ru
Feedback

Не попадитесь на канал ботавода! Telemetrio находит и помечает такие каналы 👉 Хотите видеть метку — оформите подписку 👈

ፍኖተ-አሻራ ሚዲያ (Finote Ashara Media)

ፍኖተ-አሻራ ሚዲያ (Finote Ashara Media)

Открыть в Telegram

የተመሠረተው የአማራን ሕዝብ ለማንቃት፣ ለማደራጀት እና ለማስተባበር ነው። የአማራ ሕዝብን ✅ ፖለቲካዊ ✅ ማህበራዊ ✅ ኢኮኖሚያዊ ታሪካዊ ጥያቄዎችን ለማሰማት እና የአማራን ሕዝብ በማንቃት ሰፊውን ሕዝብ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ይሰራል። ወደዱም ጠሉም የኃላ ታሪካችን በእኛ እጅ ይፃፋል። አማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ ( አፋብን)

Больше
4 061
Подписчики
+224 часа
+4287 дней
+1 25730 дней
Архив постов
እጅ ስለሰጡት ሳይሆን ጠላትን ስለምንበቀልበት የክብር ትግል ላይ ነን!! የአንበሳው ጋይት ክፍለ ጦር ክንዳለም ሻለቃ ዋና ፊታውራሪ የአባቱ ምትክ የሆነው ክንደ ነበልባሉ አንደበት ክንዳለም ጋይንት ላ
እጅ ስለሰጡት ሳይሆን ጠላትን ስለምንበቀልበት የክብር ትግል ላይ ነን!! የአንበሳው ጋይት ክፍለ ጦር ክንዳለም ሻለቃ ዋና ፊታውራሪ የአባቱ ምትክ የሆነው ክንደ ነበልባሉ አንደበት ክንዳለም ጋይንት ላይ የማን ልጅ እንደሆነ በእጅ ሰጭዎችና በታጋዬች መካከል ያለውን ልዩነት ጠላትን ማርኮ አሳይቷል። ቃል የእምነት እዳ ነው። ትናት በደም በአጥንታቸው ውዱን ዋጋ ከፍለው የማረኩትን ዲሽቃ መልሰው ለጠላቶቻችን ሲያስረክቡ የአባቱ ልጅ ጠላትን አራግፎ የያዘውን ትጥቅ ተቀብሎታል። ትናንት ጥር 15/2018 ዓ.ምን ከቀኑ 7:00 ጀምሮ እስከ 9:00 ሰዓት ከጥጥራ እስከ ዳሞት በእንቅስቃሴ ላይ የነበረን የጠላት በኃይል፦ ## 9 ሙት ## 15 ከባድና ቀላል ቁስለኛ ሲያደርገው ## 6 የክላሽ ትጥቅ ከጠላት ተረክቧቸዋል። በሌላኛው አውደ ውጊያ ከክምር ድንጋይ ወደ አጃ ሬሽን ጭኖ በእንቅስቃሴ ላይ የነበረ የብልጽግናው ወንበር አስጠባቂ ሚሊሻ፣መከላከያና ፖሊስ በተራራው ራስ ጉና ክፍለ ጦር አናብስቶች ውቅሮ መድሃኒያለም ላይ ከፍተኛ ሙትና ቁኛ አድርገውታል። ዛሬም ጀግና እማያልቅበት ምድር አንገቱን ከፍ እሚያደርግባቸው ልጆቹ እንዳሉ ምስክር ነው። ሌላው ደግሞ በጀግኖቹ ሲምልና ሲገዘት የሚዉለው የትግል ሾተላይ መሰሪው ቡድን እጁን አንከርፍፎ ጀግና የማረከውን ዲሽቃና እስናፐር ሲያስረክብ እንዲህ ያባቶቹን አደራ የማይበላ እንቁ አማራ ሜዳው ላይ አለ። አማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ (አፋብን) ጎንደር ዕዝ 206ኛ ከፉያለው ደሴ ኮር ህዝብ ግንኙነት ክፍል አላፊ አርበኛ

የፋኖን አንድነት ተከትሎ ከስምሪት ቀጠናቸው በመጥፋት ፋኖን የሚቀላቀሉ ወታደሮች ቁጥር ከወትሮው በተለየ ሁኔታ ጨምሯል ተባለ! ወታደሮቹ በጉጉት ሲጠብቁት የነበረው የፋኖ አንድነት መበሰሩን ተከትሎ፡
የፋኖን አንድነት ተከትሎ ከስምሪት ቀጠናቸው በመጥፋት ፋኖን የሚቀላቀሉ ወታደሮች ቁጥር ከወትሮው በተለየ ሁኔታ ጨምሯል ተባለ! ወታደሮቹ በጉጉት ሲጠብቁት የነበረው የፋኖ አንድነት መበሰሩን ተከትሎ፡ ጨርቄን ማቄን ሳይሉ ከቡድን መሣሪያ ብሬንና ስናይፐር ጀምሮ ሙሉ ትጥቃቸውን እንደያዙ ፋኖን በገፍ እየተቀላቀሉ መሆኑን መረብ ሚዲያ ካሰባሰበው መረጃ ለማረጋገጥ ችሏል። ይህ ጉዳይም በአገዛዙ ቤት ከባድ ሽብርና ድንጋጤን የፈጠረ ሲሆን፡ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ባለቤታቸው ዝናሽ ታያቸውን በአንድ ግንባር፡ የስድብ አማካሪው አቶ ዳንኤል ክብረትን በሌላኛው ግንባር፡ እንዲሁም ሌሎች ምንጣፍ ጎታቾቻቸውን በቀሪው ግንባር አሰልፈው ይዋጉ ካልሆነ በስተቀር ወታደሩስ "ማን ሞቶ የማን ስልጣን ሊቀጥል" በሚል ልክ እንደ እምቧይ ካብ እየተናደ አልቋል።

ጥር 15/ 2018 ዓ.ም ከእኔ ከፋኖ ትልቅአለም አሳብ ለአቶ ዋለ አባተ ለምስራቅ ጎጃም ምክትል አስተዳዳሪ የተሰጠ ይፋዊ ምላሽ። በቀደሙ ጥቂት ቀናት በፊት አስጨነቅ ታደለ ጀግኖች ተናንቀው ጀብድ ሰርተው መስዋትነት በከፈሉበት ባሶሊበን፣ ሰራዊታችን ሲፋለሙባቸው የነበሩ ዲሽቃዎችን ይዞ በመጥፋት እርምጃ ሊወሰድበት ሲል ለጠላት እጅ ሰጦ የአማራ ህዝብንና ህይወታቸውን ገብረው ይህን ትግል አደራ የሰጡ ጓዶችን መክዳቱ እንዳበሳጨኝ የማልደብቀው ሀቅ ነው። በሴት ተደልሎ 14 ንፁህ ታጋዮችን በተኙበት አስከብቦ በጉያችሁ የወደቀው ባንዳ አስክሮህ ለእኔ ለፋኖ ትልቅአለም በwhatsapp ቁጥሬ የአማራን ህዝብ ብሎም በየ በረሀው ተንከራትቸ ያደራጀውትን ሰራዊት በአማራ ምድር ሁሉ በዚህ የህልውና ትግል የተሰው ወንድሞቸን ደም እረግጨ እጅ እንድሰጥ የላክልኝ መልዕክት እንድበቀልህ የሚያነሳሳኝ እንጂ ንፁሀንን ስታስጨፈጭፍ ለነበረው ለአንተ፣ እናቶችን ፣ ሴቶችንና ህፃናትን በጅምላ የሚደፍረውን ሰራዊት አሰማርተህ በወገኖቸ ላይ ታሪክ ይቅር የማይለውን በደል ለፈፀምከው ለአንተ፣ አረመኔ የሆነ ሰራዊት በራስህ ህዝብ ላይ አዝምተህ ምድሪቱን በደም ለአጨቀየህው ለአንተ፣ ለጌታህ ለአብይ አህመድ ታምነህ የራስህን ወንድም ሰውነቱን ቆራርጠህ ተማኝነትህን ላረጋገጥ ጨካኝ። ሺዎችን በማጎሪያ አሰቃይተህ ገላቸው በድን እስኪሆን ላሰቃየሀቸው ባንዳ፣ ህፃናት በሚቦርቁበት መንደር ፣ ቀሳውስት በሚቀድሱበት ደብር፣ ገበሬዎች በእርሻ መሬታቸው፣ እናቶች በጓዳቸው በድሮን ለአስጨፈጨፋካቸው ጥቁር ሂትለር፣ ህፃናትን ያለ ወላጅ ሴቶችን ያለ ባል አስቀርተህ ጎዳና ለአነጠፍካቸው መርዝ በጥባጭ እጀን አንከርፍፌ ወንድነቴን አጥቸ እጅ የምሰጥ የበላይ ልጅ አይደለሁም። ምናልባት አንተ አታውቀኝ ይሆናልና ብትደፍረኝ አይገርመኝም ማነህ ቢሉህ እኔ የማትለው ዋለ አባተ ሆይ! እኔ ትልቅ እባላለሁ ስለኔ አጠገብህ ያለውን ጀነራል ብርሀኑ ጥላሁን አሊያም ሶፊያ መሐመድን ጠይቅ ወይንም ኮማደር ግርማንም ማነው ብለህ ጠይቀው ። ክንዴንም አፈሙዜንም እነሱ በደንብ ያውቁታል በየ ጁቤ ምድር በባሶሊበን አፈር ስንት ሰራዊታቸውን ቀብረዋል ስንቶችን አንገቱን ቀልተን ለሞራ ቀለብ አድርገናቸዋል። ታጠቅነውን ብሬን ያነገብነው ስናይፐር ከመንጋጋቸው ፈልቅቀን የማረክነው ነው እኛ ነን። ምነው ዘነጋሀው ዉሎ አዳርህን እይ ስትፍረከረክ የምትውል በታክም በመድፍም ተከበህ የምትቃዥ እኛኑ ፈርተህ መግቢያ መውጫ አጠህ መሆኑንም አስታውስ። በሁለት ሚኒሽር የጀመርነው ትግል ዛሬ ሚሊዮኖቹን አፍርቷል! ጉዳዮ የአላማ ነው። አላማችንን ነፍስና ስግችን አድርገን መስዋትነት የምንከፍለው የአማራን ህዝብ ከጋረጣችሁበት የህልውና አደጋ አውጥተን ወደነበረበት ክብሩ ከፍ ለማድረግ እንጅ ኩሽና ተደብቆ ለሚውል ካድሪ እጅ ሰጠን ትውልድ የሚስቅብን ፈሪዎች ለመሆን አይደለም። እኛ መከራ ያልበገረን፣ በሞት ጥላ ውስጥ እያለፍን ለህዝባችንና ለተቀበልነው አደራ ታምነን የምንታገል የበላይ ዘለቀ ልጆች እንጅ እንደ ይሁዳ በሽልንግ የምንሸጠው ትግል የተሰው ጓዶች አደራ የለም። አቶ ዋለ አባተ ለአንተ በመጨረሻ ይህንን እወቅ ፣ ከእኛ ጥይት አታመልጥም ተደብቀህ የምታሳልፈው ማዕበልም የለም ወደ መቀመቁ ይዘንህ እንወርዳለን የሚመጣውን እልቂት አንተ ከአለፍከው እኛ ባንወለድ እንመርጣለን እመነኝ እንገልሀለን ሰራዊትህም ካድሪህም አይኖርም። እኔም ለአላማየ የምታገል ለአማራነቴና ለክብሬ የምሰዋ ግንባር ቀደም ታጋይ ነኝ ብወድቅ ወደኋላ ሳይመለስ ጉሮሮህን የሚያንቅ ሰራዊት ይየ ከፊት እቆማለሁ ቀናትን ብቻ ጠብቀኝ። ለመላ ሰራዊታችን እና ለባሶሊበን ወረዳ ለመላው የአማራ ህዝብ ፣ በተፈፀመብን ክህደት ፈፅሞም ከአላማችን ፈቀቅ እንደማንል እያረጋገጥኩ በባንዳዎችና በዳካማ ጠላታችን ላይ ለምናደርገው ትንቅንቅ በቁጭትና በወኔ ጠላትን ድባቅ ለመምታት እንድትረባረቡ አሳስባለሁ። አዲስ ትውልድ! አዲስ አስተሳሰብ! አዲስ ተስፋ አርበኛ ትልቅ አለም ከአፋብን ቴዎድሮስ ዕዝ 206ኛ ኮር 34ኛ ክ/ጦር ባሶሊበን

#የሜጀር_ጀኔራል_ዉባንተ_አባተ_የአብራክ_ክፋይ ተመስገን ዉባንተ እና ደረበ መኮነን በላይ ዘለቀ ዕዝ ዉባንተ አባተ ኮር ተወርዋሪ ክ/ጦር አዛዥ ተመስገን ዉባንተ እና የሚኒልክ ዕዝ ሚዲያ እና ኮሚኒኬ
#የሜጀር_ጀኔራል_ዉባንተ_አባተ_የአብራክ_ክፋይ ተመስገን ዉባንተ እና ደረበ መኮነን በላይ ዘለቀ ዕዝ ዉባንተ አባተ ኮር ተወርዋሪ ክ/ጦር አዛዥ ተመስገን ዉባንተ እና የሚኒልክ ዕዝ ሚዲያ እና ኮሚኒኬሽን መምሪያ ኃላፊ አርበኛ ደረበ መኮነን

የአገዛዙ አሸርጋጅ ቡጅሌ እና ሰራዊቱ ክፉኛ ሽንፈትን አስተናገዱ!!! በትናንትናው እለት ጥር15 /2018 የጠላት ሀይል መነሻውን ማእከላዊ ጎንደር አለፋ ወረዳ አፀደማርያም ከተማ በማድረግ ወደ ችማ ለምበዝ ቀበሌ ሚኒሻ እና ፋሽስታዊው የአገዛዙ ሰራዊት በመሆን የአርሶአደሩን ትጥቅ ለማስፈታትና ለመዝረፍ አቅደው ወደ ቀጠናው መግባት ቢችሉም ከአድዋ ክ/ጦ አሀድ ተመርጠው ወደ ቀጠናው በተላኩ የፋኖ ሀይሎች  ቀድሞ መረጃውን በመከታተል ሚኒሻው ወደ አርሶአደሩ ቤት ፍተሻ ለማድረግ እየተንቀሳቀሰ ባለበት ስአት ከፊት ለፊት መከላከያውን በመግጠም  እና ቆራጭ ሀይል  በማስገባት ለመዝረፍ  የገባውን ሚኒሻ  እቅዱን ከማክሸፍ ባሻገር ሙትና ቁስለኛ ሆኖ እግሬ አውጭኝን ፈርጥጦ ወደ መጣበት ተመልሷል። ይሄን ስምሪት በማስተባበር ላይ የነበረው ዋሴ የተባለው ጅብ የስርአቱ ተላላኪ ቤተክርስትያን ገብቶ የካህናትን አልባሳት ለብሶ እንዳመለጠ የውስጥ መረጃዎቻችን አድርሰውናል። በዚህ መብረቃዊ ጥቃት ጠላት የደረሰበት ኪሳራ:        7 እስከ ወዲያኛው የተሰናበተ       3 ከባድ ቁስለኛ ቀኑን በሙሉ ከባድ መሳሪያ በመተኮስና በቁጥር በርካታ ሀይል በማስገባት ሙት እና ቁስለኛውን ይዞ ወደ መጣበት ጉድጓድ ተመልሶ ገብቷል። ይህ በእንዲህ አንዳለ የስርአቱ አስፈፃሚ አመራሮች እና ጥምር ሰራዊቱ በህዝባችን ላይ  ፀያፍ ተግባራትንና ጀኖሳይድን ከመፈፀም ባሻገር  በአርሶ አደሩ ላብ ለመክበርና የስጋ ፍላጎታቸውን ለማሟላት ውድድር ላይ ስለሚገኙ የአማራ ህዝብ እና ሰው የሆነ ሁሉ በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ አንዲታገላቸው መልእክታችን ነው። ኅልውናችን በተባበረ ክንዳችን!!! አፋብኃ ሰሜን አማራ ቀጠና በላይ ዘለቀ ዕዝ መይሳው ካሳ ፪ኛ ኮር የህ/ግ ፋኖ መ/ር አስተዉል አምሳሉ   ጥር 15/2018 ዓ.ም

፩ አላማ፤ ፩ ድርጅት፤ ፩ ዓምሐራ🔑✊ እኛ ዓምሐሮች ለትግላችን እሥከጠቀመን ድረሥ ከምንፈልገው አካል ጋር ተገናኝቶ ለመሥራት የማንንም ፈቃድ አንጠይቅም። ለትግላችን እሥከጠቀመን ድረሥ ከሰይጣንም ጋር እናብራለን። በእኛ ላይ ከልካይውም ሆነ ፈቃጁ እኛው ራሳችን የዓምሐራ ፋኖዎች ነን። ነጻነት ይጠየቃል እንጅ አይለመንም ነውና የዓምሐራ ብሒሉ❗ ዓምሐራ ምርጫው አንድ መሆን ነው። ይህ ማለት ከአጥፊ ቁማር የፀዳ ዓምሐራዊ አንድነት ያሥፈልጋል ማለት ነው። የትኛውም አካል ከትግላችን በታች እንደሆነ የሚያምን አንዳዊ የዓምሐራ ትግልን ማራመድ ውዴታ ሳይሆን ግዴታ ነው። በአንድ አላማ፤ በአንድ መዋቅር ጎጠኛን ማሽቀንጠር ፀረ ዓምሐራን መመንጠር አንድ ያልሆነ አንድነትን ማባረር ውሉደ ፋፍን ወደ እንጦሮጦሥ መወርወር በዓምሐራነት ማማር🔑 ዝንተዓለም ዓምሐራ Forever AMHARA🔑 ዘረ ውባንተ አባተ[ፈለገ ውባንተ አባተ] ፋኖ ኃቅ-ዓለው ፀጋ ዘ ብሔረ ዓምሐራ N.B ልዩ ማሥታወሻ፦ ✔ጥቁር ጣልያናዊነት፣ ወዶ ገብነት፣ ባሪያነት፣ ባንዳነት እና ፀረ ዓምሐራነት ማንን ይመሥላል ቢሉ የዳውንት ቁጥቋጦ ሥር ቁማርተኛ ተደራዳሪዎችን ይመሥላል ነው መልሱ። ✔የዳውንት ቁጥቋጦ ሥር ቁማርተኞች የገቡት ብቻ ሳይሆን ያልገቡትም የአማራ ሕዝብን ትግል ወደኋላ የጎተቱና የጫካው ብአዴን ጭምብል አጥላቂ የእንግዴ ልጆች ናቸውና ምሽግ ሰርቶ መደበቅ ከወንጀለኞቹ በላይ ወንጀለኛ መሆን ነው። ለፋሕፍዴን ጥብቅና የሚቆም ቁ #1 ፋሕፍዴን ነውና እርሱ ከእኛ ዘንድ አይደለም። መሥዋዕትነትን በከፈለ አንገተ ቅጥል ወንድሞቻችን ደም የምትቀልዱ ሁሉ አድቡ። ✔ለትግል ጠላፊውና ተቋም አፍራሹ ቅጥ-እረኛ ኃብታሙ አያሌውና መሰሎቻቸው ዓምሐሮች ቦታ የላቸውም፤ የፈለከውን ያህል አሽላላ፣አሽቃብጥ፣ ሳሙና ሁንም ምን ማንም አይሰማህም። ፈጣሪ በአካል ቢወርድ ሜ/ጀ ውባንተ አባተን ባዋከባችኹት በአንተና በመሰሎችህ ምንም ዓይነት የይቅርታ ልብ የለንም። ቋሚ ምሥል፦ ከዕውነትና ፍትሕ ውጭ የትኛውንም ጎጠኛ፣ ቁማርተኛ፣ የሥልጣን ጥመኛ፣ የአፍ አማራ የልብ ጎጠኛና በአጠቃላይ ማሥመሰልን ሕይወታቸው ያደረጉ የእንግዴ ልጆችን አምርሮ የሚጠላው እንዲሁም ዕውነተኛ ትግልን ከብርጋዴር ጀነራል አሣምነው ፅጌ፣ ከአርበኛ ባዬ ቀናው፣ ከአርበኛ አራጋው እንዳለ፣ ከአርበኛ አሥቻለው ደሤ፣ ከሜጀር ጀነራል ውባንተ አባተ፣ ከአርበኛ አሰግድ መኮንን እና ከፕሮፌሰር አሥራት ወልደየሥ የተማረው የትግሉ ባለቤት ዘረ ውባንተው/ፈለገ ውባንተው ፋኖ ኃቅ-ዓለው ዘ ብሔረ ዓምሐራ

ሶስት የአገዛዙ ሰራዊት አባላቶች ባለ ሽርጡ ክፍለ ጦርን ተቀላቀሉ:: በሰሜን ወሎ ዞን ሀብሩ ወረዳ በጊራና መሽጎ የሚገኘው የአብይ አህመድ ዙፋን ጠባቂ ሰራዊት እየፈረሰ ፋኖን እየተቀላቀለ ይገኛል::
+1
ሶስት የአገዛዙ ሰራዊት አባላቶች ባለ ሽርጡ ክፍለ ጦርን ተቀላቀሉ:: በሰሜን ወሎ ዞን ሀብሩ ወረዳ በጊራና መሽጎ የሚገኘው የአብይ አህመድ ዙፋን ጠባቂ ሰራዊት እየፈረሰ ፋኖን እየተቀላቀለ ይገኛል:: የ35ኛ ክፍለ ጦር እንደጉም ተበትና አልቃለች። ከተለያዩ አሀዶች አውጣቶ ኮማንዶዎች ቢያመጣም ከወንድሞቻችን ጋር አንዋጋም ብለው ሶስት የሰራዊቱ አባላቶች ከነ ሙሉ ትጥቃቸው ምኒልክ ዕዝ ምስራቅ አማራ ኮር 1 ባለሽርጡ ክፍለ ጦር ጋር በሰላም ተገናኝተዋል። መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልዉና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል! ህልዉናችን በተባበረ ክንዳችን! የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ (አፋብን) ምኒልክ ዕዝ ጥር 15/2018 ዓ.ም

ልባዊ ጥምረት፣ ወንድማዊ አንድነት!...የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ‼️ በላይ ዘለቀ ዕዝ እና ሚኒልክ ዕዝ በጋራ በመሆን በአገዛዙ ሰራዊት ላይ የማያዳግም እርምጃ በመዉሰድ ድል ተጎናፀፉ። አፋብን ምስራቅ አማራ ቀጠና ሚኒልክ ዕዝ ላስታ አሳምነዉ ኮር ነብሮ ተወርዋሪ ኮማንዶ ብርጌድ እና በላይ ዘለቀ ዕዝ ሜጀር ጀኔራል ዉባንተ አባተ ኮር በጋራ በመሆን በአገዛዙ ሰራዊት ላይ የማያዳግም እርምጃ ወስደዉበታል። ሬሽን ለመቀበል መነሻዉን ከላሊበላ ጋሸና - ከጋሸና ላሊበላ አድርጎ እየተንቀሳቀሰ የነበረዉ የአገዛዙ ሰራዊት በዛሬዉ ዕለት ማለትም በ ቀን 15/2018 ዓ.ም ከንጋቱ 1:00 -10:00 ሲቀጠቀጥ የዋለ ሲሆን ከወደ ጋሻና የመጣዉን ግትልትል ሰራዊት በነብሮ ኮማንዶ ብርጌድ በተለምዶ እንኳይ በር ላይ ሲያረግፉት የዋሉ ሲሆን ከወደ ላሊበላ የመጣዉን የአገዛዙ ሰራዊትን ደግሞ የዉባንተ አባተ ግስላወች በተለምዶ ቆጋ ተብሎ ከሚጠራዉ ቦታ ላይ ጠቁር አስፖልቱን ግጥም አድርገዉ ዘግተዉ ሲወቁት ዉለዋል። በዚህም ዉጊያ ላይ ብዛት ያለዉ የአብይ አህመድ ወንበር አስጠባቂ ሰራዊት ሙት እና ቁስለኛ የሆነ ሲሆን ብዛት ያላቸዉ መሳሪያዎች እና ተተኳሾችም ተማርከዋል። የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል ምስራቅ አማራ ቀጠና ሚኒሊክ ዕዝ ሚዲያ እና ኮሚኒኬሽን መምሪያ ኃላፊ አርበኛ ደረበ መኮንን! መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልዉና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል! ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን! ©አፋብኃ ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ 15/ዐ5/2018 ዓ.ም

ስምንት የብልፅግና መከላከያ ሰራዊት አባላት ካላኮርማ ክፍለ ጦርን ተቀላቀሉ:: የአማራ ህዝብ መሪ ድርጅት "አፋብን" መመስረትን ተከትሎ ስምንት የፋሽስቱ ብልፅግና አገዛዝ መከላከያ ሰራዊት አባላት ም
+1
ስምንት የብልፅግና መከላከያ ሰራዊት አባላት ካላኮርማ ክፍለ ጦርን ተቀላቀሉ:: የአማራ ህዝብ መሪ ድርጅት "አፋብን" መመስረትን ተከትሎ ስምንት የፋሽስቱ ብልፅግና አገዛዝ መከላከያ ሰራዊት አባላት ምኒልክ ዕዝ ምስራቅ አማራ ኮር 2 ካላኮርማ ክፍለ ጦርን ተቀላቅለዋል:: የክፍለ ጦሩ አመራሮችም አቀባበል አድርገውላቸዋል:: የፋኖን አንድ መሆንና የመሪ ድርጅቱ አፋብን መመስረትን ተከትሎ የፋሽስቱ አገዛዝ ዙፋን ጠባቂ ሰራዊት በሰፊው ፋኖን እየተቀላቀሉ ሲሆን ስምንት አባላቶቹ ሰባት ክላሽ፣ 1400 ተተኳሽ፣ ሰባት የወገብ ትጥቅና ስድስት F1 ቦምብ ይዘው ካላኮርማ ክፍለ ጦርን ተቀላቅለዋል:: መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልዉና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል! ህልዉናችን በተባበረ ክንዳችን! የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ (አፋብን) ምኒልክ ዕዝ ጥር 15/2018 ዓ.ም

የፋሽስቱ አገዛዝ ብልፅግና መከላከያ ሰራዊት 203ኛ ኮር ከፍተኛ አመራር ኮሎኔል ገዳሙን አጃቢ ጨምሮ አራት አባላቶች ምኒልክ ዕዝ ልዩ ዘመቻን ተቀላቀሉ:: የብልፅግና መከላከያ ሰራዊት 203ኛ ኮር አ
+1
የፋሽስቱ አገዛዝ ብልፅግና መከላከያ ሰራዊት 203ኛ ኮር ከፍተኛ አመራር ኮሎኔል ገዳሙን አጃቢ ጨምሮ አራት አባላቶች ምኒልክ ዕዝ ልዩ ዘመቻን ተቀላቀሉ:: የብልፅግና መከላከያ ሰራዊት 203ኛ ኮር አመራር የሆነው ኮሎኔል ገዳሙ አጃቢ የኮማንዶ ጥርጥር ክላሽ በመያዝ እና 83ኛ ክፍለ ጦር ቃኝ የሆነው ሌላኛው አባል እንዲሁም ሌሎች ሁለት ሶስት ክላሽ በመያዝ ባጠቃላይ አራት የአገዛዙ ወታደሮች ምኒልክ ዕዝ ልዩ ዘመቻን ተቀላቅለዋል:: የክፍለ ጦሩ አመራሮችም አቀባበል አድርገውላቸዋል:: መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልዉና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል! ህልዉናችን በተባበረ ክንዳችን! የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ (አፋብን) ምኒልክ ዕዝ ጥር 15/2018 ዓ.ም

የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ /አፋብን/ ቴዎድሮስ ዕዝ 102ኛ ኮር 11ኛ ክ/ጦር በወሰደው ስምሪት የሻለቃ አንሙት ያዛቸው ልጆች በአዲሱ ሪፎርም መሰረት ሻለቆችን ወደ ቀደመ ቁመናቸው መመለስ ተችሏል። በዚህ መሰረት በአንዳንድ ወቅታዊ ጉዳዮች ዙሪያ በሰፊው የተወያየን ሲሆን 1.አባላትን ስለመጠርነፍና ለግድጅ ዝግጁ ስለማድረግ፣ 2.በህገ ወጥ መንገድ የማህበረሰብ በደል የሚያደርሱና የሚዘርፉ አካላት ላይ እርምጃ ስለመውሰድ፣ 3.አዲሱን ድርጅታዊ መዋቅር ስለመቀበልና ስለማስፈጸም፣ 4.ጊዚያዊ መንግቱ በአስቸኳይ ወደ ስራ የሚገባበትንና ለማህበረሰቡ ተደራሽ የሚሆንበትን በሰፊው ተወያይተን የስራ አቅጣጫ አስቀምጠናል። ድል ለአማራ ፋኖ!!! ክፋት ለማንም በጎነት ለሁሉም!!! አንድ አማራ እስከ ምጽዓት አማራ!!! አዲስ ትውልድ ፣ አዲስ አስተሳሰብ ፣ አዲስ ተስፋ!!! ©Dawit Shiferaw Takele

60 የሚሊሻ አባላት 2ብሬንና 45 ክላሽ በመያዝ ፋኖን ተቀላቀሉ። አንድነቱ በተበሰረ ማግስት በርካታ የአገዛዙ ሰራዊት አባላት እየፈራረሱ ወደ ፋኖ እየተቀላቀሉ እንደሚገኙ ይታወቃል። ይህ ብቻ ሳይሆን
+1
60 የሚሊሻ አባላት 2ብሬንና 45 ክላሽ በመያዝ ፋኖን ተቀላቀሉ። አንድነቱ በተበሰረ ማግስት በርካታ የአገዛዙ ሰራዊት አባላት እየፈራረሱ ወደ ፋኖ እየተቀላቀሉ እንደሚገኙ ይታወቃል። ይህ ብቻ ሳይሆን በተለያዩ ቀጠናዎች #ብልፅግና ሲያሳድዳቸዉ የነበሩ ኃይሎች ታጥቀዉ ራሳቸውን ከአረመኔዉ መንግስት ጥቃት ሲከላከሉ የቆዩ፣ በመተከል አዉራጃ ዳንጉር ወረዳ በሻለቃ #ሲሳይ ገነት ሲመሩ የነበሩ 60 የአገዉ ተወላጅ ወንድሞቻችን አባላትና መሪዉ ሻለቃ ሲሳይ ገነት በቀን 14/05/2018 ዓ.ም #2 ብሬን እና ከ45 በላይ ክላሽንኮቭ በመያዝ የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ ቴዎድሮስ ዕዝ 105ኛ ኮር 66ኛ ክ/ጦርን በመቀላቀል አረመኔዉን የአብይ አህመድ መንግስት ስርዓት በማዉገዝ እስከመጨረሻው ለማስወገድ ቃል መግባታቸውንም አስታዉቀዋል።

"የምዕራብ ዕዝ 401ኛ ኮር ቃኝና መሐንዲስ 4 (ጋንታ) አዛዦች 206ኛ ኮርን ተቀላቀሉ" ጥር 15/ 2018 ዓ.ም ======================== ፲ አለቃ ደርብ ምስጌ፣ ፲ አለቃ አትርሳው
+4
"የምዕራብ ዕዝ 401ኛ ኮር ቃኝና መሐንዲስ 4 (ጋንታ) አዛዦች 206ኛ ኮርን ተቀላቀሉ" ጥር 15/ 2018 ዓ.ም ======================== ፲ አለቃ ደርብ ምስጌ፣ ፲ አለቃ አትርሳው መዝገቡ ፣ ፲ አለቃ ሸጋየ ተሸገር፣ ፲ አለቃ መኳንት አዱኛ የምዕራብ ዕዝ 401ኛ ኮር ቃኝና መሐንዲስ ጋንታ አዛዦች የአማራ ፋኖ አንድነት ምስረታ በፈጠረባቸው ደስታ ከኦሮሚያ ክልል በመነሳት ቀናትን የወሰደ ጉዞ ተጉዘው 206ኛ ኮር 14ኛ ክ/ጦር አብራጅት ሻለቃን ተቀላቅለዋል። የአረመኔው ሰራዊት አባላት ሁነን በህዝባችን ላይ የሚደርሰውን ግፋና በደል ተመልክተናል ያሉት የጋንታ አዛዦች የአማራ ፋኖ አንድ አለመሆን ስርዓቱን ለቀው ትግሉን ለመቀላቀል እንቅፋት እንደሆነባቸው የተናገሩ ሲሆን ጥር ዘጠኝ የተሰማውን የአንድነት ብስራት ተከትሎ በግንባር ቀደምነት ድርጅቱን ለመቀላቀል ረጅም መንገድ በእግራችን ተጉዞን ጎጃም ገብተናል ሲሉ አክለው ገልጸዋል። የመከላከያ ሰራዊት ከተቋቋመለት አላማ በተቃራኒው በራሱ ህዝብ ላይ በመዝመት ፀረ -አማራ እንቅስቃሴ እያደረገ በመሆኑ የአብይ አህመድን የጭካኔ ተልዕኮ የተቀበሉ የአረመኔው ሰራዊት አባላት ወደ ህዝባቸው መተኮሱን አቁመው የፋኖን ትግል እንዲቀላቀሉ  አዛዦች ጥሪ አቅርበዋል። የአረመኔውን ስርዓት በተቀናጀ መልኩ እያፈረሰ የሚገኘው 206ኛ ኮር 61ኛ ክላሽ ከጠላት የተቀበለ ሲሆን የሰራዊት አባላትን የተሀድሶ ስልጠና በመስጠት ላይ ይገኛል። አዲስ ትውልድ! አዲስ አስተሳሰብ! አዲስ ተስፋ! የአፋብን ቴዎድሮስ ዕዝ 206ኛ ኮር ህዝብ ግንኙነት በአምስቱም ማዕዘን የፋኖን አውደ ውጊያዎች ከግንባር  ሁነን እየሰራን 24 ስዓት እንገኛለን ከታች ባለው ቴሌግራም ሊንክ ጆይን በማድርግ ይወዳጁን። https://t.me/httpsuYkZrGfSZrNjNjFk

"የምዕራብ ዕዝ 401ኛ ኮር ቃኝና መሐንዲስ 4 (ጋንታ) አዛዦች 206ኛ ኮርን ተቀላቀሉ" ጥር 15/ 2018 ዓ.ም ======================== ፲ አለቃ ደርብ ምስጌ፣ ፲ አለቃ አትርሳው
+1
"የምዕራብ ዕዝ 401ኛ ኮር ቃኝና መሐንዲስ 4 (ጋንታ) አዛዦች 206ኛ ኮርን ተቀላቀሉ" ጥር 15/ 2018 ዓ.ም ======================== ፲ አለቃ ደርብ ምስጌ፣ ፲ አለቃ አትርሳው መዝገቡ ፣ ፲ አለቃ ሸጋየ ተሸገር፣ ፲ አለቃ መኳንት አዱኛ የምዕራብ ዕዝ 401ኛ ኮር ቃኝና መሐንዲስ ጋንታ አዛዦች የአማራ ፋኖ አንድነት ምስረታ በፈጠረባቸው ደስታ ከኦሮሚያ ክልል በመነሳት ቀናትን የወሰደ ጉዞ ተጉዘው 206ኛ ኮር 14ኛ ክ/ጦር አብራጅት ሻለቃን ተቀላቅለዋል። የአረመኔው ሰራዊት አባላት ሁነን በህዝባችን ላይ የሚደርሰውን ግፋና በደል ተመልክተናል ያሉት የጋንታ አዛዦች የአማራ ፋኖ አንድ አለመሆን ስርዓቱን ለቀው ትግሉን ለመቀላቀል እንቅፋት እንደሆነባቸው የተናገሩ ሲሆን ጥር ዘጠኝ የተሰማውን የአንድነት ብስራት ተከትሎ በግንባር ቀደምነት ድርጅቱን ለመቀላቀል ረጅም መንገድ በእግራችን ተጉዞን ጎጃም ገብተናል ሲሉ አክለው ገልጸዋል። የመከላከያ ሰራዊት ከተቋቋመለት አላማ በተቃራኒው በራሱ ህዝብ ላይ በመዝመት ፀረ -አማራ እንቅስቃሴ እያደረገ በመሆኑ የአብይ አህመድን የጭካኔ ተልዕኮ የተቀበሉ የአረመኔው ሰራዊት አባላት ወደ ህዝባቸው መተኮሱን አቁመው የፋኖን ትግል እንዲቀላቀሉ  አዛዦች ጥሪ አቅርበዋል። የአረመኔውን ስርዓት በተቀናጀ መልኩ እያፈረሰ የሚገኘው 206ኛ ኮር 61ኛ ክላሽ ከጠላት የተቀበለ ሲሆን የሰራዊት አባላትን የተሀድሶ ስልጠና በመስጠት ላይ ይገኛል። አዲስ ትውልድ! አዲስ አስተሳሰብ! አዲስ ተስፋ! የአፋብን ቴዎድሮስ ዕዝ 206ኛ ኮር ህዝብ ግንኙነት ባየ ደስታ

የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ ይፋዊ የፌስ ቡክ ገጽ ነው። ማንኛውንም የድርጅቱን ኦፊሻል መረጃወች ለማግኘት ገፁን እንድትከተሉ ይሁን። https://www.facebook.com/profile.php?id=61586791120575

የተቋም እህል ሊዘረፍ የመጣው ሰራዊት በጀግኖቹ የሽፈራው ልጆች ሙት እና ቁስለኛ አድርገውታል!! ጥር 15/2018 ዓ.ም የአፋብን ቴዎድሮስ ዕዝ 201ኛ ኮር 64ኛ ክፍለ ጦር በሸበል በረንታ የዕዱውኃ
+1
የተቋም እህል ሊዘረፍ የመጣው ሰራዊት በጀግኖቹ የሽፈራው ልጆች ሙት እና ቁስለኛ አድርገውታል!! ጥር 15/2018 ዓ.ም የአፋብን ቴዎድሮስ ዕዝ 201ኛ ኮር 64ኛ ክፍለ ጦር በሸበል በረንታ የዕዱውኃ እና አካባቢው ጎይ ቀበሌ የተቋም እህል ሊዘርፍ ከመጣው የአገዛዙ ሰራዊት ጋር በተደረገ ውጊያ ከአራት በላይ የመከላከያ ሰራዊት አባላት ሙት እና ቁሰለኛ ሆነዋል። በየዕዱኃ እና አካባቢው ጎይ ቀበሌ የተቋም እህል ለመዝረፍ የመጣው ዘራፊ ሀይል አቶ አንለይ እውነቱ የተባለ ንፁሀን እረሽኖ ወደ መጣበት ቦታ ሄዶል። አዲስ ትውልድ፣ አዲስ ተስፋ፣ አዲስ አስተሳሰብ!! ጥር 15/2018 ዓ.ም አፋብን ቴዎድሮስ ዕዝ 201ኛ ኮር ሕዝብ ግንኙነት