ru
Feedback

Не попадитесь на канал ботавода! Telemetrio находит и помечает такие каналы 👉 Хотите видеть метку — оформите подписку

ፍኖተ-አማራ ሚዲያ (Finote Amhara Media)

ፍኖተ-አማራ ሚዲያ (Finote Amhara Media)

Открыть в Telegram

የተመሠረተው የአማራን ሕዝብ ለማንቃት፣ ለማደራጀት እና ለማስተባበር ነው። የአማራ ሕዝብን ✅ ፖለቲካዊ ✅ ማህበራዊ ✅ ኢኮኖሚያዊ ታሪካዊ ጥያቄዎችን ለማሰማት እና የአማራን ሕዝብ በማንቃት ሰፊውን ሕዝብ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ይሰራል። ወደዱም ጠሉም የኃላ ታሪካችን በእኛ እጅ ይፃፋል። አማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ ( አፋብን)

Больше
4 406
Подписчики
+1324 часа
+277 дней
+1 21530 дней
Архив постов
በዘመቻ አደም አሊ(አባናደዉ) ዘመቻ የተማረኩ የሚሊሻ እና የፖሊስ አባላት በፍቃዳቸዉ ፋኖን እንደሚቀላቀሉ ተናገሩ። አፋብኃ ምስራቅ አማራ ቀጠና ሚኒልክ ዕዝ ከ መስከረም 14/2018 እስከ መስከረም 30/2018 ዓ.ም  በፈጀዉ ዘመቻ አድም አሊ(አባ ናደዉ) አመርቂ ድል ማስመዝገቡ የሚታወቅ ሲሆን በዚህም ዘመቻ ላይ የአገዛዙ የብልፅግና ሰራዊት  ቡዙ አካላዊ እና ቁሳዊ ኪሳራ እንደደረሰበት ይታወቃል። በዚህም ዘመቻ ላይ ከ679 ምርኮኞች መካከል 100ዎቹ የፖሊስ እና የሚሊሻ አባላት ሲሆኑ እነዚህ ምርኮኞችም እስካሁን በማወቅም ባለማወቅም  የአማራን ህዝብ በድለናል ከአሁን ስዓት  ጀምሮ ህዝባችንን በበደልነዉ ልክ  ከፋኖ ወንድሞቻችን ጋር ተቀላቅለን እንክሰዋለን ሲሉ ተናግረዋል። ምርኮኞቹ አክለዉም ይህ ፋሽዝም ስርዓት ምላሱ ብቻ እንደቀረ ገልፅዉ አሁንም በዚህ አገዛዝ ስር ያላቹህ ፋሽስቱ የብልፅግና አገዝ ጥምር ጦር የሚላቹህ የሰራዊት አባላት እና አመራሮች አሁንም ሳይረፍድባቹህ ያላቹህበት ስርዓት አገር አፍራሽ መሆኑን አዉቃቹህ ወደ እዉነተኛ ትግል ወደሆነዉ የአማራ ፋኖ እንድትቀላቀሉ ሲሉ ጥሪ አቅርበዉ እኛ ተማርከን ህይወታችን ሰለተረፈ እድለኞች ነን ብለዋል። በዚህም ለይ የ አፋብኃ ምስራቅ አማራ ቀጠና ሚኒልክ  ዕዝ ፅ/ቤት ኃላፊ አርበኛ ደስታዉ መለሰን ጨምሮ  ሌሎች የድርጅቱ ከፍተኛ አመራሮች እና የዚሁ ዕዝ ክንፍ የሆነዉ  ግዙፉ ላስታ አሳመነዉ ኮር ከፍተኛ አመራሮች ተገኝተዉ ምርኮኞችን በሚፈልጉት ቀጠና ባሉት ኮሮች እና  ክ/ጦሮች ሂደዉ እንዲታገሉ የድልድል ስራ ሰርተዋል። መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልዉና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል! አፋብሃ ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ ላስታ አሳመነዉ ኮር ሚዲያ እና ኮምኒኬሽን ክፍል ኋላፊ ጋዜጠኛ ፋኖ ደረበ መኮንን! ጥቅምት 15 /2018 ዓ.ም

ለሰራዊታችንና አመራሩ!
ለሰራዊታችንና አመራሩ!

የአፋብኃ ምዕራብ አማራ ቀጠና ቴዎድሮስ ዕዝ ሳሙኤል አወቀ ክፍለ ጦር አባይ ሸለቆ ብርጌድን ( 4 )አራት የሚሊሻ አባላት ተቀላቅለዋል። ከደብረወረቅ ከተማ እና መርጠለ ማሪያም ከተማ የሚገኜው የአብይ
+3
የአፋብኃ ምዕራብ አማራ ቀጠና ቴዎድሮስ ዕዝ ሳሙኤል አወቀ ክፍለ ጦር አባይ ሸለቆ ብርጌድን ( 4 )አራት የሚሊሻ አባላት ተቀላቅለዋል። ከደብረወረቅ ከተማ እና መርጠለ ማሪያም ከተማ የሚገኜው የአብይ አህመድ አረመኔው አገዛዙ እየፈፀመ ያለውን አፀያፊ ተግባር በመረዳት  አባይ ሸለቆ ብርጌድን ተቀላቅለዋል። 1, ብርቁ አስኔ 2, አበበ ደምሴ 3, አየነው ላቄ 4, አበረ ቸሩ የተባሉ የአገዛዙ ተልዕኮ አስፈፃሚ ሚሊሻ እንደተናገሩት በሁሉም ከተማ የሚገኜው የማሊሻ አባል መውጫ ቀዳዳ ፍለጋ ላይ እንደሆነ እና የአማራ ፋኖ እንደሚቀላቀል አስርድተዋል። በ2ተኛ ተፈራ ዳምጤ ክፍለ ጦር በሚያደረጋቸው የሰርጎ ገብ እና የደፈጣ ውጊያ እንዲሁም መደበኛ ውጊያ ያስመረራቸው የአገዛዙ የሚሊሻ አባላት ወደ ፋኖ ተቀላቀሉ። 1.ጎሹ በሌ 2.ደሳለኝ ጌታ 3.ዮሐንስ ዳኛው 4.ይበልጣል ሽታየ መላኩ 5.ቸኮል ተሆነ 6.ጌታሰው ደሜ 7.ይርጋ ሰዋለኝ የተባሉ የሚሊሻ አባላት ትጥቅ የሌላቸው የጓደኛቸውን መሳሪያ በመቀማት ቀሪዎቹ  ያለ ትጥቅ ወደ ፋኖ በመምጣት ህይወታቸውን ማትረፍ ችለዋል። በሌላ ስቦ ማስከዳት ሁለት የአረመኔው ብልጽግና ሠራዊት አባላት ቀኝ ጌታ ዮፍታሄ ንጉሴ 6ኛ ክፍለ ጦር የኢንጅነር ክበር ተመስገንን ብርጌድ  ተቀላቅለዋል። 1/ ነብዩ አርባ ወላይታ 2/ ሙዲን ኢብራሄም የተባሉ የ23ኛ ክፍለጦር አምስተኛ ሬጅመንት ቲም መሪዎች የመከላከያ አባላት የኢንጅነር ክበር ተመስገን ብርጌድን ተቀላቅለዋል። አዲስ ትውልድ፣ አዲስ አስተሳሰብ፣ አዲስ ተስፋ !     ጥቅምት 15/2018 ዓ.ም

ጡት ቆራጩ የብልፅግና ቡድን በጎንደር ቋራ ቴዎድሮስ ከተማ በፈፀመው የድሮን ጥቃት፡ ቅዳሜ ገበያ ለመገብየት የተሰባሰቡ ገበያተኞች መገደላቸው ተሰምቷል። ዛሬ ጥቅምት 15/2018 ዓ/ም ረፋድ 4:00 አከባቢ በቋራ ቴዎድሮስ ከተማ የቅዳሜ ገበያ ለመገብየት በተሰባሰቡ ገበያተኞች ላይ በተፈፀመ የድሮን ጥቃት፡ በርካታ ንፁኋኖች ሲገደሉ በርካቶች መቁሰላቸው ታውቋል። በተመሳሳይ ይሄው ፀረ አማራ ኃይል ከቀናት በፊት በላይ ጋይንት ወረዳ ዛጎች ቀበሌ ላይ በፈፀመው የድሮን ጥቃት አንዲት እናት ከነ ልጇ ተገድላለች። ይህ ጡት ቆራጭና ፀረ አማራ የብልፅግና ኃይል ዛሬም በቋራ ቴዎድሮስ ከተማ የቅዳሜ ገበያን ለመገብየት በተሰባሰቡ ንፁኋኖች ላይ ዘግናኝ ጭፍጨፋ ፈፅሟል። Mereb media

ከጥይት የተረፈውን አንድ በአንድ እናፈርሰዋልን! መለሰ አይተነው ይባላል። በዛሬው ዕለት የጓደኛውን መሳሪያ ጭምር ይሶ ሶማ ብርጌድ የተቀላቀለ ሚሊሺያ ነው። ጠላት እየሟሟ እኛ ደግሞ በዛው ልክ እየጠ
ከጥይት የተረፈውን አንድ በአንድ እናፈርሰዋልን! መለሰ አይተነው ይባላል። በዛሬው ዕለት የጓደኛውን መሳሪያ ጭምር ይሶ ሶማ ብርጌድ የተቀላቀለ ሚሊሺያ ነው። ጠላት እየሟሟ እኛ ደግሞ በዛው ልክ እየጠነከርን እንገኛለን። አፋብኃ|ቴዎድሮስ ዕዝ ሕ.ግንኙነት መምሪያ           ጥቅምት 15/2018 ዓም

የፋሽስቱ ብልፅግና አገዛዝ ሰራዊት እየፈረሰ ፋኖን እየተቀላቀለ ነው:: ከዘመቻ አባ ናደው መጠናቀቅ በኋላ ከተለያዩ የክልሉ አካባቢዎችና ዕዞች ወደ ቤተ-አማራ የገባው የአብይ አህመድ ዙፋን ጠባቂ ሰራዊት እየፈረሰና እየኮበለለ ምኒልክ ዕዝን በስፋት እየተቀላቀለ ነው:: የኦሮሞ ብልፅግና ልዩ ሃይል ኦሮሚያ ላይ በአማራ ተወላጆች ላይ ሲፈፅመው የነበረውንና ዛሬም እየፈፀመው ያለውን ግፍ በተመሳሳይ የመከላከያ መለዮ ለብሶ ወደ አማራ ክልል በመግባት የሚፈፅመውን ግፍ እያየን እኩል የሃገር መከላከያ ሰራዊት ተብለን ልንጠራ አንችልም ያሉ አባላቶቹ ባለፉት አስር ቀናቶች ብቻ 4 ስናይፐርና 28 ክላሽ 7000 የክላሽ ተተኳሽ 600 የስናይፐር ተተኳሽ እንዲሁም 60 የእጅ ቦምብ በመያዝ ከ32 በላይ ሰራዊት ምስራቅ አማራ ኮር 1 አሳምነው ክፍለጦርን ተቀላቅለዋል:: ፋኖን ከተቀላቀሉት የ104ኛ ኮር የሰራዊቱ አባላቶች መካከልም 4 ሻምበል መሪና 3 የመቶ መሪ አመራሮች ይገኙበታል:: በቀጣይም የፋሽስቱ ብልፅግና አገዛዝን ሰራዊት የማፍረስና የማስኮብለሉ ስራ ተጠናክሮ ይቀጥላል:: •ማስታወሻ፦ ስም ዝርዝርና ምስል ያላካተትነው በቀጣይ ለምንሰራው ስራ ደህንነት ስንል ነው! መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልዉና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል! ህልዉናችን በተባበረ ክንዳችን! አፋብኃ ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ ጥቅምት 15/2018 ዓ.ም

በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል በዘይሴ ማሕበረሰብ እና በአገዛዙ ወታደሮች መካከል ከባድ ግጭት መቀስቀሱ ተሰምቷል! የዘይሴ ማሕበረሰብ "የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር የሆነው አቶ ጥላሁን ከበደ በ
በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል በዘይሴ ማሕበረሰብ እና በአገዛዙ ወታደሮች መካከል ከባድ ግጭት መቀስቀሱ ተሰምቷል! የዘይሴ ማሕበረሰብ "የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር የሆነው አቶ ጥላሁን ከበደ በፌደሬሽን ምክር ቤት ያለውን ተሰሚነት ተጠቅሞ የዘመናት የልዩ ወረዳ ጥያቄያችንን አፍኖብናል" በሚል የስራ ማቆም አድማ ያደረጉ ሲሆን፡ የወረዳና የክልሉ ፀጥታ ኃይሎች የስራ ማቆም አድማውን ለማስነሳት ሲንቀሳቀሱ ከባድ የሆነ ጥቃት ተከፍቶባቸዋል። ለክልሉና ለወረዳው ፀጥታ አካላት እገዛ ለማድረግ ወደ አከባቢው የገባው እራሱን "መከላከያ ሰራዊት" እያለ የሚጠራው የመንደር ዱርየ ስብስብ፡ ማሕበረሰቡ ላይ የዘፈቀደ ተኩስ በመክፈት በርካቶችን ለሞትና ለአካል ጉዳት እንደዳረጋቸው የመረብ ሚዲያ ምንጮች ገልፀዋል። ማሕበረሰቡ በተደራጀ መልኩ በአገዛዙ ወታደሮች የተከፈተበትን ጥቃት እየመከተ ሲሆን፡ ትናንት በስቲያ ጥቅምት 13/2018 ዓ/ም ምሽት ላይ በተፈፀመ ደፈጣ ጥቃት በአንድ ፓትሮል ላይ ተሳፍረው የነበሩ እራሳቸውን "መከላከያ ሰራዊት" ብለው የሚጠሩ ከ10 በላይ ወታደሮች ሲገደሉ፡ ተሳፍረውበት የነበረው ወታደራዊ ተሽከርካሪ ፓትሮልም ሙሉ በሙሉ መውደሙ ታውቋል። ሕዝባዊ አመፁ ተቀጣጥሎ የቀጠለ ሲሆን፡ ፀረ ሰላሙ የብልፅግና ቡድንም አመፁን ለማስቆም ያግዙኛል ያላቸውን የጦር መሣሪያዎችን እየተጠቅመ እንደሚገኝ ነው የተነገረው።

በትናንትናው እለት ግምባሩን ተብሎ የተወገደው የባንዳው የህይወት ታሪክ በዚህ መልኩ ተሰንዶ ለትውልዱ ይተላለፋል። ለማ ወንድአፈራው የተባለው ባንዳ የአብይ አህመድን ወንበር ለማስጠበቅ ከጠላት ከብልፅ
በትናንትናው እለት ግምባሩን ተብሎ የተወገደው የባንዳው የህይወት ታሪክ በዚህ መልኩ ተሰንዶ ለትውልዱ ይተላለፋል። ለማ ወንድአፈራው የተባለው ባንዳ የአብይ አህመድን ወንበር ለማስጠበቅ ከጠላት ከብልፅግና/ኦህዴድ/ ጦር ጎን ተሰልፎ የአማራ ህዝብን ሲወጋ፣ ትምህርት ቤትና ጤና ጣቢያ በድሮን ሲያስወድም ፣ የአማራ ሴቶችን ጡት ሲያስቆርጥና ሲያስደፍር እንዲሁም ምጥ የተያዘችን እናት ሲያስገድል ከኖረ በኋላ የህዝብ ልጂ በሆኑት በፋኖ ሀይሎች ግምባራቸውን ተብለው ተቀንድሸው ተወግደዋል። የሸዋሮቢት ከተማ አስተዳደር ሰላም እና ፀጥታ ቢሮ ኀላፊ የሆኑት አቶ ለማ ወንድአፈራው ሲቀነደሹ ጠባቂ ተብለው የተመደቡት 3 ባንዳወችም አብረው ተደምስሰዋል። ቻው ባንዳው ለማ መቃብርህን ሚጥሚጣ ያድርግልህ

በእነ ጋዜጠኛ መዓዛ መሀመድ መዝገብ ተከሳሾች ላይ ዐቃቤ ሕግ አሉኝ ካላቸው 50 ምስክሮች መካከል 7 የሚሚሆኑትን አሰምቷል ፤ እስከ ጥቅምት 22 ምስክሮችን እንዲያቀርብ ተፈቅዶለታል። በእነ ጋዜጠኛ መዓዛ መሀመድ መዝገብ ተከሳሾች ላይ ዐቃቤ ሕግ አሉኝ ካላቸው 50 ምስክሮች መካከል 7 የሚሚሆኑትን በፌደራል ከፍተኛ ፍ/ቤት ልደታ ምድብ ችሎት አሰምቷል ፤ ፍ/ቤቱም እስከ ጥቅምት 22 ምስክሮችን እንዲያቀርብ ተፈቅዶለታል።  ከኢቢኤስ ጋዜጠኞች መካከልም የዐቃቤ ሕግ 6ኛ ምስክር ሉላ ገዙ እና ዘወትር የምስክርነት ቃላቸውን ሰጥተዋል። በኢቢኤስ ሚዲያ የአዲስ ምዕራፍ ፕሮግራም አቅራቢ ሆና ስለመስራቷ እና የመደፈር ወንጀል ተፈፀመብኝ ያለችውን ብርቱካን ተመስገንን ፕሮግራሟ ላይ እንዳቀረበቻት መስክራለች ። ተጎጅዋን ታሪኩ ኃይሌ የተባለ ሰራተኛ ይዟት ወደ ስቱዲዮ መምጣቱንና ማንኛውም ባለ ታሪክ የሚጠየቀውን የማጣሪያ ጥያቄ ተጠይቃ ስለመግባቷ አስረድታለች። ብርቱካን የተደፈረች ስለመሆኗ የሚያሳይ የሕክምና ማስረጃ የያዘች ስለመሆኗ እና ምስክሯም በወቅቱ በተመለከተችው ድርጊት በጣም በማዘኗ ስሜቷን መቆጣጠር ባለመቻሏ ያለቀሰች መሆኑን ተናግራለች። ሉላ የሰጠችው ምስክርነት ለፖሊስ ከሰጠችው ጋር ልዩነት አለው በሚል ምንም እንኳ ዐቃቤ ሕግ "አስጠቂ" ምስክር ናት ቢልም ጉዳዩን የተመለከተው የፌደራል ከፍተኛ ፍ/ቤት ዳኞች ግን አልተቀበሉትም ፣ ለፍ/ቤት የሚሰጥ ቃል ለፖሊስ ከተሰጠ ቃል ጋር የግዴታ መመሳሰል አለበት የሚለውንም ሕጋዊ መሰረት እንደሌለው ጠቁመዋል። ምስክሮችን የመስማት ሂደት ጥቅምት 12 እና 13/2018 የተካሄደ ሲሆን ዳኞች ስብሰባ ላይ ናቸው በመባሉ ጥቅምት 14/2018 ተቋርጦ ይዋል እንጅ ሂደቱ እስከ ጥቅምት 22/2018 ይቀጥላል ተብሏል። ተጎጅዋ ብርቱካን ተመስገን በታጠቁ ኦነጋዊያን መደፈሯን በኢቢኤስ ሚዲያ መግለጧን ተከተትሎ አገዛዙ አፍኖ ወደ ሜክሲኮ የምርመራ ማዕከል በመውሰድ የማስተባበያ ዶክሜንታሪ መስራቱ አይዘነጋም።  በእነ ጋዜጠኛ መዓዛ መሀመድ መዝገብ ከ16 ሰዎች መካከል መዓዛ መሀመድ እና ተስፋየ ወ/ስላሴ በሌሉበት የተከሰሱ መሆኑ ይታወቃል።     (አውሎግሶን አንድነት ፣ ጥቅምት 14/2018)

#የጥንቃቄ_መረጃ‼ ፨፨፨፨፨፨፨፨፨ ሆሮ ጉዱሩ ወለጋ ዞን አቤዶንጎሮ ወረዳ አማራ ወደሚኖርባቸው የገጠር ቀበሌውች አገዛዙ ጥምር ሀይሉን ከጧት ጀምሮ እያስገባ ሲገኝ ወደ ሎምጫ ቀበሌ ከቱሉ ጋና ከተማ በመነሳት የተንቀሳቀሰው ሀይል ተደጋጋሚ ሀይል እያስጨመረና ቀጠናው ላይ ከበባ ለመፈጸም በምሽትም ሳይቀር እንቅስቃሴ እያደረገ ሲገኝ ከወረዳው ዋና ከተማ ወደ ገርጅ ቀበሌ የተንቀሳቀሰው ሀይል ባለበት በመቆም ተጨማሪ ሀይል እየጠበቀ እንደሚገኝ የአካባቢው ኗሪዎች ለቢዛሞ ሚዲያ ገልጸዋል። በነገው ዕለት የተጠናከረ በሁሉም ቀጠናዎች ማህበረሰባችን ላይ ጦርነት ሊከፈት ይችላልና መላው ህዝባችን አስፈላጊውን ጥንቃቄ እንድታደርጉ እናሳስባለን። በተያያዘ ዜና የጊዳ አያና ወረዳ አስተዳዳሪ አቶ ሁነኛ ከፋኖ ጋር ግንኙነት አለህ በሚል ከስልጣኑ ወርዶ ምርመራ እየተደረገበት እንደሚገኝ የደረሰን መረጃ ያመላክታል። 14/ዐ2/2018 ዓ.ም

የሶስቱ ፎቶዋች ወግ እና የጣና ፎረም ፖለቲካ ! የ1ኛው. ፎቶ ትርጉም ፅንፈኛውን አጥፍተናል ባህር ዳርም ክልሉም ፍፁም ሰላም ነው የሚል አንድምታ ያለው ምስል ነው ። ስብሰባው ጭንቀት፣ ፍርሐት እና አለመረጋጋት ከተላላኪነት ጋር የሚታይበት ቅብ ፖለቲካ ነው ። የ2ተኛው. ፎቶ ትርጉም ደግሞ ደሞዙ እና ጥቅማጥቅሙ እስካልተቆረጠ ድረስ የሀሰት ፋኖን ደምሰሰናል ሪፖርት ለአረጋ ካቬኒ አባል እያደረሰ በተግባር እየተማረከ ጭንቅ ውስጥ የገባ የካድሬ የግል ዘበኛ የሆነ እና ለህዝብ ወጦ ህሌናውን በሆዱ የሚያስተዳድር በሰማያዊ ቀለም የተነከረ ልብስ የሚለብስ እንደ ጓዶቹ ለመማረክ የተሰበሰበ ካድሬ አምላኪ ሐይል ነው ። ፎቶውም የተወሰደውም ምናለ ፎረሙን እስክንጨርስ እንኳን ባታወርዱን የሚል ይዘት ያለው የግልምጫ ስብሰባ ላይ ነው ። የ3ኛው. ፎቶ ደግሞ የሚያስረዳው የፋኖን በነፃ ለነፃነት ተፋልሞ የመፈፀምን እና በኩራት ወደ ነፃነት የመገስገስ የአርበኝነትን ልክ ነው ። ይሄን ፍፁም ጀግንነት የፈፀሙት ደግሞ የጣናው መብረቅ እና የባህርዳር ብርጌድ ሲሆኑ ውጊያው የተደረገው   በባህር ዳር ከተማ አስተዳደር ውስጥ በመግባት የጣና ፎረም እየተካሔደ በአለበት ወቅት ነው ። ብአዴን አባትሽ ማነው ? ፈረስ አጎቴ ነው። አልተገናኝቶም ! ©ግሩም ምሳሌ የቴዎድሮስ ዕዝ ም/የፖለቲካ ሓላፊ

📝ሰበር መረጃ 📌አሰቦት ገዳም ምን ተፈጠረ ? 👉በዛሬው ዕለት የኦነግ ሸኔ  በአሰቦት ገዳም ገዳም አገልጋዮች እና በአካባቢው ክርስቲያኖች ላይ ጥቃት መድረሱን የመረጃ ምንጮቻችን ከቦታው አድርሰውናል ።  👉በጥቃቱም አንድ ሰው ሲገደሉ  አንድ  ልጅ ተጎድቶ ተርፏል። ሁለቱ ሰዎች ደግሞ ተወስደዋል። ድርጊቱ የተፈጸመው በገዳሙ ክልል ውስጥ ሲሆን . 👉 ሁለቱ የተወሰዱት የገዳሙ አገልጋዮች. 1ኛ አይዋ ግርማ መሸሻ  እና 2ኛ ደቀመዝሙር ክንፈ    ሲሆኑ . የሞተው አባት:- አቶ አንበስ ፍላቴ     እና  ተጎድቶ ሆስፒታል የሚገኘው :- በትረ አንበስ  የአካባቢው ክርስቲን ናቸው።ሟች አባት የተረፈው ደግሞ ልጁ ነው። 🙏አሁንም ቀጣይ አደጋ እንዳይደርስ የሚመለከተው ባለድርሻ አካል እንዲደርስላቸው  ድምፅ እንሁናቸው ።      📍ኢትዮ ቤተሰብ ሚዲያ

የጨቅላው ዓብዮት አሕመድ ፍርሃትና አዲስ ጦርነት!! የሥልጣን ዘመኑን በሙሉ በጦርነት እያሳለፈ ያለው የሰላም ኖቬል ተሸላሚው ጨቅላው አብዮት አህመድ ከኋላ መጭ በሚሉት ጋላቢዎቹ ገፋፊነት በኤርትራ ላይ ጦርነት መክፈቱ የማይቀር ሆኗል። ጨቅላው በፍርሃት እምቢ ቢል እንኳን ጋላቢዎቹ የሚስማሙ አይመስልም። ታዲያ ከሰሞኑን ሁለት ተያያዥ ግን ደግሞ ወሳኝ መረጃዎችን አግኝተናል፦ 1) የፌድራል ፖሊስ ፣ የአዲስ አበባ ፖሊስ እና የማረሚያ ፖሊስ አባላት ለ45 ቀናት የሚቆይ ስልጠና እንዲገቡ ተደርገዋል። ይህ ስልጠና ዋና ዓላማ ወደ ኤርትራ ጦርነት ሲጀመር ፋኖ ወደ አዲስ አበባ ሊገሰግስ ስለሚችል፣ ለዚህ ዝግጁነት የመፍጠር ኦሬንቴሽን ነው ተብሏል። 2) ሌላኛው ተያያዥ መረጃ ደግሞ የኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥት ከውጭ በቀጥታ ግዥ በርካታ የጦር መሳሪያ መሸመቱ ታውቋል። ይህ የተገዛው መሳሪያ የክልሉን የፀጥታ ኃይሎች በመከላከል ሰራዊት ቁመና ልክ ለማስታጠቅ ያለመ እንደሆነም ተነግሯል። እነዚህ ሁለት መረጃዎች የሚያስረዱን እንግዲህ ጦር አውርዱ ጨቅላው አብዮቶ አህመድ አዲስ ጦርነት ለመክፈት እየተንፈራገጠ ያለው በከፍተኛ የአገር ውስጥ ስጋትና ፍርሃት ውስጥ ሆኖ እንዳላ ማሳያ ነው። አዲስ አበባ የብቻዬ ናት የሚለው፣ ለኢትዮጵያ ጥቅም የአሰብ ዘማቹ ጨቅላ፣ ይህ ጦርነት የኢትዮጵያውያንን ድጋፍ ዳግም ያስገኝልኛል የሚል ስሌት የያዘ ቢሆንም ደጋግሞ የሚሞኝ ወገን ያለ አይመስልም።

አማራው ወደ ቤቱ እየገባ ነው፣ የጠላት ጦር እየፈራረሰ ይገኛል። በዛሬው ዕለት፣ 1. ሀብታሙ ዋለ 2. ታለማ መርሻ 3. አባትነህ ተመቸ የተባሉ ወገኖች የጠላትን ፀረ አማራ ሴራ በመረዳት ከእናርጂ እ
አማራው ወደ ቤቱ እየገባ ነው፣ የጠላት ጦር እየፈራረሰ ይገኛል። በዛሬው ዕለት፣ 1. ሀብታሙ ዋለ 2. ታለማ መርሻ 3. አባትነህ ተመቸ የተባሉ ወገኖች የጠላትን ፀረ አማራ ሴራ በመረዳት ከእናርጂ እናዉጋ (ደብረወርቅ) ወረዳ ሚሊሻ ካምፕ በመዉጣት ሳሙኤል አወቀ ፱ኛ ክ/ጦር፣ ሶማ ብርጌድን ተቀላቅለዋል አፋብኃ|ቴዎድሮስ ዕዝ ሕ.ግንኙነት መምሪያ            ጥቅምት 14/2018 ዓም

#ባህርዳር_ቀጠና_የዛሬው_ምርኮ‼️ #ዐንድ_አማራ‼️ #ላንጨርስ_አልጀመርንም‼️ #ምረር_አማራ💪 #ድል_ለአማራ_ፋኖ💪 #ድል_ለአማራ_ህዝብ💪 14/ዐ2/2018 ዓ.ም ፍኖተ-አማራ ሚዲያ ወቅታዊና ትኩ
+4
#ባህርዳር_ቀጠና_የዛሬው_ምርኮ‼️ #ዐንድ_አማራ‼️ #ላንጨርስ_አልጀመርንም‼️ #ምረር_አማራ💪 #ድል_ለአማራ_ፋኖ💪 #ድል_ለአማራ_ህዝብ💪 14/ዐ2/2018 ዓ.ም ፍኖተ-አማራ ሚዲያ ወቅታዊና ትኩስ የፋኖ እንቅስቃሴን መረጃን ከግንባር ሁነን በአራቱም ማዕዘን እየሰራን እንገኛለን። ለሁሉም አማራ ተደራሽ እንሆን ዘንድ እየሰራን እንገኛለን የበኩሉዎን አስተዎፆ የቴሌግራምና ፊስቡክ ቻናላችን እና ጆይን ሸር አድርጉ አድራሻችን👇👇👇👇 ‼️ https://t.me/httpsuYkZrGfSZrNjNjFk   https://www.facebook.com/share/p/17FBBgD9

............. የአደረጃጀት ዜና !! ............. በአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል ( አፋብኃ ) የቴዎድሮስ ዕዝ 201ኛ ኮር የ54ኛ ክፍለጦር ምስረታ ተጠናቋል ። በአፋብኃ ቴዎድሮስ ዕዝ የመልሶ ማደራጀት እና የመዋቅር ማሻሻል ተግባራት መካከል አንዱ የሆነው የኮር አደረጃጀት እና የክፍለጦር መልሶ ማደራጀት ይገኝበታል ። በዚህም አዲስ ተዋቅሮ የተጠናቀቀው 54ኛ ክፍለጦር በቀደመው አደረጃጀት የመብረቁ ተፈራ  ብርጌድ ፣ የመዝገበ ጮቄ ብርጌድ እና መዝገበ ዋለልኝ ብርጌድን ያካተተ ሆኖ ተመስርቷል ። ክፍለጦሩ በአምስት ሬጅመንቶች የተዋቀረ ሲሆን ለቀጣይ የህልውና ትግል ዝግጁ መሆናቸውን የክፍለጦሩ ፣ የሬጅመንቶች አመራሮች እና አባላት አረጋግጠዋል ። የክፍለ ጦር መልሶ ማደራጀት ስራው በዕዙ ህዝብ ግንኙነት ሀላፊ ማርሸት ፀሐው ደምሴ ፣ በዕዙ ጽህፈት ቤት ሀላፊ ይትባረክ አንዳርጌ እና በዕዙ ዘመቻ መምሪያ ሀላፊ መቶ አለቃ አበበ ሰውመሆን አስተባባሪነት ተጠናቋል ። አዲስ ትውልድ አዲስ አስተሳሰብ አዲስ ተስፋ !!