ru
Feedback

Не попадитесь на канал ботавода! Telemetrio находит и помечает такие каналы 👉 Хотите видеть метку — оформите подписку

ፍኖተ-አማራ ሚዲያ (Finote Amhara Media)

ፍኖተ-አማራ ሚዲያ (Finote Amhara Media)

Открыть в Telegram

የተመሠረተው የአማራን ሕዝብ ለማንቃት፣ ለማደራጀት እና ለማስተባበር ነው። የአማራ ሕዝብን ✅ ፖለቲካዊ ✅ ማህበራዊ ✅ ኢኮኖሚያዊ ታሪካዊ ጥያቄዎችን ለማሰማት እና የአማራን ሕዝብ በማንቃት ሰፊውን ሕዝብ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ይሰራል። ወደዱም ጠሉም የኃላ ታሪካችን በእኛ እጅ ይፃፋል። አማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ ( አፋብን)

Больше
4 490
Подписчики
+1024 часа
+847 дней
+87330 дней
Архив постов
አልሽኮረመምም። የምችለውን ሁሉ አደርጋለሁ። ሰይጣንን ተዋጉት እንጂ ተማጸኑት አልተባልንም። ሃይማኖታችንን፣ ሕዝባችንን፣ ሃገራችንን ለማዳን በጸሎትም በጥይትም በአፍም በመጽሐፍም እንሰለፋለን። ©ዲያቆ
+2
አልሽኮረመምም። የምችለውን ሁሉ አደርጋለሁ። ሰይጣንን ተዋጉት እንጂ ተማጸኑት አልተባልንም። ሃይማኖታችንን፣ ሕዝባችንን፣ ሃገራችንን ለማዳን በጸሎትም በጥይትም በአፍም በመጽሐፍም እንሰለፋለን። ©ዲያቆን ባንተ አምላክ እያሌው ውድ አማራዊያን ከግንባር መረጃዎቻችን በሁሉም አማራ ተደራሽ እንሆን ዘንድ እየሰራን እንገኛለን የበኩሉዎን አስተዎፆ ያድርጉ ‼️ የቴሌግራም ቻናላችን ጆይን ሸር አድርጉ እንወያያለን እንማማራለን እንደራጃለን አብርን እናሸንፋለን አድራሻችን👇👇👇👇 https://t.me/httpsuYkZrGfSZrNjNjFk

🔥#ሕዝባዊ_የውይይት_መድረኮች_ተጠናክረው_ቀጥለዋል‼️ የአፋብኃ ምዕራብ አማራ ቀጠና ቴዎድሮስ ዕዝ ቀኝ ጌታ ዮፍታሄ ንጉሴ 6ኛ ክፍለ ጦር በሚያስተዳድራቸው ቀጠናዎች ማሕበረሰባዊ ውይይቶችን እያካሄደ
+1
🔥#ሕዝባዊ_የውይይት_መድረኮች_ተጠናክረው_ቀጥለዋል‼️ የአፋብኃ ምዕራብ አማራ ቀጠና ቴዎድሮስ ዕዝ ቀኝ ጌታ ዮፍታሄ ንጉሴ 6ኛ ክፍለ ጦር በሚያስተዳድራቸው ቀጠናዎች ማሕበረሰባዊ ውይይቶችን እያካሄደ ይገኛል። በትናንትናው ዕለትም የማቻክል በላይ ዘለቀ ብርጌድ ከሚያስተዳድራቸው ቀጠናዎች አንዱ ከሆነው የደብረ ቀለሙ ማሕበረሰብ ጋር ሰፊ ውይይት አካሂዷል። በውይይቱ የአማራ ፋኖ የትግል ደረጃን፣ አሁናዊ ቁመናንና የወደፊት የትግል አቅጣጫዎችን አስመልክቶ ጥልቅ ውይይት የተደረገ ሲሆን በትግሉ መሠረታዊ ነጥቦች ዙሪያም ለማሕበረሰቡ የስርጸት ስራ ተሠርቷል። መስከረም 05/2017 ዓ.ም ድል ለሕዝባችን! ©ቀኝ ጌታ ዮፍታሄ ንጉሴ 6ኛ ክፍለ ጦር 05/ዐ1/2018 ዓ.ም ውድ አማራዊያን ከግንባር መረጃዎቻችን በሁሉም አማራ ተደራሽ እንሆን ዘንድ እየሰራን እንገኛለን የበኩሉዎን አስተዎፆ ያድርጉ ‼️ የቴሌግራም ቻናላችን ጆይን ሸር አድርጉ እንወያያለን እንማማራለን እንደራጃለን አብርን እናሸንፋለን አድራሻችን👇👇👇👇 https://t.me/httpsuYkZrGfSZrNjNjFk

🔥2 የአገዛዙ የሞርተር ምድበተኛ አባላት ግዮን ብርጌድን ተቀላቀሉ‼️ ===================== ሰከላ ወረዳ ግሽ አባይ ከተማ የመሸገው የ73ኛ ክፍለጦር 4ኛ ሻለቃ ሞርተር ምድብተኛ የነበሩ
+2
🔥2 የአገዛዙ የሞርተር ምድበተኛ  አባላት ግዮን ብርጌድን ተቀላቀሉ‼️ ===================== ሰከላ ወረዳ ግሽ አባይ ከተማ የመሸገው የ73ኛ ክፍለጦር 4ኛ ሻለቃ ሞርተር ምድብተኛ የነበሩ አንዋር አባዝናብ ሞርተር 120 እና ፉአድ ለዲን ሞርተር 82 ምድበተኛ የነበሩ አባላት አገዛዙን በመክዳት ሁለት ጥቁር ክላሽ ከእነ ተተኳሹ፣ ሁለት የሞርተር ቅንቡላ እና አንድ አስቃጥላ የዲሽቃ ጥይት በመያዝ አፋብኃ ምዕራብ አማራ ቀጠና ቴዎድሮስ ዕዝ ጎጃም አገው ምድር 3ኛ ክፍለ ጦር ግዮን ብርጌድ ኃይለእዬሱስ አድማሱ ሻለቃን ተቀላቅለዋል። አዲስ ትውልድ!አዲስ አስተሳሰብ!አዲስ ተስፋ! ©የግዮን ብርጌድ ህ/ግንኙነት    መስከረም ፭/፳፻፲፰    ጎጃም-ዓምሓራ 05/ዐ1/2018 ዓ.ም ውድ አማራዊያን ከግንባር መረጃዎቻችን በሁሉም አማራ ተደራሽ እንሆን ዘንድ እየሰራን እንገኛለን የበኩሉዎን አስተዎፆ ያድርጉ ‼️ የቴሌግራም ቻናላችን ጆይን ሸር አድርጉ እንወያያለን እንማማራለን እንደራጃለን አብርን እናሸንፋለን አድራሻችን👇👇👇👇 https://t.me/httpsuYkZrGfSZrNjNjFk

የሀይል ማፍረሱ ተጠናክሮ ቀጥሏል። በአፋብኃ ምዕ/ አ/ ቀ/ ቴ/ዕ 2ተኛ/ተፈራ ዳምጤ/ ክፍለ ጦር የዮሐንስ አለማየሁ ብርጌድን አትኩት ቢተውና ከ303ኛ ኮር፣1ኛ ሻለቃ፣1ኛ ሻምበል ፲ አለቃ አስራት
+1
የሀይል ማፍረሱ ተጠናክሮ ቀጥሏል። በአፋብኃ ምዕ/ አ/ ቀ/ ቴ/ዕ  2ተኛ/ተፈራ ዳምጤ/ ክፍለ ጦር የዮሐንስ አለማየሁ ብርጌድን አትኩት ቢተውና ከ303ኛ ኮር፣1ኛ ሻለቃ፣1ኛ ሻምበል ፲ አለቃ አስራት ማርቆስ የተባሉ  አንድ ሚሊሻና አንድ የመከላከያ አባላት ከነሙሉ ትጥቃቸው ተቀላቅለዋል። በሰላም ፋኖን የተቀላቀሉት ሁለቱ የመንግስት ሀይሎች በተለይ የሚሊሻ አባላትን በተለያዩ ጥቅማጥቅሞች አታለው ካስገቡ በኋላ የፋኖ መረጃ ናችሁ እያሉና ሌሎችንም ተልካሻ ምክንያቶች በመፈለግ  ከፍተኛ የሆነ ድብደባና ጭቆና  እንደሚፈፅሙባቸው ገልፀዋል።      አዲስ ትውልድ      አዲስ አስተሳሰብ      አዲስ ተስፋ የዮሐንስ አለማየሁ ብርጌድ ህዝብ ግንኙነት  መስከረም 04/2018 ዓ.ም ውድ አማራዊያን ከግንባር መረጃዎቻችን በሁሉም አማራ ተደራሽ እንሆን ዘንድ እየሰራን እንገኛለን የበኩሉዎን አስተዎፆ ያድርጉ ‼️ የቴሌግራም ቻናላችን ጆይን ሸር አድርጉ እንወያያለን እንማማራለን እንደራጃለን አብርን እናሸንፋለን አድራሻችን👇👇👇👇 https://t.me/httpsuYkZrGfSZrNjNjFk

ደብረማርቆስ ከተማ ላይ በመሸገው አረመኔ ሰራዊት ላይ ሰርጎገብ ጥቃት ተፈፀመ። በቀን 05/01/2018ዓ.ም የአፋብኃ ምዕራብ አማራ ቀጠና ቴዎድሮስ ዕዝ የሐዲስ ዓለማየሁ 7ኛ ክ/ጦር የአዋበል መብረቁ ብርጌድ ሰርጎ ገብ ሀይሎች ደብረ ማርቆስ ውሀ ጋኑ ላይ በመግባት ምሽግ በተኛው የአረመኔው አገዛዝ ሰራዊት ላይ የቦምብ ጠቃት ፈፅመዋል። በተሰራው ኦፕሬሽን የአብማ ክፍለ ከተማ ምልመላና ስልጠና ሀላፊ የሆነውን ባንዳ ንጉሴ ጨምሮ 3 ሰላም አስከባሪ ምሊሻዎች ሲደመሰሱ 2 አድማ ብተናዎች ከባድ ቁስለኛ ሆነዋል። ባንዳን የማፅዳት ዘመቻው ተጠናክሮ ይቀጥላል። አዲስ ትውልድ፣አዲስ አስተሳሰብ፣አዲስ ተስፋ!! የሐዲስ ዓለማየሁ 7ኛ ክ/ጦር ህ/ግንኙነት ሀላፊ ፋኖ መ/ር እንደሰው ታምሩ ውድ አማራዊያን ከግንባር መረጃዎቻችን በሁሉም አማራ ተደራሽ እንሆን ዘንድ እየሰራን እንገኛለን የበኩሉዎን አስተዎፆ ያድርጉ ‼️ የቴሌግራም ቻናላችን ጆይን ሸር አድርጉ እንወያያለን እንማማራለን እንደራጃለን አብርን እናሸንፋለን አድራሻችን👇👇👇👇 https://t.me/httpsuYkZrGfSZrNjNjFk

✍️ከላይ በምስሉ የሚታየው አርበኛ  የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ሀይል ሰሜን አማራ ቀጠና በላይ ዘለቀ ዕዝ ራስ አሞራው ውብነህ 3ኛ ኮር የጭና ክ/ጦር ዋና ሰብሳቢ አርበኛ ዳንኤል አስረስ ይባላል። ‎አርበኛ ዳንኤል የአማራ የህልውና ትግል ከመጀመሩ በፊት ከወንድሞቹ ጋር የፋኖነት ስነ ልቦናዊ ትጥቅ በመታጠቅ ከ2008 ዓ,ም ጀምሮ ለአማራ ህዝብ እታገለና እያታገል የሚገኝ በሰራዊቱና በሰራዊት አመራሮቹ ከፍተኛ ተወዳጅኘት ያለው ወንድማችን ሲሆን  የአማራ የህልውና ትግል እንደተጀመረም ሳያቅማማ ከወንድሞቹ ከነ አርበኛ ሀብቴ ወልዴ ጋር በመሆን  #መኪናውን_ሽጦ ሰናይፐርና ብሬን  የተባለውን   ውድ የጦር መሣሪያ ገዝቶ ለትግል እያዋለ የሚገኝ በታላቅ የትግል አላማ ና ታሪክ የሚታወቅ በባህሪው ደግነትን የተጎናፀፈ ጅግናችን ነው። አርበኛ ደንኤል አስረስ ወደፊት የሚገሰገሥ የጦር ጠበብት መሪ ሢሆን ለአማራ ትግል በርካታ ዋጋ እየከፈለ የሚገኝ ሲሆን በቅርቡ ታላቅ ወንድሙን #አርበኛ_አይቶልኝ_አስረስን  ለአማራ  ህልውና ትግል ሲዋደቅ ሰማዕትነትነትን የተቀበለ ሲሆን አርበኛው ወንድሙ የወደቀለትን  አላማውን በጀግንነት  ወደፊት አያስቀጠለ የሚገኝ እዩኝ እዩኝ ከማይሉት ቆራጥ የቤጌምድር  አርበኞች መካከል አንዱ ነው። ‎በአርበኛው የሚመራው የጭና ክፍለጦር መጀመሪያ በአራት በርጌዶች ተመስርቶ  የመጀመሪያ ተቋም መሥራች ክፍለጦርም ሲሆን አሁን ግን የሰራዊት ቁጥሩን በመጨመር  በስሩ  አምስት በርጌዶች ያሉት ሲሆን  ‎✅  አጅሬ ብርጌድ ‎✅ ቢትወድ አዳነ በርጌድ ‎✅ አንጋው ተገኘ ብርጌድ ‎✅ ሊማሊሞ ብርጌድ ናቸው። ‎✅ራስደጀን ብርጌድ እነዚህ አምስት ብርጌዶች በርካታ የሰው ሀይል ያላቸው ሲሆን ከዚህ በፊት በነበረው ተጋድሎ  አስደማሚ ጀብድ በመፈጸም ከጠላት የሚከተሉትን ማለትም :- ✅ አንድ ሞርተር ✅ስድስት ስናይፐር ፣ ✅20 ብሬን  እና መትረየስ ✅ ከ300 በላይ የነብስ  ወከፍ የጦር መሣሪያ  ከጠላት #ማርኮ  መታጠቅ የቻለ   አንጋፋ ክፍለጦር ነው። ‎አንጋፋው ጭና ክፍለጦር ከተላያዩ አጎራባች ክፍለጦሮች ጋር የጥምር አወደ ውጊወችን የሚያደርግና እያደረገ የሚገኝ ሰፊ ቀጠና ሽፍኖ የሚንቀሳቀስ በመሆኑ ከጠገዴ አርማጭሆ እስከ አዲርቃይ ዘሪማ እንዲሁም ከደባርቅ ዳባት የሚንቀሳቀስ ክፍለጦር ነው። ‎በጭና ክፍለጦር ነፃ የወጡና አስተዳደራዊ የህዝብ ችግሮች አተፈቱ ያሉበቸው ቀጠናዎች ጥርሀይና ንዑሥ ወረዳላይ የሚገኙ ቀበሌዎችና በርካታ የደባርቅ ዙሪያ ወረዳ የሚገኙ ቀበሌዎች ሙሉው አስተዳደራዊ ስርዓት ዘርግቶ አገልግሎት  አየተሠጠ ይገኛል። ‎ ‎ከውጊያ ኸመልካም አስተዳደር ጎን ለጎን ጭና ክፍለጦርን በርካታ የሥርዓቱ አገልጋይ  ሠራዊቶች ‎አየተቀላቀሉት የሚገኝ ሲሆን የአገዛዙን መዋቅር አያፈራረሠ በርካታ የአገዛዙ ወንበር አስጠባቂ ብአዴን አርምጃ  እየወሰደ አብዛኞቹን  ደግሞ የትግሉን አላማ በማስገንዘብ ትግሉን አየተቀላቀሉ ይገኛሉ። አርበኛ ዳንኤል አስረስ በርታ ጀግናው ወንድማችን🙏 ‎ ‌‎መረጃው: የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ሀይል ‎ሰሜን አማራ ቀጠና በላይ ዘለቀ እዝ ራስ አሞራው ውብነህ ፫ኛ ኮር የጭና ክፍለጦር ህዝብ ግንኙነት ክፍል አላፊው አርበኛ አዳነ ስጦታው ነው። ድል ለአማራ ፋኖ ‎ እኛ ከግንባር መረጃዎቻችን በሁሉም አማራ ተደራሽ እንሆን ዘንድ እየሰራን እንገኛለን የበኩሉዎን አስተዎፆ ያድርጉ ‼️ የቴሌግራም ቻናላችን ጆይን ሸር አድርጉ እንወያያለን እንማማራለን እንደራጃለን አብርን እናሸንፋለን አድራሻችን👇👇👇👇 https://t.me/httpsuYkZrGfSZrNjNjFk

ተቋሙ እየፈረሰ ነው ስንል በምክኒያት ነው ከድማ ብተና ተቋሙ ወደ አመራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል ምዕራብ አማራ ቴዎድሮስ ዕዝ ፩ኛ ክፍለጦር ባሕርዳር ብርጌድን ተቀላቅለዋል መስከረም 05/2018 ዓ.ም 1.
+2
ተቋሙ እየፈረሰ ነው ስንል በምክኒያት ነው ከድማ ብተና ተቋሙ ወደ አመራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል ምዕራብ አማራ ቴዎድሮስ ዕዝ ፩ኛ ክፍለጦር ባሕርዳር ብርጌድን ተቀላቅለዋል  መስከረም 05/2018 ዓ.ም 1.ማንደፍሮ ታድሎ 2. አብርሃም ተሾመ 3 ታየ ፈንቴ የተባሉ የአድማ ብተና አባላት ጭስ አባይ ሻለቃ እና በላይ ዘለቀ ተቀላቅለዋል። የአመራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል ምዕራብ አማራ ቴዎድሮስ ዕዝ ፩ኛ ክፍለጦር ህዝብ ግንኙነት ፋኖ ሐብታሙ የሱፍ መስከረም 05/2018 ዓ.ም እኛ ከግንባር መረጃዎቻችን በሁሉም አማራ ተደራሽ እንሆን ዘንድ እየሰራን እንገኛለን የበኩሉዎን አስተዎፆ ያድርጉ ‼️ የቴሌግራም ቻናላችን ጆይን ሸር አድርጉ እንወያያለን እንማማራለን እንደራጃለን አብርን እናሸንፋለን አድራሻችን👇👇👇👇 https://t.me/httpsuYkZrGfSZrNjNjFk

➾አብይ አህመድ ህዝቡን አስወጡትና በሰልፍ ይደግፈኝ የሚል ቀጭን ትዕዛዝ ለክልል ርዕሰ መስተዳድሮች አስተላለፈ‼ በዘፈቀደ ሃገሪቱን የሚመራው አብይ አህመድ  የክልል መስተዳደሮችን በአባይ ግድብ መፈጸምን በማወደስ ስለ አሰብ ወደብ እና ቀይ ባህር በአስቸኳይ ውይይት እንዲደረግ ትናንት ከቤተ-መንግስት ታዘዋል። ይህን ጉዳይም የህዝብ አጀንዳ ለማስመሰል ህዝቡ ሰልፍ እንዲወጣ ቀጭን ትዕዛዝ አስተላልፏል ። እኛ ከግንባር መረጃዎቻችን በሁሉም አማራ ተደራሽ እንሆን ዘንድ እየሰራን እንገኛለን የበኩሉዎን አስተዎፆ ያድርጉ ‼️ የቴሌግራም ቻናላችን ጆይን ሸር አድርጉ እንወያያለን እንማማራለን እንደራጃለን አብርን እናሸንፋለን አድራሻችን👇👇👇👇 https://t.me/httpsuYkZrGfSZrNjNjFk

ብርሀኑ ነጋ እና ብርሀኑ ጁላ የተባሉ የአብይ አህመድ ደንገጡሮች በአይን ጥቅሻ ተግባብተው የኢትዮጵያውያንን ብርሃን እያጨለሙ ነው ስንል በምክኒያት ነው።ብርሀኑ ነጋ ባልተመዘነ ፈተና ሳይመዝን የጣለው
ብርሀኑ ነጋ እና ብርሀኑ ጁላ የተባሉ የአብይ አህመድ ደንገጡሮች በአይን ጥቅሻ ተግባብተው የኢትዮጵያውያንን  ብርሃን እያጨለሙ ነው ስንል በምክኒያት ነው።ብርሀኑ ነጋ ባልተመዘነ ፈተና ሳይመዝን የጣለውን ተማሪ ብርሀኑ ጁላ ከትምህርት ቤት በግድ አፍሶ የተማሪ መለዮውን በመከላከያ መለዮ ለውጦ ወደ ጦርነት ሜዳ በመላክ የአብይ አህመድ ቅዠት ይሳካ ዘንድ ትውልዱ የራሱን ህልም ተነጥቆ ባጭር እንዲቀር ይደረጋል። አርበኛ ዳሞት አለኸኝ እኛ ከግንባር መረጃዎቻችን በሁሉም አማራ ተደራሽ እንሆን ዘንድ እየሰራን እንገኛለን የበኩሉዎን አስተዎፆ ያድርጉ ‼️ የቴሌግራም ቻናላችን ጆይን ሸር አድርጉ እንወያያለን እንማማራለን እንደራጃለን አብርን እናሸንፋለን አድራሻችን👇👇👇👇 https://t.me/httpsuYkZrGfSZrNjNjFk

የታሪካችን ማስጠላት። ይኸንን በታሪክ መጽሐፍ ደጉሰን ማስቀመጣችን አይቀርም። ግን እንዴት ተብሎ ነው ለልጅ ልጆቻችን ሊነራቸው የሚችለው? ለትውልዶቻችን የዐማራ ሕዝብ አስክሬን በጊንደር ታፍሶ በአንድ
የታሪካችን ማስጠላት። ይኸንን በታሪክ መጽሐፍ ደጉሰን ማስቀመጣችን አይቀርም። ግን እንዴት ተብሎ ነው ለልጅ ልጆቻችን ሊነራቸው የሚችለው?  ለትውልዶቻችን የዐማራ ሕዝብ አስክሬን  በጊንደር ታፍሶ በአንድ ጉድጓድ በጅምላ ተቀበረ ብለን ስንነግራቸው ኢትዮጵያን ጭራቅና ዘር አጥፊ ናት ብለው ይስሏታል። ግን ደግሞ ታሪክ ነው መጻፉ አይቀርም። ሰው አልባው አማራ እንደ አሸዋና ድንጋይ ታፍሶ ተቀበረ😥 በታሪክ የመጀመሪያ ሊሆንም ይችላል ይህ ሰው አልባ እንስሳት አቀባበር። "ሞጣ ቀራኒዎ ሞልቶ ካህናቱ እነ ራስ በዛብህ ሳይፈቱ ሞቱ" የሚለው ተረት ይሉት ታሪክ በዘመናችን ሲፈጸም አየን። ይህ ብቻ አይደለም። ገና ብዙ አማራዎች/አገዎች በጅምላ ተጨፍጭፈው በጅምላ ይቀበራሉ። ለመናገር ሆነ ታሪክ አድርጎ ለመጻፍ የቸገረ ነገር ቅስም ሰባሪ። መንግሥት ይህን አይቶ ሀገር እመራለሁ ብሎ እንዳያስብ። ይፈር። ለነገሩ ምን ያፍራልና። እሱ ወግ አጥባቂውን ሀገር ጠባቂውን ሕዝብ ካላጸዳ ብልጽግና አይመጣም የሚል ብሂል ይዟልና አያፍርም። ሳታስቡት በድንገት ለንስሓ ሳትበቁ በግፍ የተረሸናችሁ ወገኖቼ ነፍሳችሁን ይማር😥ረ ይህን ሀሉ ግፍና መከራ አይቶ ፈጣሪ ፋኖን ሰጠን ይክበር ይመሰገን አሁን። እኛ ከግንባር መረጃዎቻችን በሁሉም አማራ ተደራሽ እንሆን ዘንድ እየሰራን እንገኛለን የበኩሉዎን አስተዎፆ ያድርጉ ‼️ የቴሌግራም ቻናላችን ጆይን ሸር አድርጉ እንወያያለን እንማማራለን እንደራጃለን አብርን እናሸንፋለን አድራሻችን👇👇👇👇 https://t.me/httpsuYkZrGfSZrNjNjFk

የአማራ ህዝብ አምላክ ፈጣሪ በረዳንና በእኛም ብርታት መጠን ትልቅ ሥራ አስበን ለመጀመር ዛሬ  አንድ ሁለት ብለናል። ሚዛናዊ ሆነን ከእውነት ሳንሸሽ፣ ታሪክን በማስረጃና በመረጃ ጠርዘን፣ ወቅታዊና የዕለት ዜናዎችን ለአእምሯችን ምቹ እንዲሆኑ አድርገን፣ ከወሬ ባሻገር ዕውቀትና ለውጥ አግኝተን ለታላቋ ሀገራችን ታሪክ መሥራት እንድንችል የሚያግዙንን ዘገባዎች በምስል፣ በድምፅና በጽሑፍ ለማቅረብ ጉዞ ጀምረናል። ክቡራንና ክቡራት ለዕቅዳችን ስኬት ለሥራችን ጥራት እንደምትወዳጁን ተስፋ እያደረግን በቅድሚያምም እናመሰግናለን። እኛ ከግንባር መረጃዎቻችን በሁሉም አማራ ተደራሽ እንሆን ዘንድ እየሰራን እንገኛለን የበኩሉዎን አስተዎፆ ያድርጉ ‼️ የቴሌግራም ቻናላችን ጆይን ሸር አድርጉ እንወያያለን እንማማራለን እንደራጃለን አብርን እናሸንፋለን አድራሻችን👇👇👇👇 https://t.me/httpsuYkZrGfSZrNjNjFk

የአማራ ህዝብ አምላክ ፈጣሪ በረዳንና በእኛም ብርታት መጠን ትልቅ ሥራ አስበን ለመጀመር ዛሬ አንድ ሁለት ብለናል። ሚዛናዊ ሆነን ከእውነት ሳንሸሽ፣ ታሪክን በማስረጃና በመረጃ ጠርዘን፣ ወቅታዊና የዕለት ዜናዎችን ለአእምሯችን ምቹ እንዲሆኑ አድርገን፣ ከወሬ ባሻገር ዕውቀትና ለውጥ አግኝተን ለታላቋ ሀገራችን ታሪክ መሥራት እንድንችል የሚያግዙንን ዘገባዎች በምስል፣ በድምፅና በጽሑፍ ለማቅረብ ጉዞ ጀምረናል። ክቡራንና ክቡራት ለዕቅዳችን ስኬት ለሥራችን ጥራት እንደምትወዳጁን ተስፋ እያደረግን በቅድሚያምም እናመሰግናለን። እኛ ከግንባር መረጃዎቻችን በሁሉም አማራ ተደራሽ እንሆን ዘንድ እየሰራን እንገኛለን የበኩሉዎን አስተዎፆ ያድርጉ ‼️ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን ‼️ የቴሌግራም ቻናላችን ጆይን ሸር አድርጉ እንወያያለን እንማማራለን እንደራጃለን አብርን እናሸንፋለን አድራሻችን👇👇👇👇 https://t.me/httpsuYkZrGfSZrNjNjFk

የፋኖ መሰረታዊ ጥያቄ ብልጽግን ሪፎርም ለማድረግ ሳይሆን ከሥሩ ነቅሎ በመጣል የሚደረግ የአዲሱ ትውልድ  የሞት ሽረት ትግል እንጂ ትናንት ገዳይ አስገዳይ የነበሩ አሮጌ አኩፋዳን በጀርባው ላይ አዝሎ የሚጓዝ የትላንቱ አጋሰስ ሳይሆን በአዲስ አሰተሳሰብ የሚመረ አዲስ ትውልድ እንጂ ያረጀ ያፈጀ ጥርስ የለሌውን የትናንት የፌክ አንበሳ የሚጎተትበት ሰንሰለት ከገበያ ገዝቶ እውር በድንብሩ አይጎትታቸውም። ገዱ ይሁን ጅዋር ይሁን ለማ ወዘተ ጊዜ ያለፈባቸው የትላንት ወንጀለኞችና  የታሪክ አተላዎች መሆናቸውን  ክደው ዛሬ በጉሽ ጠላ ተሳክረው እኛም የትግሉ አካል ነን በማለት በተካኑበት የሀሰት ትርክት አንጎበር ታግዘው ከተፍ ማለታቸው የሚያስገርም አይሆንም። ያ ሆነ ይህ ይህ ትግል ላለፉት 34 ዓመታት ኢትዮጵያን በኋላ ቀር የጋርዮሽ የጎሳና የቋንቋ  እሳቤ ድምር ወጤት በሆነው የፍጥኝ ወደኋላ አሰሮ በህገመንግሥት አጽድቀው ሰጨፈጭፉ፣ ሲያስጨፈጭፉ፣ ሲያፈናቅሉ የነበሩ ታሪክ ይቅር የማይላቸውን የሰው በላ አምባገነን የካድሬዎች ሥርዓት መስራቾችና አራማጆች ፣ ብሔራዊ የደህንነት አማካሪ፣ የወጭ ጉዳይ ሚኒስትር፣ መከላከያ ሚኒስትር፣ ቄሮን አስተባብሮ ንጹሓን አማራን፣ የደቡብ፣ የትግራይ ወዘተርፈ ኢትዮጵያውያን ሞት፣ጭፍጨፋ፣ መፈናቀል፣ በአንዱ ወይም በሌላኛው ተባባሪ የነበሩ ማዕከላዊ ተዋያን የነበሩ የትላንት አክተሮች በምን ሂሳብ የዛሬው ትግል ባለቤት ሊሆኑ ይችላሉ?  ራሳቸው እያሽመነመኑት ሲደግፉትና ተልዕኮ ተቀብለው በህዝብ ላይ በደል እንዲፈጽሙ ሲያደርግ የነበረው መንግሥት እንድ ሸንኮራ መጥጦ ጥሏቸው ከጨወታ ወጭ  እንዲሆኑ አድርጓቸው ቀይ ካርድ መዞባቸው ያባረራቸው ቤት አልባ መሆናቸውን መገንዘብ ተስኗቸው አሁን ለዳግም ጥፋት ተፍ ተፍ ማለት ቦታ መያዝ እንደማይችል ቁስ የተንሳፈፉ አልቦ መሆናቸውን መገንዘብ አስፈላጊ ይሆናል!!! ዳዊት ተመስገን ከግንባር መረጃዎቻችን በሁሉም አማራ ተደራሽ እንሆን ዘንድ የበኩሉዎን አስተዎፆ ያድርጉ ‼️ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን ‼️ የቴሌግራም ቻናላችን ጆይን ሸር አድርጉ እንወያያለን እንማማራለን እንደራጃለን አብርን እናሸንፋለን አድራሻችን👇👇👇👇 https://t.me/httpsuYkZrGfSZrNjNjFk

ሶስት እግራ መቀሌ ባሕር ዳር ጮማ የምትቆርጠው፣ ወንበር አስጠባቂው የዙፋን ዘበኛው፣ እንዴት ነህ ልዑኩ እንዴት ነህ ወረኛው። ያገር ሽማግሌው ቄስና ኡስታዙ፣ ባህር ዳር መቀሌ ሁሌ ስትጓዙ፣ ሜክስኮ
ሶስት እግራ መቀሌ ባሕር ዳር ጮማ የምትቆርጠው፣ ወንበር አስጠባቂው የዙፋን ዘበኛው፣ እንዴት ነህ ልዑኩ እንዴት ነህ ወረኛው። ያገር ሽማግሌው ቄስና ኡስታዙ፣ ባህር ዳር መቀሌ ሁሌ ስትጓዙ፣ ሜክስኮ አራዳ አማራ መስቀያ፣ ዝዋይ ድሬደዋ የሰው መቀቀያ፣ ቂሊንጦ ቃሊቲ ከአባ ሳሙኤል፣ አልሸተተህ ወይ አማራው ሲቀቀል? እንዴት ነህ ልዑኩ አውርቶ አደሩ፣ ለዚያ ለጨፍጫፊው እርካቡ መንበሩ። ፈረስ ሆንከው አሉኝ ያሻው ይጋልብህ፣ ባሕር ዳር መቀሌ ጎንደር የሚጭንህ። ሶስት እግር ሆነህ ፣ ጉዞ እንዴት ተቻለህ። እንዴት ነህ ልዑኩ አንተ ሶስት እግራ፣ ቂሊንጦና ዝዋይ አትልም ወይ ጎራ። እኛ እስክንመጣ እስክንደርስላቸው፣ የሀሰት ወሬህን ምነው ነፈግካቸው። በእርግጥ ከአባይ ማዶ አረቂ ለምዳችህ፣ መቀሌ ስትሄዱም አንባሻ በልታችህ፣ ቂሊንጦና ዝዋይ ሰው ያለ አይመስላቹህ? ቂሊንጦና ዝዋይ አረቂ እያቀርቡ አንባሻ አይመግቡ፣ ጥፊ እና እርግጫ ነው ሁሌ እሚመገቡ። የአማራን ጭፍጨፋ መስማት የማትፈልግ፣ ከብልግናው ጋራ አብረህ የምትባልግ፣ ውይ ይቅርታ ተሳሳትኩ መሰለኝ፣ ብልጽግና ልል ስል ከብልግናው አልኩኝ። ይቅርታ አድርጉልኝ እንዳትቀየሙኝ፣ ከተማን የማላውቅ የገጠሩ ልጅ ነኝ፣ ፖለቲካ እማልችል ስርዓቱን ጠል ነኝ።       (ገጣሚ- ባለ ዳዊቱ) (አውሎግሶን አንድነት-Awulogson Andinet ፣ መስከረም 4/2018 ፣ አዲስ አበባ- ኢትዮጵያ) ከግንባር መረጃዎቻችን በሁሉም አማራ ተደራሽ እንሆን ዘንድ የበኩሉዎን አስተዎፆ ያድርጉ ‼️ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን ‼️ የቴሌግራም ቻናላችን ጆይን ሸር አድርጉ እንወያያለን እንማማራለን እንደራጃለን አብርን እናሸንፋለን አድራሻችን👇👇👇👇 https://t.me/httpsuYkZrGfSZrNjNjFk

የአማራ ፋኖ ብሄራዊ ኃይል የምዕራብ አማራ ቀጠና የቴዎድሮስ ዕዝ የጎጃም አገዉ ምድር ክ/ጦር ሰብሳቢ ንስሩ አርበኛ ዘመን ተሻለ ‼️ ፅናት፣ቁርጠኝነት፣ጀግንነት፣የመሪነት ጥበብ ሁሉን አሟልቶ የሰጠዉ
+2
የአማራ ፋኖ ብሄራዊ ኃይል የምዕራብ አማራ ቀጠና የቴዎድሮስ ዕዝ የጎጃም አገዉ ምድር ክ/ጦር ሰብሳቢ ንስሩ አርበኛ ዘመን ተሻለ ‼️ ፅናት፣ቁርጠኝነት፣ጀግንነት፣የመሪነት ጥበብ ሁሉን አሟልቶ የሰጠዉ እንቁ መሪ‼️ ከግንባር መረጃዎቻችን በሁሉም አማራ ተደራሽ እንሆን ዘንድ የበኩሉዎን አስተዎፆ ያድርጉ ‼️ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን ‼️ የቴሌግራም ቻናላችን ጆይን ሸር አድርጉ እንወያያለን እንማማራለን እንደራጃለን አብርን እናሸንፋለን አድራሻችን👇👇👇👇 https://t.me/httpsuYkZrGfSZrNjNjFk

አዲሱ ትውልድ... ራሱን ከውስጣዊ የህልወና አደጋ ካመጡት አካላት እና ባህርይ የጸዳው ትውልድ ነው ‼️ - (በኮሜንት የቀረበ ጥያቄን መነሻ አድርጎ የተለጠፈ😊) አዲስ ትውልድ የሚለው አግላይ ነው የሚል ሀሳብ ይነሳል። መልሱ አዎ ያገላል ነው። ሆኖም አለማው  ከማግለል አስቀድሞ አዲስነትን ማስረገጥ እና ማስረጽ ነው። የሚገለለው ማን ነው ከተባለ ፦ የከሰረው፣ ከጎሰቀለው (corrupted) ፣ በአስተሳሰብ ኋላኛው ላይ ተቸንክሮ ዘመኑን ካልዋጀው ፣ ተላላኪነት እና ተለጣፊነት መገለጫው ከሆነው፣ የአስተሳሰብ ጥገኝነት ካለበት፣ ምሁራዊ አድርባይነት ከተጠናወተው፣ ከእውቀት አክፍሎተኛው፣ .... ይህ አይነቱ የፖለቲካ መደብ በትግሉ ውስጥ ዕድል ፈንታ የለውም። ትግሉ "የአዲሱ ትውልድ" ነው። በሀገር ውስጥ ካሉት ሌሎች የፖለቲካ ቡድኖች ውስጥም ሆነ በሌላው አለም፣ የፖለቲካ career expiration አለው። የእኛ ትግል ጉበኞች (watchdog's) ስላልነበሩት እና በደንብ ኦዲት ስለማይደረግ "የከሰረው" ሁሉ ተስቦ መጥቶ ከሞት የሚነሳበት፣ ውስጥ ያለውም ደግሞ ስም እና ግብር እየቀያየረ የሚሸቅጥበት መሆኑ አብቅቷል። ትግሉም ሆነ የፖለቲካ ምህዳሩ ከየት እስከ የት ተብሎ የተሰመረ እና ባለቤት ያለው በመሆኑ እንዲሁ መግባት እና መውጣት የለም። አይኖርምም። . . የአማራ ትግል የትውልዶች ጦርነትን የማሸነፍ ነው። ይህን አረፍተነገር በዚህ ልጥፍ አላብራራም። ነገር ግን በዚህ ሀሳብ መነሻነት የአማራን ጦርነት ውስጣዊ እና ውጫዊ ገጽታ መጥቀስ ግን ይገባል። የአማራ ህልውና ጦርነት አንደኛው አካል ከውጭ ወደ ውስጥ የሚነሳ ነው። ጦርነቱ በአካል በዚህ ዘመን የህልውናችን ዋነኛ ተላብሶ የሆነው አረመኔን የአብይ ብልጽግና ደመኛ ጠላትነት የመነጨ ነው። ሆኖም የዘመኑ ጦርነት ደጋግመን እንደምንለው የራሱ ታሪካዊ መነሻ ያለው የአማራን ሁለንተናዊ ራስ በቅነት የሚገዳደሩ አካላት በተለያዬ ዘመን የጋረጡበት አደጋ የቀጠለ እና ህልውናን ጨርሶ ወደ ማጥፋት የደረሰበት ነው። የአደጋው ሁለተኛ ገጽታ ውስጣዊ ነው። ዋነኛ ውስጣዊ የህልውና አደጋ ባለቤቶች ከአመለካከት እና ባህሪ አንጻር  በዋናነት ፦ 1) ራስ ጠል ሀሳብ፣ ዕሳቤ እና ባህል 2) የፖሊቲው ድብታ እና ራስን ማግለል 3) ከፋፋይነት እና አቆርቋዥነት 4) ጥገኝነት 5) ያልተደራጀ እና የማይተመማን ፖለቲካዊ ማህበረሰብ 6) በጠላት ፍላጎት ልክ የተቀረጹ ኤሊቶች የስልጣን ወንበር ይዘው፣ አማራን እንዳይደራጅ መከልከል/መከላከል 7) መጥፎ/ደካማ ኤሊት ( corrupted elite ) እነዚህ ውስጣዊ ችግሮች የህልውና አደጋ ምክንያት ከመሆን ባሻገር ከውጭ የመጣብንን ጥቃት ለመከላከልም እንዳንችል አድርገውን ለዛሬው አደጋ ተጋላጭ ሆነናል። አሁንም የህልውና ትግሉ ውስጥ በተለያዩ መልኩ የሚገለጡ ሆነው ይታያሉ። አብዮታችን እነዚህን ውስጣዊ የህልውና አደጋዎች በየምዕራፉ፣ በየአጋጣሚው እና በየደረጃው ሊያጸዳ ይገባል። 👉 አዲስ ትውልድ ስንል ራሱን ከውስጣዊ የህልውና አደጋ ማጽዳት የመጀመሪያው ክፍል ሲሆን ቀጣዩ እና ዋነኛው ስራ በአማራነት የጸና መሠረት ላይ የቆመ ትወልድ መሆንን ይመለከታል። አዲሱ ትውልድ በብሔራዊ ንቃት እና ቁጭት፣ በፍጹም ራስ በቅነት የሚመራ ሀይል ነው። አማራነትን የሚወድ፣ በብሔራዊ ንቃት እና ቁጭት ድብታን እና ትኙነትን ያሸነፈ፣ ጸረ ራስ የሆነውን አቆርቋዥ ከፋፋይነት እንዲሁም ጥገኝነት በአማራነት ያሸነፈ፣ ሁሌም በልህቀት እያደገ የሚሄድ የጸና አደረጃጀትን የሚሻ እና የመጥፎ ልሂቃን የጎሰቀለ የፖለቲካ ባህል ውርስ በቅንነት ያሸነፈ እና የሚያሸንፍ ትውልዱ ነው። አዲሱ ትውልድ እንዲህ ያለ ነው። አዲስነት ከአሮጌነት ካልተፈታ እና ካልተፋታ ጉዞው አድካሚ ነው! የብልሽት እና የንቅዝ ውርስ የሆነ ሀሳብ ጀምሮ በተለያየ መልኩ የሚገለጽ ባህል እና ድርጊት በአማራነት አብዮት ሊጸዳ ይገባል። ባንዳን ብቻ ሳይሆን ባንዳዊ አስተሳሰብን፣ ልማድን፣ የዚያ ውርስ ዝንባሌን በጥቅሉ ጸረ-ራስነት ከመላው የአማራ ተዋስኦ፣ የፖለቲካ መድረክ እና አደረጃጀት ሊጸዳ ይገባል። ይህ አዲስነት ነው። ይህ ውስጣዊ የህልውና አደጋ አምጪ ተዋሲያንን ማስወገድ ነው። ይህ የህልውና ጦርነቱ አካል ነው። አዲሱን ትውልድ ከአሮጌ ሀሳብ፣ ስሌትም፣ ባህል እና አሳለለፍ ጋር ፈንታ የለውም። እናም ታጋየም ሆነ ደጋፊው ውስጡን በዚህ አብዮታዊ የብሔርተኝነት ሀሳብ ያርም፣ ራሱን ያርቅ (ማረቅ-አውቆ መታረም)። በተለይ ተነቃዩ ( ከፊሉ ዲያስፖራ እና በራስ ጠልነት የተጠመቀው የሀገሬው አማራ ) ከታወረ ራስ ወይም ከራስ እውርታ  (the self as a blind spot) ወጥቶ ራሱን ሊፈትን፣ ሊሰልል እና አውቆ በአብዮታዊ መንገድ ከራሱ ጋር ሊተዋወቅ እና ፖለቲካዊ ጉስቁልና ካደበተው ባህል ነጻ ሊወጣ ይገባል። 👉 የወቅቱ የአማራ ትግል ከተለያየ የፖለቲካ መስመር እና የፖለቲካ አሰላለፍ ታሪክ የመጡ ሀይሎች በደጋፊነት አንዳንዴም በታጋይነት ይገኙበታል። ይህ ሀቅ ሆኖ ሳለ ለትግሉ የመስመር ጥራት ሲባል ዝብርቅርቁ መጥራት አለበት፤ ይጠራልም። በተለይ ደጋፊው ሀይል ሚናውን በልኩ ከመመዘን ባሻገር በቀደመ የፖለቲካ አሰላለፉ እና ታሪኩ ምክንያት ትግሉ ላይ ሊመጣ የሚችልን ችግር አውቆ ከወዲሁ ራሱን ማረም ይጠበቅበታል። እኛም ደጋግመን ማሳሰቡን እንቀጥልበታለን። ለማገዝ የሚመጣን አካል መቀበል ተገቢ ነው። ሆኖም ማገዝን ተከትሎ የሚመጣን መበረዝ ግን መታገል አለብን። እንታገላለን። 👉 ፖለቲካችን ከሀቀኛ የራስ ወይም የውስጥ ትንተና'ና እና ግንዛቤ መነሳት የአዲሱ አስተሳሰብ መሠረት ነው። ሆኖም ከዚህ በተቃራኒ የችግር ሁኔታን በማለባበስ ወይም በማስተናነስ እና ያልተፈተነ ራስን ይዞ ለመፍትሄ መቅረብ ተደራራቢ ሸክም ሆኖብናል። የህልውናችን ውስጣዊ አደጋ የሆነው መጥፎ ልሂቅ ዛሬም ለህልውና በምናደርገው ትግል ውስጥም ተከትሎ የትግላችን ውስጣዊ የህልውና አደጋ ሆኖ እንዳይቀጥል መታገል የአዲሱ ትውልድ የአዲስነት ግዴታ ነው። አዲስነት የዕድሜ አይደለም፤ አዲስነት የመስመር ነው። ሆኖም በነባሩ የአማራ ትግል ውስጥ ጥቂት የማይባለው የከረመ ልምድ ያለው አካል በአንድም ሆነ በሌላ መልኩ ባልጠራ ሲያልፍም በተበላሸ መስመር የከረመ መሆኑ ግልጽ ነው። መፍትሄው ከላይ በተጠቀሰው መልኩ ራስን ማረቅ እና ለመታረም በቅንነት መዘጋጀት ነው። አብዮታዊ እርማት መውሰድ ለትውልዱ አዲስ አስተሳሰብ ስምረት ብሎም የአዲስ ተስፋው ማህተም ለሆነው አሸናፊነት ወሳኝ ነው። ህልውናችን በክንዳችን! ክፋት ለማንም በጎነት ለሁሉም! አማራነት ያሸንፋል! እስከ ምጽአት አማራ! አዲስ ትውልድ አዲስ አስተሳሰብ አዲስ ተስፋ! እስቲበል ዓለሙ ከግንባር መረጃዎቻችን በሁሉም አማራ ተደራሽ እንሆን ዘንድ የበኩሉዎን አስተዎፆ ያድርጉ ‼️ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን ‼️ የቴሌግራም ቻናላችን ጆይን ሸር አድርጉ እንወያያለን እንማማራለን እንደራጃለን አብርን እናሸንፋለን አድራሻችን👇👇👇👇 https://t.me/httpsuYkZrGfSZrNjNjFk

ፍኖተ-አማራ ሚዲያ (Finote Amhara Media) - Статистика и аналитика Telegram-канала @mezmure122124