ru
Feedback
ፍኖተ- አማራ ሚዲያ (Finote- Amhara ) Midea

ፍኖተ- አማራ ሚዲያ (Finote- Amhara ) Midea

Открыть в Telegram

የተመሠረተው የአማራን ሕዝብ ለማንቃት፣ ለማደራጀት እና ለማስተባበር ነው። የአማራ ሕዝብን ✅ ፖለቲካዊ ✅ ማህበራዊ ✅ ኢኮኖሚያዊ ታሪካዊ ጥያቄዎችን ለማሰማት እና የአማራን ሕዝብ በማንቃት ሰፊውን ሕዝብ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ይሰራል። ወደዱም ጠሉም የኃላ ታሪካችን በእኛ እጅ ይፃፋል። አማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ ( አፋብን)

Больше
3 589
Подписчики
+524 часа
+5667 дней
+97730 дней
Архив постов
ሰበር የአደረጃጀት ዜና ቀን 12/07/2018 🌿🌿🌿🌿=====🌿🌿🌿🌿 አፋብን ጎንደር ጠቅላይ ግዛት ዕዝ 204ኛ አስቻለው ደሴ ኮር ግዙፉ እትጌ ጣይቱ ክፍለ ጦር አደረጃጀት ሪፎርም  ሰርቷል። 🌿🌿🌿🌿====🌿🌿🌿🌿   የአማራነት መሰረት ለአማራነት መታመን ገብርየነት ከትግል ፊደላቸው አርበኛ አስቻለው ደሴ በመቀበል በኃላም በታማኙ አስተዋዩ እና የጽናት ተምሳሌቱ አርበኛ ተሾመ ስትመራ የቆየችው እትጌ ጣይቱ ክፍለ ጦር የመሪነት ችቦውን  በአማራነት ስነልቦና ተቀርጸው ላደጉት ወጣት ታጋዮች ; አታጋዮች እና መሪወች ዛሬ የጎንደር ጠቅላይ ግዛት ዕዝ  ዘመቻ መሪ እና የ204ኛ አስቻለው ደሴ ኮር ዋና አዛዥ አርበኛ ተሾመ አበባው በተገኙበት ሪፎርም አድርገናል። ➊ ዋና ወታደራዊ አዛዥ------  አርበኛ መልካም አበባው ➋ ምክትል ወታደራዊ አዛዥ---- አርበኛ አዛናው ታረቀኝ ➌ ፅ/ቤት -------መ/አለቃ ገዳም ካሳ ➍ ዘመቻ ኃላፊ ---------- አርበኛ ድግሴ አብራራው ➎ ም/ዘመቻ----------- አርበኛ ደስየ ገብሩ ➏ መረጃና ደህንነት ኃላፊ----------##### ➐ ወታደራዊ ምልመላና ስልጠና ኃላፊ ------አርበኛ አሽናፊ አበራ ➑ ምክትል  ምልመላና ስልጠና -----አርበኛ አብዩ ካሳው ➒  ወታደራዊ እቅድና ስትራቴጂ ኃላፊ----- አርበኛ አዲሴ ከበደ ❿አደረጃጀት ዘርፍ ኅላፊ -----------አርበኛ አረጋ ደሴ  ⓫ የሰው ሀይል ------- አርበኛ እርቂሁን አበራ ⓬ ፋይናንስና ንብረት ኃላፊ ----አርበኛ ቄሴ ስንታየሁ አደባባይ ⓭ ገንዘብ ያዥ ------- አርበኛ ክብሬ ጥጋብ ⓮ ፍይናንስ ፀሀፊ -----አርበኛ ሰፊው ደስታው ⓯  ፖለቲካ ዘርፍ ኃላፊ ----አርበኛ ቴዎድሮስ መስፍን ⓰ ም/ፓለቲካ ዘርፍ -----አርበኛ መልኬ ገነቱ ⓱ ሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ----አርበኝ ሙሉየ ደሴ ⓲ ሕዝብ አስተዳደር ኃላፊ------አርበኛ ሳለአምላክ እሽቴ ⓳ ቀጠናዊ ትስስር -----------አርበኛ አንጋው ሹመት ⓴ ህግ ጉዳይ   ኃላፊ----------አርበኛ አገኝ እጂጉ ➋➊  ዳንኤል አዲስ  ------------- ወታደራዊ አስተዳደር ሆኖ  ተደራጂቷ፡፡ ድል ለአማራ ፋኖ!!! ድል ለአማራ ህዝብ!!! አፋብን ጎንደር ጠቅላይ ግዛት ዕዝ 204ኛ አስቻለው ደሴ ኮር ህዝብ ግንኙነት ክፍል!

ሰበር ዜና! በአማራ ሕዝብ ላይ ለታቀደው የምርጫ ድራማ ተባባሪ በሚሆኑ አካላት ላይ እርምጃ እንደሚወሰድ የ206ኛ ኮር 14ኛ ክፍለ ጦር አስጠነቀቀ! የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ (አፋብን) የ206ኛ
ሰበር ዜና! በአማራ ሕዝብ ላይ ለታቀደው የምርጫ ድራማ ተባባሪ በሚሆኑ አካላት ላይ እርምጃ እንደሚወሰድ የ206ኛ ኮር 14ኛ ክፍለ ጦር አስጠነቀቀ! የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ (አፋብን) የ206ኛ ኮር 14ኛ ክፍለ ጦር፤ ፋሽስታዊው የብልፅግና ሥርዓት የአማራን ሕዝብ ለማጥፋት የጀመረውን እኩይ ሴራ "ምርጫ" በሚል ሽፋን ዕድሜውን ለማራዘም እያደረገ ያለውን እንቅስቃሴ በጽኑ እንደሚቃወም ክፍለጦሩ በዛሬው ዕለት ባወጣው መግለጫ ገልጿል። አገዛዙ ይህንን የማጭበርበሪያ ካርድ በመጠቀም ለሚቀጥሉት አምስት ዓመታት የአማራን ሕዝብ ለመጨፍጨፍ የሚያስችለውን ሕጋዊ ከለላ ለማግኘት ደብረ ማርቆስ እና ደብረ ኤልያስ ከተሞች ውስጥ ሆድ አደር ግለሰቦችን፣ የመንግሥት ሠራተኞችን እና ወጣቶችን በመሰብሰብ ስልጠና እየሰጠ መሆኑን ክፍለ ጦሩ እንደደረሰበት አስታውቋል። በመሆኑም ክፍለ ጦሩ የሚከተሉትን ጥብቅ መመሪያዎች አስተላልፏል፦ 1. በምርጫ ስም የሚደረገውን የሥርዓቱን ዕድሜ የማራዘም ድራማ ለማስፈጸም የምትሳተፉ መምህራን፣ የመንግሥት ሠራተኞች እና ወጣቶች ከድርጊታችሁ በአስቸኳይ እንድትቆጠቡ እናሳስባለን። 2. ይህንን መመሪያ ተላልፎ ለገዳዩ የብልፅግና ሥርዓት ሎሌ በመሆን በምርጫው ሂደት ውስጥ በሚሳተፍ ማንኛውም አካል ላይ ክፍለጦሩ የማያዳግም እርምጃ የሚወስድ መሆኑን በጥብቅ ያሳውቃል። 3. በማስጠንቀቂያው መሰረት ካልተገቡ እና በሂደቱ በመሳተፋቸው ምክንያት ለሚደርስባቸው ማንኛውም ዓይነት ጥቃት ተሳታፊዎቹ ራሳቸው ኃላፊነቱን እንደሚወስዱ ክፍለ ጦሩ ያስገነዝባል። በምርጫም ሆነ በሰላማዊ የፖለቲካ ትግል የሚመጣ የአማራ ነፃነት እንደሌለ የታወቀ በመሆኑ፣ መላው ሕዝባችን ከጥፋት ኃይሎች ጎን በመቆም የታሪክ ተወቃሽ እንዳይሆን ጥሪ ቀርቧል።

ሰበር ዜና! ስምንት የአገዛዙ የፀጥታ ኃይል አባላት የሰሜን አማራ ቀጠና በላይ ዘለቀ ዕዝን ተቀላቀሉ! የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ (አፋብን) የሰሜን አማራ ቀጠና በላይ ዘለቀ ዕዝ፣ ሜጀር ጄኔራል ውባንተ አባተ 1ኛ ኮር ስር የሚገኘውን የጉና ክፍለ ጦርን ስምንት የአገዛዙ የፀጥታ ኃይል አባላት መቀላቀላቸው ታወቀ። ዛሬ መጋቢት 12 ቀን 2018 ዓ.ም ወደ ህዝባዊው ትግል የተቀላቀሉት እነዚህ አባላት፤ "የአገዛዙን ዕድሜ ለማራዘሚያ አንሆንም" በሚል ውሳኔ ከአንዳቤት ብርጌድ ጋር መገናኘታቸው ተገልጿል። የጉና ክፍለ ጦር የህዝብ ግንኙነት ክፍል፣ የአንዳቤት ብርጌድ አመራሮች እና የወረዳው የፋኖ ጊዜያዊ መንግስት አመራሮች በተገኙበት ለአባላቱ አቀባበል ተደርጎላቸዋል። ወደ ፋኖ የተቀላቀሉት አባላት ዝርዝር እንደሚከተለው ቀርቧል፦ 1. ተረፈ አበበ ስዩም ➙ (አድማ ብተና) 2. ዋሴሁን ሀብታሙ ጣሰው ➙ (መከላከያ) 3. ምትኩ ሙላት ቸኮል ➙ (መከላከያ) 4. ፈንታሁን ጌጤ አንዱዓለም ➙ (መከላከያ) 5. ልብሞኝ የኔሰው እንግዳ ➙ (መከላከያ) 6. ሀብታም አሽቴ ታየ ➙ (መከላከያ) 7. አቡቧል እሱባለሁ አሰፋ ➙ (መከላከያ) 8. መንግስት አብራረው እጅጉ ➙ (ሚሊሻ) አዲሶቹ ተቀላቃዮች አስፈላጊውን ፎርም ሞልተው የትግሉ አካል እንዲሆኑ የተደረገ ሲሆን፣ በቆይታቸውም ሰፊ የፖለቲካ ግንዛቤ ማስጨበጫ ትምህርት እንደተሰጣቸው የዕዙ የህዝብ ግንኙነት ክፍል ገልጿል። የጉና ክፍለ ጦር የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ ፋኖ መምህር ያሬድ ገደፋው፤ የአገዛዙ ሰራዊት መፍረክረክ በቀጠለበት በዚህ ወቅት፣ ሌሎች የሰራዊቱ አባላትም የህዝባቸውን ጥሪ በመቀበል ወደ ወገን ኃይል እንዲቀላቀሉ ጥሪ አቅርበዋል።

አፋብን በላይ ዕዝ 4ኛ ደጃዝማች ኮር አርበኞች ክፋለ ጦር አለም አቀፍ ስታንዳርድ መሰረት አድርጎ መልሶ የማደራጀት ስራ ተሰርቶ ተጠናቀቀ። ከፋተኛ የድርጅት እና የዕዝ አመራሮች ይህን አደረጃጀት ያዋ
+5
አፋብን በላይ ዕዝ 4ኛ ደጃዝማች ኮር አርበኞች ክፋለ ጦር አለም አቀፍ ስታንዳርድ መሰረት አድርጎ መልሶ የማደራጀት ስራ ተሰርቶ ተጠናቀቀ።      ከፋተኛ የድርጅት እና የዕዝ አመራሮች ይህን አደረጃጀት  ያዋቀሩ ሲሆን አጫጭር  ወታደራዊ ኣና የሰራዊቱን ፓለቲካዊ ጤንነት ሊጠብቅ በሚችሉ  አግባብ ስልጠና ተሰጥቷል።  አደረጃጀቱን እና ስልጠናዉን በበላይነት የመሩት ከፈተኛ አመራሮች:- 1ኛ/  አርበኛ ሳሙኤል ባለዕድል ____  የአፋብን ስልጠና መምሪያ ኃላፊ አስተባባሪ 2ኛ/  አርበኛ ስጦታዉ መልኬ ___  የበላይ ዕዝ ም/ሎጆስቲክ መምሪያ ኃላፊ አባል 3ኛ/ አርበኛ ወዳጅ አለሙ ___  የበላይ ዕዝ ም/መካናይዝድ መምሪያ ኃላፊ አባል 4ኛ/ አርበኛ ቢኒያም አለምነዉ ___  የበላይ ዐዝ ም/ፋይናስ መምሪያ ኃላፊ አባል 5ኛ/አርበኛ ጌጡ ድረስ ___ የበላይ ዕዝ ም/ዕቅድ መምሪያ ኃላፊ አባል   በነዚህ ልምዱ ባላቸዉ ከፍተኛ አመራሮች የአደረጃጀት ስልጠና ተሰጥቶ ተጠናቋል።

አፋብን ያስተላለፈውን የምሕረት አዋጅ ተቀብለው ሁለት የአድማ ብተና አባላት የ206ኛ ኮር 14ኛ ክፍለ ጦርን ተቀላቅለዋል‼️ መጋቢት 12/2018 ዓ.ም የኦሕዴድ መራሹን የብልጽግና ጨፍጫፊ ቡድን የው
አፋብን ያስተላለፈውን የምሕረት አዋጅ ተቀብለው ሁለት የአድማ ብተና አባላት የ206ኛ ኮር 14ኛ ክፍለ ጦርን ተቀላቅለዋል‼️ መጋቢት 12/2018 ዓ.ም የኦሕዴድ መራሹን የብልጽግና ጨፍጫፊ ቡድን የውሸት መደለያ ተቀብለው የገዛ ሕዝባቸውን በመጨፍጨፍ ተግባር ተሰማርተው የነበሩ እሸት ጌታቸውና ወንድምነህ ንጉስ የተባሉ ሁለት የአድማ ብተና ቲም መሪዎች የአፋብን ቴዎድሮስ ዕዝ 206ኛ ኮር 14ኛ ክፍለ ጦር የበረኸኛው ጅበላ ሙተራ ሻለቃን ተቀላቅለዋል። ድል ለአማራ ፋኖ! የ206ኛ ኮር 14ኛ ክፍለ ጦር ሕዝብ ግንኙነት ክፍል 12/ዐ7/2018 ዓ.ም

#የክብር_እና_የድል_የእንኳን_ደህና_መጣችሁ_መልዕክት‼️ ​ክቡራን የንጉሥ ተክለሃይማኖት ሻለቃ የቁርጥ ቀን ልጆች፤ ​በመጀመሪያ፣ የጀግንነት ታሪክ ጽፋችሁ፣ ከሻለቃችሁ ዋና መቀመጫ ደብረዘይኑ እስከ 105ኛ ኮር ቀጠና ጃዊ መተከል ድረስ ያለውን እልህ አስጨራሽ ውጣ ውረድ በፅናት አልፋችሁ፣ ለቀጣዩ የነፃነት ጉዟችን ወሳኝ የሆነውን የሎጂስቲክስና የትጥቅ አቅርቦት በድል ይዛችሁ የተመለሳችሁት ጀግኖች በሙሉ፡- እንኳን ደህና መጣችሁ! ​ከጥር 30 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ እስከ መጋቢት 11 ቀን 2018 ዓ.ም ድረስ የነበረው ጉዟችሁ ተራ የውጊያ ግዳጅ ብቻ አልነበረም፤ የጽናት፣ የፍቅርና ለዓላማ የመኖር ትልቅ ማሳያ እንጂ። እናንተ የሄዳችሁበት መንገድ ተራ ተራራን መውጣትና መውረድ ብቻም አልነበረም፤ የጠላትን ምሽግ በጥበብ ማለፍ፣ የተፈጥሮን ፈተና በቆራጥነት መቋቋም እና "ለዓላማዬ እሞታለሁ" የሚል የጥቁር አንበሳ ልብን ለዓለም ያሳያችሁበት ጉዞ ነበር።"አንበሳ መንገድ አይመርጥም" የሚለውን የጀግንነት ብሂልም በተግባር አሳይታችኋል። ይህ ድል የሻለቃችሁን ብርታት ብቻ ሳይሆን፣ የቴዎድሮስ ዕዝን የማይበገር ኃይል ለዓለም ያስመሰከረ ነው። ጠላትን አፈር ድሜ ለማብላት የሚያስችለውን ትጥቅ በደማችሁና በላባችሁ አሳክታችሁ በመመለሳችሁ መላው ሕዝባችንና ድርጅታችን  ይኮራባችኋል። ​በዚህ ታላቅ ግዳጅ ወቅት፣ ውድ የትግል ጓዳችን አብርሃም በልስቲ መስዋዕትነትን ከፍሏል። አብርሃም የወደቀው ጉዟችን እንዲቀጥል፣ ትጥቃችን እንዲሟላ እና ሕዝባችን ነፃ እንዲወጣ ነው። ጀግና አይሞትም፣ ይተካል እንጂ! አብርሃም ደሙ የነፃነት ፋና ሆኖ ይበራል፤ ስሙም በነፃነት የታሪክ መዝገብ ላይ በወርቅ ቀለም ይጻፋል፤ በልባችንም ሁሌም ሕያው ሆኖ ይኖራል። ለእሱ የምንሰጠው ትልቁ ክብር፣ የጀመረውን የነፃነት ትግል ዳር በማድረስ ይሆናል። ለቤተሰቦቹና ለጓዶቹ መጽናናትን እየተመኘን ጀግንነቱን በክብር እናስባለን። ​ እናንት ጀግኖቻችን፤ ​እናንተ ዛሬ ይዛችሁት የተመለሳችሁት እንዲህ እንደሚታየው ተተኳሽ ብቻ አይደለም፤ የነገው ድላችን ዋስትና፣ የጠላቶቻችን የራስ ምታት እና የአማራ ሕዝብ የህልውና ጋሻ ነው። ከጃዊ መተከል እስከ ደብረ ማርቆስ  ድረስ የረገጣችሁት መሬት ሁሉ የጽናታችሁ ምስክር ነው። ፈታኙን ግዳጅ በአግባቡ በመወጣት፣ የጠላትን ምሽግ በመበታተንና የገባችሁትን ቃል በማክበር ወደ መነሻ ካምፓችሁ በሰላም ስለተመለሳችሁ እንኳን ደስ አላችሁ! እናንተ የሕዝብ መከታ፣የሕዝብ ጋሻ፣ የፍትህ ጮራ፣  የታሪክ ባለአደራዎች ናችሁ።  በቆራጥነት ሄዳችሁ በድል መመለሳችሁ ለጠላት ድንጋጤን፣ ለሕዝባችሁ ደግሞ ተስፋን ሰጥታችኋል። ከጃዊ እስከ ደብረ ዘይት የፈሰሰው ላባችሁና የታየው ጀግንነታችሁ ሁሌም ሲወሳ ይኖራል። ​"የጀግና መንገድ እሾህ ቢበዛውም፣ መጨረሻው ግን የክብር ታሪክ ነው።" ​በድጋሚ፣ እንኳን ደስ አላችሁ‼️ እንኳን ደህና መጣችሁ‼️ እግዚአብሔር አምላካችን ለጓዳችን አብርሃም በረከተ ሰማዕታትን ያድልልን ‼️ ነፍሱን በአፀደ ገነት ያኑርልን‼️ ​ድል ለፍትህ ፈላጊው የአማራ ሕዝብ! ክብር ለተሰውት ጀግኖቻችን!

🔴የማስጠንቀቂያ መልዕክት ለሚመለከተው ሁሉ! እንደሚታወቀው ፋሽስታዊው የብልጽግና ሥርዓት መንበረ ሥልጣኑን ከተቆናጠጠበት ጊዜ ጀምሮ ሥልጣኑን ለረከሰና ለግል ዓላማ ማስፈጸሚያ በማድረግ የተከበረውንና ሀገር ሰሪ የሆነውን የአማራን ሕዝብ ለማጥፋትና ስም አጠራሩን ከታሪክ መዝገብ ላይ ለመፋቅ እየተጠቀመበት ይገኛል። በዚህ እኩይ ተግባሩም የተከበረውን የሕዝብ ሥልጣን ለራሱ ለሕዝቡ መጥፊያ በማድረግ በዓለማችን ቀዳሚው ሥርዓት ሳያደርገው አይቀርም። በዚህ ሰይጣናዊ ተግባሩ ክፉኛ ካማረረው ዘንድ ከብዙኃን ኢትዮጵያውያን ዜጎች ልቡና ውስጥ የተተፋው ይህ ሥርዓት "ምርጫ" በሚል የማጭበርበሪያ ካርድ በድጋሚ የሥልጣን ዘመኑን በማራዘም ወገቡን ታጥቆ ለያዘው አማራን በጅምላ የመፍጀት ተግባር ሕጋዊ ከለላና እውቅና ለማግኘት ከላይ ታች እያለ መሆኑን እየተመለከነው ነው። ይህ ርካሽ ተግባሩ መሬት ድረስ ወርዶ ተግባራዊነቱ ይረጋገጥ ዘንድ ደግሞ "ክብራቸውን በነውራቸው ሆዳቸው አምላካቸው" የሆኑ ሁሉን ነገር በገንዘብ ማያ የሚያዩ ሆድ አደር አማራዎች የትወናውን ስራ ለመስራት በእጅጉ እየተዘጋጁ መሆኑን ሰምተን ታዝበናል። ለአብነት ያህልም በደብረ ማርቆስና ደብረ ኤልያስ ከተሞች ውስጥ የተወሸቀው ሆዳም የብልጽግና ስብስብ መምሕራንን፣የመንግስት ሰራተኞችን፣ ወጣቶችንና አስቀድሞ በጥቃቅንና አነስተኛ ያደራጃቸውን ወጣቶች በመሰብሰብ የምርጫ ሂደቱን ያስፈጽሙለት ዘንድ ስልጠና እየሰጠ መሆኑን ደርሰንበታል። ይህ ተግባርም አገዛዙ የአማራን ለመጨፍጨፍ ተጨማሪ አምስት ዓመት እንዲኖረው የሚያስችለውን ሕጋዊ ማረጋገጫ ለመያዝ የሚያደርገው ሩጫ መሆኑን ልብ ይሏል። በመሆኑም አሁን ላይ በምርጫም ሆነ በሰላማዊ የፖለቲካ ትግል የሚመጣ የአማራ ነጻነት አለመኖሩ እየታወቀ ለዚህ አውዳሚ አገዛዝ ሎሌ በመሆን የዚህ ጨዋታ ተዋናይ ለመሆን አውቃችሁም ሆነ ባለማወቅ እየተረባረባችሁ የምትገኙ ከላይ የተጠቀሳችሁ አካላት ይህ ተግባር በድርጅታችን የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ ፈጽሞ የተወገዘና እርምጃ የሚያስወስድ መሆኑን አውቃችሁ ከድርጊታችሁ እንድትቆጠቡ ስንል እያሳሰብን ይህን መመሪያ ተላልፎ በሚገኝ ማንኛውም አካል ላይ እርምጃ የምንወስድ መሆኑንና በዚህ ተግባር ስትሳተፉ ለሚደርስባችሁ የትኛውም ጥቃት ኃላፊነቱን የምትወስዱ መሆኑን እናሳስባለን።      ድል ለአማራ ፋኖ!    የአፋብን 206ኛ ኮር 14ኛ ክፍለ ጦር              መጋቢት 12/2018 ዓ/ም

የፓራ ኮማንዶ አባላቱ የምረት ጥሪውን በመጠቀም ክላሽ ትጥቅ እና ተተኳሽ በመያዝ ወደ ፋኖ ተቀላቀሉ ። ➽➽➽➽➽➽➽➽➽➽➽➽➽➽➽➽ መጋቢት 12/2018 ዓ.ም በዛሬው እለትም ከሸበል በረንታ እና ሰዴ ወረዳ መሽጎ የነበረው ሀይል ስርዓቱ በአማራ ላይ እየፈፀመ ያለውን ድርጊት በመቃወም በርካቶቹ ወደ 201ኛ ኮር 64ኛ እና 54ኛ ክፍለ ጦርን ተቀላቅለዋል። 1ኛ ታምሩ እማኝ.. 6ኛ ዕዝ 605ኛ ኮር ፐርሰኔል የነበረ 2ኛ.ይሁኔ ውዱ.. ሸበል በረንታ ወረጎ እና አካባቢው 3ኛ.እሸቱ አለማየሁ ...እናርጅ እናውጋ አብራራው 4ኛ.ሙክታር አህመድ..25ኛ ክ/ጦር ከሰዴ ወረዳ 5ኛ. ሁነኛው አጥናፉ ...ሰዴ ወረዳ ፓራ ኮማንዶ በመያዝ ከደብረወርቅ እና ሸበል በረንታ የአገዛዙን አፀያፊ ስራ በመቃወም አፋብን ቴዎድሮስ ዕዝ 201ኛ ኮር የተቀላቀሉ ሲሆን በአመሪሩም አቀባበል ተደርጎላቸዋል። አሁንም አልረፈደም ሁሉም ከዚህ አረመኔያዊ ከስርአቱ ተቋም በመውጣት ወደ ቀድሞ ማንነታቹህ ተመለሱ የአፋብን ቴወድሮስ ዕዝ 201ኛ ኮር ህዝብ ግንኙነት

74ኛ ክ/ጦር በሚያስተዳድራቸው ሶስት ወረዳወች ጊዜያዊ መንግስቱ ጥልቅ ግምገማወች ተከሄ። ➺➺➺➺➺➺➺➺➺➺➺➺➺➺➺➺➺ መጋቢት 11/2018 ዓ.ም የ201ኛ ኮር እና የ74ኛ ክ/ጦር አመራሮች እንዲሁም
+3
74ኛ ክ/ጦር በሚያስተዳድራቸው ሶስት ወረዳወች ጊዜያዊ መንግስቱ ጥልቅ ግምገማወች ተከሄ። ➺➺➺➺➺➺➺➺➺➺➺➺➺➺➺➺➺ መጋቢት 11/2018 ዓ.ም የ201ኛ ኮር እና የ74ኛ ክ/ጦር አመራሮች እንዲሁም የሶስቱ ወረዳወች የጎንቻ ሲሶ እነሴ፣እናርጅ እናውጋ እና እነብሴ ሳር ምድር ወረዳ ጊዜያዊ አስተዳደር አካላት በተገኙበት ለተከታታይ 7 ቀናት ጥልቅ ግምገማና ውይይት ተካሂዷል። ኮሩ እና ክ/ጦሩ ባካሄደው ጥልቅ የግምገማ ሃሳብ መሰረትም በሶሰቱም ወረዳዎች ባለፉት አራት ወራት ስለተከናወኑ አበይት ግባራት ውይይት በማካሄድ የአደረጃጀት ማሻሻያ በማድረግ የቀጠይ የስራ ተልኮወችን በመስጠት ውይይቱ ተፈፅሟል። አዲስ ትውልድ፣አዲስ አስተሳሰብ፣አዲስ ተስፋ የአፋብን ቴድሮስ ዕዝ 201ኛ ኮር ህዝብ ግንኙነት

መብረቅ ክፍለ ጦር ለወራቶች ያሰለጠናቸውን ምልምል ፋኖዎች አስመረቀ! ምኒልክ ዕዝ ንጉስ ሚካኤል አሊ ኮር መብረቅ ክፍለ ጦር ለወራቶች ያሰለጠናቸውን ምልምል ፋኖዎች አስመረቀ:: ከአፋብን ምኒልክ ዕዝ
+2
መብረቅ ክፍለ ጦር ለወራቶች ያሰለጠናቸውን ምልምል ፋኖዎች አስመረቀ! ምኒልክ ዕዝ ንጉስ ሚካኤል አሊ ኮር መብረቅ ክፍለ ጦር ለወራቶች ያሰለጠናቸውን ምልምል ፋኖዎች አስመረቀ:: ከአፋብን ምኒልክ ዕዝ ስልጠና መምሪያ በወረደላቸው አቅጣጫ መሰረት ኮርና ክፍለ ጦሮች ምልመላ በማካሄድና ስልጠና በመስጠት ራሳቸውን በሰው ሃይል በማደራጀትና በማጠናከር ላይ ይገኛሉ:: በዚህም ንጉስ ሚካኤል አሊ ኮር መብረቅ ክፍለ ጦር የመለመላቸውን ወጣቶች ለወራቶች ስልጠና በመስጠት አስመርቋል:: በቀጣይም ስልጠናው ተጠናክሮ ይቀጥላል ሲሉ አመራሮች ገልፀዋል:: መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልዉና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል! ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን! አፋብን ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ መጋቢት 11/2018 ዓ.ም

በሀገር ውስጥ እና በመላው ዓለም ለምትገኙ የእስልምና እምነት ተከታይ ኢትዮጵያውያን ወገኖቻችን በሙሉ፥ እንኳን ለ1447ኛው የኢድ-አልፈጥር በአል አደረሳችሁ የሚል መልእክቴን እያስተላለፍኩ፥ በአሉ የ
በሀገር ውስጥ እና በመላው ዓለም ለምትገኙ የእስልምና እምነት ተከታይ ኢትዮጵያውያን ወገኖቻችን በሙሉ፥ እንኳን ለ1447ኛው የኢድ-አልፈጥር በአል አደረሳችሁ የሚል መልእክቴን እያስተላለፍኩ፥ በአሉ የፍቅር እና የደስታ እንዲሆንላችሁ መልካም ምኞቴን እገልጻለሁ። ኢድ ሙባረክ! ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር ፍቅር ያሸንፋል!!! ቴዎድሮስ ካሳሁን (ቴዲ አፍሮ)

ቀን 11/07/18 ከትግሉ ሜዳ 🌿🌿🌿◌◎🌿🌿🌿 ጎንደር ጠቅላይ ግዛት 204ኛ አስቻለው ደሴ ኮር በስሩ ካሉ ክፍለ ጦር አመራሮች ጋር ውይይት አድርገናል። ኮሩ ሪፎርም ከሰራ በኃላ ከትግሉ ጎን
+3
ቀን 11/07/18 ከትግሉ ሜዳ 🌿🌿🌿◌◎🌿🌿🌿 ጎንደር ጠቅላይ ግዛት 204ኛ አስቻለው ደሴ ኮር በስሩ ካሉ ክፍለ ጦር አመራሮች ጋር ውይይት አድርገናል። ኮሩ ሪፎርም ከሰራ በኃላ ከትግሉ ጎን ለጎን ● ያለፉትን የትግል እንቅስቃሲያችን መገምገም ● የቀጣይ የስራ አቅጣጫ ማስቀመጥ ➸ ከተለመዷዊ የአተጋገል ስልት በመውጣት ተቋማዊ አተጋገልን ተግባራዊ ማድረግ ለትግሉ ትልቅ ሚና ይኖረዋል‼️ ድል ለአማራ ፋኖ የጎንደር ጠቅላይ ግዛት ዕዝ 204ኛ አስቻለው ደሴ ኮር የህዝብ ግንኙነት ክፍል

የጠላት ኃይል መፍረሱን ቀጥሏል ! ኢድ ሙባረክ ብለናል!! አቤ ጉበኛ ሻለቃ ማስከዳቱን ቀጥሏል ። በአፋብን ቴዎድሮስ ዕዝ 105ኛ ኮር 55ኛ ክፍለ ጦር አቤ ጉበኛ ሻለቃ ተቀላቀለዋል። ከተቀላቀሉት መ
+3
የጠላት ኃይል መፍረሱን ቀጥሏል ! ኢድ ሙባረክ ብለናል!! አቤ ጉበኛ ሻለቃ ማስከዳቱን ቀጥሏል ። በአፋብን ቴዎድሮስ ዕዝ 105ኛ ኮር 55ኛ ክፍለ ጦር አቤ ጉበኛ ሻለቃ ተቀላቀለዋል። ከተቀላቀሉት መካከለም ፦ 1ኛ.10 አለቃ ቢኒያም አስማማው ጋንታ መሪ 2ኛ.10 አለቃ ባንተጊዜ አለማየሁ ቲም መሪ 3ኛ.10 አለቃ እንዳልክ ጋንታ መሪ 99ኛ ክፍለ ጦር 3ኛ ሻለቃ 1ኛ ሻምበል አባል ናቸው ። የክፍለ ጦሩ ም/ል ጦር አዛዥ ኮማንዶ አስፋው በክብር ተቀበሎታል ። በርቱ እንበርታ !

አፋብን ምዕራብ አማራ ቀጠና ቴዎድሮስ ዕዝ ለተከታታይ 6 ወራት ያሰለጠናቸውን የልዩ ግዳጅ ኮማንዶዎችን አስመረቀ። 105ተኛ ኮር 55ተኛ ክ/ጦር የቢትወደድ አያሌዉ መኮነንን ሻለቃ ለተከታታይ 6 ወራት
+3
አፋብን ምዕራብ አማራ ቀጠና ቴዎድሮስ ዕዝ ለተከታታይ 6 ወራት ያሰለጠናቸውን የልዩ ግዳጅ ኮማንዶዎችን  አስመረቀ።       105ተኛ ኮር 55ተኛ ክ/ጦር የቢትወደድ አያሌዉ መኮነንን ሻለቃ ለተከታታይ 6 ወራት   ያሰለጠናቸዉን ሰልጣኞች የቲዎድሮስ እዝ ም/ፓለቲካ ዘርፍ አርበኛ ግሩም ምሳሌ፣የቲዎድሮስ ዕዝ ኦርዲናንስ ሃላፊ 10 ዓለቃ ታደሰ  ስመኝ እንዲሁም የ55ተኛ ክ/ጦር አመራሮች የቢትወደድ አያሌዉ መኮነንን ሻለቃ አመራሮች የሰሜን አቸፈር ወረዳ የጊዜዊ መንግስት አሰተዳደር አመራሮች የአካባቢዉ  ማህበረሰቦች በተገኙበት በደማቅ ሁኔታ በቀን 11/07/2018 ዓ/ም ተመርቀዋል።

አፋብን ምንሊክ ዕዝ 101ኛ ኮር ፖለቲካ ዘርፋ ሀላፊ አርበኛ መሀመድ መጎስ እና የኮሩ ዘመቻ መሪ አርበኛ እንድሪስ ጉደሌ እንዲሁም ቴዎድሮስ ዕዝ 201ኛ ኮር ህዝብ ግኑኝነት አርበኛ ሃብታሙ የሱፍ እ
+2
አፋብን ምንሊክ ዕዝ 101ኛ ኮር ፖለቲካ ዘርፋ ሀላፊ አርበኛ መሀመድ መጎስ እና የኮሩ ዘመቻ መሪ አርበኛ እንድሪስ ጉደሌ እንዲሁም ቴዎድሮስ ዕዝ 201ኛ ኮር ህዝብ ግኑኝነት አርበኛ ሃብታሙ የሱፍ እንኳን ለኢድ አልፈጥር በዓል በሰላም አደረሳችሁ መሪዎቻችን

ፋሽስቱ የብልፅግና አገዛዝ በንፁሀን ሰዎች ላይ እስርና እንግልት እየፈፀመ ይገኛል ። ዛሬም ከትላንት ስህተቱ መማር ያልቻለው ለፖለቲካዊ ጥያቄዎች ፖለቲካዊ መፍትሄ ከመስጠት ይልቅ ጦርነትን እና ንፁሀኖችን ማሰርና ማንገላታት ብቸኛው መፍተሄ አድርጎት የቀጠለው የብልግናው አገዛዝ እጅግ ኢ-ሰበዓዊ ድርጊቶችን እየፈፀመ እንደሚገኝ ተገለፀ ። በወቅቱ ከፍተኛ እብሪት ዉሰጥ እና የተሳሳተ ግምገማ ዉስጥ  የነበሩት የብልፅግና ከፍተኛ አመራሮች እና የጦር አዛዦች በ15 ቀኑ ዉስጥ አማራን አይደለም ትጥቁን ቀበቶዉን እናስፈታዋለን ብለዉ ፎክረዉ ቢገቡም በተገላቢጦሽ አማራዉ አይቶት የማያዉቀዉን የዘመናዊ ትጥቅ ባለቤት አድርገዉት ማረፋቸዉ የአደባባይ ሀቅ መሆኑ ይታወቃል ። በቡልጋ ቀጠና አገዛዙ በተደጋጋሚ ኔትወርክ በማጥፋትና በሌሊት ኦፕሬሽኖችን በማድረግ ከኪሳራ ዉጪ ምንም አይነት ለዉጥ ማምጣት ያልቻለዉ የአብይ አህመድ ሰራዊትና ካድሬ፤ ከመጋቢት 08/2018 ዓ.ም ጀምሮ የቀጠለው፤ በበረኸት ወረዳ መተህብላ ከተማ ላይ የፋኖ ቤተሰቦች ናችሁ በማለት ከፍተኛ ቁጥር ያላቸዉ አቅመ ደካሞች ፥ ሴቶችና ህፃናት ለእስርና እንግልት እየዳረጉ እንደሚገኝ የውስጥ አርበኞቻችን መረጃውን አድርሰውናል ። ንፁሀንን ማሰርና ማንገላታት የአምባገነኖች መገለጫ ቢሆንም ዉድቀትን ከማፋጠን በቀር የሚቀይረዉ አንዳች ለዉጥ እንደሌለ ታሪኮች ምስክሮች ናቸው ። በህዝባችን እየተፈፀመ ያለዉ ግፍና በደል ትግላችንን በከፍተኛ ወኔ እና ተነሳሽነት እንድናስቀጥለዉ ከማድረግ በቀር የሚያስቆመን እና አንገት የሚያስደፋን እንዳልሆነ በዚህ ሶሰት አመት ዉስጥ ያደረግነዉ ተጋድሎ ምስክር ነው ። ለመላዉ የከተማችን ማህበረሰቦች በሙሉ ይሄን ፀረ አማራ እና ፋሽስታዊ ስርዓት ከስር መሰረቱ ነቅለን መጣል እስካልቻልን ድረስ የነፃነት አየር መተንፈስ እንደማይቻል እያያችሁት ስለሆነ ራሳችሁን ለዚህ ለተቀደሰና ለማይቀረዉ የህልዉና ትግል ታዘጋጁ ዘንድ ግድ ነው ። ይሄን ለማድረግ ዝግጁ ያልሆነ ህዝብ ትርፉ እንግልት ፥ እስርና ሞት መሆኑን የአማራ ህዝብ በዚህ ሶስት የጦርነት አመታቶች ዉስጥ ያየዉና የተረዳው ሃቅ ነው፤ በማለት ከሰም ፪ኛ ኮር የቡልጋ ክ/ጦር ህ/ግንኙነት መረጃውን አድርሶናል ። "ንፁሃኖችን በማሰርና በማሰቃየት የሚቀጣጠል እንጂ የሚቆም ትግል የለም " - መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነዉ የአማራ ህዝብ የህልዉና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል ። - ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን !! - አፋብን ደቡብ አማራ ቀጠና አሳምነዉ ዕዝ ከሰም ፪ኛ ኮር ህዝብ ግንኙነት መምሪያ ።