ፍኖተ- አማራ ሚዲያ (Finote- Amhara ) Midea
Открыть в Telegram
የተመሠረተው የአማራን ሕዝብ ለማንቃት፣ ለማደራጀት እና ለማስተባበር ነው። የአማራ ሕዝብን ✅ ፖለቲካዊ ✅ ማህበራዊ ✅ ኢኮኖሚያዊ ታሪካዊ ጥያቄዎችን ለማሰማት እና የአማራን ሕዝብ በማንቃት ሰፊውን ሕዝብ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ይሰራል። ወደዱም ጠሉም የኃላ ታሪካችን በእኛ እጅ ይፃፋል። አማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ ( አፋብን)
Больше3 678
Подписчики
+2624 часа
+3797 дней
+1 10930 дней
Архив постов
በይፋት ግንባር በተደረገ ተጋድሎ ታዳጊዋ የለን ከተማና ሌሎች አከባቢዎች በፋኖ ቁጥጥር ገቡ!
በተጋድሎው 22 አየር ወለድ ኮማንዶ አባላት ሲገደሉ፡ በሁለት አይሱዙ ኤፍኤስ አር ተሽከርካሪ ሙሉ ቁስለኛ ኮማንዶዎች ለሕክምና ወደ ሸዋሮቢት ይፋት ሆስፒታል መወሰዳቸውን የመረብ ሚዲያ የጦር ግንባር ዘጋቢዎች ለማረጋገጥ ችለዋል።
በውጊያው የቆሰሉ ኮማንዶዎች ብዛት ከንፃር፡ በሆስፒታሉ አልጋ ይዘው እየታከሙ የነበሩ ንፁኋን ታካሚዎች አልጋቸውን ለቀው እንዲወጡ መደረጋቸው ታውቋል።
ዐብይ አህመድ ሳይቀር "የባለ ምጡቅ አዕምሮ ባለቤቶች" በሚል የሚያሞካሻቸውና "የመጨረሻ የጥንካሬችን ማሳያ" በሚል የመከላከያ ሰራዊት ተቋም የሚመካባቸው የአየር ወለድ ኮማንዶዎችና የሪፐብሊካን ጋርድ አባላት የሸዋ አፈር ሲሳይ ሆነው እየቀሩ ነው።
+1
አፋብን የምህረት አዋጅ ማወጁን ተከትሎ የመከላከያ ሰራዊቱ እየፈረሰ ፋኖን እየተቀላቀለ ነው!!
ምኒልክ ዕዝ አሳምነው ክ/ጦርን የተቀላቀሉ ናቸው!!
በመጀመሪያው የአፋብን የምህረት አዋጅ የመጀመሪያው ተጠቃሚ 109ኛ ኮር 77ኛ ክ/ጦርን ተቀላቀለ!!
===============
በዛሬው ዕለት በቀን 05/06/2018 የወጣውን የአፋብን የምህረት አዋጅ መሰረት በማድረግ ደረጀ ዘላለም የተባለ ፍኖተሰላም ከተማ ከመሸገው የጠላት ሀይል ጋር በመሆን አምባገነኑን የብልጽግና ስርዓት ሲያገለግል የነበረ ሲሆን በዛሬው ዕለት አፋብን ቴዎድሮስ ዕዝ 109ኛ ኮር 77ኛ ክ/ጦርን ተቀላቅሏል።ወጣት ደረጀ፤ አብይ አህመድ ከኤምሬትስ በብድር ያመጣውን ሁለት እግር ክላሸንኮቭ ከእነ ተተኳሹ በመያዝ የወጣ ሲሆን በ109ኛ ኮር አመራሮችና በ77ኛ ክ/ጦር አመራሮች ደማቅ አቀባበል ተደርጎለታል።
በመጀመሪያው የአፋብን የምህረት አዋጅ ተጠቃሚ በመሆኑና ልዩ እንደሚያደርገው እና ደስተኛ እንደሆነ ወጣት ደረጀ ተናግሯል።
👉የብልጽግና አመራሮች ቤተሰቦቻቸውንና ልጆቻቸውን ውጭ ሀገር ልከው እያሰተማሩ ሲሆን የድሀውን የኢትዮጵያ ወጣት በሀይል እየታፈነ የስልጣናቸው ማስጠበቂያ የጥይት እራት እያደረጉት እንደሆነ አውቆ ሁሉም አካል የወጣውን የምህረት አዋጅ በመጠቀም ህይወቱን እንዲያተርፍ በማለት መልዕክቱን አስተላልፏል።
አዲስ ትውልድ፣ አዲስ አስተሳሰብ፣ አዲስ ተስፋ!
የአፋብን ቴዎድሮስ ዕዝ 109ኛ ኮር ህ/ግንኙነት
የካቲት 6/2018ዓ.ም
የአንድ ሥርዓት መዝጊያ እና የሕዝብ ንቃት፦ ከአፍሪካ ኅብረት ስብሰባ ማግስት ምን ይጠብቀናል?
እኛ አማራዎች የታሪክን መዝገብ ስንገልጥ የምንማረው አንድ ትልቅ እውነት አለ፤ እርሱም "ጦርነትን ማንም ሊጀምረው ይችላል፣ ፍጻሜውን ግን ማንም ሊወስነው አይችልም" የሚል ነው።
ዛሬ በሀገራችን ያለው ሁኔታም ይህንኑ እውነት እያሳየን ነው።
1. የታገደው የጦርነት ጉሰማ እና የጊዜያዊ ጸጥታ ተንኮል (የቀሩትን በፋኖ የሚረሸረሹትን ጭነዉ ለምን አላመጡልንም?)
አሁን የሚታየው አንጻራዊ የጦርነት ጉሰማ መቀዝቀዝ ወይም ከወደነሱ መሸነፍ፣ ወታደር ስላለቀ ሳይሆን የአፍሪካ ኅብረት ስብሰባ አዲስ አበባ ላይ በመሆኑ ዓለምን ለማታለል የተደረገ "የዲፕሎማሲያዊ መጋረጃ" ነው። ስብሰባው እንዳለቀ ነገሮች በፍጥነት ሊቀያየሩ ይችላሉ። ኢንተርኔት የመዘጋትና ዳግም የማጥቃት ሙከራዎች ሊኖሩ እንደሚችሉ ከወዲሁ መገመት ስልታዊ ብልህነት ነው።
2. የአማራ ክልል ወደ ሕዝባዊ አስተዳደር የመሸጋገሪያ ሰዓት
አሁን ያሉት ተጨባጭ ሁኔታዎች የሚጠቁሙት የአማራ ክልል ሙሉ በሙሉ በፋኖ እጅ የሚገባበት ጊዜ መቃረቡን ነው። ይህ ድል ግን ትልቅ ኃላፊነትንም ጭምር ይዞ የሚመጣ ነው። አካባቢው በሕዝባዊ ኃይሉ ቁጥጥር ስር ሲውል፣ ከወታደራዊ ድል በበለጠ "የአስተዳደር ድል" ያስፈልገናል።
3. ተቋማዊ ጥበቃ እና የባለሀብቶች ደህንነት
ሥርዓቶች ይወድቃሉ፣ ሕዝብና ሀገር ግን ይቀጥላሉ።
ስለዚህ፦
የመንግሥት ተቋማት፦ ሆስፒታሎች፣ ትምህርት ቤቶች እና የመገልገያ ተቋማት የሕዝብ ንብረት እንጂ የገዥው አካል አይደሉም። እነዚህ ተቋማት እንዳይወድሙና እንዳይዘረፉ ሕዝቡ በየቀበሌው ተደራጅቶ ጥበቃ ሊያደርግ ይገባል።
የባለሀብቶች ንብረት፦ የአማራ ባለሀብቶችና ንብረቶቻቸው እኩይ ዓላማ ባላቸው ግለሰቦች እንዳይወሰዱና ትርምስ እንዳይፈጠር ከፍተኛ ጥንቃቄ ያስፈልጋል። የግል ንብረት መከበር የሥልጣኔ መጀመሪያ ነው።
4. ለድንገተኛ መፈራረስ ዝግጁ መሆን
በወታደራዊ ድጋፍ ብቻ የቆመው የአብይ አገዛዝ፣ ከታሰበው ጊዜ በፊት ፈጥኖ ቢፈርስ አማራዎች ሀገርን ለማረጋጋትና ወደ ባሰ ትርምስ እንዳንገባ ከወዲሁ በሃሳብ መዘጋጀት አለብን። ታጋዮች እና ምሁራን በዚህ ሽግግር ወቅት ሕዝቡን በመምራትና ስርአት በማስያዝ ረገድ ታሪካዊ ድርሻ አለባቸዉ።
የመጨረሻ መልዕክት፦
ድል የሚረጋገጠው በወታደራዊ የበላይነት ብቻ ሳይሆን፣ ሕዝብን በማረጋጋትና ሀገራዊ ተቋማትን በመጠበቅ ጭምር ነው። የአማራ ልጆች ሆይ! በአስታዋይ ልቦና፣ ለነገዉ ሥርዓት ባለው ድል ከወዲሁ እንዘጋጅ!
አዲስ✍️
የደብረ ታቦር ከተማ ባለሕንጻዎች በአገዛዙ ሕንጻችኹ ላይ የተሰራባችኹን ምሽግ አፍርሱ፣ ተቃወሙ፣ እምቢ በሉ፣ አትቀበሉ❗
[የካቲት 05/2018ዓ.ም]
አብረን እንብላ ያላለህ ካድሬና የአገዛዙ ታጣቂ ዛሬ አብረን እንሙት ሢል በመጨረሻው መጨረሻ የታሪክ ጥላሸት ባለቤት እንድትሆን የተደረግኸው የከተማዋ ባለሕንጻ አካል የምትነቃበትና ለምን የሚል ተጠየቅን አንሥተህ የሕንጻው ባለቤትነትህን የምትገልጥበት ጊዜ አኹን ነው።
የዓምሐራ ፋኖ በደብረ ታቦር ከተማ የአገዛዙን ቅጥረኛና ወዶ ገብ ከሃዲ በተባበረ ዓምሐራዊ ክንድ ማምበርከኩ ይታወቃል። ነገር ግን የአገዛዙ ወታደሮች ለምሽግነትና ለተኩሥ የመረጡት ቦታ 80% የከተማው ትላልቅ ሕንጻዎችን ሲሆን ካድሬዎቹ ደግሞ እንደ አይጥ ጉድጓድ የተጠቀሙት የሕንጻውን Under ground ነው።
ሢኖር ለማየት የተጸየፈህ የአገዛዙ ወታደርና የአገዛዙ ካድሬ የጭንቁ ሠዓት አብረን እንሙት የሚል ልክ አልባ ድርጊት ፈጽሞብሃል። መከራሕን ዓይተህ በገነባኸው ሕንጻ አገዛዙ እንዲጠቀምበት ፈቅደሃል። የአገዛዙ ታጣቂና ካድሬ ሕንጻዎቻችኹን የሕይወት መማጸኛ አድርጎ መመሸጉን በብሌናችን ተመልክተናል። ሕንጻዎቻችኹ ላይ ሆኖ ሲዋጋ መዋሉንና ካድሬዎቹም የአይጥ ጉድጓድ ማድረጋቸውን ተመልክተናል።
ሞርተር 120፣ ሞርተር 82 እና RPG-07 መሣሪያዎችን በበቃኝ የታጠቀው የዓምሐራ ፋኖ ምሽግ በሆኑት ሕንጻዎች ላይ ጥቃት ያልፈጸመው ሕዝባዊነትን በማሥቀደሙ ነበር። ሠራዊታችን በተባበረ ዓምሐራዊ ክንዱ ጠላትን የማምበርከክ አቅምም ሆነ ምልዑ የሆነ የሥነ ልቦና የበላይነትን የተላበሰ እንደሆነ ይታወቃል። ሥለሆነም የምንናገረው ማድረግ የምንችለውን ነውና ከዚህ በኋላ ሕንጻችኹን ለገዳይ አቢይ ታጣቂ መሥጠት እንደሌለባችኹ በጥብቅ እናሳስባችኋለን። ሕዝቡም ሆነ የሕንጻ ባለቤቶች እምቢ ማለትን መልመድ መቻልና መጀመር አለባችኹ።
ይህንን ጥብቅ ማሳሰቢያ ተላልፎ ሕንጻውን ለአገዛዙ ምሽግነት የሚያሥረክብ ከሆነ ለሕዝባችን ነጻነት ሥንል በሞርተርና RPG-07 መሣሪያዎቻችን ርምጃ ለመውሰድ እንገደዳለን።
በአጠቃላይ ለደብረ ታቦር ሕዝብና ለመላው ዓምሐራ ሕዝብ የምናሥተላልፈው መልዕክት ቢኖር የአገዛዙ ታጣቂ ከከተማ ወጥቶ እንዲገጥም እንደ ሕዝብ ሊጠይቅና ለምን ሊል ይገባል። ሕዝብን ጋሻና ከለላ አድርጎ ለመዋጋት ከመሞከር ባለፈ ንጹሑን ማሕበረሰብ፣ የዕምነት ተቋማትና፣ ሕዝባዊ ተቋማትንና መኖሪያ ቤቶችን ታይቶ ቀማይታወቅ ጭካኔ ከአየር ጥቃት እሥከ ምድራዊ ጥቃቶች እየፈጸመብህ ትገኛለህ። ይህንን ፋሽሥታዊ ድርጊትም ወጥተህ አውግዘው እምቢኝ በለው፤ በሕንጻህ ላይ እንዲመሽግም አትፍቀድለት።
ደብረ ታቦር ከተማ የነበሩ ታጣቂዎችና ካድሬዎች በምሽግነት የተጠቀሙባቸውና ሲተኮስባቸው የዋሉ ሕንጻዎች ዝርዝር በከፊል፦
✅አሐዱ ሕንጻ
✅ሕብረት ሆቴል
✅የጥላኹን ገሰሰ ልጅ ሕንጻ(የድሮው መዘጋጃ ቤት ላይ የተገነባ)
✅የድሮው ሼል ማደያ ጎን ያለው ጅምር ሕንጻ
✅ አደባባይ ሕንጻ( የባሕር ዳሩ ናይል ቪው ሆቴል፣ጉና ውኃ ባለቤት የሆነው)
✅ከግራሩ ፊት ለፊት የሙልዬ ሆነልኝ ሕንጻ(ዳሽን ባንክ ያለበት)
✅ከድሮው መብራት ኃይል ፊት ለፊት (ጉራጌው ሥጋ ቤት)
✅አያል ፀጋዬ ሕንጻ ( ከቴዎድሮሥ አደባባይ ጀርባ መሥከረም ሆቴል ፊት ለፊት)
✅ከፈራረሰው ፔርሙዳ ፊት ለፊት ያለው G+6 የማሕበር ሕንጻ
✅ሥፍራሽ ሕንጻ
✅ዋሴ ቦጋለ ሕንጻ
✅ማርከሽ ሕንጻ(ሥላሴ ሰፈር)
✅ዞን አሥተዳደር ሕንጻ(የአራጂ አቢይ ኮንዶም ብአዴን ጥላሁን ደጀንና መሰሎች ሕንጻ)
✅ብልጽግና ጽ/ቤት ሕንጻ
✅ፒተር ሕንጻና አካባቢው ላይ ያለ ሕንጻ በሙሉ
✅ዘርጋው ሕንጻ
✅መንገሽ ሕንጻ እና ሌሎችም ይገኙበታል።
ኅልውናችን በተባበረ ክንዳችን❗
አፋብን ሰ/አ/ቀ በላይ ዕዝ
ሜጀር ጀነራል ውባንተ አባተ ፩ኛ ኮር ሕ/ግ
ፋኖ ኃቅአለው ፀጋ አለባቸው!
እውነትም አፍሪካ ህብረት ጥርስ አወጣ!
ከስሙ ውጪ አንዳችም የረባ ነገር ሲከውን የማይስተዋለው የአፍሪካ ህብረት ፣ በታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ በሚባል መልኩ በተለይም በምስራቅ አፍሪካ ጂኦፖለቲካዊ ትርምስና የጥፋት እጆች ዙሪያ ተመሳሳይ አቋም ወደማራመድ እየተሸጋገረ ይገኛል። ለዚህ ደግሞ የህብረቱ የሰላምና የፀጥታ ካውንስል ዛሬ ያወጣው ታሪካዊ መግለጫ ጉልህ ማሳያ ነው።
የህብረቱ መቀመጫ የሆነችው ኢትዮጵያን ጨምሮ ኢማራትን የሱዳንን የውስጥ ቀውስ በማባባስ በተዘዋዋሪ መልኩ የከሰሰ ሲሆን እጃቸውን እንዲሰበስቡም አሳስቧል።
ይህ #ለካሊጉላ ስርአተ ማህበር በሜዳውና በዲምላይቱ ፊት ትልቅ ነጥብ ያስጣለና መፃኢውን ዲፕሎማሲያዊ እጣፋንታቸውን በጉልህ ያመላከተ ተደርጎ ሊወሰድ ይችላል።
መግለጫው ቢን ዛይ ድ ፣ አብይና ሄሜቲ በሱዳን ህዝብ ላይ እያደርሱት ያለውን ወድመትና ፍጅት አጥብቆ ያወገዘ ብሎም በዲፕሎማሲያዊ ቋንቋ በብዙ ፈርጁ የሚመነዘር ጠንካራ መግለጫ ነው።
RSF በአልፋሸር የፈጸመውን የዘር ፍጅት በፅኑ ያወገዘው ይህ የህብረቱ መግለጫ በሄሜቴ የተቋቋመው የጎንዮሽ አስተዳደር ተቀባይነት እንደሌለውም አስረግጦ አስታውቋል።
ካውንስሉ በሱዳን ጦርነት እጃቸውን ያስገቡ የውጪ ሀይሎችን ( እነዚያ የውጪ ሀይሎች እናማን እንደሆኑ የታወቀ ነው) በፅኑ የኮነነ ሲሆን ጠንከር ያለ ማስጠንቀቂያም ሰጥቷል።
'' የአፍሪካ ህብረት ጦርነትን የሚያድበሰብስ ግጭቶችን የሚሸፍን ለአምባገነኖች ከለላ የሚሰጥ ጥርስ አልባ ተቋም!'' ተብሎ ለአመታት የተወቀሰ ቢሆንም ... ዘንድሮ ግን በሱዳን ቀውስና በምስራቅ አፍሪካ በሚስተዋለው የቀውስ አዙሪት ላይ እየያዘ ያለው አቋም ይበል የሚያሰኝ ነው።
ይህ የAU አቋም ለኢማራትና ለተላላኪ ሀይሎች ጥሩ ዜና እንደማይሆን የታወቀ ነገር ነው። የአፍሪካ ህብረት እንኳን በግልፅ ያወገዘው ጣልቃ ገብነትና የቀውስ ድግስ በሌሎች ተቋማትና አለምአቀፉ ማህበረሰብ ዘንድ ምን ሊባል እንደሚችል በቀላሉ መገመት አይከብድም። የህብረቱ አሁናዊ አቋም መፃኢ የአፍሪካ ቀንድን የዲፕሎማሲያዊ ምህዋርና የትርምስ አውድ የመቀየር አቅም ያለው ነው!
በእውነቱ ቢን-ዛይድና ካሊጉላ አህመድ ጥሩ ሳምንት እያሳለፉ አይደለም!😂
ምኒልክ ዕዝ ተወርዋሪ በላጎ ሻለቃ ለወራቶች የሰለጠኑ ኮማንዶ ፋኖዎችን አስመረቁ::
ምኒልክ ዕዝ ተወርዋሪ በላጎ ሻለቃ ለወራቶች ያሰለጠኗቸውን በርካታ ምልምል ኮማንዶ ፋኖዎች ዛሬ የካቲት 5/2018 ዓ.ም በሃይማኖት አባቶችና በሃገር ሽማግሌዎች ምርቃን ታጅበው በደማቅ ሁኔታ አስመርቀዋል::
ደሴ ከተማ ዙሪያ ወረዳ እና በተለያዩ የቤተ-አማራ አካባቢዎች በርካታ ተጋድሎዎችን እያደረጉ አመርቂ ድሎችን እያስመዘገቡ ያሉት የምኒልክ ዕዝ ተወርዋሪ በላጎ ሻለቃ አናብስቶች በትጥቅና በሰው ሃይል ራሳቸውን እያጠናከሩና እያደራጁ ይገኛሉ:: በቀጣይም ተጨማሪ ስልጠናዎችን በማካሄድ በእውቀትና በሰው ሃይል እንዲሁም በትጥቅ የበለጠ ራሳቸውን እንደሚያደራጁ የተወርዋሪ ሻለቃዋ አመራሮች ገልፀዋል::
ከዚህ ጋር ተያይዞም አባቶች በተገኙበት ለወራቶች የሰለጠኑ ምልምል ኮማንዶ ፋኖዎችን በማስመረቅ የሰው ሃይላቸውን ያጠናከሩ ሲሆን በምርቃን ዝግጅቱ ላይ የተገኙ አባቶችም የአማራ ህዝብ የብዙ እሴቶች ባለቤት ነው እናንተ ልጆቻችንም ይሄንን እሴታችንን ተላብሳችሁ የህልውና ትግሉን ከዛሬ አድርሳችኋል ወደፊትም ይህንን ጠብቃችሁ ለድልና ነፃነት እንድታበቁን አደራ ጥለንባችኋል በማለት መልዕክት አስተላልፈዋል::
ሰልጥነን እንዋጋለን፣ እየተዋጋን እንሰለጥናለን!
መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልዉና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል!
ትግላችን በተባበረ ክንዳችን!
አፋብን ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ
የካቲት 5/2018 ዓ.ም
ጡረታ የወጡ ፣ በዲሲፕሊን የተሰናበቱ ፣ ጠፍተው የቀሩ ፣ በተለያዩ ሁኔታዎች ከአባልነት የተቀነሱ የኦሮሚያ ልዩ ሃይል አባላት በአስቸኳይ አመልክተው ወደ ሰራዊቱ እንዲመለሱ ማስታወቂያ ወጥቷል። ይህ ማስታወቂያ የመከላከያ ሰራዊት ከክልሉ ሲወጣ ተክተው ከOLA ጋር እንዲዋጉ የቀረበ ጥሪ ነው።
በተጨማሪም ከፍተኛ ቁጥር ያለው የሚሊሻ ታጣቂዎች በየሁለት ሳምንቱ እየተመረቁ ነው። እነዚህ ሚሊሻዎች እድሜያቸው የገፋ ፣ ቤተሰብ የሚያስተዳድሩ ፣ በግብርና ላይ የተሰማሩ ምስኪን አርሶአደሮች ናቸው።
#ብልፄ ሰሞኑን በኢ-መደበኛ ሀይል የክልል ፀጥታን ለመቆጣጠር ሲጣጣር በእነዚህ ስምንት አመታት ውስጥ ብቻ ያስመረቃቸው የመከላከያ ሰራዊት ሆነ የክልል ልዩ ሀይሎች የት ሄደው ነው ወይ ያስብላል ??
ኦሮሚያና አማራ ክልል ተሰማርተው የነበሩ የመከላከያ ሰራዊት አባላት አብዛኞቹ ነቅለው በመውጣት ወደ ትግራይ ድንበር ላይ ተጠግተዋል። በተመሳሳይ በTDF በኩልም የጦርነት ዝግጅት እየተደረገ ነው። የጦርነቱን አይቀርነትም መገመት አይከብድም።
እነዚህ ዝግጅቶች ሲታዩ ጦርነቱ ምን ያህል አውዳሚ ሊሆን እንደሚችልና በከፍተኛ የሀይል አቅም እንደሚሆን የሚያሳይ ነው። በአንፃሩ አማራና ኦሮሚያ ክልል ላይ በልዩ ሀይል ፣ በአድማ በታኝና በሚሊሻ ለውጊያ እየተዘጋጀ ነው።
ይህ ጦርነት በሶስት ክልሎች ላይ እየተካሄደ ኢትዮጵያ የሊቢያ እጣፋንታ አይገጥማትም ብሎ የሚፎክር ካለ የብልፅግና ህልመኛ ነው 🤔
...... የድል ዜና ....
አራስ እናቶችን፥ካህናትን ከጠላት ማሰቃያ ካንፕ ነፃ የተደረጉበት እና ምርኮዎች የተገኙበት የዛሬዉ ዕለት #የሰቀለት ግንባር ትንቅንቅ‼️
አፋብን ቴዎድሮስ ዕዝ 102ኛ ኮር በዚህ ሳምንት በተለያዩ ግንባሮች በተከታታይ በርካታ ድሎችን እያስመዘገበ መሆኑ ይገኛል።
ትንቅንቁ ዛሬም በተለያዩ ግንባሮች የቀጠለ ሲሆን ከ/ባዳር በቅርብ ርቀት በምትገኘዉ #ሰቀለት በምትባል ልዩ ቦታ ብቻ አድማ ብተና እና ሚሊሻ የተማረከ ሲሆን ከከ20በላይ አድማ ብተና ከ7በላይ ሚሊሻ እስከወዲያኛው ተሸኝተዋል ።
እግሬ አውጭኝ ብለው የፈረጠጠዉ የጠላት ኃይል አሁንም እየተለቀሙ ሲሆን ከገበሬ ያስወረዱትን ጨምሮ በርካታ የነፍስ ወከፍ መሳሪያ ተማርኳል።
በዛሬዉ የሰቀለት ግንባር የተማረኩ ምርኮዎች:-
➤ ከ30 በላይ ክላሽ፤
➤ከ40 በላይ የክላሽ ካዘና፤
➤ ከ5000 በላይ የክላሽ ተተኳሽ፤
➤ 03 መገናኛ ሬዲዮ፤
➤ሙሉ ሬሽን እና በርካታ ወታደራዊ አልባሳት ተማርኳል
በአማራ-ጠሉ ስርዓት የባህርዳር ዙሪያ ወረዳ ማህብረሰብ ከፍተኛ በደል ሲፈፀምባቸዉ ካምፖች መካከል አንዱ የሆነው ሰቀለጥ ካምፕ በወገን እጅ በገባባት ወቅት በጠላት እጅ ወድቀው ግፍ ሲቀበሉ የነበሩ እስረኞችን እና ለፋኖ ምግብ መግባችኃል ተብለው ምግብ ተከልክለው ታጉረዉ ሲሰቃዩ የነበሩ እናቶችን ማስፈታት ተችሏል።
በዚህ ማሰቃያ ቤት ታጉረዉ ሲሰቃዩ ከነበሩ ከ30 በላይ እስረኞች እና በርካታ ቁጥር ያላቸው ተንቀሳቃሽ ሀብት ንብረቶችን ማስለቀቅ የተቻለ ሲሆን በፋኖ እጅ ነፃ ከወጡ እስረኞች መካከል ለአብነት ያክል:-
➤ሁለት አራስ(መጫት) ሴቶች ከነ ህፃን ልጆቻቸው ምግብ ተከልክለው ይሰቃዩ የነበሩ
➤ ሁለት የቤተክርስቲያን አገልጋይ ካህናት
➤ በተለያዩ የዕድሜ ክልል ውስጥ ያሉ ወጣቶች ሲሆኑ ከ80,000 ሺ ብር -100,000ሺ ብር ተጠይቀው መክፈል ስላልቻሉ እየተሰቃዩ የነበሩ እስረኞች
➤ ከአርሶ አደሮች ተነጥቀዉ ለእርድ የተዘገሠጁ 10ቁም ከብቶች ከ25 በላይ ፍየል በአንድ ግንባር ማስለቀቅ ተችሏል።
በባህርዳር ዙሪያ በዚህ ሰዓት በሌሎች ቀጠናዎችሜ ዉጊያዎች እየተደረጉ ሲሆን የተለያዩ ድሎችም እየተመዘገቡ ይገኛሉ።
አዲስ ትዉልድ፣አዲስ አስተሳሰብ፣አዲስ ተሰፋ!!
(05/06/18 ዓ.ም )
አፋብን| ቴዎድሮስ ዕዝ
የካቲት 05/2018ዓ.ም
__፩
102ኛ ኮር ባህርዳር ዙሪያ ድል ተቀዳጀ።
ትንቅንቁ ዛሬም በተለያዩ ግንባሮች የቀጠለ ሲሆን ከ/ባዳር በቅርብ ርቀት በምትገኘዉ ሰቀለት በምትባል ልዩ ቦታ ብቻ አድማ ብተና እና ሚሊሻ የተማረከ ሲሆን ከከ20በላይ አድማ ብተና ከ7በላይ ሚሊሻ እስከወዲያኛው ተሸኝተዋል ።
በዛሬዉ የሰቀለት ግንባር የተማረኩ ምርኮዎች:-
➤ ከ30 በላይ ክላሽ፤
➤ከ40 በላይ የክላሽ ካዘና፤
➤ ከ5000 በላይ የክላሽ ተተኳሽ፤
➤ 03 መገናኛ ሬዲዮ፤
➤ሙሉ ሬሽን እና በርካታ ወታደራዊ አልባሳት ተማርኳል
➤ከ30 በላይ እስረኞችን ማስፈታት ተችሏል። እመጫት ሴቶች እና ካህናት የዚህ ሰለባዎች መሆናቸውን አረጋግጠናል።
➤ ከአርሶ አደሮች ተነጥቀዉ ለእርድ የተዘጋጁ 10ቁም ከብቶች ከ25 በላይ ፍየል በአንድ ግንባር ማስለቀቅ ተችሏል።
_፪
አፋብን ቴዎድሮስ ዕዝ 109ኛ ኮር 99ኛ ክ/ጦር ከ6 ወር በላይ ያሰለጠናቸውን ኮማንዶዎች አስመረቀ።
አፋብን ከውጊያ ጎን ለጎን በተለያዩ ቀጠናዎች የሀይል ግንባታ ስራ እሰራ ይገኛል። በዛሬው ዕለትም ከ6ወር በላይ ሲያሰለጥናቸው የቆዩ ኮማንዶዎችን በደመቀ ሁኔታ አስመርቋል። ይህ ቀጣይነት ያለው ስልጠና ለድላችን መቃረብ እና የቀጣይ ሀገር ተረካቢ ሀይል የማፍራት ስራ ተጠናክሮ የሚቀጥል ይሆናል።
አዲስ ትውልድ፣ አዲስ አስተሳሰብ ፣አዲስ ተስፋ!
ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን !
አፋብን| ቴወድሮስ ዕዝ ሕዝብ ግንኙነት መምሪያ
የካቲት 05/2018 ዓ.ም
ግዙፉ የኮማንዶ ኃይል ከምዕራብ ዐምሓራ ቀጠና!
👉የጠላትን ኃይል በመደምሰስ ከነፍስ ወከፍ እስከ መካናይዝድ መሳሪያዎች፣ከመሰረታዊ ወታደር እስከ ኮረኔል ማዕረግ ያላቸውን የጠላትን ሀይል በመደምሰስና በመማረክ የሚታወቀው በአፋብን ቴዎድሮስ ዕዝ 109ኛ ኮር 99ኛ ክ/ጦር ከ6 ወር በላይ ሲያሰለጥናቸው የነበሩና የውጊያ ማርሽ ቀያሪ የሆኑ ኮማንዶዎችን ከአማራ ፋኖ አንድነት መመስረት ማግስት ለመጀመሪያ ጊዜ የሀገር ሽማግሌዎች፣የሀይማኖት አባቶችና የጦር አመራሮች በተገኙበት ዛሬ የካቲት 05/2018 ዓ/ም በደማቅ ሁኔታ አስመርቋል።
ምንጭ፦በአፋብን ቴዎድሮስ ዕዝ 109ኛ ኮር ህ/ግንኙነት ክፍል!
የንፁሃን ህፃናት ደም ይጮኻል!
በሸዋ ደራ አካባቢ ከጉዟቸው ላይ ታግተው የተወሰዱ ህፃናት በአሰቃቂ ሁኔታ ተገድለው አስከሬናቸው መገኘቱን የሚገልፀው መረጃ መላውን የሰው ልጅ ህሊና የሚፈትን ታላቅ ግፍ ነው። ይህ ድርጊት የሞራል ዝቅጠትን ብቻ ሳይሆን፣ ማፍያው ቡድን የደራን ህዝብ አደገኛ ደረጃ ላይ እንደደረሰ የሚያሳይ ማሳያ ነው።
ህፃናት የጦርነትም ሆነ የፖለቲካ ግጭት ሰለባ አደሉም! በማንኛውም ምክንያት ህፃናትን ማገትና መግደል ፈፅሞ ተቀባይነት የሌለው እና በአለም አቀፍ ህግም እንደ ጦር ወንጀል የሚቆጠር ተግባር ነው።
በተለይም ደግሞ የመከላከያ አቅም የሌላቸውን ህፃናት ደህንነት የመጠበቅ ሳይሆን ለጠላት በር ከፍቶ ድርጉቱ እንዲከናወን ተባባሪ ሆኖ ቆሟል።
ይህንን አረመኔያዊ ድርጊት የፈፀሙ አካላት ተለይተው ለፍትህ ሊቀርቡና የሚገባቸውን ቅጣት ሊያገኙ ይገባል። ግፍ ሰርቶ በነፃነት መዞር ለሌሎች ወንጀለኞች ማበረታቻ ነው።
የማህበረሰቡ ድምፅ ሊሰማ ይገባል! የንፁሃን ደም በከንቱ መፍሰስ ሊቆም የሚችለው ሁላችንም በአንድነት ግፍ ይብቃ" ብለን ስንቆም ነው።
የህፃናት ህይወት ለድርድር የሚቀርብ ጉዳይ አይደለም። በሸዋ ደራ የተፈፀመው ይህ አሰቃቂ ድርጊት በወረዳ አመራር እና በመከላከያ ትብብር ጭምር ነው። የወረዳው አመራር እና መከላከያው በትብብር ደራ ላይ ያለውን አማራ ለማጥፋት መምከራቸውን ተከትሎ ይህ ድርጊት እየተፈፀመ ነው። ይሄን ድርጊት ህዝቡ እንዲያውቅ እንዲረዳ እያሳሰብኩ ለመላው ለደራ ህዝብ ለሟች ቤተሰቦች እና ወገኖች በሙሉ መፅናናትን እመኛለሁ።
ፍትህ በግፍ ለተገደሉ ህፃናት!
