ፍኖተ-አማራ ሚዲያ (Finote Amhara Media)
Открыть в Telegram
የተመሠረተው የአማራን ሕዝብ ለማንቃት፣ ለማደራጀት እና ለማስተባበር ነው። የአማራ ሕዝብን ✅ ፖለቲካዊ ✅ ማህበራዊ ✅ ኢኮኖሚያዊ ታሪካዊ ጥያቄዎችን ለማሰማት እና የአማራን ሕዝብ በማንቃት ሰፊውን ሕዝብ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ይሰራል። ወደዱም ጠሉም የኃላ ታሪካችን በእኛ እጅ ይፃፋል። አማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ ( አፋብን)
Больше4 130
Подписчики
-824 часа
+887 дней
+1 19430 дней
Архив постов
የአደረጃጀት ዜና
የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል (አፋብኃ) ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ ምስራቅ አማራ ኮር 1 ሀውጃኖ ክፍለ ጦር የአመራር ሪፎርም አደረገ::
ቀናትን የፈጀ ውይይት እና ግምገማ ከተደረገ በኋላ አዳዲስ አመራሮች የተሰየሙ ሲሆን ከነባሮች የኃላፊነት ርክክብ አድርገዋል::
የምስራቅ አማራ ኮር 1 ሰብሳቢ አርበኛ ሞገስ አማራ በተገኘበት የተካሄደው የውውይት እና ግምገማ መድረክ በስኬት መጠናቀቁ የተገለፀ ሲሆን ጉባኤተኞች ከዚህ በታች ስማቸው የተዘረዘሩትን አርበኞች የክፍለ ጦሩ አመራሮች አድርገው መርጠዋል :: በዚህም፦
1ኛ. አርበኛ ካሳ አበበ- የክፍለ ጦሩ አዛዥ
2ኛ. አርበኛ ደሳለ መራጊያው - የክፍለ ጦሩ ምክትል አዛዥ
3ኛ. አርበኛ ኩርፋ መንገሻ - ዘመቻ መምሪያ ኃላፊ
4ኛ. አርበኛ ተመስጌን ሞገስ_ምክትል ዘመቻ መምሪያ ሀላፊ
5ኛ. አርበኛ መረሳ አድሱ __ አስተዳደር
6ኛ. አርበኛ በርሄ ቸኮለ - የፖለቲካ ዘርፍ ሀላፊ
7ኛ. አርበኛ አሰፋ መለሰ- የህዝብ ግንኙነት ዘርፍ ኃላፊ
8ኛ. አርበኛ ቢኒያም ዝናቡ - ስልጠና መምሪያ ኃላፊ
9ኛ. አርበኛ ፈረጃ ሞላ _የፋይናንስ ሀላፊ
10ኛ. አርበኛ ጋሻው ንጉስ _ሎጀስቲክ ሀላፊ
11ኛ. አርበኛ ክብሮም ከበደ _ የሰው ሀይል አስተዳደር
12ኛ. አርበኛ አበራ ፀጋይ___ኦርድናንስ ሀላፊ
13ኛ. አርበኛ ***መረጃና ደህንነት
14ኛ. አርበኛ ስዩም ካሳው ____ ህግ አገልግሎት
16ኛ. አርበኛ አረቂ መረሴ _ ሀብት አፈላላጊ ክፍል
መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልውና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል!
ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን!
አፋብኃ ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ
ታህሳስ 17/ 2018 ዓ.ም
+1
የብልጽግናን ተልዕኮ በመቀበል ህዝብን እየዘረፉ ሲያማርሩ የነበሩ ሌቦችን በ109ኛ ኮር የማጽዳት ስራው ተጠናክሮ ቀጥሏል
=====================
በረከት ወይም በቅፅል ስሙ አስካል የሚባል ፋኖ መሳይ ሌባ በጅጋ ሻለቃ ተጠርንፎ አስፓልት እየወጣ ህገወጥ ቀረጥ የሚቀርፅ የቃል ኪዳን ቀለበት ሳይቀር የዘረፈ ባንዳ ፤ በቴዎድሮስ ዕዝ 109ኛ ኮር መረጃ እና ደህንነት ክትትል ሲደረግበት የዘረፈዉን ዘርፎ ወደ አዲስ አበባ ሄዶ ኑሮዉን ለመኖር እየተንቀሳቀሰ ባለበት ወቅት ክትትል በማድረግ በደንበጫ ወረዳ የዘለቃ ቀበሌ በቁጥጥር ስር ዉሏል። የጠላትን ተልዕኮ በመያዝ በአፋብኃ ቴዎድሮስ ዕዝ ተሰግስጎ የነበረ ሌባና ባንዳ የማጽዳት ስራው ተጠናክሮ ቀጥሏል። በቀጣይ ትግሉን ለመጉዳት የሚሞክሩ ማናቸውም ቡድን ሆነ ግለሰብ በመረጃ በማነፍነፍ የትግሉን ጤንነት ለመጠበቅ አፋብሃ ቴዎድሮስ ዕዝ የመረጃ እና ደህንነት ሀይሉ 24/7 በተጠንቀቅ ላይ ነዉ።
👉የሌባና የባንዳ ፀሀይ እየጠለቀችበት ነው!!!
አዲስ ትውልድ! አዲስ አስተሳሰብ! አዲስ ተስፋ!
109ኛ ኮር 77ኛ ክ/ጦር ህ/ግንኙነት
ታህሳስ 17/2018 ዓ/ም
"ደብረ ማርቆስ ሆስፒታል በቁስለኞች እንደታጨቀ ነው"
ታህሳስ 17/2018.ዓ.ም
ሞት አይፈሬው 206ኛ ኮር በጠላት ላይ በተከታታይ ባደረገው ተጋድሎ፣በሉማሜ፣ስናን እና ደብረ ኤልያስ የተደቆሱ የጠላት ከባድ ቁስለኞች በደብረ ማርቆስ ሆስፒታል በድን ሁነው እየወጡ ይገኛሉ።
በጃማው ድንቅ ኦፕሬሽን የጠላት ኃይል ከተቀጠቀጠ በኋላ በርካታ ከባድ ቁስለኞች በደ/ማ ሆስፒታል መግባታቸው የታወቀ ነበር ይሁን እንጂ እስከ አሁን የሚሞቱት ቁጥር እየጨመረ ሲሆን ኢንስፔክተር መሀሪ መላክ በድን ሁኖ በቁይ ከተማ ሲቀበር ኢንስፔክተር ባምላክ ወደ አዲስ አበባ ተጉዞ ጥቁር አንበሳ ሆስፒታል መድረሱ ተረጋግጧል።
በደብረ ኤልያስ ወረዳ የተቀጠቀጠችው 32ኛ ክ/ጦር 5 ሬጅመንት በርካታ ቁስለኞች ደብረ ኤልያስ ሆስፒታል የሚያቃስቱት እንዳሉ ሁሉ ፻ አለቃ ፋሚ ኡመር እና ፻ አለቃ መዝገብ ካሴን ጨምሮ በርካቶች ደብረ ማርቆስ ሆስፒታልን አጥለቅልቀውታል።በስናን የተወቀጠችው 25ኛ ክ/ጦር በበኩሏ ኮተቷን ይዛ ከዕረቡ ገበያ ወጣ እነራታ ቀበሌ ተሰባስባ ቁስለኞቿን እያገላበጠች ትገኛለች።
በሉማሜ ከተማ እስከ አሁን መረጋጋት ያልቻለው የብልፅግና ስብስብ፦
1.በአዋበል ወረዳ ፖሊስ ፅ/ቤት ሃላፊ---በድሉ ሰዋለ
2.በከተማ አስተዳድር ሰላምና ደህንነት ---ላመስግን
3.የዙሪያ ወረዳ ሰላምና ደህንነት----አዲሱ ቸሬ አማካኝነት ከሞት የተረፉ ሚኒሻዎችንና ፓሊሶችን ለማረጋጋት ሙከራ ቢያደርጉም ጥርሳቸውን የሚያንቀራጭጩት እና በቁማቸው የሚቃዮትን ድጋሚ ወደ ግዳጅ ማስወጣት ተስኗቸው ስብሰባው ያለ መግባባት ተበትኗል።
በጃማው ድንቅ ምት ሲፍረከረኩ የነበሩ 10 ሚኒሻዎች ደብዛቸው በመጥፋቱ ምክንያት ግራ የተጋባው የአረመኔው ሰራዊት በፀበል እና በገዳም አካባቢዎች ፍለጋውን እያጧጧፈው መሆኑን አረጋግጠናል።
አዲስ ትውልድ! አዲስ አስተሳሰብ! አዲስ ተስፋ
የአፋብኃ ቴዎድሮስ ዕዝ 206ኛ ኮር ህዝብ ግንኙነት
አይበገሬዋ 88ኛ ክ/ጦር ጠላትን ደምስሳ 5 ክላሽ ማረከች!!
*//
ታህሳስ 17/2018 ዓ.ም መነሻውን ከቡሬ ዙሪያ ወረዳ ቁጭ ከተማ ያደረገው የአብይ አህመድ ዘር ጨፍጫፊ ሠራዊት እኩይ የጥፋት ተልዕኮውን አንግቦ አ/አደር ለመዝረፍና ለመጨፍጨፍ ቅጥረኛ ሠራዊቱን ከንጋቱ 10 ሠዓት አካባቢ ጀምሮ ወደ ጭራር ቀበሌ አንቀሳቅሷል። በአፋብኃ ቴዎድሮስ ዕዝ 109ኛ ኮር አይበገሬዎቹ የ88ኛ ክ/ጦር 1ኛ ሻለቃ እና 6ኛ ሻለቃ (ቃኝና መሃንዲስ) የጠላትን የእንቅስቃሴ መረጃ በማጤን ጠላትን ቀጥቅጠው እና ጉሮሮውን አንቀው 5 ክላሽኮቭ ማሮከዋል።
ግዳጁ ክ/ጦሩ በአዲስ ጥቅምት 29/2018 ዓ ም ከተመሰረተ ወዲህ ለ7ኛ ጊዜ የተፈጠረ ግዳጅ ሲሆነ በግዳጁ 1ኛ እና 6ኛ ሻለቆች የጀግንነትን ልካቸው ያስመሰከሩበት፣ ቦታን እንደ ሁኔታው አብቦ የመጠቀም ወታደራዊ እውቀታቸውን ያሳዩት፣ ወደፊት ተወርውረው እኔ ልቅደም እኔ እያሉ የጠላትን አፈሙዝ የነጠቁበት፣ የጠላትን አከርካሪ የሰበሩበት፣ ጠላትን ጉልበቱ እስኪርድ እያሯሯጡ ጀርባ ጀርባውን በጥይት የነደሉበት፣ በሲቃ የጣረሞት ድምፅ ያላዘነበት፣ ግሩም ቀን ድንቅ ውሎ በወምበርማዋ ጭራር ቀበሌ ተስተውሏል።
#አንድ ከሞት የተረፈ ሚሊሻ ጉልበቱ እስኪብረከረክ ከጭራር ቀበሌ ቁጭ ከተማ ድረስ እሩጦ ለም/ቅ ዕዝ ምክትል አዛዥ ሜጀር ጀ/ል ተስፋየ ረጋሳ ህዝብ ሰብስቦ እያለ በስብሰባው አዳራሽ ዘሎ በመግባት ጀኔራል እናንተም እያላችሁ አለቅን ፈጁን ብሎ እያለቀሰ አቤት ሲለው በል ዝምበል እንደዚህም አይባልም ብሎ ከመድረክ አባሮታል።
#በግዳጁ ጠላት ከ43 በላይ ወደ ማይመለስበት የተሸኘ ሲሆን ከ27 በላይ ማቁሰል ተችሏል።
🙏ክብር ለውጤቱ ለደከማችሁ!
#አዲስ(ትውልድ ፣አስተሳስብ፣ተስፋ)
ልጅ እያሱ ኮር 24ኛ ክፍለ ጦር የፋሽስቱ ብልፅግና አገዛዝ ዙፋን ጠባቂ ሰራዊት መድፍ እና አራት ተኳሾቹን ጨምሮ በሞርተር በማውደም ታላቅ ድል ተጎናፀፉ::
በርካታ የፋሽስቱ ብልፅግና አራዊት ሰራዊት ከውጫሌ ከጎልቦና ጭሳ በመነሳት ትናትና ታህሳስ 16/2018 ዓ.ም ጀምሮ ዛሬ ታህሳስ 17 ሙሉ ቀንም ጨምሮ ወደ አምባሰል ዙሪያ አበት ማጥቃት ያደረገ ሲሆን ልጅ እያሱ ኮር 24ኛ ክፍለ ጦር ባግባቡ በመመከትና በርካታ ሃይሉን ሙትና ቁስለኛ በማድረግና ከባድ ሰብዓዊ ኪሳራ በማድረስ ታላቅ ድል ተጎናፅፈዋል::
ልጅ እያሱ ኮር 24ኛ ክፍለ ጦር በተጋድሎው መካናይዝዳቸውን በመጠቀምና ሞርተር በማስወንጨፍ ውጫሌ ልዩ ስሙ ደንካ የተባለ ቦታ ላይ የነበረ የጠላት መድፍ ኢላማውን ጠብቀው በማውደምና አራት ተኳሾችን ጭምር በመደምሰስ ታላቅ ድል ተጎናፅፈዋል::
በዚህም ከባድ ሰብዓዊ እና ቁሳዊ ኪሳራ የደረሰበት የፋሽስቱ አገዛዝ ሰራዊት በተከታታይ ሁለት ቀን በተደረገው ተጋድሎ የጄትና ድሮን ቅኝት እያደረገ የተዋጋ ሲሆን ንስሮቹ 24ኛ ክፍለ ጦርም ምንም ነገር ሳይበግራቸው ጠላትን አይወጡ ቅጣት ቀጥተው ወደመጣበት በመመለስ እንዲሁም ቀጠናቸውን ጭምር በማስከበር ታላቅ ድል አስመዝግበዋል::
ከባድ ሰብዓዊ እና ቁሳዊ ኪሳራ ደርሶበት ሽንፈት የተከናነበው ፋሽስቱ አገዛዝም እንደተለመደው የበቀል አፈሙዙን ወደ ንፁሃን ያልታጠቁ አማራዎች በማዞር ከባድ መሳሪያ ሲያስወነጭፍ ውሎ በሰው ህይወት እና እንስሳቶች ላይ ጉዳት ያደረሰ ሲሆን ቤትና ንብረትም አውድሟል::
መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልውና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል!
ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን!
የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል (አፋብኃ)
ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ
ታህሳስ 17/2018 ዓ.ም
የጀመረው
ጠጠር ድንጋይ ከረገጠችበት ቀን ጀምሮ ፈረስ ቤት እንደገባች ክትትል አንድ ተብሎ ተጀምሯል። የጠላት ሠራጊ ሃይል ማንነቱ ከተለየ ቀን ጀምሮ በጠላት ውስጥ መልሶ ሠርጎ እንደመግባት 50% ያክል እንደሆነ ጠንቀቅው የምናውቅ የፋኖ ፀረ መረጃ አመራሮች እድሉን በአግባቡ ገልብጦ የመጠቀም ስልት ላይ ትኩረት እንድናደርግ አስችሎናል።
2.2. የተግባር ሥራ
የጠላት ተባባሪዋ ወደ ልጀንጉስ ከገባች ቀን ጀምሮ የምታገኛቸውን ሰዎች፣ ሌላ ቀድሞ የገባ ሠላይ ካለ ለመለየት በሚል በጥንቃቄ ክትትል በማድረግ እንዲሁም እየዞረች ሰዎችን ስትጠይቅ ትክክለኛ መረጃ ሳይሆን መረጃው የተዛባ እና ጠላትን እንዲያሳስት ተደርጎ የተዘጋጀ በተቀራረበቸው ሰው አማካኝነት እንዲደርሳት ተደርጓል።
በሥራ ሥምሪቷ ወቅት ከልጀየንጉስ አካባቢ ውጭ የሰቀላን፣ የዳማማርቆስ፣ጣዕመ እና አረፋም እየደወለች መረጃ እንድትጠይቅ ስምሪት ተሰጧታል። በስልክ ግንኙነቷ ወቅት መረጃ መምሪያው ለመረጃ አሰባሰብ የሚጠቀምበት የቢሮ ቁጥር(+251113727801)በሆነ ቁጥር ሪፖርት እንድታደርግ ስለተሰጣት እየደወለች መረጃ አስተላልፋለች። በተደጋጋሚ በዚህ ቁጥር አትደውይ የስልክ ግንኙነት መፈተሻ ዲቫይሶች ሊኖራቸው ስለሚችል ለባለቤትሽ እየደወልሽ ንገሪው እሱ ለኛ ይነግረናል ብለው ስላስጠነቀቋት የተባለችውን አድርጋለች።
በተግባር ሥራዋ ላይ ዝርዝር አቅጣጫ በተሰጣት መሠረት:-
➔ መከላከያ ሲገባ እነ ዝናቡ በየት አቅጣጫ እንደሚያፈገፍጉ
➔ የፋኖ ካምፖች እና መመገቢያ እና ማደሪያ ቦታዎችን ለአየር ሃይል ጥቃት እንድናደርግ በሚያመች መልኩ
ፍልፈል አዳኝ ጭልፊቶች(Mole raider Falcons)
የአፋብኃ ቴዎድሮስ ዕዝ ወታደራዊ መምሪያ ፀረ-መረጃ ክፍል ጠላት በተለያየ መልኩ አስርጎ የሚያስገባቸውን የጠላት መረጃ ሰብሳቢዎችን ወደ ቀጠናው ሲገቡ ጀምሮ ክትትል በማድረግ ፣በቁጥጥር አውሎ ምርመራ ከማድረግ ባሻገር ገልብጦ በመጠቀም የጠላትን ስምሪት ማዛባት እና የውጊያ ዕቅድ ማክሸፍ የሁልጊዜም ተግባሩ ነው። በተለያየ ጊዚያት የሚሞከሩ ሙከራዎችን በማክሸፍ አመራሮችን በመጠበቅ ረገድ የተዋጣለት ስራ በመስራት ለጠላት ቅዠት እንደሆነበት ጠላት ራሱ ምስክርነት የሰጠበት ጉዳይ ነው።
በሥለላ ቋንቋ ወገን በሚንቀሳቀስበት ቀጠና ጠላት አስርጎ የሚያስገባቸውን ሠላዮች በመከታተል ህዝቡን፣ ድርጅቱን፣ መሪዎችን፣ እና ሠራዊቱን ከጠላት ሥርገት እና ጥቃት የመከላከል ሚናው የሚሆነው የፀረ መረጃ ክፍል(counter Intelligence)የሚባለው ዋና ተግባር ሲሆን፤ ወገን በጠላት ቀጠናዎች ላይ መረጃ ሲሰበስብ መሰለል/ስለላ/ምንተፋ ተብሎ የሚገለፅ ነው። የዛሬው ዋናው ጉዳይ የፀረ መረጃ ክፍል በክትትል እና በምርመራ ከደረሰባቸው 11 ኬዞች መካከል ያበቃለት ህዝብ ቢሰማው የማይጎዳ መረጃ ወይም በመረጃ ምደባ የሚስጢርነት ደረጃው እንዲወርድ የተደረገ (declassified level ) በመድረሱ ምክንያት እንዲበተን የተደረገ ሪፖርታዥ ማቅረብ ነው።
➩ ጠላት ለተልዕኮ ያሰማራት ግለሰብ
ስም: ፈጠነች ጌታነህ
ትውልድ ቦታ : ደጋ ዳሞት ወረዳ ልጅየንጉስ ቀበሌ
መኖሪያ አድራሻ: አዲስ አበባ ኮ/ቀራንዮ ክፍለከተማ ወረዳ 06
ፎቶ እና መታወቂያ ከታች ተያይዟል።
1: የምልመላ እና ስልጠና ሂደት
1.1 የአመላመል ሂደት
በአዲስ አበባ ሴቶች ማህበር የአማራ ተወላጅ አባላት ሴቶችን ለብቻ በክፍለ ከተማው ስብሰባ እንዲጠሩ በማድረግ ድጋፍ እናደርጋለን በሚል በተለይ በአማራ ፋኖ ትግል እንቅስቃሴ ላይ መረጃ ከሰጣችሁን በሴፍትኔትም ሆነ የቀበሌ ቤቶች እንደሚያገኙ በማስረዳት አዲስ አበባ ውስጥ የሚመጡ የፋኖ አባላትን አጋልጠው እንዲሰጧቸው እና የአማራ ህብረተሰብ ሴቶችን ስለሚያምን ስልጠና ተሰጧችሁ ወደ ትውልድ አካባቢ በመንቀሳቀስ የፋኖን እንቅስቃሴ፣ የአመራሮች ውሎ እና የህዝቡን አስተያየት በመሰብሰብ እንዲሰሩ ጭምር ያለመ ነበር።
ከስብሰባው ማጠናቀቂያ መታወቂያ በመሰብሰብ የትውልድ አካባቢ በመለየት ሂደት ላይ ስብሰባውን ያስተባበሩት የነበሩት የክፍለ ከተማው የብሄራዊ መረጃ አስተባባሪ፣ የመከላከያ መረጃ እና የአዲስ አበባ ፖሊስ አመራሮች በስብሰባው መካከል የተገኘች አንዲት ከምዕራብ ጎጃም ዞን ደጋ ዳሞት ወረዳ ልጅ የንጉስ ቀበሌ የተወለደች እንደሆነ ሲመለከቱ ለምንፈልገው አካባቢ አስፈላጊ ሰው እንደሆነች አምነዋል። ደጋ ዳሞት ወረዳ ልጅ የንጉስ ቀበሌ የቴዎድሮስ ዕዝ ወታደራዊ አዛዥ ሻለቃ ዝናቡ ልንገረው የትውልድ ቀበሌ እና መንቀሳቀሻ አካባቢ እንደሆነ ስለሚታወቅ የተገኘችዋን ግለሰብ አሳምኖ ወደ ስራ ማሰማራት ከተቻለ ሻለቃ ዝናቡን ማስወገድ የሚቻልበት እድል እንዳገኙ ተስፋ አድርገዋል።
ግለሰቧን መታወቂያሽን በኋላ ነው የምትወስጅ ብለው ከስብሰባው ሲበተን ከሌሎች በስም እና ትውልድ ወረዳ ከምታውቃቸው ሰዎች ጋር ወደ ኋላ እንዲቆዩ ትደረጋለች። በዚህም ሌሎችን ከማስተናገዳቸው በፊት በቅድሚያ ዋነኛ ታርጌት የሚንቀስቀስበት አካባቢ ህዝብ ሠላይ ፍልፈል ሁና የምትሰማራን ሴት በመኪና ከቦታው በመጫን ወደ መከላከያ ጠቅላይ መመሪያ ግቢ ወታደራዊ መረጃ ክፍል ( በእሷ አጠራር ብዙ ጠጠር የደረደረ እና ዘንባባ ያለበት ማዕረግማዕረግ የለበሰ) ጀነራል አጠገብ አቅርበዋታል። ልጅቷ ሁለት ልጆች እንዳሏት እና በመጠነኛ ሆቴል ወጥ ቤት ሠራተኛ እንደምትሠራ በኑሮ ውድነት እየተቸገረች እንዳለች እንዳስረዳች ትናገራለች። ይሄ ስልት በገንዘብ እና በኑሮ አስፈራርቶ በማሠማራት መረጃ መሰብሰብ ጠቃሚ የመመልመያ መስፈርት እንደሆነ የመረጃ አመራር መኮነኑ አምኖበታል።
ሥራውን በአግባቡ ከተወጣች የቀለብ እና የቤት ኪራይ ጨምሮ እንደሚመቻችላት ቃል በመግባት ሥራዋን እንድትሠራ ያሳምኗታል። ሥራው በነሱ አጠራር በከፍተኛ የስጋት ደረጃነት የተመደበ(high profile target) አመራር የሚንቀሳቀስበት ቀጠና ከመሆኑ ጋር ተያይዞ የፀረ መረጃ ሥራዎችም ስለሚኖሩ ይሄን ለማለፍ የሚያስችል ገንዘብ በጅተንልሽ ለ3 ወር ድረስ በቂ ስልጠና እንደምትወስድ ያግባቧታል። ግለሰቧም ከባለቤቴ ጋር ተማክሬ ልምጣ በማለት ተነጋግረው ይለያያሉ። በቀጣይ ቀን እንደተስማመች በመግለፅ በተሰጣት የቢሮ ስልክ ቁጥር በመደወል በማሳወቅ ስልጠና እንደምትጅምር ይነግሯታል።
1.1. የስልጠና ሂደት
ስራውን ለመስራት መስማማቷን ከገለፀች በኋላ ከማንም ሰው ጋር እንዳትገናኝ በማድረግ በጦር ኃይሎች ግቢ ለልዩ ልዩ ስራዎች ስልጠና መስጫ ማዕከል ውስጥ ለብቻዋ ለ3 ወራት ያክል
- መረጃ መሰብሰብ
- መረጃ ማስተሊለፍ
- ፎቶ አነሳስ
-gps ማብራት እና ማጥፋት
- መከላከያ በቦታው ሲገባ እንዴት ከታርጌቶች ጋር መሸሽ እንደሚቻል።
-ከፋኖ ወታደራዊ አመራሮች ዙሪያ ካሉ አባላት ቅርርብ መፍጠር
- መርዝ አጠቃቀም እና ሌሎች የጥንቃቄ ጉዳዮች ላይ በተመለከተ ሰፊ ገለፃ እንደተደረገላት ነግራናለች። በስልጠና ሂደቱ ላይ ሌሎች አካባቢ ላይም በተመሣሣይ እንደ አንች ያሰማራናቸው ብዙ አለ ህፃናትን ጨምሮ በማለት ነግረዋታል።
በስልጠና ሂደቱ ላይ ሌሎች ወረዳዎች እጅ እየሠጡ ስለሆነ የደጋ ዳሞት ወረዳ ፋኖዎች ናቸው ያስቸገሩን መሪውን አንቺ በምትሰጭን መረጃ ካስወገድነው እና በአግባቡ ከፈፀምሽ ትልቅ ሽልማት እንደሚጠብቃት በማጓጓት የበለጠ በምታገኘው ጥቅም ላይ እንዳተኩር እንደተደረገች በምርመራ ሂደት ቃሏን ሰጥታለች።
2: የስምሪት ሁኔታ
ለሶስት ወራት የነበራትን የሥልጠና እና ኦረንቴሽን ስራ ከተጠናቀቀ በኋላ ምልምል ተባባሪነት ደረጃ ስላደገች ወደ ቀጥታ ስምሪት መስጠት ዝግጁ መሆኗ ተረጋግጦ ወደ ስምሪት ጉዞ እንድታደርግ ህዳር 19፣ 2018 ዓም በጧት ከአዲስ አበባ ከአውቶብስ ተራ የመከላከያ መረጃ የበታች አመራር እና ባለቤቷ ( የስራው ተባባሪ)ትኬት በመቁረጥ ለጉዞ የሚሆን 3000 ብር ጥሬ ገንዘብ በመስጠት እንዲሁም ለባለቤቷ 10,000 ብር እንዲሰጠው ተደርጓል።
ተባባሪዋ ለጉዞ ላይ ግንኙነት እንዲያመቻት የተዘጋጀ አዲስ ሲም ካርድ በመስጠት ፈረስቤት ያለ ሰው በዚህ መስመር ይደውልልሻል በማለት ለማንም እንዳትደውይ በዚህ ስልክ ብለው በማስጠንቀቅ ይልኳታል። በዚሁ ቀን በመንገድ ላይ እያለች በዚሁ መስመር ደብረ ማርቆስ መድረሷን ለማረጋገጥ የተደወላለት (ስልኳ ላይ መዝግባው የነበረ በምርመራ ሂደት የሰጠችን)ሲሆን ደብረ ማርቆስ በማደር በማግስቱ( በቀን 20/2018) ወደ ደጋ ዳሞት ተንቀሳቅሳለች።
ህዳር 20/2018 ዓም ፈረስቤት ከተማ መግቢያ ጠጠር ድንጋይ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ ኬላ ፍተሻው ላይ ከማዕከል የታዘዘው ግለሰብ በቀጠናው የተሰማራው የ23ኛ ክፍለጦር መረጃ ኃላፊ እና አንድ ሌላ ሰው ከፍተሻ ለብቻ በመለየት መካከል በመለየት አንቺ ነሽ አይደል ስምሪት ተሰጦሽ የመጣሽ ? ብሎ በመጠየቅ ከስልኳ ውስጥ የነበረውን ሲም ካርድ በማውጣት ሰብሮ በመጣል አዲስ አበባ ስምሪት ከሰጠሽ ሰው ጋር ቀጥታ በመገናኘት ስራሽን ቀጥይ ብሎ አሰናብቷታል። የቴዎድሮስ ዕዝ ወታደራዊ መምሪያ ፀረ መረጃ ክፍል ሥራውን
የአንድ ድርጅት መወለድ ፣ ማደግ ፣ መስፋፋት ፣ መፅናት ፣ የህዝብን ማህበራዊ ደህንነት ማስጠበቅ ፣ ፖለቲካዊ ተሳትፎውን ማጉላት ( በተለይም እንደ ኢትዮጵያ በተፈጥሮዋ የሪፐፕሊክ ስርአት አስገዳጅ በሆነባት አገር) ፣ የኢኮሊሚ ፍትሐዊ ተጠቃሚነቱን በማረጋገጥ እድገትን ማስቀጠል ብሎም አሁገራዊና ቀጠናዊ የስልጣኔ ግጭቶችን እና የስልጣኔ ግጭት የወለዳቸውን አለማቀፋዊ ፖለቲካዊ አሻጥሮችን በመተንተን ስትራቴጅካዊ ምላሽ በመስጠት እየቀለበሱ ህልውናን ማስጠበቅ በእጅጉ አስፈላጊ ነገር ነው።
አለም አቀፍ የፖለቲካ አሻጥር ቀማሪ ሊህቃን የሐገራቸውን ብሔራዊ ጥቅም ለማስከበር ወይም የተገዳዳሪያቸውን የፖሊሲ አቅጣጫ ለማስቀየረ የአለም ሰላም የሚሰፍነው ከፊሎች ከሐሳባዊነት ( idealism) አስተሳሰብ አንፃር ስለሰላም ምንጭነት ሲወተውቱ ቀሪወቹ ደግሞ እውናዊ ( realism) አስተሳሰብ አንፃር አንድ አገር ወይም ቀጠና ሰላሙን የሚያረጋግጥበትን አማራጭ ያቀርባሉ።
ከዚህ አንፃር ሐሳባዊያን (idealists) አለም ሰላም የምትሆነው በመተማመን ላይ ተመስርተን የጋራ ደህንነታችንን የሚያስከብሩ አለም አቀፍ ተቋማትን በመመስረት በጋራ መርህ እና እሴት ተቃኝተን በጋራ ህግ ስንመራ አንዱ ከሌላው ጋር ስንተባበር የጋራ ሰላምን እንፈጥራለን ብለው ያምናሉ።
እውናዊያን ( realists) በበኩላቸው የአንድ ሉአላዊ አካል ጥቅም እና ደህንነት የምናስከብረው በምንፈጥረው ተነፃፃሪ አቅም ( Power Balance) ነው ብለው ያምናሉ።
የሐባዊያን መርህ ከአንደኛው የአለም ጦርነት ማለቅ ማግስት ጎልቶ ቢቀነቀንም የሀለተኛውን የአለም ጦርነትን መዋለድ ማስቀረት የሚችል ዶግማዊ ኃይል አጥቶ አግኝተነዋል። ሁለተኛውን የአለም ጦርነትም ያሸነፉትም ተግተው በመስራት ኃይል መገንባት የቻሉት መሆኑ ታሪክ ያረጋገጠልን ሐቅ ነው።
ሐሳባዊያን ከሁለተኛው የአለም ጦርነት ማግስትም አሁንም ብቸኛ አማራጩ አለም አቀፋዊ እሴቶች ናቸው በማለት ከተባበሩት መንግስታት እስከ አውሮፖ እና አፍሪካ ህብረት ከዛም ኢጋድ እና ሌሎች የፖለቲካ እና ኢኮኖሚያዊ ትስስር የሚፈጥሩ ተቋማትን መመስረት ቢቻልም ቀዝቃዛው የአለም ጦርነት ከቬትናም እስከ ጀርመን እና አፍሪካ አገሮች ድረስ የፈጠረውን ምስቅልቅል ማስቀረት አልቻለም። ሐሳባዊያን የአውሮፖ ቅኝ ገዥወች በአፍሪካ እና በተቀረው የአለም ክፍል ሁሉ ጎሳን ከጎሳ የሚያጫርስ የፖለቲካ መርዝ እረጭተው በቅኝ ገዥነት ዘመናቸው ማቀንቀናቸው ሳይቀር በጎሳወች መካከል በግዴለሽነት በፈጠሩት ድንበር ለተፈጠረው ደም አፋሳሽ እልቂት እንኳን ለማቅለል እርባና ያለው ሐሳብ ሲያመነጩ አልተስተዋሉም።
አለማቀፋዊ እና ሐጉራዊ የተባሉት የሰባዊ መብት አሌንታ ይሆናሉ ተብሎ ሲታሰብ ከጀርባ ዋነኛ አላማቸው ምዕራባዊ የፖለቲካ እና የኢኮኖሚ አስተሳሰባቸውን ማንሰራፋት እና ምዕራባዊነትን (Westernazation) የአለም አስተሳሰብ ለማድረግ በሩቅ ምስራቅ ፣ በመካከለኛው ምስራቅ እና በአፍሪካ ያሉ ስልጣኔወችን በመሰልቀጥ ጠቅላላውን አለም ጥሬ እቃ ሐብት በርካሽ ዋጋ በመዝረፍ የሸቀጥ ማራገፊያ ማድረግ እንደሆነ ከተረጋገጠ ውሎ አደረ። በመሆኑም ፍትህን ከአለም መጠበቅ የዋህነት ነው። አለም የጠንካሮች ብቻ ወይም ብዙ ጠንካሮች ተስማምተው የሚኖሩባት እንጅ የፍትህ ችሮታ በፍፁም ከጇ አይጠበቅም።
ካልተደራጀ ትልቅ አገር የተደራጀች ትንሽ ከተማ ሙያ ትሰራለች እንዳለው ገብረ ህይወት ባይከዳኝ ህልውናን ለማስከበር ብቸኛው መድሐኒት እራሳቸውን ከጅብ ለመጠበቅ ተመሳቅለው እንደሚቆሙ ፈረሶች አንዱ አማራ ለሌላውን ወንድሙ ጉልበት እና አሌንታ ከመሆን በላይ እንደ ችቦ እንጨጦች በአንድ ላይ በመቆም ታሪካዊ የነቃ ዜጋ ሚና ሆኖ አግኝተነዋል።
አለም በጠበበችበት እና ግፊ በበዛበት አለም ላይ ከገደል አፋፍ ላይ መቆም በመንገድ ላይ የሚፈጥኑ አካላት ሆንብለውም ሆነ በአንተ ነሁላላነት ወደ ገደሉ ተጨመሩህ እጣፈንታህ መንኮታኮት እንደሆነ ተገንዝበህ በአስተማማኝ ጥንቃቄ መጓዝ አስፈላጊ መሆኑ አሌ አይባልም።
ይህ አስከፊ የአለም ገፅታ በተራቀቀ የዲፕሎማሲ አቅም ፣ በወደረኛ ፊት በሚያስከብር የአላማ ጥራት እና ፅናት ፣ ከብረት አለሎ በበረታ አማራዊ ወንድማማችነት ሲታሽ አሸናፊ ኃይል ሆነን እንወጣለን።
ከዚህ ወጭ በአውራጃዊ አደረጃጀት መመናቸክ ፤ በወንዜልጅ እና ዘመድ አዝማድ ለመሰባሰብ መፈለግ ፣ ወዘተ የአማራ ብሔርተኝነት ካንሰር መሆናቸው ይታወቅ።አማራዊ ወንድማማችነት ከብሔርተኝነት መሰረታዊያን ጋር ተገናዝቦ በአላማ ቁርጠኝነት ፣ ታማኝነት ፣ ክህሎት ሲለካ በርግጥም የማሸነፋችን ዋዜማ ይመጣል። መሪያችን አባመቻል አርበኛ ዘመነ ካሴ እንዳለውም ድልን እናረጋግጣለን።
ከዚህ ባለፈ በአማራ ብሔርተኝነት ውስጥ ወንዜነት ፣ የዘመድ አዝማድን ቁርኝት በድርጅቱ ውስጥ ለማንሰራፋት መሞከር የጫጉላ ሽርሽር ( Honey Moon) ያህክል እንኳን ጊዜ ለመቀለድ እድል እንደማይሰጥ በውል በመረዳት ወደ ቀልብ መመለስ እንዳለባችሁ ወድማዊ ምክራችሁን እንካችሁ።
አዲስ ትውልድ
አዲስ አስተሳሰብ
አዲስ ተስፋ
Kinfemelak N kassa የቴዎድሮስ ዕዞ የ109ኮር ምክትል ሰብሳቢ
ታህሳስ 17/ 2018 ዓ.ም
መልዕክት ከአርበኛ ዘመነ ካሴ
አንዳንድ ነገሮች‼️
✅ተፈጥሯዊ እውነታ!
የጋራ ጠላት ያላቸው ኃይሎች ቢተባበሩ ተፈጥሯዊ ነው። የዘር ፍጅት የገጠመው ህዝብ አላማውን ሳያመቻምች፥ ጥቅሙን አሳልፎ ሳይሰጥ ከሌሎች የሩቅና የቅርብ ኃይሎች ጋር ቢተባበርም ተፈጥሯዊ ነው።የእሳት ባህር ውስጥ የተጣለ ህዝብ ነዶ ከማለቅ እስካዳነው ድረስ የትኛውንም አይነት እርምጃ ቢወስድም ሁሌም ልክ ነው።ዘራችን ከስብእና ካርታ ላይ ሊሰርዝ በምድርና በሰማይ የዘመተ ጠላታችን ከማን መቆም እንዳለብንና እንደሌለበን፥ ወዳጅና ጠላት ሊመርጥልን አይችልም።
✅መብት!
እንደ ህዝብ ከማን ጋር መስራት እንዳለብን በጥንቃቄ አስልቶ የመወሰን፥ አቅሙም መብቱም አለን።
ማንም ርእዮተዓለም ጽፎ ሰጦን፥ የፖለቲካ ፕሮግራም አስጠንቶን ወደ ትግል አልገባንም። ዘመኑን ዋጅተን የነቃንም፥ ያነቃንም፥ የተደራጀንም፥ ያደራጀንም፥ የታጠቅንም ያስታጠቅንም እኛው ራሳችን ነን። የጠላትን አከርካሪ የሰበርነው አንድ ዲሽቃ አምስት ሚሊዬን ፥ አንድ የዲሽቃ ጥይት አምስት መቶ ብር ገዝተን ነው።
✅ግዴታ!
ያም ሆኖ ወደ ዋናው ጠላታችን ጠጠር ከሚወረውር ጋር ሁሉ ተባብሮና አስተባብሮ የማዝመትና የመዝመት ፥ ግብን የመምታት ታሪካዊ ኃላፊነትና ግዴታም አለብን።
በጠላቶቻቸው እጅ ወድቀው ወደ ኦሽዊትዝ የመታረጃ ጉረኖ የሚነዱ አይሁዳውያን ድንገት ቅጽበታዊ እድል አግኝተው መሳሪያ አንስተው ቢፋለሙ ነውር ነበርን? አይደለም። ከኦሽዊትዝ በተአምር የተረፈ ይሁዲ ጠብመንጃ አንስቶ ጠላቶቹ ላይ ቢተኩስ ነውር ነበርን? አይደለም!
በኦሽዊትዝ ካምፕ ውስጥ አንድ ሚሊዮን አንድ መቶ ሺህ(1100000) ገደማ ንፁሐን በናዚዎች እጅ አልቀዋል።
ከእነዚህ ውስጥ፦
➡️አይሁዶች=አንድ ሚሊዮን(1000000) ገደማ
➡️ሮማዎችና ሲንቲዎች=21000 ገደማ
➡️አይሁድ ያልሆኑ ፖሊሾች=75000 ገደማ
➡️የሶቭየት የጦር እስረኞች=15000 ገደማ
➡️ፈረንሳዮች፥ ቸኮች፥ ኦስትሪያዎች፥ ቤላሩሳውያንና ሌሎች=12000 ገደማ
እና እነዚህ ሁሉ ወገኖች ተባብረው ናዚን ቢያስወግዱ ነውር ይሆን ነበርን? ኃያላን ተባብረው ሂትለርን ማስወገዳቸውስ ነውር ሆነ? በፍፁም አይደለም፥ አልሆነም።
የኛዎቹ አብይ መራሽ ጥቁር ናዚዎች በዓለም ፊት የአማራ ህዝብ ላይ የዘር ፍጅት እየፈፀሙ ባሉበት፥ኢትዮጵያን ህምጥ ይሁን ስምጥ ሊከቷት እየተንደረደሩ በሚገኙበት በዚህ ወቅት ምን ያስጮሃቸዋል ከተባለ መልሱ ፍርሐት ነው። ጭንቀት ነው። ግራ መጋባት ነው።ምሕረት አልባው የታሪክ ማዕበል በራቸው ላይ መድረሱን ሲረዱ የሚያሳዩት መወራጨት ነው።
በዚህ ሁሉ መካከል ታዲያ ወገን መወናበድ የለበትም።
ባንዳ ለአረብ ኢሚሬት በወርቅ ቆፋሪ ሎሌነት ተቀጥሮ፥ አካፋና ዶማ ተሸክሞ ከሱዳን እስከ ኢትዮጲያ ሸለቆዎች እያላበው ሲዞር የሚውለው አብይ እንጅ ሌላ ማንም ግለሰብ አይደለም።
ባእዳ የራሱን ህዝብ በጅምላ የሚፈጀው፥ የራሱ ክልል ላይ የእጅ አዙር ጦርነት የከፈተው አብይ አህመድ እንጅ ሌላ አካል አይደለም። ባዳ እንጀራውንም የእንጀራ እናቱንም ከዱባይ ያገኘው ኮሎኔል አብይ አህመድ እንጅ ከቶ ሌላ ሰው አይደለም።
ባንዳና ባዳ ሃገሩን ምርት ገበያ ድርጅት አውጥቶ በጥቂት ፈረሱላ ቡና ዋጋ የሸጠው አብይ አህመድ ነው።
ባንዳና ባዳ የበቀለበት አፈር፥ ያደገበት መንደር፥ ያሳደገው ህዝብ ላይ በአንዳች የአስተዳደግ ስብራት ምክንያት አንዳች አይነት ጥላቻ ያዳበረና የበቀል እብደት ውስጥ ያለው፥የራሱን ስጋ ቀቅሎ የሚበላው አብይ አህመድ ነው።
እንኳን የዳንኤል ክብረት የቃል መቁንን የቱርክ ድሮን ከውድቀት አያድንም። ሂትለር በጆሴ ጎብልስ ፕሮፓጋንዳ እንዳልዳነው ሁሉ አብይም በዳንኤል ክብረት ቅጥፈት አይድንም።
በመጨረሻም ማዕበሉ ወደ ጓዳ ሲገባ የናዚ ፓርቲ መሪ ሂትለር ራሱን ገደለ፥ የናዚው የፕሮፓጋንዳ አለቃ ፓውል ጆሴፍ ጎብልስ ስድስት ልጆቹን ገድሎ ሲያበቃ ከነ ሚስቱና ቅጥፈቱ ራሱን አጠፋ። አብይና ዳንኤልስ?
እድሜ ይስጠን!!
ቅንነት የአዲሰ ትውልድ የአመራርም የመኖርም ፍልስፍና ነው!
አንድ አማራ እስከ ምፅዓተ አማራ!
ክፋት ለማንም በጎነት ለሁሉም!
አርበኛ ዘመነ ካሴ
የአንሻ ክፍለ ጦር አብሪ ፋኖዎች የጥላት ሰራዊትን እንቅስቃሴ በመከታተል በፈፀሙበት የደፈጣ ጥቃት እርስ በርሱ ጭምር ተታኩሶ ከባድ ሰብዓዊ ኪሳራ ደረሰበት::
ከፍላቂት ተንቀሳቅሶ ጥቃት ፈፅሞ ሊመለስ አስቦ በነበረው የጥላት ሰራዊት ላይ ባላሰቡት ሁኔታ የአንሻ ክፍለ ጦር ቃኞች በመከሰት የፋሽስቱን ሰራዊት ሙትና ቁስለኛ አድርገውታል። በዚሁም ጥቃት አንድ ጓድ ጠላት የብርሃኑ ጁላ ወታደሮች ሙትና ከባድ ቁስለኛ ሆነዋል::
የፋሽስቱ ሰራዊት ወደ ምሽጉ ከተመለሰም በኋላ በተሰነዘረባቸው ቅስፈታዊ ጥቃት የተነሳና መረጃ አላደረሳችሁንም በሚል ምክንያት አለመተማመን በመፈጠሩ የአረጋ ከበደ ወታደሮች ከሽመልስ ከብርሃኑ ጁላ ሰራዊት ጋር እርስ በርስ እስከ መታኮስ ደርሰው ሰብዓዊ ጉዳት መድረሱን ለማረጋገጥ ችለናል::
መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልዉና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል!
ህልዉናችን በተባበረ ክንዳችን!
አፋብኃ ምኒልክ ዕዝ የደጋው መብረቅ ኮር
ህ/ግንኙነት መምሪያ
ታህሳስ 16/2018 ዓ.ም
ከአፋብኃ ምዕራብ አማራ ቀጠና ቴወድሮስ ዕዝ 105ኛ ኮር 44ኛ ክፍለ ጦር የተላለፈ ጥብቅ ማስጠንቀቂያ‼
የአማራን ትጥቅ በሃይል አስፈታለሁ በሚል ቀቢጠ ተስፋ ወደ ክልሉ የገባዉ የብልጽግና ሃይል ትጥቅ የማስፈታት እቅዱ ሁሉ ከሽፎበት በተቃራኒዉ ወደ ክልሉ ይዞት የገባዉን ከነፍስ ወከፍ እስከ ቡድን መሳሪያዎች ድረስ የአማራ ህዝብ የቁርጥ ቀን ልጅ በሆነዉ ፋኖ እየተማረከና እያስታጠቀን ይገኛል።
ይሁን እንጅ ጥቁር መሳሪያን ጨምሮ በምርኮ ያጣቸዉን በርካታ ዘመናዊ መሳሪያዎችና የግልም ይሁን የድርጅት ትጥቆችን ከፍተኛ ገንዘብ በመመደብ ባሰማራቸዉ ጥቅመኛ ኮንትሮባንዲስቶች አማካኝነት ግዥ እየፈጸመና የጦር መሳሪያዎችን በመሰብሰብ ላይ እንደሆነ ለማወቅ ችለናል።
ስለሆነም ይህ የማስጠንቀቂያ መልክት ከተሰጠበት ከ17/04/2018 ዓ.ም ጀምሮ
1. ማንኛዉም የድርጅታችን አመራርም ይሁን አባላት ከድርጅቱ እዉቅና እና ፈቃድ ዉጭ የጦር መሳሪያ መሸጥ መለወጥ አይቻልም።
2. ድርጅታችን እዉቅና እና ፈቃድ ከሚሰጣቸዉ ግለሰቦች ዉጭ ማንኛዉም የጦር መሳሪያ ዝዉዉር ስራ ላይ በመሰማራት የስርዓቱ ተባባሪ ሆኖ ግዥ ወይም ሽያጭ ሲፈፅም የተገኘ አካል ድርጅቱ እርምጃ ይወስዳል።
ማሳሰቢያ፦
1ኛ ሁሉም የክ/ጦሩ አባላትና አመራሮች ክፍለ ጦሩ በሚንቀሳቀስባቸው ሁሉም ቀጠናዎች አስፈላጊዉን ሁሉ ክትትል በማድረግ በዚህ ድርጊት የተሰማሩ አካላት ላይ እርምጃ እንድትወስዱ በጥብቅ እናሳስባለን።
2ኛ መላው አቃፊና ደጋፊ ህዝባችን በሙሉ ይህን መሰል እንቅስቃሴ የሚያደርጉ አካላትንና ድርጊቱ በተፈፀመበት ጊዜ መረጃውን እንድታደርሱን እናሳስብለን።
አዲስ ትዉልድ፣ አዲስ አስተሳስብ፣አዲስ ተስፋ
ከአፋብኃ ምዕራብ አማራ ቀጠና ቴወድሮስ ዕዝ 105ኛ ኮር 44ኛ ክፍለ ጦር
ከአፋብኃ ምዕራብ አማራ ቀጠና ቴወድሮስ ዕዝ 105ኛ ኮር 44ኛ ክፍለ ጦር የተላለፈ ጥብቅ ማስጠንቀቂያ‼
የአማራን ትጥቅ በሃይል አስፈታለሁ በሚል ቀቢጠ ተስፋ ወደ ክልሉ የገባዉ የብልጽግና ሃይል ትጥቅ የማስፈታት እቅዱ ሁሉ ከሽፎበት በተቃራኒዉ ወደ ክልሉ ይዞት የገባዉን ከነፍስ ወከፍ እስከ ቡድን መሳሪያዎች ድረስ የአማራ ህዝብ የቁርጥ ቀን ልጅ በሆነዉ ፋኖ እየተማረከና እያስታጠቀን ይገኛል።
ይሁን እንጅ ጥቁር መሳሪያን ጨምሮ በምርኮ ያጣቸዉን በርካታ ዘመናዊ መሳሪያዎችና የግልም ይሁን የድርጅት ትጥቆችን ከፍተኛ ገንዘብ በመመደብ ባሰማራቸዉ ጥቅመኛ ኮንትሮባንዲስቶች አማካኝነት ግዥ እየፈጸመና የጦር መሳሪያዎችን በመሰብሰብ ላይ እንደሆነ ለማወቅ ችለናል።
ስለሆነም ይህ የማስጠንቀቂያ መልክት ከተሰጠበት ከ17/04/2018 ዓ.ም ጀምሮ
1. ማንኛዉም የድርጅታችን አመራርም ይሁን አባላት ከድርጅቱ እዉቅና እና ፈቃድ ዉጭ የጦር መሳሪያ መሸጥ መለወጥ አይቻልም።
2. ድርጅታችን እዉቅና እና ፈቃድ ከሚሰጣቸዉ ግለሰቦች ዉጭ ማንኛዉም የጦር መሳሪያ ዝዉዉር ስራ ላይ በመሰማራት የስርዓቱ ተባባሪ ሆኖ ግዥ ወይም ሽያጭ ሲፈፅም የተገኘ አካል ድርጅቱ እርምጃ ይወስዳል።
ማሳሰቢያ፦
1ኛ ሁሉም የክ/ጦሩ አባላትና አመራሮች ክፍለ ጦሩ በሚንቀሳቀስባቸው ሁሉም ቀጠናዎች አስፈላጊዉን ሁሉ ክትትል በማድረግ በዚህ ድርጊት የተሰማሩ አካላት ላይ እርምጃ እንድትወስዱ በጥብቅ እናሳስባለን።
2ኛ መላው አቃፊና ደጋፊ ህዝባችን በሙሉ ይህን መሰል እንቅስቃሴ የሚያደርጉ አካላትንና ድርጊቱ በተፈፀመበት ጊዜ መረጃውን እንድታደርሱን እናሳስብለን።
አዲስ ትዉልድ፣ አዲስ አስተሳስብ፣አዲስ ተስፋ
ከአፋብኃ ምዕራብ አማራ ቀጠና ቴወድሮስ ዕዝ 105ኛ ኮር 44ኛ ክፍለ ጦር
