ru
Feedback

Не попадитесь на канал ботавода! Telemetrio находит и помечает такие каналы 👉 Хотите видеть метку — оформите подписку

ፍኖተ-አማራ ሚዲያ (Finote Amhara Media)

ፍኖተ-አማራ ሚዲያ (Finote Amhara Media)

Открыть в Telegram

የተመሠረተው የአማራን ሕዝብ ለማንቃት፣ ለማደራጀት እና ለማስተባበር ነው። የአማራ ሕዝብን ✅ ፖለቲካዊ ✅ ማህበራዊ ✅ ኢኮኖሚያዊ ታሪካዊ ጥያቄዎችን ለማሰማት እና የአማራን ሕዝብ በማንቃት ሰፊውን ሕዝብ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ይሰራል። ወደዱም ጠሉም የኃላ ታሪካችን በእኛ እጅ ይፃፋል። አማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ ( አፋብን)

Больше
4 363
Подписчики
+5424 часа
+2347 дней
+1 43730 дней
Архив постов
"የጠላትን ቅስም ለመስበር ሁሌም ዝግጁ መሆን ያስፈልጋል" ስረዓቱ የፋኖን ጠንካራ ስራዎችን ለማዳከም ትግሉን ለመጥለፍ ሰርጎ ገብ አመራር እና አባላት በማስገባት በሐሰት የfb ሳይቨር በማቆቋም ሰይጣ
"የጠላትን ቅስም ለመስበር ሁሌም ዝግጁ መሆን ያስፈልጋል" ስረዓቱ የፋኖን ጠንካራ ስራዎችን ለማዳከም ትግሉን ለመጥለፍ ሰርጎ ገብ አመራር እና አባላት በማስገባት በሐሰት የfb ሳይቨር በማቆቋም ሰይጣናዊ ተግባራት እየሰራ ይችላል። የዚህ አረመኔዊ ስረዓትና አገልጋዩቹ ሚሊሻ፣ ፖሊስ፣ አድማ ብተና፣ በሆዳቸው ያደሩ ካድሬዎች እንደ እብድ ውሻ ነፍሳቸው እስከሚወጣ ድርስ ማናፋታቸው አይቀርም። የአብይ አህመድ ሰይጣናዊ ስረዓት ለማጥፋት የስጋ ጥቅምን እንደ ሽንት ቤት እቃ በማየት ሁሌም የአማራን ህዝብ ስቃይና ሰቆቃ አስቦ የአማራን ህዝብ የነፃነት ማማን ለማምጣት ሁላችንም እርብርብ ልናደርግ ይገባል። ድርጅታችን የሰጠንን የትኛውም አይነት ተልዕኮ እና ግዳጅ ለመፈፀም ቅልጥ ባለው በረሃ እራሳችን እና ህዝባችን የገጠመውን የህልውና አዳጋ ለመቀልበስ ፊታችን ከሰል እስኪመስል ድርስ እየሰራን እንገኛለን። ከግዳጅ መልስ በስራ ገበታችን ከታች ሸበል በረንታ ግራ ሸበል ከላይ እነማይ ስር-እየሱስ ሱሃ ተፋሰስ አፋፍ የተነሳነው ፎቶ ነው።

የዘር ማጥፋት እየተፈጸመበት ያለው አማራ ጥርሱን ነክሶ እየተፋለመ ነው። መንገድ ተዘግቶበት፣ ሸቀጣ ሸቀጥ አልቆበት፣ መብራትና ውኃ ተቋርጦበት አስፈጭቶና አቡክቶ እንዳይበላ ሆኖ፣ በሌላ በኩል የአማራው አባት ልጆቹ ሲታፈኑ ሲገረፉ ሲረሸኑ ይባሱንም እሱ እራሱ ሲረሸን፣ ዕንባ ከዓይኑ ወዙ ከጉልበቱ ሲወርድ፣ ወገቡን በገመድ ታጥቆ ፊቱን በኀዘን ቋጥሮና ጥቁር ልብስ አገልድሞ ክፉውን ዘመን እየረገመ ጥርሱን ነክሶ መቋሚያውን ተንተርሶ ቀን ይወጣል ያልፍልኛል ብሎ አረመኔውን ሀገር አፍራሹን አገዛዝ ይፋለማል። አማራ ጨለማው ያልፋል ቀጣዩ ትውልድ ነፃነት ያስፈልገዋል ብሎ ልጆቹን ወታደር አድርጓል። አማራ ማዳበሪያ ይሰጠኝ ብሎ አቤቱታ ሲያቀርብ "የጅራፍ ፖለቲካ ነው" የሚል ምላሽ ሲሰጠው ነው ልቡ የቆረጠው። ሀገር አማን ብሎ ድንግል መሬት ሲያርስና ሲቆፍር ዲሽቃና ሞርተር ሲወረወርበት ነው በመሪው ተስፋ ቆርጦ ጫካ የገባው። ለዚህም ነው አማራ እንደ ሕዝብ የሚዋጋው ልጆቹን ፋኖ የሚያደርገው። አማራ ፋኖ የሚሆነው በፈቃዱና ለራሱ ሲል ነው። ከጥቁር አማራዎች ውጭ ሁሉም አማራ ባለበት ፋኖ ነው። ፋኖ ሠራዊት የሚመለምለው እንደ አረመኔው ብልጽግና አስገድዶ አይደለም። ሁሉም ለራሱ ሲል ፋኖ ይሆናል። እነዚያን የቀደሙ አባቶቹን ወኔና ሀገር ጠባቂነት እያሰበ በደም የተሠራችን ሀገር በደም ሊያስከብር በፍቅር ይዘምታል። አገዛዙ ግን እያፈሰ ወታደር ያደርጋል። የአገዛዙ አረመኔነትና ዐይን አውጣነት ልኩን አልፎ ከራሱ ከፍትሕ ፈላጊው አማራ መካከል ወጣቱን ሕጻናቱን አፍሶ ብርሸለቆ ያስገባል። ዳሩ ግን በግድ ያስገባቸው ወጣቶች መልሰው ራሱን ያጠቁታል። ይከዱታል ምሥጢር ያወጡበታል። የሕልውና ትግሉ ከተጀመረ ጀምሮ በብዙ ሺዎች የሚቆጠሩትን ከመላው የሀገሪቱ ክፍል ሰብስቦ ያሠለጠናቸውና ያዘመታቸው ወታደሮች ቢኖሩም እየከዳ እየተገድለና እየተማረከ የአገዛዙ ሕልም እንዳሰበው አልሆነም። ዛሬም በመላው አማራ በየቀኑ ከነ መሣሪያቸው እየከዱ ፋኖን የሚቀላቀሉት ቁጥራቸው ቀላል አይደለም። ©ብላክ ላዬን ሚዲያ

አፋብኃ ደቡብ አማራ ቀጠና አሳምነው ዕዝ ከሰም ኮር ነበልባል ክፍለ ጦር።       ታህሳስ 03/04/2018 ዓ ም የነበልባል ክፍለ ጦር ቃኚ/ተወርዋሪ/ነብሮ ሻለቃ በከተማ ኦፕሬሽን አንድ ባንዳ ሚሊሻ ላይ እርምጃ ወሰዱ።    ስሙ አለማየሁ የተባለ ባንዳ በዛሬው ዕለት በአረርቲ ከተማ ከንቦልሻ በር አካባቢ የለመደውን የባንዳነት ድርጊት ለመፈፀም ሲንቀሳቀስ የነብሮ ሻለቃ ሸማቂዎች እጃቸው በማስገባት ወደ ማይመለስበት አለም በመሸኘት የታጠቀውን ትጥቅ በመማረክ ለነበልባል ክፍለ ጦር ገቢ ማድረጋቸውን ለሚዲያው አሳውቀውናል።    ወንበሬን ይጠብቁልኛል በማለት በብዙ ጥቅማጥቅም እና መደለያ የሰበሰባቸው ሆድ እንጂ ማሰቢያ ጭንቅላት የሌላቸው የሰፈር ወሮ በላ ስብስብ እንኳን ጌቶቻቸውን እራሳቸውን ከነበልባል ሸማቂዎች መጠበቅ የማይችሉበት ደረጃ ላይ መሆናቸውን በነበልባል ክፍለ ጦር ሸማቂ ፋኖ አባላቶች በሚወሰድባቸው መብረቃዊ የሽምቅ ጥቃት በሰራነው ተደጋጋሚ ዘገባ ማሳያ መሆኑን ማሳወቅ እንፈልጋለን።     ድል ለአፋብኃ   ክብርና ሞገስ ለትግሉ ሰማዕታት ድላችን በተባበረ ክንዳችን   ታህሳስ 03/04/2018 ነበልባል ክፍለ ጦር ሚዲያ ክፍል

ሰበር‼ በዛሬው ዕለት ከጧት ጀምሮ የአማራ ፋኖ በወለጋ ከጌጤ ግርማ መብረቅ ክ/ርና ከአንገር ጉትን ብርጌድ የተወጣጡ ሻለቆች እያደረጉ ባሉት ከባድ ጦርነት ምስራቅ ወለጋ ዞን ጉዳያ ቢላ ወረዳ ላይ ከ
ሰበር‼ በዛሬው ዕለት ከጧት ጀምሮ የአማራ ፋኖ በወለጋ ከጌጤ ግርማ መብረቅ ክ/ርና ከአንገር ጉትን ብርጌድ የተወጣጡ ሻለቆች እያደረጉ ባሉት ከባድ ጦርነት ምስራቅ ወለጋ ዞን ጉዳያ ቢላ ወረዳ ላይ ከፍተኛ ድል ማስመዘገባቸውን ፋኖ ዳዊት አማረ የአማራ ፋኖ በወለጋ ህ/ግንኙት መምሪያ ክፍል ሀላፊ  ገልጿል። ዳዊት አክሎም አዲስ የገባው የኦሮሚያ ልዩ ሀይል ከመከላከያ ጋር በመጣመር በጧቱ ጦርነት ቢከፍቱም ሁለቱም ሀይሎች ከፍተኛ ጉዳት ማስተናገዳቸውን ተከትሎ ወደ ኋላ እያፈገፈጉ እንደሚገኙ ገልጾልናል። በተያያዘ ዜና ጊዳ አያና ወረዳ አሊ ቀበሌ ላይ ከፍተኛ ውጥረት መንገሱን አክሎ ገልጿል። ታህሳስ 03/2018ዓ.ም

ኢንጅነር ደሳለኝ ክፍለ ጦር ዙፋን ጠባቂ ሰራዊቱ ላይ የደፈጣ ጥቃት በመፈፀም ድል ተጎናፀፉ:: በመካነሰላም ግንባር የ45ተኛ ክፍለ ጦር ወታደሮች ላይ ከፍተኛ ጉዳት ማድረስ መቻሉን የአማራ ብሔራዊ ኃይል (አፋብኃ) ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ ንጉስ ሚካኤል አሊ ኮር እንጂነር ደሳለኝ አሰፋ ክፍለ ጦር ጌታሰው አስረስ ብርጌድ ቃል አቀባይ ገልጿል:: ትናንት ከቀኑ 10:00 ሰዓት ጀምሮ እስከ ሌሊት 6:00 ሰዓት በቀጠለው ተጋድሎ ሞት አይፈሬዎቹ የጌታሰው አስረስ ብርጌድ ፋኖዎች ድል ቀንቷቸዋል:: የሰሜን ምስራቅ ዕዝ 801ኛ ኮር 45ተኛ ክፍለ ጦር ወታደሮች በ6 ተሽከርካሪዎች ተጭነው ወደ ጌታሰው አስረስ ብርጌድ ፋኖዎች የጦር ሰፈር ገብተው ከበባ ለመፈፀም ሲንቀሳቀሱ ደፈጣ ተጥሎባቸው ስለነበር የሞት ሸለቆ ውስጥ ገብተው በርካታ አባል ተነጥቀዋል:: ጠላት በ2 አቅጣጫ ተቆርጦ መግቢያ መውጫው ጠፍቶት የነፍስ አውጭኝ እሩጫ ላይ ባለበት ቅጽበት ጥቃት ተሰንዝሮበት አንድ ሲኖትራክ ሙሉ ወታደር ገደል መግባቱ ተረጋግጧል:: ሲኖትራኩ ከጥቃት ለማምለጥ ሲሮጥ ሰኞ ገበያ አቅራቢያ ሲደርስ በብሬን ጎማው ተመቶ በርካታ ወታደሮች አልቀዋል:: ቁስለኞችም ወደ መካነሰላም ጄኔራል ሆስፒታል ተወስደው ስለነበር ሆስፒታሉ ለተከታታይ 3 ቀናት ለሲቪል ታካሚዎች አገልግሎት እንደማይሰጥ አስታውቋል ሲሉ የመረጃ ምንጮቻችን ጠቁመዋል:: በኢንጅነር ደሳለኝ አሰፋ ክፍለ ጦር ም/አዛዥ አርበኛ ዱቤ የተመራው ኦፕሬሽን የጠላት አከርካሪ የተሰበረበት ልዩ ኦፕሬሽን መሆኑን የጠቆሙት ምንጮች የ45ተኛ ክፍለ ጦር ሜካናይዝድ ክፍል ሞርተር ጭምር በውጊያው ቢጠቀምም ከሽንፈት አለመዳኑን ነው የገለፁት:: መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልውና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል! ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን! አፋብኃ ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ ህዳር 3 ቀን 2018 ዓ.ም

ዋና ሳጅን አስናቀ ማናየ በአረመኔው ሰራዊት ተገድሎ ደጀን ከተማ አስክሬኑ ወድቆ ተገኝቷል። ታህሳስ 3/2018 ዓ.ም የአረመኔውን ስርዓት በታማኝነት ሲያገለግል የነበረው ዋና ሳጅን አስናቀ ማናየ በመ
ዋና ሳጅን አስናቀ ማናየ በአረመኔው ሰራዊት ተገድሎ ደጀን ከተማ አስክሬኑ ወድቆ ተገኝቷል። ታህሳስ 3/2018 ዓ.ም የአረመኔውን ስርዓት በታማኝነት ሲያገለግል የነበረው ዋና ሳጅን አስናቀ ማናየ በመጨረሻም በአረመኔው ሰራዊት ተገድሎ አስክሬኑ ደጀን ከተማ መንገድ ላይ ተጥሎ ተገኝቷል ። ከህዝብ ነፃነት ይልቅ ለአረመኔው ስርዓት በመታመን የራሱን ህዝብ ሲገድል የነበረው የደጀን ከተማ ፖሊስ ማንነቱን መለየት እስከሚከብድ ድረስ በጭካኔ አካሉ ተቆራርጦ መገደሉ ተረጋግጧል። ይህ በእንዲህ እንዳለ ከሌሊቱ 10:00 ስዓት ከደጀን ከተማ በመውጣት የአርሶ አደሮችን ሀብት ንብረት ለመዝረፍ ሲንቀሳቀስ በነበረ አንድ ፓትሮል ላይ የዛምበረሃ ሻለቃ በአደረገችው የደፈጣ ጥቃት ከ5 በላይ የጠላት ሰራዊት ሲገደሉ ከ15 በላይ የሚደርሱ የአረመኔው ሰራዊት አባላት ከባድ ቁስለኛ ሁነዋል። ያልተገመተውን የደፈጣ ጥቃት በፍጥነት ለማምለጥ በሚጣደፈው ፓትሮል ላይ ኢላማውን የጠበቀ ተኩስ የከፈተችው 206ኛ ኮር 34ኛ ክ/ጦር ዛምበረሃ ሻለቃ ሰራዊቱን ከነፓትሮሎ በመፈጥፈጥ ተሽከርካሪውን ከጥቅም ውጭ አድርገዋለች። አዲስ ትውልድ! አዲስ አስተሳሰብ! አዲስ ተስፋ! የአፋብኃ ቴዎድሮስ ዕዝ 206ኛ ኮር ህዝብ ግንኙነት

ደጀን ክፍለጦር በሌሊት ባደረጉት ተጋድሎ ድል ተጎናፀፉ:: አፋብኃ ምስርቅ አማራ ቀጠና ሚኒሊክ ዕዝ የደጋው መብረቅ ኮር ደጀን ክፍለጦር ታህሳስ 3/2018 ዓ/ም ከሌሊቱ 11:30 እስከ 6:00 ሰዓት
ደጀን ክፍለጦር በሌሊት ባደረጉት ተጋድሎ ድል ተጎናፀፉ:: አፋብኃ ምስርቅ አማራ ቀጠና ሚኒሊክ ዕዝ የደጋው መብረቅ ኮር ደጀን ክፍለጦር ታህሳስ 3/2018 ዓ/ም ከሌሊቱ 11:30 እስከ 6:00 ሰዓት በዘለቀው ከባድ ፍልሚያ የጥላትን ሰራዊት ሙትና ቁስለኛ በማድረግ ድል ተጎናፅፈዋል:: በጋዞ ወረዳ ብር አፋፍ 01 ቀበሌ ላይ በተደረገ አውደ ውጊያ የደጋው መብረቅ ኮር ደጀን ክፍለጦር ፅናት ሻለቃና ኮማንዶ ሶስተኛ ሻለቃ ባደረጉት የማጥቃት ውጊያ በርካታ የጥላት ሰራዊት በመደምሰስ ምሽግ የተሰበረ ሲሆን ከጋሸናና ከአሁንተገኝ ከተማ በገፍ የመጣው የጥላት ሰራዊት ምሽጉን ለቅቆ ወደ መጣበት እግሬ አውጭኝ በማለት ፈርጥጧል። ደጀኖች ጠላትን ባደረሱበት ከባድ ጥቃት የተደመሰሰ ሰራዊቱን በምሽጉ እየቀበረ ሌሎች ቁስለኛና ሙቱን በመኪና በመጫን ወደየመጣበት ተግተልትሎ ሸሽቷል። ሻለቃዎቹ በተጠናከረ መልኩ ጠላት ላይ በወሰዱት እርምጃ ከሙትና ቁስለኛ ባሻገር በርካታ  ተተኳሾችን መማረክ ተችሏል። መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልዉና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል! ህልዉናችን በተባበረ ክንዳችን! የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል (አፋብኃ) የደጋው መብረቅ ኮር ህ/ግ መምሪያ ህዳር 6/2018 ዓ.ም

//<#ፋኖነትን እንደዋዛ የምትለብሰውም ሆነ የምታወልቀውም አይደለም>// ፋኖነትን ትናንት ፋኖነትትን ዛሬ ፋኖነትን ነገ የኖሩትም እየኖሩት ያሉም ነገም ጸንተው የሚኖሩት እና መልካም አማራዊ መገለጫውን የነፍጠኝነት እሳቤውን ለአዲሱ ትውልድ የሚያስረክቡት እነዛ አቡይነትን መታበይን ታይታነትን ተመኔታዊነትን ሳይሆን አማራነትን ፋኖነትን በልባቸው የታጠቁ ጀግኖች ናቸው። ፋኖነትን በችግር በመከራ ማንም ፋኖ ነኝ በማይልበት ሆነ ወጀቦች በበዙበት አጋር በጠፋበት በድፍረት ፋኖ ነኝ ማለት እንደዛ ዋጋ በሚከፈልበት ዘመን ፋኖነትን የኖሩት ተምሳሌቶች ናቸው ለዛሬው የዘመናዊ የፋኖነት ግንባታ መሰረቶች ፈር ቀዳጆች እሩቅ ተላሚዎች አሻጋሪ ተመልካቾች ናቸው እነከተላቸዋለንም እንመካባቸዋለንም እናከብራቸዋለንም እንዘክራቸዋለንም። ፋኖነት ሲሞቅ የሚለበስ ሲበርድ የሚወለቅ ተገለባባጭ ማንነት ሳይሆን እንደ አጼ ቴዎድሮስ እንደ እና ራስ አሞራው ወብነህ እንደ እነ በላይ ዘለቀ እንደ እነ አስማረ ዳኘ እንደእነ ሽፈራው ገርባው እንደ እነ እጅጉ ዘለቀ እንደነ ዋዋ ጎቤ እንደ እነ ሙሃቤ በለጠ እንደ እነ አስቻለው ደሴ እንደ እነ ውባንተ አባተ እንደ አሳምነው ጽጌ እንደእነ ቻላቸው እንየው ....... ተዘርዝረው የማያልቁ ህያው የሆኑ እልቆ ቢስ ፋኖነትን ኑዋሪዎች እና አላፊዎች እንደኮሩ ፋኖነትን እንዳኮሩ እንደተከበሩ እንዳስከበሩ የሄዱ ህያው ጀግኖች ጀግነው የሚኖሩበት ማንነት እንጂ በቀረርቶ በሽለላ በሞቅታ በሆይሆይታ አማራጭም ሲጠፋ ለግል እና ለቡድን ፋላጎትህ እኔ ፋኖ ነኝ እያልክ #ነፍጥ የምታወዛውዝበት ተሰፋ የቆረጥክ ሲመስልህ የተገፋህ ሲመስልህ የአሰብከው ያልተሳካ ሲመስልህ መልሰህ ነፍጥ የምትዘቀዝቅበት እና ከጠላት ወገንም ለመሰለፍ በዚህ የህልውና ትግል #በወደል ባንዳነት ለመመዝገብ የምትሽቀዳድምበት አይደለም በፍጹም ፋኖነት እሱ አይደለም ለሰሞነኛም ጠመንጃ ስላወዛወዝክም ፋኖ አይደለህም። ፋኖነት አማራነት ለጸነት አምቢ ባይነት በወዶ ገብ በባንዳነት አይደለም በጎጥ በአውራጃ በትርክት ተሸካሚነት በመንደርተኝነት በብአዴናዊ እሳቤ አስተሳሰቡን ተሸካሚነት ዘውግ ውስጥ ተወሽቆ ፋኖ ነኝ ማለት ራሱ የማይገለጽ እነዚህን እና መሰል ምግባሮችን የተሸከምክ በሙሉም ፋኖነትን የተጠለለ እንጂ እየኖረ ያለም አይደለም ነገም ከተሳፈረበት ፋኖነት ቅርብ ወራጅነትን የምትጠባበቅ ነህ!! ፋንነትን የመጠነ ታጋይ ሆነ ደጋፊ ብቻ አማራን ያሻግረዋል✊ ድል ለአማራ ፋኖ ድል ለአማራ ህዝብ

በመተከል እና በወለጋ የሚፈጸሙ ግድያዎች ፋኖ ውጊያ ከጀመረ በኋላም ቢሆን አማራን ማዳን አይችልም የሚል መልዕክት የያዙ ሲሆኑ ፍርሐት ወለድ ናቸው ። ትናንት በባዶ ዕጁ የነበረውን አማራ በየ አቅጣጫው ሲገድል የነበረ የአማራ ጠላት ያልጠበቀው ነገር ገጥሞት ወለጋ እና መተከል ላይ የተደራጀ እና እስከ አፍንጫው የታጠቀ የፋኖ ሀይል በማየቱ ከባድ ስጋት ውስጥ ወድቋል ። የዘለዓለም ባርነት አሊያም ፈጽሞ ጥፋት የታወጀበት አማራ በሀያ እና ሰላሳ ወራት ብቻ እስከ አፍንጫው መታጠቁ ፣ ትኩረት ሳቢ የፖለቲካ እንቅስቃሴ ማድረጉ ፣ ራሱን በሚገባ ተከላክሎ ወደ ሀይል ማጥቃት በመሸጋገሩ ፣ አገዛዙን ማፈራረሱ ፣ አዲስ የፖለቲካ ትርክት መገንባቱ በኢትዮጵያ የፖለቲካ ሰማይ ስር አዲስ ድባብ ፈጥሯል ፤ ጠላቶቻችን እርደዋል ። ለዚያም ነው በቀረቻቸው እንጥፍጣፊ ጊዜ መግደልን ብቸኛ ምርጫቸው ያደረጉት ። የዘር ፍጅት የፈጸመብንን ፣ ስልጣኔያችንን ያወደመብንን ፣ ለም መሬታችንን የወረረብንን ጠላት ድባቅ መትተን ህዝባችንን ነፃ እናወጣዋለን ። " ድርድር ንግግር ምንግርግር ጅኒ ጃንካ ብሎ ነገር የለም መግጠም ነው !! " ድል ለጀግናው አማራ ! ድል ለጀግናው ፋኖ ! አዲስ ትውልድ አዲስ አስተሳሰብ አዲስ ተስፋ !!

"መሬን አትነካኩ ባለበት ይቀመጥ፣ የክፉ ቀን ሲደርስ ያወጣል ከረመጥ!! "አርበኛ ፊትአዉራሪ ባዩ አለባቸው ኢ/ር, የአፋብኃ አሳምነው ዕዝ!!'' ዋና ወታደራዊ አዛዥ "አርበኛ ስለሽ የአፋብኃ አሳምነ
+1
"መሬን አትነካኩ ባለበት ይቀመጥ፣ የክፉ ቀን ሲደርስ ያወጣል ከረመጥ!! "አርበኛ ፊትአዉራሪ ባዩ አለባቸው ኢ/ር, የአፋብኃ አሳምነው ዕዝ!!'' ዋና ወታደራዊ አዛዥ "አርበኛ ስለሽ የአፋብኃ አሳምነው ዕዝ ዋና ዘመቻ መሪ !!'' #ማርሽ ቀያሪዎቹ እማይበገሩት መሪዎቻችን!! የአፄዎቹ ፈለቀየንጉሥ ልጅ የነገሥታቱ

የኔ ዘመን በላይ ዘምዋ የኔ ንጉሥ❤️🤗🥰 ራስ አርበኛ ዘመነ ካሴ ማለት በእኔ እይታ☺️ @አዋቂ ነው @ተመራማሪ ነው @አስተማሪ ነው @አርአያ ያለው ነው @አስተዋይ ነው @ሲበዛ ትሁት ነው @ለነገሮች ትኩርት ስጭ ነው @በቶሎ የስወችን ስሜት መርዳት ይችላል @ችግርህን ያቀልልሀል @በቶሎ ከስወች ጋር እምነት መገንባት ይችላል @ማንኛውንም ፈተና መቋቋም ይችላል @ለቀርቡት መላመድ ይችላል @አዳዲስ ሀሳቦችን ያበርታታል @ሌሎችን ማበርታታትና ማነቃቃት ይችልበታል @ የራሱን ጠንካራና ደካማ ጎኖች ጠንቅቆ ያውቃል @ሁልግዜም ለመማር ፣ለማንበብ ፣ለማወቅ፣ለመርዳት፣ዝግጁ ነው @ላመነበት ነገር ወደ ፌት እንጅ ወደሗላ አይልም @ በዛሬ ቀመር የነገን ኗሪ ነው @ሩቅ አሳቢ ቀና ነው @ሩቅ አዳሪ ኩራት ነው ለወገኖቹ @ያስደፋል አንገት ለጠላቶቹ @አሽናፌ ነው በየሔደበት @እንኳንስ ዛሬ ከጎኑ እያለ ሚሊየን ፋኖ ያስጨንቅ ነበር ስሙ ሲጠራ ብቻውን ሁኖ የተባለለት የዘመናችን ክስተት!! #ራስ አርበኛ ዘመነ ካሴ የመሪነት ችሎታ ስላለው የአማራን ወጣት ከተኛበት ቀስቅሶ የታስርበትን ስንስለት በጥሶ ለመብቱ፣ለክብሩ፣ለፖለቲካ ጥያቄው፣ለህልውናው ታጋይ እንዲሆን ያደርገው አማራው አርበኛ ዘመነ ካሴ ስላለው ታድሏል ወላሂ ህዝቤ ሆይ ይህን ባለ ምጡቅ አዕምሮ ተፈልጎ አይገኝምና በጅ የያዙት ወርቅ እንደ መዳብ ይቆጠራል እዳይሆን ነገሩ የመሪህን ቃል ጠብቅ፣የመሪህን ትዕዛዝ አክብር!!መሪህን እንዳይንህ ብሌን ጠብቅ😌😍 አንድ አስርግጨ የምነግራችሁ ነገር ቢኖር ራስ አርበኛ ዘመነ ካሴ ባይኖር ወይ እራሱን ቢያገል ይህ ህዝብ ባሪያ ሁኖ ይኖራል ባሪያ ላለመሆን ደግሞ ብቸኛው አማራጭ አንድ ሁኖ በጋራ ጥርስን ነክሶ መታገል ብቻ ነው!! ታስፈልገናለህና አላህ እድሜህን ያርዝምልን የኔ ንስር ደግሞ ዛሬም ነገም ሙቸ እወድሃለሁ አከብርሃለሁ ወላሂ🥺 ድል ለመላው የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል አፋብኃ ድል ለመላው የአማራ ህዝብ አድስ ትውልድ አድስ አስተሳስብ አድስ ተስፋ ክፋት ለማንም በጎነት ለሁሉም አማራ ማንንም ሳይለማመጥ ማንነቱን በክንዱ ያስከብራል

አማራን ትጥቁን ቀርቶ ቀበቶዉን እናስፈታዋለን ብለዉ እስካፍንጫቸዉ ታጥቀዉ የመጡ ሀይሎችን አፍንጫቸዉን ይዘን ትጥቃቸዉን እየተቀበልናቸዉ እንገኛለን።
+3
አማራን ትጥቁን ቀርቶ ቀበቶዉን እናስፈታዋለን ብለዉ እስካፍንጫቸዉ ታጥቀዉ የመጡ ሀይሎችን አፍንጫቸዉን ይዘን ትጥቃቸዉን እየተቀበልናቸዉ እንገኛለን።

#ከአፋብኃ_ምዕራብ_አማራ_ቀጠና_ቴዎድሮስ_ዕዝ #_201ኛ_ኮር_ህዝብ_ግንኙነት_የተላለፈ_ማሳሰቢያ ታህሳስ 03/2018 ዓ.ም በ64ኛ ክፍለ ጦር በምናስተዳድረው ቀጠና ሸበል በረንታ እና እነማይ ወረዳ በቅርብ ቀን በእነማይ ወረዳ ቢቸና ዙሪያ ሰርገን ገብተናል የተሳካ ኦፕሬሽን ሰርተናል እያሉ በውሸት የማህበራዊ ሚዲያ ስርጭት የሚያሰራጩ፣የሚያራግቡ እና የሚያናፍሱ አካላት ፍፁም ታማኝነት እና አመኔታ የሌለው በመሆኑ በ64ኛ ክፍለ ጦር ስር ካሉ "5"ሬጅመንቶች ውስጥ በአዲሱ አደረጃጀት #1ኛ_ጠቅል_ሻለቃ_እምባል የሌለ መሆኑን እንገልፃለን። በመሆኑም በ64ኛ ክፍለ ጦር የሚደርጉ የትኛውም አይነት ኦፕሬሽኖች፣ የህዝብ ውይይቶች እና ሌሎች መሰል ተግባራት በክፍለ ጦሩ ህዝብ ግንኙነት ሰንሰለቱን ጠብቆ ለ201ኛ ኮር እና ቴዎድሮስ ዕዝ መርጃዎች በወቅቱ ደርሰው ለህዝባችን እና ለጦራችን ሰንሰለታቸውን ጠብቀው የሚዲያ ሽፋን እያገኙ ይገኛሉ። ማሳሰቢያ:- በድርጅት የሚዲያ አጠቃቀም ህግ መሰረት በአፋብኃ ቴዎድሮስ ዕዝ 201ኛ ኮር 64ኛ ክፍለ ጦር ህዝብ ግንኙነት የውጊየም ይሁን የህዝብ ውይይት መሰል መድረኮች በተለያዮ የሐሰት #የFacebook አካውንቶች የሚራገቡት ፍፁም ተቀባይነት እና ውሸት መሆናቸውንን ለድርጅታችን፣ ታጋዩቻችን፣ ደጀኑ ህዝባችን እንዲሁም የአለማቀፍ ማህበረሰብ እውቅና እንዲኖረው በአክብሮት እንገልፃለን። አዲስ ትውልድ፣ አዲስ አስተሳሰብ፣ አዲስ ተስፋ! ታህሳስ 03/2018 ዓ.ም ቴዎድሮስ ዕዝ 201ኛ ኮር ሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ

206ኛ ኮር በተቆጣጠራቸው ነፃ ቀጠናዎች የፖሊዮ ክትባት እየሰጠ መሆኑን የኮሩ ጤና መምሪያ አስታወቀ።  ታህሳስ 3/2018 ዓ.ም ህልውናው የተረጋገጠ ጤናማ ትውልድ ለመፍጠር በሁሉም የአማራ ክ/ሀገራት ከጠላት ጋር የሚተናነቀው የአማራ ብሔራዊ ኃይል ፋኖ ቀይ መስቀልን ጨምሮ የጤና ተቋማት ለገልግሎት ክፍት በማድረግ ለባለሙያዎች እና ለተቋማት ልዩ ጥበቃ በመመደብ ማህበረሰቡ የጤና አገልግሎት እንዲያገኝ ሰፊ ስራ እየሰራ መሆኑን የገለፀው የ206ኛ ኮር ጤና መምሪያው በነፃ ቀጠናዎች ከሚገኙ ጤና ጣቢያዎች ጋር በመተባበር በሁሉም ቀበሌዎችና ከተሞች የፖሊዮ ክትባት እየተሰጠ መሆኑን ገልጿል። ከአምስት አመት በታች ያሉ ህፃናትን የሚያጠቃው የልጅነት ልምሻ ለሞት የሚዳርግ በመሆኑ ክትባቱ  በአመት በዘመቻ መልክ ለሁለተኛ ጊዜ እየተሰጠ ሲሆን ኮሩ በስሩ ካሉ የክ/ጦር ጤና መምሪያዎች ለማህበረሰቡ ግንዛቤ በመፍጠር ክትባቱን ከጤና ባለሙያዎች ጋር በመቀናጀት እየሰጠ መሆኑን መምሪያው አክሎ ገልጿል። ወላጆች ከልማዳዊ አስተሳሰብ በመውጣት ልጆቻቸውን ማስከተብ እንዳለባቸው በክትባቱ ማዕከል ግንዛቤ በመፍጠር  በደብረ ኤልያስ ወረዳ ጓይ ከተማ ክትባቱን ያስጀመሩት  የ206ኛ ኮር 14ኛ ክ/ጦር ጤና መምሪያ ኃላፊ ፋኖ ዮሴፍ ታከለ ከትግሉ ጎን ለጎን ጤናማ ትውልድ ለመፍጠር መምሪያው የተሰጠውን ድርጅታዊ ተልዕኮ ለመፈፀም ከወትሮው በተለየ እየሰራ ይገኛል ሲል ለአገልግሎቱ ተጠቃሚዎች ገልጿል። አዲስ ትውልድ! አዲስ አስተሳሰብ ! አዲስ ተስፋ የአፋብኃ ቴዎድሮስ ዕዝ 206ኛ ኮር ህዝብ ግንኙነት

ታጋይ ይሞታል ትግል ይቀጥላል። በጀመርነው የህልውና ትግል 30 ወራትን እያስቆጠርን ቢሆንም አለምን ያስደመሙ አያሌ ሁነቶችንና፤ በርካታ ድሎችን ብናስመዘግብም ትግል ነውና ብዙ ፈተናዎችንም አስተናግደንበታል። ለአማራ ህዝብ ነፃነት ሲሉ የሞቀ ቤታቸውንና ኑሯቸውን ትተው በዱር በገደሉ አጥንታቸውን ከስክሰው ደማቸውን አፍስሰው አይተኬ የሆነውን ውድ ህይዎታቸውን ገብረውበታል። የአማራ እናቶች ያፈራቻቸው ጀግና አርበኞች በደማቸው ደማቅ ታሪክ እየፃፋ ካለፉ በርካታ አርበኞች መካከል የቴዎድሮስ፤የሚኒልክ፤ የበላይ፤ የአሳምነው አናብስቶች ፋኖዎች እነ አስራት ወልድየስ፤ እነ ናሁሰናይ፤ አርበኛ ውባንተ የመሳሰሉ እልፍ ጀግኖችን ያጣን ቢሆንም በደማቻው የለኮሱት የትግላችን ሻማ ወደኋላ ላይመለስ ከትናንት በበለጠና በተፋጠነ መልኩ ተጠናክሮ ቀጥሏል። ጀግንነትን ከአባቶቹ የወረሰው የሚኒልክ የአስራት ወልድየስ ግብርን የተላበሰው ውጊያ ሲገባ ሳቅ ሳቅ የሚለው የትግል አባልኑ ሳይወጣ የማይሸሽ የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል ደቡብ አማራ ቀጠና ዓፄ ዘርዓ ያዕቆብ ፩ ኮር  የሰባት ለሰባ ክፈለ ጦር የሰብር ሻለቃ ምክትል አዛዥ የነበር በአሁኑ ስዓት የሰባት ለሰባ ክፍለ ጦር የቃኘች አዛዥ  የጦሩ ገበሬው ዝምተኛውና አመለ ሸጋው  የአማራ የቁርጥ ቀን ልጅ የነበረው ሸጋው ግርማ በተወለደባት ቦታ ካራለጎማ ለሁለት ስዓት(2:00) ያህል  ከአማራ ጠሉ አብይ አህመድ ጡት ቆራጭ አስጠባቂ አረመኔያዊ ሰራዊት ጋር እልህ አስጨራሽ መደበኛ ውጊያ ከወንድሞቹ ፋኖ ጓደኞቻቸው ጋር በመሆን  የብልፅግናን መከላከያ 103ኛ አየር ወለድ ኃይል ሙት እና ቁስለኛ አድርጎ በመጣል  በቀን 02/04/2018 ዓ.ም ውድ አንድዬ  ህይወቱን ለአማራ ህዝብ ሰውቶ አልፈዋል። ለተሰዋው ጀግናችን የዋሁ የአማራ ነፃነት የሚናፍቀው ሸጋው ግርማ ነፍስህን ልዑል እግዚአብሔር በአፀደ ገነት ያሳርፍልን። ለሰማዕቱ ቤተሰቦችና የትግል አጋሮች በሰባት ለሰባ ክፍለጦር የተሰማንን ጥልቅ ሀዘን እየገለፅን ለወዳጅ ዘመዶቹም  መፅናናትን እንመኛለን። በስተመጨረሻም ውድ የሰባት ለሰባ አባላትና አመራሮች ሀዘናቹሁ ሀዘናችን ስለሆነ ያጣናውን  ታጋይ ወንድማችን አርበኛ እንደ ስሙ ሸጋው ግርማን ከእንግዲህ የማናገኘው ስለሆነ ሰራዊቱን በማፅናናት የጀመርነውን ትግል ከግብ ለማድረስ ማሰልጠንና ማደራጀት የግድ ስለሆነ እንደነ ሸጋው ግርማ  ያለ ጀግኖችን የምንፈጥርበት ሰዓት ይሆናል ።    ታጋይ ይሞታል ትግል ይቀጥላል።