ፍኖተ-አማራ ሚዲያ (Finote Amhara Media)
Открыть в Telegram
የተመሠረተው የአማራን ሕዝብ ለማንቃት፣ ለማደራጀት እና ለማስተባበር ነው። የአማራ ሕዝብን ✅ ፖለቲካዊ ✅ ማህበራዊ ✅ ኢኮኖሚያዊ ታሪካዊ ጥያቄዎችን ለማሰማት እና የአማራን ሕዝብ በማንቃት ሰፊውን ሕዝብ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ይሰራል። ወደዱም ጠሉም የኃላ ታሪካችን በእኛ እጅ ይፃፋል። አማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ ( አፋብን)
Больше4 387
Подписчики
+124 часа
+757 дней
+1 40730 дней
Архив постов
“የአፋር ሕዝብን ቁማር ያስያዘው የአወል አርባ አገዛዝም ሆነ የአለቃው አብይ አህመድ አገዛዝ በሕዝቦች ትብብር ትግል ይወገዳል!”
#ከአፋር_ብሔራዊ_አንድነት_አብዮታዊ_ግንባር_የተሰጠ_ወቅታዊ_መግለጫ!
የተከበራችሁ መላው የአፋር ሕዝብና የኢትዮጲያ ሕዝብ በሙሉ የአፋር ብሔራዊ አንድነት አብዮታዊ ግንባር (ኡጉጉሞ) ለአፋር ሕዝብ ክብርና ነጻነት፣ እንዲሁም ሉዓላዊነት ሲዋደቅ የኖረና እየተዋደቀ ያለ ግንባር ነው።
ግንባራችን “ኡጉጉሞ” አብይ አህመድና አወል አርባ እንዲሁም ሌሎች ኃይሎች በጋራ ትብብር መሰረተ ልማት ማልማት ሲያቅታቸው ውድመት ለመፈፀም በሕዝባችን ላይ በግራና በቀኝ እያሳሉት ያለውን ግጭት ጠማቂነት እንዲያቆሙ ለማሳሰብና እኛም ኡጉጉሞ ይሄን አገዛዝ ለመጣል ከሌሎች ብልጽግናን መታገል ከሚፈልጉ ኃይሎች እንደምንተባበር ስናሳውቅ በታላቅ የመታገልና የማታገል ስሜት ውስጥ ሆነን መሆኑን መግለጽ እንወዳለን።
የአብይ አህመድ አገዛዝ የሆነው የብልጽግና ስርዓት የአፋር ሕዝብን እንዲጠፋ ወስኗል ስንል ምን ማለታችን ነው:-
1ኛ. በነ ጀነራል ተስፋዬ አያሌው አስተባባሪነት የኤርትራን መንግስት በትጥቅ ትግል ለማስወገድ የሚሰሩ ታጣቂዎች መሰልጠኛ ሆኗል፣ ከሕውሓት አኩርፈው የወጡ የትግራይ የሰላም ኃይል ነን የሚሉ መሰልጠኛና መዋጊያ ቀጠና አድርገውታል፣ ይህ በመሆኑም የአፋር ሕዝብ የከባድ መሳሪያና የድሮን ድብደባ ሰለባ ሁኗል።
2ኛ. በሌላ በኩል በሙስጠፌ መሐመድ የሚመራው የሱማሌ ክልል በአብይ አህመድ የግል ጀነራሎች እገዛ የኢሳ ኃይል ከሱማሌ ክልል ልዩ ኃይል እገዛ እየተደረገለትና አልፎ አልፎም በቀጥታ ተሳታፊነት ከፍተኛ ዋጋ እየከፈለ ነው።
3ኛ. በብልጽግናው አለቃ አብይ አህመድ የቀን ቅዥት አማካኝነት ቀበሌ ማስተዳደር ያቃተው አገዛዝ የገጠመውን አገራዊ ተቃውሞ ለማብረድ በሚል “የቀይ ባህር” አጀንዳ መዞ የጦር ሜዳውንም አፋር መሬት ለማድረግና የአፋር ሕዝብም እንዲጠፋ ወስኖ እየሰራበት ይገኛል።
4ኛ. የአብይ አህመድ ተላላኪ የሆነው አወል አርባ የክልሉን በጀት በማጠፍ ለጦር አገልግሎት እየዋለው ከመሆኑ ጋር ተያይዞና እንዲሁም ባለው የኑሮ ውድነት አሁን ላይ በአፋር ክልል ከፍተኛ የሆነ የርሃብ፣ የመልካም አስተዳደር ችግር ተከስቷል፣ በተጨማሪም የመብት ጥያቄ የሚያነሱ ሰዎች ከፍተኛ የሆነ ወከባ፣ እንግልት፣ እስር እና ድብደባ እየተፈፀመባቸው መሆነ የአደባባይ ሀቅ ነው። የአፋር ሕዝብ ለዘርፈ ብዙ ጥቃት ተጋላጭ ሁኗል።
ስለሆነም:-
- የአፋር ሕዝብ የገጠመውን የህልውና አደጋ በመረዳት የአብይ አህመድ ተላላኪ በመሆን እንደ አጠቃላይ አፋርን የጦር ሜዳ ለማድረግ እየሰራ ያለውን የተላላኪውን አወል አርባ አገዛዝ በቃህ እንዲለው ጥሪ እናቀርባለን።
- የብልጽግናው አገዛዝ እንዲወገድ የሰላማዊ ትጥቅ ትግል እያደረጋችሁ ያላችሁ፣ በሰላማዊ ትግል እንቅስቃሴ እያደረጋችሁ ያላችሁ፣ ወደ ትግል ያልገባችሁ የኢትዮጲያ ብሔር ብሔረሰቦችና ሕዝቦች የጋራ ትግል እንድናደርግና ኢትዮጲያ ከፍርሰት እንድንታደግ ጥሪ እናቀርባለን።
- በአፋር ክልል በብልጽግና ድጋፍ የትጥቅ ትግል ለማድረግ እየተንቀሳቀሳችሁ ያላችሁ የትኛውም አካላት በአስቸኳይ ክልሉንነለቃችሁ እንድትወጡ እያሳሰብን፣ የአፋር ሕዝብም ቀጠናው የጦር ሜዳና ውሎ መግባት፣ ተኝቶ መነሳት ከመክበዱ በፊት ቀጠናውን ለቀው እንዲወጡ ጫና እንድታደረግ ማስታወስ እንፈልጋለን።
- ዓለም አቀፍ የሰብዓዊ መብት ተቋማትና መንግስታት ጦረኛው የብልጽግና አገዛዝ አፋርን፣ አማራን እና ትግራይን በማተራመስ አጠቃላይ ምስራቅ አፍሪካ የጦር ሜዳ ለማድረግ እየሰራ ያለውን የብልጽግና አገዛዝ ጋር ያላችሁን ግንኙነት እንድታጤኑትና እንድታስቡበት እንገልጻለን።
በመጨረሻም በሕዝብ ደም እየተጫወተ የሚገኘው የብልጽግና አገዛዝ በሕዝቦች አንድነትና ተጋድሎ እንደሚወድቅ እናምናለን፣ ይህ እንዲሆንም በቀጠናችን ጠንካራ ስራዎችን እየሰራን እንገኛለን፣ ሌሎች ኃይሎችም የጀመሩትን የህልውና ትግል አጠናክረው እንዲቀጥሉ እናሳስባለን።
ድልና ድምቀት ለአፋር ኡጉጉሞ!
የአፋር ብሔራዊ አንድነት አብዮታዊ ግንባር (ኡጉጉሞ)
ህዳር 1 ቀን 2018 ዓ.ም
የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ ላስታ ጄኔራል አሳምነው ፅጌ ኮር!
ፋኖ በተቆጣጠራቸው ነፃ ቀጠናዎች ህዝባዊ መድረኮች እንደቀጠሉ ናቸው!
ህዳር 01/2018 ዓ.ም
በአፋብኃ ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ ግዙፉ ላስታ ጄኔራል አሳምነው ፅጌ ኮር ማረጉ ተማረ ክፍለ ጦር በተቆጣጠራቸው የላስታ ወረዳ ቀበሌዎች መካከል 02 ቀበሌ ብልባላ ገጠሩ የወልደንጉስ ህዝቦች ጋር የክፍለ ጦሩ አመራሮች ጥቅምት 30/2018 ዓ.ም ጥልቅ ውይይት አድርገዋል።
ውይይቱ የተካሄደው የክፍለ ጦሩ ዋና አዛዥ አርበኛ ፋኖ አውራሪስ ደረሰና ሌሎች አመራሮች በተገኙበት ሲሆን ህዝቡም ሃሳቡን በነፃነት የገለፀበት ከአመራሮቹም በቂ ምላሽ የተሰጠበት መሆኑን ከህዝቡ በተገኙ አስተያየቶች ተረጋግጧል።
ህዝቡም ፋኖ ከመምጣቱ በፊት ሰብላችን ይበላና ይወድም ነበር፣የከብቶቻችን መዋያ ጥብቅ ስፍራዎች በህገወጥ በነፍስ ወከፍ ደኖች እየተጨፈጨፉ ለእርሻ ስራ ይውሉ ነበር፣ሌቦችና ወንበዴዎች በዝተው ነበር፣ህዝቡ በነፃነት ማሳ ውሎ አይመጣም ነበር፣በአጠቃላይ ህዝቡ በስጋትና በፍራቻ ቆፈን ውስጥ ይኖር ነበር ነገር ግን ፋኖ ከመጣ ወዲህ ነፃነታችንን አግኝተናል ስራዎችን እየሰራችሁ ነው የቀሩ ስራዎች ካሉ እነዛን በቶሎ ስሩና አስተካክሉልን ትግሉን እኛም እንደግፈዋለን ከጎናችሁ ነን በማለት ህዝቡ ለፋኖ ድጋፉን ችሮታል።
መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልውና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል ሲል የአፋብኃ ምስራቅ አማራ ቀጠና ግዙፉ ላስታ ጄኔራል አሳምነው ፅጌ ኮር ማረጉ ተማረ ክፍለ ጦር ቃል አቀባይ ፋኖ የፀዳው አመረ መረጃውን አድርሷል።
ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን!!!
የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል (አፋብኃ)
ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ
ህዳር 01/ 2018 ዓ.ም
ለደብረ ኤልያስ ወረዳ መምህራንና የመንግስት ሰራተኞች በሙሉ!!!
እነሆ ይህ ጡት ቆራጭ ኦሆዴድ መራሹ የብልፅግና ቡድን በአማራው ህዝብ ላይ እያደረሰ ያለውንና ሊፈጽመው ያቀደውን ሁለንተናዊ ጥፋት በደንብ ተረድታችሁ እያሳያችሁ ላለው ቁርጠኝነት ከልብ እናመሰግናለን።
ሆኖም በቀን 29/02/2018 ዓ.ም "የሚሉሽን በሰማሽ ገቢያ ባልወጣሽ" እንደሚባለዉ:ደብረ ኤልያስ ከተማ ውስጥ ተወሽቆ የሚገኘው የኦህዴድ አሽከሩ ጡት ቆራጩ የብልጽግና ስብስብ ከበላዮቹ የተሰጠውን የውሸትና የማታለያ ዘባተሎውን ይነዛ ዘንድ "የውጭ ባዕዳዎች የውስጥ ባንዳዎች"ብሎ እየቀዣበረ በሰበሰባችሁ ሰዓት ያሳያችሁት ቁርጠኝነት አሰደስቶናል።
በዚሁ ስብሰባም "የግድ ሀሳብ መስጠት አለባችሁ"እያሉ ሲሳደቡ መዋላቸውን በውስጥ አርበኞቻችን በኩል ደርሶናል።
ከመሠረቱ በእውነት ሳይሆን በማስመሰል ተግባር የተሽሞነሞነው ይህ የጥፋት ስብስብ በእውነት አርበኞች አሁን ላይ መቃብራዊ ማንነቱ እየተገለጠ የውጩን መንቆጥቆጥ የሚያስንቅ ውሳጣዊ ጉስቁልናው እየተገለጠ ነው። በዚህ ስብሰባም የሆነው ይህ ነው።
ስለሆነም በአማራው ላይ የሚደርሰው ግፍና መከራ ያከትም ዘንድ ይህንን ግፈኛ አማራ ጠል የብልፅግና ቡድን በአንድነት ነቅለን እንድንጥል የተለመደውን የእምቢተኝነት አማራዊ ስነ ልቦናችሁን አጠንክራችሁ እንድትቀጥሉ ጥሪያችንን እናስተላልፋለን።
ቀኜ የውስጥ አርበኞቻችንም የምትሰሩት ስራ የሚየያስመሰግን ስኬታማ ነውና በርቱልን!!!
ህዳር 01/2018 ዓ.ም
ድል ለአማራ ፋኖ
አዲስ ትውልድ! አዲስ አስተሳሰብ! አዲስ ተስፋ!!!
በቴዎድሮስ ዕዝ በ206ኛ ኮር 14ኛ ክፍለ ጦር የሕዝብ ግንኙነት ክፍል ኃላፊ
ሰበር አሳዝኝ ዜና‼️
በኦሮሚያ ክልል አርሲ ዞን፡ አሰኮ ወረዳ በጡሌ ቢዮ ቀበሌ፤ ጠለታ አከባቢ 3 የኦርቶዶክስ ሃይማኖት ተከታዮች በአሰቃቂ ሁኔታ ተገደሉ ።
በምሥራቅ አርሲ ዞን፡ አሰኮ ወረዳ በጡሌ ቢዮ ቀበሌ፤ በቀን 01/3/2018 ዓ.ም ልዩ ቦታው ጠለታ ገብርኤል ደብር በተባለ አከባቢ፤ ከጠዋቱ 3:00 ሰዓት ላይ፤ ሶስት ኦርቶዶክሳውያን በአውድማ ላይ እህል እየወቁ ሳሉ በጥይት ተደብድበው በግፍ ተገድለዋል ።
በዚህ ጨካኝና አረመኔ የኦነግ ሸኔ ቡድን እና በአስጨፍጫፊው ብልፅግና መራሹ መንግሥት፤ የኦርቶዶክስ ሃይማኖት ተከታዮች እና አማራ ስለሆኑ ብቻ ጭካኔ በተሞላበት ድርጊት በጥይት ተደብድበው ተገድለዋል ። በዚህም፤ ዛሬ ከጠዋቱ 3:00 ሰዓት ላይ፤
➣ ጥላሁን ቦጌ
➣ እዮብ እጅጉ ፡ እንዱሁም፤
➣ #የ_10_ዓመት_ህፃን ልጅ፡ ፃድቃኔ ሰራዊቱ
የተባሉ ኦርቶዶክሳውያን እና አማራ ግለሰቦች በዘግናኝ ሁኔታ እና በግፍ ተገድለዋል ።
- የአከባቢውን ግፍና ሰቆቃ ገፈት-ቀማሾችን ነዋሪዎችን ለማነጋገር ሞክረናል፤ እንዲህ ሲሉ ተደምጠዋል "በዚህ አገዛዝ ለብዙ አመታት እየተገደለን ፥ እተፈናቀልን ፥ እየታፈንን ፥ እየታረድን...እንገኛለን... 'ፍትህ' በሌለበት 'ፍትህ...ፍትህ...' ብለን ጮኸን ነበር፤ ነገር ግን አሁን የገባን እራሱ "መንግሥት ነኝ..." የሚለው አካል ነው የሚጨፈጭፈን ፥ የሚያስጨፈጭፈን..." ቀጥለውም "እኛ በአርሲ አከባቢ የምንኖር ኦርቶዶክሳውያን እና አማራዎች እንደ ዜጋ ተነጥለን ስለምንገደል፤ የዓለም መንግሥት ሆይ አንድ መፍትሄ ሊያመጣልን ይገባል..." ሲሉ ነው ለከሰም ሚዲያ አቤቶታቸውን ያቀረቡት ።
© ዘገባው፦ የአበባየሁ ሰይፈ ነው ።
#ኦርቶዶክሳውያን_እና_አማራዎች_ሼር_በማድረግ_ለዓለም_መንግሥት_ጩኸታችን_ይድረስልን !🙏 😭 💔 🖤
#share #ሼር
Repost from ፍኖተ-አማራ ሚዲያ (Finote Amhara Media)
የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ ላስታ ጄኔራል አሳምነው ፅጌ ኮር!
የማህበረሰቡን የንፁህ መጠጥ ዉኃ ችግር የሚቀርፍ የውኃ ፕሮጀክት ተመረቀ!
ህዳር 01/2018 ዓ.ም
በአፋብኃ ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ ግዙፉ ላስታ ጄኔራል አሳምነው ፅጌ ኮር ጄኔራል ኃይሉ ከበደ ክፍለ ጦር በተቆጣጠራቸው ዋግ ኸምራ ብሔረሰብ ዞን ጋዝጊብላ ወረዳ ቀበሌዎች አንዱ የሆነው የ09 ቀበሌ ላልኪው ታዳጊ ከተማ ለረጅም ዓመታት የማህበረሰቡ ችግርና ዕጥረት የነበረውን የንፁህ መጠጥ ውኃ አገልግሎት የቀረፈ የውኃ ፕሮጀክት የኮሩና የክፍለ ጦሩ አመራሮች እንዲሁም የወረዳው ወታደራዊ ሲቪል አስተዳደር፣የግብረ ሰናዩ ድርጅት አመራሮችና ማህበረሰቡ በተገኙበት የውኃ ፕሮጀክቱ ጥቅምት 30/2018 ዓ.ም ተመርቋል።
ይህ ፕሮጀክት ወርልድ ቪዥን ኢትዮጵያ በተባለ ግብረ ሰናይ ድርጅት በ7 ነጥብ 5ሚሊዮን ብር የተሰራ ሲሆን ፕሮጀክቱ ተሰርቶ እስኪጠናቀቅም ክፍለ ጦሩ አስፈላጊውን ጥበቃና ድጋፍ እንዲሁም የወረዳው ወታደራዊ ሲቪል መዋቅር ህብረተሰቡን በማስተባበር በጉልበት እንዲሁም እንደ ጠጠር፣ድንጋይና አሸዋ ያሉ ግብዓቶችን በማቅረብ በትብብር በሦስት ወር አጭር ጊዜ ውስጥ ተሰርቶ እንዲጠናቀቅ መደረጉና ተመርቆ ለማህበረሰቡ፣ለትምህርት ቤት እንዲሁም ለጤና ጣቢያ አገልግሎት የሚሰጥ ሲሆን ይህ በሶላር የሚሰራ የውኃ ፕሮጀክት ከ1500 በላይ አባውራና እማውራዎችን እንደሚያስጠቅም ታውቋል።
በመጨረሻም ኮሩ በተቆጣጠራቸውና በሚንቀሳቀስባቸው ዋግ ኸምራ ብሔረሰብ ዞንና ሰሜን ወሎ ዞን ወረዳዎች መሰል የማህበረሰብ እንደ ንፁህ መጠጥ ውኃ አገልግሎት ዕጥረት ድርቅና ወረርሽኝ ችግሮችን እንድትቀርፉልን ለግብረ ሰናይ ድርጅቶች ጥሪ እያስተላለፍን አስፈላጊውን ጥበቃና ከለላ፣የሰው ኃይል ጉልበትና የቁሳቁስ ድጋፍ ምቹ ሁኔታዎችን እንፈጥራለን ሲሉ የኮሩ ምክትል ፖለቲካ ዘርፍ ኃላፊ የሆኑት አርበኛ ፋኖ አለምነው መብራቱ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።
መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልውና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል ሲል የአፋብኃ ምስራቅ አማራ ቀጠና ግዙፉ ላስታ ጄኔራል አሳምነው ፅጌ ኮር ህዝብ ግንኙነት ኃላፊ ፋኖ ቢሆነኝ ቢያበይን መረጃውን አድርሷል።
ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን!!!
የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል (አፋብኃ)
ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ
ህዳር 01/ 2018 ዓ.ም
ፍኖተ-አማራ ሚዲያ ወቅታዊና ትኩስ የፋኖ እንቅስቃሴን መረጃን ከግንባር ሁነን በአራቱም ማዕዘን እየሰራን እንገኛለን።
ለሁሉም አማራ ተደራሽ እንሆን ዘንድ እየሰራን እንገኛለን የበኩሉዎን አስተዎፆ የቴሌግራም ቻናላችን ጆይን ሸር አድርጉ አድራሻችን👇👇👇👇 ‼️
https://t.me/httpsuYkZrGfSZrNjNjFk
የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ ላስታ ጄኔራል አሳምነው ፅጌ ኮር!
የማህበረሰቡን የንፁህ መጠጥ ዉኃ ችግር የሚቀርፍ የውኃ ፕሮጀክት ተመረቀ!
ህዳር 01/2018 ዓ.ም
በአፋብኃ ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ ግዙፉ ላስታ ጄኔራል አሳምነው ፅጌ ኮር ጄኔራል ኃይሉ ከበደ ክፍለ ጦር በተቆጣጠራቸው ዋግ ኸምራ ብሔረሰብ ዞን ጋዝጊብላ ወረዳ ቀበሌዎች አንዱ የሆነው የ09 ቀበሌ ላልኪው ታዳጊ ከተማ ለረጅም ዓመታት የማህበረሰቡ ችግርና ዕጥረት የነበረውን የንፁህ መጠጥ ውኃ አገልግሎት የቀረፈ የውኃ ፕሮጀክት የኮሩና የክፍለ ጦሩ አመራሮች እንዲሁም የወረዳው ወታደራዊ ሲቪል አስተዳደር፣የግብረ ሰናዩ ድርጅት አመራሮችና ማህበረሰቡ በተገኙበት የውኃ ፕሮጀክቱ ጥቅምት 30/2018 ዓ.ም ተመርቋል።
ይህ ፕሮጀክት ወርልድ ቪዥን ኢትዮጵያ በተባለ ግብረ ሰናይ ድርጅት በ7 ነጥብ 5ሚሊዮን ብር የተሰራ ሲሆን ፕሮጀክቱ ተሰርቶ እስኪጠናቀቅም ክፍለ ጦሩ አስፈላጊውን ጥበቃና ድጋፍ እንዲሁም የወረዳው ወታደራዊ ሲቪል መዋቅር ህብረተሰቡን በማስተባበር በጉልበት እንዲሁም እንደ ጠጠር፣ድንጋይና አሸዋ ያሉ ግብዓቶችን በማቅረብ በትብብር በሦስት ወር አጭር ጊዜ ውስጥ ተሰርቶ እንዲጠናቀቅ መደረጉና ተመርቆ ለማህበረሰቡ፣ለትምህርት ቤት እንዲሁም ለጤና ጣቢያ አገልግሎት የሚሰጥ ሲሆን ይህ በሶላር የሚሰራ የውኃ ፕሮጀክት ከ1500 በላይ አባውራና እማውራዎችን እንደሚያስጠቅም ታውቋል።
በመጨረሻም ኮሩ በተቆጣጠራቸውና በሚንቀሳቀስባቸው ዋግ ኸምራ ብሔረሰብ ዞንና ሰሜን ወሎ ዞን ወረዳዎች መሰል የማህበረሰብ እንደ ንፁህ መጠጥ ውኃ አገልግሎት ዕጥረት ድርቅና ወረርሽኝ ችግሮችን እንድትቀርፉልን ለግብረ ሰናይ ድርጅቶች ጥሪ እያስተላለፍን አስፈላጊውን ጥበቃና ከለላ፣የሰው ኃይል ጉልበትና የቁሳቁስ ድጋፍ ምቹ ሁኔታዎችን እንፈጥራለን ሲሉ የኮሩ ምክትል ፖለቲካ ዘርፍ ኃላፊ የሆኑት አርበኛ ፋኖ አለምነው መብራቱ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።
መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልውና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል ሲል የአፋብኃ ምስራቅ አማራ ቀጠና ግዙፉ ላስታ ጄኔራል አሳምነው ፅጌ ኮር ህዝብ ግንኙነት ኃላፊ ፋኖ ቢሆነኝ ቢያበይን መረጃውን አድርሷል።
ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን!!!
የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል (አፋብኃ)
ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ
ህዳር 01/ 2018 ዓ.ም
የትግሉ መምረርና ክፋት በዚህ ምስል ብቻ ካልገባህ/ሽ/ አንተ ወንይም አንቺ መቼም ሊገባችሁ አይችልም!
እነዚህ ሁለት አባት አርበኞች ከራሳቸው በለይ የሚወዷቸውን እና የሚሳሱላቸውን ልጆቻቸውን በቀኝ እና በግራ ወድቀውባቸዋል። ለዛውም ሩጠው ያልጠገቡ፣ የወጣትነት ዘመናቸውን እንደማንኛውም ወጣት ያልኖሩ አባቶቻቸውን ተከትለው ጫካ ገብተው ይህችን ርጉም ዓለም እስከተሰናበቱበት ቀን ድረስ ከሰው አውሬዎችና ከዱር አውሬዎች ጋር ሲዋጉ የኖሩ ለጋ ልጆቻቸውን ገብረዋል። ይህ ሁሉ ሁኖ ግን ለማፅናናት ብትሞክሩ ከሚሊዬን አማራ ልጆቼ ውስጥ ሁለቱን አጣሁ የሚል ምላሽ ሲመልሱላችሁ ተጨማሪ ቃል መናገር ይሳናችኋል!
ምድረ ደናቁርት የፌስቡክ አርበኛ ደግሞ በወጣቶቹ ሞት የራሱን የቆሸሸ ፖለቲካ ሲሰራባቸው ስታዩ ለዚህ ስብስብ ተብሎ የሚከፈል የህይወት መሰዋዕትነት ያንገበግሻችኋል። የእውነት በሞተና ለእውነት ለመሞት በተዘጋጀ ሰው ላይ እንዴት ፖለቲካ ይሰራል?
ትግሉን ሰበብ አድርጎ ገበሬን ሲያሰቃይ፣ንብረት ሲዘርፍ፣ሲያፈናቅልና በደካሞች ላይ ሲበረታ የሚያዩትን ዘራፊ ግን ሲናገሩትና ሲታገሉት አታገኟቸውም! ምክንያቱም እነሱም የዚያ ቡድን ተካፋይ እስከሆኑ ድረስ የመናገር ሞራል ስለሌላቸው!
ለአርበኞች አባቶቼ ግን ፅናቱን ይስጣችሁ አልላቸውም እነሱ አንዴ በፅናት ላይ የቆሙ ናቸውና! እንዴውም የነሱን ፅናት ለኛም ይስጠን! ዲቭ
በተለያዩ ከተሞች እየወጡ ስላሉ የመሬት ሊዝ ጨረታን አስመልክቶ ከአፋብኃ ምስራቅ አማራ ቀጠና ምንሊክ ዕዝ የተሰጠ ማስጠንቀቂያ!
አማራን በአማራ ማውደምና ማጥፋት በሚል ፋሽስታዊ እሳቤ አማራንና የአማራን ሁሉ በሆድ አደር የአማራ ሚሊሻ፣ የአማራ ፖሊስ፣ የአማራ አድማ ብተና እና መከላከያ፤ በስልጣን መስተፋቅርና በሆዳቸው የወደቁ የአማራ ካድሬዎችን በመጠቀም በአማራ ላይ ጦርነት ከከፈተ ዓመታት ተቆጥረዋል።
ሰልቃጩ የአብይ አህመድ አገዛዝ አማራን ለማውደም ከሚከተለው አሠራር የአማራን አንጡራ ሃብት በመጠቀም አማራን መውጋት ሲሆን ለዚህ እኩይ ሥራው ግንባር ቀደም ተባባሪዎች እነዚህ የብልጽግና ስርዓት ደንገጡር ካድሬዎች እና የአማራ ሆድ አደር የጸጥታ አካላት ናቸው።
በክልሉ ውስጥ የሚገኝ የከተማ መሬት ደግሞ አገዛዙ ለዕኩይ ሥራው ተባባሪዎቹ ለሆኑት ከሃዲ ግለሰቦችና ማህበራት በሊዝ ስም የሚቸበችበው ሃብት ነው። ይሄንን አስመልክቶ ፋኖ ግልጽ የሆነ ማስገንዘቢያዎችንና ማስጠንቀቂያዎችን በተደጋጋሚ ለህዝብ ሲያድርስ ቆይቷል። ከሀምሌ 1 / 2015 ዓ.ም. ጀምሮ የተፈጸመ የመሬት ሊዝ ግዥ በፋኖ ፊት እንደማይጸና (ለአማራ ሕዝብ እንደሚመለስ ማለትም እንደሚወረስ) እና እንደውም ለዚህ አውዳሚ ስርዓት ተባባሪነት ስለሆነ በወንጀል የምንጠይቅ መሆኑን በተደጋጋሚ አስጠንቅቀናል።
ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ደግሞ በደሴ፣ በኮምቦልቻ እና በቆቦ በተለይም በወልደያ ከተማ ይሄው የመሬት ሽያጭ ተጠናክሮ መቀጠሉን በዕዛችን የመረጃና ደህንነት ክፍል ማረጋገጥ ችለናል።
የወልዲያ ከተማና መሰረተ ልማት መምሪያ ከጥቅምት 12 እስከ 25/2018 ዓ.ም. ድረስ የቆየ የመሬት ሊዝ ጨረታ ማስታወቂያ ያወጣ ቢሆንም ብዙሃኑ ሕዝባችን በዚህ ጨረታ ሊሳተፍ አልቻለም። በዚህ የሕዝባችን ንቃት በእጅጉ ደስ ብሎናል። ይሁን እንጂ አማራ ሆነው ሳለ ፀረ አማራ በመሆን ከአብይ አህመድ ስርዓት ጋር በመተባበር በአማራ ሕዝብ መቃብር ላይ ለመበልጸግ የሚናፍቁ ጥቂት የስርዓቱ የጥቅም ተጋሪዎች አሉ። ስለሆነም የወልድያ ከተማ ሆድ አደር ካድሬዎች በድጋሚ ከጥቅምት 26 እስከ ህዳር 2/2018 ዓ.ም. የመሬት ጨረታውን አራዝመው የሃጢያታቸው ተጋሪዎችን በመጠበቅ ላይ ይገኛሉ።
ከዚሁ ጋር ተያይዞ የወልድያ ከተማ ባንዳዎች ከወልድያ ከተማ ማዘጋጃ ቤት ወረድ ብሎ የሚገኘውን የአረጋውያን ማሕበር መሬት (መሰረት የወጣለትን ህጋዊ ይዞታ) የዚሁ የሊዝ ሽያጭ አካል በማድረግ ለጨረታ አቅርበውታል። አረጋውያን ማህበሩ ከ160 በላይ አረጋዊ አባላትን ያቀፈ ማህበር ነው።ይሁን እንጂ አረጋዊ ማህበሩ ህጋዊ ይዞታቸው ስለሆነ ባቀረቡት ቅሬታ 5 የማህበሩ ኮሚቴዎች በወልድያ ከተማ ተቀዳሚ ከንቲባ ተብዬው በባንዳው ዱባለ አብራሬ ትዕዛዝ ለእስር ተዳርገዋል። በዱባለ አብራሬ የታሰሩት የአረጋውያን ማህበርሩ ኮሚቴዎች አበበ ዳውድ (ሰብስቢ)፣ ሰፊው አማረ (የኮሚቴ አባል)፣ ምስጋናው ወርቁ (የኮሚቴ አባል)፣ ይማም መሃመድ (የኮሚቴ አባል) እና ሌሎችም ይገኙበታል።
የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል (አፋብኃ) ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ በዚህ የሊዝ ጨረታ ከገዳዩ የአብይ አህመድ ስርዓት ጋር ለመተባበር ላቀዳችሁ ሁሉ እንደወትሮው ወገናዊ ምክሩን ለማድረስ ይወዳል። ነገር ግን ለፋኖ ትዕዛዝ አሻፈረኝ ብሎ አማራን ሳላጠፋ አላርፍም በማለት በመደበኛና በኢ-መደበኛ ቅጥረኛ ሰራዊቱ አማራን በክልሉና በኦሮሚያ ውስጥ ለሚጨፈጭፍ የብልጽግና ስርዓት ተባባሪ የሚሆን ካለ አፋብኃ ምስራቅ አማራ ቀጠና ምንሊክ ዕዝ እርምጃ የሚወስድ ይሆናል።
በመጨረሻም በዛሬው ዕለት ለወልደያ ከተማ አስተዳደር ያወጣነው መግለጫ ለሁሉም ከተማ አስተዳደሮችና የወረዳ አስተዳደሮች እንደሚያገልግል እየገለጽን፣ ይሄን መመሪያ ጥሶ በተገኘ ሻጭም ሆነ ገዥ እርምጃ የምንወስድ መሆኑን እያሳወቅን፣ ከአገዛዙ ጋር ሽርክና የገባችሁ አካላት በሙሉ ገንዘባችሁን ከማባከን ወይም ከመበላት እንድታድኑ እያስታወስን፣ ይሄን መመሪያ ተላልፎ ከአገዛዙ ጋር የተሰለፈ ሁሉ ከአማራ ሕዝብ ነጻነት ማግስት የገዛችሁት መሬት ለሕዝብ፣ እናንተም በሕግ ተጠያቂ እንደምትሆኑ ማሳወቅ እንወዳለን!
መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ሕዝብ የህልውና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል!
ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን!
አፋብኃ ምስራቅ አማራ ቀጠና ምንሊክ ዕዝ
ህዳር 1 ቀን 2018 ዓ.ም
+4
#አዲናስ
ወጣቶቹ የተኩስ ልዉዉጥ አድርገዉ ከጠላት ካምፕ ወጡ‼️
አዲስ ቅዳም ከተማ ከተከማቸዉ የብልፅግና ታጣቂ ዉስጥ
አብርሀም ተሰማ እና
ባንቲገኝ የኋላ የተባሉ #2 አባላት ስርአቱ በአማራ ህዝብ ላይ እያደረሰ ያለውን በደል በመፀየፍ ከስዕራቱ ጎን አንቆምም በማለት ዛሬ ለሊት ጥቅምት 30/2018 ዓ/ም በተመደቡበት አካባቢ ከሚገኙ የስርአቱ ወንበር አስጠባቂ ታጣቂዎች ላይ ተኩስ በመክፈት #3 አጥቦ አይለብስ ሚሊሻ በከባድ ሁኔታ አቁስለዉ ከበባዉን በመጣስ እረመጧን የአፋብኃ ምዕራብ አማራ ቀጠና ቴዎድሮስ እዝ ፫ኛ ጎጃም አገዉ ምድር ክ/ጦር ፲አለቃ ኤፍሬም አጥናፉ ብርጌድ በሰላም ተቀላቅለዋል።
ይቀጥላል ገና
ህዳር 1/2018 ዓ.ም
🔥አርበኝነት በጀግኖች መስዕዋትነት የደም ቀለም የሚከተብ ህያው የኪዳን ብራና ነው‼️
ከአፋብኃ በላይ ዘለቀ ዕዝ የተላለፈ የሀዘን መግለጫ
ከጥንት ታሪካችን ከዛሬ ተግባራችን ከራስ በላይ ለሀገር ከራስ በላይ ለህዝብ በማስቀደም በላብ ተጠምቀን ደማችን አፍሰን አጥንታችን ከስክሰን አንጡራ ንብረት አባክነን በድልና በክብር ሀገር ፀንቶ እንደቆየና ዛሬም የህዝባችን ማንነታዊ ህልው ዕጣ አስቀጣይነት አርበኝነታችን መሆኑን እንገነዘባለን።
ጥቅምት 29/2018 ዓ.ም በሰሜን ጎንደር ዞን ዳባት ወረዳ አጅሬ የተሰኘች አነስተኛ ከተማ የጠላትን የእጅ አዙር ተልዕኮ ሳያነግቡ እንዳልቀረ በተጠረጠሩ ግለሰቦች በተተኮሰ ጥይት የሰሜን አምባራስ ክ/ጦር አዛዥና የራስ አሞራው 3ኛ ኮር አስተዳደር ኃላፊ የሆነው ጀግናው አርበኛ ጌትነት መሳፍንት መስዕዋትነት ከፍሏል።
ከአስር ዓመት በላይ ከወላጅ አባቱ ከአይበገሬው አርበኛ መሳፍንት ተስፉ ጋር በመሰለፍ የለጋነት ዕድሜውን ሁሉ በአርበኝነት በላቀ ወታደራዊ ብቃት በተሻለ ፖለቲካዊ ንቃት ፍዳ የገጠመውን የአማራ ህዝብ ለመታደግ አያሌ የጦር ግንባሮችን በድል የቋጨው ጌትነት መሳፍንት በተለያዩ ግንባር ተጋድሎዎች አምስት ጊዜ ቆስሎ የነበረ ቢሆንም ከቁስሉ ሳያገግም ፍልሚያ ተመልሶ እየተሰለፈ ሲሻው በክላሽ ሲሻው በብሬን ጠላትን እየገረፈ ድል ሲነሳ ኑሯል።
ወላጅ አባቱ አርበኛ መሳፍንት ተስፉ፣አጎቱ መከተ ተስፉን፣ወንድሞቹ ሻምበል መሳፍንት፣ገብሬ መሳፍንትን ጨምሮ ከ30 በላይ ቤተሰቦቹ በነቂስ በተሰለፉበት የአስርት ዓመታት የአማራ ትግል የጨለማው ዘመን ፅልመት አለንልህ አማራ ብለው የተስፋ ጮራ ከፈነጠቁት ጀግና አርበኞች መካከል በለጋ ዕድሜያቸው የተሰለፉት ብላቴናዎች ጌትነት መሳፍንትና ሻምበል መሳፍንት እንደነበሩ ሀገር ያወቀው ፀሀይ የሞቀው ሀቅ ነው።
አርበኛ ጌትነት መሳፍንት ተስፉ በድንገተኛ አጋጣሚ የህይወት መስዕዋትነት እስከከፈለበት ዕለት ድረስ ደከመኝ ሰለቸኝ ሳይል በቀናነትና በጀግንነት የተሰጠውን ህዝባዊ ተልዕኮ ሁሉ ሲፈፅም ቆይቷል።
ከዚህ ቀደም በርካታ ቤተዘመድ በትግል መስዕዋትነት ያጣው የምንጊዜም ወደር የለሽ ጀግና አርበኛ መሳፍንት ተስፉ የአብራኩ ክፋይ የሆኑትን ልጆቹን አርበኛ ገብሬ መሳፍንትና አርበኛ ጌትነት መሳፍንት በማጣቱ እንዲሁም የዕዛችን ጠንካራ አርበኛ ጌትነት መሳፍንት መስዕዋትነት የተሰማንን ልባዊ ሀዘን እየገለፅን
አርበኝነት በጀግኖች መስዕዋትነት የደም ቀለም የሚከተብ ህያው የኪዳን ብራና ነውና አርበኛ ጌትነት መሳፍንት ተስፉ እና ሌሎች እልፍ ጀግና አርበኞቻችን ዓላማ ግብ ለማድረስ ከመቸውም ጊዜ በላይ በብስለትና በቁርጠኝነት እንተጋለን።
ለወዳጅ ቤተ ዘመድ መፅናናቱን እንመኛለን!!
©የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል (አፋብኃ
ሰሜን አማራ ቀጠና በላይ ዘለቀ ዕዝ
01/ዐ3/2018 ዓ.ም
በጉልህ እንደሚነሳው ሁሉ፤ በአማራ ትግል ውስጥ የተሳተፈ የትኛውም ታጋይም ለዘላለም በደማቅ ቀለም ስሙ የሚመዘገብ ይሆናል።
ስለሆነም መላው የአማራ ሕዝብ፣ የኢትዮጵያ ሕዝብና በውጭ የምትኖሩ ኢትዮጰያዊያንና ትውልደ ኢትዮጵያዊያን ትግላችንን ከመደገፍም አልፎ ከአማራ ሕዝብ ጎን በመቆም አብርን የምንሰራበት ቀን ቅርብ እንደሚሆን ባለሙሉ ተስፋ ነኝ።
ኅልውናችን በተባበረ ክንዳችን!!!
የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል ደቡብ
የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል ምዕራብ
የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል ሰሜን
የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል ምስራቅ
የወለጋ ክፍለሀገር ፋኖ ዕዝ (ቢዛሞ)
አማራ፣ ኢትዮጵያ! ዳዊት
30/02/2018 ዓ.ም
+7
➾ ደማቁ የግዮን ብርጌድ ልዩ የኮማንዶ ምርቃት‼
የአፋብኃ ምዕ/አማራ ቀጠና ቴዎድሮስ ዕዝ ጎጃም አገው ምድር 3ኛ ክ/ጦ ጀብደኛው ግዮን ብርጌድ ለአምስት ለወራት ያሰለጠናቸውን ልዩ የኮማንዶ አባላትን አስመርቋል።
በጎጃም አገው ምድር 3ኛ ክ/ጦር ግዮን ብርጌድ ልዩ የኮማንዶ ስልጠና የወሰዱ ምልምል ኮማንዶዎችን አስርቋል።
ትውልዱን በአካል ብቃት የዳበረ ፣ በስነልቦና የጠነከረ ፣ የፖለቲካ ሪዮት ከጠብ መንጃ ጋር የታጠቀ ለማድረግ እስከ ምፅዋት ድረስ እንተጋለን ።
አፋብኃ ከውጊያ ጎን ለጎን አዲሱ ትውልድ የነፃነት ጥሙን በደሙ ለመቁረጥ ይሰበሰባል፣ ፣ ይደራጃል ፣ ይሰለጥናል ፣ ይታጠቃል ፣ ጠላቱን ታግሎ ያሸንፋል ።
የአማራን ህዝብ በራሱ ሜዳ ፣ በራሱ ህዝብ ፣ በራሱ ሐብት ፣ በራሱ የፖለቲካ ሪዮት እንዲታገል አድርገነዋል ።
ተመራቂ ኮማንዶዎች ታዳሚውን ያስደመመ ደማቅ ትርኢት ያቀረቡ ሲሆን በፕሮግራሙም የአፋብኃ ቴወድሮስ ዕዝ ም/ዘመቻ መምሪያ ኃላፊ መቶ አለቃ ማርቆስ አሞኘ እና በተዋረድ በተለያዬ ኃላፊነት ያላቸው የዕዝ አመራሮች፣ የአፋብኃ ቴወድሮስ ዕዝ ጎጃም አገው ምድር 3ኛ ክ/ጦር ወታደራዊ አዛዥ አምሳ አለቃ ደሞዝ ግርማ፣ የክፍለ ጦር ዘመቻ መምሪያ ኃላፊ መቶ አለቃ መለሰ አይናለም፣ የግዮን ብርጌድ ሰብሳቢ አምሳ አለቃ ተፈራ እንዲሁም የከቡሬ ዳሞት እና የአረንዛው ዳሞት ብርጌድ አመራሮች ታድመዋል፤
አዲስ ትውልድ አዲስ አስተሳሰብ አዲስ ተስፋ !!
+9
ጥቅምት 30/2018 ዓ.ም
በደህና ማርያም ቀበሌ የህዝብ ተቋማት እና የግለሰቦች ሆቴል እና ሱቆች በአብይ ሰራዊት ዝርፊያ ተፈፀመባቸው።
ሁሌም የፋኖን ብትር መቋቋም ያቃተው የአብይ ሰራዊት በደህና ማርያም ቀበሌ የጤና ተቋማትን እና የግለሰብ ሱቆችን ሆቴሎችን እና መኖሪያ ቤቶችን የሚችለውን ያህል ዘርፎ በአይሱዚ ጭኖ የሄደ ሲሆን መሸከም ያልቻሉትን ደግሞ ሰባብረው ከጥቅም ውጭ አድርገው አውድመወት ሄደዋል።
በጥቅሉ በዛሬው እለት የተወሰድ ንብረቶች
➢ 3 አግዳሚ ፍሪጅ
➢ 2 ፍላት ቴሌቪዥን
➢ 2 መዝቦሎድ አልጋ
➢ ከ 3በላይ የቁም ከብቶች በሬወች
➢ 6 ኩንታል ጤፍ
➢ 3 ኩንታል ድቄት
➢ 27 ካሳ ቢራ እና ለስላሳ ከነ ሳጥኑ የተወሰደባቸው ሲሆን፦
1ኛ የእናቶች እና ህፃናት መገልገያጤና ኬላ
2ኛ ሙልየ የፍየል ..ምግብ ቤትሙሉ እቃ
3ኛ መቅደስመላኩ..ሙሉየምግብየቤትእቃ
4ኛ እንዳለው ሰንደቁ ...ሙሉ የቤትእቃ
5ኛ አቢቴ ይበል....ሙሉ የቤት እቃ 3በሬ በአጠቃላይ የአማራ የሆነን ማንኛውንም ነገር ሁሉ ለማጥፋት አልሞ የተነሳ ስለሆነ
መብታችን ነፃነታችን ልናስከብር የምንችለው ብቸኛው መዳኛ መንገድ እንደ አማራ ሁሉም በመደራጀት መሰልጠን እና በመታጠቅ ህዝባዊ ማዕበል በሆነ መንገድ ጠላት በገባበት ቦታ ሁሉ ዘምተን ለመጨረሻ ጊዜ ማንነታችን ማስከበር አለብን ለዚህም በቀጣይ ለሚደረጉት ጥሪ ሁሉም እራሱን ማዘጋጀት አለበት።
ሐብታሙ የሱፍ
ጥቅምት 30/2018 ዓ.ም
+2
የአማራ ፋኖ ብሄራዊ ኃይል ደቡብ አማራ ቀጠና አሳምነው ዕዝ ሁለተኛ ኮር መመስረቱን አስታወቀ!!
የቀደሞዉ ከሰም ክፍለጦር ዛሬ ጥቅምት 30/2018 ዓ.ም በይፋ ወደ ኮር አድጓል።
በውስጡ ግዙፍ ሰራዊት የገነባዉ ከሰም ክፍለጦር አደረጃጀቱን ወደ ኮር እንዲያድግ ተደርጓል።
ኮሩ በስሩ ነበልባል ክፍለጦ፣ኃ/ ማሪያም ማሞ ክፍለጦ እና ቡልጋ ክፍለጦር እንዲሁም ሻምበል ፋንታ እና የረር ብርጌዶችን በማቀፍ የደቡብ አማራ ቀጠና አሳምነዉ ዕዝ ሁለተኛ ኮር ሁኖ ተመስርቷል።
በምስረታ ስነስርዓቱ የአፋብኃ ሴንትራል ኮማንድ አባል ጄነራል ተፈራ ማሞ፣የአፋብኃ ሴንትራል ኮማንድ አባል እና የደቡብ አማራ ቀጠና አሳምነዉ ዕዝ ስራ አስፈፃሚ አባል ፕሮፌሰር ማርከዉ መንግስቴ፣የአፋብኃ ደቡብ አማራ ቀጠና አሳምነው ዕዝ ፅ/ቤት ሀላፊ አርበኛ ዳግም እንዲሁም የዕዙ ህዝብ ግንኙነት ኃላፊ አርበኛ ዶክተር አብደላ እንድሪስ እና የዕዙ ምክትል ወታደራዊ አዛዥ አርበኛ አምሳ አለቃ ካሳ ተገኝተዋል።
