ru
Feedback

Не попадитесь на канал ботавода! Telemetrio находит и помечает такие каналы 👉 Хотите видеть метку — оформите подписку 👈

ፍኖተ-አሻራ ሚዲያ (Finote Ashara Media)

ፍኖተ-አሻራ ሚዲያ (Finote Ashara Media)

Открыть в Telegram

የተመሠረተው የአማራን ሕዝብ ለማንቃት፣ ለማደራጀት እና ለማስተባበር ነው። የአማራ ሕዝብን ✅ ፖለቲካዊ ✅ ማህበራዊ ✅ ኢኮኖሚያዊ ታሪካዊ ጥያቄዎችን ለማሰማት እና የአማራን ሕዝብ በማንቃት ሰፊውን ሕዝብ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ይሰራል። ወደዱም ጠሉም የኃላ ታሪካችን በእኛ እጅ ይፃፋል። አማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ ( አፋብን)

Больше
4 133
Подписчики
Нет данных24 часа
+4247 дней
+1 14930 дней
Архив постов
የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኅይል (አፋብኅ) በየጊዜው እያሳዬ ያለው የፖለቲካና የስነልቦናዊ ግንዛቤ ሥልጠናዎች እንዲሁም የመዋቅርና የአስተዳደር አደረጃጀቶችን የማጠናቀር ሂደት ይበልና ተጠናክሮ ይቀጥል የሚያሰኝ ነው የአፋብኅ አመራሮች በየወቅቱ እያደረጉት  ያለው በሳል አመራር የአማራንና የፋኖን ትግል የሚደግፉ ወገኖችን እያኮራ ሲሆን በጠላት ሰፈር ደግሞ ድንጋጤንና ሽብርን ፈጥሯል መንግሥት ተብየው ብልፅግና በመቶ ሚሊዮን ብር የሚገመት ወጪ እየከፈለ በሶሺያል ሚዲያና በመንግሥት የመገናኛ አውታሮች ፕሮፓጋንዳውን ቢቀጥልም በመሬትና በውጊያው ቦታ ያለው እውነታ ግን ብልፅግናን እንቅልፍ እየነሳው ይገኛል በየቀኑ በመቶዎች የሚቆጠሩ የብልፅግና ወታደሮችና ሚሊሻዎች ለአፋብኅ እጅ እየሰጡ ሲሆን በሌላ በኩል ደግሞ በሺዎች የሚቆጠሩ ምርኮኞችና ህይወታቸውን እያጡ ይገኛሉ በተጨማሪ ከአገዛዙ ጋር ሆነው በባንዳነት ብልፅግናን የሚያገለግሉ ባንዳዎችና ሆዳሞች ለምሳሌ የደብረሲናው ከንቲባ አይነት አድርባዮች የማይቀረውን የአማራን ሕዝብ ቅጣት እየተቀበሉ ይገኛሉ ትግሉ ወደመጨረሻው የድል ጉዞ እየሄደ ለመሆኑ ዋና ማመላከቻ ደግሞ በማስመሰል ከአማራ ሕዝብ ጋር እንታገላለን እያሉ የብልፅግናን አላማ በተዘዋዋሪ ለማሳካት በፋኖ መሀል ተሰግስገው የነበሩ ባንዳዎች ተልእኮአቸው አልሳካ ሲል አንድ በአንድ በየቀኑ የአማራን ትግል እንዲያፈርሱ ከላካቸው አባት ፖርቲያቸው ብልፅግና ጉያ ተመልሰው እየገቡ ይታያሉ እነኝህ ግለሰቦች በፋኖ ውስጥ በነበሩበት ወቅት ምንም ተከታይ እንደሌላቸው የሚያሳየው ማስረሻ ሰጤ ብልፅግና ጋ ተመልሶ ሲገባ የተከተለው አብረው የነበሩት የፋኖ ተዋጊዎች ሳይሆኑ ጌታዋን ተከትላ የምታድረው አንዲት ውሻው ብቻ ናት መቅለልና መዋረድ ማለት ይኸ ነው የአፋብኅ አመራሮች በአሁኑ ወቅት ሌት ተቀን በትእግስትና በሰከነ መንገድ አንድ ወጥ ፓለቲካዊ አስተዳደራዊና ወታደራዊ መዋቅር ለመመስረት እያደረጉ ያሉበት ሂደት ደግሞ ለብልፅግናና ተከታዮቹ ድንጋጤን የአማራንና የፋኖን ትግል ለሚደግፉት መላ ኢትዮጵያውያን ደግሞ ደስታን እየፈጠረ ይገኛል ያለ ጥርጥር የአፋብኅና የአማራ ትግል ያቸንፋል

206ኛ ኮር ትምህርትን ለማስጀመር ከመምህራንና ከርዕሰ መምህራን ጋር እያደረገ ያለው ውይይት የአረመኔው ሰራዊት በመምህራን ላይ በሚያደርገው አፈናና እስር ምክንያት ተደናቅፏል። ጥር 8/ 2018 ዓ.ም =================================== የ206ኛ ኮር በድርጅቱ በአፋብኃ መመሪያና ደንብ መሰረት ትምህርትን በተመለከተ ባቀረበው ጥናታዊ ሰነድ ተንተርሶ 206ኛ ኮር የመማር ማስተማሩን ሒደት ለማጀመር ከባለ ድርሻ አካላት ጋር ውይይት እያደረገ ሰንብቷል። ከሩ በሚንቀሳቀስባቸው ባሉ ሁሉም ወረዳዎች መምህራንን በማወያየትና ሰነዱን ለታሳታፊዎች በማቅረብ ትምህርትን ለማስጀመር የጋራ ኮሚቴ አቋቁሙ ወደ ስራ በሚገባበት ወቅት የአረመኔው ስርዓት መምህራንን በማፈን ደሞዛቸውን በመንጠቅ ከፍተኛ በደል እየፈፀመባቸው ይገኛል። ኮሩ በተቆጣጠረባቸው ቀጠናዎች በአረመኔው ሰራዊት የፈራረሱ ትምህርት ቤቶችን ጨምሮ አገልግሎት የሚሰጡ የጤና ተቋማትን ክፍት በማድረግ መምህራን እንዲጎበኙ ሲሆን የህዝብ አገልግሎት ሰጭ ተቋማትን በልዩ ሁኔታ ጥበቃ በሚያደርገው 206ኛ ኮር ቀጠና ባንኮች፣ ጤና ጣቢያዎችና የንግድ ተቋማት ለህዝብ ክፍት ሁነው አገልግሎት ሲሰጡ መምህራን ተዘዋውረው ተመልክተዋል። የትግላችንን አላማ በማጠልሸት የተጠመደው የብልፅግና ተራ ፕሮፓጋንዳ በገሀድ መጋለጥ ሲጀምር መምህራንን በማሰርና በማሰቃየት ተጀምረው የነበሩ እንቅስቃሴዎችን አደናቅፏል ። ኮሩ ከሚመለከተው አካል ጋር በመወያየት ዘላቂ መፍትሔ ለማምጣት የሚያደርገውን ሙከራ አጠናክሮ የሚቀጥል ሲሆን ተከታታይ የውይይት መድረኮችን በማዘጋጀት ለተለያዩ ባለ ድርሻ አካላት ጥሪ ያደርጋል። አዲስ ትውልድ! አዲስ አስተሳሰብ! አዲስ ተስፋ የአፋብኃ ቴዎድሮስ ዕዝ 206ኛ ኮር ህዝብ ግንኙነት

አጋልጥ! የብርጌድ አደረጃጀት የተቀየረው ሰኔ 2017 ዓ.ም ነው። ከሰሞኑ በደብረብርሃን ዙሪያ ከፍተኛ ጡጫ ያስተናገደው አገዛዙ በዲጅታል ሚድያዎቹ አማካኝነት የሀሰት ፕሮፖጋንዳ እየነዛ ይገኛል። በአ
አጋልጥ! የብርጌድ አደረጃጀት የተቀየረው ሰኔ 2017 ዓ.ም ነው። ከሰሞኑ በደብረብርሃን ዙሪያ ከፍተኛ ጡጫ ያስተናገደው አገዛዙ በዲጅታል ሚድያዎቹ አማካኝነት የሀሰት ፕሮፖጋንዳ እየነዛ ይገኛል። በአፋብኃ ደቡብ አማራ ቀጠና አሳምነው ዕዝ ስር የሚገኙ ክ/ጦሮች ሰኔ 2017 ዓ.ም ከአፋብኃ በወረደ የአደረጃጀት መመሪያ መሰረት የብርጌድ አደረጃጀት ቀርቶ ሻለቃ ከዛም ክ/ጦር እንደሆን ተደርጓል። ስለሆነም አንበሳው ብርጌድ የሚባል አደረጃጀት በአሳምነው ዕዝ ስር የለም። ውሸትም ልክ አለው!

ትግሉ ሲጀመር ሠራዊት ገንብቶ የፀና ሃሳብ ይዞ የገባው የመጨረሻውን የድል ዋንጫ ያነሳል። የfacebook አካውንት እና ወ.ዘ.ተ...አጀንዳዎች ይዞ የገባው አይፀናም።   ገና ዙሩ እየከረረ ጨዋታው አማራዊ የጀግንነት  ስነልቦናን፣ መልካም ስብዕናን፣ አዕምሮን ፣ አቅምን እና ተዓማኒነትን የሚጠይቅበት ውስብስብ ደረጃ ላይ  እየደረሰ እየመጣ ስለሆነ  ..... የሚጠበቅ ነው። ...ማንም ይሁን ማን (ነጋዴ ይሁን ደላላ) የአጭበርባሪነት ባህሪ ያለው ግለሰብ ሆነ ቡድን በትግሉ ውስጣዊ ጉዳይ በመግባት ትግሉን በመጥለፍ  የሚፈልጉትን ግላዊ አጀንዳ በማስፈፀም ትግሉን እና መሪዎችን compromise በማድረግ በታትኖ በችርቻሮ  ለጠላት አሳልፎ ለመሸጥ  የተለመደ የሽቀጣ ፍላጎት ያለውም የትም አይደርስም።  የደንባራ እና ፋራ  ብዓዴን አመራሮች ላይ የተለመደች "ሿሿ"  በዚህ ትውልድ ትግል ላይ ቦታ የላትም። የእያንዳንዱን ፍላጎት  በፈርጅ በፈርጁ map ማድረግ ላይ ሰነፍ እንዳልሆንንም መታወቅ አለበት። ©በዛብህ

ሁለት ቃኝ እና መሀንዲስ የአገዛዙ ሰራዊት ፋኖን ተቀላቀሉ። ጥር 08/2018 ዓ.ም 1ኛ.ኤሊያስ ጫሌ.... አዳነ ከ6ኛ ዕዝ 602 ኮር 75ኛ ክፍለ ጦር 5ኛ ሬጅመንት 64ኛ ክ/ጦር ከእነማይ ወረዳ
+3
ሁለት ቃኝ እና መሀንዲስ የአገዛዙ ሰራዊት ፋኖን ተቀላቀሉ።        ጥር 08/2018 ዓ.ም 1ኛ.ኤሊያስ ጫሌ.... አዳነ ከ6ኛ ዕዝ 602 ኮር 75ኛ ክፍለ ጦር 5ኛ ሬጅመንት  64ኛ ክ/ጦር ከእነማይ ወረዳ 2ኛ. መኳንት መላኩ....25ኛ ክ/ጦር 3ኛ ሬጅመንት ከሰዴ ወረዳ 54ኛ ክ/ጦርን  የተቀላቀሉ ሲሆን አገዛዙ በአማራ ላይ እያካሄደ ያለውን አስነዋሪ ተግባር እና ስራ በማስጠላቱ ጥር 08/2018 ዓ.ም  የአፋብኃ ቴዎድሮስ ዕዝ 201ኛ ኮር 64ኛ እና 54 ክፍለ ጦርን ተቀላቅሏል። አዲስ ትውልድ፣ አዲስ አስተሳሱብ፣ አዲስ ተስፋ!! የቴወድሮስ ዕዝ 201ኛ ኮር ህዝብ ግንኙነት

ከድርጅታዊ እርምጃ ያመለጡ ሌቦች እንጅ ፋኖዎቻችን አልጠፉንም!! ዛሬ በጠዋቱ የብልፅግና ሳይበር ሚሊሾች ከወደ ሸበል በረንታ ፋኖ እጅ ሰጠ የሚል ዜና ይዞ ብቅ ብሏል። ዜናው ለብልፅግና ሰይበር ሚሊሾች በደስታ ያስፈነጠዘ እንደሆነ ያስታውቃል። ምክንያቱም በአባኮስትር መንደር ክላሽ አንከርፍፎ እጅ የሚሰጥ ፋኖ ፍለጋ ቢኳትኑም ሳይሳካላቸው ቀርቷል። ለማለዳው የብልፅግና ድራማ ተዋናይ ፎቷቸው የተለጠፉ አራቱ ሰዎች በህግ ማስከበር እርምጃ ከተወሰደባቸው ያለው ብዙነህ እና ጎዶቹ ጋር በመሆን በፋኖ ላይ ጥቃት በመፈፀም እና ለጠላት መረጃ ሆነው በደራና ወሎ በረሃማ ቦታዎች እየተንቀሳቀሱ ህዝብን ሲያሰቃዩ ከነበሩት ሽፍቶች መካከል ናቸው።ወደጠላት ሲሄዱ በኋላ ደጀናችን በተደረገባቸው የተኩስ ልውውጥ ከሞቱት በተጨማሪ ፎቶው ላይ ከሚታዩት አንደኛው ቁስለኛ ነው።ከነዚሁ ሌቦች ጋር ግንኙነት በመፍጠር ሰው በማገት፣ እና ዘረፋ ላይ የነበሩትንም 64ኛ ክ/ጦር በቁጥጥር ስር አውሎ ምርመራ እያደረገ ይገኛል። ይህን እውነት ሙሉ የሸበል በረንታ ህዝብ የሚያውቀው ሃቅ ቢሆንም አይናችሁን ጨፍኑና ላሞኛችሁ የሚለን የሸበል በረንታው ብልፅግና ፋኖ እጅ ሰጠኝ ለማለት የፋኖ ዩኒፎርም አልብሶ ፎቶ ሲያዘዋውር አርፍዷል። እውነታውን ለሸበል በረንታ ህዝብና ለ64 ክ/ጦር ሰራዊት እንተወውና በብልፅግና ዘገባ የተወዛገባችሁ በአባኮስትር ቀየ ለጠላት ክላሽ አንከርፍፎ በሰልፍ እጅ የሚሰጥ ፋኖ እንደሌለ እና እንደማይኖርም ማሳወቅ እንወዳለን። መረጃው የ64ኛ ክ/ጦር ሕዝብ ግንኙነት ነው።

ሰበር- የደብረሲና ከተማ ከንቲባ ወንድምሲገኝ ማሙዬ እርምጃ ተወስዶበታል። የፋኖ ሰርጂካል ኦፕሬሽን ምድብተኞች ታላቅ ድል ተቀዳጅተዋል። ዝርዝሩን ይዘን የምንመለስ ይሆናል። የቴሌግራም ገፃችን👉
ሰበር- የደብረሲና ከተማ ከንቲባ ወንድምሲገኝ ማሙዬ እርምጃ ተወስዶበታል። የፋኖ ሰርጂካል ኦፕሬሽን ምድብተኞች ታላቅ ድል ተቀዳጅተዋል። ዝርዝሩን ይዘን የምንመለስ ይሆናል። የቴሌግራም ገፃችን👉

😂😂😂😂ታግተው ደብዛቸው የጠፋው የደምቢዶሎ አማራ ልጃገረድ ተማሪዎችን የት ቀቅሎ እንደበላ መልስ ሊሰጥ ዛሬ ሲኦል ገብቷል ቅዳሜለት መርዝ አብልቶ ወደ ዲሲ የልኡካን መሪ አርጎ የላከው አብይ አ
😂😂😂😂ታግተው ደብዛቸው የጠፋው የደምቢዶሎ አማራ ልጃገረድ ተማሪዎችን የት ቀቅሎ እንደበላ መልስ ሊሰጥ ዛሬ ሲኦል ገብቷል ቅዳሜለት መርዝ አብልቶ ወደ ዲሲ የልኡካን መሪ አርጎ የላከው አብይ አመድ እንደ አይጥ በመርዝ ገሎታል ፦ እስከ ዛሬ አብይ አመድ በመርዝ የገደላቸው አበረ አዳሙ ማዲንጎ ኢሄ ሰውዬ ወዘተ ⚫️▪️😂😂😂😂😂

ማንነት ለምን ይጠፋል? ( "Why a Nation Extenict?") =============================== አንድ ህዝብ ራሱን ከዘር መሳሳትና ከመጥፋት ለመከላከል የሚያደርገው ተጋድሎ ተፈጥሮዊ ብቻ ሳይሆን ፍትሐዊ ጭምር ነው። ራሳቸውን ከተገዳዳሪያቸው አካላዊ ጥቃት (Direct violence ) እና መዋቅራዊ ጥቃት ( Structural violence ) መከላከል ባለመቻላቸው ብዙ የራሳቸው ቋንቋ ፣ ታሪክና እሴት ያላቸው የጎሳ መደቦች (ethnic groups ) እንደጠፉ ታሪክ አስነብቦናል። ዛሬ ዘመን ኦሮምያ በሚባለው ከባቢ ከደርዘን በላይ ጎሳወች እንደጠፋ በኢትዮጵያ ረጅሙ ታሪክ ውስጥ ከአንድ ድርዘን በላይ ጎሳወች ጠፍተዋል። ለአብነትም በዛሬው አዋሽ ዙሪያ እስከ ደብረ ዘይት ማያ የሚባሉ ጀግና ቀስተኛ ህዝቦች ፣ በዛሬው ሰላሌና ወለጋ ዙሪያ ጋፋት የሚባል ማህበረሰብ እንደተዋጠ ታሪክ አረጋግጦልናል። የአልጠረጠረ ተመነጠረ እንደተባለው ማንነቱን ያልተንከባከበ እና ከወራሪወች ያልጠበቀ ሁሉ መጥፉቱ የማይቀር ነው። ህልውና የሐይል ሚዛን (Power Balance) ጉዳይ ነው የሚባለው ከዚህ ተጨባጭ ጉዳይ አንፃር ነው። አለም የሐያሎች ወይም ሐያላን ተስማምተው የሚኖርባት ፍትህ አልባ እውነት ናት። አንድን ህዝብ ለመጥፋት የሚዳርጉት 6 ዋና ዋና ተፅኖወች አሉ:- 1. ቅኝ ግዛትና ወረራ (Colonization and Conquest ) 2. የተፈጥሮ አደጋ (Environmental Catastrophe ) 3. የማንነትና ሉዓላዊነትን መጣስ /መጥፋት ( Loss of Identity & Sovereignty ) 4. የህዝብ ቁጥር መቀነስ (Depopulation ) 5. የፖለቲካ ቀውስ ( Internal Collapse ) 6. የእውቅና ማጣት ( Lack of Recognition ) ከላይ ከተዘረዘሩት አንድን ህዝብ ለመጥፋት ከሚዳርጉ ምክንያቶች ውስጥ በተፈጥሮ አደጋ ማለትም እንደ እሳተ ገሞራ ፣ የጎርፍ መጥለቅለቅ ፣ የተራዘመ ድርቅ ፣ አውሎ ነፋስ እና መሰል አደጋወች ውጭ ያሉት ምክንያቶች ሰው ሰራሽ እና የተገዳዳሪ የጥላት ኃይል የሚፈጥረው እንደመሆኑ መጠን የጥፋት ምክንያት ሊሆኑ የሚችሉት አደጋው በአንጃበበት ጎሳ ፣ ህዝብ  ወይም ብሔር ስንፍና ብቻ ነው ለማለት ያስደፍራል። አማኝ እና ፆለተኛ የሆነው የአማራ ህዝብ ከተፈጥሮ አደጋውጭ ከላይ የተዘረዘሩት አንድን ህዝብ ለመጥፋት የሚዳርጉ ነገሮች ሁሉ ተተግብረውበታል ፤ ጥንት በዝሆን ላይ ሆነው በሚያደርጉት ህንዳዊያን በሐገራችን ላይ ከሞከሩት ወረራ ጀምሮ በኃያልነቱ አብዝቶ የሚነገርለት የታላቁ እስክንድር ኢትዮጵያን የመውረር ፍላጎት በግሪኩ እውቅ ፈላስፋ አርስቶትል ማስጠንቀቂያነት ሐሳቡን ቀየረ እንጅ ፍላጎት ነበረው ፣ ግብፅ የአባይን መነሻ ለመቆጣጠር በምዕራብ እና በሰሜን ምስራቅ ሐገራችን ለመውረር የተደረገውን ሙከራ ያከሸፍን ጀግና ህዝቦችነነ ፣ በጣሊያን በተደጋጋሚ የተደረገውን የቅኝ ግዛት ሙከራ በመቀልበስ ኢትዮጵያን ብቻ ሳይሆን አፍሪካን ከመጥፋት የታደገ ጀግና ህዝብ ልጆች መሆናችን ህያው ታሪካችን ነው። የቅኝ ግዛት ወረራን በጀግንነት ሲቀለብስ የኖረውን ጀግናውን ህዝብ በባዕዳን የፖለቲካ ፍረጃና የሐሰት ትርክት ጥላቻ የናወዙ የሐገር ወስጥ ጥቁር ፋሽሽቶች ከ1980ወቹ ጀምረው ትውልዱን ዘር አምካኝ መድሐኒት በመመረዝ ዘሩን ሊያጠፉት ከመሞከራቸው በተጨማሪ በአንድ ወቅት 3 ሚሊዮን በመጠጋ መጠን የአማራ ህዝብ ቁጥር ቀንሷል የሚል የህዝብ ቆጠራ ሪፖርት በፓርላማ ቀርቦ ያውቃል። በዚህም አልበቃቸው ብሎ በጨካኝ ጭቆና ስርዓት ቀፍድደው የያዙትን አማራ አማራ የሚባል ማንነት የለም ሲሉ በሚሊዮን የሚቀጠርን አማራ ከስብዕና ካርታ ላይ ሊፍቁት ሞክረዋል። በዚህ መንገድ ያልተሳካለት ይህ ፈሪ አገዛዝ በአማራው ላይ በምድር እና ሰማይ ላይ የሞት አዋጅ አውጆበት ይገኛል። ኢትዮጵያ አትጠፋም --- የአስራት  አገር ናት አትጠፋም --- የሚለው ብሒል ተጨባጭ የህልውና አደጋ ላንጃበበት የአማራ ህዝብ ዋስትና የለውም። ኢትዮጵያም ሆነ አማራ የሚድነው ይህ ትውልድ የነቃ ፣ የተናበበ ፣ የስልጡን ዜጋ ሚናውን ዛሬውኑ መወጣት ሲችል ብቻ ነው። ግዙፉ የአማራ ህዝብ ከሰውልጅ ቁጥጥር ውጭ በሆነ ምክንያት ካልሆነ በስተቀር በቀሪ አምስት ምክንያቶች እንደማይጠፋ አኩሪ የአማራ ግዙፋን አባቶች ታሪክ ምስክር ነው። የአማራ ህዝብ ለጨቋኞች የማይንበረከክ ጀግና ህዝብ ነበር ማለት ግን ሳይደራጅና መራር ትግል ሳያደርግ ይተርፋል ማለት አይደለም። ከልተደራጀ ትልቅ አገር የተደራጀች ትንሽ ከተማ ሙያ ትሰራለች እንዳለው አንድ የብዕር ሰው የአማራ ህዝብ ለባለፉት ስድስት አስርት አመታት የአንጃበበትን የህልውና አደጋ የሚቀለብሰው የጀመረውን የአማራ ህዝብ አብዮት ኃላፊነት እና ተጠያቂነትን ባሰፈነ ማዕከላዊነትን በማረጋገጥ በሐቀኛ የውስጥ ትግል እየታሸ በእውቀት መር ፖለቲካ እንጅ በአውራጃዊ ብሎም በወንዜ አመለካከት በታጀለ ስንፍና እየተጓተትን አይደለም አይደለም። የተደራጀ ህዝብ ስንልም በምስራቅ አፍሪካ ለምራባዊያን ፤ ሌሎች ኃያላን በአጠቃላይ ለፖለቲካ ማህበረሰቡ ግባር ቀደም ኃይል ሆኖ የሚታይ አንድ የአማራ መሪ ድርጅት በአፋጣኝ መፍጠር ያስፈልጋል። በእርግጥ አንድ የአማራ ድርጅት መፍጠር በራሱ ለድል ለስኬት ሊያበቃ አይችልም ፤ የብሔርተኝነት ትግል ከመርህ በላይ በወንድማማችነት እና የነፍስ ግንኙነት ላይ የተገነባ መሆን አለበት። አንድ አማራ ታሪክ ፣ እሴትና ስነ-ልቦና የሚጋራው የአማራ ፋኖ ታጋዮች ትንሽ የቅንነት ቅመም በመካከላቸው ካለ ምቀኝነት እና መጣላለፍ ህልው ስለማይሆኑ ወንድማማችነት ያብባል። አዲስ ትውልድ ፣ አዲስ አስተሳሰብ ፣ አዲስ ተስፋ! Kinfemelak N Kassa

#ለወገን_ሀይል‼️ አሁን በዚህ ሰዓት (ከጠዋቱ 3:10) ከደ/ማርቆስ አንድ FSR እና አንድ ፓትሮል የአብይ መከላከያ ከወደ ዩኒቨርስቲ ወደ አደባባይ እየወጣ ነው ወዴት እንደሚሄድ አይታወቅም በአካባቢው ያለ የወገን ሀይል ዝግጁ ይሁን‼️ 08/ዐ5/2018 ዓ.ም

አገዛዙ በውጊያ የተገደሉ የራሱ ወታደሮችን አ*ስ*ከ*ሬ*ን በድሮን ደበደበ! በምስራቅ ዐምሓራ ቀጠና ከወልድያ ከተማ ዙሪያ አከባቢዎች ጀምሮ እስከ ቃሊምና ቃሊም ዙሪያ አከባቢዎች ድረስ በተደረገው ተጋድሎ በመቶዎች የሚቆጠሩ የአገዛዙ ወታደሮች ሙትና ቁስለኛ መደረጋቸውን ጣቢያችን ለማረጋገጥ ችሏል። ውጊያው የተካሄደው ጥር 05/2018 ዓ/ም ማለዳ ጀምሮ እስከ ምሽት ድረስ ሲሆን፡ ከ13 ሰዓታት በላይ የጨበጣ ትንቅንቅ ነው የተደረገው። በአፋብኃ ምኒልክ ዕዝ ከሀውጃኖ ክ/ጦር እና ከጄነራል አሣምነው ፅጌ ክ/ጦር የተወጣጡ የፋኖ አሃዶች ጥር 05/2018 ዓ/ም ማለዳ ጀምሮ፡ ከወልድያ ዙሪያ ማለትም ጥቁር ውሃ ምላሽን ይዞ እስከ ቃሊም ድረስ በወሰዱት ውጤታማ ነው በተባለ የመከላከልና የመልሶ ማጥቃት እርምጃ በመቶዎች የሚቆጠሩ የአገዛዙ ወታደሮችን በመደምሰስና በርካታ ክላሽንኮቭ መሣሪያ ከነ ተተኳሹ በመማረክ ድል መቀዳጀታቸውን በእለቱ ጣቢያችን መዘገቡ አይዘነጋም። ያለምንም ማቋረጥ ለተከታታይ 13 ሰዓታት በተደረገው የጨበጣ ውጊያ፡ ከወልድያ ከተማ ዙሪያ ሚጦና ጃርሳን ጨምሮ ከጥቁር ውሃ ምላሽ ጀምሮ አላገዶ፡ አፍሪኬር፡ ቃሊም መገንጠያ፡ ዘንዶ ጅራት(ከሳምት በፊት የአየር መቃዎሚያ እስከ ኦራሉ የወደመበት ቦታ)፣ ቃሊም መገንጠያና ቃሊም ድረስ የሸፈነ ተጋድሎ ተደርጓል። አገዛዙ ሁለት ሰው አልባ አውሮፕላኖችን ጨምሮ በወልድያ ሼይኽ መሐመድ ሁሴን አል አሙዲን ስታዲየም እና በከተማዋ ኢንዱስትሪ መንደር ተብሎ በሚጠራው አከባቢ ባጠመደው ጄነራል መድፍ እንዲሁም በከተማዋ አዲሱ ማረሚያ ቤት እየተሰራ በሚገኝበት ጉቦ ተብሎ በሚጠራው አከባቢ ባጠመደው ሞርተር፣ ቢኤምና ዙ23 ታግዞ ከሁለት ዕዝ የተወጣጡ ከሦስት ክፍለጦር በላይ ወታደሮችን በሚኒሻና አድማ ብተና መንገድ መሪነት በማሰለፍ ሲዋጋ የዋለ ቢሆንም፡ ነገር ግን ይህ ሁሉ ግትልትል ኃይል የፋኖን ጥቃት መቋቋም አቅቶት ከባድ የሆነ የሰብአዊና ቁሣዊ ኪሳራን በመከናነብ "ሺ ፈሳም አንድ ጎማ አይነፋም" ሆኖ ቀርቷል። በምኒልክ ዕዝ ስር ከሀውጃኖ ክ/ጦር እና ከጄነራል አሣምነው ፅጌ ክ/ጦር የተወጣጡ የፋኖ አሃዶች በወሰዱት ስኬታማ በሆነ የመከላከልና የመልሶ ማጥቃት እርምጃ በመቶዎች የሚቆጠሩ የአገዛዙ ወታደሮችን መደምሰስ ችለዋል። የጠላት ኃይል በሚደመሰሱበት ወታደሮች ልክ ተጨማሪ ኃይል እያስገባ የዋለ ሲሆን፡ ምሽት ላይ ግን  የሚጨምረውን ኃይል በማቆም ሁለት ሰው አልባ አውሮፕላኖች በማሰማራት ተከታታይ የዘፈቀደ ድብደባዎችን ፈፅሟል። በዚህም በሰዓታት ልዩነት ከ12 ጊዜ በላይ የድሮን ጥቃት የተፈፀመ ሲሆን፡ አገዛዙ የእሱን ስልጣን ለማራዘም ሲሉ ሲዋጉ በፋኖ የተገደሉ የመከላከያ ሰራዊት አባላትን አ*ስ*ከ*ሬ*ን ደብድቧል። ይህም፡ የፋኖ አባላቱ በውጊያው ከተገደሉ የመከላከያ ሰራዊት አባላት ላይ ክላሽና ሌሎች ወታደራዊ ንብረቶችን እንዳይሰበስቡበት በማሰብ የፈፀመው ዘግናኝ ድርጊት ነው ሲሉ  ወታደራዊ ምንጮች ገልፀዋል። በድሮን ጥቃቱ በፋኖ በኩል የደረሰ ጉዳት ባይኖርም ነገር ግን በቤታቸው ውስጥ የነበሩ ንፁኋኖች ተገድለዋል። በጥቃቱ ከተገደሉ ንፁኋኖች መካከል አንድ የቤተክርስቲያን ጠባቂ አባትን ጨምሮ ሌሎች በቤታቸው ውስጥ የነበሩ ሴትና ህፃናት እንደሚገኙበት ታውቋል። በተጨማሪም ከወልድያ ከተማ በሚወነጨፍ መድፍ ሕይወታቸው ያለፈና የቆሰሉ ንፁኋኖች መኖራቸው የተነገረ ሲሆን፡ የመድፍ ጥቃቱ የቤት እንስሳቶችንና ተሰብስቦ የተከመረ የማሽላና የጤፍ ነዶ ማውደሙን የመረብ ሚዲያ የምስራቅ ዐምሓራ ዘጋቢዎች ለማረጋገጥ ችለዋል።

🕯🕯 ዝክረ ሰማዕትነት ጥር /07/2017 ዓ.ም 🕯 _🕯🕯__ ቆራጡ ፦ ሸ አለቃ እንዳሸዉ ጎሽሜ እጄን ለጠላት አልሰጥም ብሎ በኩራት ጠላትን እረፍርፎ እራሡን ሰማዕትነት ያደረገ የእኛ ዘመን ዳግማዊ አፄ ቴዎድሮስ አርበኛ አለቃ እንዳሻው ጎሽሜ በዚህች ዕለት ቀን 08/05/2017 ዓ.ም ነበር በርሲሳይ አላላ መገንጠያ የአብይን አህመድ ጡት ቆራጩ ኃይል ብዝዎችን ሙትና ቁስለኛ አድርጎ ሰማዕትነት የተቀበለው። ነገሩ እንዲህ ነው ማረክን እንዳይሉ ሰው የለ በእጃቸው፤ ገደልን እንዳይሉ ሞተው አገኟቸው፥ ምናሉ እንግሊዞች ሲገቡ አገራቸው፥ ይላሉ የአማራ አበው በመፃፍ ዝክራቸው። አርበኛ እንዳሻው ጎሽሜ የምድሩ ድሮኑ የሽዋው መብርቅ የሚኒልክ ልጅ ጥር 08 /05/2017 ዓ ም የማለዳዋ ያቺ የምታበራዋ ፀሐይ የዛሬን ቀን ነበር ብርሃኗን ማብራት ያቆመችው። የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል ደቡብ የአማራ ቀጠና አሳምነው ዕዝ ጀግኖች በኤፍራታ ግድም ወርዳ ካፈራቻቸው የ7ለ70 ክፍለጦር ዘመቻ መምሪያ ኋላፊ ሁኖ በመስራት በውጊያ ስልቱ ከአባቶች በወረሰው አዋጊ ተዋጊ የተዋጣለት የይፋቴው አንበሳ በክብር ሰማዕትነት የተቀበለበት ቀን ነው። ይህ ትግል ለእውነት ሲሉ ከሞቀ ቤታቸው ወጥተው ለአማራ ህዝብ ነፃነት ከውጣ ውረድ ባለፈ አንድያ ነፍሳቸውን ሰጥተው ብዙዎቹ አልፈዋል። መውደቅን ፣መቁሠልን ፣መድማት ከምንም የማይቆጥሩት ጀግኖች እንደ ሺ አለቃ እንዳሻዉ አይነት ብዙ ዕልፍ ዓላፍ ለጠላት እጅ መስጠት ነውር መሆኑን የተገነዘቡ ለክብርና ለማንነት መውደቅን ለነፃነት መፋለምን ማሸነፍን ግባቸው ያደረጉ ብዙ ጀግኖች ተፈጥረዋል። ብዙ ዕልፍ ዓላፍ ጀግኖች ከትናንት እስከ ዛሬዋ ቀን ድረስ የትግል አደራ ተሸክመው ከ33 ወር በላይ በፈጀው የጦርነት አውደ ውጊያ ለቃላቸው እየታመኑ በተኩስ ድምፅ የሚዘከሩ ለሰማዕትነት የተዘጋጁ የትግልን አላማ የትግልን መዳረሻ አውቀውና አስበው የሚራመዱ ጀግኖች ታሪካቸውን በደምና በአጥንታቸው እየፃፉ የሚልፉ የአሳምነውን ልብ የተላበሱ እንደ ይፋቱ ጀግና እንዳሻው ጎሽሜ አቤት ውጊያ ወደፊት እንጅ ወደ ኃላ የማይሉ አናብስቶች ተፈጥረዋል ። አይለቀስ በስማቸው አይቀለድ በደማቸው፣ ወደቁ አይላቸውም ያቆሙት ህዝባቸው። ያቆዩልን ንፁህ ስምን ያኖሩልን ነፃ ሀገርን፣ እንጠብቀዋለን ሞተን እየኖርን። ነፃነቱን መርጦ እልፍ ሞት የናቀ፣ ለውነት ተሰልፎ ለውነት የወደቀ። ልክ እንደ ጥንቶቹ እንደጀግኖቻችን፣ ለህዝብ መቆም ነው ምን ጊዜም ትግላችን። ህዝብን የማይጠላ ፅንፈኛ ያልሆነ፣ በመገንጠልን ሳይሆን ባንድነት ያመነ። ሀይማኖት አክባሪ ፍትህ ያስቀደመ፣ በደሙ ነጠብጣብ ሀገሩን ያቆመ። የፅናት ተምሳሌት የነፃነት ጮራ፣ ስማችን ፋኖ ነው ነገደ አምሓራ። ትናንት እነሱ አልፈው በንፁህ ደማቸው ታሪክን ፅፈዋል፣ ጠላት ሞቱ ቢልም በልባችን ማህደር ህያው ሆነዋል ። 🕯 ጀግኖች ሁሌም በልባችን ትኖራላችሁ🕯 🕯🕯ታሪክ እናወሳለን ሰማዕታትን እዘክራለን ትግል ይቀጥላል 🕯🕯 ጥር 08/05/2018 ዓ ም ከግንባር

Attention❗ በፍጥነት #Share ይደረግ አረመኔው የአብይ አህመድ ነብሰ-በላ ስርዓት በደቡብ ጎንደርና አርማጭሆ ዙሪያ መጠነ ሰፌ የድሮን ድብደባ ዕቅዶች እንዳ'ቀደ መረጃዎች እየወጡ ስለሆነ ሰራ
Attention❗ በፍጥነት #Share ይደረግ አረመኔው የአብይ አህመድ ነብሰ-በላ ስርዓት በደቡብ ጎንደርና አርማጭሆ ዙሪያ መጠነ ሰፌ የድሮን ድብደባ ዕቅዶች እንዳ'ቀደ መረጃዎች እየወጡ ስለሆነ ሰራዊታችንና መላው በቀጠናው የሚገኝ የሲቪል ማህበረሰብ ከጥቃቱ ራሱን ለመከላከል ከምንጊዜውም በላይ ጥረት እንዲያደርግና ለኢላማ ምቹ የሆኑ የመሰባሰቢያ ቦታዎች ላይ ማለትም ጤና ጣቢያዎች፣ ትምህርት ቤቶች፣ እንዲሁም የአምልኮ ቦታዎች(ቤተክርስቲያንና መስጂድ) አካባቢ ከመሰባሰብ መቆጠብ እንዳለበት በአፅንዖት እንገልፃለን። መኮንን አስፋው!

የመምህራንን ደህንነትና ህልውና እንጠብቃለን" ከአፋብኃ ቴዎድሮስ ዕዝ 206ኛ ኮር የተሰጠ መግለጫ ጥር 7/2018 ዓ.ም ≡================================== የአማራን ህዝብ የህልውና ትግል በመቀስቀስ ጉልህ ሚና የነበረው የመንግስት ሰራተኛውና የመምህራን ንቅናቄ ከፍተኛ አሰተዋጽኦን የማይዘነጋው 206ኛ ኮር እስከ አሁን ድረስ ትግሉን ከፊት ሁነው በአመራርነት የሚመሩ የመንግስት ሰራተኞች እና የመምህራን ቁጥር ቀላል የሚባል አይደለም። የአረመኔው ሰራዊት በአማራ ህዝብ ላይ ወረራ ከፈፀመ በኋላ የመሰረተ ልማት ስራዎች ሙሉ ለሙሉ ተቋርጠው የሀገሪቱ ገቢ ለጥይት መግዣ ሲሆን፣ አገልግሎት ይሰጡ የነበሩ ትምህርት ቤቶች፣ ጤና ጣቢያዎች፣ ኮሌጆች፣ የኃይማኖት ተቋማት እና የንግድ ቦታዎች ወደ ጦር ካምፕነት መቀየራቸው ከአማራ ህዝብ የተደበቀ ሚስጢር አይደለም። ይህንን ተከትሎ በቁጥር ለመጥቀስ በሚያዳግት ሁኔታ የጤና ባለሙያዎችና ዶክተሮች፣ መምህራንና ተማሪዎች፣ ካህናት፣ ቄሶች፣ የአብነት ተማሪዎች እና ነጋዴዎች በድሮን ሲደበደቡ በርካቶች በአረመኔው ሰራዊት በግፍ ተረሽነዋል እልፎችም በማጎሪያ ጣቢያ ተወርውረዋል። ኮሩ በሚንቀሳቀስበት የምስራቅ ጎጃም ዞን መቀመጫ ደብረ ማርቆስ ከተማ አስተዳደር ጨምሮ በ8 የወረዳ ከተሞች ያሉ መምህራን፣ መንግስት ሰራተኞች እና ቤተሰቦቻቸው በከፍተኛ ስቃይና በደል እየተንገላቱ ሲሆን ህፃናት ያለ ወላጅ መቅረታቸውንም የተመለከተው ኮሩ በሚንቀሳቀስበት ሁሉም ቀጠናዎች ባሉ ወረዳዎችና ደብረ ማርቆስ ከተማ አስተዳደር ያሉ 417 (አራት መቶ አስራ ሰባት) የአንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤቤቶች፣ 33 (ሰላሳ ሶስት)የሁለተኛና መሰናዶ ትምህርት ቤቶች በአረመኔው ሰራዊት ከጥቅም ውጭ መሆናቸውን የኮሩ የዳሰሳ ጥናት ያረጋግጣል ። የሀገሪቱን ሙሉ በጀት ለጦርነት እያዋለ የሚገኘው አረመኔው ስርዓት ኮሩ በሚንቀሳቀስበት ቀጠና ያሉ የ11676 (አስረ አንድ ሺህ ስድስት መቶ ሰባ ስድስት) መምህራን የሁለት ወር ደሞዝ 326,928,000 ብር (ሦስት መቶ ሀያ ስድስት ሚሊዮን ዘጠኝ መቶ ሀያ ስምንት ሺህ ብር) በመንጠቅ ለሚኒሻና ካድሪ የአበል ክፍያ መዋሉን አረጋግጠናል ። ከ800 በላይ ርዕሰ መምህራን እና መምህራን በደብረ ማርቆስ ፣ሉማሜ፣ አምበር፣ ደጀን፣ ቁይ፣ ረቡዕ ገበያ እና ደብረ ኤልያስ ከተሞች ማጎሪያ ጣቢያ ታስረው እየተሰቃዩ ሲሆን ከአፈናው ያመለጡ በርካታ መምህራን ቤተሰቦቻቸውን በትነው መሰደዳቸውም ታውቋል። በዚህና መሰል የአረመኔው ሰራዊት ግፍ ቤተሰቦቻችሁን በትናችሁ የምትሰቃዩ ወገኖቻችን እና ልጆቻችሁን መመገብ የተሳናችሁ መምህራን 206ኛ ኮር በተቆጣጠረባቸው ሁሉም ቀጠናዎች በማንኛውም የስራ ዘርፍ ተሰልፋችሁ እራሳችሁንም ሆነ ቤተሰቦቻችሁን ማስተዳደር የምትችሉ መሆኑን እያረጋገጥን ኮሩ አስፈላጊውን ትብብርና ድጋፍ እንደሚያደርግ በማረጋገጥ ነው። ከአረመኔው ሰራዊት ጋር በመተባበር በወገኖቻችን ላይ መከራን የሚጭኑትንም የጠላት እጆች ተከታትሎ ኮሩ እርምጃ እንደሚዎስድ ማሳወቅ እንወዳለን ። አዲስ ትውልድ! አዲስ አስተሳሰብ! አዲስ ተስፋ! የአፋብኃ ቴዎድሮስ ዕዝ 206ኛ ኮር

ተቀራረቡ ተነጋገሩ !! ደውለህ 'እንዴት ሰነበትክ ?' ብለህ ጠይቀው ወንድምህን። በዛው የእራስህንም ደህንነት ታውቃለህና ! እሱ ደህና ሲሆን ብቻ ነው አንተም ሰላም የምትሆነው። ከተዳከምክ ሊበላህ
ተቀራረቡ ተነጋገሩ !! ደውለህ 'እንዴት ሰነበትክ ?' ብለህ ጠይቀው ወንድምህን። በዛው የእራስህንም ደህንነት ታውቃለህና ! እሱ ደህና ሲሆን ብቻ ነው አንተም ሰላም የምትሆነው። ከተዳከምክ ሊበላህ ጥርሱን አግጦ ያሰፈሰፈው ብዙ ነው። ክንድህ ቢዝል አጥፊህ ዕልፍ ነው። መርጦ አይተውህም ! ለይቶ አይምርህም። ያጠፋህ "እንዲህ ሁኖ በዚህ ሁኖ ተሳሳትኩ ይቅርታ" በለው ደፍረህ። እሱም ደፍሮ ይቅርታውን ይሰጥሃል!! አማራጭ የለውም። "ከወንድምህ ጋር ታረቅ፣ ወንድምህ እሱ ነው!" ያልኩህን የ'ኔን የወንድምህን ምክር ስማ። ሌላው ሊጠቀምብህ ነው የሚፈልገው በሰበብ ለይቶ !! ፋኖነት ✊✊ አማራነት ✊✊

የሚኒልክ ፋኖ የአሁኑ ትውልድ💪💪💪
+3
የሚኒልክ ፋኖ የአሁኑ ትውልድ💪💪💪