ፍኖተ- አማራ ሚዲያ (Finote- Amhara ) Midea
Открыть в Telegram
የተመሠረተው የአማራን ሕዝብ ለማንቃት፣ ለማደራጀት እና ለማስተባበር ነው። የአማራ ሕዝብን ✅ ፖለቲካዊ ✅ ማህበራዊ ✅ ኢኮኖሚያዊ ታሪካዊ ጥያቄዎችን ለማሰማት እና የአማራን ሕዝብ በማንቃት ሰፊውን ሕዝብ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ይሰራል። ወደዱም ጠሉም የኃላ ታሪካችን በእኛ እጅ ይፃፋል። አማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ ( አፋብን)
Больше3 613
Подписчики
+6624 часа
+5877 дней
+1 04130 дней
Архив постов
የ77ኛ ክፍለ ጦር ቃኝና መሀንዲስ በአገዛዙ ወታደሮች ላይ በደፈጣ ጥቃት ፈጸሙ!!!
በዛሬዉ እለት በቀን 03/07/2018 ዓ.ም የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ (አፋብን) ቴዎድሮስ ዕዝ 109ኛ ኮር 77ኛ ክ/ጦር ቃኝና ምሀንዲስ ወታደራዊ ክንፎች በተያዘ እቅድ ደፈጣ በመያዝ በአገዛዙ ጥምር ሰራዊት ላይ መብረቃዊ ጥቃት በመፈጸም ጠላትን የማስወገድ ስራ ኦፕሬሽን ሰርተዋል።
የክፍለ ጦፘ በራሪ ኃይል በከፈተችው ጥቃትም የአገዛዙ የጥፋት ሰራዊት ላይ እርምጃ መውሰዳቸውን አስታወቁ። በተወሰደው እርምጃም ከቡሬ ወደ ውንድጊ ሲሄድ የነበረን የአገዛዙ የጥፋት ሰራዊት ከንጋቱ 12:00 ሰዓት አካባቢ በርካታ የጠላትን ሀይልን መደምሰስ እና ማቁሰል ተችሏል።
እራሱን የአገዛዙ ጥምር ጦር ብሎ የሚጠራው የጥፋት ሰራዊቶች በተሰራባቸው ኦፕሬሽን እሬሳቸውን ከእየጥሻው እየለቃቀሙ እየቀበሩ ነው ሲሉም ታማኝ የመረጃ ምንጮቻችን ገለጹ።
የ77ኛ ክፍለ ጦር ቃኝ እና መሃንዲስም የጦር ክንፎች እንደተናገሩትም፡-ዐማራን ለማውደም፣በእናቶቻችን በእህቶቻችን ላይ ሰቆቃ ለመፈጸም እና በዘር በሃይማኖት ለመከፋል ተልዕኮ ይዞ በመጣው የጥፋት ሰራዊቶችን ከቀጠናው ለማስወገድ ከምንጊዜውም በላይ ዝግጁ መሆናቸውን ተናገሩ፡፡
አዲስ ትውልድ፣ አዲስ አስተሳሰብ ፣አዲስ ተስፋ!
ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን !
አፋብን| ቴወድሮስ ዕዝ 77ተኛ ክፍለጦር ሕዝብ ግንኙነት መምሪያ
መጋቢት 3 / 2018 ዓ.ም
የአደረጃጀት ዜና!
የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ (አፋብን) ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ የ102ኛ ኮር የ49ኛ ክ/ጦር አመራር ለተከታታይ ቀናት ባደረጉት አስቸኳይ ስብሰባ የአመራር መተካካትና አጠቃላይ ግምገማ አድርገዋል።
በተጨማሪም በባለፈው አጠቃላይ የ102ኛ ኮር የስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባላትና የድርጅት አመራር በሰጡት አቅጣጫ መሰረት ካላኮርማ ክፍለጦር ይባል የነበረውን ስያሜ 49ኛ ክፍለጦር በማለት እንዲጠራ የተወሰነ መሆኑ ይታወቃል።
በመሆኑም የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅንቄ (አፋብን) ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ የ102ኛ ኮር የ49ኛ ክፍለጦር በዘመቻ አርበኛ አደም አሊ (አባናደው) የነበሩ ጠንካራና ደካማ ጎን በመለየት ለወደፊት ለሚሰራቸው ተግባራት ጥልቅ ሂስ ግለ- ሂስ (ግምገማ) በማድረግ መጋቢት 2/2018 ዓ.ም አዳድስ የስራ ሀላፊነትና የአመራር ሽግሽግ በአዲሱ የአደረጃጀት ሪፎርም በሚከተለው መልኩ ሰርቷል ።
1.ወታደራዊ አዛዥ...........አርበኛ ለገሰ ሰማው
2.ም/ወታደራዊ አዛዥ.......አርበኛ ጋሻው ደርሶ
3.ዘመቻ መሪ ..................አርበኛ ተስፋ አየሁ
4.ም/ዘመቻ.መሪ..............አርበኛ ጥላሁን ሞላ
5.የፖለቲካ መምሪያ...........አርበኛ ጥላሁን ደርቤ
6.ወታደራዊ አሰተዳር.........አርበኛ ደረጀ አማረ
7.የሰው ሀይል አስተዳደር.....አርበኛ ዋሱ ወዳጆ
8.ኦርድናንስ መምሪያ...........አርበኛ መሰለ ታደሰ
10. ጤና መምሪያ.............አርበኛ እንዳለ አበበ
11.ስልጠና መምሪያ.........አርበኛ ብርሀኑ ውዱ
12.ሎጂስቲክ መምሪያ.........አርበኛ ሻምበል ደምሌ
13. ም/ሎጂስቲክ..........አርበኛ ሀይለማሪያም ጌታቸው
14.ፋይናንስ ሀላፊ..............አርበኛ አብቦ በላይ
15.ሴቶች ጉዳይ................አርበኚት ቃልኪዳን በላይ
16.የህዝብ ግንኙነት............አርበኛ መላሹ አወቀ
18.የህግ መምሪያ...............አርበኛ መስፍን ጠመረ
መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልውና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል!
ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን!
የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ (አፋብን) ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ የ102ኛ ኮር ህዝብ ግንኙነት አርበኛ መ/ር አታሎ ሙሉጌታ!
መጋቢት 3/2018ዓ.ም
የምህረት አዋጁን የተቀበሉ የአገዛዙ ሰራዊት አባላት 5 ጥቁር ክላሽ እና 1 ስናይፐር በመያዝ ምኒልክ ዕዝን ተቀላቀሉ‼️
የ11ኛ ዕዝ 104ኛ ኮር መሃንዲስ የሆኑ ስድስት የአገዛዙ ሰራዊት አባላት ከነ ሙሉ ትጥቃቸዉ አፋብን ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ 303ኛ ግዙፉ አሳምነዉ ኮር ነብሮ ተወርዋሪ 16ኛ ክፍለ ጦርን በዛሬዉ እለት ተቀላቅለዋል።
የሰራዊት አባሎቹም 5 ጥቁር ክላሽ እና 1 ስናይፐር ይዘዉ ሲመጡ በ303ኛ ኮር ከፍተኛ አመራሮች ደማቅ አቀባበል ተደርጎላቸዋል።
ኮብልለዉ አፋብን ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ 303ኛ ኮር ነብሮ ተወርዋሪ 16ኛ ክፍለ ጦር የተቀላቀሉ የአገዛዙ ሰራዊት አባለት መካከል አራቱ የአስር አለቃ ማዕረግ ያላቸው ሲሆኑ ሁለቱ እግረኛ ናቸው:: እነዚህ የአገዛዙ ሰራዊት የነበሩ አባላትም እኛ አፋብን ያወጣዉን የምህረት አዋጅ ተቀብለን ወደ አማራ ፋኖ ተቀላቅለናል አሁንም እኛ በነበርንበት ቦታ ያላቹህ የሰራዊት አባላት እና አመራሮችም ጊዜዉ ሳይረፍድባቹህ በላቹህበት ቀጠና ወደ ፋኖ እንድትቀላቀሉ ሲሉ ጥሪ አስተላልፈዋል።
የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ (አፋብን) ምስራቅ አማራ ቀጠና ሚኒሊክ ዕዝ ሚዲያ እና ኮሚኒኬሽን መምሪያ
መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልዉና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል!
ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን!
©አፋብን ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ
መጋቢት 3/2018 ዓ.ም
03/ዐ7/2018 ዓ.ም
+1
የ206ኛ ኮር አዳኝ ቡድን ከሌሊቱ 7:45 በደብረ ማርቆስ ከተማ በፈፀሙት የቦምብ ጥቃት ዋና ሳጅን ተስፋሁን ዋለልኝን ጨምሮ 7አድማ ብተና አባላት ተገድለዋል ።
መጋቢት 3/2018 ዓ.ም
=================================
የ206ኛ ኮር አዳኝ ቡድን በደብረ ማርቆስ መሀል ከተማ ተነስቶ ወደ ለቅለቂታ ቀበሌ እየሔደ በነበረ ኦባማ መኪና ላይ በፈፀሙት የቦንብ ጥቃት 7 አድማ ብተናዎች ሲገደሉ 11 የሚሆኑት ከባድ ቁስለኛ ሁነዋል ።በተመሳሳይ ሰዓት የአብማ ክ/ከተማ ሚኒሻ ጽ/ቤት ስልጠናና ስምሪት ኃላፊ በሆነው በላይነህ አጃናው ቤት ተጨማሪ ጥቃት ተፈፅሟል።
ጨለማን ተገን በማድረግ በሚንቀሳቀስ የጠላት ኃይል ላይ ያነጣጠረ የተጠና ኦፕሬሽን የሚፈፅሙት የ206ኛ ኮር አነፍናፊ አዳኝ ቡድኖች በትናትናው ተመሳሳይ ጥቃት በተሽከርካሪው መሀል ስፖንዳ ላይ የተሳካ የቦምብ ፍንዳታ በመፈፀም በ18 የአድማ ብተና ሰራዊት ላይ ከፍተኛ ጉዳት ደርሷል።
ከትናት በስተያ እንዲሁ በብርሸለቆ እና ደብረ ማርቆስ ወታደራዊ ማሰልጠኛዎች ስልጠና በመስጠት የሚታወቀው ኮ/ር ግዛቸው በሾላምባ ቀበሌ ወደ መኖሪያ ቤቱ በፒክ አፕ መኪና እየሔደ ባለበት በተደረገበት የቦምብ ጥቃት ከሞት የተረፈ ቢሆንም ከባድ ቁስለኛ መሆኑ የሚታወስ ነው።
አዲስ ትውልድ! አዲስ አስተሳሰብ !አዲስ ተስፋ!
የአፋብን ቴዎድሮስ ዕዝ 206ኛ ኮር ህዝብ ግንኙነት
የንስሮቹ ዳግም ውህደት የሸዋ ምድር የአንድነት ዝማሬ
በሸዋ ወይና ደጋማ ተራራዎች ላይ ለሁለት ዓመታት ያህል የቆየው የሀሳብ መለያየት አክትሞ አዲስ ብርሃን የታየበት ታሪካዊ ዕለት ሆኗል። በአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ ስር የሚንቀሳቀሱት የደቡብ አማራ ቀጠና አሳምነው ዕዝ እና የሸዋ ጠቅላይ ግዛት ዕዝ ለሁለት ዓመታትን በኃሳብ ልዩነት መንገድ ሲጓዙ ቆይተው፣ ዛሬ ግን የሸዋን ህዝብ የአንድነት ጥሪ ሰምተው ወደ አንድ ታላቅ አደረጃጀት ተመልሰዋል።
በዚህ ታሪክ ውስጥ እንደ ንስር የተመሰሉት የአሳምነው ፋኖ አባላት ንስር ከከፍታ ላይ ሆኖ ጠላቱን የመለየት እና ሳይታሰብ የመወርወር ብቃት እንዳለው ሁሉ እነዚህ ታጋዮችም በቀጠናው ውስጥ ያላቸውን ወታደራዊ ንቃትና ፍጥነት የሚያሳይ ሲሆን በዚህም ከሁለት አምት በላይ በሁለት የተለያዩ ዕዞች ስር ሆኖ ሲመራ የነበረው የሸዋ ፋኖ፣ አሁን ወደ አንድ ጠንካራ ማዕከል መምጣቱ በወታደራዊ ኃይል ከመለያየት አብቅቶ ወደ አንድ አደረጃጀት መምጣቱ በቀጠናው ለሚደረገው እንቅስቃሴ አዲስ ስልታዊ ጥንካሬን እየሰጠ ይገኛል።
የሁለቱ ዕዞች ውህደት ተከትሎ በተለያዩ ግንባሮች የሚገኙ ክፍለ ጦሮች እየተገናኙ ደስታቸውን በመግለጽ ላይ ይገኛሉ። ይህ በታጋዮች መካከል ያለውን ስነ ልቦናዊ አንድነት የሚገነባ "አንድ ልብ አንድ ዓላማ የሚለውን መርህ በተግባር ያሳየ ክስተት ሆኗል። በቀጠናው ያለውን ወታደራዊ የበላይነት ከማረጋገጡም በላይ በሽዋ በደቡብ አማራና በሸዋ ጠቅላይ ግዛት ውስጥ የሚንቀሳቀሱት ሸዋ ጠቅላይ ግዛት ዕዝ ዓፄ አምደ ጺዮን ክር ደጅ አዝማች ተሰማ እርገጤ ክፍለጦር አመራሮች እና የአሳምነው ዕዝ አፄ ዘር ዓ ያዕቆብ ፩ኛ ኮር ሰባት ለሰባ ክፍለጦር አመራሮች እና የፋኖ አባላት ቅንጅታዊ አሰራር ወደ ላቀ ደረጃ አሻግሮታል። የሸዋ ተራራዎች ዛሬ በደስታና በአንድነት ዝማሬ እያስተጋቡ ይገኛሉ።
መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልውና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል!!
ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን!!
የአፋብን ደቡብ አማራ ቀጣና አሳምነው ዕዝ ዓፄ ዘርያዕቆብ ፩ ኮር ህዝብ ግንኙነት ኃላፊ አርበኛ አማረ ታዘዘ !!
መጋቢት 03 /06/2018 ዓ.ም
+4
ም/አስር አለቃው እና የፖራ ኩማንዶ አባሎች የምህረት ጥሪውን ተቀብለው 201ኛ ኮር 54ኛ ክ/ጦርን ተቀላቀሉ። ➺➺➺➺➺➺➺➺➺➺➺➺➺➺➺➺➺
........መጋቢት 03/2018 ዓ.ም
1ኛ.ም/አስር ዓለቃ ሚካኤሉ ደሰታ
ከሰዴ 25ኛ ክ/ጦር 6ኛ ሬጅመንት 1ጥቁር ክላሽ በመያዝ
2ኛ. ጌታሰው ግዛ... የ16ዓመት ታዳጊ የሆነው ፓራ ኮማንዶ 1ኮሪያ ክላሽ በመያዝ
3ኛ.ምስጋናው በለጠ ..ከድጎ ፅዮን 25ኛ ክ/ጦር 5ኛ ሬጅመንት 1ጥቁር ክላሽ በመያዝ ወደ ፋኖ የተቀላቀሉ ሲሆን በክፍለ ጦር አመራሮች አቀባበል ተደርጎላቸዋል።
አዲስ ትውልድ፣አዲስ አስተሳሰብ፣አዲስ ተስፋ
የአፋብን ቴዎድሮስ ዕዝ 201ኛ ኮር ህዝብ ግንኙነት
አያ በለው በለው ና በለው፣
በልየ ምን አለ እምቢ እንጃ ነው ያለ፣
የአባ ኮስትርን ወኔውን ታጥቆ፣
የእጅጉን ዝናር ክብሩን ጠብቆ፣
ሀገሩ አምሓራ ሳይንት የበቀለበት፣
አይመለስም ከተነሳበት።
......የነዚያ ዘር....🔥
••••••••••••••••••••••••••••••••••••••
የከባቢያችን አየር በነጎድጓድ በታጀበ ብርቅርቅታ ውስጡ ያዘለውን ኮረንቲ ወደ ምድር ሲወረውረው መብረቅ እንለዋለን። በአምሓራ ሳይንት ወግዲ ሰማይ ስር ደሞ የሀብታሙ ደምሴ ልጆች ከጠላት ማርከው በታጠቁት ዲሽቃ እሳተ ጎመራ በመሰለ አብሪ ጥይት ጠላት ግንባር ላይ ሲያስጓሩትና ሲያፈነዱት ነው መብረቅ የምንለው።
መብረቅ ብዙን ጊዜ ከዝናብ ጋር ተያይዞ ይምጣ እንጂ ከእሳተ ጎሞራ ወይም ደግሞ ከአውሎንፋስ ጫፍ ላይ ተፈናጥቆ ወደምድር የመምዘግዘግ ባህርይም ያሳያል። በአባኮስትር በላይ ዘለቀ ቀየ ደሞ የምድር ድሮኖቹ መብረቅ የሚያዘንቡት በፀሀይም ፤ በዝናብም ፤ በቀን፤ በጨለማ'ም መሆኑ ልዩ ያረጋቸዋል።
ከከባቢው አየር በሚነሳው ኮረንቲ የሚወድቀው መብረቅ ፣ ጫፉ እስከ 60ሺህ ሜትር በአንድ ሰከንድ እስከ መሄድ ይችላል። የሀብታሙ ደምሴ ልጆች መብረቅ ሲያዘንቡ ግን ከወግዲ - መካነሰላም - መሀል ሳይንት - አምሓራ ሳይንት ድረስ የሚዘረጋ እጅግ አስፈሪ ምድረ አንቀጥቅጥ መብረቅ ነው የሚወርደው።
በነገራችን ላይ በአመት እስከ 16 ሚሊዮን ጊዜ መሬትን መብረቅ ይመታታል። በወግዲ ሰማይ ስር መብረቅ ክፍለጦር ደሞ የአቶ ዘውዱ ሰጣርጌ 'ን ተላላኪ ሰራዊት በቀን ሁለት ጊዜ በወር 60 ጊዜ በአመት 720 ጊዜ ክፉኛ ይመታዋል።
በምዕራብ ቤተአማራ ወግዲ ሰማይ ስር የሚሰሩ ስራዎች ወታደራዊ ግዳጆች ፣ ሪፎርሞች እንዲሁም ስልጠናዎች ላይ አሻራውን እንጂ ፣ ድምፁን ሆነ ምስሉን ሚዲያ ላይ አናየውም። በስራ እንጅ በወሬ ብዙም አያምኑም። ዝምተኞቹ እውነተኛ መብረቅ ናቸው።
ሰራዊቱ መሪውን ነው የሚመስለው። ሻለቃ ሀብታሙ ደምሴ ብዙ ከሚናገር ፣ ማዳመጥ እሱን ለማስረዳት ነገሮችን በሁለት ሀረግ ነገሮችን የሚረዳበት ፍጥነት የግሉ ስጦታወቹ ናቸው።
ከራስ ደጀን ተራራ የገዘፈ ፣ ከጣና ሃይቅ የሰፋ ፣ ከግዮን ወንዝ የረዘመ ፣ ከ ዋሸራ ቅኔ የረቀቀ ፣ ከላሊበላ ውቅር አብያተ ክርስትያናት ድንቅ ጥበብ የላቀ ፣ በደላንታ ተራሮች ማህጸን ውስጥ ከ ሚገኙት የከበሩ ማዕድናት የነጠረ ማንም እንዳሻው ሊያደርገው ቢሞክር ስብር የማይል ታላቅ የሞራል ልዕልና ያለው እንቁ ወርቅ አርበኛ ነው።
የመንደር ጫጫታ ፣ የጥይት ጩኸት ፣ የጠላት መፍጨርጨር ለአፍታ የማያስጨንቀው የጦር መሐንዲስም ጭምር ነው። የምዕራብ ቤተአማራ የፋኖ አደረጃጀት እና አሁን ለደረስንበት የትግል አመራቂ ውጤት ከመጋረጃ ጀርባ ሆኖ የጦር ስልታዊ ንድፍ ቀራፂ ሆኖ በዝምታው ሰሪ ፣ ከካሜራ እና ከሚዲያ በብዙ ርቀት ርቆ ለድል እና እና ለነፃነት ለወገኑ በንፁህ ህሊና ጥበብ በአመራርነት ላይ የሚገኝ ... ዝምተኛው መብረቅ ነው።
ቋሚ ምስል፦ በአፋብን ምኒልክ ዕዝ ንጉስ ሚካኤል ኢሊ ኮር ስር ስማቸው ከግብራቸው ጋር የተመሳሰለው የመብረቅ ክ/ጦር ፋኖዎችና የዕዙ ከፍተኛ አመራር የሆነው አርበኛ ሀብታሙ ደምሴ ጋር ከግዳጅ መልስ።✊
ሰማእቱ ይታገሱ አራጋው
የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ ወሎ ቤተአምሃራ ቀጠና የራያ ቆቦ ወረዳ ጊዜዊ መንግስት አስተዳዳር፣ በወረዳው ስር የሚገኙ የንዑስ ወረዳ አመራሮች ጋር ከድርጅት እና ከ ምኒሊክ ዕዝ ምስራቅ አማራ102 ኮር ከፋተኛ አመራሮች በተገዩበት ጥልቅ ግምገማና ውይይት በማድረግ ለቀጣይ የአማራን ትግል ህዝባዊ በማድረግ ሰራዊቱን ከህዝቡ ህዝቡን ከሰራዊቱ በማስተሳሰር የመገናኛ ድልድይ ሆነው እደሚያገለግሉ እና ለማንኛውም ግዳጅ ዝግጁ መሆናቸውን አሳውቀዋል።ከውይይቱ የነበረው ከፍተኛ የድርጅትና የኮር አመራርም ትግሉ ቀና እና የተቀላጠፈ እድሆን ህዝባችነን ማክበር አለብን ብሏል።ህዝብን የምናከብረውም እናተን ሲቪል አደረጃጀት መዋቅሩን ስናከብር ነው እኛ እናተን ስናከብር እናተ ህዝባችነን አክብሩልን የምንሞትለትን ህዝብ ከብአዴን እና ከብልጽግና አመራር በተለየ ሁኔታ ሁናቹሁ በቀናነት፣ ከወገተኝነት ፣ከሙስና ከማጎላላት በጸዳ መልኩ አገልግሎት ሰጡልን የምንሞትለትን ህዝብ ከፍቶት ማየት አንፈልግም ምክኒያቱም አማራ ተከፍቶብን ፣ፍትህ አጥቶብን ተሳዶ ተፈናቅሎብን ፣ተደፍሮብን ፣ ሞቶ በጅምላ ተቀብሮብን ሰለሆነ ወድትግል የወጣነው።
ሠለዚህ የሲቪል አደረጃጀት ላይ ወታደራዊ አደረጃጀት ጥልቃ ገብነቶች ይበዛሉ ከዚህ በኋላ ጣልቃ ገብነቶች እዳይኖሩ ትዕዛዝ እናወርዳለን ህዝብ አስተዳደሩ ህዝቡን በቀናነትና በተቀላጠፈ የአገልግሉት አሰጣጥ እድሰጡን ትልቅ አደራ ጥለንባቹኋል በማለት ውይይታቸውን ቋጭተዋል።
ለእኛ ለፋኖ ህዝባችን ሁሉነገራችን
ሰለዚህ እኛ ፋኖዎች ለደጉ ህዝባችን ትለፍ ሂወታችን።
አማራ ማለት ፋኖ ነው ፋኖ ማለት አማራ ነው።
አማራ ያሸንፋል።💪💪💪💪💪
የድል ዋዜማ ሽብር
በሸገር ሰማይ ስር ድቅድቅ ጨለማ በነገሰበት በነዚህ የጭንቀት ቀናት ውስጥ፣ አዲስ የሴራ ድር እየተጎነጎነ ነው። የሽዋው አሳምነው አናብስቶች አንድነትን ፈጥረው ስጋት በሆኑበት በዚህ ወቅት የብልፅግናው ተላላኪ አብይ አህመድና የኦህዴዱ ወሮበላ ሽመልስ አብዲሳ የፍርሃት ቆፈን ውስጥ ገብተዋል።
ሰሞኑን ሸገር ሲቲ" በሚል የሽንገላ ስያሜ በከለሉት ክልል ውስጥ፣ ከሰላሳ ሺህ በላይ የሚሆኑ የኦሮሙማ ሚኒሻዎችን አስታጥቀው የከተማዋን ሰላም ለማናጋት ድንግርግርና ምንግርግር ሲሉ ይስተዋላሉ። ይህ የከንቱ ሙከራ ግን የፍጻሜያቸው መቅረብ ምልክት እንደሆነ በአዲስ አበባ የሚገኙ የፍኖተ አማራ ሚዲያ ምንጮች ለጣቢያችን በላኩት ግንባር ቀደም መረጃ አረጋግጠዋል።
ጠላት መጨረሻው መቃረቡን አውቆ በጭንቀት ቢታወክም፣ ድል ግን የህዝብ መሆኑ አይቀሬ ነው። ለማንኛውም፣ የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ በብርሃን ፍጥነት ወደ ከተማዋ እየገሰገሰ ነው!
እውነት ሁሌም ታሸንፋለች!
መረጃዎች በፍጥነት እንዲደርሱዎት፦ ሼር! ሼር! ሼር! እያደረጉ ይወዳጁን።
" አሰብን ከማስመለስ፤ አዲስ አበባን ማስመለስ ! " አይ ኦህዴድ !
በአንድ ሌሊት፣ ሰው በተኛበት አዲስ አበባ ከተማን ዙሪያውን ከቦ "ሸገር ከተማ" የሚባል ግዙፍ ከተማ ፈጥሮ እስከ ሰወቹና ህንፃወቹ ለኦሮሚያ ክልል ያበረከተው የኦህዴድ አገዛዝ አሁን ደግሞ የኦሮሚያ ልዩ ጥቅም እያለ ሲያለቃቅስበት የኖረውን ነገር አንድ ደረጃ ከፍ አድርጎ አዲስ አበባን ማስመለስ የሚል ረቂቅ ሰነድ አዘጋጅቶ እየተወያዬ ነው።
በመጀመሪያ እቅዳቸው "አዲስ አበባን የማትጠቅም ከተማ ማድረግ" የሚል ነበር። ለዚህ ነበር ከቦሌ ኤርፖርት 40 ኪ.ሜ ርቀት ላይ ሌላ ኤርፖርት ግንባታ ጀምረው እየሰሩ ያሉት። በተመሳሳይ ሸገር ሲቲ ምስረታም ለዚህ ነበር።
ከምርጫ በኋላ ተፈፃሚ የሚሆን አዲስ አበባ፣ ሀረርና ድሬዳዋን ማስመለስና ወደ ታላቋ ኦሮሚያ ማጠቃለል የሚል ሰነድ ተዘጋጅቶ በየደረጃው ውይይት እየተደረገበትም ነው።
አሰብ ምናምን የሚባለው አገራዊ አጀንዳ አማራን ለማደንዘዝ እንጅ በጭራሽ ውሸት ኑሯል፤ ውሸትም ነው። አሁን የሚፈልጓት ለቀጣይ 5 አመት እንደ ሽፋን የሚያገለግላቸውን የጨበራ ምርጫ ብቻ ነው። ከዚህ በኋላ የቀራቸውን ነገር በሙሉ አሟልተው ከቻሉ መግዛት ካልቻሉ መገንጠል ነው።
አማራ አሁን ትኩረት ማድረግ ያለበት ኢትዮጵያ ከምትባለው አገር ምንድን ነው ድርሻዬ፣ ሌሎችን የአገሪቱ ብሔሮች አቀናጅቼ ልታደጋት አልያም በጉልበትም ሆነ በሰላም የሚገባውን መውሰድ ነው። የአባይና ጣናን አበርክቶ በካሳ መልክ ማግኘት ባይችል እንኳ ቢያንስ ከእነዚህ የተፈጥሮ ሀብቶቹ የሚመነጩትን ጣና በለስና የአባይ ግድብ ኤሌክትሪክን መውሰድ አለበት፤ ካልሆነ ደግሞ ገዳዮቻችን እንዳይጠቀሙበት ማድረግ ነው።
ኢትዮጵያ ለአማራ ካሳ የምትከፍልበት ዘመን እንጅ አማራ እንደ ሺህ አመታት ታሪኩ አማራ ለኢትዮጵያ የሚሞትበት ዘመን ማብቃት ያለበት ወሳኝ ጊዜ ላይ የደረሰ ይመስለኛል፤ ያውም እንደደረሰብን ሁኔታ ያረፈድን ያህል ይሰማኛል።
አሁን እየተረዳን ያለነው ይሄው አማራ ለአሰብ እንደማይዋጋ ሲያውቁ ትግራይ ያስገቡትን 24 ክ/ጦር ሰራዊት አዙረው አማራ ክልል ላይ እያሰፈሩት ነው።
ለማንኛውም እንደ ተጨማሪ አማራ የኢኮኖሚ ጦርነቱንም ማሸነፍ መቻል አለበት። እውነት ለመናገር በኢኮኖሚ ጦርነት አማራ በእጥፍ እንደሚያሸንፍ እርግጠኛም ነኝ።
ድል ለአማራ ህዝብ፤ የአማራ ህዝብ ለዘላለም ይፅና !
@ይኸነው
/// ሸዋ////
አማን ይሁን ብሎ ሸዋ ከመከረ፣
አሁን ነው በእውነቱ ሀገር ጠነከረ፤
ወዮላችሁ ብሎ ትንቢተ ኢሳያስ፣ (1፥4)
የአንድነቱ ድግስ ተጉለት ሲደገስ፣
ልመነው ሲጠበቅ ደረሰ ሽመልስ፤
ሙሉቀን አከበርን የመፃጉን ሰንበት፣
በዳዊት በገና በያሬድ ዝማሬ ቃልን አፀኑባት፤
አንድነቱ አበበ የባዕለወልድ ዕለት፣
ብሩክ ይሁን ብሎ አስቀዳሽ መርቆት፣
ይኸው ዛሬን አየን ለእርሱ ምንተስኖት፤
መሀራ ስንበላ ቀድሰው ካህናት፣
የአብርሀም ቤት ያድርገው ብለው መርቀውት፣
ማዕዱ ሳይነሳ መጣ ቢሉ ጠላት፣
የከሰሙን ጀግና ማርከው ብለው ላኩት፤
ብስራት ለንጋቱ ማነገረው ሲሉ፣
ደስ ይበልህ ብለው ለባዩም ደወሉ፤
በልዩነት ቁርሾ ውስጤን እየከፋኝ፣
አንድ ሆንን ሲሉን ዛሬ ግን ደሳለኝ፤
የአማራ ታጋዩን ሲመራው ተፈራ፣
ህግ እና ስርዓት በሙሴ ተሰራ፤
በአሉባልታ ወሬ ስሙ የማይነሳው፣
አንድ እንሁን ብሎ በፍቅር ዳኛቸው፤
ሲገድለው እንዳይኖር የመጣ የሄደው፣
ፋኖ አይደለም እንዴ የአማራ መከታው፤
ሸዋ ተሞሸሯል ጠጁንም ተጎንጩት ጨፍሩ ደልቁ፣
ጎንደርንም ሳምንት የገብርሔር እለት ጠብቁ፤
ለነ ፀረ አንድነት ለሴረኛ ጠላት፣
ይድነቃቸው ብለው በዜና ዘገቡት።
//
የአፋብን ቴዎድሮስ ዕዝ 105 ኛ ኮር ታዓምር መስራቱን እንደቀጠለ ነው !
4/አራት የአድማ ብተና አባላት 12/አስራ ሁለት ክላሽ በመያዝ ፋኖን ተቀላቀሉ‼️‼️‼️
መጋቢት 01/2018 ዓ/ም የአገዛዙ 4/አራት የአድማ ብተና አባላት አዲስ ቅዳም ከመሸገው የጠላት ካፕ በመውጣት 105ኛ ኮር የ44ኛ ክፍለ ጥር የፋኖ አባላትን ተቀላቅለዋል።
1ኛ.እስራኤል እየሱስ አድማ ብ/አባል
2ኛ.ሞገስ እሸቱ አድማ ብ/አባል
3ኛ.አበበ መልካሙ አድማ ብ/አባል
4ኛ.ሞገስ ክንዱ አድማ ብ/አባል ናቸው
የአድማ ብተና አባላቱ አገዛዙ በአማራ ህዝብ ላይ የሚያደርሰውን ሁለተናዊ ውድመት በማየታቸው ምሬትና ቁጭት ሲፈጥርባቸው እንደቆየ ተናግረው፣አጋጣሚውን ተጠቅመን ታሪክ ለመሥራትና ለህዝባችን አንድ ውለታ ለማዋል ጥረት ስናደርግ ቆይተናል ብለዋል።
ጊዜና ሁኔታወችን ለማመቻቸት ጊዜ ቢወሥድብንም በመጨረሻ ተሳክቶልን ጋ/መሪውንና ዋርድያው መጋዘን ሲጠብቅ የነበረን ተላላኪ ቦንዳ አፉን አፍነው ከግድ ጋር በማሠር መካዘን ውስጥ የተቀመጠን 12/አስራ ሁለት መሳሪያና 12/አስራ ሁለት ትጥቅ ይዘን ወንድሞቻችንን ተቀላቅለናል ሲሉ አስረድተውናል።
ከአገዛዙ ጋር በመወገን ወገናቸውን ለሚወጉ የተለያዩ አባላት ማለትም አድማ ብተና፣ሚሊሻ፣ፓሊስ፣ መከላከያና ማንኛውም የብልጽግና አደረጃጀት ውስጥ ለሚያገለግሉ አማራዎች መልክታቸውን አስተላልፈዋል።
የአማራ ህዝብ በማንነቱ ተለይቶ በተወለደበት ቀየ እንደአውሬ እየታደነ ሲገደል፣ሴቶች ሲደፈሩ፣የሚበላው የአመት ቀለብ ሲቃጠል፣ቤተምነቶች ሲወድሙ፣የሀይማኖት አባት ሲገደሉ፣የህዝብ ተቋማት ሢወድሙ ባይናችን አይተን ተመልክተናል።ስለዚህ ከዚህ አረመኔ ስርዓት ጋር መወገን በታሪክ ባንዳ ከመሆንም አልፎ እራስን እንደማጥፋት ስለሚቆጠር፣ፈጥናችሁ ወደወገናችሁ በመቀላቀል ለታላቁ አማራ ውለታ እንድትውሉለት ሲሉ መልክታቸው አስተላልፈዋል።
በመጨረሻም ከፋኖ ሲቀላቀሉ በኮር አመራር፣በክፍለ ጦር አመራርና አባላት የጀብደኝነት አቀባበል ተደርጎላቸዋል።
አዲስ ትውልድ፣ አዲስ አስተሳሰብ፣ አዲስ ተስፋ‼️
አፋብን ቴዎድሮስ ዕዝ የ105ኛ ኮር ሕዝብ ግንኙነት
ፍሬዘር መንግስት ዘለቀ
የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ ደቡብ አማራ ቀጠና አሳምነው ዕዝ ዓፄ ዘርዓያዕቆብ ፩ኛ ኮር ዓፄ ይኩኖአምላክ ክፍለ ጦር በኤፍራታ ግድም ወረዳ ካራ ቆሪ አካባቢ በቀን 30/05/2018 ዓ.ም የአብይን አህመድ ኃይል ሲያሯርጡት መዋላቸውን በዜና መልኩ መዘገባችን ይታወቃል።
ሆኖም በተካሄደው በዚህ እልህ አስጨራሽ ውጊያ፣ የክፍለ ጦሩ አባላት ከጠላት ኃይል ጋር ባደረጉት ፍልሚያ የአብይ አህመድ አራዊት ሰራዊት አየር ወለድ መከላከያ ኃይል ሲያሯርጡት መዋላቸውን በዕለቱ ባወጣው ዜና የጠላትን ኃይል መደምሰሱንና አካባቢውን መቆጣጠራችን ይፋ አድርገን ነበር።
በዚሁ በካራ ቆሪ ግንባር በነበረው አውደ ውጊያ አራት የኦሮሞ ተወላጅ የሆኑ ግለሰቦች መንገድ ስተው ወደ ዓፄ ይኩኖአምላክ ክፍለ ጦር ሰራዊት ተቀላቅለው የነበር ሲሆን እነዚህ ግለሰቦች ወደ ክፍለ ጦሩ ከገቡበት ጊዜ ጀምሮ አስፈላጊው እንክብካቤ ሲደረግላቸው ቆይተው በዚህ ሂደት ውስጥም የአማራ ፋኖ ከስረዓቱ እንጅ ከኦሮሞ ቤሔርሰብ ጋር ምንም አይነት ፀብና ጥላቻ እንደሌለው የፋኖ አናብስቶች የላቀ የጦር ሜዳ ስነ ምግባር አሳይተዋል።
ሆኖም የዓፄ ይኩኑ አምላክ አናብስቶች በእነዚህ የኦሮሞ ተወላጆች በከፍተኛ ዲሲፕሊንና በንፁህ ሰብዓዊ እንክብካቤ ሲያድረጉላቸው ከቆዩ በኋላ ወደ መጡበት ቀጠና በሰላም እንዲመለሱ ተደርጓል።
ይህ ተግባር የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ የታጠቀው መሳሪያ ለፍትህና ለነፃነት እንጂ በንፁሃን ላይ ጉዳት ለማድረስ እንዳልሆነ በተግባር ያሳየ መርህ መሆኑን ከግለሰቦቹ ኃሳብ ተሰጥቷል።
መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልውና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል!!
ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን!!
የአፋብን ደቡብ አማራ ቀጣና አሳምነው ዕዝ ዓፄ ዘርያዕቆብ ፩ ኮር ህዝብ ግንኙነት ኃላፊ አርበኛ አማረ ታዘዘ !!
መጋቢት 02/07/2018 ዓ.ም
