮ ደረጃ ስትመዘን ካደጉት አገሮች ምድብ የምትገኝ ናት። የዘርፉ ምሁራን ወረቀቶች ዳሰሳ የባህር በር ለእድገት ዋስትናም ሆነ ቅድመ-ሁኔታ አለመሆኑን በተረጋገጠ አኳኃን ይነግሩናል። ኢትዮጵያ የዚህ ልዩ ሁኔታ የምትሆንበት ምክንያት የለም። የባህር በር ለኢትዮጵያ እድገት ቅድመ-ሁኔታ እና/ ወይም ዋስትና አይደለም። በተሟላ ችጋር ውስጥ የዘለቅነው፣ ወደ ቅርቃርም የገባነው የባህር በር ስላልኖረን አይደለም፤ የባህር በር ቢኖረንም ሁለንተናዊ እድገት የምናገኝ ስለመሆኑ ማረጋገጫ አይሆንም። ይህ ማለት ግን የባህር በር ለማናቸውም አገር እድገት ትርጉም ያለው አስተዋጽኦ የለውም ማለት ከቶ አይደለም። የባህር በር ለአንድ አገር እድገት ትርጉም ያለው አስተዋጽኦ ያለው በመሆኑ ላይ ልዩነት የለም። ይህ የኃለኛውም ድምዳሜ ለኢትዮጵያም እውነት ነው።
አገዛዙ የባህር በርን አስፈላጊነትና ጠቀሜታ እንዲሁም ለኢትዮጵያ እድገት የሚኖረውን ፋይዳ በሚመለከት በብዙ ማሳሳቻዎችና ማጭበርበሮች ሊፈጥረው የሞከረው ስምምነት የባህር በር ማምጣት <ሙዝ የመላጥ ያህል ቀላል ነው፤ የባህር በሩን ካገኘንበት ቀን ጀምሮም ኢትዮጵያ ልዕለ-ኃያልና የምድር ገነት ትሆናለች> የሚል ነው። ይህ እልም ያለ ውሸትና ዓይን ያወጣ ማጭበርበር ነው። የአራት ኪሎው የፖለቲካ አማተሮች የወደብን ጉዳይ እያቀነቀኑ ሊፈጥሩት የሞከሩት ህሊናዊ ሁኔታ ፈጽሞ እውን ሊሆን የማይችል ነው። ምክንያቱ ደግሞ ይህ ትውልድ ያ ትውልድ አይደለም፤ ይህን ትውልድ ማወቅ በሚመስል ልፈፋ፣ እውነት በሚመስል ኡኡታ ልታሳስተው አትችልም። መንግስት የመረጃ ሞኖፖሊውን ብቻ ሳይሆን የተረክ የበላይነቱን ከተቀማ ብዙ ዘመን ያለፈው ፣ የመረጃ አብዮት ፈንድቶ እልፍ አቅሞችን የፈጠረ ቢሆንም እነ አብይ አህመድ አሊ ገና ድሮ በጥራዝ ነጠቅነት በለቃቀሙት የእነ ማኪያቬሊ ምክሮች በእጅጉ የተለወጠውን ሁኔታ ለመምራት የሚዳክሩ ሆነዋል። በውጤቱም ሁኔታውን የሚከተሉ እንጅ ሁኔታ መምራት የማይችሉ ሆነው አንዱ ቀላል ችግር ሌሎች ውስብስብ ችግሮችን እየፈጠሩ የችግሮች ድር የተከመረባት አገር አድርገዋታል።
ይህ ትግል የግለሰብ ወይም የቡድን ወይም የኃይሎች ትግል አይደለም። ትግሉ የትውልድ ትግል ነው- የትግሉ አሳቢዎች፣ ተላሚዎች፣ ፈጻሚዎች እና ገምጋሚዎች የአዲሱ ትውልድ ዋኖች ናቸው። አዲስ ትውልድ፣ አዲስ አስተሳሰብ ፣ አዲስ ተስፋ ማለት የአንድ ግለሰብ ወይም የአንድ ቡድን ጥሪ አይደለም።በዚህ ልክ የሚባል የእድሜ ገደብም የለውም። መደመር እንደሚባለው መፈክር የጨበጣ ልፈፋ ሳይሆን የኢትዮጵያ ፖለቲካ የችግር ትንተና እና የመፍትሄ ትልም የታጨቀበት የዘመኑ ትውልድ ስምምነት ነው። መዋቅራዊና ስርዓታዊ ለሆነው የአማራ ህዝብ በደል፣ የህልውና አደጋ ውስጥ ገብቶ ለፈጽሞ መጥፋት የተዳረገ ህዝብ ልጆች መሰረታዊ እና ዘላቂ መፍትሄ ለማበጀት በተካሄደ ማማጥ የተገኘ የትውልዱ አዋጅ ነው። ይህ ትውልድ በከረሙ ስልቶች ልትሸውደው የማትችል ከመሆኑ እኩል የሚያውጀውን ትግልም የማትገዳደረው ብርቱ ነው። ይህ ብርታቱ የትግሉን የስር ምክንያቶች፣ ዓላማዎችና ግቦች በጥልቀትና በጥራት ከመገንዘቡ የተነሳ በያዘው የሞራል ልዕልና ምክንያትም ነው።
በከረመው ስሪት እና በአሁኑ አገዛዝ ላይ ያመጸው ትውልድ ከሌሎች አገራት አቻዎቹ የሚወስደው ትምህርትም የሚያቀብለው ቁም-ነገርም አለው። አገዛዝን የሚነቀንቁ እና የሚያስወግዱ የዚህ ትውልድ አመጾችን በብዙ መልክእ፣ በልዩ ልዩ አቅጣጫ፣ በመንታ ስልቶች የሚመራ እንጅ በነጠላ ጉዳይ እና በአንድ ዘንግ ብቻ የሚቆም አይደለም። የትጥቅ ትግል መሪዎች የህዝባዊ አመጽና ተቃውሞ ጥሪ ሲያደርጉ እንግዳ የሚሆነውም የትውልዱን የመግባባት ጥልቀት ካለማወቅ፣ የተለወጠውን ህሊናዊና ነባራዊ ሁኔታ ካለመገንዘብ እንዲያውም የትጥቅ ትግል እና የህዝባዊ አመጽ ትግል የሚጠፋፉ መሆናቸውን ከሚያምን የአስተሳሰብ ውቅር የሚመነጭ ነው።
የብሄር ማንነት እና ኢትዮጵያዊነት የሚጠፋፉ አስመስሎ የሚተነትንን ብሄርተኝነት ሲያቀነቅን የኖረ ሁሉ የትጥቅ ትግል እና የህዝባዊ እምቢተኝነት ትግል የሚሞላሉ ናቸው ሲባል ግራ መጋባቱ የማይጠበቅ አይደለም። ይህ ትውልድ የትግሉ ርዕዮተ-ዓለማዊ ቅኝት ብሄርተኝነት ሲሆን ብሄርተኝነቶቹ በአዎንታዊ የታሪክ ትንተና እና በበጎ የህዝቦች መስተጋብር እይታ ላይ የተመሰረተ ነው። ይህ የብሄርተኝነት ብያኔ <<እሳት እና ጭድ ናቸው>> የተባሉትን እና <<ቋሚ-ጠላቶች ናቸው>> የሚባሉትን የጸረ-አገዛዝ ትግሉን ልዩ ልዩ ኃይሎችና ህዝቦች ብቻ ሳይሆን የሚጠፋፉና አብረው የማይቆሙ ተደርገው የሚታዩትን የትግል ስልቶችም የሚያመጋግብበትን የትግል ቀመር አበጅቷል።
የማዳካስካር ወጣቶች ለባህር በር ሳይሆን ለነጻነትና ለዴሞክራሲ ወደ አደባባይ የወጡት የባህር በር ያላቸው በመሆናቸው ሳይሆን እጣ ፈንታቸውን የሚወስነው የመንግስታቸው ተፈጥሮ፣ የአስተዳደሩም ዘይቤ እነሱን የሚመስል ሲሆን ብቻ መሆኑን ስላወቁ ነው። በኢትዮጵያ ሁኔታም ከአገዛዝ ተላቅቆ በእኩልነት፣ በነጻነት፣ በአንድነት እና በፍትሃዊነት ላይ የተመሰረተ የህዝቦችን ህልውና፣ መብቶች እና ጥቅሞች የሚያከብርና የሚያስከብር ስርዓትና መዋቅር መፍጠር እና መገንባት ለእድገት ቅድመ-ሁኔታ እና ዋስትናም ነው። ገዥ ስልት ሆኖ እየተተገበረ ግዙፍ ድሎችን እያስመዘገበ ባለው የትጥቅ ትግል ማዕቀፍ የሚመራ የህዝባዊ አመጽና ተቃውሞ አስፈላጊና ተገቢ ነው።
***
1. የዘርፉ ተንታኞች እና ምሁራን የዛሬውን ትውልድ የሰላማዊ አመጽና ተቃውሞ የትውልድ ዜድ አብዮት(GEN Z REVOLUTIONS) እያሉ የሚጠሩት ነው።
ሀጅ ሁሴን ሀሰን
ህዳር 11/2018 ዓ.ም
