ru
Feedback

Не попадитесь на канал ботавода! Telemetrio находит и помечает такие каналы 👉 Хотите видеть метку — оформите подписку 👈

ፍኖተ-አማራ ሚዲያ (Finote Amhara Media)

ፍኖተ-አማራ ሚዲያ (Finote Amhara Media)

Открыть в Telegram

የተመሠረተው የአማራን ሕዝብ ለማንቃት፣ ለማደራጀት እና ለማስተባበር ነው። የአማራ ሕዝብን ✅ ፖለቲካዊ ✅ ማህበራዊ ✅ ኢኮኖሚያዊ ታሪካዊ ጥያቄዎችን ለማሰማት እና የአማራን ሕዝብ በማንቃት ሰፊውን ሕዝብ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ይሰራል። ወደዱም ጠሉም የኃላ ታሪካችን በእኛ እጅ ይፃፋል። አማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ ( አፋብን)

Больше
4 129
Подписчики
Нет данных24 часа
+4197 дней
+1 13230 дней
Архив постов
አሁን ዉስጣችንን እያጠራን ነዉ!! *** በድርጅታችን ውስጥ ትክክል መስለው ትክክል ያልነበሩ መስየዋች ወደ ሰለጠኑበት ካምፓስ አየተመለሱ ነው። የውስጥ ባንዳዋች የታሪክ ጠላት የወለደው ስርአት አስፈፃሚ የነጻነት ታጋዯችን ለማፈረስ ስልጠና አሰልጥኖ በውስጥ አስርጎ በማስገባት ተልኮ የሰጣቸው ትክክል መስለው ትክክል ያልነበሩ ፀረ ፋኖዋች አላማቸው ስላልተሳካ ወደ ግንዳችው እየተመሙ ይገኛሉ። እነዚህ እኩይ ተግባር አንግበው ሲቀሳቀሱ የነበሩ አካላት በዋናነት ሁለት ተልእኮ ነበራቸው። እነሱም:- 1ኛዉ ዓላማቸዉ:- ➤ሰራዊቱ በሃላፊው እንዳይመራ ማድረግ ➤ሰራዊቱ ከአላማው ወጭ ወደ ገንዘብ ፍላጎት እንዲገባ ማድረግ ➤በሰራዊቱ ውስጥ ብሔርተኝነት መፍጠር ➤ማህበረሰቡን ማንገላታትና ከሰራዊቱ መነጠል ➤በውጊያ ወይም ግዳጅ ሰአት ሽብር መፍጠር ➤ትግሉ የግል እንደሆነ ፕሮፖጋንዳ መንዛት ሲሆን 2ኛው አላማቸው ደግሞ:- ➤ጉዳዮ ሲነቃባቸው የነፃነት ታጋይ የነበሩ በመምሰል እና ትግሉ አላማ እንደሌለው በማስመሰል ህዝብን ተስፋ ለማስቆረጥ ፕሮፖጋንዳ በመንዛት በምህረት መልክ ወደ አሰልጣኛቸው መመለስ ነው። ስለሆነም እነዚህ ከላይ የተዘረዘሩት ተግባር አላማቸው ታወቆ እርምጃ ሲወሰድባቸውና ሲታደኑ ከየተደበቁበት ጉድጓድ በመዉጣት እየበረሩ ጠፍተዋል። ከተማ ውስጥም በመሰግሰግ ለጠላት የተለያየ የሃሰት ማስረጃ በመስጠት ማህረሰባችን ለእስራትና ለእንግልት እየዳረጉት ይገኛሉ። ይህ ደግም ሁለተኛ በደል መሆኑን ማህበረሰቡ እንዲረዳ ስንል እያሳሰብን በሚቀጥለው ቀን ሙሉ ስማቸውን ከሰሩት ጥፋት ጋር ውሳኔውን ጨምረን ይፋ የምናደርግ መሆኑን እናሳዉቃለን። የአ.ፋ.ብ.ሃ ሰሜን አማራ ቀጠና በላይ ዘለቀ ዕዝ 4ኛ ደጃዝማች ኮር ሰብሳቢ አርበኛ አንዳርግ ጫቅሉ

የአፋብኃ ደቡብ አማራ ቀጣና አሳምነው ዕዝ ከሰም ፪ኮር ኃይለማሪያም ማሞ ክፍለ ጦር የአውደ ውጊያ ውሎ። የአፋብኃ ደቡብ አማራ ቀጠና አሳምነው ዕዝ ከሰም ፪ኛ ኮር ኃይለማርያም ማሞ ክ/ጦር  ሰላም ሰው ሻለቃ ላይ ጥቃት ለማድረስ  የመጣው ኃይል ላይ ጥቃት ሰነዘረ። ከኮረማሽ ንዑሥ ወረዳ በሆነውበሶስት አምባ ቀበሌ ከበባ ውስት አሥገብቶ ለማጥቃት ቢሞክርም ቀደመው የጠላትን እንቅስቃሴ የሰሙትና የተረዱት የፍኖ አባለትና አመራሮች ምሸግ በመያዝ ፊት ለፊት ገጥመውት በብሬናና በስናይፐር ጥምር ተኩሥ ያናወጡትና ሲቀጠቀጡት አርፍደው በጠላት ላይ 3 ሙትና 5 ቁሥለኛ ተሸክሞ ተመልሷል። ጠላትም ያሰበውና ያቀደው የውጊያ ሥልት ቀድሞ በወጣው መረጃ የከሸፈበትና የከሰረው የብልፅግና ሎሌ ሰራዊት  ያካክሥልኛል ያለውን የህዝብ ንብረት የሆነው የትምህርት ቤት ንብረት  የቤተ መፅሐፍት ቁልፍ በመገንጠል ሶላር ምጣድየሶላር ፤ድንጋይ፤የመማር ማሥተማሪያ ሬዲዎ፤የተለያዩ የሥልክና የሶላር ቻርጀርና አዳፖተሮች በአጠቃላይ የኤሌክትሮኒክሥ እቃዎችን በመዝረፍ የዘውትር ተግባሩ የሆነውን መንገድ ላይ የተገኜ ንፁህ አረሶ አደሮችን በማሰርና አግቶ በመውሰድና በመደብደብ የውጊያ መሳሪያ በግዳጂ በማሸከም የግፍና የበደል ሥራውን አካሂዷል።        መረጃው የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል ደቡብ አማራ ቀጠና አሳምነው ዕዝ የከሰም 2ኛ ኮር ህዝብ ግንኙነት ኃላፊ አርበኛ ይታገስ ነው         " ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን" ‎አፋብኃ ደቡብ  አማራ ቀጠና አሳምነው ዕዝ   የህዝብ ግንኙነት ዜና ክፍል ጥር 03/2018 ዓ.ም

ስቦ ማስከዳት ተጠናክሮ ቀጥሏል‼️         ጥር 3/2018 ዓ.ም ስርአቱ በአማራ ህዝብ ላይ እየተፈፀመበት ያለውን ግፍ እያየን መቀጠል ስላልቻልን ከወንድሞቻችን ጎን ተሰልፈን ህዝባችን መካስ አለብን በማለት በግፈኛው አብይ አህመድ ትዛዝ ታፍሶ የአድማ መከላከል የ34ኛ ዙር ሰልጣኝ የ28 ሻለቃ አባል የነበር አብርሃም አያሌው  የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል ደቡብ አማራ ቀጠና አሳምነው ዕዝ ዓፄ ዘርዓያዕቆብ ፩ የሰባት ለሰባ ክፍለ ጦር የአሳምነው አናብስቶች ተቀላቅሏል። በመሆኑም ወንድማችን አረመኔያዊ አብይ አህመድ ያአስታጠቀውን ክላሽ ከነሙሉ ትጥቁ በመያዝ የዓፄ ዘርዓያዕቆብ ፩ ኮር የሰባት ለሰባ ክፍለ ጦር ዘመቻ መምሪያ አርበኛ ነጋ ንጉሴና የክፍለ ጦሩ ድርጅታዊ ጉዳይ አርበኛ እሸቱ በቀለ በአመራሮች አቀባበል ተደርጎለታል። በመሆኑም በሰሜን ሽዋ መሃል ሚዳ የመሸገው አድማ መከላከል ኃይል በዚህ ሰዓት እርስ በእርሱ መተማመን ያጣበት ከመሆኑም አንፃር የአማራ ተወላጅ የሆኑት አድማ መከላከልና መካላከያ አስሯቸው ይገኛል። በመጨረሻ ሁሉም የአማራ ተወላጅ ለመውጣት ይፈልጋሉ ነገር ግን ይገሏቹሀል ነው የሚባለው ቢሆንም ግን ለመውጣት አልመቻች እያለ ነው እንጂ አሁን ላይ ማንም መቆየት አይፈልግም በማለት ገልፃል። የአፋብኃ ደቡብ አማራ ቀጠና አሳምነው ዕዝ ዓፄ ዘርዓያዕቆብ ፩ ኮር ህዝብ ግኑኝነት ኃላፊ አማር ታዘዘ ጥር 3/5/2018 ዓ.ም

ለአባት አርበኞች ጦር በኮረብታ ቀበሌ ስልጠና ተሰጠ!! ➺➺➺➺➺➺➺➺➺➺➺➺➺➺➺➺ 🎄🎄🎄ጥር 03/2018 ዓ.ም በ54ኛ ክ/ጦር የቢቡኝ ወረዳ ጊዜያዊ መንግስት በኮረብታ ቀበሌ አመራር እና ከአባት
+1
ለአባት አርበኞች ጦር በኮረብታ ቀበሌ ስልጠና ተሰጠ!! ➺➺➺➺➺➺➺➺➺➺➺➺➺➺➺➺ 🎄🎄🎄ጥር 03/2018 ዓ.ም በ54ኛ ክ/ጦር የቢቡኝ ወረዳ ጊዜያዊ መንግስት በኮረብታ ቀበሌ አመራር እና ከአባት አርበኛው ጦር ጋር ውይይት ተደርጓል። ➢ስለ ፍትህ አሰጣጥ ➢ስለ አደረጃጀት ➢ የትግሉ ቁመና ➢የወርዳ ጊዜያዊ መንግሥት መዋቅር እና የቀበሌ መዋቅር የስራ ሀላፊነት በማስተዋዉቅ የአማራ ታሪካዊ ጠላት የሆነው የብልፅግና አረመኔ ስርአት እንታገላለን በማለት ሀሳባቸውን የገለፁ ሲሆን፦ የቀበሌውን ህዝብ እራሳቸውን እና አካባቢያቸውን ብሎምለገራቸውን ከወራሪው አረመኔው ስርአት እንዲጠብቁ የማደራጀት ስራ ተሰርቷል ። አዲስ ትውልድ፣አዲስ አስተሳሰብ፣አዲስ ተስፋ ጥር 03/2018 ዓ.ም አፋብኃ ቴወድሮስ ዕዝ 201ኛ ኮር ህዝብ ግንኙነት

206ኛ ኮር ከሌሊቱ 7:45 በደብረ ማርቆስ ከተማ በፈፀመው የቦንብ ጥቃት 8 የጠላት ሰራዊት ተገድለዋል‼️ ጥር 3/ 2018 ዓ.ም =================================== የ206ኛ
206ኛ ኮር ከሌሊቱ 7:45 በደብረ ማርቆስ ከተማ በፈፀመው የቦንብ ጥቃት 8 የጠላት ሰራዊት ተገድለዋል‼️ ጥር 3/ 2018 ዓ.ም =================================== የ206ኛ ኮር አዳኝ ቡድን በደብረ ማርቆስ ከተማ ከሌሊቱ 7:45 በሶሰት አቅጣጫ በፈፀመው አስደናቂ የቦንብ ጥቃት ከመሐል አደባባይ ወደ ውኃ ጋን ስትከንፍ የነበረችውን ፓትሮል  በማጋየት 4(አራት) አድማ ብተና አባላት ሲገደሉ ሁለቱ ከባድ ቁስለኛ ሁነዋል። በተመሳሳይ ስዓት በጎዛምን ጤና/ፅ/ቤት በመሸጉ ሚኒሻዎች ላይ በደረሰ ተጨማሪ የቦንብ ጥቃት አንድ የፖሊስ ጠርናፊን ጨምሮ 3 ሚኒሻዎች ህይወታቸው ሲያልፍ ሶስት ፖሊሶች ከባድ ቁስለኛ ሁነው ደብረ ማርቆስ ሆስፒታል ገብተዋል። ሶስተኛው ጥቃት በመርማሪ ፖሊሱ ታረቀኝ ስንሻው ቤት ላይ ያነጣጠረ ሲሆን ንፁሐንን እያደነ ሲያሰቃይ የነበረው ታረቀኝ ስንሻው በደረሰበት የቦንብ ጥቃት ከባድ ቁስለኛ ሁኖ እያጣጣረ ይገኛል። ለአራት ተከታታይ ጊዜ በደብረ ማርቆስ ከተማ አስደናቂ ኦፕሬሽን እየሰራ የሚገኘው የ206ኛ ኮር አዳኝ ቡድን 23 የጠላት ኃይል በቦንብ አጋይቶ 20 የሚሆኑትን ከባድ ቁስለኛ አድርጓል። በዛሬው ከባድ ጥቃት የተደናገጠው የአረመኔው ሰራዊት የከተማዋን ህዝብ  በገፍ እያፈሰ ማጎሪያ እየወረወረ ሲሆን ማርቆስ ከተማ በታላቅ ጭንቅ ውስጥ ትገኛለች። አዲስ ትውልድ! አዲስ አስተሳሰብ! አዲስ ተስፋ! የአፋብኃ ቴዎድሮስ ዕዝ 206ኛ ኮር ህዝብ ግንኙነት 03/ዐ5/2018 ዓ.ም

ጋዜጠኛ ኤሊያስ ደባሱን በተመለከተ !! ጋዜጠኛ ኤሊያስ ደባሱ የተባለ ግለሰብ በትናንትናው ዕለት ከአፋብኃ ቴዎድሮስ ዕዝ በመክዳት ወደ ብልፅግና እንደተቀላቀለ ተደርጎ እየተገለፀ መሆኑን ታዝበናል። ነ
ጋዜጠኛ ኤሊያስ ደባሱን በተመለከተ !! ጋዜጠኛ ኤሊያስ ደባሱ የተባለ ግለሰብ በትናንትናው ዕለት ከአፋብኃ ቴዎድሮስ ዕዝ በመክዳት ወደ ብልፅግና እንደተቀላቀለ ተደርጎ እየተገለፀ መሆኑን ታዝበናል። ነገር ግን ኤሊያስ ደባሱ በቀደመው የአማራ ፋኖ በጎጃም ወይም በአሁኑ ቴዎድሮስ ዕዝ ውስጥ በየትኛውም የአደረጃጀት እርከን ውስጥ አባላችን ያልነበረ መሆኑን እየገለፅን እርሱን ተከትሎ ወደጠላት የገባ ሌላ አባል እንደሌለ ለማሳወቅ እንወዳለን ። አፋብኃ ቴዎድሮስ ዕዝ

ታሪክ ራሱን ይደግማል፤ ታሪክ ህይወት እንዳለው ነገር ሁሉ ተፈጥሮ - ይወለዳል፣ ያድጋል ይሞታል። ይህን ኡደት የሚያመጣዉ ደግሞ በምድራዊ መተዳደሪያ ደንብና ስርአት ውስጥ በተፈጥሮ እኩል የሆኑ ነገሮችን እኩል እንዳልሆኑ እና እኩል ያልሆኑ ነገሮችን ደግሞ እኩል እንሆኑ በህግ ደረጃ ሲፀድቅ ዘረኝነት ይወለዳል ያድጋል ይህንም ለመግደል ትግል ይወለዳል። በዚህ ስርአተ ኡደት ደግሞ ታጋይና ባንዳነት ይፀነሳል፣ ይወለዳል፣ በመጨረሻ ስርአቱ ሲወገድ ባንዳም ይሞታል። አድር ባይ ደግሞ ይወለድና ቀዝቀዝ ያለ የህይወት ውጣ ውረድ ይመጣል። ይህ ደግም ሰወች ተፈጥሯቸውን ሲነጠቁ እና የመኖር ዋስትናቸው አደጋ ላይ ሲወድቅ፣ ሀገር ባለቤት ስታጣ፣ ራስን ለመከላከል ወደ ትግል መግባት አማራጭ የሌለው ጉዳይ ይሆናል። በዚህ ሒደት ሁለት አይነት ሰወች ይገኛሉ። እነዚህም:- እውነተኛ ሰዋችና ሀሰተኛ ሰዋች ወይም የነጻነት ታጋይ(ፋኖ) እና ባንዳዎች (ሀሰተኞች) ናቸው። ባንዳ ማነው? ባንዳ ማለት:- በነጻነት ትግል አገላለጽ በአንድ ሀገር ውስጥ የሚኖሩ ዜጎች በሀገራቸው በእርስታቸው እንዲሁም በማንነታቸው ዙርያ ማግኘትና መከበር ያለባቸውን ሁለንተናዊ ጉዳይ የሚያሳጣ ስርአተ መንግስት በመኖሩ ብቻ ለነጻነት እና የመኖር መብታቸውን ዋስትና ይኖረው ዘንድ ስርአቱን ለመቀየር በጥጃ ብረታቸው እንዲሁም በእስክሪቶ የሚታገሉ ታጋዯችን ከጠላት ስልጣን እና ገንዘብ ለማግኘት ሲሉ ለነጻነት የሚታገሉ ታጋዯችን ጠላትን በመምራት በማስገደልና በማሳደድ የተካኑ የከሸፉና ስርአቱን እንደፈጣሪ ያመኑ ግለሰቦች ናቸው። ፋኖ ማለት:- ሀገር ሲወረር፣ ዜጎች ማንነታቸውን ሲነጠቁ፣ ጠቃሚ ባህል ሲሸረሸር፣ የዜጎች እምነት በባአድ አምልኮ ሲወረር፣ ዜጎች በስርአቱ ምክኒያት ነጻነት ሲያጡ ሀገራዊ ለውጥ ለማምጣት እና ዜጎች በሀገራቸው ላይ የመኖር ዋስትና እንዲኖራቸው ለማድረግ በዱር በገደል የገዥውን ስርአት ብቻ የሚቃወም ታሪካዊ የኢትዮጵያ የትግል ማንነት ነው። ስለሆነም ፋኖ ዓላማዉ በሀገራችን ለሁለተኛ ጊዜ የተከሰተውን የፋሽሽቱን ስርአት መገርሰስና ሀገራዊ እንዲሁም በዜጎች ማነነት ላይ የተመሠረተ አካታች ስርአት እንዲኖር ማድረግ ነው ። ዜጎች በሀገራቸው ነዋሪ ብቻ ሳይሆኑ ሙሉ በሙሉ ባለቤት መሆን አለባቸው ብለን እናምናለን። ፋኖ የብሔር ፓለቲካ ሪዮት አለምን አጥብቆ የሚቃወም እና ማንኛውም ኢትዮጵያዊ በእኩልነት የሚኖርባት ነባር ኢትዮጵያን መልሶ ማቋቋም እንደለበት አጥብቆ ያምናል። የምንቃወመው የገዢው ፓርቲ አስተዳደራዊ ስርአት እንጅ ብሔርን አይደለም። በአንድ ገዢ ፓርቲ በጊዜው ጠንካራ ጎን እና ደካማ ጎን ሊኖረው ይችላል ነገር ግን የስርአቱ መሪ ማንነቱ በማጥናትና በመለየት ደካማ ጎኑን እና መሠል ታርጋ በመለጠፍ ለራስህ ስልጣን ማራዘሚያ ለማድረግ ዘሩን በመቁጠር የዛሪውን ትውልድ ጨቋኝና እና ረጋጭ እንደነበር በማስረዳት የብሔር ፓለቲካን መወለድና ማሳደግ ሀገርን ከማፍረስ ውጭ ሌላ ለውጥ አያመጣም ስለሆነም አጥብቀን መቃወም አለብን። የሰው ልጅ ማንነቱ ሰውነቱ ብቻ ነው ሌላው በሚሰራው ስራ የሚመዘን እና የሚለካ ይሆናል። በኢትየጵያ ያልተፈጠረ ዘረኝነት ቢኖር የጾታ ብሔርተኝነት ብቻ ነው። ስለሆነም መላው ህዝባችን የፋሽስቱን የኢትዮጵያ ስርአት በመቃወም ሀገርን እንደ ሀገር ሊያስቀጥል የሚችል ስርአት እንዲዘረጋ በማድረግ እውነተኛ ሚና ሊወጣ ይገባል። እውነተኛ ትግል ለሀገር ለውጥ እንጅ ለግል ክብርና መበልጸጊያ መሣርያ አይደለም። እውነተኛ ትግል ባንዳወችን ሁሉ በማደስ ነጻ ያወጣል። በሀገር በቀል የባርነት ቀንበር አንገትን መድፋት ታሪካዊ ጀግንነትን ይሰርሳል። በትግል ያገኘነዉን አለም አቀፍ የጀግንነት ማንነት የማስከበር ሃገራዊ ሀላፊነት አለብን። ማንነታችን በክንዳችን ይከበራል፣ አገራችን በደማችን ትታደሳለች። ሰዎች ሰዉ በመሆናቸዉ ብቻ ማግኘት ያለባቸዉን ተፈጥሯዊ ክብር ማስከበር የህሊና ግዳጅ አለብን። ድል ለጭቁኑ ህዝብ!! የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል ሰሜን አማራ ቀጠና በላይ ዘለቀ ዕዝ 4ኛ ደጃዝማች ኮር ሰብሳቢ አርበኛ አንዳርግ ጫቅሉ

ስራዎች ተጠናክረው የሚቀጥሉ መሆናቸውን እናረጋግጣለን። የበላይ መዋቅሩ ፍተሻና ማሻሻያም የሚቀጥልና የምዕራፉ ዋነኛና ተጨማሪ ተግባራችን ነው። የዚህ የቁመና ማሻሻያ መርሃ-ግብር በስኬት መጠናቀቅን ተከትሎ የዘመኑ ህዝባዊ ግዳጃችንን ለመወጣት እጅግ የተሻለ ቁመና ላይ እንደምንገኝ ስናሳውቅ በከፍተኛ መተማመን ሲሆን ይህም ለወገንና ለወዳጆች የምስራች ሲሆን ለጠላት ደግሞ ሌላ የራስ ምታት መሆኑን እየተገነዘብን በበዚህም መሠረት የሚከተለውን ጥሪ እናስተላልፋለን፦ 1ኛ ለዕዛችን አባላትና አመራሮች ውድ የአማራ ህዝብ የቁርጥ ቀን ልጆች የሆናችሁ የዕዙ አመራርና አባላት ጓዶቻችን፤ ይህ ትግል በታሪካችን ውስጥ ልዩ ቦታ ያለው ወሳኝ ጉዳይ ነው። ታላቁ ህዝብ በህልውና አደጋ ላይ ወድቆ መገኘቱ ውርደታችን ቢሆንም ይህንን አደጋ ለመቀልበስና ወደሌለኛው ህዝባዊ ግርማዊ ነገን ለማዋለድ በትናንቱ ክቡር ታሪካችን፣ በነባራዊው አደጋ ወለድ ውርደታችንና በመፃኢው ተስፋችን መካከል ህዝባዊና ሀገራዊ ጥፋትን ለማስቆም እንደሻማ እያበራንና እየቀለጥን ከራሳችን ይልቅ ህዝባችንንና ሀገራችንን ማስቀደማችን አኩሪ ዘላለማዊ ታሪካችን ነው። ይህ ታሪክ የአዲሱ አማራዊ ትውልድ የእያንዳንዱ ፋኖ የወል ታሪክ ነው። ጓዶች ሆይ ከከፈልነው የእስከዛሬ መስዋዕትነት የከፋ ሊገጥመን አይችልምና የምንከፍለውን ክቡር መስዋዕትነት ከህዝባዊ አደጋውና ተስፋችን አንፃር በመመዘን ከነበረን የበለጠ መበርታትና መጽናት ይገባናል። ትግላችን የበለጠ ወደድል አነስተኛ መስዋዕትነትና ጊዜ መስፈንጠር እንዲችል ለማስቻል የተሰራው መዋቅራዊ ማሻሻያ የሁላችንም ርብርብ የወለደው ስኬት ነውና በያለንበት ለቀጣዩ ግዙፍ ህዝባዊና ሀገራዊ ግዳጅ ሁሌም ወትሮ ዝግጁነታችንን እንድናረጋግጥ እናሳስባለን። 2ኛ ለደጋፊዎቻችን በቅርብም በሩቅም የምትገኙ ውድ ደጋፊዎቻችን የእስከዛሬው ልዩ ልዩ ድጋፋችሁ መሬት ላይ ያለንን ቁመና በማጎልበት አፈፃፀማችንን አሻሽሏል፣ የጠላትን አቅም አዳክሟል፣ በዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ዘንድ ተሰሚነትን በማሻሻል ላይ ይገኛል። ለዚህም ከፍተኛ አድናቆትና ምስጋና እናቀርባለን።

ነጻ በወጡ ቀጠናዎች ሕዝባዊ ውይይቶች እንደቀጠሉ ነዉ። የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል ምስራቅ አማራ ቀጠና ሚኒሊክ ዕዝ ላስታ አሳምነዉ ኮር ነፃ ባወጣቸው ቀጠናዎች በሰሜን ወሎ ዞን ላስታ ወረዳ ከሚገኙ ቀበሌዎች መካከል ከድብኮ ቀበሌ ነዋሪዎች ጋር ህዝባዊ ውይይት ተደርጓል። ዛሬ በዕለተ ቅዳሜ በቀን 2/05/2018 ዓ.ም በሰሜን ወሎ ዞን በላስታ ወረዳ ከድብኮ ቀበሌ ነዋሪዎች ጋር ህዝባዊ ውይይት በማድረግ እና ማህበረሰባዊ የቀጣይ አቅጣጫ በማስቀመጥ ውይይቱ ባማረ መልኩ ተጠናቋል፡፡ በውይይቱ የተነሱ ሃሳቦችም 1 የትግሉ መነሻ ምክኒያቶች ምን ነበሩ? * ትግሉ አሁን ያለበት ጠቅላላ ሁኔታ * ትግሉ ያመጣው መልካም አጋጣሚ * የትግሉ ተግዳሮቶች * የትግሉ የቀጣይ አቅጣጫ *የግል ታጣቂዎችን በማደራጀት አካባቢያቸውን ከፋሽቱና ወራሪው የአብይ አህመድ ሰራዊት እንድጠብቁ ግንዛቤ ተስጥቷል። 2 መንግሥት አሁን ያለበት ወቅታዊ ሁኔታ * በወታደራዊ ቁመና * በፖለቲካ ተቀባይነት * የዲፕሎማሲ አቅም እና ሌሎችም 3 በራስ አስተዳደር እና በፀጥታ ጉዳይ * የሃገር ሽማግሌዎች የሰላም ኮሚቴዎች የቅሬ እና የእድር እንዲሁም የእምነት አባቶች ሚና እንዲሁም የወጣቱ ሃላፊነት * የህዝብ እና የኛ ግኑኝነት ምን መሆን አለበት 4 ይህን ትግል እንዴት የራሳችሁ እንደሆነ አምናችሁ ኮትኩታችሁ ታሳድጉታለችሁ? በሚሉ አንኳር ጉዳዮች ተነስተው ሰፊ ውይይት በማድረግ ህዝብ ላይ የነበረን የተዛባ አረዳድ እና ስሁት እሳቤ ለማጥራት ተሞክሯል፡፡ በዚህም ዉይይት ላይ ከዚህ ቀደም በላስታ ወረዳ ጊዜአዊ አስተዳደር ለቀበሌዉ አስተዳዳሪ የሆናሉ ተብለዉ የነበሩ የቀበሌዉ እና የጎጥ የሲቪል መዋቅር አመራሮችን ሹምሺር በማድረግ እንደ አዲስ ለአማራ ህዝብ እና ለአማራ ፋኖ ይጠቅማሉ ያላቸዉን አመራሮችን መድቧል። ማህበረሰቡም አዲስ በተሾሙት የቀበሌ እና የጎጥ አመራሮች ደስተኞች እንደሆኑ ተናግረዋል። በዚህ ህዝባዊ ዉይይት ላይም የአፋብኃ ምስራቅ አማራ ቀጠና ሚኒልክ ዕዝ ም/ወታደራዊ አዛዥ እና የላስታ አሳምነዉ ኮር ሰብሳቢ አርበኛ ወንድሙ ማሩ ፣የሚኒልክ ዕዝ ሚዲያ እና ኮሚኒኬሽን መምሪያ ኃላፊ አርበኛ ደረበ መኮንን ፣የላስታ ወረዳ ጊዜአዊ አስተዳደር ዋና አስተዳዳሪ 10 አለቃ ነጋ ፈንቴ ፣ የላስታ ወረዳ ጊዚአዊ አስተዳደር አመራሮች እና የእሸት ክ/ጦር አመራሮች ተገኝተዉ ማብራሪያ ሰጥተዋል። መረጃው የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል ምስራቅ አማራ ቀጠና ሚኒሊክ ዕዝ ሚዲያ እና ኮሚኒኬሽን ነው። የቴሌግራም ገፃችን👉https://t.me/MerebMedia24 ከአፋብኃ ቴዎድሮስ ዕዝ የአደረጃጀት ማሻሻያ መጠናቀቅ በማስመልከት የተሰጠ መግለጫ የአማራ ሕዝብ እንዲሁም ሀገራችን ኢትዮጵያ ረጅም እና ግርማዊ የትናንት ታሪክ ባለቤት መሆናችንን በሙሉ ባለቤትነት የምናምንበት ጉዳይ ነው። ለረጅም ዘመናት በፈተናዎች መካከል ሁሉ የረጋ ስርዓት መገንባትም ተችሎ ነበር። ሆኖም ከሺህ ለሚበልጡ ዓመታት በተለይም ከመካከለኛው ዘመን ጀምሮ የስልጣኔ ግጭት በወለደው የትውልዶች ጦርነት በዘመናዊው ታሪካችን በቀጥታ አማራን ጠላት በማድረግ ባደረገው ዘመቻ በውስጣዊ ድክመቶች ታግዞ የሀገረ መንግስት ግንባታውን በማቋረጡ ሀገራችንን ላልተረጋጋና ለሚለዋወጥ ስርዓት ህዝባችንንም ለከፋ የመጥፋት (ህልውና) አደጋ አጋልጦታል። ይህንን በራሳችን ወገኖች ኢትዮጵያዊያን ባለቤትነትና ቅጥረኝነት የሚመራ ውስብስብ ሀገራዊ እና ህዝባዊ አደጋ ለመረዳትና ለመግባባት ብሎም መፍትሔ ለማበጀት ብዙ ማገዶ ፈጅቷል። የአማራ ሕዝብ ራሱን በመዘንጋትና ሀገሩን በማስቀደም እየኖረ በራሱም ሆነ በሀገሩ ላይ የተፈጠረውን ታላቅ ተቃርኖ በጊዜው ባለመረዳቱ ራሱን ያገኘው ሀገሩን ተነጥቆ ሀገር አልባ ሆኖ እንዲሁም መንግስት መር በሆነ የዘር ማጥፋት በከፋ የመጥፋት አደጋ ውስጥ ሆኖ ነው። በእርግጥ አማራው በመጥፋት ላይ ያለ ህዝብ ነው። ይህንን ህዝባዊ አደጋ ለመቀልበስ ብሎም ሁለንተናዊ ህዝባዊ ጥቅሞቹን ለማስከበርና የተቋረጠ የሀገር ግንባታውን ዘመኑን በሚመጥን መልኩ ለማደስ፣ የቀጠለና አዲስ ስልጣኔ ለመገንባት አዲስ አማራዊ አብዮት በማካሄድ ላይ እንገኛለን። የዚህ ህዝባዊ ቁጣ መነሻ ምክንያት የህልውና አደጋው ቢሆንም አደጋውን ከመቀልበስ ባሻገር ግዙፍ ራዕይ የቀነበበ ህዝባዊና ሀገራዊ እንዲሁም ቀጠናዊና ዓለም አቀፋዊ መሻቶችን ቀርጿል። የህልውና ትግሉ ባለፉት ከ30 በላይ ወራት ራሱን በማጠናከርና ጠላትን በማዳከም እንዲሁም በዲፕሎማሲው መስክ የዓለም አቀፉን ማህበረሰብ ተደራሽ ለማድረግ ትኩረቱን አድርጎ ቆይቷል። በዚህም ሂደት ትግሉ የሚጠይቀውን መስዋዕትነት ስልታዊ በሆነ መልኩ በመቀነስ አያሌ ግቦችን አሳክቷል። የጠላትንም ወረራ በመመከትና ሊያደርስ ያቀደውን የዘር ማጥፋት መጠን ከመቀነስ ባሻገር በወታደራዊ፣ በፖለቲካ፣ በኢኮኖሚ፣ በመረጃና በዲፕሎማሲ ግንባሮች ሁሉ ማዳከም ተችሏል። በውጤቱም ጠላት አንዲት የእረፍት ቀን እንዳይኖረውና በአዲስ አበባም ድንጉጥ ሆኖ መጨረሻውን እንዲጠባበቅ ማድረግ ተችሏል፤ በዓለማችን ኃያላን መንግስታት ዘንድም የተናቀና የተጠላ እንዲሁም በሌላ ኃይል መቀየሩ አስፈላጊ መሆኑን የታመነበት ማድረግ ተችሏል። ይህንን ሁኔታ ለብዙ ወራት የገመገመውና በተግባርም በጥናትም ያረጋገጠው ቴዎድሮስ ዕዝ ስትራቴጅክ ሰነዶችን አዘጋጅቶ በ2017 ዓ.ም የክረምት ወራት ከአባልና አመራሩ እንዲሁም ከህዝቡና ደጋፊዎቹ ጋር የሁኔታ ትንተና እና ቀጣይ አቅጣጫ ላይ መግባባት በመፍጠር ህዝባዊ ትግሉን ወደላቀ ድርጅታዊ ቁመና የሚያሸጋግርና ለህዝቡ ሁነኛ ዋስትና፣ ለሀገራችንም ተዓማኒ የቀጣዩ ስርዓት ኃይል መሆናችንን የሚያረጋግጥ መዋቅራዊ ማሻሻያ ተቋማዊና ስልታዊ በሆነ መልኩ ታቅዶ ተከናውኗል። የቴዎድሮስ ዕዝ ኃይል ከአካል እስከ ዕዝ እንደገና በመዋቅራዊ ማሻሻያ በ 05ኮር፣ በ15 እግረኛ ክፍለ ጦር፤ በ01 ኮማንዶ ክፍለ ጦር እና ሻለቆች የተደራጀ ሲሆን ግዙፍ ኮሮች፣ ደምሳሽ ክፍለጦሮችና ሰባሪ ሻለቃዎች ተደራጅተው ለቀጣይ ህዝባዊና ድርጅታዊ ግዳጅ ዝግጁ ከመሆናቸውም ባሻገር የጠላትን የቡድን፣ የነፍስ ወከፍና ሜካናይዝድ መሳሪያዎች መማረክ ጀምረዋል። በሂደቱም የህዝብ አስተዳድርን እና የኃይላችንን ኃላፊነትና ግንኙነት በግልፅ በመለየት የጊዜያዊ መንግስት አስተዳድር (ጊዜአኮ) ማደራጀት ተችሏል። ዕዙ መዋቅራዊ ማሻሻያውን በጥናቱ መሰረት በዓብይ ኮሚቴ የተመራው ሲሆን የስራ አስፈፃሚ ኮሚቴው የውሳኔ ሰጭነት ሚናውን በየሰዓቱ ያረጋገጠበት ውጤታማ ድርጅታዊ ስምሪት ሆኖ ተመዝግቧል። በዚህም በየኮር የስምሪት ቀጠናው መልሶ ማደራጀቱን የመራችሁ ልዑካንና መላው የድርጅታችን በየደረጃው ያላችሁ አመራሮችና አባላት ላሳያችሁት ቁርጠኛ ርብርብ የአደረጃጀት ማሻሻያው መሪ ዓብይ ኮሚቴ ከፍተኛ አድናቆትና ምስጋና ያቀርባል። ይህ ግዳጃችሁ በትግላችን ታሪክ ውስጥ በደማቅ የሚመዘገብና የሚዘከር ጭምር ነው። ምክንያቱም ግዳጁ ሁነኛ ድርጅታዊ የአባልና አመራር እንዲሁም የጊዜያዊ መንግስት ቁመና የፈጠረና ትግሉን ወደ አዲስ ምዕራፍ በማሻገር ወደሚፈለገው ህዝባዊ ድል መስፈንጠሪያ መሠረት ነውና። በሂደቱ የተፈጠሩ ከለውጥ ተቋቋሚነት ጋር የሚገናኙ ቀላል የማይባሉ ፈተናዎች በመላው የድርጅታችን አባላትና አመራሮች ቁርጠኛ አቋም መከላከል የተቻለ ሲሆን በተገኘው ልምድና መረጃ የድርጅታዊ የሰው ኃይል ጥራት መረጋገጥና የአቋም ፍተሻ

ሠራዊታችን ይልቅ በማይረባ ሰበባሰበብ ድጋፋችሁን ማስተጓጎል እንደማይገባችሁና በጽናት ከጎናችን እንድትቆሙ  ጥሪያችንን እናቀርብላችሗለን። 3ኛ ለፀረ-ብልጽግና ትግሉ ማህበረሰብ ኢትዮጵያ ሀገራችን እና አጎራባቾቿ ሁሉ እየተተራመሱ ወደ ከፋ እልቂት እየገሰገሱ በሚገኙበት በዚህ አደገኛ ወቅት አተራማሹንና የእጅ አዙር ጦርነት ተላላኪውን አረመኔያዊ የብልጽግና አገዛዝ የሚታገለው ማህበረሰብ መበራከቱ ለሀገራችንም ሆነ ለቀጠናው ተስፋን አጭሯል። የነበረው ተናጠላዊ ጥረት ለጠላት ምቹ አጋጣሚ እንደሆነለት ሁሉ የተጀማመሩ መቀራረቦች ጠላትን ሲያስበረግጉት በአደባባይ ተመልክተናል። ኢትዮጵያዊያን የትግሉ ማህበረሰብ አካላት የጠላትን የጥፋት ፍጥነትና የመፍትሔውን አስቸኳይነት በመገንዘብ ከነበረው ቀርፋፋ አካሄድ የተላቀቀ ትብብር በማድረግ ከቀጠናው የፀረ-ብልጽግና ኃይሎች ጋር በመቀናጀት እንዲሁም የተሳለጠ የጋራ ዲፕሎማሲ በመስራት ድላችንን በአጭር ጊዜ እናደርግ ዘንድ ብርቱ ጥሪያችንን እናቀርባለን። በበኩላችን የህዝባችንንና የሀገራችንን ጥቅም ለሚያስከብር ትብብር ሁሌም ዝግጁነታችን እናረጋግጣለን። 4ኛ ለአማራ ሕዝብ የተከበርህው ህዝባችን ሆይ እኛ የገጠመንን ህዝባዊ አደጋ ለመቀልበስና መፃኢ ተስፋችንን በጎ ለማድረግ የአደጋው ባለቤት የሆነውን አረመኔያዊ አገዛዝ ጠላትን እየተናነቅን የምንገኝ መሆናችንን አቅፈህና ደግፈህ እያታገልህን ለምትገኘው ጀግና ህዝባችን ለማስረዳት የምንኳትን አይደለንም። ይልቁንስ የገጠመንን ውስብስብ አደጋ በቀላል መስዋእትነትና በአጠረ ጊዜ ለመቀልበስ ሠራዊታችንን ማጠናከር፣ በየዘርፉና በያለንበት ሁሉ የትግሉ አካል መሆንን ይጠይቃል። ራሳችንን ከጥፋት ለመከላከል ከጠላታችን የማጥፋት ርብርብ የላቀ ርብርብ ያስፈልጋል። 5ኛ ለኢትዮጵያዊያን ሁሉ የተከበርህው የታላቋ ኢትዮጵያ ሕዝብ ሆይ የዘመናት ተጨባጭ ህዝባዊ ፍላጎትህና ተስፋህ በውስን ቡድናዊ ፍላጎትና አንባገነናዊ እንዲሁም ሗላቀር የፖለቲካ ከባቢ ምክንያት አርቲስቱ እንዳለው ከዓለም ፊት እንዳልነበርህ ወደሗላ ቀርተህ በማይመጥንህና አዋራጅ ሁኔታ ውስጥ ትገኛለህ። በፖለቲካ ወለድ የጋራ ራዕይ ማጣት፣ የእርስ በርስ መጠራጠርና መጠቃቃት፣ ርሀብ፣ መፈናቀልና መሰደድ፣ አፈናና ከባድ የእንቅስቃሴ ገደብ እንዲሁም ከቅርብና ሩቅ ዓለም አቀፍ መገለልና መናቅ ገጥሞሀል። በጥቅሉ ተጨባጭ ሀገራዊ የጋራ የህልውና አደጋ ውስጥ እንገኛለን። በመሆኑም ለዚህ ሁሉ ችግር ባለቤት የሆነውን አረመኔያዊ አገዛዝ ለማስወገድና በሁላችን ድርሻና መዋጮ ላይ ቆማ ለሁላችን የምትሆን ታላቅ አፍሪካዊትና ዓለም አቀፋዊት ሀገር ለመገንባት የጋራ የመስዋዕትነት አሻራ ለማስቀመጥ እንድትንቀሳቀስና የሚደረጉ የቅርብም ሆነ የሩቅ የፀረ-ብልጽግና ትግል ትብብሮችን በቀናነት በመረዳትና በመደገፍ የመከራችንን ጊዜ በማሳጠር ተስፋችንን ቅርብ እንድናደርግ የከበረ ጥሪያችንን እናቀርብልሀለን። 6ኛ በጠላት አሰላለፍ ውስጥ ለምትገኙ አመራርና አባላት እናንተ በቀጥታ የጠላት አሰላለፍ ውስጥም ሆነ በባንዳነት የተሰለፋችሁ ዘመኑን ያልዋጃችሁ "ወገኖቻችን" ያደረሳችሁት ህዝባዊና ሀገራዊ በደል ከበቂ በላይ ሆኖ ሞልቶ የፈሰሰ መሆኑን ተረድታችሁ ከግለሰባዊ ጊዜያዊ ጥቅምና ፍላጎታችሁ በመላቀቅ ለህዝባዊና ሀገራዊ ጥቅምና ፍላጎቶቻችን ትገዙ ዘንድ ጥሪያችንን እናቀርብላችሗለን። ትግል ነውና በጠላት አሰላለፍ እስካላችሁ ድረስ መራራ እርምጃዎችን ወስደናል፤ ይህ ተጠናቅሮ የሚቀጥል ይሆናል። ሆኖም አሰላለፋችሁን ብታስተካክሉና ባሉን አማራጮች ሁሉ ብትቀላቀሉ የምህረት በራችን ሁሌም ክፍት መሆኑን እያሳወቅን ለራሳችሁም ሆነ ለቤተሰቦቻችሁ ብሎም ለህዝብና ሀገር የሚያኮራ ታሪክ ብቻም ሳይሆን የዘመን ግዳጅም ነውና ተጨማሪ ጊዜ እንደማታጠፉ ተስፋ እናደርጋለን። 7ኛ  ለዓለም አቀፍ ሰብዓዊ መብት ተቋማትና ለዓለም አቀፉ ማህበረሰብ የአማራ ህዝብ ሁኔታ፤ የኢትዮጵያ ሁኔታ ለውስጣዊ ሰብዓዊ ቀውስ ብቻም ሳይሆን ለአፍሪካ ቀንድና ለመካከለኛው ምስራቅ ሁሉ የትርምስ ምንጭና አካል እየሆነ በመሆኑ የትርምሱ ምንጭ የአረመኔው አብይ አህመድ አገዛዝ እንዲያበቃና በኢትዮጵያ፣ በአፍሪካ ቀንድና በመካከለኛው ምስራቅ የዴሞክራሲ አየር ነፍሶ ነፃነት፣ ሰላም፣ ፍትህና እኩልነት እንዲረጋገጥ በሰብዓዊነት ላይ በሚፈፀሙ ወንጀሎች፣ በጦር ወንጀል፣ በዘር ማጥፋት ወንጀል የተጨማለቀውን አረመኔያዊ አገዛዝ ባለመደገፍና በማውገዝ፣ ልዩ ልዩ አስገዳጅ የለውጥ ማዕቀቦችን በመጣልና የትግሉን ማህበረሰብ በመደገፍ ዓለም አቀፋዊ ግዴታችሁን እንድትወጡ እያሳሰብን ለመሰል ትብብር ቀናኢ መሆናችንን እናሳውቃለን። በተጨማሪም በየአውደ ውጊያው የሚማረኩ እና ወዶገብ የጠላት ሠራዊት አባላትና አመራሮችን ዓለምአቀፍ የጦር ህግን ተከትለን ለመያዝ እየተጋን ያለን መሆኑ ታውቆ ያደረ ጉዳይ ነው። በአሁኑ ወቅት ለረጅም ወራት የቆዩ እና አዳዲስ ምርኮኛና ወዶ ገቦች በስፋት በጊዜያዊ ማቆያ ካምፖቻችን የሚገኙ ሲሆን እንደ ቀይ መስቀል ያሉ የሰብዓዊ መብት ተቋማትና ረጅዎች ፈጣን ሰብዓዊ ድጋፍ በማቅረብ ኃላፊነታችሁን እንድትወጡ እና በተለይም ዓለምአቀፉ የቀይ መስቀል ማህበር ምርኮኞችን እንደተለመደው ለአገዛዙ የአየር ጥቃትና መሰል የከፋ አደጋ ከመጋለጣቸው በፊት በፍጥነት እንዲረከበን ጥሪያችንን እናቀርባለን።በመጨረሻም በጉጉት የምትጠብቁት አማራዊ አንድነታችን የመጨረሻው ከፍታ ላይ የደረሰ ሲሆን ሳምንት ባልሞላ ጊዜ ውስጥ ትልቁን ብስራት ይዘን እንወጣለን ። አፋብኃ ቴዎድሮስ ዕዝ

የጠላት ሀይል እየተናደ ነው ተቋሙኝ እየፈረሰ ነው ‼️ ጥር 01/2018 ዓ.ም ከመከላከያ ተቋም በመውጣት በዛሬው እለት 201ኛ ክር 54ኛ ክፍለ ጦርን ተቀላቅለዋል። 1ኛ ዳንኤል ፈይሳ 602ኛ ኮር
+1
የጠላት ሀይል እየተናደ ነው ተቋሙኝ እየፈረሰ ነው ‼️ ጥር 01/2018 ዓ.ም ከመከላከያ ተቋም በመውጣት በዛሬው እለት 201ኛ ክር 54ኛ ክፍለ ጦርን ተቀላቅለዋል። 1ኛ ዳንኤል ፈይሳ 602ኛ ኮር 25ኛ ክ/ጦር 1ኛ ሬጅመንት 2ኛ ጫላ ጉታ 602ኛ ኮር 25ኛ ክ/ጦር 1ኛ ሬጅመንት የነበሩ በዛሬው እለት በአማራ ላይ እየተፈፀመ ያለውን ግፍ እና መከራ እያየን መቋቋም ስላቃተን በቀሪ ጊዜያችን ህዝባችን ለመካስ ቆርጠን ተነስተናል። ጥር 01/2018 ዓ.ም አዲስ ትውልድ፣ አዲስ አስተሳሰብ፣ አዲስ ተስፋ የቴወድሮስ ዕዝ 201ኛ ኮር ህዝብ ግንኙነት

የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል ደቡብ አማራ ቀጠና አሳምነው ዕዝ ዓፄ ዘርዓያዕቆብ ፩ኛ ኮር በፍቃዱ በላይ ክፍለ ጦር ድልን እየተቀናጀ ይገኛል!! የአብይ አህመድ አረመኔያዊ ሰራዊት ኃይል በየትኛውም የአማራ ግዛቶች በመግባት እንደ ቄራ ከብት እያርደንና እያሳደደን የቆየ መሆኑ የሚታወቅ የምድር ሀቅ ነው ሁኖም በሸዋ ደራ የበፍቃዱ በላይ ክፍለጦር ከሰው በላው አብይ አህመድ ሰራዊት ጋር ከፍተኛ ተጋድሎ እያደረገ ይገኛል። በዚሁም በትናትናው ዕለት ማለትም በቀን 01/05/2018 ዓ.ም ከጀማ ወንዝ እስከ ሰለልኩላ በሻለቃ አባዬ አብዬ የሚመራው የጀማ ዘቦቾ ባደረጉት ትንቅንቅ ጠላት ሙትና ቁስለኛ የሆነ ሲሆን እግረኛ ኃይሉም በኦራል ሲንቀሳቀስ የነበረ ተጨማሪ ኃይል ተደምስሷል። በዚህ አውደ ውጊያ ያለምንም የወገን መሰዋትነት የመጣው ድልም የዓፄ ዘርዓያዕቆብ ፩ኛ ኮር የበፍቃዱ በላይ ክፍለጦርን የሽምቅ ውጊያ ብቃትና አይን ከቅንድብ ለይቶ የመምታት ብቃት በጠላት ዘንድ ከፍተኛ ድንጋጤ እንዲፈጥር በማድርግ እየሰሩ ይገኛል።በተመሳሳይ ማሞ መሳለሚያ አገዛዙ ለመረጃ በሞተር የላከው ሚኒሻ በአሳምነው ተርቦች እስከወዲኛው የተሸኘ ሲሆን የደራ አማራን ህዝብ ሳልጨርስ እንቅልፍ አልተኛም ያለው ብልፅግና የጫካው ሸኔን ተጠጉልኝ በማለት ጩኸቱን እያሰማ ይገኛል። ስለሆነም ማህበረሰቡ ከመሰል ጥቃቶች ራሱን እንዲጠብቅ፤እንዲሁም ጥር በተለይም በክርስቶስ እምነት ዘንድ የአስተርዮ ባዓል በሰላም እንዲከበር ማህበረሰቡና አባት አርበኛው ሳይዘናጋ አከባቢውን እንዲጠብቅ በዚሁ አጋጣሚ መልዕክቴን ማቅረብ እወዳለሁ። መረጃው የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል ደቡብ አማራ ቀጠና አሳምነው ዕዝ የዓፄ ዘርዓ ያዕቆብ ፩ኛ ኮር ህዝብ ግንኙነት ኃላፊ አርበኛ አማርረ ታዘዘ ነው " ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን" ‎አፋብኃ ደቡብ አማራ ቀጠና አሳምነው ዕዝ የህዝብ ግንኙነት ዜና ክፍል ጥር 03/2018 ዓ.ምየአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል ደቡብ አማራ ቀጠና አሳምነው ዕዝ ዓፄ ዘርዓያዕቆብ ፩ኛ ኮር በፍቃዱ በላይ ክፍለ ጦር ድልን እየተቀናጀ ይገኛል!! የአብይ አህመድ አረመኔያዊ ሰራዊት ኃይል በየትኛውም የአማራ ግዛቶች በመግባት እንደ ቄራ ከብት እያርደንና እያሳደደን የቆየ መሆኑ የሚታወቅ የምድር ሀቅ ነው ሁኖም በሸዋ ደራ የበፍቃዱ በላይ ክፍለጦር ከሰው በላው አብይ አህመድ ሰራዊት ጋር ከፍተኛ ተጋድሎ እያደረገ ይገኛል። በዚሁም በትናትናው ዕለት ማለትም በቀን 01/05/2018 ዓ.ም ከጀማ ወንዝ እስከ ሰለልኩላ በሻለቃ አባዬ አብዬ የሚመራው የጀማ ዘቦቾ ባደረጉት ትንቅንቅ ጠላት ሙትና ቁስለኛ የሆነ ሲሆን እግረኛ ኃይሉም በኦራል ሲንቀሳቀስ የነበረ ተጨማሪ ኃይል ተደምስሷል። በዚህ አውደ ውጊያ ያለምንም የወገን መሰዋትነት የመጣው ድልም የዓፄ ዘርዓያዕቆብ ፩ኛ ኮር የበፍቃዱ በላይ ክፍለጦርን የሽምቅ ውጊያ ብቃትና አይን ከቅንድብ ለይቶ የመምታት ብቃት በጠላት ዘንድ ከፍተኛ ድንጋጤ እንዲፈጥር በማድርግ እየሰሩ ይገኛል።በተመሳሳይ ማሞ መሳለሚያ አገዛዙ ለመረጃ በሞተር የላከው ሚኒሻ በአሳምነው ተርቦች እስከወዲኛው የተሸኘ ሲሆን የደራ አማራን ህዝብ ሳልጨርስ እንቅልፍ አልተኛም ያለው ብልፅግና የጫካው ሸኔን ተጠጉልኝ በማለት ጩኸቱን እያሰማ ይገኛል። ስለሆነም ማህበረሰቡ ከመሰል ጥቃቶች ራሱን እንዲጠብቅ፤እንዲሁም ጥር በተለይም በክርስቶስ እምነት ዘንድ የአስተርዮ ባዓል በሰላም እንዲከበር ማህበረሰቡና አባት አርበኛው ሳይዘናጋ አከባቢውን እንዲጠብቅ በዚሁ አጋጣሚ መልዕክቴን ማቅረብ እወዳለሁ። መረጃው የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል ደቡብ አማራ ቀጠና አሳምነው ዕዝ የዓፄ ዘርዓ ያዕቆብ ፩ኛ ኮር ህዝብ ግንኙነት ኃላፊ አርበኛ አማርረ ታዘዘ ነው " ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን" ‎አፋብኃ ደቡብ አማራ ቀጠና አሳምነው ዕዝ የህዝብ ግንኙነት ዜና ክፍል ጥር 03/2018 ዓ.ም

በአብይ አህመድ አገዛዝ ታፍሰው ብር ሸለቆ ወታደራዊ ማሰልጠኛ ተቋም የገቡ 20 ምልምል ሠልጣኝ ሠራዊት አፋብኃ ቴዎድሮስ ዕዝ 109ኛኮር 88ኛ ክ/ጦርን ተቀላቀሉ * በምዕ/ጎጃም ዞን ብር ሸለቆ ወታደ
+1
በአብይ አህመድ አገዛዝ ታፍሰው ብር ሸለቆ ወታደራዊ ማሰልጠኛ ተቋም የገቡ 20 ምልምል ሠልጣኝ ሠራዊት አፋብኃ ቴዎድሮስ ዕዝ 109ኛኮር 88ኛ ክ/ጦርን ተቀላቀሉ * በምዕ/ጎጃም ዞን ብር ሸለቆ ወታደራዊ ማሰልጠኛ ተቋም ከኦሮሚያ ክልልና ከተለያዩ የሀገሪቱ አካባቢዎች ታፍሰው ወደ ብር ሸለቆ ወታደራዊ ማሰልጠኛ ተቋም ከመጡት መካከል 20 ወጣቶች ተልዕኮ በተሰጣቸው ቀኘዎቻችን በኩል ወደ 109ኛ ኮር 88ኛ ክ/ጦር እንዲቀላቀሉ ማድረግ ተችሏል። ወጣቶቹ ከት/ቤት፣ከመዝናኛ ቦታ(ከፑል ቤት)፣ከተለያዬ የስራ ቦታ ታፍሰው እንደመጡና ቤተሰቦቻቸው ያሉበትን ቦታ አሁን ላይ እንደማያወቁ የገለጹ ሲሆን አብዛኛው ምልምል ሰልጣኝ የመውጫ መንገዱን ካገኘው የመክዳት ፍላጎት እንዳለው ተናግረዋል። 👉ከአሁን በፊት በ109ኛ ኮር :-          1.በ77ኛ ክ/ጦር 58 ምልምል ሰልጣኞችን          2.በ99ኛ ክ/ጦር 42 ምልምል ሰልጣኞችን በድምሩ 100 ሰልጣኞችን ወደ አፋብኃ ቴዎድሮስ ዕዝ 109ኛ ኮር ተቀላቅለዋል።          አዲስ ትውልድ!አዲስ አስተሳሰብ!አዲስ ተስፋ! 109ኛ ኮር ህ/ግንኙነት ጥር 02/2018 ዓ.ም