ru
Feedback

Не попадитесь на канал ботавода! Telemetrio находит и помечает такие каналы 👉 Хотите видеть метку — оформите подписку

ፍኖተ-አማራ ሚዲያ (Finote Amhara Media)

ፍኖተ-አማራ ሚዲያ (Finote Amhara Media)

Открыть в Telegram

የተመሠረተው የአማራን ሕዝብ ለማንቃት፣ ለማደራጀት እና ለማስተባበር ነው። የአማራ ሕዝብን ✅ ፖለቲካዊ ✅ ማህበራዊ ✅ ኢኮኖሚያዊ ታሪካዊ ጥያቄዎችን ለማሰማት እና የአማራን ሕዝብ በማንቃት ሰፊውን ሕዝብ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ይሰራል። ወደዱም ጠሉም የኃላ ታሪካችን በእኛ እጅ ይፃፋል። አማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ ( አፋብን)

Больше
4 379
Подписчики
-924 часа
+2477 дней
+1 42930 дней
Архив постов
✍️አንቺን መርሳት እንደምን ይሆንልናል? *** ንጹሐን ኦርቶዶክሳውያን ደማቸው የፈሰሰብሽ የደም መሬቷ አርሲ ሆይ አንቺን መርሳት እንደምን ይቻላል? ጠላት ዲያብሎስ አንቺን ለመርሳት፣ የወገኖቻቸን ደም ደመ ከልብ ለማድረግ ዝክራቸውንም፣ ፍትሐቸውንም እንዳንጠይቅ ምክንያት ሲፈለፍል ይውላል፡፡ ዳሩ ግን አኬልዳማዋ አርሲ ሆይ በድሆች ደም፣ በጭቁኖች እንባ ተጥለቅልቀሻል እና ከቶውንም ልንረሳሽ፣ የምስኪኖችንም ፍትሕ ትቀብሪ ዘንድ ልንተውሽ አይሆንልንም፡፡ አንቺ የመቅደሱን መልክ ቄስ አስፋው መኩሪያን ለወራት በጫካዎችሽ ጉያ፣ በአርመኔዎች እጅ ላይ በስቃይ ይኖሩ ዘንድ የፈረድሽባቸው አርሲ ሆይ አንቺን እንዴት መርሳት ይቻላል? አንቺ እኮ ጨካኞችን አብቅለሽ፣ በጨካኞች የሚበሉትንም ወለደሽና አሳድገሽ በተቃርኖ ዐለምሽን የምትገፊ አስጨናቂ ምድር ነሽ፡፡ የመከረኛውን የሕጻኑን የታምራት አውግቸው ሙሉ ቤተሰብ ያለ ሐፍረት ቀርጥፈሽ ከበላሽ በኋላ እርሱን ደግሞ በሞትና በሕይወት መካከል ይሆን ዘንድ እግሩን ጭምር አሳጥተሽ፣ ሰላምሽን የምትመኚ ከንቱ ምድር እኮ ነሽ፡፡ አርሲ ሆይ! አንቺ እኮ የስምንት ዐመቷን ብላቴና የስንታየሁን ቤተሰቦቿን መንጠቅሽ ሳይበቃሽ፣ በዓለም ታይቶ የማይታወቅ የአረመኔዎችን ጭካኔ በትከሻዋና በጭንቅላቷ ላይ ያሸከምሽ የመከራ ሸክምሽ የበዛ ይሉኝታ ቢስ እና ፍርድ የማታውቂ የጨካኞች ምድር ነሽ፡፡ አርሲ ሆይ! እንደ መልክአምድርሽ በአስተሳሰባቸው ቆላና ደጋ የሆኑ ሰዎችን አቅፈሽ በሰላም ከማኖር ይልቅ፣ ጊዜ የሰጠውን ቅልሽን በድንጋዮች ላይ የምታበረቺ ንጹሑን ጋዜጠኛ መንግሥቱ አማራንከአቦምሳ አሳንቀሽ በዘብጥያሽ ያቀፍሽ ሆነሽ ሳለ እንድንረሳኝ የምትመጻደቂ ሐሰትን ገንዘብ ያደረግሽ ጨካኝና ይሉኝታ ቢስ ምድር ነሽ፡፡ አርሲ ሆይ! ወገኖቻችንን ያለ ርኅራኄ መቀርጠፍሽ ሳያንስና ፍትሕ ተጠይቀሽ ጆሮ ዳባ ለበስ ማለትሽ ሳያሳፍርሽ፣ ንጹሑን በግ ዮሴፍንም በፈርዖናዊው ወኅኒሽ ውስጥ የምትወረውሪ የልበ ደንዳናው ፈርዖን ድንኩ አልጋ ነሽ፡፡ አርሲ ሆይ! ይኸንን ሁሉ አስቀያሚ ገጽታ ይዘሽ 'እርሱኝ' ፣ማለትሽ ድሮውንም ዲያብሎስ ለጭካኔ መገለጫ ለማድረግ የመረጠሽ ይሉኝታ የማታውቂ ሐፍረታም መሆንሽን ያሳያል፡፡ ዳሩ ግን እንኳን ልትረሺ ይቅርና የያዘሽ ዲያብሎስ ዝናርና ትጥቁን ፈትቶ አንቺም ትፈወሺ ዘንድ የቅን ፈራጁ የእግዚአብሔር ፍትሕ ርትዕ የግድ የሚል ነውና የክርስቲያኖች ደም ዛሬም ይካሰስሻልና ልትረሽ የማትችይ ስለመሆንሽ ተፋሽን ቁረጪ፡፡ ይልቁንስ አርሲ ሆይ! 'ዝም በሉ፣ በጨለማ ልቀርጥፋቹህ' ማለትሽን ትተሽ፣ ከፍትሕ ጋር መቆምና ለቀረጠፍሻቸው ነፍሳት ፍትሕን መስጠት፣ በስቃይ ጉያሽ ውስጥ ያፈንሻቸውንም ኦርቶዶክሳውያንን ደግሞ መልቀቅና መጸጸት ለአንቺም ፈውስ ይሆንልሻል፡፡ ከዚያ ውጭ ያለው ጩኸትሽ ከንቱ ድካም ከመሆን ባለፈ የክርስትናን ታሪካ የማታውቂና የታሪክ ማኅደርም ያላገላበጥሽ የሰነፎች አለቃ መሆንሽን ከማሳየት ያለፈ ፋይዳ የለውም፡፡ ©ዲያቆን ዶክተር አረጋ አባተ

"ከዚያች ቀን በፊት ወንድ ወይም የወሲብ ግንኙነት አላውቅም ነበር። በተክሊል ማግባት ነበር ዕቅዴ አበላሽተውኝ ሄዱ ቢገድሉኝ ይሻለኝ ነበር።" በመከላከያ የተደፈረችው የአማራ ወጣት ለቢቢሲ የተናገረች
"ከዚያች ቀን በፊት ወንድ ወይም የወሲብ ግንኙነት አላውቅም ነበር። በተክሊል ማግባት ነበር ዕቅዴ አበላሽተውኝ ሄዱ ቢገድሉኝ ይሻለኝ ነበር።" በመከላከያ የተደፈረችው የአማራ ወጣት ለቢቢሲ የተናገረችው💔

አሳዛኝ መረጃ ከወደ ሐረርጌ‼️ በምዕራብ ሐረርጌ በጉባ ጉቱ እና አው ጉዲና ወረዳዎች እንዲሁም በጭሮ ወረዳ በረብሱ አካባቢ እስከ አሁን ድረስ #የስድስት አማራ ኦርቶዶክሳውያን ሕይወት በአሰቃቂ ሁኔታ ተቀጥፏል ። በምስራቅ ሐረርጌ እና ምዕራብ ሐረርጌ ዳር ዳር ባሉ ቦታዎች ላይ ኦርቶዶክሳዊያን አሁንም በስጋት ላይ ናቸው ። ይህ መረጃ መንጋውን ለሚጠብቁ አደራ ለተሰጣቸው ለሀገረ ስብከቱም ለቤተ-ክህነቱም የተላለፈ ቢሆንም አባቶች ዝምታን መርጠዋል ። ነፍስ ይማር ! በግፍ እየተገደ,ሉ ላሉ ኦርቶዶክሳዊያን ሁላችንም ድምጽ እንሁን !  💔😭😭😭

🔥የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል ሰሜን አማራ ቀጠና በላይ ዕዝ ራስ አሞራው ውብነህ ፫ኛ ኮር መብረቃዊ ጥቃት ፈፅሟል‼️ የአፋብኃ በላይ ዘለቀ እዝ ራስ አሞራው ውብነህ 3ኛ  ኮር በሚያሰታዳደረው ቀጠና ጠላት በብዙ አቅጣጫ የዘመተ ቢሆንም የራስ አሞራው ውብነህ 3ኛ ኮር ስቦ በማስገባት በቆረጣ እያደቀቀው ይገኛል። ከራስ አሞራው ውብነህ 3ኛ ኮር ውስጥ ጭና ክፍለጦር እና ድብ ጠለምት ክፍለ ጦር በጥምር ከ 7/3/2018 እስከ 8/3/2018 ጥራይና ከምትባል ንዑስ ወረዳ የገባውን  ሲያደባዩት ሰንብተዋል::በዚህም አስደማሚ ውጤት ተግኝቷል:: በቀን 9/2018 ደግሞ ከዳባት ወደ አጅሬ ከአጅሬ ወደ ዳባት በሚሰደው መንገድ የዳባት እና የአጅሬ ጠላት ታች አረቡር ቀብሌ ላይ አመራር ተቀባብሎ የዳባቱ ወደ ዳባት የአጅሬው ወደ አጅሬ ሲመለስ  የደጃች አያሌው ብሩ ክፍለ ጦር ሰራዊት አቦ ገዳም ከሚባል ቦታ እና አስራ ሶስት ተብሎ ከሚጠራው ቦታ ላይ ከሁለት ቦታ ደፈጣ በመጣል በሲኖ እና በኦራል ሲኳዝ ከነበረው አረመኔ አራዊት ሰራዊት በሲኖ የተጫነውን አረመኔ ደም ጠጭ የዓብይ ወንበር አስጠባቂ አራዊት ሰራዊትን #ሙሉ_በሙሉ_በቦንብ_አጋይተውታል:: በኦራል ወታደራዊ ተሽከርካሪ ሲጓጓዙ የነበሩት ሰራዊት ከእነ ኦራላቸው ከጥቅም ውጭ የተደረጉ ሲሆን ከ30 በላይ ሲሞት ከ20 በላይ ከባድ ሰብዓዊ ጉዳት ደርሶበት ወደ ዳባት አፈግፍጓል።   በሌላ አቅጣጫ የተጠጋ ጠላት ጋር በቀጠናው አውደ ውጊያው ተጠናክሮ የቀጠለ ሲሆን የተሟላ መረጃ በቀጣይ የምናደርስም ይሆናል።       ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን!!  አፋብኃ ሰሜን አማራ ቀጠና  በላይ ዕዝ               10/ዐ3/2018 ዓ.ም

አሁናዊ መረጃ ወለጋ‼ ፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨ ማህበረሰባችን አዝመራ ስብሰባ ላይ መሆኑን ተከትሎ ብንችል እንወስደዋለን ባንችል ግን አቃጥለነው እንወጣለን ባሉት መሰረት ከትናንትና ማታ ጀምሮ ከጉዳያ ቢላ ከአቤዶንጎሮና ከጊዳ አያና ወረዳዎች የተወጣጣ ሀይል ወደ ውባንጭ ማምራቱን ተከትሎ በአሁኑ ስዓት ሆሮ ጉዱሩ ወለጋ ዞን አቤዶንጎሮ ወረዳ የአማራው ማህበረሰብ ብቻ የሚኖርባት ውባንጭ ቀበሌ ላይ ሀይለኛ በከባባድ መሳርያ የታገዘ ጦርነት እዬተደረገ እንደሚገኝና እናቶች እህቶችና አዛውንቶች አካባቢውን ለቀው  እዬተሰደዱ እንደሚገኙ የአካባቢው ኗሪዎች ለቢዛሞ ሚዲያ ገልጸዋል። ድል ለተገፋው የአማራ ህዝብ‼ ህዳር 10/2018ዓ.ም    

ህዳር 10/2018 ዓ.ም መዋቅራችን እየጠነከረ ሲመጣ ሌባው መፈርጠጥ ጀምሯል።   ህግ የማስከበር ዘመቻችን ተጠናክሮ የሚቀጥል ይሆናል ድርጅታችን እና መሪወቻችን የመጠበቅ ግዴታ አለብን በፋኖ መዋቅር ውስጥ ተሰግስገው በስውር የብልፅግናን ተልዕኮ በማስፈፀም ትግሉን ሲበጠብጡ እና ማህበረሰቡን ሲያሰቃዩ የነበሩ የበግ ለምድ የለበሱ ተኩላወች ፋኖ አሰራሩን ሲያዘምን እና የጠነከረ መዋቅር ሲያመጣ ተልኳቸውን ለማስፈፀም እንደሚቸገሩ ስለተገነዘቡ ከቀጣሪያቸው ብልፀግና ጋር ተቀላቅለዋል።   ህዳር 9/2018 ዓ/ም ተመስገን ሽመልስ የተባለ ተላላኪ ሁለት አጃቢወችን ይዞ ምኒሻ ልቀበል በማለት ሁለት አጃቢዎችን ይዞ ወደግንደወይን ከተማ ሲጓዝ ነገሩ የገባው ገዛሃኝ የተባለው አንዱ አጃቢ ከግንደወይን ከተማ በቅርብ ርቀት ተታኩሶ በማምለጥ ከእውነተኛ ታጋይ ወንድሞቹ ፋኖዎች ጋር የተቀላቀለ ሲሆን ቅጥረኛዉ ወንድሞቹን ሲበላና ሲያስበላ የቆየው ተመስገን ሽመልስ ግን አንድ አጃቢ በመያዝ አሸባሪውን ብልፅግናን ተቀላቅሏል። "<<< ካልደፈረሰ አይጠራም "" ሐብታሙ የሱፍ የቴወድሮስ እዝ 201ኛ ኮር ህዝብ ግንኙነት ህዳር 10/2018 ዓ.ም

የእንግሊዙ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን ቢቢሲ የአብይ አህመድ አገዛዝ ወታደሮች በአማራ ክልል በንጹህን ሴቶች ላይ የፈጸሙትን አስገድዶ መድፈር የሚያጋልጥ ዝርዝር ሪፖርት አወጣ ቢቢሲ አማርኛ በአማራ ክልል በፋኖ እና በአገዛዙ ጦር መካከል እየተካሄደ ያለውን ውጊያ ተከትሎ በመከላከያ ሰራዊት አባላት በህዝቡ ላይ የሚደርሱ ግፎችን ፣ በወታደር የሚደፈሩ ሴቶችን እንዲሁም በግፍ የሚረሸኑ ወጣቶችን አስመልክቶ ዝርዝር ዘገባ አውጥቷል። በዘገባውም የባለታሪኮችን ስምና ማንነታቸውን የሚገልጹ ነገሮችን ለደህንነታቸው ሲል መቀየሩን አሳውቋል። ታሪኩ እንዲህ ይጀምራል እናት እሁድ ጠዋት ወታደሮች ወደ ቤቷ ሲመጡ ከስምንት ዓመት የእህቷ ልጅ ጋር እንደነበረች ትናገራለች። መከላከያው  ታኅሣሥ 27/2017 ዓ.ም የቤት ለቤት ፍተሻ እያደረገ ነበር። እናት የመከላከያ ሠራዊት የደንብ ልብስ የለበሱ ሦስት ወታደሮች ደቡብ ጎንደር ወደ ሚገኘው ቤታቸው እንደመጡ እና ስለማንነቷ እንዲሁም ፋኖዎች  ከምትሠራበት ጠላ ቤት እንደሚመጡ መጠየቅ መጀመራቸውን ትናገራለች። የ21 ዓመቷ እናት ፋኖዎች እንደሚመጡ ማረጋገጧን ትገልፃለች። "እንዴት ብለን እንዋሻለን? እንዴት ብለን እንክዳለን?" የምትለው እናት ነገሮች ወዲያው ብዙም ሳይቆዩ ተካረሩ ትላለች። ስለቤተሰቦቿ ማንነት ከጠየቋት በኋላ እናት ወታደሮቹ በአፀያፊ ቃላት እንደሰደቧት ትናገራለች። ከዚያም ሕፃኗ ማልቀስ ስትጀምር በመሣሪያቸው እንዳስፈራሯት ታስታውሳለች። እናት ከዚያም አንደኛው ወታደር በሌሎች ወታደሮች እርዳታ በእህቷ ልጅ ፊት እንደደፈራት ተናግራለች። "እንዳይጎዱኝ ተማፀንኳቸው። ታቦታትን እየጠራሁ ለመንኳቸው። ግን ልባቸው አልራራልኝም። አበላሹኝ።" እናት ብቻዋን አይደለችም፤ እናት የአማራ ክልል የትጥቅ እንቅስቃሴ ከተቀሰቀሰ ከሐምሌ 2015 ዓ.ም. ጀምሮ ወሲባዊ ጥቃት ደርሶባቸዋል ተብሎ ከሚታመኑ በሺህዎች ከሚቆጠሩ ሴቶች ውስጥ አንዷ ናት። ምንም እንኳ እውነተኛው ግጭት ነክ የወሲባዊ ጥቃት መጠን ሪፖርት ባለመደጉ እና ባለመርመሩ በትክክል ባይታወቅም፤ ቢቢሲ ያሰባሰበው መረጃ ከሐምሌ 2015 እስከ ግንቦት 2017 ዓ.ም. ድረስ ከስምንት ዓመት እስከ 65 ዓመት ዕድሜ ያላቸው በሺህዎች የሚቆጠሩ ሰዎች የአስገድዶ መድፈር ጥቃት እንደደረሰባቸው ያመለክታል። ገለልተኛ መገናኛ ብዙኃን በክልሉ ያለውን ግጭት ለመዘገብ በተጣለባቸው ክልከላ እና ገደብ ምክንያት ወደ ክልሉ መግባት ባይችሉም የቢቢሲ የናይሮቢ ጋዜጠኞች ቡድን የአስገድዶ መድፈር ጥቃት ተጎጂዎችን እና የጤና ባለሙያዎችን በማነጋገር ቀውሱ በሰብዓዊነት ላይ እያሳረፈ ያለውን ጠባሳ የሚመለከት መረጃ አግኝቷል። እናት የጥቃቱ ሰለባ ከመሆኗ በፊት በቤተሰቧ ውስጥ እንዳሉ ሌሎች ሴቶች ሁሉ በኦርቶዶክስ ሃይማኖት አስተምህሮ መሠረት በተክሊል የማግባት ዕቅድ ነበራት። "ከዚያች ቀን በፊት ወንድ  አላውቅም ነበር" ትላለች። "አበላሽተውኝ ሄዱ። ቢገድሉኝ ይሻል ነበር።" የ18 ዓመቷ ትዕግሥት የምዕራብ ጎጃም ነዋሪ ስትሆን የመድፈር ጥቃቱ ከመፈጸሙ በፊት በቤተሰቦቿ ሻይ ቤት ትሠራ ነበር። ጥር 2016 ዓ.ም. 'ሻይ ቡና' ለማለት የሚመጣ ወታደር ተደጋጋሚ ጉንተላ ሲያደርስባት፤ "ሥነ ሥርዓት ያዝ" በሚል የሰጠችው ምላሽ ለደረሰባት ጥቃት ዋነኛ ምክንያት እንደሆነ ታምናለች። "'ቆይ አሳይሻለሁ' ብሎ ዝቶብኝ ወጣ።" ምሽት አካባቢ ከሥራ ወደ ቤት ስትመለስ ትዕግሥት ቀን ላይ የጎንተላትን ጨምሮ ሦስት ወታደሮች መንገድ ላይ አድፍጠው እንደጠበቋት እና መንገድ ዳር በደቦ እንደደፈሯት ተናግራለች። "ቤተሰቦቼ ስቆይባቸው እኔን ፍለጋ ሲወጡ መንገድ ዳር ወድቄ አገኙኝ" ስትል ታስታውሳለች ትዕግሥት። "አፋፍሰው ወደ ጤና ጣቢያ ወሰዱኝ። እዚያም አምስት ቀን ቆየሁ።" ጥቃቱ ከተፈጸመባት ጊዜ አንስቶ ትዕግሥት በሰዎች እና በውጭው ዓለም ፍርሃት ተሸብባ ከቤቷ መውጣት እንደማትችል ትናገራለች። "ፍርሃት ስላደረብኝ ሥራውንም ተውኩት። . . . ወታደሮችን ሳይ በጣም እፈራለሁ። ወንዶችንም ሳይ ፍርሃት ያድርብኛል፤ እሸሻለሁ" ትላለች ጥቃቱ ከደረሰባት ከዓመት በኋላ። ትዕግሥት የምታውቀው ሕይወት እንዴት እንደተመሰቃቀለ ስትገልፅ ከእጮኛዋ ጋር መለያየቷን እና ምን እንደተፈጠረ ምክንያቷን እንዳልነገረችው ትገልፃለች። በተስፋ መቁረጥ ስሜት የተዋጠችው ትዕግሥት ራሷን ለማጥፋት ብትሞክርም ቤተሰቦቿ በጊዜ ደርሰው አትርፈዋታል። ከዚህ ጊዜ በኋላ ትዕግሥት በተደጋጋሚ ራሷን ለማጥፋት አስባ እንደነበር ሳትደብቅ፤ ነገር ግን ለቤተሰቦቿ ራሷን ለማጥፋት በድጋሚ እንደማትሞክር ቃል መግባቷን ተናግራለች። ቢቢቢ በአማራ ክልል ስለተፈጠረው ቀውስ መረጃ ለማግኘት 4 በመቶ ከሆኑት የክልሉ 43 ጤና ጣቢያዎች እና የሕክምና ምንጮች መረጃዎች መሰብሰቡን ይገልጻል በእነዚህ ተቋማት ከሐምሌ 18/2015 ዓ.ም. እስከ ግንቦት 2017 ዓ.ም. ድረስ 2,697 ሰዎች የአስገድዶ መድፈር ጥቃት እንደደረሰባቸው ሪፖርት አድርገዋል። ከእነዚህም ውስጥ 45 በመቶ የሚሆኑት ከ18 ዓመት በታች የሆኑ ታዳጊዎች ናቸው። ከተጎጂዎች ውስጥ ከግማሽ በላይ የሚሆኑት በደረሰባቸው ጥቃት በአባላዘር በሽታ ሲያዙ፤ በርካቶች ደግሞ ለእርግዝና እና ለከባድ የሥነ ልቦና ቀውስ ተዳርገዋል። ይሁን እንጂ በርካታ የወሲባዊ ጥቃት ተጎጂዎች መገለልን በመፍራት፣ የአባላዘር በሽታ መያዛቸውን ወይም መፀነሳቸውን ላለማወቅ የተፈፀመባቸውን የመደፈር ጥቃት ሪፖርት ማድረግም ሆነ የሕክምና አገልግሎት ማግኘት አይፈልጉም። ለዚህም ነው በደኅንነት ስጋት ስማቸው እንዳይጠቀስ የፈለጉ አንድ ከፍተኛ የጤና ባለሙያ በአማራ ክልል ግጭት ወደ ጤና ተቋማት የመጡ ተጎጂዎች "ከባሕሩ በጭልፋ ናቸው" የሚሉት። ለምለም እንደ ኤችአይቪ ዓይነት በሽታ ተላልፎብኝ ሊሆን ይችላል በሚል ስጋት የተፈፀመባትን የአስገድዶ መድፈር ጥቃት ሪፖርት ካላደረጉት እና የሕክምና እርዳታ ካላገኙ ተጎጂዎች መካከል ናት። የ23 ዓመቷ የደቡብ ጎንደር ነዋሪ ታኅሣሥ 28/2017 ዓ.ም. የመንግሥት ወታደሮች በተለመደ እንቅስቃሴያቸው "መሣሪያ ያለውን ሠው ጠቁሚን ብለው" መረጃ ፍለጋ ወደ ቤታቸው መምጣታቸውን ትናገራለች። የሚፈልጉትን መረጃ ባለመስጠቷ አንደኛው ወታደር ከዛተባት በኋላ እንደደፈራት ተናግራለች። "'ጩኸት ብታሰሚ አንድ ጥይት ነው የሚበቃሽ' ብሎ አስፈራራኝ" ትላለች ለምለም። አንድ ወር ሙሉ አለቀስኩ። ምግብ አይርበኝም። ሥራዬ ማልቀስ ብቻ ቆሜ ለመሄድም ተቸገርኩ። ሕመምተኛ ሆንኩ።" ማኅበረሰባዊ ሐሜትን በመፍራት ጭንቀት ውስጥ መግባቷን የምትናገረው ለምለም፤ ከቤተ ክርስቲያን መራቋንም ተናግራለች። "ሴት ሆኖ መፈጠር ያስጠላል። ወንድ ብሆን ደብድበው ጥለውኝ ይሄዳሉ እንጂ እንደዚህ ሕይወቴን አያበላሹትም ነበር" ስትል ለምለም የደረሰባት ጥቃት ቁስል በሴትነቷን ላይ ያሳደረባትን ከባድ ስሜት ታብራራለች። "እያለቀሱ፤ በፍርሃት እየተንቀጠቀጡ፤ ለማውራት እየከበዳቸው ነው የሚመጡት" ሲሉ አንድ የጤና ባለሙያ የተጎጂዎችን ስሜት ይገልፃሉ። ሆኖም ወደ ጤና ተቋማት የሚመጡ ተጎጂዎች የአጥቂዎቻቸውን ማንነት ለመናገር እንደሚያመነቱ እና ፍትሕን ፈልገው እንደማይመጡ ባለሙያዎች አመልክተዋል። ይህም በከፊል በግጭቱ ምክንያት ሕግ እና ሥርዓት በመስተጓጎሉ ነው። ቢቢሲ ያነጋገራቸው የጤና ባለሙያዎች ለሕክምና ወደ ጤና ተቋማት የሚመጡ ተጎጂዎች በእርግዝና ፍርሃት ምክንያት መሆኑን ተናግረዋል።

ሰበር ሰበር !! #አምስት_የአገዛዙን_ሰራዊት_አባላትን_አጋድመው_ሁለት_ክላሽ_ከእነሙሉ_ትጥቁ_ደርበው #64ኛ_ክፍለጦር_ተቀላቀሉ። ህዳር 10/2018 ዓ.ም አማራ በመሆናቸው ብቻ በደባ እንዲገደሉ በአገዛዙ አመራሮች ትዛዝ የተሰጠጠው የታጠቁት ስናይፐር የወረደባቸው በጄሌ እንዲንቀሳቀሱ የተደረጉት የአገዛዙ የአረመኔዊ የመከላከያ ሰራዊት አባላት የነበሩ:- 1ኛ. ሙሉቀን ንጉስ 6ኛ ዕዝ 14 ክ/ጦር 1ኛ ሬጅመንት 2 ኮሪያ ክላሽ እና 220 ጥይት በመያዝ 2ኛ. አንደበት ሞላ 2 ኮሪያ ክላሽ 220 ጥይት 4 ኤፍዋን ቦንብ 2 ካዘና በመያዝ 3ኛ. ዘነበዉ ደሴ 1 ኮሪያ ክላሽ 4 ኤፍዋን ቦንብ 4 ካዘና በመያዝ በአጠቃላይ 5 ክላሽ 440 ተተኳሽ እና 8 ኤፍዋን ቦንብ ደርቦ በመያዝ ህዳር 10/2018 ዓ.ም #በእነማይ_ወረዳ_ወይራ_ቀበሌ በእንቅልፍ ላይ የነበሩ የአገዛዙ አረመኔዊ ሰራዊት አባላትን በማስወገድ በዋርድያ ላይ የነበሩ ጥበቃዎችን አስወግደው ከአምስት በላይ ሙት እና ቁስለኛ አድርገው የአፋብኃ ቴዎድሮስ ዕዝ 201ኛ ኮር #64ኛ_ክፍለጦር ከእነ ሙሉ ትጥቃቸው ተቀላቅለዋል። በተጨማሪም በእነማይ ወረዳ #ቢቸና ከተማ መሽጎ የሚገኘው የአገዛዙ አረመኔዊ ሰራዊት አባላት እየፈራረሰ ይገኛል። ህዳር 10/2018 ዓ.ም አራት የአገዛዙ አረመኔዊ ሰራዊት አባላት:- 1ኛ. በላይነህ ካሳ 2ኛ. ደመቀ አሰፋ 3ኛ. አዲሴ ያዜ 4ኛ. ጊዚአለው ክንዱ የተባሉ ቢቸና ከተማ ከሚገኜው 75ኛ ክፍለ ጦር ቀኝና መሀንዲስ የነበሩ የአገዛዙ አረመኔዊ ሰራዊት አባል አገዛዙ በአማራ ህዝብ ላይ እያካሄደ ያለውን ዘር ተኮር ጭፍጨፋ በመረዳት የአፋብኃ ቴዎድሮስ ዕዝ 201ኛ ኮር #64ኛ #ክፍለጦር ከእነሙሉ ትጥቃቸው ተቀላቅለዋል። አዲስ ትውልድ፣አዲስ አስተሳሰብ፣አዲስ ተስፋ! ፋኖ ይበልጣል 64ኛ ክፍለ ጦር ሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ

BBC በአማራ ክልል ስለተፈጠረው ቀውስ መረጃ ለማግኘት 4 በመቶ ከሆኑት የክልሉ 43 ጤና ጣቢያዎች እና የሕክምና ምንጮች መረጃዎች ሰብስቧል። በእነዚህ ተቋማት ከሐምሌ 18/2015 ዓ.ም. እስከ ግንቦት 2017 ዓ.ም. ድረስ 2,697 ሴቶች በመከላከያ የአስገድዶ መድፈር ጥቃት እንደደረሰባቸው ሪፖርት አድርገዋል። ከእነዚህም ውስጥ 45 በመቶ የሚሆኑት ከ18 ዓመት በታች የሆኑ ታዳጊዎች ናቸው።

201ኛ የኮር አመራሮች ክ/ጦሮችን የማብቃት ድጋፍ እና ክትትል ስራ ተሰራ። አፋብሃ የቴዎድሮስ እዝ 201ኛ ኮር ድርጅቱ እያደረገ ያለውን ፈጣን የሆነ የሽግግር፣ የኮር እና የክ/ጦር አደረጃጀቶችን በ
+2
201ኛ የኮር አመራሮች ክ/ጦሮችን የማብቃት ድጋፍ እና ክትትል ስራ ተሰራ። አፋብሃ የቴዎድሮስ እዝ 201ኛ ኮር ድርጅቱ እያደረገ ያለውን ፈጣን የሆነ የሽግግር፣ የኮር እና የክ/ጦር አደረጃጀቶችን በፍጥነት የማሳደግ፣ የመፐወዝ እና ጊዜያዊ የወረዳና የቀበሌ መዋቅሮችን አደራጅቶ በማጠቃለል ያጋጠሙ ችግሮችን በማንሳት ውይይት አካሂዷል። በዚህ ውይይትም የ74ኛ ክ/ጦር ሰብሳቢ ክ/ጦሩ ባለፉት 2ሳምንታት የሰራቸውን ስራዎች፣ ያጋጠሙ ችግሮች፣ የተወሰዱ መፍትሄዎችና በቀጣይ ስለሚሰሩ ተግባራት በመለየት ከኮሩ በመጡት ድጋፍ ሠጭ አመራሮች የኮሩ የፖለቲካ ሃላፊ የኮሩ ም/ጦር አዛዥ የ74ኛ ክ/ጦር አመራሮች በተገኙበት አንድ ቀን የፈጀ ግልፅ ውይይት ተካሂዷል። ከዚህ በተጨማሪም በቀጣይ በክ/ጦሩ መሰራት ስላለባቸው ኢኮኖሚያዊ እና ፖለቲካዊ አሰራሮችን አዘምኖ እንዲቀጥል የሚያስችሉ ብልሃቶችን በመነጋገር የድርጅቱን ስራወች የበለጠ ወደፊት አጠናክረው እንደሚቀጥሉ የጋራ የስራ ስምሪት በመስጠት ውይይቱ ተጠናቋል። የቴድሮስ እዝ 201ኛ ኮር ህዝብ ግንኙነት ህዳር 10/2018 ዓ.ም

ከቆቦ ከተማ በቅርብ ርቀት ላይ በተደረገ አውደ ውጊያ በርካታ ወታደሮች ሙትና ቁስለኛ መደረጋቸው ታወቀ! የሐውጃኖ ክፍለጦር እና አሳምነው ክፍለጦር አሃዶች በጥምረት ጮቢ በር ባደረጉት ተጋድሎ ታላቅ ድል ማስመዝገባቸው ታውቋል። በአፋብኃ ምኒልክ ዕዝ ምስራቅ አማራ ኮር 1 የሐውጃኖ ክፍለጦር እና አሳምነው ክፍለጦር አሃዶች በጥምረት ህዳር 8/2018 ዓ.ም ከቀኑ 9:00 ጀምሮ ራያ ቆቦ ጮቢ በር እና አዩብ አካባቢ ባደረጉት ተጋድሎ በርካታ የጠላት ሃይል ሙትና ቁስለኛ በማድረግና የጠላትን የማጥቃት እቅድ በማክሸፍ ታላቅ ድል ተጎናፅፈዋል:: የፋሽስቱ ብልፅግና ሰራዊት ከመሸገበት ጮቢ በር ወደ አዩብ መድፍ ቢ ኤም ሞርተርና ዙ23 በመያዝ ማጥቃት ያደረገ ሲሆን የሁለቱ ክፍለጦር አሃዶች በጥምረት ባደረጉት ድንቅ መከላከልና መልሶ ማጥቃት አመራሮችና የቡድን መሳሪያ ተኳሾችን ጨምሮ በርካታ የጠላት ሃይል ሙትና ቁስለኛ በማድረግና ወደ መጣበት ጮቢ በር በመመለስ ታላቅ ድል ተጎናፅፈዋል:: ቀን 9:00 ጀምሮ እስከ ምሽት 2:30 ድረስ በዘለቀው ተጋድሎ በርካታ ሰራዊቱ የተመታበት ጠላት በአምቡላንስና በኦራል ቁስለኛ ወደ ወልድያ እያመላለሰ ባለበት ሁኔታ ቆቦ ከተማ አካባቢ አንድ ባጃጅና ሁለት ብስክሌት በመግጨት በሰው ህይወትና በንብረት ላይ ጉዳት አድርሷል:: በተጋድሎው ከባድ ሽንፈት የደረሰበት ፋሽስቱ አገዛዝ ህዝብ በሚበዛባቸው የመኖሪያ አካባቢዎች ማለትም ራያ ቆቦ አማያ አዲስ አለም እና ቢጭሮ የሚባሉ አካባቢዎች እንዲሁም ራያ አላማጣ ኩቢ ቀረንሳ እና ቦታ ማርያም የተለያዩ ከባድ መሳሪያዎችን በማስወንጨፍ ሶስት ሰዎች በከባድ ሁኔታ ያቆሰለ ሲሆን በእንስሳቶችና በቤት ንብረትም ላይ ጉዳት አድርሷል:: የቴሌግራም ገፃችን

ኦርቶዶክሳውያን አይገደሉ ብለው የሚጽፉ የቤተ ክርስቲያኒቱ ልጆች በአገዛዙ እየታፈኑ ነው ተባለ። ሰሞኑን በአርሲ ዞን "ለምን ኦርቶዶክሳውያን እየተለዩ ይገደላሉ" በሚል አዲስ አበባ ያሉና በመላው ኢት
ኦርቶዶክሳውያን አይገደሉ ብለው የሚጽፉ የቤተ ክርስቲያኒቱ ልጆች በአገዛዙ እየታፈኑ ነው ተባለ። ሰሞኑን በአርሲ ዞን "ለምን ኦርቶዶክሳውያን እየተለዩ ይገደላሉ" በሚል አዲስ አበባ ያሉና በመላው ኢትዮጵያ የሚኖሩ እንዲሁም በውጭ ሀገር ያሉ ኢትዮጵያውያን ወጣቶች የተለያዩ የማኅበራዊ ሚዲያ "የአትግደሉን" ዘመቻ እያደረጉ ነበር። ከእነዚህ ወጣቶችና ምእመናን መካከል ትጉኅና አሳላሳይ የሆነው ከዚህ በፊትም "ቤተ ክርስቲያን ልዕልናዋ ይከበር መንግሥት ጣልቃ መግባቱን ያቁም" በማለቱ በአገዛዙ ለእሥር ተዳርጎ የነበረው ዲያቆን ዮሴፍ ፍሥሓ ከቀናት በፊት ከአዲስ አበባ ከሥራ ቦታው ታፍኖ ተወስዶ የት እንዳለም ቤተሰቦቹ እንደማያውቁ ነው የተገለጸው። የአንድን ሕጋዊ ተቋም ለዚያውም ጥንታዊቷን፣ ሀገር መሥራችና ጠባቂ የሆነችውን የቅድስት ቤተ ክርስቲያንን ሕልውና የማክበር ግዴታ ያለበት የብልጽግናው መንግሥት፤ ስገድላችሁ ዝም በሉ በማለት ምእመናንን እየገደለና እያሠረ፣ ለገዳዮችም ሕጋዊ ሽፋን እየሰጠ፣ በሞቱት ላይም ፖለቲካዊ ዘገባና ሪፖርት በብሔራዊ ቴሌቭዥን እያሠራጨም ነበር።

በሸበል በረንታ ወረዳ ባንዳው እርምጃ ተወሰደበት! ህዳር 09/2018 ዓ.ም አለመኘው ዋለ የተባለ የአገዛዙ ቅጥርኛ በሸበል በረንታ ወረዳ ሰለልኩላ ቀበሌ ተወላጅ የነበር የአገዛዙ አረመኔዊ ሰራዊት ህ
+1
በሸበል በረንታ ወረዳ ባንዳው እርምጃ ተወሰደበት! ህዳር 09/2018 ዓ.ም አለመኘው ዋለ የተባለ የአገዛዙ ቅጥርኛ በሸበል በረንታ ወረዳ ሰለልኩላ ቀበሌ ተወላጅ የነበር የአገዛዙ አረመኔዊ ሰራዊት ህዳር 08/2018 ዓ.ም ከመርገጭ ንዑስ ወረዳ ወደ የዕዱኃ ከተማ በጉዞ ላይ እያሉ የፋኖ ሀይሎችን ለመክበብ ሲሞክር በሽፈራው ገርባው ልጆች በተደርገው የተኩስ ልውውጥ በቁጥጥር ስር ውሎ በሽፈራው ገርባው ልጆች እርምጃ ተወስዶበታል። ቴወድሮስ ዕዝ 201ኛ ኮር ህ/ግንኙነት ፋኖ ሐብታሙ የሱፍ            ህዳር 09/2018 ዓ.ም

ሰበር ዜና! የደጋው መብረቅ ኮር በርካታ የአገዛዙ ሰራዊት በመደምሰስ እና የከፍተኛ መኮነኖችን ተሽከርካሪ በመማረክ ታላቅ ድል ተጎናፀፈ:: ህዳር 9/2018 ዓ/ም በመቄት ወረዳ አንሻ ክፍለ ጦር በጥ
+1
ሰበር ዜና! የደጋው መብረቅ ኮር በርካታ የአገዛዙ ሰራዊት በመደምሰስ እና የከፍተኛ መኮነኖችን ተሽከርካሪ በመማረክ ታላቅ ድል ተጎናፀፈ:: ህዳር 9/2018 ዓ/ም በመቄት ወረዳ አንሻ ክፍለ ጦር  በጥላት ላይ ትልቅ ታሪክ በመስራት ከቤተ-አማራ እስከ ሸዋ እየተምዘገዘገ ብዙ ታሪኮችን ሲሰራ የነበረው ጨለፍ አስፋው ከትግል አጋሩ አርበኛ ቅዱሴ ጋር በጋራ በመሆን በመሩት ተጋድሎ በፋሽስቱ ሰራዊት ላይ ታላቅ ጀብድን በመፈፀም ታላቅ ድል ተቀናጅተዋል። የፋሽስቱ ሰራዊት አንድ ፓትሮልና በርካታ ሲኖትራክ መኪናዎች የተማረኩ ሲሆን በርካታ የጥላት  ሰራዊትችም ተደምስሰዋል። የተማረኩት ሲኖ ትራኮች የግለሰብ በመሆናቸው ለባለቤቶቹ እንዲመለሱ አድርገናል:: በአማራ ህዝብ ላይ ጥፋትንና ጭፍጨፋን ተጭኖ የመጣው የስርዓቱ ቅጥረኛ ሰራዊት በአንሻ ክፍለ ጦር ሙትና ቁስለኛ ተደርጓል። የብርሀኑ ጁላ ሰራዊት በመቄት ወረዳ እንደ ክረምት አግቢ እድሜ በፋኖዎች ባሩድ እየተቀነደሸ እና እየተቀሰፈ ይገኛል። መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልዉና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል! ህልዉናችን በተባበረ ክንዳችን! የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል (አፋብኃ) የደጋው መብረቅ ኮር  አንሻ ክፍለ ጦር ህዳር 9/2018 ዓ.ም