ፍኖተ- አማራ ሚዲያ (Finote- Amhara ) Midea
Открыть в Telegram
የተመሠረተው የአማራን ሕዝብ ለማንቃት፣ ለማደራጀት እና ለማስተባበር ነው። የአማራ ሕዝብን ✅ ፖለቲካዊ ✅ ማህበራዊ ✅ ኢኮኖሚያዊ ታሪካዊ ጥያቄዎችን ለማሰማት እና የአማራን ሕዝብ በማንቃት ሰፊውን ሕዝብ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ይሰራል። ወደዱም ጠሉም የኃላ ታሪካችን በእኛ እጅ ይፃፋል። አማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ ( አፋብን)
Больше3 613
Подписчики
+1324 часа
+4187 дней
+1 05630 дней
Архив постов
የአናብስቱ እረኛ አርበኛው አማረ
ፀሐይ በደቡብ አማራ ቀጠና ተራራዎች ጀርባ ልትጠልቅ ስታዘግም የሰማዩ ቀለማት ደም መስለው ይታያሉ። በዚህ አስፈሪና ግርማ ሞገስ ባለው ተፈጥሮ መካከል፣ እንደ ዓለት የጸና አንድ ሰው ቆሟል። እርሱ አርበኛው አማረ ታዘዘ ነው።
አማረ በትምህርት ገበታ ላይ ቆይቶ የዲግሪ ማዕረግን የጨበጠ ምሁር ቢሆንም የእውቀቱ ጥልቀት ግን ከጥቁር ሰሌዳና ከወረቀት በላይ ነበር። ከተፈጥሮ ጋር ያለው ቁርኝት የሚገርም የነፋሱን ሽውሽውታ የወፎቹን ዝማሬና የተራራውን ዝምታ እንደ መጽሐፍ ያነባቸዋል።
ነገር ግን የእርሱ ታላቅነት በምሁርነቱ ብቻ አይወሰንም። አማራነት የታለች? ተብሎ ቢጠየቅ፣ መልሱ የሚገኘው በአማረ ግርማ ሞገስና በፅናት የተሞላ ማንነት ውስጥ ነው።
አንድ ምሽት፣ የአሳምነው ዕዝ የዓፄ ዘርዓያዕቆብ ፩ ኮር የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊነቱን ጎን ለጎን አድርጎ እየሰራ፣ የጦር መሣሪያውን አነገተ አብርውት ወደ ጫካ የገቡትኝ የሰባት ለሰባ ክፍለ ጦር የአሳምነው አናብስቶች "አይገባህም፣ አንተ የምትመራንና የምታስተዳድረን መሪ ነህ" ቢሉትም፣ አማረ ግን ፈገግ ብሎ እንዲህ አለ
መሪነት በመድረክ ላይ መናገር ብቻ ሳይሆን፣ ከጀግኖች ጋር አብሮ ግንባር ላይ መቆም ጭምር ነው። ይላል የጦርነቱ ነጎድጓድ ሲሰማና ምድሪቱ በባሩድ ጭስ ስትታወክ አማረ በመጀመሪያው ረድፍ ላይ ተሰልፎ ይታያል። ያ ምሁርነቱ ወደ ጀግንነት ያ ዝምታው ወደ ቆራጥ ውሳኔ ተቀይሯል የፈሰሰው ደምና ላብ የአማረን ስም ከሕዝቡ ልብ ጋር አጣበቀው።
"አማረ" እና "አማራ" የሚሉት ቃላት ተመሳሳይ የፊደል መገጣጠም ብቻ አይደሉም፤ ይልቁንም የአንድ ትልቅ ሕዝብ ዕጣ ፈንታና የአንድ ቆራጥ አርበኛ የደም ትስስር መገለጫዎች ናቸው። አማረ ታዘዘ ለአማራ ሕዝብ ያለው ፍቅር በቃላት አይገለጽም፤ በተግባር ግን በተራራዎቹ ድንጋይ ላይ ሳይቀር ታትሞ ይገኛል።
+2
➮ህዝባዊ ውይይቶች ተካሂደዋል‼️
በደብረ ገነት እና ባርጃኖ ከተማ 74ኛ ክፍለ ጦር ተከታታይ ሁለት ቀን ህዝባዊ ውይይቶች ተካሂደዋል።
➻➻➻➻➻➻➻◊◊➻➻➻➻➻➻➻➺➺
የካቲት 27/2018 ዓ.ም
በውይይቱ መድረኩ
➣የአፋብን ምስረታን በተመለከተ
➣የድርጅቱ አሁናዊ ቁመና በተመለከተ
➣የሀብት አሰባሰብን በተመለከተ
➣የመልካም አስተዳደርን በተመለከተ ህዝባችን ከተደቀነበት የህልውና ችግር ለመውጣት እና አገዛዙ በህዝባችን ላይ እያካሄደ ያለውን ዘር ተኮር ጭፍጨፋ ግንዛቤ በመስጠት የኮር እና የክፍለ ጦሩ አመራር እና የወረዳ ጊ/መንግስት አመራሮች የቀጣይ የስራ አቅጣጫ ተሰጥተዋል።
አዲስ ትውልድ፣ አዲስ አስተሳሰብ፣ አዲስ ተስፋ!
አፋብን ቴዎድሮስ ዕዝ 201ኛ ኮር ህዝብ ግንኙነት
#የድሮን_ቅኝት‼️
በመላው አማራ በተለይም በጎጃም በበርካታ ቦታዎች የድሮን ቅኝት ዛሬ በሰፊው እየተደረገ ይገኛል። ሰለሆነም የወገን ሀይል በጥንቃቄ እንዲንቀሳቀስ እንዲሁም የገቢያ ቀን ስለሆነ ማህበረሰባችን በጥንቃቄ ይንቀሳቀስ ዘንድ መረጃው ይዳረስ‼️
28/ዐ6/2018 ዓ.ም
የአማራ ፋኖ የትጥቅ ትግል ያለበትን ወቅታዊ ሁኔታ በማስመልከት ለህብርተሰቡ ሰፊ ግንዛቤ ተሰጥቷል።
የካቲት 28/2018 ዓ.ም
የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል ቴዎድሮስ ዕዝ 201ኛ ኮር 64ኛ ክፍለ ጦር በእነማይ ወረዳ ዴንሳ እነቆራ እና ሸበል በረንታ ወረዳ አራጤ ቀበሌ ሰፊ የህዝብ ውይይቶች አካሂዶል።
በውይይቱ መድርኩ ስለ አማራ ህዝብ የትጥቅ ትግል የተነሱ ሲሆን በዚህ ሰዓት የአማራ የትጥቅ ትግል ከአራቱም አቅጣጫ የተወጣጡ ጠንካራ መሪዎችን መርጦ ወደ አንድ መምጣቱን በማስረዳት ድርጅቱ ከትላንቱ ዛሬ የተሻለ ደረጃ ላይ መድረሱን ብዙ ዋጋ የተከፈለበትና የተደከመበት የአማራ ህዝብ የትጥቅ ትግል ህዝባችን አሉ የሚላቸውን የትኛውም አይነት ጥያቄዎች ለማስመለስ የአማራ ህዝብ አንድ ሆኖ መታገል እንዳለበት በስብሰባ መድርጉ ሰፊ ግንዛቤ ተሰጥቷል።
የአማራ ህዝብ ትግል ከፍ ያለ ደርጃ መድርሱን የአብይ አህመድ አረመኔዊ አገዛዝ በአማራ ህዝብ ላይ እያካሄደ ያለውን የዘር ማጥፋት ወንጀል ለማስቆምና የአማራ ህዝብ ከተደቀነበት የህልውና አዳጋ ለመመከት ህዝባችን ዛሬም ከትላንቱ የተሻለ ተሳትፎ ማድርግ እንዳለበት የጀመርነው የትጥቅ ትግል ህዝባችን በፋይናስ በመረጃ መሰል ጉዳዩችን ዛሬም እንደትላንቱ ከፋኖ አባላቱ ጎን መሆን እንዳለበት በስብሰባ መድርኩ ለተገኙት የማህበረሰብ ክፍል በክፉለ ጦሩ አመራሮችና በወረዳ ጊ/መንግስት አመራሮች ሰፊ ግንዛቤ ተሰጥተዋል።
አዲስ ትውልድ፣ አዲስ አስተሳሰብ፣ አዲስ ተስፋ!!
የካቲት 28/2018 ዓ.ም
አፋብን ቴዎድሮስ ዕዝ 201ኛ ኮር 64ኛ ክፍለ ጦር ሕዝብ ግንኙነት
#ሰበር ዜና፦ #የብልጽግና_ዕድሜ_ማብቂያ?
#የሠራዊቱ_ቁልፍ_አካላት_ፋኖን_እየተቀላቀሉ_ነው!
༻༺༻༺༻༺༻༺
[የካቲት 28/2018 ዓ.ም፣ ዐፋብን 102ኛ ኮር 33ኛ ክ/ጦር ሕዝብ ግንኙነት]
በኢትዮጵያ ፖለቲካዊ ምህዳር ውስጥ የአገዛዙ የሰላም ግንብ እየተናደ መሆኑን የሚያሳብቁ "ክህደቶች" ሳይሆኑ "የወገንተኝነት ጥሪዎች" ከየጦር ግንባሩ እየተሰሙ ነው።
ከምሥራቅ ዕዝ 302ኛ ኮር፣ 76ኛ ክፍለ ጦር የወጡት መረጃዎች እንደሚያመለክቱት፣ የሠራዊቱ ቁልፍ መኮንኖች አፈሙዛቸውን ወደ ሕዝባቸው ከማዞር ይልቅ የነፃነት ታጋዮችን መቀላቀል መርጠዋል።
#በአገዛዙ ፻ አለቃ ተክሉ አጃቢ (የ2ኛ ሬጅመንት መሪ) ፲ #አለቃ_ተቀባ_ሙሐባው እና #ም/፲ አለቃ #ታደለ_ገበየሁ (በኮሎኔል አቢዮት የሚመራው 3ኛ ሬጅመንት 1ኛ ጋንታ ም/መሪ) በዐፋብን ቴዎድሮስ ዕዝ 102ኛ ኮር 33ኛ ክፍለ ጦርን ተቀላቅለዋል።
እነዚህ መኮንኖች ተራ ወታደሮች ሳይሆኑ የጦር ሜዳ ውሎንና የሠራዊቱን ስነ-ልቦና ጠንቅቀው የሚያውቁ ስትራቴጂስቶች ናቸው።
የእነሱ መውጣት ለብልጽግና ሠራዊት የሞራል ውድቀት፣ ለፋኖ ደግሞ የስትራቴጂካዊ የበላይነት ማረጋገጫ እና ተደማሪ ጉልበት ተደርጎ ተወስዷል።
"#አፈሙዙ_ወደ_ብልጽግና_ይዞራል!" ሁለቱ ወታደሮች ከተናገሩት
ፋኖን የተቀላቀሉት አመራሮች የሰጡት ምስክርነት የአገዛዙን ውስጣዊ ዝገት ፍንትው አድርጎ የሚያሳይ ነው። ወታደሮቹ በቁጭት እንደተናገሩት፣ "ሠራዊቱ ከገዛ ሕዝቡ ጋር የመዋጋት ፍላጎት የለውም። አገዛዙ ሕዝብን የመጠበቅ ኃላፊነቱን ወደ ጎን በመተው በዘረፋና በሀብት ማከማቸት ላይ ተጠምዷል ብለዋል።
ይህ ንግግር የብልጽግና አስተዳደር የቆመበት መሠረት እየተሸረሸረ መሆኑንና ሠራዊቱ በቅርቡ በጅምላ አፈሙዙን ወደ አገዛዙ በማዞር ለሕዝባዊ ወገንተኝነቱ ማረጋገጫ እንደሚሰጥ ትልቅ ተስፋን የጫረ ሆኗል።
⚠#የውስጥ_አጥሮችና_የሚሊሻው_ሚና
እነዚህ ከአገዛዙ የወጡ ወታደሮች እንዳጋለጡት፣ አገዛዙ በሕይወት ያለው በራሱ ጥንካሬ ሳይሆን፣ "መክዳት የሚፈልገውን ሠራዊት አጥር ሆነው በያዙ" የአካባቢው ተወላጅ ሚሊሾች አማካኝነት ነው። እነዚህ ሚሊሾች የገዛ ወንድሞቻቸውን እየጨፈጨፉ የአገዛዙን ዕድሜ እያራዘሙ መሆኑን በመጥቀስ፣ የታሪክ ተጠያቂነት እንዳይመጣባቸው የመጨረሻ ማስጠንቀቂያ አስተላልፈዋል።
የታሪክ ምሁራን እንደሚሉት፣ አንድ ሠራዊት አፈሙዙን ወደ መሪዎቹ ማዞር ሲጀምር፣ ያ ሥርዓት የጥፋት ደወሉ ተደውሏል ማለት ነው።
የወታደሮች ንግግር እንደሚያስረዳው ጦርነቱ በፋኖና በሕዝባዊ ኃይሎች ድል አድራጊነት እንደሚደመደም ነው።
▶ ድል ለነጻነት ፈላጊው ሕዝብ💪💪💪
22ኛ ክፍለ ጦር ሶስተኛ ሻለቃ የተሳካ የሚባል የደፈጣ ኦፕሬሽን በመፈፀም ድል አስመዘገበች::
አፋብን ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ 106ኛ ኮር በ22ኛ ክፍለ ጦር የካቲት 27/2018 ዓ/ም በደፈጣ የጥላት ሰራዊት ላይ እርምጃ በመውሰድ ድል አስመዝግበዋል::
የድሀን ልጅ የቀን ስራ ከሚሰራበት እየጋፈፈ ሳያሰለጥን ለስልጣን ማስጠበቂያ ጦርነት የሚማግደው የብልፅግናው አገዛዝ እንደ ሁልጊዜው ዛሬም የድሀን ልጅ ያለምንም ወታደራዊ ስልጠና የመከላከያን ዩኒፎርም በማልበስ ወደ አማራ ክልል እስገብቶ የአማራን ህዝብ ጨፍጭፉ ብሎ በሰጠው ትዛዝ መሰረት መነሻውን ጋሸና አድርጎ ወደ መቄት ሲጓዝ በነበረ የብርሀኑ ጁላ እና የአረጋ ከበደ ጥምር ሰራዊት ላይ እርምጃ ተወስዷል።
ከቀኑ 8:30 ሰዓት የ22ኛ ክፍለ ጦር ሶስተኛ ሻለቃ ገጣጢት ላይ በተወሰደ መብረቃዊ ጥቃት ሶስት የጁላ ሰራዊቶች ሲደመሰሱ አምስቶቹ ደግሞ ከባድ ቁስለኛ ተደርገው ወደ ሆስፒታል የገቡ ሲሆን፤ቀሪዎቹ የምርኮኛው ብርሀኑ ጁላ ሰራዊትም በደረሰበት ቅስፈታዊ ጥቃት እና የተኩስ እሩምታ መንፈሳቸው የተጨነቁት ወደ መጡበት ጋሸና እግሬ አውጭኝ ብለው ፈርጥጠዋል። ሽሽትን እንደ ነፍስ አድን የመጀመሪያ አማራጭ የሚጠቀሙት ተጋፈው የመጡት የጁላ ወታደሮች ቀን የገጠማቸው እለት እጃቸውን በአካባቢያቸው ለሚገኝ ፋኖ እየሰጡም ይገኛል።
መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልዉና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል!
ህልዉናችን በተባበረ ክንዳችን!
የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ (አፋብን) የደጋው መብረቅ ኮር ህ/ግ ክፍል
የካቲት 28/2018 ዓ.ም
ሰበር የድል ዜና ‼
አፋብን አፄ ቴወድሮስ ዕዝ 102ኛ ኮር 11ኛ ክፍለጦር ጥምር ሀይል እና አህዶች ሻምበል መማር ጌትነት 2ኛ ሻለቃ ዛሬ በሰሩት ጀብዱ በጥላት ላይ ከፍተኛ ድል ተገኝቷል ።
ዛሬ የካቲት 27/2018 ዓ/ም ከመርዓዊ ከተማ እና ልዩ ሥሙ ቻይና ካፕ ከተባለ ካፕ ተንቀሳቅሶ ወደ የፋኖ ቀጠና ወደሆነችው አማሪት ከተማ የተንቀሳቀሰው የዐብይ አህመድ ወንበር አስጠባቂ አራዊት ሰራዊት በጀግናው ፋኖ ከፉኛ ተገርፎ ቀኝ ሗላ ዞሮ ከአትሊቲክስ በፈጠነ እሩጫ ወደመጣበት ተመልሷል ።
በነረው አውደ ውጊያ የኮሎኔል ታደሰ ሙሉነህ መንፈሶች በጥላት ላይ ከፍተኛ ኪሳራ ያደረሱ ሲሆን ሙት እና ቁስለኛ ከሆነው በተጨማሪ ምርኮ ወይም በጨበጣ የተማረከም ይገኝበታል ።
በተሰራው አስደናቂ ኦፕሬሽን ብሬንን ጨምሮ በርካታ ክላሽንኮቭ ጠመጃወች እና ተተኳሾች እንዳሁም ወታደራዊ ቁሳቁሶች በስፋት ተማርከዋል ።
የተማረከውን የሰው ሀይል እና መሳሪያ እና ተተኳሽ እንዲሁም ወታደራዊ ቁሳቁስ በዝርዝር የምንመለስበት ይሆናል የዐብይ አህመድ ዙፋን ጠባቂ አራዊት ሲሸሽ እንዲህ ይሮጣል እንዴ እሮጠ እኮ !!😂
በዝርዝር እመለሳለሁ ሸር አድርጉ !!
ድል ለተገፋው አማራ !!
ድል ለጀግናው ፋኖ 💪!!
በደቡብ አማራ ቀጠና በኤፍራታ ግድም ወረዳ በንጹሃን ማህበረሰብ ላይ በአብይ አህመድ ኃይሎች ለእስርና እንግልት እየተዳርጉ ይገኛሉ!!
በደቡብ አማራ ቀጠና በኤፍራታና ግድም ወረዳ ስር በምትገኘው በርግብ ቀበሌ፣ የአብይ አህመድ ወንበር አስጠባቂ የብአዴን ሃይሎች ነዋሪዎችን በማስገደድና በማሰር ላይ በህዝባችን ላይ እንግልት እየፈፀሙ ይገኛሉ።
የብልፅግና ሚኒሻና አካላት የበርግቤ የቀበሌ ነዋሪዎች በመሰብሰብ 45 ሴቶችና 30 ወንዶች በአጠቃላይ 75 ሰዎችን "ሚኒሻ መሆን አለባችሁ" በሚል አስገዳጅ ጥያቄ አቅርበውላቸዋል። ይህንን ጥያቄ ያልተቀበሉ ከ75 በላይ የሚሆኑ የበርግብ ነዋሪዎች በዛሬው ዕለት በቁጥጥር ስር ውለው ከፍተኛ እንግልትና ስቃይ እየደረሰባቸው መሆኑ ይገኛል።
እንደሚታወቀው የአጣዬ ከተማና ከ11 ጊዜ በላይ በቃጠሎ መውደሟ የሚታወስ ሲሆን፣ አሁንም በህዝቡ ላይ የሚፈጸመው ግፍ ተባብሶ ቀጥሏል።
እንዲሁም በኤፍራታና ግድም ወረዳ ስር ያሉ አካባቢዎችን ወደ ኦሮሞ ልዩ ዞን ለማጠቃለል የታቀደ እንቅስቃሴ እየተደረገ ይገኛል። የአብይ አህመድ ወንበር አስጠባቂ ካድሬዎችና የሚኒሻ አመራሮች በህዝቡ ላይ የሚፈጸመውን እንግልት በማስተባበርና ጫና በመፍጠር በንጹሃን ላይ እየተፈጸመ ያለው እስራትና "በግዴታ ታጠቁ" የሚል ጫና በአካባቢው ላይ ያለውን ማህበራዊ ቀውስ እንዲገባ እያደርጉት ንገኛሉ።
ዝርክርኩ የመከላከያ ቡድን ዛሬም ተዝረክርኳል💪
አፋብን ምዕራብ አማራ ቀጠና ቴዎድሮስ ዕዝ 105ኛ ኮር 44ኛ ክፍለ ጦር የጠላት ሃይል ላይ በወሰደዉ እርምጃ 13 መከላከያ ሜዳ ላይ ወድቆ እንዲቀር በማድረግ 7 ክላሽ እንኮፍ ገቢ አድርጓል።
ልማደኛዉ 44ኛ ክፍለ ጦር በሚንቀሳቀስበት ጠላት ትናንት ከሰከላ አጉት በመነሳት ቲሊሊ ዶርሶ በመመለስ ላይ እያለ ፈረዳ ተብሎ ከሚጠራዉ አካባቢ ላይ በተደረገዉ ትንቅንቅ እሬሳዉን ሳያነሳ እያዝረከረከ፣ ቁስለኛዉን ተሸክሞ ተዛዝሎ እንዲፈረጥጥ ሁኗል።
አረመኔው ቡድን እንደተለከፈ ዉሻ እየተልከፈከፈ፣ የንፁሃንን ህይወት እየቀጠፈ፣ የቀጠለ ቢሆንም 105ኛ ኮር 44ኛ ክፍለ ጦር ነበልባሎች ዛሬ በ27/2018 ዓ.ም ቲሊሊ ወረዳ ላይ ባደረሱበት ጠንካራ ምት 23ቱ ወንበዴ ቡድን ጀርባ ጀርባውን እየተነደለ ባፍጢሙ ተደፍቶ ሜዳ ላይ ወድቆ የጅብ እራት ሁኖ ሲቀር 9 የሚደረሱትን ደግሞ ተሸክሞት ፈርጥጧል።
አፋብን ምዕራብ አማራ ቀጠና ቴዎድሮስ ዕዝ 105ኛ ኮር 44ኛ ክፍለ ጦር ህዝብ ግንኙነት
27/ዐ6/2018 ዓ.ም
"ታሪካችን ህይወትን በመገበር በደምና አጥንት ሃገር መንግስት መስርቶ አፅንቶ መኖር ነው"። የታሪካዊቷ ጉና ክፍለ ጦር የፋኖ አመራሮች
=========================
የካቲት 27/2018/ ዓ.ም
አፋብን ሰሜን አማራ ቀጠና በላይ ዕዝ ሜጀር ጀኔራል ውባንተ አባተ ፩ኛ ኮር ጉና ክፍለ ጦር በታሪካዊቷ ጥንታዊ መካነ ኢየሱስ ከተማ በቀጣይ ለሚደረጉ ወታደራዊ ግዳጅ ብቻ ሳይሆን ፖለቲካዊ አቅጣጫ ጭምር ውይይት አካሄደ።
የግዙፋ ሜጀር ጀኔራል ውባንተ አባተ ፩ኛ ኮር አንድ አካል የሆነችሁ በሰብሳቢ አርበኛ ወንዱአንተ አሰፋ እና በዋና ወታደራዊ አዛዥ አርበኛ አዛዥ ደሳለኝ የምትመረው ታሪካዊቷ ጉና ክፍለ ጦር ከተመሰረተች ጊዜ ጀምሮ በቀጠናው በወታደራዊ ግዳጅ አስደማሚ ተጋድሎዎችን እየፈፀመች ቆይታለች።
በውስጧም አምስት ግዙፍ ብርጌዶችን በማቀናጀት እረፍት አልባ የግንባር፣ የደፈጣ እና ስቦ የመምታት የአውደ ውጊያ ስልቶችን በመፈፀም በቀጠናው በጠላት ሃይል ላይ ፍፁም የበላይነት ወስዳለች፤ እየወሰደችም ትገኛለች።
በመሆኑም ሁሉም የክፍለ ጦር አመራሮች በታደሙበት ለ2 ተከታታይ ቀናት ጥልቅ ውይይት እና ግምገማ በመድረግ በሚከተሉት ጉዳዮች ስፋ ውይይት ማድረጉን አስታውቋል።
✔️በቀጣይ በሚሰሩት ቸክ ሊስት ዙሪያ፤
✔️ የህዝብ አስተዳደር ፍትህ ማስፈን እና የከተማዎችን ሰላምና ደህንነት ማስጠበቅ፤
✔️ የህዝብ አገልግልት ሰጭ ተቋም አገልግሎት በተመለከተ፤
✔️ ጠንካራ የህዝብ አደረጃጀት በመፍጠር ቀጠናውን ከሌባና ከዘራፊ ሃይለ መጠበቅ፤
እንዲሁም ሌሎች የፖለቲካ ጉዳዮችን ተመላክቷ ሰፊ ምክክር አድርጎል።
በመጨረሻም የቀጣይ የስራ አቅጣጫዎችን በማስቀመጥ እና ስምሪት በመስጠት መርሃ ግብሩ ከሁልጊዜውም በበለጠ ፍፁም ቁርጠኝነት በታየበት መልኩ ተጠናቋል።
ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን‼️
አፋብን ሰ/አ/ቀ/ ሜ/ጀ/ ውባንተ አባተ ፩ኛ ኮር ጉና ክፍለ ጦር ህዝብ ግንኙነት ክፍል
ፋኖ መምህር ያሬድ ገደፍው
#አስቸኳይ_መረጃ‼️
አሸባሪው የብልፅግና ቡድን አሁን አመሻሽ ም/ጎጃም ዞን ፍኖተሰላም እና አካባቢው የገበሬውን የግል ትጥቅ ለማስፈታት እንቅስቃሴ ጀምሯል መረጃውን ለአካባቢው የግል ታጣቂና ለአናብስቶች ይድረስ ሲሉ የንስር አማራ ምንጮች መልዕክት አስተላልፈዋል‼️
ሼርርርርር ይደረግ!
27/ዐ6/2018 ዓ.ም
መረጃ ወለጋ‼
ምስራቅ ወለጋ ዞን ሲቡ ስሬ ወረዳ ደንገዮ ጉዩ ቀበሌ ልዩ ስሟ ከረዩ የምትባል አካባቢ በዛሬው ዕለት ከጧት ጀምሮ ገዳ ኮማንዶና ሚኒሻ የአማራ ቤቶችን እያቃጠሉ እንደሚገኙ የደረሰን መረጃ ያመላክታል።
አካባቢያቸው ላይ ምንም አይነት ጦርነት የሌለባቸውና አማራ በአነስተኛ ደረጃ የሚርባቸው አካባቢዎችን እዬለዩ ሀብት ንብረት መዝረፍና ማውደም አጠናክሮ የቀጠለው የሽመልስ አብዲሳው ልዩ ኮማንዶ አጸፋው የከፋ ነዉ።
እኛ ፋኖዎች የህዝባችን ጥቅምና ደህንነት ታማኝ ዘቦች ነን!!
የአማራ ህዝብ ጥቅምና ደህንነትን ሙልጭልጭ የፖለቲካ ሴረኞች የኤምሬትስ ተላላኪዎች ዶሮ ሶስት ጊዜ ሳይጮህ
ገቢያ አውተው ሽጠውታል።የደህንነት ጥበቃ የአማራ ልዩ ኃይልን በማፍረስና በመበተን፣ቀሪውን በራሳቸው ጫማ ልክ ጠፍጥፈው በፀረ አማራነት በማሰማራት፣ፋኖም ሆነ አርሶ አደሩ በጭር ጊዜ ትጥቅ እንዲፈታ የአማራ ህዝብ ጥያቄዎችን በማዳፈን መጠነ ሰፊ ወታደራዊ ዘመቻ በማድረግ ጨፍጭፈዋል፣አማራን አድቅቀዋል፣ሀቀኛ ጥያቄዎቹን አፍነው አያሌ በደል ለማድረስ ታትረው ነበር።
ቢሆንም የአማራ ፋኖ ሁለንተናዊ ጫና እና ብርቱ ቁርጠኛ ተጋድሎ የጎን ውጋት ሁኖ ሰቅዞ ሲያፈርሳቸው በፖለቲካ ተቀባይነት የተተፋው ቡድን በደንባራ ዓይኑ ስስ ጉዳዮቻችንን አዛብቶ በማቅረብ ተደናብሮ ለማደናበር ሲታትር ይስተዋላል።
በስልጣን ለመቆየት በቂ ምክንያት እና ተስፋ የለሹ ወለቅላቃው ወንጀለኛ አገዛዝ እንደ ሰው ለመኖር ሰብዓዊ መብታችን ላይ በመዝመት ክህደቱን አጠናክሮ ቀጥሏል።
የህዝባችን ጥቅምና ደህንነት ለማስከበር የመነንን የሁሉም አማራ አልፎም የሀገሪቱ ታማኝ ዘቦች ነን!!
44 ነጥብ!!
ባንታመን አትታመኑን!!
ዮሐንስ ንጉሱ ሙጨ
ለደብረ ማርቆስ ከተማና ለአካባቢው ማህበረሰብ ከ206ኛ ኮር የተላለፈ አስቸኳይ የጥንቃቄ መልዕክት!!
የካቲት 27/2018 ዓ.ም
================================
በአማራ ህዝብ ትግል ፈር ቀዳጅ እንቅስቃሴ በማድረግ ወደር የለሽ ሚና ሲወጣ የነበረው የደብረ ማርቆስ ከተማ ማህበረሰብ ትግሉ እዚህ ደረጃ እንዲደርስና አደረጃጀቶች ጎልብተው ጠንካራ ወታደራዊ አቅም እንዲገነቡ ፣ ጠንካራ ግዳጆችን በጠላት ላይ እንዲያሳርፉ ላበረከተው ከባድ አስተዋጽኦ 206ኛ ኮር ምስጋናውን ያቀርባል።
ይሁን እንጂ ይህንን የህዝብ ቀና ተሳትፎ እንደ መልካም አጋጣሚ የተጠቀሙ አንድአንድ አካላት በኮሩ፣ በክ/ጦርና፣ በሻለቆች እንዲሁም በተዋቂ ሰዎች ስም በማጭበርበር ከህብረተሰቡ ገንዘብ እንደሚሰበስቡ ደርሰንበታል።
በህዝቡ ጥያቄና ጥቆማ መሰረት በአፋብን ቴዎድሮስ ዕዝ የፋይናስ መመሪያ ድንጋጌ አንቀፅ 6 ንዑስ አንቀፅ 6.7 የተቀመጠው የተቋም አሰራር ይተገበር ዘንድ 206ኛ ኮር መግለጫ እስከሚሰጥ ድረስ የደብረ ማርቆስ ከተማ እና የአካባቢው ማህበረሰብ ከአጭበርባሪዎች እና ከዘራፊዎች እራሱን እንዲጠብቅ እናሳስባለን። ከዚህ ጋር በተያያዘ ድርጅታዊ አሰራርን ተላልፎ ከህዝቡ ባልተገባ መንገድ ሀብት የሚሰበስቡ፣ ማህበረሰቡን የሚያጭበረብሩ አካላትን በመከታተል ኮሩ አስተማሪ እርምጃ እንደሚወስድ ያረጋግጣል።
አዲስ ትውልድ ! አዲስ አስተሳሰብ! አዲስ ተስፋ!
የአፋብን ቴዎድሮስ ዕዝ 206ኛ ኮር!!
