ru
Feedback
ፍኖተ- አማራ ሚዲያ (Finote- Amhara ) Midea

ፍኖተ- አማራ ሚዲያ (Finote- Amhara ) Midea

Открыть в Telegram

የተመሠረተው የአማራን ሕዝብ ለማንቃት፣ ለማደራጀት እና ለማስተባበር ነው። የአማራ ሕዝብን ✅ ፖለቲካዊ ✅ ማህበራዊ ✅ ኢኮኖሚያዊ ታሪካዊ ጥያቄዎችን ለማሰማት እና የአማራን ሕዝብ በማንቃት ሰፊውን ሕዝብ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ይሰራል። ወደዱም ጠሉም የኃላ ታሪካችን በእኛ እጅ ይፃፋል። አማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ ( አፋብን)

Больше
3 712
Подписчики
+2624 часа
+3797 дней
+1 10930 дней
Архив постов
Amhara Fano National Movement: ኑ ጠላትን በጋራ ታግለን የአማራን ህዝብ ሕልውና እናረጋግጥ! የካቲት 05 ቀን 2018 ዓ.ም ከአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ የተላለፈ የምህረት አዋጅ ሀ) መግቢያ: አረመኔው የብልፅግና አገዛዝ የአማራን ህዝብ ህልውና አደጋ ላይ ለመጣል የጀመረውን ጦርነት ለማሳካት ይችል ዘንድ በርካታ አረመኔያዊ ተግባራትን ሲፈፅም መቆየቱ ይታወቃል። የአማራን ህዝብ ያለ ልዩነት ለመፍጀት አቅሙ የፈቀደውን ሁሉ እየተጠቀመ ያለው አገዛዝ የመካከለኛው ምስራቅ ሀገራት ጂኦ ፖለቲካዊ እና ኢኮኖሚያዊ ፍላጎቶችን በማገልገል በፈጠረው የማውደም አቅም ተማምኖ በከፈተው ጦርነት ራሱ እየተለበለበበት ይገኛል። የአማራን ህዝብ ለማጥፋት ከሚጠቀምባቸው ስልቶች መካከል ነባሩን የብአዴን መዋቅር በመጠቀም ባሰባሰበው የምሊሻ እና የአድማ ብተና ኃይል ከፋኖ ጋር እንዲዋጋ እና ህዝባችን በሁለት ጎራ ተሰልፎ እንዲጠፋፋ የሞከረበት መንገድ አንደኛው ነው። በአንድ ህዝብ መካከል እና በኢትዮጵያዊያን መካከል እንዲሁም ቀጠናዊ ጦርነቶችን በማስነሳት ለአፍሪካ ቀንድ የቀውስ ዘበኛ የሆነውን አገዛዝ በወንድማማችነት እና በጥበብ በማስወገድ የጋራ መንግስት መመስረት እንደሚገባን በተደጋጋሚ ጥሪወች ስናስተላልፍ የቆዬን መሆኑ ይታወቃል። በተለይም ከሰሞኑ ደግሞ ጠላት በአንድ በኩል የህዝብ መገናኛ መስመሮችን በመዝጋት ንፁሃን ላይ ጭፍጨፋ እያደረገ በሌላ በኩል ደግሞ ብሔራዊ አጀንዳ ያለው እና ለሀገር ብሔራዊ ተልዕኮ የተሰለፈ በመምሰል የሚያደርገውን የማደናገሪያ ስልት በንቃት በመከታተል የፋኖ ሰራዊት በወሰዳቸው እርምጃወች ወራሪው የብልፅግና ኃይል ከፍተኛ ትርምስ ውስጥ ገብቷል። የድርጅታችን የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ መወለድ ያስገኘው የአንድነት መንፈስ ለተገኙ ወታደራዊ ድሎች ቁልፍ ሚና ተጫውቷል። የድላችን ምስጢር ያለው አንድነታችን ላይ መሆኑም በተግባር ተረጋግጧል። ድርጅታዊ አንድነታችንን በጠበቀ መልኩ ከኢትዮጵያዊያን እና ከቀጠናው ኃይሎች ጋር የሚደረግ ትብብር አገዛዙን ሙሉ በሙሉ ለማስወገድ ወሳኝ ሂደት መሆኑ ግልፅ ነው። ህዝባዊ ዓላማችንን የተጋራን ጋር በመርህ የምናደርገው ትብብር እና አንድነት የአረመኔውን አገዛዝ እድሜ ለማሳጠር ትልቅ ፋይዳ ያለው ጉዳይ ነው። ይህንን ተከትሎ ባቀረብነው ወገናዊ ጥሪ በርካታ የአገዛዙ አገልጋይ የነበረ ምሊሻ፣ አድማ ብተና እና የመከላከያ ኃይል የወገንን ኃይል እየተቀላቀለ ይገኛል። ስለሆነም ዛሬም አገዛዙን በማገልገል ላይ ለምትገኙ የምሊሻ፣ የአድማ ብተና፣ የመደበኛ ፖሊስ፣ መከላከያ እና በሌሎች የአገዛዙ ታጣቂ አደረጃጀቶች ውስጥ ላላችሁ ተመሳሳይ ጥሪወችን እናስተላልፋለን። ይህንን  ጥሪ ያስተላለፈው የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ ስራ አመራር በጉዳዩ ላይ በዝርዝር ተወያይቶ ጥሪዉን በመቀበል ወገናቸውን ለመካስ ለሚፈልጉ የአገዛዙ ሰራዊት አባላት እና የካድሬ መዋቅር የምህረት አዋጅ አውጇል። ለ) የምህረት አዋጁ የተላለፈላቸው የአገዛዙ መዋቅር አካላት:- ፩) በየደረጃው የሚገኙ የብልፅግና አመራር አባላት ፪) ምሊሻ፣ ሰላም አስከባሪ እና በሌላም ስያሜ ብልፅግና ያደራጃቸው ታጣቂወች ፫) የክልል አድማ ብተና እና መደበኛ ፖሊስ አባላት ፬) በሀገር መከላከያ ሰራዊት ስም በየቀጠናው የተሰማሩ እግረኞች እና የአገዛዙ መኮንኖች ሐ) የምህረት አዋጁን ማውጣት ያስፈለገበት ምክንያት ሶስት ዓመታትን ሊደፍን ጥቂት ጊዜ በቀረው የጦርነት ሂደት በግልፅ መገንዘብ እንደሚቻለው የብልፅግና መዋቅር በአማራ ህዝብ ማህበራዊ እና ፖለቲካዊ ድቀት ላይ ስልጣኑን ከማራዘም ያለፈ ለአማራ ህዝብ የሚጠቅም አንድም አጀንዳ የሌለው በመሆኑ የአማራ ህዝብ እንደ ህዝብ በተለያዬ ጎራ የተሰለፍን የአማራ ልጆችም እንደ የአንድ እናት ልጆች በመቀናጀት የህዝባችንን ህልዉና ማስጠበቅ ከእኛ የሚጠበቅ ተግባር ነው።  በመሆኑም:- ፩) ለአማራ ህዝብ ሁለንተናዊ መብት እና ነፃነት እንጅ ለአብይ አህመድ ወንበር መፅናት የሚወድቅ የአማራ ወጣት መኖር ስለሌለበት፤ ፪) ህዝባችንን በጅምላ ለሚጨፈጭፍ አገዛዝ በማገልገል የዘቀጠ ታሪክ ውስጥ ራስን ከማግኘት ይልቅ ለነፃነቱ የሚዋደቅን ኃይል በመቀላቀል ደማቅ ታሪክ መፃፍ ታሪክ የጣለብን ግዴታ በመሆኑ፤ ፫) ህዝብን ታግሎ ያሸነፈ አገዛዝ እንደሌለው ሁሉ አብይ አህመድም የአማራን ህዝብ ማሸነፍ ስለማይችል እና በተሸናፊነት ለሚያጠናቅቀው ብልፅግና በመላላክ እና በራስ ወገን ላይ በመተኮስ የታሪክ፣ የህሊና እና የፍትህ ተጠያቂነትን ከማስተናገድ ለመዳን ሲባል፤ ፬) አገዛዙን በጋራ ታግለን በማሸነፍ ለህዝባችን ሰላም ማምጣት የትውልዱ ግዴታ በመሆኑ፤ ፭) እንዲሁም የምንታገለው ለአማራ ህዝብ ህልውናና መዳን እንደመሆኑ መጠን የፋኖ ትግልም የአማራ ህዝብ ትግል ስለሆነ በሁሉም ጎራ ላሉ አማራዊ ወንድሞች ጥሪ ማድረግ እና ማታገል የድርጅታችን ተልዕኮ በመሆኑ፤ ይህንን የምህረት አዋጅ በአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ ስራ አመራር ውሳኔ መሰረት ለህዝብ ይፋ ማድረግ አስፈላጊ ሆኖ ተገኝቷል። መ) የምህረት አዋጁ አተገባበር ፩) የምህረት አዋጁ ተጠቃሚ እንዲሆኑ ካላይ በተራ ቁጥር "ለ" ስር የተዘረዘሩት የምሊሻ፣ አድማ ብተና፣ መከላከያ እና ሌሎች የታጠቁ የብልፅግና ኃይሎች እንዲሁም በየደረጃው ያሉ አመራሮች በየአካባቢያቸው ላለው የድርጅታችን መዋቅር እና ለዚህ ጉዳይ በተቋቋመው ግዜያዊ ግብረ ኃይል በአካል ቀርበው ሪፖርት ያደርጋሉ። ፪) ምህረት ጠይቀው ወገናቸውን ለመካስ የሚመጡ ግለሰቦች የአካል ደህንነት ዋስትና ይሰጣቸዋል። በተዘጋጀላቸው ማረፊያ የተሃድሶ ስልጠና እንዲወስዱ ይደረጋል። ፫) ለትግል አገልግሎት ከሚዉል የጦር መሳሪያን ጨምሮ ማንኛውም የምህረት ጠያቂወች ንብረት በባለቤቶች እጅ ይቆያል። ፬) ምህረት የተደረገላቸው ግለሰቦች ድርጅቱ ባዘጋጀው ፎርም መሠረት ለአማራ ህዝብ ነፃነት ሊሰሩ ካልተቻለም ከጠላት ወገን ላይሰለፉ ቃለ-መሃላ ይፈፅማሉ። ፭) አቅሙ እና ፍላጎቱ ያላቸው የምህረት ተጠቃሚወች የወገንን ወታደራዊ እና ፖለቲካዊ መዋቅር ተቀላቅለው ለህልዉና ተጋድሎው የበኩላቸውን ድርሻ ይወጡ ዘንድ በሌላ ማናቸውም ለህዝብ ጠቃሚ በሚሆኑ ተልዕኮወች ላይ ይሰማሩ ዘንድ ድርጅቱ ሁኔታወችን ያመቻቻል። ፮) ይህ የምህረት አዋጅ ከዛሬ የካቲት 04 ቀ 2018 ዓ.ም ላሉት ተከታታይ 15(አስራ አምስት ቀናት) ብቻ ተፈፃሚ ይሆናል። ሠ) የምህረት አዋጁን በማስፈፀም የሰራዊታችን እና የድርጅታችን አመራር ግዴታ ፩) የምህረት አዋጁን አፈፃፀም ለመከታተል በማዕከል የተቋቋመው ግብረ ኃይል የመመሪያዉን አተገባበር ይከታተላል፤ መረጃወችን ይሰጣል፤ መፍትሔ ያስቀምጣል። ፪) የድርጅቱ መዋቅር አመራር እና ሰራዊቱ ለምህረት ጠያቂወቹ የአካል ዋስትና መስጠትን ጨምሮ በእንክብካቤ በማስተናገድ በፍፁም ጨዋነት አዋጁን ይተገብራል። ፫)በአፈፃፀም ሂደት የሚያጋጥሙ ችግሮችን ወዲያውኑ ለግብረኃይይሉ ያሳውቃል፣ የተሰጠዉን የመፍትሔ አቅጣጫ ይተገብራል። ፬ በግል ቂም ቁርሾ ወይም በሌላ ግላዊ እና ቡድናዊ ፍላጎቶች ምክንያት ከዚህ አዋጅ በተቃረነ መንገድ በማንኛውም ምህረት ጠያቂ ላይ አካላዊ እና ስነ ልቦናዊ ጉዳት ማድረስ ወይም ንብረት መቀማት ፍፁም የተከለከለ ተግባር ነው።

109ኛ ኮር 77ኛ ክፍለ ጦር በርካታ ጠላት በመደምሰስ ታላቅ ጀብድ ሰራ አፍብን ምዕራብ አማራ ቀጠና ቴወድሮስ ዕዝ 109ኛ ኮር 77ኛ ክ/ጦር የተቀበለውን ግዳጂ ለማክሸፍ ጠላት ለብዙ ቀናት ያደረገው
109ኛ ኮር 77ኛ ክፍለ ጦር በርካታ ጠላት በመደምሰስ ታላቅ ጀብድ ሰራ አፍብን ምዕራብ አማራ ቀጠና ቴወድሮስ ዕዝ 109ኛ ኮር 77ኛ ክ/ጦር የተቀበለውን ግዳጂ ለማክሸፍ ጠላት ለብዙ ቀናት ያደረገውን ከበባ ከአጋር ሀይሎች ጋር በመሆን የጠላትን እቅድ አከክሺፈውታል፡፡ በአገዛዙ ሰራዊት ላይ ከፍተኛ ሰብዓዊ እና ቁሳዊ ጉዳት በማድረስ ታላቅ ድል አስመዝግበዋል:: ጀግናውና አይበገሬው 77ኛ ክ/ጦር ከአጋር ሀይሎች ጋር በመሆን ረጅም ጉዞ በመጓዝ ወደ ጠላት ምሽግ ሰርገው በመግባት የጥይት ናዳ አውርደውበታል በዚህም አስራ አምስት(15)ሙት ሲሆን ከሀያ(20) በላይ ቁስለኛ ሆኗል፡፡ በዚህ የተናደደው የፋሽስቱ አገዛዝ ሰራዊት የመጨረሻው አማራጩን ኔትወረክ በመዝጋት አምልጧል፡፡ መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልውና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል፡፡ አዲስ ትውልድ፣ አዲስ አስተሳሰብ ፣አዲስ ተስፋ! ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን ! አፋብን| ቴወድሮስ ዕዝ 77ተኛ ክፍለጦር ሕዝብ ግንኙነት መምሪያ የካቲት 05/6/2018 ዓ.ም

በኦሮሚያ ክልል በተካሄደ የአመራሮች ስብሰባ ላይ የክልሉ ፕሬዘዳንት አቶ ሽመልስ አብዲሳ የሚከተለውን ሀሳብ አጋርተው ነበር፦ ​ ከዓመታት በፊት ከአማራ ልዩ ኃይል ጋር በመሆን ሕወሓትን መትተን ከሰበ
በኦሮሚያ ክልል በተካሄደ የአመራሮች ስብሰባ ላይ የክልሉ ፕሬዘዳንት አቶ ሽመልስ አብዲሳ የሚከተለውን ሀሳብ አጋርተው ነበር፦ ​ ከዓመታት በፊት ከአማራ ልዩ ኃይል ጋር በመሆን ሕወሓትን መትተን ከሰበርን በኋላ፣የአማራ ልዩ ኃይሉ እንዲፈርስ አድርገናል። አሁንም በአማራ ክልል እየሰለጠነ ያለውን የአድማ ብተና ኃይልና ሚሊሻ፣ ፋኖን ከወጋን በኋላ ወይ ማፍረስ ወይም በሴራ መምታት ይኖርብናል። ያ ካልሆነ ነገ አፈሙዙን ወደ እኛ ሊያዞር ስለሚችል 'Plan B' ሊኖረን ይገባል ። ​ሊታሰብባቸው የሚገቡ ነጥቦች ለቆሙለት ዓላማ ውድ መስዋዕትነት ለከፈለው ያላዘነው የአማራ ልዩ ኃይል ፣ ዛሬ ላለው የአድማ ብተና እና ሚሊሻ አባላት ቅንጣት ታክል ርህራሄ አይኖራቸውም። እንዲሁም የአማራን ህዝብ እርስ በእርስ እንዲባላ በማድርግ ሰፊ ሰራ መስራት አለብን የሚል ጠጠር ያለ ኃሳብ አንስቷል ​አሁን ላይ የአማራ ፋኖ እንቅስቃሴ የክልሉ የጸጥታ መዋቅር እንደ ስጋት እንጂ እንደ አጋር እንደማይታይ ነው።በመጨረሻም ​ጊዜው ሳይረፍድ በአድማ ብተና እና በሚሊሻ ውስጥ የምትገኙ ወንድሞችና አባቶች፣ ሁኔታዎችን በንቃት እንድትከታተሉ ይገባል። እያንዳንዱ አማራ በተገኘው አጋጣሚ እነዚህ የጸጥታ አካላት ከአረመኔው አብይ አህመድ መዋቅር እንዲወጡና ከህዝባቸው (ከፋኖ) ጎን እንዲቆሙ ሊመክራቸው ይገባል።

አስቸኳይ መረጃ በርካታ መኪና ከመኮድ የተነሳ ሀይል አሁን ወደ ጎንደር እየወጣ ነው ደፈጣ አዛምቱ

አሁን ህወሓት ሆነች ሻእቢያ የሚሸዉደዉ የሚያባብለዉ አማራ የለም። አሁን 1966 ወይም 1983 አሊያም 1997 ወይም 2010 የሿሿ ዘበን አዶለም። አሁን 80 ሚሊዮን አማራ ዉለታ በሰራላት ሀገር የተ
አሁን ህወሓት ሆነች ሻእቢያ የሚሸዉደዉ የሚያባብለዉ አማራ የለም። አሁን 1966 ወይም 1983 አሊያም 1997 ወይም 2010 የሿሿ ዘበን አዶለም። አሁን 80 ሚሊዮን አማራ ዉለታ በሰራላት ሀገር የተገፋበት ትርክቶቹን የገመገመበት፣ ጠላቶቹን የለየበት፣ ክፉና ደጉን ያወቀበት ጥቃት መካች ልጅቹ ከአፍ እስከ አፍንጫው ድረስ የታጠቁበት ዘመን ላይ ነዉ። ቴግባባን ኧደል? ዠለስካ፥ እንዴዣ ነገር ኖ። አማራ ገስግስ ወደፊት!

የአፋብን፣ ቴዲ ዕዝ፣ 102ኛው ኮር ውሎ፦ ቀን፦ የካቲት 04/2018 ዓ.ም በአማራ ፋኖ ብሄራዊ ንቅናቄ (አፋብን) በምዕራብ አማራ ቀጠና ስር የሚንቀሳቀሰው የቴዎድሮስ ዕዝ፣ 102ኛው ኮር ከፍተኛ ድል እያስመዘገበ ይገኛል። የኮሩ ስብጥርና የክዋኔ ቀጠና 102ኛው ኮር የሚሸፍናቸው፦ • ወረዳዎች፦ ቋሪት፣ ጎንጅ ቆለላ፣ ይልማና ዴንሳ (አዴት)፣ ሜጫ( መርሐዊ) እና ባህርዳር ዙሪያ። • የተካተቱ ብርጌዶች፦ የገረመው ወንዳውክ (የቋሪቱ) ፣ የአርበኛ ዮሐንስ አለማየሁ(የጎንጅ ቆለላ)፣ የሻለቃ አንሙት ያዛቸው( ይልማና ዴንሳ)፣ የኮለኔል ታደሰ ሙሉነህ ( መርሐዊ)፣ የጣናው መብረቅ እና የባህርዳር ብርጌድ (ባህርዳርና ዙሪያው)። የተመዘገቡ ስኬቶች ኮሩ የአደረጃጀት ስራውን አጠናቆ ለከፍተኛ መልሶ ማጥቃት ራሱን እያዘጋጀ ባለበት በዚህ ወቅት፣ ተከታታይ ጥቃቶችን በመሰንዘር የሚከተሉትን ቀጠናዎች ከጠላት ነፃ አድርጓል፦ 1. ከአዴት ቀጠና (11ኛ ክፍለ ጦር)፦ ዴንሳ ባታን። 2. ከባህርዳር ቀጠና (22ኛ ክፍለ ጦር)፦ ደና ማርያም፣ ጭስ አባይ እና ጎንባትን። የጠላት ወቅታዊ ሁኔታ፦ በኮሩ ወታደራዊ የበላይነት የተደናገጠው የገዥው ስርዓት ሰራዊት የሚከተሉት ምልክቶች እየታዩበት ይገኛል፦ • መፈራረስና መሸሽ፦ በየካምፑ ያሉ የጠላት ኃይሎች ከፍተኛ መዋከብ ላይ ሲሆኑ፣ በባንክ ያሉ ጥሬ ገንዘቦችን በመሸከፍና ጓዛቸውን በመኪና በመጫን ለመሸሽ እየተዘጋጁ መሆናቸው ተረጋግጧል። • ክህደትና ተሳትፎ፦ የሰራዊቱን መዳከም የተረዱ በርካታ የአድማ ብተና እና የሚሊሻ አባላት ስርዓቱን በመክዳት ፋኖን እየተቀላቀሉ ይገኛሉ። • ተጨማሪ ትጥቅ፦ በዛሬው ዕለት ብቻ በርካታ የቡድንና የነፍስ ወከፍ መሣሪያ የታጠቁ ኃይሎች የትግሉ አካል ለመሆን 102ኛውን ኮር ተቀላቅለዋል። መረጃው፦ የወንድም ታደሰ ነው።

የአፋብን ሊቀመንበር አርበኛ ዘመነ ካሴ በጎንደር አማራ ቀጠና ኮማንድ ካሉ አመራሮች እና ነበልባል ተዋጊዎች ጋር። ዝርዝሩን ወደኋላ አቆይተን መሪያቸውን እንዴት በስስት እንደሚያዩት ይገርማል። ስሜቱ,
የአፋብን ሊቀመንበር አርበኛ ዘመነ ካሴ በጎንደር አማራ ቀጠና ኮማንድ ካሉ አመራሮች እና ነበልባል ተዋጊዎች ጋር። ዝርዝሩን ወደኋላ አቆይተን መሪያቸውን እንዴት በስስት እንደሚያዩት ይገርማል። ስሜቱ,,,,,,አንድ ህጻን ልጅ ከአባቱ ትክሻ ላይ ተቀምጦ መውደቅ እንደማይችል፣ለመውደቅ ቢሞክርም አባቱ እንደሚያተርፈው አይነት ነው። በአባቶቻችን ትክሻ ላይ ስንሆን የሚሰማን በራስመተማመን ልዩ ነው። እነዚህ ጀግኖችም እንደዛ ናቸው።

የአፋብን ሊቀመንበር አርበኛ ዘመነ ካሴ በጎንደር አማራ ቀጠና ኮማንድ ካሉ አመራሮች እና ነበልባል ተዋጊዎች ጋር 💪💪
የአፋብን ሊቀመንበር አርበኛ ዘመነ ካሴ በጎንደር አማራ ቀጠና ኮማንድ ካሉ አመራሮች እና ነበልባል ተዋጊዎች ጋር 💪💪

ያልተነገረለት የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ ደቡብ አማራ ቀጠና አሳምነው ዕዝ ዓፄ ዘርዓ ያዕቆብ ፩ ኮር የሰባት ለሰባ ክፍለ ጦር ዲሽቃ ተኳሹ የድርጅት ጉዳይ ኃላፊው እሸቱ በቀለ አርበኛ "እሸቱ በቀለ በሸዋ ደቡብ አማራ ኤፍራታ አማራ ፋኖ ውስጥ በጀግንነቱና በልዩ የዲሽቃ ተኩስ ብቃቱ  በተለይም በቅርብ ጊዜያት በነበሩት ውጊያዎች ላይ ያሳየው ፅናትና የጦር ሜዳ ብቃት በብዙዎች ዘንድ አድናቆትን አትርፎለታል። ​አርበኛ እሸቱ በቀለ የጀግንነቱ መገለጫ አርበኛው ተራ ተዋጊ ብቻ ሳይሆን፣ የከባድ መሳሪያ (ዲሽቃ) አጠቃቀም ላይ ልዩ ጥበብ ያለው አርበኛ ነው። አብዛኛውን ጊዜ ዲሽቃን እንደ ቀላል መሳሪያ ተሸክሞ፣ ጠላትን ፊት ለፊት በመጋፈጥ ይታወቃል። የእሱ ልዩ የሚያደርገው  ​የልብ ትርታ በከባድ ጥይት ዝናብ ውስጥ ሳይበገር መቆሙ። ​ትክክለኛ ኢላማ የዲሽቃ ጥይትን በቁጥብነትና በትክክለኛ ኢላማ ላይ የማሳረፍ ችሎታው ነው። ​ ለጓደኞቹ ያለውን የውጊያ ወኔ የመቀስቀስ አቅሙ እና የውጊያ ውሎ የሽዋ ተራራማና ገደላማ ስፍራዎች በከባድ መሳሪያ ታጅቦ ከሚወዳቸው ፋኖዎች ጋር ሆኖ የጠላትን እንቅስቃሴ አልሞ የመምታት እይታው አጅጉን ማራኪም ነው። አርበኛ እሸቱ በቀለ በአንድ ስትራቴጂካዊ ቦታ ላይ አደላድሎ ይይዛል። የጠላት ጦር መስመር ሰብሮ ለመግባት ሲሞክር፣ እሸቱ "ቁጭ ብሎ" ሳይሆን በቆራጥነት መሳሪያውን በማንቀሳቀስ ተኩስ ይከፍታል። የዲሽቃው ድምፅ ብቻ የጠላትን ስነ-ልቦና ይሰብራል። አርበኛ እሸቱ የዲሽቃ ጥይት የሚተኩሰው በዘፈቀደ ሳይሆን፣ የጠላትን አሰላለፍ እየመረጠ በመምታት ግስጋሴያቸውን እንዲገታ ያደርጋል። ​መስዋዕትነትና ፅናት ብዙ ጊዜ በቪዲዮዎች ላይ እንደሚታየው፣ ዙሪያውን ጥይት እየዘነበ እሱ ግን በእርጋታና በፈገግታ የታጀበ የጀግንነት ተግባር ሲፈፅም ይታያል። ይህ ለደጋፊዎቹ "የማይበገሩት ጀግኖች" ተምሳሌት አድርጎታል ተምሳሌታዊነቱ ​እሸቱ በቀለ ዛሬ ላይ ለአማራ ፋኖ ትግል የፅናት ምልክት ሆኗል።ጀግንነቱ  የጥንካሬው መገለጫ ተደርጎ ይወሰዳል። የጀግናው ውሎ በየጊዜው በሚለቀቁ የመረጃ አውታሮች ላይ የሚዘገብ ሲሆን፣ የእሱ ተጋድሎ በታሪክ ድርሳናት ውስጥ የአማራን ህዝብ የመኖር ህልውና ለማስከበር ትልቅ ተጋድሎ እያደርገ ይገኛል።

~ ቁስለኛ #በሄሊኮፕተር ተነሳ !!! በዛሬዉ እለት በቀን 04/06/2018 ዓ.ም ጃዊ ላይ የአብይ አህመድ ቅጥረኛ ገረድ ሰራዊት ቁስለኛ አመራሮች በሂሊኮፕተር ተለቅመዋል። ለ8 ተከታታይ ቀናት በጀግኖች የአማራ ፋኖ ብርቱ ክንድ የተወቃዉ የአብይ ወንበር አስጠባቂ ሰራዊት አመራሮች ለጊዜዉ ከሞት የተረፉት ቁስለኞች መዉጫ አጥተዉ ዛሬ በሂሊኮፕተር ተነስተዋል። አዲስ ትዉልድ፣አዲስ አስተሳሰብ፣አዲስ ተስፋ!!! የአፋብን ቴዎድሮስ ዕዝ 105ኛ ኮር 66ኛ ክ/ጦር ህ/ግንኙነት

የጥንቃቄና ጥብቅ መረጃ! የብልጽግና አመራሮችና ጀሌ ሰራዊታቸው በፋኖ ጠንካራ ጡንቻ ቀምሰው የተለያዩ ከተሞችን ለቀው ሲፈረጥጡ ትምህርት ቤት፣ ጤና ጣቢያ እና መሰል የሕዝብ ተቋማትን በማቃጠል ፋኖ እ
የጥንቃቄና ጥብቅ መረጃ! የብልጽግና አመራሮችና ጀሌ ሰራዊታቸው በፋኖ ጠንካራ ጡንቻ ቀምሰው የተለያዩ ከተሞችን ለቀው ሲፈረጥጡ ትምህርት ቤት፣ ጤና ጣቢያ እና መሰል የሕዝብ ተቋማትን በማቃጠል ፋኖ እንዳቃጠለው አድርገው ፕሮፓጋንዳ ለመስራት እየተንቀሳቀሱ ነው፣ አሁንም እያደረጉት ነው። ስለሆነም የሕዝብ ልጅ የሆነው ፋኖም ሆነ ጋሻ መከታ የሆነው ሕዝባችን ተቋማትን እንዲጠብቅ ማሳሰብና ማስታወስ እንፈልጋለን። አፋብን ዮሃንስ ሙጨ

የምሽት ዜና! የአዋባል ወረዳ ስልጠናና ክህሎት ም/ኃላፊ አዲሱ አለምነህ በተገደለበት ውሎ 206ኛ ኮር 34ኛ ክ/ጦር ማምሻውን ድል ተቀናጅቷል። የካቲት 4/2018ዓ.ም =================================== በሉማሜ ከተማ ከሌሊቱ 6:00 ሰዓት በተፈፀመ ድንገተኛ መብረቃዊ ጥቃት የአዋባል ወረዳ ስልጠናና ክህሎት ምክት ኃላፊ የነበረው አዲሱ አለምነህ በ206ኛ ኮር 34ኛ ክ/ጦር በተወሰደበት እርምጃ በመኖሪያ ቤቱ ተገድሏል። ድንገተኝነትን በማሳካ በጨላማ ካድሪውን በቦምብ ያጋዩት 34ኛ ክ/ጦር ከቀኑ 9:00 እስከ 12:00 ሰዓት በጃማ ከተማ በአደረጉት እልህ አስጨራሽ ትንቅንቅ የአረመኔውን ሰራዊት ደባቅ በመምታት 12 ከባድ ቁስለኛ ከ25 በላይ አስክሬን ለጠላት አሸክመውታል። ከደብረ ማርቆስ ደጀን ባለው አውራ ጎዳና መሐል በምትገኘው ስትራቴጂካዊ ከተማ በሆነችው ሉማሜ ከተማ በሌሊት አስደናቂ ኦፕሬሽን የፈፀሙት የ34ኛ ክ/ጦር ነበልባሎች በድጋሚ ከምሽቱ 12:00 ሰዓት በሉማሜ ከተማ በመሸገው ጠላት ላይ በከፈቱት አውደ ውጊያ እስከ ምሽቱ 2:00 ሰዓት ተፋልመው ጠላትን አነባብረው ወጠዋል። በሉማሜ ሚካኤል ቤተክርስቲያን አቅራቢያ በተደረገው ውጊያ በርካታ ጠላት የተደመሰሰ ሲሆን የአረመኔው ሰራዊት የከተማዋን ወጣቶች እያፈሰ ይገኛል። በዛሬው እልህ አስጨራሽ የጨበጣ ውጊያ 206ኛ ኮር 34ኛ ክ/ጦር ድል የተቀናጀ ሲሆን የኮሩ አሀዶች በጃዊ መተከል በተደረገ ትንቅንቅም እየተፋለሙ ይገኛሉ። አዲስ ትውልድ! አዲስ አስተሳሰብ! አዲስ ተስፋ! የአፋብን ቴዎድሮስ ዕዝ 206ኛ ኮር ህዝብ ግንኙነት

ጀምበር የጠለቀችበትና ጣዕረ ሞት ላይ ያለው ብልፅግና የመጨረሻ ያለውን እርምጃ እየወሰደ ንፁሃንን እየጨፈጨፈ ንብረትም እያወደመ ነው‼️ ሽንፈቱን በተግባር የተረዳው ተረኛ ስብስብ እኔ ከሞትኩ ሰርዶ አይብቀል ነውና የቻልኩትንና ያገኘሁትን የአማራ እና አማራ አጥፍቸ ነው በማለት ሲጠፋ አመታቶች አስቆጥሯል።ዛሬ ግብዓተ መሬቱ ሲቃረብ ደግሞ በክፋትላይ ክፋት በጭካኔ ላይ አረመኔዊነቱን በንፁሀን ላይ እያሳየን ይገኛል።በዛሬው እለት ደቡብ ወሎ ወረኢሉ ወረዳ ላይ የሶስት አርሶ አደሮች ቤት ከነሙሉ ንብረቱ ቤንዚን አርከፍክፎ ያቃጠለ ሲሆን ቤት ንብረታቸው የተቃጠለባቸው አርሶደሮች ፦ 1. አቶ አያሌው አህመድ ሁለት ቆርቆሮ ቤት 2. አቶ አሊ ይማም ሶስት ቆርቆሮ ቤት 3. አቶ ከበደ ማህሙድ ሁለት ቆርቆሮ ቤት የሶስቱም አርሶደሮች ከነሙሉ ንብረቱ በሀገር አፍራሹ የብልፅግና ራሱን ጥምር ጦር ብሎ የሰየመ የአብይና ሽመልስ አማራን የማጥፋት፣የማቆርቆዝና የማዳከም ልዩ ተልኮ የተሰጠው ተላላኪ ቡድን አማራ መቸም የማይረሳውና ይቅር የማይለው ነውር እየፈፀመ ይገኛል። በመጨረሻም ከፋሽስቱ ብልፅግና አገዛዝ ጋር ሆናችሁ ወገናችሁ የአማራ ህዝብ ላይ ዘር ማጥፋት እየፈፀማችሁና ቤት ንብረት እያወደማች ያላችሁ ሃይሎች ያለውን ነባራዊ ሁኔታ በመረዳት ከድርጊታችሁ እንድትቆጠቡና ከህዝብ ጎን እንድትቆሙ ስንል መልክታችንን እናስተላልፋለን! መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልዉና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል! ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን! አፋብን ምኒልክ ዕዝ ልጅ እያሱ ኮር የጎፍ ክፍለ ጦር 04/ዐ6/2018 ዓ.ም

አንድነት በተግባር የተገለጠበት የዓምሐራ ፋኖ በደብረ ታቦር ከተማ    [የካቲት 04/2018ዓ.ም] 01 👉👉👉 13:00 ሠዓታትን የፈጀ አውደ ውጊያ በደብረ ታቦር ከተማ                                       የአገዛዙ አራዊት ሰራዊትን ለማምበርከክ የአፋብን ሰ/አ/ቀ በላይ ዕዝ ሜጀር ጀነራል ውባንተ አባተ ፩ኛ ኮር  ለየካቲት 04/2018ዓ.ም የተጠና ዕቅድ ሲያዘጋጅ ሜጀር ጀነራል ውባንተ አባተ ተወርዋሪ ክፍለ ጦር እና የጉና ክ/ጦር ገ/መሥቀል ብርጌድ አካል የሆነችው ጣይቱ ሻለቃ በጋራ የውጊያው ዋዜማ  ከ04:00 ጀምሮ ሌሊቱን የደብረ ታቦር ከተማ ቁልፍ ቁልፍ ቦታዎችን ተቆጣጥረው  ያለ ተኩሥ የአገዛዙ ወታደሮችን ሲያፈራርሥ አድሯል። ውጊያውንም ከማለዳ  እሥከ ጠዋቱ 3:20  ደብረ ታቦር የከተመውን የአገዛዙ ታጣቂ በአባታቸው ውባንታዊ ሰይፍ ሲያናፍጡት አርፍደዋል። ከጠዋቱ 03:20 በኋላ የበላይ ዕዙ ግዙፍ ጉና ክፍለ ጦር እና የጠቅላይ ግዛቱ ክፍለ ጦሮች በመናበብና የውጊያ ቀጠናዎችን በመከፋፈል ጠላትን ሲያምበረክኩ ውለዋል። ከቀኑ 6:30 ገደማ ጀምሮ የ5ኛ ኮር ሰራዊት በአርበኛ ሻምበል ሙሉሰውና አርበኛ ግዛቸው አሌ የውጊያው አካል ሆኗል። በውጊያው ተሳታፊ የሆኑ የአፋብን ሰ/አ/ቀ በላይ ዕዝ እና ጎንደር/ጠ/ግ/ዕዝ ክፍለ ጦሮች፦ 👊ሜጀር ጀነራል ውባንተ አባተ ተወርዋሪ ክ/ጦር 👊ግዙፉ ጉና ክፍለ ጦር 05ቱም ብርጌዶች 👊የዕቴጌ ጣይቱ ክፍለ ጦር የተውጣጣ ሰራዊት 👊የጀነራል ፋንታ በላይ ክፍለጦር የተውጣጣ ሰራዊት 👊የተራራው ራሥ ጉና ክፍለ ጦር የተውጣጣ ሰራዊት 👊የአፄ ኢያሱ ክፍለ ጦር የተውጣጣ ሰራዊት 👊የዞዝ አምባ ንጉሱ ክፍለ ጦር የተውጣጣ ሰራዊት እና 👊የጋፋት ክ/ጦር 01 ሻለቃ 👊ታሪኳን በወርቅ የደም ቀለም የጻፈችው የነበልባሉ ፎገራ ክ/ጦር አካል የሆነችው ክርሥትያን ታደለ ብርጌድ እና ከነበልባሉ ክፍለ ጦር የተውጣጡ አካላት ከወረታ እሥከ ዓለም ሣጋ የሸፈኑ የጠላት አሰላለፍ የአገዛዙ ዙፋን ጠባቂ ቅጥረኞች ከ13 ወረዳ የነበረው  የአድማ ብተና፣ ሚሊሻ፣ ፖሊሥና ከሁሉም ወረዳ የተሰባሰበው ከሃዲ ወዶ ገብ ነው። ከቀኑ 5:30 ጀምሮ ደግሞ ✅በመጀመሪያው ዙር ከባሕር ዳር የመጣ 250+ መከላከያ፣ 200+ አድማ ብተና እና 60+ ወዶ ገብ ከሐዲ የጸዳሉ አጃቢዎች ከ02 ዙ-23፣ 02 ዲሽቃ፣ 120 ሞርታር ይዞ የመጣውን ✅ በመቀጠል ከባሕር ዳር የመጣው 54 ተሽከርካሪ መከላከያ 03 መድፍ፣ 02 ታንክ፣ ከ17  ዲሽቃዎች ✅3ኛ ዙር ከአርኖ ጋርኖ በ10 ተሺከርካሪ የመጣውን መከላከያ ✅4ኛ ዙር ከአዲሥ ዘመን የመጣውን አድማ ብተና አፋብን ሰ/አ/ቀ በላይ ዕዝ እና ጎንደር ጠቅላይ ግዛት ዕዝ  በጋራ በሥፋት የመጣውን የአገዛዙ አራዊት ሰራዊት መደበኛ ውጊያ ገጥመውት ውለዋል። አገዛዙ የሰራቸው የኮንክሪት ምሽጎች ተሰባብረዋል። ተሥፋ የቆረጠው የአቢይ አሕመድ ፋሽሥት አገዛዝ ለደብረ ታቦር ከተማ 07 ድሮኖችን መድቦ ውሏል። 14 የድሮን ጥቃቶችን በደብረ ታቦር ከተማና ታቦር ዙሪያ ቦታዎች ጥሏል። ሞርታር ክርሥትያን ታደለ ብርጌድ ላይ ብቻ 23 ጊዜ ጥሏል፤ ነገር ግን የሲቪል መኖሪያ ቤቶችንና የመንግሥት ትምሕርት ቤቶች ነው ያወደመው።   ነገር ግን በዚህ የድሮን ጥቃት በጅምላ የተመቱት አገር አማን ብለው የተቀመጡ የማሕበረሰቡ አካላት ናቸው። ማሰቢያውን የተቀማው የአገዛዙ አራዊት ሰራዊት ከወጂ እሥከ ደብረ ታቦር ከተማ ድረሥ  02 ዙ-23፣ ቁጥሩ ያልታወቀ ሞርታር፣ ከ17 በላይ ዲሽቃ፣ 03 መድፍ፣ 02  ታንክ እና መሰል የቡድን መሳሪያዎችን ቢይዝም ጥበበኛው የአማራ ፋኖ በክንዱ ሲያደቅቀው ውሏል። ከ11:30 በኋላ የፀዳሉ ደሴን ወደ ዓለም በር መምጣት መረጃው የደረሳቸው የሜጀር ጀነራል ውባንተ አባተ ተወርዋሪ ክፍለ ጦር  በፍጥነት ወደ ቦታው አምርተው ከበባ ፈጽመዋል። ፀዳሉ ደሴን መከላከያው ወደ ባሕርዳር እንዲያመልጥ ሲያደርጉ ራሳቸው ዋጋ ከፍለዋል። ምሽት 01:00 ፀዳሉ ደሴ ከመማረክ ያመለጠበት መዳኛ ሠዓቱ ሆኖ ተመዝግቧል። ሙሉ ቀናትን በተደረገው አውደ ውጊያ ከሁሉም ሰራዊት የተማረከውን ቅጥረኛ፣ መሣሪያ፣ ተተኳሽና ቁሥ  በነገው ዕለት በቪዲዮ እና በማሥረጃ የምናቀርብ ይሆናል። 02.👉👉👉ደራ ሐሙሲት ከአገዛዙ አራዊት ሰራዊት በትናንትናው ዕለት 01 ዲሽቃ፣ ከ115+ ክላሽና አንድ ኦባማ ሙሉ የክላሽና የዲሽቃ ተተኳሽ መማረካቸው ይታወሳል። በተመሣሣይ ከትናንት የተረፈውን 01 ክላሽ በጠዋቱ ሐሙሲት ከተማ ላይ ማርከውታል። ኅልውናችን በተባበረ ክንዳችን❗ ዝንተዓለም ዓምሐራ Forever AMHARA👊 አፋብን ሰ/አ/ቀ በላይ ዕዝ ሜጀር ጀነራል ውባንተ ፩ኛ ኮር ሕ/ግ ክፍል ፋኖ ኃቅአለው ፀጋ አለባቸው

ታላቅ ትንቅንቅ የተደረገበት የደብረ- ታቦሩ ውጊያ አፋብን ጎንደር ጠቅላይ ግዛት ዕዝ ሁለቱ ኮሮች( 206ኛ እና 204ኛ) እና አፋብን በላይ ዕዝ ሜጀር ጄኔራል ውባንተ አባተ ፩ ኮር ጋር ጥምረት በመፍጠር  በደብረ ታቦር ታላቅም ተጋድሎ ሲደረግ ውሏል ። ዛሬ የካቲት 04/2018 ዓ.ም   ከደብረ -ታቦር ሙያና ቴክኒክና እስከ ፋርጣ ወረዳ ዙርያ  የነበረን ምሽግ በቅንጅት ተሰባብሮ  የአገዛዙን ምርኮና ሎጅስቲክስ የማረከው  የፋኖ ቅንጅት ፣ ከተማው አደባባይ  እስከ አንደኛ ፖሊስ ጣቢያ በመዝለቅ ከፍተኛ ትንቅንቅ በማድረግ የጠላትን አንገትን አስደፍቶ  ደቁሶታል። የሁሉም ኮሮች ቅንጅት የተሞላበት  ይህ ውጊያ  ከወይብላ ምሽግ  እስከ  እየሱስ   ድባቅ ሲመታ ማረሚያ ቤትን እንደመማፀኛ የነፍስ አውጭኝ የሞት ሽረት  ትግል ሲያደርግ ውሏል። ጠላት  በድሮን የታገዘ ውጊያ በማድረግ በንጹሀን ቤትና ንብረት  ላይ በከፍተኛ ሁኔታ ጉዳት እንዲደርስ አድርጓል። በዚህ አውደ ውጊያ ከፍተኛ የሰው ሀይል ምርኮ ፣ሙትና ቁስለኛው የሆነበት ጠላት ለቁጥር የሚያስቸግር  የትጥቅና የተተኳሽ  አይነት ገቢ ሆኗል። ድል ለአማራ ፋኖ!!! ድል ለአማራ ህዝብ!!! የአማራ ፋኖ ብሄራዊ ንቅናቄ (አፋብን) ጎንደር ጠቅላይ ግዛት ዕዝ 206ኛ ከፍያለው ደሴ ኮር ህዝብ ግንኙነት !!! የካቲት 04 / 2018 ዓ.ም