ru
Feedback

Не попадитесь на канал ботавода! Telemetrio находит и помечает такие каналы 👉 Хотите видеть метку — оформите подписку

ፍኖተ-አማራ ሚዲያ (Finote Amhara Media)

ፍኖተ-አማራ ሚዲያ (Finote Amhara Media)

Открыть в Telegram

የተመሠረተው የአማራን ሕዝብ ለማንቃት፣ ለማደራጀት እና ለማስተባበር ነው። የአማራ ሕዝብን ✅ ፖለቲካዊ ✅ ማህበራዊ ✅ ኢኮኖሚያዊ ታሪካዊ ጥያቄዎችን ለማሰማት እና የአማራን ሕዝብ በማንቃት ሰፊውን ሕዝብ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ይሰራል። ወደዱም ጠሉም የኃላ ታሪካችን በእኛ እጅ ይፃፋል። አማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ ( አፋብን)

Больше
4 487
Подписчики
-524 часа
+677 дней
+84830 дней
Архив постов
አማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል (አፋብኃ) ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ ሰበር ዜና የልጅ እያሱ ኮር ክፍለጦሮች በጋራ በከፈቱት ጠንካራ ውጊያ የአምባሰል ወረዳ መቀመጫ የሆነችውን ውጫሌ ከተማን ተቆጣጥረው ታላቅ ድል ተጎናፀፉ:: ዛሬ ጳጉሜ 02/2017 ዓ.ም አፋብኃ ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ እዝ በልጅ እያሱ ኮር ስር ያሉ ክፍለ ጦሮች የደቡብ ወሎ ዞን የአምባሰል ወረዳ መቀመጫ በሆነችው ውጫሌ ከተማ ከጠዋቱ 12:00 ጀምሮ በቀጠለው ተጋድሎ እስከ መሀል ከተማ በመግባት የየጁ ክፍለ ጦር ራስ አሊ ክፍለ ጦር ሁለተኛ ሻለቃ እና ራምቦ ክፍለ ጦር ሁለተኛ ሻለቃ በጋራ በመሆን በተናበበ ፍፁም በተቀናጀ መልኩ የተሳካ ውጊያ በማድረግ ጠላትን ሙት እና ቁስለኛ ሲያደርጉት ውለዋል ። እስካሁን ከ10 በላይ ፖሊስ እና ሚሊሻ ሲገደል በቁጥር ያልተረጋገጠ የወራሪው መንግስት ወታደር ሚሊሻ አድማ ብተና አና ፖሊስ ቁስለኛ ሆኗል:: በተጨማሪም ሶስት የሚሊሻ አባላት ምርኮኛ በማድረግ ውጊያው እንደ ተፋፋመ ቀጥሏል:: በዚህ ውጊያ የልጅ እያሱ ኮር የበቀል በትሩን አጠናክሮ በመቀጠል ውጫሌ ከተማ ያለውን የብልፅግና ግብስብሰ የፀጥታ ኀይል እና ካድሬ እያጠራ ይገኛል፡፡ የአብይ ሠራዊት ከወልድያ እና ከደሴ ሁለት ዙ23 እና አንድ መድፍ ያመጣ ቢሆንም ከብዙ ኪ.ሜ ርቀት ቆሞ ከመተኮስ በዘለለ ምንም ፋይዳ ያለው ተግባር ሊፈፅሙ አልቻሉም፡፡ በተጨማሪም በተደረገው ከፍተኛ የከበባ ውጊያ አንድ ከፍተኛ (ኮሎኔል ሊሆን እንደሚችል ይገመታል) የመከላከያ አመራርም ጭምር ተገድሏል። ጠላትን ከበባ ውስጥ በማስገባት ውጊያው አሁንም የቀጠለ ሲሆን ከዚህ የተሻለ ጮቤ የሚያስረግጥ ድል እየጠበቅን ከበባውን አጠናክረን ይዘናል፡፡ መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልውና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል! ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን! አፋብኃ ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ የልጅ እያሱ ኮር ህዝብ ግንኙነት ክፍል ጳጉሜ 3/2017 ዓ.ም ዋግነር የአማራው ፋኖ በመወዳጀት መረጃዎቻችን በሁሉም አማራጭ ተደራሽ እንሆን ዘንድ የበኩሉዎን አስተዎፆ ያድርጉ ‼️ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን ‼️ የቴሌግራም ቻናላችን ጆይን ሸር አድርጉ እንወያያለን እንማማራለን እንደራጃለን አብርን እናሸንፋለን አድራሻችን👇👇👇👇 https://t.me/httpsuYkZrGfSZrNjNjFk

የአማራው ኩራት #ራስ አርበኛ ዘመነ ካሴ የሳቱ ጉማጅ ✅ ያ የባህርዳር ስታዲየም በስሙ የደመቀበት ✅ሺወች በፎቶው ሹራብ ያስሩለት ✅ሚሊዮኖች ከእርሱ ጎን ነን ብለው በፎቶው ባነር አስርተው ሰልፍ የወጡለት ✅ብዙዎች በምስሉ ስአት እና ጌጣጌጥ ያስሩለት ✅መላው አማራ ድምፁን ሲስማ በወኔ የሚሽበርለት ✅ከማንም የገዘፈ የሞራል ልዕልና ያለው ✅ዕንቁ አርበኛ ✅ዕንቁ ታጋይ ✅ዕንቁ የህዝብ ልጅ በስሜን ኢትዮጵያ ፣በደቡብ ኢትዮጵያ ፣በምዕራብ ኢትዮጵያ ፣በመካከለኛው ኢትዮጵያ ከጫፍ እስከ ጫፍ ያሉት ነገደ አማሮች በተስፋ የሚጠብቁት ልዩ የዘመኑ ክስተት የትውልዱ አብሪ ኮኮባችን ዘሜችን መከታ ጋሻችን የነፃነት ድልድያችን ከኔ እድሜ ቀንሶ ላንተ ይስጥልኝ የስማዩ ጌታ አንተ ላይ የሚስነዘሩ ላንተ የማይገቡ ነገሮችን በሙሉ አላህ ለኔ ያድርግልኝ ላንተ የሚገቡና አንተን የሜስደስቱ መልካም ነገሮች በሙሉ የምታምነው አምላክ እግዚአብሔር ወዳንተ ያቅርብልህ በሄድክበት ሁሉ ደስታንና ድልን ያጎናፅፍህ ሽርኛን ምቀኛን ሴርኛን በስው ተመስለው ከሚቀርቡ ተኩላዎች አላህ ይጠብቅህ ክንዳለሜ በርግጥም አንተን የሚያውቁና ስላንተ ዱአና ፀሎት ሲያደርጉ የሚውሉ ሚሊዮን እናቶች አሉህ የነሱም ድምፅ ነው ዛሬን እድትኖራት ያደርገህ ከአምላክ በታች ወደፌትም የጀመርከው ትግል ከጫፍ ደርሶ አላማህ ፍላጎትህ ተሳክቶ ያዘነው ህዝብህ ተደስቶ ፣የተራበው ጠግቦ ፣ያጣው አግኝቶ ፣ያመመው ተፈውሶ ህዝቡ በደስታ ፍንድቅ ፏ ፈሺ ብሎ ዋጋ ለከፈልክልን በሙሉ ውለታህን ከፍለን ባንጨርስ እንኳን የሚገባህን ክብርና ምስጋና እደምናቀርብልህ አልጠራጠርም ይሄ ደግሞ የምንግዜም ምኞትና ህልሜ ነው ደግሞም ይሳካል ኢንሻ አላህ!! በበኩሌ የአማራን ትንሳኤ ያየሁ ቀን ደከመኝና ስለቸኝ ሳልል ማይክራፎኔን ይዥ እየዞርኩ ለከፈልክልን መስዋዕት በሙሉ ስላንተ ስለጀግንነትህ ፣ ስለ ጥንካሬህ ፣ ስለ ትዕግስትህ ፣ ስለ የትግል ቆራጥነትህ ፣ አስተዋይነትህ፣ስለ ትህትናህ ፣ ትንሺ ትልቅ ሳትል ስው አክባሪነትህ፣ ወዳድነትህ፣ሁሉንም እደራስህ የምታይበትን ንፁህ ልብህ ፣ ተስፋ ስጭነትህ፣ እና ለህዝብህ ያለህን አመለካከትና፣የመሪነት ብቃትህን ድምፄን ጎላ በማድርግ ህዝብ አይደለም አበደች እንደ ብለው ቀርፀው አለም አቀፍ ማህበርስብ ስለ አንተ እዳይልኝና እድስማልኝ የምንግዜም ምኞቴ ነው ይሄንን የማደርገው ስለምወድህ ብቻ አይደለም ስለሚገባህም ጭምር ነው ወላሂ ላንተ የማይገባህ ነገር ምን ሊኖር ይችላል??በምድር ላይ አሉ የተባሉ ውብ እና ውድ እና መልካም ነገሮች በሙሉ ይገቡሀል!! #በርግጥ አንተን የሚጠሉ አሉ ነገር ግን አስርግጨ የምናገርው ነገር ቢኖር ጥላቻ ሳይሆን ምቀኝነት & የበታችነት ስሜት የተጠናወታቸው ፀር አማራ፣ፀር ስላም እንዲሁም የብልፅግና ካልሲ አጣቢወች አሽርጋጆች & አጎብዳጆች በተጨማሪም ለህዝባቸው ሳይሆን ለሆዳቸው ያደሩ ከርሳሞች ብቻ ናቸው። ዳግማዊ በላይ ዘለቀ ብየሃለሁና በርታልኝማ አለቃ❤️🤗 አድስ ትውልድ አድስ ተስፋ አድስ አስተሳስብ ክፋት ለማንም በጎነት ለሁሉም አንድ አማራ ለሁሉም አማራ ሁሉም አማራ ለአንድ አማራ ድል ለአማራ ብሔራዊ ኃይል አፋብኃ🦾🦾 ድል ለመላው የአማራ ህዝብ💚💛❤️ አይስማም እናሽንፋለን🔥🔥 ዋግነር የአማራው ፋኖ በመወዳጀት መረጃዎቻችን በሁሉም አማራጭ ተደራሽ እንሆን ዘንድ የበኩሉዎን አስተዎፆ ያድርጉ ‼️ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን ‼️ የቴሌግራም ቻናላችን ጆይን ሸር አድርጉ እንወያያለን እንማማራለን እንደራጃለን አብርን እናሸንፋለን አድራሻችን👇👇👇👇 https://t.me/httpsuYkZrGfSZrNjNjFk

"በሽምቅ እና መደበኛ ውጊያ ጥበብ አንታማም፤ ይህን ጥበብ የከተማ ውጊያ ላይም እንደግመዋለን" (ኮሎኔል ፋኖ ሞገስ ዘገዬ ከጳጉሜው የቃሊሙ ጀብዱ አንድ ሳምንት ቀደም ብሎ የተናገረው) ኮሎኔል ብላችሁ አትጥሩኝ "ፋኖ ሞገስ" ነው ስሜ ብሎ በቁጣ ተናግሮ ያውቃል። ኮሎኔል ሲሉት አይወድም። ሌሎች አቶ ሆነው ሳሉ ጄኔራልነት ያምራቸዋል፤ እሱ ግን ኮሎኔል ሆኖ ሳለ በወል ስም ፋኖ ብላችሁ ጥሩኝ አለ። ይህ ሰው ንፁህ እና ጀግና ነው። ምንም አይነት ግላዊ እና ቡድናዊ ፍላጎት የለውም። የእሱ ፍላጎት ህዝብ ተኮር ነው። የአማራ ህዝብን ማዳን እና ኢትዮጵያን ከመፍረስ መታደግ ይሻል። ሁሌም ይህን ዘረኛ ስርዓት ብሎ ነው ንግግር የሚጀምረው። ዘረኝነትን አጥብቆ ይጠላል። ለሁሉም ብሄር ብሄረሰቦችና ህዝቦች ልዩ ፍቅር አለው። እነሱ ቢበደሉ የእነሱ ፋኖ ይሆናል። እሱ እንዲህ ነው። ፍትሀዊ ነፍስያ ናት ያለችው። የተናገረው ነገር ንግግር ብቻ ሆኖ አይቀርም ይልቁንስ በተግባር ነው የሚታየው። ይህ ጀግና እጅጉን ታማኝ እና ሀቀኛ እንዲሁም ገራገር እና ደፋር ወታደር መሆኑን አብረውት የሰሩ እና የኖሩ ሁሉ ይመሰክራሉ። ኮሎኔል ሞገስ ዘገዬ ከምኒልክ ዕዝ ልዩ ዘመቻ ሰራዊት ጋር በነበረው ቆይታ ኮሎኔሉ ስለ ከተማ ውጊያ ተናግሮ ነበር። በሳምንቱ ቃሊም ከተማ ውስጥ የምኒልክ ዕዝ ሰራዊት ገብቶ ታላቅ የጦር ሜዳ ጀብዱ ፈፀመ። በዚያኑ ሰሞን ዋርካው ምሬ ወዳጆ "በቅርቡ ተአምር እንሰራለን" የሚል ፉከራ መሳይ ንግግር አድርጎ ነበር። አርበኛ አበበ ፈንታው ደግሞ "ትግሉ ህዝባዊ ነው" ብሏል። ህዝብ የፋኖን የማድረግ አቅም ገምግሞ ድጋፍ እየሰጠ መሆኑን አርበኛው መስክሮ ህዝባዊ መሰረት አለን ሲል አርበኛ ሔኖክ አዲሴ በበኩሉ "እናሸንፋለን" የሚል ምኞት መሳይ ንግግር ማድረጉን ልብ ይሏል። እነዚህ ንግግሮች እንግዲህ በወርሀ ነሀሴ መጨረሻው ሳምንት ላይ በተለያዩ መድረኮች የተደረጉ ናቸው። የአመራሮች ንግግር በተግባር የተተረጎመበት የጳጉሜው ድል አስደማሚ ነበር። በወቅቱ ማለትም አምና ልክ በዛሬው እለት በወሎ ቤተ አምሓራ ሰማይ ስር በሰሜኑ ክፍል ከወልዲያ እና ሳንቃ መሀል ተራራማይቱ ቃሊም ከተማ ውስጥ እነ ሞት አይፈሬ በጨለማ ዳብሰው ደመኛቸው የሆነውን የ48ኛ ክፍለ ጦር አንድ ሬጅመንት ሰራዊት በየማሽላው ውስጥ እየተከተሉ ሲለቅሙት አድረዋል። ቃሊም ከተማ ዙሪያዋን እንደተከከበበች ያወቀው ጠላት በከባድ መሳሪያ እገዛ ሊመክት ቢሞክርም ላታመልጭኝ አታሯሩጭኝ አይነት ነገር ገጥሞት የጨለማ ጥይት ሲሳይ ሆነ። ስትራቴጅክ የጦር ሰፈር ተብሎ የሚጠራውና ወያኔ ደርግ ጋር ሁለት ወር የተዋጋችበት በላጎ ተራራ አቅራቢያ የምትገኘውን ቃሊም ከተማን ለማትረፍ ከደጋ በላጎ ስትንቀዥቀዥ የመጣችው 48ኛ ክፍለ ጦር አንድ ሬጅመንት ሰራዊት ሰምጥ ትግባ ስርጥ ሳይታወቅ በአንድ ሰአት ልዩነት ብቻ ለቁጥር አዳጋች አባል እጅ ወደ ላይ ብሎ በሰልፍ ገቢ ሆኗል። እጅ አብሰጥም ያሉት በርካቶች ባሉበት ጭቃ ሆነዋል። የቆሰሉም አሉ። እስከ ሌሊቱ 9 ሰአት በዘለቀው የቃሊሙ ጦርነት 2 ሞርተር፣ 1 ዲሽቃ፣ በርከት ያሉ ብሬኖች እና ስናይፕሮች፣ ብዛት ያለው ክላሽ እና በሳጥን ሙሉ ሙሉ ተተኳሽ ለምኒልክ ዕዝ ገቢ ሆኗል:: ካምፕ ውስጥ ያለውን ጠቃሚ ነገር ሁሉ የያኔው የአማራ ፋኖ በወሎ (የዛሬው ምኒልክ ዕዝ) ፋኖዎች ቆጥረው ጭነዋል። 48ኛ ክፍለ ጦር መስከረም 2015 ዓ/ም በሰሜኑ ጦርነት ወቅት በበላጎ ግንባር የምስራቅ አማራ ፋኖ ሰራዊትን ስላስበላች በጥቁር ደም ስትፈለግ የነበረች ክፍለ ጦር ናት። የምስራቅ አማራ ፋኖ በመጨረሻው ዙር ወያኔ ጋር እንዳይዋጋ አድርገው ራያን ለትግሬ ሊሰጡ አስበው እነ ግርማ የሺጥላ በወልዲያው ውይይት ላይ ውሳኔ አሳልፈው ፋኖ በላጎ ተራራን ይልቀቅ ሲሉ ዋርካው ምሬ "አንለቅም" በማለቱ ይቺ ክፍለ ጦር እና በጄኔራል ሞሲሳ የሚመራው 105ኛ ልዩ ዘመቻ ሰራዊት በስተምዕራብ እና በጀርባ በኩል ሆነው አዋክበው በሴራ 31 ፋኖዎችን የሞሲሳ ኃይል ገድሏል። ክፍለ ጦሯ ወዲያው ከበላጎ ተነስታ አላውሀን ተሻግራ ስትጓዝ ሞሲሳም በልዩ ዘመቻ ሰራዊቱ እነ ሲላምላክ ደጉን እና ሌሎች በወቅቱ የአሳምነው ብርጌድ ጓድ የነበሩትን ጀግኖች ሲበላ ወያኔ የቀንየለይ ብላ ከተፍ አለች። ጀግናው ሰማዕት ሲላምላክ ደጉ በወቅቱ የአሳምነው ብርጌድ አስተዳደር እንደነበር ልብ ይሏል። በወንድሞቹ አምና ደሙ በደንብ ተመለሰለት። የአምናውን ውጊያ ንድፍ እነ ኮሎኔል ሞገስ ሰርተውት በዝነኛው አርበኛ በለጠ ሸጋው አዋጊነት ለማመን የሚከብድ ድል ነው የተመዘገበበት:: ይህ ጀግና ባለበት ግንባር ሁሌም ድል አለ። ማርሽ ቀያሪው ይሉታል ጓዶቹ። ቃሊም ከተማ ውስጥ አምና በጳጉሜ በሌሊት የተሰራው ጥንቅቅ ያለ ስራ የዋርካው ልጆች ስትራቴጅክ የጦር ሰፈር የተቆጣጠሩበት ድንቅ ተጋድሎ ነው። በላጎ ተራራ ማለት ወደ ሮቢት እና ጎብዬ እንድሁም ሳንቃ ከተሞች የሚያልፍን የጠላት ኃይል መቆጣጠሪያ ሲቱዌሽን ሩም ማለት ነው:: ከወልዲያ ወደ ባህርዳር የሚጓዘውን መንገድ ድልብ ላይ ለመቁረጥ የሚያስችል የጥቁር አስፋልት መቀስ የሆነ ተራራ መሆኑንም ልብ ይሏል። በላጎ ተራራ በወገን ኃይል ቁጥጥር ስር መግባቱ ወልዲያ ላይ ያለውን ጠላት ጭምር እረፍት ለመንሳት ያስችላል ተብሎ ስለሚታመን ነው ኦፕሬሽኑ የተሰራው። በኦፕሬሽኑ ሞርተር ተማርኳል፤ ሞርተር ደግሞ 16 ኪ/ሜ ድረስ ይመታል። የጠላት ክምችት ያለበትን ካምፕ እና ተግተልትሎ በኦራል የሚጓዝን ጠላት ድባቅ ለመምታት ሞርተር ተመራጭ ነው። የሞርተር ቅንቡላ የመታው ጠላት ሰውነቱ ተቦጫጭቆ ነው እንደ ቅጠል የሚረግፈው። በቃሊሙ ውጊያ የወንድሞቻቸውን ጀርባ ለጠበቁት መንገድ ቆራጭ የወገን ኃይል አባላትም አክብሮት መስጠት እና አብሮ ማስታወስ ተገቢ ነው። በተለይ የሰማዕቱ ጀግና (ሻለቃ ደምስ ይመር) ልጆች ወልዲያ ውስጥ ካሉ ካምፓች ጠላት እንዳይወጣ መንገድ ዘግተው ሲታኮሱ ነበር። ወደ ቃሊም አናስገባም ብለው የብረት አጥር ሆነው አድረዋል። የያኔው ልጅ እያሱ ክፍለ ጦር (የዛሬው ኮር) ኃይልም ሌላ ቦታ መንገድ ዘግቶ እንደነበር ሰምቻለሁ። የኮሎኔል ፈንታው አንጃ የሆነው ፅናት ክፍለ ጦር ጓዶችም ተመሳሳይ የወንድምነት እና ፋኖነት ስራ ሰርተዋል። መንገድ መዝጋት ደጀንነት ነው። ከተፋላሚው ወገን ያላነሰ አበርክቶ ነው። የጠላት ኃይል እብዳይጨመር ማድረግ የወገንን ሰራዊት ማትረፍ እና ጠላትን ነጥሎ ኃይሉን አሳስቶ ማስመታት ነው። የጨለማ ጥይት ሳይፈሩ በሞት ሸለቆ ውስጥ ተረማምደው አኩሪ ገድል ለፈጸሙ ወንድሞቻችን ያለኝን አክብሮት ዛሬም ለመግለጽ እወዳለሁ። የሀውጃኖ እውነተኛ ወንድሞች፣ የንጉሥ ሚካኤል አሊ የመንፈስ ልጆች እና የጄኔራል አሳምነው ጽጌ አምሳያ ወንድሞቻችን ሆይ በእናንተ ስራ መላው አማራ እና ሀገር ወዳድ ኢትዮጵያዊ ሁሉ እጅጉን እንደሚኮራ ልገልፅላችሁ እወዳለሁ። የቀራችሁ ነገር ቢኖር ድሉን መደጋገም ነው። 48ተኛን በመታችሁበት አግባብ ሌሎችንም ማቅመስ ከእናንተ ይጠበቃል። ሰሜን ምስራቅ ዕዝ፣ ደቡብ ዕዝ፣ 6ተኛ ዕዝ እንዲሁም የአየር ወለድ እና ኮማንዶ ዕዝ ወሎ ቤተ አምሓራ ውስጥ እንዳሉ ይታወቃል። የእነዚህ 4 እዞች ኃይል ለምኒልክ ዕዝ ነው የተመደበው። ምኒልክ ዕዝ 4 ዕዞችን እንደ ዘንዶ ውጦ ልናየው እንሻለን። ድል ለወንድሞቻችን። ዋግነር የአማራው ፋኖ በመወዳጀት መረጃዎቻችን በሁሉም አማራጭ ተደራሽ እንሆን ዘንድ የበኩሉዎን አስተዎፆ ያድርጉ ‼️

የአፋብኃ ማዕከላዊ ኮማንድ አባልና የምስራቅ አማራ ቀጠና ሚኒሊክ ዕዝ ሰብሳቢ ወንድማችን አርበኛ ምሬ ወዳጆ!! #ምሬ ጥላት አይምሬ! 🔥 💪 ዋግነር የአማራው ፋኖ በመወዳጀት መረጃዎቻችን በሁሉም አ
የአፋብኃ ማዕከላዊ ኮማንድ አባልና የምስራቅ አማራ ቀጠና ሚኒሊክ ዕዝ ሰብሳቢ ወንድማችን አርበኛ ምሬ ወዳጆ!! #ምሬ ጥላት አይምሬ! 🔥 💪 ዋግነር የአማራው ፋኖ በመወዳጀት መረጃዎቻችን በሁሉም አማራጭ ተደራሽ እንሆን ዘንድ የበኩሉዎን አስተዎፆ ያድርጉ ‼️ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን ‼️ የቴሌግራም ቻናላችን ጆይን ሸር አድርጉ እንወያያለን እንማማራለን እንደራጃለን አብርን እናሸንፋለን አድራሻችን👇👇👇👇 https://t.me/httpsuYkZrGfSZrNjNjFk

የዘመቻ ሰማዕታት ልዩ ታሳቢ የዳሞቱ ጦረኛ ነብዩ ጌትነት ማን ነው⁉️ የጀግኖቹ ጎሬ፣ የአናብስቱ ዋሻ ሲሻ ለመዋጋት፣ ሲከፋ መሸሻ እንዴት ነው ገውቻ፣  እንደምን ነው ሽምብጥ ነብይ ወላዶቹ በጭንቅ እና በምጥ …………………………………………… ተብሎ የተገጠመለት፣ የጎራ እና አድባሩ ክብር… የቀየው አውራ… የተከፋው ወገኑ ህመም ቀድሞ የሚያመው አንድ ከወገኖቹ ሁሉ ቀድሞ የነቃ  ጀግና በጎጃም ዳሞት ሰማይ ስር "#ነብይ" በሚል የተስፋ ትንቢት ስም ተወለደ። የአርበኛ  ነብዩ ጌትነት የትግል ህይወት በአጭሩ ከህይወት ታሪክ:-                                   ➾ አርበኛ ነብዩ ከአባታቸው  ከአቶ ጌትነት ደስታ እና ከእናታቸው ጥሩወርቅ አበባየሁ በ1972 ዓ.ም በቀድሞው ቆላ ደጋዳሞት አውራጃ በጃቢጠህናን ወረዳ በፍኖተ ሰላም ከተማ በሸበቁማ ቀበሌ ልዩ ስፍራው ብርብጥ በሚባል ጎጥ ተወለደ።   ➾አስተዳደጉ እንደማነኛውም የገጠር ልጅ በጎጃም ለምለም ሜዳዎች ስቆ ቦርቆ ተጫውቶ ካደገ በኃላ እንደ እኩዮቹ የአብነት ትምህርት ቤትገብቶ መማር ጀመረ።    ➾ የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርቱን በ1980 ዓ.ም በፍኖተ ሰላም ዕድገት በር ት/ቤት በመግባት ከ1ኛ -6ኛ ክፍል  ተምሮል። በመቀጠልም ከ1986 እስከ 1987ዓ.ም ቀ/ኃ/ስ ወይም ጁኒየር ከ7ኛ-8ኛ ክፍል ተምሯል ።    ➾የሁለተኛ ደረጃ ትምህርቱንከ1988 እስከ 1991 ዓ.ም በዳሞት አጠቃላይ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት 9ኛ-11ኛ ክፍል በመማር ወደ 12ኛ ክፍል ተዘዋውሯል።  ጀግናው አርበኛ ነብዩ   ሰው ወዳድ፣ተግባቢ፣ተጫዋች እና እጅግ አዛኝ ደግ ወጣት ነበር።   ➾ አርበኛ ነብዩ ባለትዳር ና የአንድ ወንድ ልጅ አበት ነው።   ➾ አርበኛው ሲበዛ ሀቀኛ፣ቅን፣ትሁት፣ክብር ጠባቂ፣ጀግና፣ቆራጥ፣ሚዛናዊ፣አብዛኛውን ጊዜ ከተከፋ እና ከተበደሉ ሰወች ጎን የሚገኝ የጀግኖች መለኪያ ነው ።    ➾ በወቅቱ የህወሓት መራሹ ኢህዲግን ስርዓት የፖለቲካ ብልሽት በልጅነቱ ቀድሞ የተረዳው የሚወደውን ትምህርት ትቶ የብቻውን ከስርዓቱ ሎሌወች ጋር ግብግብ በመግጠም ዱሩ ቤቴ በማለት ከ1993  እስከ 1999 ዓ.ም ጥር ድረስ ለ6 ዓመታት አንድ ሁኖ እንደሺህ ስርዓቱን አቀጥቅጦታል።     ➾አርበኛው አጅጉን እምነት የሚጥል በመሆኑ በጓደኛወ አቀናባሪነት/በመከዳት  በጥር 11/1999 ዓ.ም በወያኔ አገዛዝ እጅ ገባ። ➾ በወያኔ አሽከር ብዐዴን ተላልፎ ተሰጥቶ ለስምንት ዓመት  በሽብር ወንጀል በመከሰስ ከታሰረ በኋላ የካቲት 2007 ዓ.ም  ሲለቀቅ በቀጥታ ወደኤርትራ በረሃ ገብቶ ለ2 ዓመት ከህወሓት/ኢህአዴግ የግፍ አገዛዝ ጋር  በጨበጣ ታግሏል።   ➾ የፍኖተሰላምና አካባቢውን 2008 ዓ.ም  ሰርጎ በመግባት ህዝባዊ አመፁን  ያደራጀ የመራ እና ህዝቡ ቆርጦ በስርዓቱ ላይ እንዲነሳ ሰፊ ስራ ሰርቷል።  ከመስከረም 2009 ዓ.ም በኋላ ትግሉ ሙሉ በሙሉ በተደራጀ የትጥቅ ትግል መመራት እዳለበት ሲረዳ በኤርትራ ያለውን የትጥቅ ትግል አዲኃንን በመቀላቀል ቀጠለ።   ➾ የአምሓራ ህዝብ በኦህዴድ ኢህአዴግ ቁማር የተበላበት በስም  አገራዊ ለውጥ  በሚል ስም በኤርትራ የነበሩ አርበኞች ሲበተኑ ጷጉሜ 05/2010 ዓ.ም ወደ አገርቤት ገብቷል ። በ2011ዓ.ም ታህሳስ ወር  ጀነራል አሳምነው በጠራው ስልጠና ወደ ማርቆስ  ፖሊስ  ማሰልጠኛ ኮሌጅ  ለተኃድሶ በመግባት ለ3ወር የአማራ አድማብተና  ፖሊስ በመሆን ሰልጥኖ ጎደር ተመድቦ 3 ወር ከሰራ በኋላ የስርዓቱ ፈፅሞ አለመሸሻሉን ሲረዳ እና ቁልፍ የአምሓራ አዛዦች ሲገደሉ ግንቦት 2011ዓ.ም  ስራውን ለቆ ወደ ህቡዕ ትግል ገብቷል።     ➾ የህወሓት ጦርነት ከተጀመረ በኋላ  ዳግም የልዩ ኃይል ስልጠና በብርሸለቆ ማሰልጠኛ በመግባት ከህዳር 15/2013እስከ ታህስስ 28 /2013 ዓ.ም አንድ ወር ከአስራምስት ቀን በመሰልጠን በተከዜ ብርጌድ በ2ኛ ሻለቃ  ወስጥ ተመድቦ ታግሏል ።    ➾በ በማይጠብሪ ግንባር  ፣በፍየል ውሃ፣በዲማ እና ባማድሪ አኩሪ ገድል በመፈፀም አድናቆት  ሽልማት አግኝቷል ። በመጨረሻም በይፋ የአምሓራ ነፃ አውጭ ጦር ፋኖን በጎጃም ዳሞት ፍ/ሰላም ዙሪያ እያሰለጠነ አገዛዙን መዋጋት ቀጠለ።    ➾በ2014ዓ.ም በገዎቻ የፋኖ ስልጠና ያስተባብር አንዳንድ ልዩ ድጋፎችን ያደርግ የነበር ። ከፍኖተ ሰላም  ቅርብ እርጠት ላይ የሚገኘው '#ገዎቻ" ጫካ እና ነብዩን ለያይቶ ማየት ፈፅሞ ይቸግራል።      ➾ በ2015ዓ.ም ሀምሌ 25  በለዛው ውጊያ የተዋጋ እና 3ክላሽ በመማረክ ያስጠቀ።የቆሰለ ምርኮኛን በወታደራዊ ዲስፒሊን ተንባክቦ የሚያሳክም ነበር ።    ➾ስርዓቱ በፈረሰ ጊዜ የፍ/ሰላም ከተማ የተረጋጋች እድትሆን ጠንክሮ ሰርቷል። የፍ/ሰላም ማረሚያ ቤት ያለምንም ተኩስ ልውውጥ  እንዲሰበር ጉልህ  አስተዋፅዎ ከአደረጉት መካከል  በስም ተጠቃሹ  እና ዋናው ፋኖ ነበር።   ➾ በቡሬ ውድጊ ላይ ጦር መርቶ የገባ እና ከበባውን ሰብሮ አንድም አባል ሳይ ጎድል  ጓዶቹን ይዞ መውጣት የቻለ ኮስታራ ጀግና የታጠቀ ወታደር ነበር።   ➾በእራሱ ተነሳሽነት በጃቢጠህናን ውስጥ ያለውን ፋኖ ጷጉሜ 02/2015 ዓ.ም ሰብስቦ  በማወያየት  የዓባይ ብርጌድን በመመስረት የመጀመሪያው እዝና ሰንሰለትን ዘርግቷል ።   ➾ አርበኛ ነብዩ ብርጌድ በመሰረተበት እለት ጷጉሜ 02/2015 ዓ.ም ምሽት ላይ የጠላት ተልኮ ይዘው  ሰርገው በገቡ ባንዳወች ጦሩን እያዋጋ እና እያደራጀ ባለበት  ከጀርባው  በመመታት ተሰውቷል ። ጳጉሜ 3/2015 ዓ.ም በሪሃ ሰማይ እለተ ሩፋኤል ቀን የበቀለባት የዳሞትን አፈር ቀምሧል። እርሱ ያቋቋማትን የአማራ ፋኖ አባይ ብርጌድ፣ በስሙ "ነብዩ ጌትነት ብርጌድ" በሚል ለመሰየም እንቅስቃሴ የተጀመረ ሲሆን፣ ይህ ጀግና እንዳይረሳ፣ አብረውት የተዋደቁ እና ግብረ ጀብዱን የሚያውቁ፣ አሁን ላይ በጎጃም ፋኖ ቴዎድሮስ እዝ ውስጥ የሚገኙ ከፍተኛ ወታደራዊ አመራሮች የዚህ ጀግና መታሰቢያን አድምቀው እንዲያሳዩ፣ በሰራው ጀብድ እና አምሓራዊ መስዋዕትነት ተካካይ ክብረ መታሰቢያ እንዲኖረው የአርበኛው ቤተሰቦች አሳስበዋል። ጀግናን በልኩ ማንሳት እና በክብር ማሰብ፣ ለሌሎቹም ነገ ፍኖት ምሳሌነት ፈጣሪ ነው! ዘላለማዊ ክብር ለትግሉ ሰማዕታት !!! ድል  ለአማራ ፋኖ  !! ድል   ለአማራ     !! ዋግነር የአማራው ፋኖ በመወዳጀት መረጃዎቻችን በሁሉም አማራጭ ተደራሽ እንሆን ዘንድ የበኩሉዎን አስተዎፆ ያድርጉ ‼️ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን ‼️ የቴሌግራም ቻናላችን ጆይን ሸር አድርጉ እንወያያለን እንማማራለን እንደራጃለን አብርን እናሸንፋለን አድራሻችን👇👇👇👇 https://t.me/httpsuYkZrGfSZrNjNjFk

ኮንፈረንስ በተካሄደ ቁጥር ይህ ድርጊት ለምን? በየአመቱ በኢትዮጵያ የሚካሄደውን የአፍሪካ ህብረት የመሪዎች ስብሰባን ጨምሮ በጣም ብዙ አለም አቀፍ ኮንፍረንሶችን ከ10 ዓመት በላይ አዲስ አበባ ላይ በጋዜጠኝነት ተካፍያለሁ። ታድያ በዚህ ሁሉ ወቅት የከተማዋ ነዋሪዎች መንገድ ሲዘጋ በትራንስፖርት እጥረት ይንከራተቱ ይሆናል እንጂ ካለፈው አንድ እና ሁለት ዓመት ወዲህ እንደሚደረገው ዘግናኝ የሆነ አፈሳ እና ወደ ማጎሪያ ቦታ መጣል ሰምቼም፣ አይቼም አላውቅም። ከሰሞኑ በርካቶች በአዲስ አበባ ይካሄዳል የተባለውን የአፍሪካ የአየር ንብረት ጉባዔ፣ የአፍሪካ-ካሪቢያን ስብሰባ እና የግድቡ ምርቃት ተብሎ የዚህ ድርጊት ሰለባ እየሆኑ ነው። መሠረት ሚድያ እንደዘገበው አንዳንዶቹ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ወረዳ 5 ውሃ ልማት አካባቢ 200 ሜትር ገባ ብሎ በሚገኝ 'ማቆያ' በሚባል መጋዘን ውስጥ ተይዘው ይገኛሉ። ብትሩ በተለይ የኔ ብጤዎች እና በመንገድ ዳር ስራ ላይ የተሰማሩት ምስኪን ዜጎች ላይ ማረፉ ያሳዝናል። ለምሳሌ ዛሬ አዲስ ኮንቬንሽን ሴንተር እንግዳ ይመጣል ተብሎ ሚካኤል ቤተክርስቲያን አካባቢ ያሉ የኔ ብጤዎች በሙሉ ተጭነው ተወስደዋል። አንድ የአይን እማኝ እንዳለኝ "በአሁን ሰአት በአራት ፓትሮል በተኙበት እየቀጠቀጡ እንደ ኩንታል ማዳበሪያ እየጫኗቸው ነው፣ አካለ ጎዶሎ አልቀረ፣ የልጅ እናት አልቀረ።" ሌላ የደረሰኝ ምስክርነት እንዲህ ይላል: "አንድ የልጅ እናት ጨቅላ ልጇን አዝላ ከፀጥታ ሀይሎች ለማምለጥ  ስትሞክር ህፃኑ ወድቆ ጭንቅላቱ ተሰንጥቆ ደም በደም ሆኖ ፊቱ በደም ተሸፍኖ ነበር። ምስሉን በስልኬ ላስቀር ሞክሬ ፍርሀት ስላለ ተውኩት፣ ሰውን በተኑት።" ታድያ ኮንፈረንስ በተካሄደ ቁጥር ይህ ድርጊት ለምን? ዋግነር የአማራው ፋኖ በመወዳጀት መረጃዎቻችን በሁሉም አማራጭ ተደራሽ እንሆን ዘንድ የበኩሉዎን አስተዎፆ ያድርጉ ‼️ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን ‼️ የቴሌግራም ቻናላችን ጆይን ሸር አድርጉ እንወያያለን እንማማራለን እንደራጃለን አብርን እናሸንፋለን አድራሻችን👇👇👇👇 https://t.me/httpsuYkZrGfSZrNjNjFk

ጀግኖቻችን የእውነት አኮራችሁን! ❤ አርበኛ ዘመነን፤አርበኛ እንጅነር ደሳለኝን፤አርበኛ ምሬ ወዳጀ ዋርካው፤አርበኛ ሀብቴ ወልዲን እንዱሁም በአራቱ ማዕዘን ይሙቱ ይረሸኑ ያላለ የአገዛዙ ተላላኪና ባንዳ
ጀግኖቻችን የእውነት አኮራችሁን! ❤ አርበኛ ዘመነን፤አርበኛ እንጅነር ደሳለኝን፤አርበኛ ምሬ ወዳጀ ዋርካው፤አርበኛ ሀብቴ ወልዲን እንዱሁም በአራቱ ማዕዘን ይሙቱ ይረሸኑ ያላለ የአገዛዙ ተላላኪና ባንዳ የለምን ሆኖም ግን ፈጣሪ ይመሰገን ምስጋና የማይሳነው ፈጣሪ በእሱ ቸርነት አማራ በጀግኖች እንደ ሰው ሳይሆን እንደቸርነቱ ዛሬ ላይ ወደ ማይቀርው የድላችን ማማ እዚህ ላይ ደርሰዋል!! ከአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል መሪዎቻችን ጋር ወደ ፊት!! ዋግነር የአማራው ፋኖ በመወዳጀት መረጃዎቻችን በሁሉም አማራጭ ተደራሽ እንሆን ዘንድ የበኩሉዎን አስተዎፆ ያድርጉ ‼️ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን ‼️ የቴሌግራም ቻናላችን ጆይን ሸር አድርጉ እንወያያለን እንማማራለን እንደራጃለን አብርን እናሸንፋለን አድራሻችን👇👇👇👇 https://t.me/httpsuYkZrGfSZrNjNjFk

የአፋብኃ ማዕከላዊ ኮማንድ አባልና የምዕራብ አማራ ቀጠና ቴዎድሮስ ዕዝ ሰብሳቢ ወንድማችን አርበኛ ዘመነ ካሴ!! ሊያጠፋን የተነሳውን ጠላት በመመከት ማሸነፍ እንደምንችል አረጋግጠናል !! የዕጣፈንታች
የአፋብኃ ማዕከላዊ ኮማንድ አባልና የምዕራብ አማራ ቀጠና ቴዎድሮስ ዕዝ ሰብሳቢ ወንድማችን አርበኛ ዘመነ ካሴ!! ሊያጠፋን የተነሳውን ጠላት በመመከት ማሸነፍ እንደምንችል አረጋግጠናል !! የዕጣፈንታችን ወሳኞች እኛ ነን ብለን ስንነሳ የመናጆነት፣ የተከታይነት፣ የአጃቢነት ልማዶችን ሰብረን የአማራዊ ማንነታችን እና ፍላጎቶቻችን በአማራ ልጆች የሚወሰንበት ምዕራፍ ለመክፈት ነውና ጀምረነው ብዙ ርቀት ሔደናል። ዋግነር የአማራው ፋኖ በመወዳጀት መረጃዎቻችን በሁሉም አማራጭ ተደራሽ እንሆን ዘንድ የበኩሉዎን አስተዎፆ ያድርጉ ‼️ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን ‼️ የቴሌግራም ቻናላችን ጆይን ሸር አድርጉ እንወያያለን እንማማራለን እንደራጃለን አብርን እናሸንፋለን አድራሻችን👇👇👇👇 https://t.me/httpsuYkZrGfSZrNjNjFk

የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ      ጷግሜ 03/2017ዓ.ም ከትጥቅ ትግሉ ጎን ለጎን ህዝባዊ ውይይቶች ተጠናክረው ቀጥለዋል! የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል(አፋብኃ) ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ ግዙፉ ላስታ ጄኔራል አሳምነው ፅጌ ኮር ከሚያስተዳድራቸው ወረዳዎች አንዱ በዋግኸምራ አስተዳደር ዞን ጋዝጊብላ ወረዳ ላልኪው ቀበሌ አንዱ ሲሆን ከቀበሌው ማህበረሰብ ጋር በተለያዩ ጉዳዮች ዙሪያ ውይይት ማድረጉ ተነገረ። ጷግሜ 02/2017ዓ.ም የኮሩ ከፍተኛ አመራሮች በተገኙበት በተደረገው ህዝባዊ ውይይት የፋኖ ሰራዊት ከማህብተሰቡ ጋር ያለው ግንኙነት፣የሲቪል አስተዳደሩ ከህብረተሰቡ  እና ከሰራዊቱ ጋር ያለው ግንኙነት እንዲሁም የፍትህ አሰጣጥን በተመለከተ ሃሳቦች የተነሱ ሲሆን በተነሱ የመወያያ ሀሳቦች ዙሪያ የጋራ መግባባት ላይ በመድረስና የቀጣይ አቅጣጫዎችን በማስቀመጥ መጠናቀቁ ታውቋል። መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልውና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል ሲል የኮሩ ህዝብ ግንኙነት ኃላፊ ፋኖ ቢሆነኝ ቢያበይን መረጃውን አድርሷል! ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን!!! የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል (አፋብኃ) ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ        ጷግሜ 03 / 2017 ዓ.ም ዋግነር የአማራው ፋኖ በመወዳጀት መረጃዎቻችን በሁሉም አማራጭ ተደራሽ እንሆን ዘንድ የበኩሉዎን አስተዎፆ ያድርጉ ‼️ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን ‼️ የቴሌግራም ቻናላችን ጆይን ሸር አድርጉ እንወያያለን እንማማራለን እንደራጃለን አብርን እናሸንፋለን አድራሻችን👇👇👇👇 https://t.me/httpsuYkZrGfSZrNjNjFk

የአፋብኃ ማዕከላዊ ኮማንድ አባልና የደቡብ አማራ ቀጠና አሳምነዉ ዕዝ ሰብሳቢ ወንድማችን አርበኛ ኢንጂነር ደሳለኝ ሲያስብሸዋ!! ዋግነር የአማራው ፋኖ በመወዳጀት መረጃዎቻችን በሁሉም አማራጭ ተደራሽ
የአፋብኃ ማዕከላዊ ኮማንድ አባልና የደቡብ አማራ ቀጠና አሳምነዉ ዕዝ ሰብሳቢ ወንድማችን አርበኛ ኢንጂነር ደሳለኝ ሲያስብሸዋ!! ዋግነር የአማራው ፋኖ በመወዳጀት መረጃዎቻችን በሁሉም አማራጭ ተደራሽ እንሆን ዘንድ የበኩሉዎን አስተዎፆ ያድርጉ ‼️ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን ‼️ የቴሌግራም ቻናላችን ጆይን ሸር አድርጉ እንወያያለን እንማማራለን እንደራጃለን አብርን እናሸንፋለን አድራሻችን👇👇👇👇 https://t.me/httpsuYkZrGfSZrNjNjFk

🔥#እንመክራለን_እንወያያለን_እንደራጃለን‼️ የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል( አፋበኃ) ደቡብ አማራ ቀጠና አሳምነው እዝ በፍቃዱ በላይ ክ/ጦር አሳምነው ፅጌ ብርጌድ በሆማ ቦነያ ቀበሌ ሕዝባዊ ውይይቶች
🔥#እንመክራለን_እንወያያለን_እንደራጃለን‼️ የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል( አፋበኃ) ደቡብ አማራ ቀጠና አሳምነው እዝ በፍቃዱ በላይ ክ/ጦር አሳምነው ፅጌ ብርጌድ በሆማ ቦነያ ቀበሌ  ሕዝባዊ ውይይቶች አደረጓል ውይይቱን የአፋበኃ ደቡብ አማራ ቀጠና አሳምነው እዝ በፍቃዱ ክ/ጦር ፖለቲካ ዘርፍ ኃላፊ መ/ር አርበኛ ፋኖ በላቸው ዳኘ የመራው ሲሆን ስለ አገዛዙ እና ተልኮ ተቀብለው ሰርገው የሚገቡ ሃይሎችን በንቃት ተከታትሎ መያዝ እና በቀጠናው ለሚንቀሳቀሰው ለፋኖ አባለት ሪፖርተር ማድረግ እንዳለበቸው በጽኑ  መልክቱን ያስተላለፈ ሲሆን አየይዞም ስለ ሕዝባው አስተዳደር ጉዳይ ማብራሪያ ሰቷል በድረጅት አሰራር እና መርሕ እንጅ ማንም በዘመድ አዝማድ  የሚሰጥ ፍትሕ እንደሌለ ለሕዝቡ አስረድቷል። አክሎም ትግሉ ሕዝብን እና ሃገርን የማዳን እስከሆነ ድረስ ሕዝባችን እና አባት አርበኞች  እራሳችሁን የትግሉ አካል በማድረግ ጥፋተኛውን በመምከር አለፍ ሲልም ለይታችሁ በመያዝ  ነፃነታችንን በጋራ እንደናሰፍን ሲል በመድረኩ ለተሰበሰቡት አባት አርበኞች እና ሕዝብ መልክቱን አስተላልፏል‼️ ድል ለአማራ ፋኖ💪 ድል ለአማራ ሕዝብ💪 ክብር እና ሞገስ ለትግሉ ሰመአታት💔 ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን💪 አፋበኃ ደቡብ አማራ ቀጠና አሳምነው እዝ በፍቃዱ በላይ ክ/ጦር ፖለቲካ ዘርፍ ኃላፊ መ/ር አርበኛ ፋኖ በላቸው ዳኜ 03/13/2017 ዓ.ም ዋግነር የአማራው ፋኖ በመወዳጀት መረጃዎቻችን በሁሉም አማራጭ ተደራሽ እንሆን ዘንድ የበኩሉዎን አስተዎፆ ያድርጉ ‼️ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን ‼️ የቴሌግራም ቻናላችን ጆይን ሸር አድርጉ እንወያያለን እንማማራለን እንደራጃለን አብርን እናሸንፋለን አድራሻችን👇👇👇👇 https://t.me/httpsuYkZrGfSZrNjNjFk

~ ተጠናክሮ የቀጠለው ሕዝባዊ የምክክር መድረክ! የአማራ ሕዝብ የሕልውና ትግል ያለ ምንም እንከንና ተግዳሮት ከድሉ ጫፍ ይደርስ ዘንድ የትግላችን መሠረቶች ከሆኑ አካላት ጋር የሚደረጉ የውይይት መድረ
+2
~ ተጠናክሮ የቀጠለው ሕዝባዊ የምክክር መድረክ! የአማራ ሕዝብ የሕልውና ትግል ያለ ምንም እንከንና ተግዳሮት ከድሉ ጫፍ ይደርስ ዘንድ የትግላችን መሠረቶች ከሆኑ አካላት ጋር የሚደረጉ የውይይት መድረኮች፣ ስልጠናዎችና የግንባታ ትምሕርቶች ተጠናክረው ቀጥለዋል። ከእነዚህ መሠረቶች መካከል ሕዝባችን ቀዳሚው ነው። በዛሬው ዕለትም  የአፋብኃ ምዕራብ አማራ ቀጠና ቴወድሮስ ዕዝ ቀኝ ጌታ ዮፍታሄ ንጉሴ 6ኛ ክፍለ ጦር በረኸኛው ጅበላ ሙተራ ብርጌድ በማይ አንገታም ቀበሌ ከሚኖረው  ማህበረሰብ ጋር በትግላችን መሠረታዊ ጉዳዮችና በወቅታዊ ሁኔታዎች ዉይይት አድርጓል። በውይይቱ ለቀበሌው ማሕበረሰብ የግንዛቤ ማስጨበጫ ትምሕርት የተሰጠ ሲሆን በቀጣይ ማሕበረሰቡ ትግሉን በሁለንተናዊ ዘርፍ የሚደግፍበትንና በትግሉ ስለ ሚኖረው ሚና አቅጣጫ ተሰጥቷል። ቀኝ ጌታ ዮፍታሄ ንጉሴ 6ኛ ክፍለ ጦር በረኸኛው ጅበላ ሙተራ ብርጌድ ዋግነር የአማራው ፋኖ በመወዳጀት መረጃዎቻችን በሁሉም አማራጭ ተደራሽ እንሆን ዘንድ የበኩሉዎን አስተዎፆ ያድርጉ ‼️ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን ‼️ የቴሌግራም ቻናላችን ጆይን ሸር አድርጉ እንወያያለን እንማማራለን እንደራጃለን አብርን እናሸንፋለን አድራሻችን👇👇👇👇 https://t.me/httpsuYkZrGfSZrNjNjFk

አማራ ነኝ የጀግኖችም ዘር ነኝ ለምን አትበለኝ ተወደደም ተጠላም ፈለክም አልፈለክም ተቀበልክም አልተቀበልክም አመንክም አላመንክም!! ተመቸህም አልተመቸህም መጭው ግዜ የአማራ ፋኖ ዘመን ነው አማራ ማ
አማራ ነኝ የጀግኖችም ዘር ነኝ ለምን አትበለኝ ተወደደም ተጠላም ፈለክም አልፈለክም ተቀበልክም አልተቀበልክም አመንክም አላመንክም!! ተመቸህም አልተመቸህም መጭው ግዜ የአማራ ፋኖ ዘመን ነው አማራ ማንንም ሳይለማመጥ የማንንም እርዳታ ሳይፈልግ የትኛውንም ምድራዊ ሴራ እየበጣጠስ ከሀይል ወደ ሀይል ይሽጋገራል ጠላት አይኑ እያየ ጆሮው እየስማ አማራ ያሽንፋል ቃሌ ነው✊ #ድል ለመላው የአማራ ፋኖ🔥🔥 #ድል ለስፌው የአማራ ህዝብ💚💛❤️ አድስ ትውልድ!! አድስ አስተሳስብ!! አድስ ተስፋ!! ክፋት ለማንም በጎነት ለሁሉም😍 ዋግነር የአማራው ፋኖ በመወዳጀት መረጃዎቻችን በሁሉም አማራጭ ተደራሽ እንሆን ዘንድ የበኩሉዎን አስተዎፆ ያድርጉ ‼️ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን ‼️ የቴሌግራም ቻናላችን ጆይን ሸር አድርጉ እንወያያለን እንማማራለን እንደራጃለን አብርን እናሸንፋለን አድራሻችን👇👇👇👇 https://t.me/httpsuYkZrGfSZrNjNjFk

ሰበር_ወለጋ‼ ፨፨፨፨፨፨፨፨ ሆሮ ጉዱሩ ወለጋ ዞን አቤደንጎሮ ወረዳ ጫንጮ ቀበሌ ለግዜው ቀዝቀዝ ብሎ የነበረው ከባድ ጦርነት መከላከያ ትናንትና ማታ ሀይል በማስጨመርና ወደ ቦታው ማቅናቱን ተከትሎ ዛሬ በጧቱ ጀምሮ በከባባድ መሳርያ የታገዘ ከባድ ጦርነት መጀመሩን የአካባቢው ኗሪዎች ለቢዛሞ ሚዲያ ገልጸዋል‼ ጳግሜ 03/2017ዓ.ም    ዋግነር የአማራው ፋኖ በመወዳጀት መረጃዎቻችን በሁሉም አማራጭ ተደራሽ እንሆን ዘንድ የበኩሉዎን አስተዎፆ ያድርጉ ‼️ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን ‼️ የቴሌግራም ቻናላችን ጆይን ሸር አድርጉ እንወያያለን እንማማራለን እንደራጃለን አብርን እናሸንፋለን አድራሻችን👇👇👇👇 https://t.me/httpsuYkZrGfSZrNjNjFk

ሲቀልዱበት የነበሩትን የሞባይል ካሜራ አስይዞ ጨረቃን ሲያስቀርፃቸው አስመሸ። ታዋቂው የፊዚክስ ሊቅ አልበርት አንስታይን እ.ኤ.አ በ1905 አዲሱን የአንፃራዊነት ፅንሰ ሃሳብ (Relativity theory) በጊዜው ለነበሩ ሰዎች ሲያስተዋውቅ ሰዎቹ ተረት ተረት ነው ብለው ስቀውበት ነበር። የሚገርመው መብሰላቸው ላይቀር ማገዶ መፍጀታው ነው። አንስታይን ሊያስረዳቸው ሞከረ እነሱ ግን ሳቁበት። ቀለል አድርጎ በምሳሌ ነገራቸው እነሱ ግን አፌዙበት። ነገር ግን እያደር ፅንሰ ሀሳቡ እየገባቸው መጣ። ሳቃቸውን በራሳቸው ላይ አደረጉ። በእሱ ግን ተደነቁ። አጨበጨቡለት፤ የኖቤል ሽልማትን ሸለሙት። በስነፈለግ ሳይንስ የሚከሰቱ የተፈጥሮ ዑደቶችን አስመልክቶ መጋቤ ሀዲስ ዶ/ር ሮዳስ ታደሰ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያንን አቡሻህር መነሻ አድርጎ የዛሬ 6 ዓመት አካባቢ ደቂቃና ሰዓት ጠቅሶ በጳጉሜ 2/2017 ዓ.ም የጨረቃ ግርዶሽ በኢትዮጵያና በተወሰኑ የአለማችን አካባቢዎች ላይ እንደሚከሰት ተናግሮ ነበር። ነገር ግን ይህ ነው ተብሎ ሊነገር የሚችል አንዳች የሆነ ነገር የሌላቸው ባዶዎች ንግግሩን ተረት ተረት ነው ብለው ሲያጣጥሉ፣ ተምረናል ባይ ቀለም ቅቦች ደግሞ ሲሳለቁበት እንደነበር የቅርብ ጊዜ ትውስታችን ነው። የሳቃቸው ምንጭ ሳይንሳዊ እውቀት አልነበረም። ጥላቻና ድንቁርና ብቻ ነበር እንጂ። ዛሬ ቀኑ ደርሶ በአንድ በኩል ባዶ ቆርቆሮዎቹ ሮዳስ የተናገረው ካልተሳካ አፋቸውን በእሱ እና በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ላይ ሊከፍቱ፤ በሌላ በኩል ያሉት ደግሞ ዶ/ር ሮዳስ የተነበየውን ትንቢት በጉጉት ሊመለከቱ ተዘጋጅተው ሳሉ ተፈጥሮ ሰዓቷን ጠብቃ የጨረቃን ቀለም መቀየር ጀመረች፤ ቆየት ብላም በመሬት ጋረዳቻት በዚህም የአቡሻህርን ቀመር ትክክለኛነት የዶ/ር ሮዳስን ትንቢት እውነተኛነት አረጋግጣለች። ይህ ዛሬ የሚታዩ ዘመናዊ የስነፈለግ መተንበያ መሳሪያዎች ሳይሰሩ፣ አሜሪካ ሳትፈጠር፣ ናሳ ሳይቋቋም፣ ኢንተርኔት ሳይታሰብ ከ1800 ሺ ዓመታት በፊት የተሰራ ቀመር ነው። ከክስተቱ በኋላ ባዶዎቹ በተበሳጨ ስሜታቸው የጨረቃ ግርዶሽ ጥቅሙ ምንድነው ወደሚል ጥያቄ ተሸጋግረው እያየንና እየታዘብን ነው። መቼስ ለመብላት የሚኖር ስለሆዱ አካባቢ ቢያወራ የሚገርም ባይሆንም የጨረቃ ግርዶሽ ጥቅሙ ምንድነው የሚል ሁሉ የሚከተሉትን የመፅሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች ማለትም የሐዋ ሥራ 2፥20 እና ራዕ 6፥12ን ያነብ ዘንድ እጋብዘዋለው። ነገር ግን ከጨረቃ ግርዶሹ ጀርባ አብዛኞቻችን ኢትዮጵያዊያን ደስ ያለን ዓለም የተለያዩ ዘመናዊ መሳሪያዎችን ተጠቅሞ የሚያውቀውን የስነፈለግ ክስተት አባቶቻችን አቡሻህር በተሰኘ ቀመር ማወቅ በመቻላቸው ነው። ደስታችን አገር በቀል በሆነው እውቀት ነው። እናም ወዳጄ መስራት ባትችል እንኳን የሚሰሩ ኦጆችን አክብራቸው። የሰራሃቸው ከሌሉ እንኳን የተሰሩትን ተቀበላቸው፤ አክብራቸውም። የዘመን አቆጣጠራችን፣ ከመስከረም እስከ ጳጉሜ ያሉ ወሮቻችን፣ ከሰኞ እስከ እሁድ ያሉ ቀኖቻችን፣ ከሴኮንድ እስከ ደቂቃ ያሉ ሰዓቶቻችን የምንኮራባቸው የአገር በቀል እውቀት ትሩፋቶቻችን ናቸው። ወገን ቆም ብለን እናስብ። አውሮፓዊቷ ኃያል አገር ጀርመን በላይብዝሽ ዩኒቨርሲቲዋ ውስጥ ለምን የግዕዝ ቋንቋን እንደምታስተምር ያወቀ ግን አለ? ኢትዮጵያዊ ተብለህ ቂጥህን ወትፈህ በየሚዲያው በአገር ሀብትና እሴት ላይ አሽሟጥጥ፣ ይወገዱ ይጥፉም በል። ምንም የሌላቸው ባዶዎች በጥላቻቸውና በድንቁርናቸው እንቁዎቻችንን እያጣጣሉ የማንነትና የሞራል ውዳቂዎች እንድንሆን ብዙ እየጣሩ ነው። ትኩረት ለአገር በቀል እውቀትም። ዋግነር የአማራው ፋኖ በመወዳጀት መረጃዎቻችን በሁሉም አማራጭ ተደራሽ እንሆን ዘንድ የበኩሉዎን አስተዎፆ ያድርጉ ‼️ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን ‼️ የቴሌግራም ቻናላችን ጆይን ሸር አድርጉ እንወያያለን እንማማራለን እንደራጃለን አብርን እናሸንፋለን አድራሻችን👇👇👇👇 https://t.me/httpsuYkZrGfSZrNjNjFk