ፍኖተ- አማራ ሚዲያ (Finote- Amhara ) Midea
Открыть в Telegram
የተመሠረተው የአማራን ሕዝብ ለማንቃት፣ ለማደራጀት እና ለማስተባበር ነው። የአማራ ሕዝብን ✅ ፖለቲካዊ ✅ ማህበራዊ ✅ ኢኮኖሚያዊ ታሪካዊ ጥያቄዎችን ለማሰማት እና የአማራን ሕዝብ በማንቃት ሰፊውን ሕዝብ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ይሰራል። ወደዱም ጠሉም የኃላ ታሪካችን በእኛ እጅ ይፃፋል። አማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ ( አፋብን)
Больше3 536
Подписчики
+2524 часа
+3407 дней
+72430 дней
Архив постов
+1
"ታሪክ በደም እና በአጥንት እንጅ በቀለም አይፃፍም"
====================================
ቆራጡ፣ጀግናው፣ሃሞተ ኮስታራው እና አይበገሬው አርበኛ ይገረም ከበደ አፈሩ ይቅለልህ አንበሳየ!!
"የማይበገረው የጥቁር አንበሳ መንፈስ"
አርበኛ ይገረም ከበደ በአማራ ህዝብ የህልውና ትግል ታሪካዊ የሚባሉ ተጋድሎዎችን ሲመራ ቆይቷል።
አባቶቻችን በጠላት መትረየስ ፊት በባዶ እጃቸው የቆሙት፣ ከኋላቸው ያላትን አገርና ሕዝብ እያዩ ነበር።ያኔ፣ ጥይት በናዳ ሲወርድ፣ ተራራው ሲንቀጠቀጥ፣ እነዚያ የቁርጥ ቀን ልጆች አልሸሹም። "አገሬ ከምትዋረድ እኔ ልቀበር" በማለት የአጥንታቸውን አጥር ሰርተው ለዛሬው ማንነታችን መሰረት ጥለዋል። ያ ደምና ወኔ ዛሬም በእኛ ትውልድ የደም ስር ውስጥ ይፈስሳል።
👉አርበኝነት ማለት መሳሪያ መያዝ ብቻ አይደለም፤
👉አርበኝነት ማለት ለፍትህ መቆም እና ለደካሞች መከታ መሆን ነው።
👉 አርበኝነት ለህዝብ ክብር እስከ መጨረሻው ታምኖ መስዋአት መሆን ነው።
ወንድሞቼ እናንተ እውነተኛ አርበኞች ሆናችሁ አልፋችሗል፤
አላማችሁንም እናሳካዋለን🙏
@ አማራ ፋኖ ሆይ አደራህን ተወጣ፤ አንተ የታላላቅ ጀግኖች ተተኪ ነህ።
ክንድህ የአገር ምሶሶ፣ ዐይንህ የነጻነት ጠባቂ ነው።
ጠላት ባንተ ፊት ይንቀጠቀጣል፣ ሕዝብህ ባንተ ይመካል!!
ክብር ለጀግኖቻችን!!
ድል ለሰራዊታችን!
ሱሪ ወንድሜ ይገርም ወንድሜ ነፍሳችሁ በሰላም ትርፍ
በጎዛምን ወረዳ የቦቅላና ቀኝ አቦ ቀበሌዎች በተፈፀመ የጀትና ድሮን ድብደባ 5 (አምስት) ንፁሀን ሲገደሉ 9 (ዘጠኝ) የሚደርሱት ከባድ ቁስለኛ ሁነዋል።
መጋቢት 21/2018 ዓ.ም
=======================================
ከሳምንታት በፊት አብይ አህመድ የጎሬቤት ሀገራትን ባስፈራራበት yak-130 ተዋጊ ጀት በጎዛምን ወረዳ በየቦቅላና ቀኝአቦ አካባቢዎች የንፁሃንን መንደር በመደብደብ መንግስታዊ የዘር ፉጅቱን አጠናክሮ ቀጥሎበታል።
ከንጋቱ 11:30 ጀምሮ የድሮን አሰሳ ከጀመረ በኋላ ከረፋዱ 4:10 አካባቢ የአካባቢው ማህበረሰብ በቅድስት ድንግል ማርያም ስም ማህበር ሰይመው ፀበል የሚጠጡ 45 (አርባ አምስት) ምዕመናን ኢላማ ያደረገ ሲሆን በተደረገ ቅድመ መከላከል የተሰበሰቡ ማህበርተኞችን ከቦታው በፍጥነት በማስነሳት የድሮን ቦቡ በተሰበሰቡበት ቦታ ኢላማ አድርጎ ሲወድቅ የማህበርተኞችን ህይወት መታደግ ተችሏል።
ቀን 5:00 ሰዓት ገደማ እንዲሁ ተጨማሪ የድሮን ድብደባ በአካባቢው ቢደረግም ጉዳት ማድረስ ግን አልቻለም ።
ከቀኑ 5:40 በቀኝአቦ ቀበሌ በyak 130 ተዋጊ ጀት በተከታታይ በፈፀመው ጥቃት የአየር ድብደባውን ለማለፍ በዛፍ ውስጥ የተሸሸጉ ንፁሃንን የጥቃቱ ሰለባ ሁነው 5 (አምስት) ሲገደሉ 9 (ዘጠኝ) የሚደርሱት ከባድ ቁስለኛ ሁነዋል።
ማህበርተኞች በሚሰበሰቡበት ቀን እና ገበያ በዋሉ ንፁሃኖች ላይ የድሮን እና የጀት ድብደባ የፈፀመው የአረመኔው ስርዓት እንዲሁ ከቀኑ 7:00 ተጨማሪ ቦምቦችን የወረወረ ቢሆንም ጉዳት ማድረስ ግን አልቻለም።
የጋሻው መርሻን የተጠናከረ ጥቃት ይፈፀም ጥሪን የተቀበለው አብይ አህመድ ከጠዋቱ 11:30 እስከ ቀን 10:45 የአርሶ አደሮችን መንደር በጀትና ድሮን ሲያጋየው ውሏል። የምርጫ ቅስቀሳ መድረክ በሚል በአገዛዙ ልሳን EBC የቀረቡት እነ ጋሻው መርሻ መንግስት አቅሙን ተጠቅሞ ጽንፈኛውን አላጠፋም ባሉት መሰረት በራሳቸው ህዝብ ላይ ለተጨማሪ እልቂት የአረመኔውን ስርዓት ሲጋብዙት ተመልክተናል።
ምርጫን የስልጣን ዘመን ማራዘሚያ ከማድረግ ባለፈ የአማራ ህዝብ እንዲጠፋ ጥሪ የቀረበበት የ7ኛው ዙር ምርጫ ከዲሽቃ እና ዙ-23 ከፍ ባለ ሁኔታ በጀትና በድሮን ታጅቦ ንፁሀን እንዲገደሉ በብልጽግና ቤት ተጨማሪ ድግስ የተዘጋጀበት የጠላቶቻችን መዶለቻ መድረክ በመሆኑ አምርረን የምንፋለም ይሆናል።
አዲስ አስተሳሰብ ! አዲስ አስተሳሰብ ! አዲስ ተስፋ!
የአፋብን ቴዎድሮስ ዕዝ 206ኛ ኮር ህዝብ ግንኙነት
+2
አብይ አህመድ ትናንትና መጋቢት 21/2018 ምስራቅ ወለጋ ዞን ሲቡ ስሬ ወረዳና ጉዳያ ቢላ ወረዳ ላይ በተዋጊ አውሮፕላኖች ቦንብ ሲያዘንብ ውሏል።
ይህ በምስሉ የምትመለከቱት ሮኬት ቦምብ በቀጠናው ያለው ፋኖ እና ሲቪሊያን ላይ አነጣጥሮ የጣለው ቢሆንም ቦንቡ አፈራማ ቦታ ላይ በማረፍ እና በመክሸፉ ምክንያት ያደረሰው ጉዳት የለም።
በመላው አማራ ክልል እና በወለጋ አብይ አህመድ ለምርጫ የሚወዳደረው¡ ብልፅግና እያዘነበው ያለው የጀት እና የድሮን ቦንቦችን ነው።
በነገራችን ላይ በአብይ ዘመን እንዲህ አይነት ሮኬት ቦንቦች በብዛት ጥቅም ላይ የዋሉት ከፋኖ ጋር ባደረገው ጦርነት ብቻ ነው።
በአርበኛ ተሾመ አበባው ደህንነቱ ተጠብቆ የቆየው የእብናት ወረዳ አስተዳደር ጽ/ቤት በስርዓቱ ወታደሮች ተቃጠለ‼️
〰️➠〰️➠〰️➠〰️〰️➠〰️
"የፋኖን ስም በማስጠፋት የፖለቲካ ትርፍ ለማግኘት መድከም የተሸናፊነት ምልክት ነው"
〰️➠〰️➠🌿〰️➠〰️➠〰️
በባለፈው ጊዜ አርበኛ ተሾመ አበባው የተቋማትን ደህንነት እየጎበኛ የሚያሳይ መረጃ ይፋ ማድረጋችን ይታወሳል። ደህንነታቸው ተጠብቆ ከተጎበኙ ተቋማት ውስጥ አንዱ አስተዳደር ጽ/ቤት ነበር። ነገር ግን በዛሬው እለት የስርዓቱ ነውረኝነት ፋኖ ጠላት ጋር ውጊያ እያደረገ ባለበት ቅጽበት የፋኖን ስም ያስጠፋልኛል ብሎ በማሰብ ወረዳ አስተዳደር ጽ /ቤቱን አቃጥለውታል። ህዝብ ግን እውነቱን ያውቃል ወረዳውን በተቆጣጠርንባቸው ጊዚያት የህዝብ ሀብት የሆኑ ተቋማት ደህንነት እንዴት ስናስጠብቃቸው እንደነበር ህዝብ እውነቱን ያውቃል።
ነገር ግን የአማራን ህዝብ ማጥፋት ሀብት ንብረቱን ማውደም ግብ አድርጎ የተነሳው ስርዓቱ አርበኛ ተሾመ አበባው ተቋሙን መጎብኘቱ ደህንነቱ እንዲጠበቅ ማድረጉ የተሸናፊነት እና የበታችነት ስሜት ስለተሰማቸው አውድመውታል።
ይህ ብቻ አይደለም ጠላት የፋኖን ምት መቋቋም ሲያቅተው የዘፈቀደ የሞርተር ተኩስ እየተኮሰ
➠ ቤተ ክርስቲያናትን
➠ የአርሶ አደር መኖሪያ ቤቶችን አውድሟል
➠ የቁም እንስሳትን
➠ ከብት እረኞችን ገድሏል
በእርግጥ የስርዓቱ ጥላች የአማራን ህዝብ ከምድረ ገጽ ማጥፋት እንደሆነ የሚፈጽማቸውን ዘግናኝ ድርጊቶችን ማየት ብቻ በቂ ነው::
በዘፈቀደ ተኩስ ሲያደርግ የዋለውን አማራን የማጥፋት ተግባሩ ከተማውንም የከተማውን ህዝባችን እንደሚያወድመው ምንም ጥርጥር የሌለው ጉዳይ ነው።
ህዝባችን ላይ የሚያደርሰውን ግፍ እና ጭፍጨፋ እንዲሁም ከተማዋን የማውደም የጠላትን ዕቅድ ግንዛቤ ውስጥ በማስገባት ፋኖ አካባቢውን ትንሽ ወደ ኃላ መልቀቅ አስፈላጊ መሆኑን በመረዳት ለህዝባችን ደህንነት ስንል አካባቢውን በተወሰነ ርቀት ለቀቅ አድርገናል።
ቋሚ ምስል አርበኛ ተሾመ ተቋማትን ሲጎበኝ
ድል ለአማራ ፋኖ‼️
የጎንደር ጠቅላይ ግዛት ዕዝ 204ኛ አስቻለው ደሴ ኮር ህዝብ ግንኙነት ክፍል
በጀግኖች ደም እና አጥንት የተገነባው አይበገሬው 64ኛ በላይ ዘለቀ ክፍለ ጦር የተሰጠውን ግዳጅ በልዩ ሁኔታ እየተወጣ ይገኛል።
64ኛ በላይ ዘለቀ ክ/ጦር መጋቢት 22/2018 ዓ.ም
የአፋብን ቴዎድሮስ ዕዝ 201ኛ ኮር 64ኛ በላይ ዘለቀ ክፍለ ጦር በኩንቡር፣ በዳንግላ እና ዱሪቤቴ መኃል፣ በብራዳማ እና ቁይ ከተማ ከሌሎች ክፍለ ጦሮች ጋር በመቀናጄት እንዲሁም በሸበል በረንታ እና እነማይ ወረዳ በተለያዩ ቦታዎች ድርጅቱ የተሰጠውን የትኛውም አይነት ግዳጅ በልዩ ብቃት ተወጥቷል።
የጀግኖች አረበኞች መፍለቂያ ምድር እነማይ እና ሸበል በረንታ ቀጠና የሚገኘው አይበገሬው 64ኛ በላይ ዘለቀ ክፍለ ጦር በድርጅቱ የተሰጠውን የትኛውም አይነት ግዳጅ በልዩ ብቃት እና ጀግንነት በተሞላበት ከባድ ውጊያዎችን በማካሄድ የአምባገነኑ አብይ አህመድ አገዛዙ ቅጥርኛ ሰራዊት ቅስም በመስበር በአንድ መር ሶስት ውጊያዎችን በማካሄድ ድል ተቀዳጅቷል።
በበሳል፣ አስተዋይ፣ አርቆ አሳቢ የሲቪል እና የጦር ጠበብቶች አመራሮ የሚመራው አይበገሬው 64ኛ በላይ ዘለቀ ክፍለ ጦር በወታደራዊ አመራር እና አባላት የጠላትን ግንባር በመበሳት በረካታ የአገዛዙ ኃይል መደምሰሳቸውን እና መማረካቸውን ጠላት ከፍተኛ የሆነ መስዋትነት መክፈሉን ክፍለ ጦሩ በተጨባጭ ማስረጃ አረጋግጦል።
በየካቲት ወራቶች በኩንብር፣ ብራዳማ ከሌሎች ኮሮች ጋር በመቀናጄት በርካታ የጠላት ኃይል በመደመሰስ ትልቅ ጀብድ በመስራት ታሪክ የሰረው መጋቢት 17/2018 ዓ.ም በሸበል በረንታ እና ቁይ ከተማ እንዲሁም መጋቢት 21/2018 ዓ.ም በሸበል በረንታ ቁጥቋጥ እና እነማይ ሰቀላ ገብርኤል ቀበሌ አይበገሬው ክፍለ ጦሩ ባካሄደው ውጊያ ማግስት የደረሱ ትክክለኛ መረጃ መሰረት የአብይ አህመድ ቅጥረኛ ሰራዊት ሙት እና ቁስለኛው እየጨመር መምጣቱን ከውስጥ የመረጃ ምንጮቻችን እና ህዝባችን በጅምላ የቀበርውን ማስረጃ ይዘናል። ክፍለ ጦሩ በኩንቡር፣ በዳንግላ እና ዱሪቤቴ መኃል፣ ብራዳማ እና ቁይ ከተማ፣ ከሌሎች ክፍለ ጦሮች ጋር በመቀናጄት እንዲሁም በሸበል በረንታ እና እነማይ ባአካሄዳቸው ግዳጆች የተገኙ ድሎች:-
➤150 በላይ የአገዛዙ መንገድ መሪ ቅጥርኛ ፖሊስ፣ አድማ ብተና፣ ማሊሻ እና የአገዛዙ አራ*ጅ ሰራዊት አባላትን ደምስሶል።
➤ከ80 በላይ የጠላት ኃይል ከባድ እና ቀላል ቁስለኛ አድረጓል።
➤22 ክላሽ እንኮቨ መሳሪያ እና ጥቁር ክላሽ መሳሪያ ገቢ አድርጓል።
➤1,000 የክላሽ ተተኮሽ ገቢ አድርጓል።
➤11 ኤፍ ቦንብ ገቢ አድርጓል።
➤10 ካዘና ገቢ አድርጓል።
➤1 መጋናኛ ጨምሮ ገቢ አድረጓል።
ክፍለ ጦሩ በሶስት ቀጠና ግዳጆች በአካሄደው ከባድ ውጊያ ማህበርሰብን ይዘረፍ እና ያሰቃዩ የነበሩ የአገዛዙ ኃይልን ከፊት ሆነው መንገድ ይመሩ የነበሩ ማርገ ቢሶችን ቀንደኛ የአገዛዙ መረጃ ደህንነቶች፣ ፖሊስ፣ መንገድ መሪ ቀንደኛ ቅጥርኛ ሚሊሻዎች እና የአገዛዙ ቅጥርኛ አስፈፃሚ መከላከያ አባላትን ደምስሶል።
የበላይ ትንፋሹ አይበገሬው 64ኛ ክፍለ ጦር መጋቢት 17/2018 ዓ.ም በመርገጭ ከተማ በአካሄደው ከባድ ውጊያ በከተማ የሚገኘው የማህበርሰብ ክፍልን ጨምሮ በቀጠናው የሚገኝ የህብረተሰብ ክፍል ለጠላት መንገድ ይመሩ የነበሩ ሚሊሻዎችን ክፍለ ጦሩ ማስወገዱ በጣም እንዳስደሰታቸው እና ሁሌም ማህበረሰቡ ከጎናቹህ እንደሆነ በአክብሮት አሳውቀዋል።
አይበገሬው ክ/ጦር መሪያችን ራስ አርበኛ ዘመነ ካሴ እና ድርጅቱ የሚሰጠውን የትኛውም አይነት ግዳጅ ዛሬም እንደ ትላቱ የተሻለ ስራ እየሰራ የገኛል። ክ/ጦሩ የቀጠናው ሚዛን አስጠባቂ ኃይል ያለው መሆኑ እና በቀጠና ጎጃምን ከወሎ እና ከሽዋ የሚያገናኘው የአባይ ወንዝ ተፋስ ባለቤት በመሆኑ በሽዋ እና በወሎ የሚገኙ ወንድሞቻችን ጋር በመተሳሰር ድርጅቱ ከወንዝ ማዶ ለሚያደረጋቸው የትኛውም አይነት ግዳጆች ኮሊደር የሆነ ቦታ ባለቤት በመሆኑ ወደፊት የተሻለ ግዳጆችን አስተሳስሮ ለመስራት በስነ ልቦናው ዝግጁ የሆነ ሰራዊት ገንብቷል።
የአገዛዙ የጠላት ኃይልን ለመደምሰስ ሲዋጉ በአይን ሙሉ የማይታዩ ተወረዋሪ ጀግኖች፣ በትጥቅ ትግሉ ጓዳዊ ዝምድና የገባቸው ጀግኖች እንቁ ታጋዩቻችን፣ ወንድሞቻችን ለአማራ ህዝብ የህልውና ትግል ብለው በተለያዩ ግዳጆች በክብር እና በጀግንነት አንድያ ነፍሳቸውን የሰጡ ለህዝባቸው እና ለድርጅታቸው ታምነው መስዋት የሆኑ የክፍለ ጦሩ አመራር እና አባላት አደራ እንዳለብን በማስገንዘብ ድርጅታችን አፋብን የሚሰጠንን የትኛው አይነት ግዳጅ ለመወጣት ዛሬም እንደ ትላንቱ የደጅ አዝማች በላይ ዘለቀ ልጆች ዝግጁ ሆነዋል።
ክብር ለአማራ ህዝብ የህልውና ትግል ብለው ለህዝባቸው ታምነው በጀግንነት መስዋት ለሆኑ የክፍለ ጦሩ አመራርና አባላት 😭😭😭
አዲስ ትውልድ፣ አዲስ አስተሳሰብ፣ አዲስ ተስፋ!!
መጋቢት 22/2018 ዓ.ም
አፋብን ቴዎድሮስ ዕዝ 201ኛ ኮር 64ኛ ክፍለ ጦር ሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ
ይህ የወላድ እናቶች የህክምና አገልግሎት ማጓጓዣ አምቡላንስ በአረመኔው ዓብይ አህመድ የድሮን ጥቃት ጉዳት ደርሶበት ከጥቅም ውጭ ሁኖ ወድሟል።
በእስቴ ወረዳ ቁሞ በነበረ አምቡላንስ ላይ የድሮን ጥቃት ያደረሰው አረመኔው አገዛዝ በሲቪሊያን መገልገያ አምቡላንስ ላይ ያነጣጠረ ጥቃት ይሰንዝር እንጅ በሰው ላይ ለጊዜው የደረሰ ጉዳት የለም።
ህልውናችን በአርበኝነታቸን!!
ዮሐንስ ንጉሱ ሙጨ
አንድ ሰው አኩርፎ ሲወጣ የሚቀንስ ወይንም ደግሞ ፈተና ውስጥ የሚወድቅ ትግል አልተጀመረም። የፋኖ የነፃነት ትግል ከተጀመረ ጀምሮ እየወጡ ያሉት የትግሉን አላማ በውል ያልተረዱ ናቸው። እነዚህ አይነት ታጋዮች በብዛት በትግል ሜዳ ላይ የማይገኙ ሲሆን ራሳቸውን በማህበራዊ ሚዲያ በትግሉ ውስጥ እንደዋና ተዋናይ በመምሰል የሚቀርቡ ናቸው። እነዚህ አይነት ሰዎች ቢወጡ ትግሉን የሚጠቅሙ እንጂ የሚጎዱ አይደሉም። እስካሁን ካስተዋልኩት መካከል በብዛት ራሳቸውን በሚዲያ ያገነኑ አንዳንድ ስለ ትግሉ ዓላማ በውል ያልተረዱ እውነተኛ ፋኖ ያልሆኑ አካላት ያልተገባ ነገር በሚዲያ በማሰራጨት አንዳንድ ጊዜም በፋኖ መካከል ያለመግባባት ችግር እንዳለ በማስመሰል የሚያቀርቡ ራሳቸውን ቁልፍ ሰው አድርገው የሚያስቡ ናቸው። ትግል ፈታኝ ስለሆነ መሰልቸት የለብንም! ትግል ከስሙ እንደምንረዳው ብዙ ተግዳሮት ቢኖረውም ለዓላማችን መጽናት ግድ ይለናል:: በፋኖ ውስጥ ሆነው ፋኖ ፋኖ የሚጫዎቱ አስመሳዮች ከመጀመርያውም የመንግስት የሴራ ስራ አስፈጻሚዎች እንጅ የፋኖ ታጋይ አልነበሩም ማለት ነው:: እነዚህ ለትግሉ አያስፈልጉም። በመውጣታቸው እናተርፋለን እንጂ አናጎድልም። ይሂዱ መንግስትም የተለመደ ድራማውን ይሥራባቸው። እውነተኛዎቹ የዝብ ልጆች ስራ ላይ ናቸው!
ፋኖ አያሸንፍም ብላችሁ የምታስቡ አይደለም ይቅርና በትንሹ የምትጠራጠሩ እንኳን ልታፍሩ ይገባችኋል፤ ምክንያቱም እናሸንፋለንና! የማናሸንፈውን ትግል አልጀመርንም። ብዙ ጊዜ ከማስተውለውና ከሚያስቁኝ ነገሮች መካከል አንዱ መንግስት አንድ የፋኖ አባላት እጅ ሲሰጥ እምቢልታ እያስነፋ ነጋሪት እየጎሰመ በሚዲያ የሚያራግበው ነገር ነው። በአይነ ስ*ው*ር ቤት አንድ ዓይና ብርቅ ነው የሚለው አባባል ምንኛ ትክክል ነው! ከዚህ መረዳት የምንችለው መንግስት እንደተሸነፈ ነው። በየዕለቱ ወደ ፋኖ የሚጎርፈው መከላከያ ሰራዊት ስፍር ቁጥር የለውም ሆኖም ግን ፋኖ አሸናፊና የሞራል ልዕልና ያለው የአባቶቹ ልጅ ስለሆነ ምንም አይመስለውም።
በስተመጨረሻም ልነግራችሁ የምፈልገው ነገር እንኳንስ ይህን ያክል መላውን ሰፊውን የአማራ ክልል ተቆጣጥሮ ያለ በቁጥርም ከመከላከያ ሰራዊት የሚልቅ ኃይል እያለ ይቅርና በትንሽ ሰዎችም እናሸንፋለን። እውነት ያሸንፋል
#እንኳን_ደህና_መጣችሁ!!!
"ከተቻለ የቡድን መሳሪያ ካልተሳካ ሁለት ክላሽ ለማምጣት ነዉ የዘገየሁት"
ዛሬ ለሊት መጋቢት 21 ለ22/2018 ዓ/ም ሁለት ክላሽንኮቭ መሳሪያ ከበቂ ተተኳሽ ጋር በመያዝ ከጠላት ካምፕ ወጥቶ ቴዎድሮስ እዝ 105ኛ ኮር 44ኛ ክ/ጦር ፭ኛ ሻለቃን የተቀላቀለዉ ወታደር #ሻምበል_አቤ ከተናገረዉ!።
ዛሬ መጋቢት 22/2018 ዓ/ም አዲስ ቅዳም ከተማ ከሚገኘዉ የጠላት ካምፕ ወጥተዉ ፋኖን የተቀላቀሉት
1ኛ #ሻምበል_አቤ የአድማ ብተና አባል የነበረ እና 2 ክላሽንኮቭ በመያዝ
2ኛ #ፋሲካው_አማረ
ምስጋናዉ ዉድነህ የተባለን ባንዳ ጉሮሮዉን አንቆ ሳፕረሰር ክላሽንኮፍ መሳሪያ በመንጠቅ የመጡ
ሲሆኑ እድለኛ ሁነዉ ለዚህች ቀን መብቃታቸውን አመስግነዉ የአፋብን አደረጃጀት እንደተሰማ አብዛኞቻቸዉ መደሰታቸዉን በመግለፅ ቀሪ ጓዶቻቸዉም ከጠላት ካምፕ ወጥተዉ ፋኖን ለመቀላቀል ሁኔታዎችን እያመቻቹ እንደሆነ ተናግረዋል።
አዲስ ትዉልድ አዲስ አስተሳሰብ አዲስ ተስፋ🙏
የፋ/ለ/ወ ጊዚያዊ አስተዳደር ሚዲያ እና ግንኙነት
መጋቢት 22/2018 ዓ/ም
በክብር የተሰው ጓዶችን አስመልክቶ የተሰጠ መግለጫ
“ክብርና ሞገስ ለቅዱስ ዓላማ ለወደቁ ጀግኖቻችን!”
አፋብን ደቡብ አማራ ቀጠና በአሳምነው ዕዝ፣ በአፄ ዘርዓ ያዕቆብ ኮር ነጎድጓድ ክፍለ ጦር ውስጥ ትግላችን ዛሬ ላይ እንዲደርስ ለህዝባችሁ ህልውና መከበር በጀግንነት ከህዝባችሁ ጎን ተሰልፋችሁ ህይወታችሁን ለሰጣችሁ ውድ ጀግና ሰማዕቶች ለአርበኛ ይገረም ከበደ ፣ለአርበኛ ሱራፌል ገብረሃና እና ለአርበኛ ሙሴ እሸቴ ለህዝባቸው የከፈሉት መስዕዋትነት ጥልቅ መሆኑን እንገልጻለን። ትግሉ ከተጀመረበት ጊዜ አንስቶ በማደራጀት እና በማሰልጠን እንድሁም ከፊት ሆኖ በመምራት በሸዋ ተራሮችና ሸጦች የጠላትን ሀይል መውጫ መግቢያ በማሳጣት ሲፈፅሙት የነበረው አኩሪ ስራ ህያው ምስክር ሆኖ በታሪክ መፅሃፍት ሲከተብ ይኖራል።
ጀግኖቻችን፤ እናንተ የታሪክ አደራን ተሸክማችሁ፣ በቆራጥነትና በፅናት ዋጋ የከፈላችሁት ለነገው ብሩህ ተስፋና ለህዝባችን ህልውና በማፅናት ሰላም ማስፈን ነው። የእናንተ መስዋዕትነት በታሪክ መዝገብ ላይ በወርቅ ቀለም ተጽፎ የሚኖር ሲሆን፣ የጀመራችሁት የትግል ጉዞ (ዓላማ) በሁላችንም ልብ ውስጥ ሲዘከር ይኖራል። በቀን 21 /07/2018 ዓ.ም ከጠላት ሀይል ጋር በነበረ ከባድ ትንቅንቅ ብዙ የአገዛዙን ሀይል ሲተናነቁ አርፍደው የሚተማመኑት እና ቃል የተገባቡት ጀግኖች ታሪክ ማህደር ውስጥ ደምቀው የሚታዩት ገጾች በብዕር ብቻ ሳይሆን፣ በቆራጥ ልጆች ደምና አጥንት የተጻፉ ናቸው እና የህልውና ትግል አማራጭ የሌለው፣ "ለመኖር መዋጋት" የሚሰኝ የሞትና የሽረት ፍልሚያ በመሆኑ ይህን መርጠው ጀግኖቹ የአገዛዙን ሰራዊት አርግፈውት የመጨረሻውን ምርጫ የአባታችንን አፄ ቴወድሮስን የጀግንነት መንገድ ተከትለዋል ።
በዚህ ፍልሚያ ውስጥ የተፈጸሙ ጀብዱዎች ደግሞ ተራ ድርጊቶች ሳይሆኑ፣ ከራስ በላይ ለሆነ ዓላማ (ለህዝብ ፣ ለትውልድና ለህልውና) በመታመን የተከፈሉ የክብር ዋጋዎች ናቸው።
የተከፈለውም መስዋዕትነት ከራስ በላይ ለጓዶች ለሌሎች ህይወት ሲባል የራስን ህይወት አሳልፎ መስጠት እና ለህዝብ ቅድሚያ በመስጠት ከፍተኛው የፍቅር ማሳያ ሆኖ ተመዝግቧል ። በዚህ ህልውና ትግል ውስጥ የወደቁት ጀግኖች "እኔ ባልኖርም ህዝቤ መኖር አለባት" የሚል ጥልቅ እምነት ያላቸው ጀግኖቹ የነበራቸው ዕምነት ለህዝብ መሰዋት ሞት ሳይሆን፣በታሪክ ውስጥ ዘላለም መኖር ነው የሚሉ ተሰውተው ያሳዩ ናቸው። የእነሱ ድፍረት እኛን ያነሳል፤ የእነሱ ተስፋ ወደፊት እንድንመራ ይረዳናል፤ የእነሱ መስዋዕት ደግሞ በእርምጃ እንድንመልስ ያደርገናል።
ጀግኖች ቢሰዉም፣ የከፈሉት መስዋዕትነት ግን የነፃነት ችቦ ሆኖ ይበራል። የእነርሱ ደም የነፃነትን ምድር ያጠጣል። የሚቀጥለው ትውልድ በሰላም እንዲኖርና አንገቱን ቀና አድርጎ እንዲሄድ መሰረት የሚጥሉት እነዚህ ታላላቅ የቁርጥ ቀን ልጆች ናቸው።
ለተሰውት ጀግኖች ቤተሰቦች፣ ወዳጅ ዘመዶችና ለመላው የኮሩ እና የክፍለ ጦሩ አመራርና አባላት መጽናናትን እንመኛለን።
''ክብር ለተሰውት ''
አፋብን ደአቀ (አሳምነው ዕዝ)
ቀን 22/07/ 2018 ዓ.ም
የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ (አፋብን) ወሎ (ቤተ አማራ) ቀጠና ምኒልክ ዕዝ 303ኛ ግዙፉ አሳምነዉ ኮር የላስታ ወረዳ ሲቪል መዋቅር 14ኛ ክፍለ ጦር ጋር በመተባበር ህዝባዊ የውይይት መድረክ ተካሔደ።
በአፋብን ወሎ (ቤተ አማራ)ቀጠና ምኒልክ ዕዝ 303ኛ ግዙፉ አሳምነዉ ኮር የላስታ ወረዳ አስተዳደር እና 14ኛ ክ/ጦር በትብብር በ016፣ 017፣ 018 ቀበሌዎች የህዝብ መድረክ በማካሔድ ጥልቅ የህዝብ ውይይት ተካሒዷል።
በስብሰባው በህብረተሰቡ ጠንካራና ገንቢ ሀሳቦች በሶስት ዋና ዋና አጀንዳ ተከፍለው ተነስተዋል ።
1)በሶስቱ ቀበሌዎች ባሉ የቀበሌ ጊዜያዊ አስተዳዳሪዎች ያሉ የመልካም አስተዳደር ችግሮች በነቂስ ተነስተዋል
2)በወረዳው ጊዜያዊ አስተዳደር ያሉ ጠንካራና ደካማ ጎኖችን በመገምገም
3)በ303ኛ ኮር ባሉ ክፍለ ጦሮች በሰራዊት፣በአመራርና በድርጅት ያሉ ጠንካራና ደካማ ጎኖች በዝርዝር መነሳት ችለዋል።
በእነዚህ ከላይ በሶስት ክፍሎች የተከፈሉ የስብሰባ አጀንዳዎችን መሰረት ያደረገ ጠንካራ ሀሳቦች የተነሱ ሲሆን በስብሰባው ማህበረሰቡ ትግሉን በአቋም መደገፍ እንዳለበትና በቁርጠኝነት መታገል እንዳለበት በሙሉ ልብ ሀሳብ በመስጠት በትግሉ ውስጥ የሚታዩ አንዳንድ የመልካም አስተዳደር ችግሮች መስተካከል እንዳለባቸው እንዲሁም አላግባብ ህዝቡን የሚያንገላቱ የቀበሌ የሲቪል መዋቅር አመራሮችን መጠየቅ መቻል እንዳለበት ችግሮቹን ጭምር በዝርዝር በማንሳት የተሳካ ስብሰባ ማድረግ ተችሏል።
ህብረተሰቡ በሰራዊቱ ፣በክፍለ ጦር አመራሩ የተነሱ አንዳንድ ጥያቄዎችን የ14ኛ ክፍለ ጦር አመራሮች መልስና ማብራሪያ በመስጠት ህዝባችን እንደወትሮው ሁሉ ከጎናችን በመሆን መደገፍ እንዳለበትና የህልውና ትግሉም አሁን ላይ አንድ ድርጅት እንደተፈጠረና መስመር እንደያዘ እንዲሁም አደረጃጀቱ እስከ ታች ድረስ በመውረድ ድርጅታችን አፋብን ጠንካራ ሰራዊት ግንባታ እየገነባ እንደሆነ በመግለፅ ይህ አደረጃጀት ግን በአንድ ጊዜ ሳይሆን በሒደት እንደሚሰራ በማስገንዘብ ለህብረተሰቡ ግንዛቤ መሰጠት ተችሏል።
የላስታ ወረዳው ጊዜያዊ አስተዳደር ዋና አስተዳደር አስር አለቃ ነጋ ፈንቴ በስብሰባው "የአማራ ህዝብ በብልፅግና እየደረሰበት ያለው የህልውና አደጋ በቁርጥ ቀን ልጆቹ ፋኖዎች በተጠናና በተደራጀ መንገድ እየተመከተ መሆኑን አስረድተው በቀበሌም ሆነ በወረዳ የተቋቋመው የጊዜያዊ ሲቪል መዋቅር አፋብን በሚያዘጋጀው መርህና ህገ ደንብ ህብረተሰቡን ማስተዳደር እንደሚገባ ገልፀው ከዚህ አካሔድ ውጭ ህዝቡንና ትግሉን የሚጎዳ ጊዜያዊ የሲቪል አመራር መጠየቅ እንዳለበት ጠቁመው ይህን ስናደርግ ግን ከአፋብን የሚወርዱ መመሪያዎችን ወደ ታች ወርዶ ስልጠናና የአቅም ግንባታ በመስጠት የአማራ ህዝብ የተጋረጠበትን የህልውና አደጋ ተናቦ መመከትና ለአሸናፊነት የሚያበቃውን ጠንካራ አደረጃጀት በማቋቋም አታጋዩን ከመልካም አስተዳደር ችግሮች ማላቀቅ እንደሚያስፈልግ በማስገንዘብ ነው።
በተጨማሪም ብልፅግና የውሸትና የማታለያ ምርጫ አካሒዳለሁ ስለሚው ድስኩር ማንኛውም አማራ ከምርጫው እጁን ማስገባት እንደሌለበት ማለትም የምርጫ አስመራጭ ኮሚቴ መሆን ፤የምርጫ ቲሸርት መልበስና ሌሎችንም ስለምርጫ ነክ ነገሮች ፈፅሞ የተገኘ በፋኖ እርምጃ እንደሚወሰድበት አክለው ገልፀዋል።
ከህዝባችንም በተሰጠው የማጠቃለያና የስብሰባ መዝጊያ አስተያየት ስብሰባው ወቅቱን ያገናዘበና ቶሎ ቶሎ ማህበረሰቡን ማወያየት እንደሚያስፈልግ ጨምረው የትግላችን ፈር ቀዳጅ የሆነው ህዝባችን አሁንም ከትግሉ ጎን እንደሆነ በማረጋገጥ ጭምር ነው።
የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ(አፋብን) ወሎ (ቤተ አማራ) ቀጠና ሚኒሊክ ዕዝ 303ኛ ግዙፉ አሳምነዉ ኮር የላስታ ወረዳ ጊዚያዊ ሲቪል አስተዳደር ህዝብ ግንኙነት ክፍል!!
ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን!
መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልዉና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል!
ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን!
አፋብን ወሎ (ቤተ አማራ) ቀጠና ምኒልክ ዕዝ
መጋቢት22/2018ዓ.ም
♦️አርበኛ ልብአርግ ሙላትን አሳዶ ለመያዝና ለመደምሰስ በሁለት አቅጣጫ የመጣው ጠላት እርምጃ ተወሰደበት።
ዛሬ መጋቢት 22/2018 ዓ.ም የዳግማዊ ቴዎድሮስ ፭ኛ ኮር ጥቁር አንበሳ ክ/ጦር ሰብሳቢ ልብ አርግ ሙላትንና የተወሰኑ አመራሮችን እንዲሁም የድል በር ብርጌድ አባላትን ለመደምሰስ ከማክሰኝትና ከደጎማ ንቅናቄ ያደረገው የብልጽግና ኃይል ሙትና ቁስለኛ ተደርጎ ተመልሷል።
በድንዛዝ ከፍተኛ ቦታዎች ያልጠበቀው ጥቃት የገጠመው ጠላት እግሩ ወዳመራው ከፈመርጠጡም በላይ ይዞት የሄደው ሰራዊቱ በየ አቅጣጫው መበተኑም ታውቋል።
♦️ይህ በእንዲህ እንዳለ በአማራ ትግል ውስጥ በመታገል ላይ በሚገኙ የፋኖ ቤተሰቦች ላይ ብልጽግና የበቀል እርምጃ እየወሰደ መሆኑ ታውቋል።
የድል በር ብርጌድ አዛዥ ሙሌ ወርቁ ወንድም ላይ አሰቃቂ ግድያ ተፈጽሟል።
የለምባ ቀበሌ ነዋሪ የሆነው ባየ ቀናው እስከ ህፃን ልጁ በብልጽግና አረመኔ ሰራዊት በአሰቃቂ ሁኔታ ተረሽነዋል።
በአማራ የህልውና ትግል ውስጥ በመሳተፍና በመታገል ላይ የሚገኙ አማራዊያንና ቤተሰቦቻቸው ላይ በሁሉም የአማራ አካባቢዎችና በመላው ኢትዮጵያ የበቀል በትር በተደጋጋሚ መፈጸሙን በተለያዩ የዜና እወጃችን መዘገባችን ይታወሳል።
ኅልውናችን በተባበረ ክንዳችን።
አፋብን ሰሜን አማራ ቀጠና በላይ ዘለቀ እዝ ዳግማዊ ቴዎድሮስ ፭ ኮር ህዝብ ግንኙነት ዘርፍ ኃላፊ አብነት ሞላ
መጋቢት 22/2018 ዓ.ም
@Baye Desta Per
የ206ኛ ኮር አዳኝ ቡድን በደብረማርቆስ ከተማ ከሌሊቱ 7:10 በፈፀመው የቦምብ ጥቃት በአንድ ኦባማ የጭነት ተሽከርካሪ የነበሩ 23 የአድማ ብተና አባላት መገደላቸው ተረጋግጧል።
መጋቢት 22/2018 ዓ.ም
=======================================
አነፍናፊ የ206ኛ ኮር አዳኝ ቡድን በጎዛምን ወረዳ ቸርተከል ንዑስ ከተማ ወረራ ፈፅሞ በተመለሰ የጠላት ኃይል ላይ በደብረ ማርቆስ ከተማ ንጉስ ተክለሃይማኖት ክ/ከተማ ጤና ጣቢያ አካባቢ በፈፀመው የቦምብ ጥቃት በአንድ ኦባማ ተሽከርካሪ ላይ የተጫኑ አየድማ ብተና አባላት ሙሉ ለሙሉ ተደምስሰዋል።
ታልጋ ቁጥር 22472 ኮድ (3) ባለቤትነቷ የግል የሆነችውን የደረቅ ጭነት ማመላለሻ ኦባማ በማስገደድ ከቸርተከል ወደ ደብረማርቆስ ከተማ እየገቡ ባለበት በንጉስ ተክለሃይማኖት ክ/ከተማ ቀበሌ ጤና ጣቢያው አካባቢ ሲደርሱ በ206ኛ ኮር አዳኝ ቡድን በደረሰባቸው የቦምብ ጥቃት ሀለት ጋንታ መሪዎችን ጨምሮ 23 አድማ ብተና አባላት መሞታቸው ተውቋል።
የጠላትን መውጫ መግቢያ በቦምብ አጥረው እያጋዩት የሚገኙት የ206ኛ ኮር አዳኞች በተከታታይ በፈፁሙት የተሳካ ኦፕሬሽን ጠላት የሚመካባቸውን ካድሪዎችና ወታደራዊ አመራሮች እያስወገዱ ሲሆን በተሽከርካሪ የሚንቀሳቀሱ የብልጽግና ነዶዎች በቦምብ ተቃጥለዋል።
የጠላትን ካድሪ ባናጠለ መልኩ ከመደምሰስ ባለፈ በአይነቱ ለየት ያለ ጥቃት መክፈት የሚያስችል አቅም መገንባቱን እንዲሁ የ206ኛ ኮር አዳኝ ቡድን አስታውቋል።
አዲስ ትውልድ ! አዲስ አስተሳሰብ ! አዲስ ተስፋ!
የአፋብን ቴዎድሮስ ዕዝ 206ኛ ኮር ህዝብ ግንኙነት
