ru
Feedback

Не попадитесь на канал ботавода! Telemetrio находит и помечает такие каналы 👉 Хотите видеть метку — оформите подписку

ፍኖተ-አማራ ሚዲያ (Finote Amhara Media)

ፍኖተ-አማራ ሚዲያ (Finote Amhara Media)

Открыть в Telegram

የተመሠረተው የአማራን ሕዝብ ለማንቃት፣ ለማደራጀት እና ለማስተባበር ነው። የአማራ ሕዝብን ✅ ፖለቲካዊ ✅ ማህበራዊ ✅ ኢኮኖሚያዊ ታሪካዊ ጥያቄዎችን ለማሰማት እና የአማራን ሕዝብ በማንቃት ሰፊውን ሕዝብ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ይሰራል። ወደዱም ጠሉም የኃላ ታሪካችን በእኛ እጅ ይፃፋል። አማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ ( አፋብን)

Больше
4 387
Подписчики
-324 часа
+2587 дней
+1 43630 дней
Архив постов
ለግብዝ ተችዎቻችን የ1ዕለት የፋኖ ቻሌጅ👇 ¶. ለ 1ዕለት ዶፍ ዝናብ ቢዘንብባችሁ በጥቅጥቅ ጨለማ አልያም ከፍተኛ ሐሩር በበዛበት ቀን ዳጋቱን በእጃችሁ እየቦጠጣችሁ ብትዉጡ ቁልቁለት በእንብርካችሁ ብትወርዱ ምን ይሰማችኋል? ¶. ለ1ዕለት ሳትበሉ ሳትጠጡ ብትዉሉ ብታድሩ ጠኔያችሁ ምን ሊያደርጋችሁ ይችላል? ¶. ለ 1ዕለት ከቤተሰቦቻችሁ(ሚስት፣ልጅ፣እናት፣አባተ ወ.ዘ.ተ) መካከል በሞትና በህይወት መካከል ሁነዉ ከመሞታችን በፊት አይናችሁን ልያችሁ ልሰናበታችሁ እያሏችሁ ሁኔታዎች ስለማይፈቅዱ ሳትሰናበቷቸዉ ብትቀሩ በቀብራቸዉ በልቅሶቸዉ እርማችሁ ሳታወጡ ብትቀሩ ቀጣይ ህይወታችሁ ምን ሊመስል ይችላል ? ¶. በደጉም በክፉዉም ዘመን አብረዉ የነበሩ ለጋራ ዓላማ እና ነፃነት የተሰለፋ የስጋም የመንፈስም እህትና ወንድሞች በየቀኑ በሞት ብታጦቸዉ ልባችሁ ምን ያህል ይደማል? ¶. "ስንሞትም አንድ ላይ ስንታመም" ያሏችሁ አንድ የቀብሮ ጉድጓድ በጋራ፣ አንድ ብርጭቆ ሻይ በጋራ የጠጥታችሁ፣አንድ ዳቦ ከብዙ ቆርሳችሁ በልታችሁ ምስጢር ያከፈላቸኋቸዉ አብረዋችሁ የደሙ የቆሰሉ ሰዎች ንዋይ አታሏቸዉ ጠላት ጠልፎቸዉ ቢከዶችሁ ምን ይሰማችኋል? ¶. ለ 1ዕለት ብቻ ከሚያምረዉ አልጋችሁ፣ከምቾቱ ፍራሻችሁ ወርዳችሁ ምኝታችሁን አሸዋ ትራሳችሁን፣ ድንጋይ ልብሳችሁን ብጣሽ ሽርጥ አድርጋችሁ ብትተኙ ሰዉነታችሁ ምን ይሰማዋል? ¶. ለ1ዕለት እኒያ ያማሩ እና የተመረጡ ብራድ ጫማ የሚለብሱ እግሮቻችሁ ያለ ጫማ በአሸዋ ፥ በጠጠር እንዲሁም በእሾህ ላይ ለ24 ሰዓት ቢራመዱ እግሮቻችሁ ምን ሊሆኑ ይችላሉ? እኒህ ከላይ በትንሹ የተዘረዘሩ ሁነቶች በብዙ የፋኖ ታጋዮች ዘንድ በየዕለቱ የሚከሰቱ ፍዳዎች ናቸዉ። so እርስዎ እነኚህን ጥቂት መከራዎች ለ 1ዕለት ሊቋቋሙ ይቻላሉ ወይ? ሚዛናዊ ትችት የስልጡን ማህበረሰብ መገለጫ የዴሞክራሲያዊ እና ሰዉ ሰዉ ለሚሸት ስርዓት መገንቢያ እርሾ ነዉ።ዳሩ ግን አስር ሜትር በእግራችሁ መጓዝ ማትችሉ፤ሙቅና ቀዝቃዛ አፈራርቃችሁ እየጠጣችሁ፤ለጤንነታችሁ የግል ዶ/ር ቀጥራችሁ ጤንነታችሁን የምትጠብቁ፤በየሰዓቱ ሸሚዞችን እየቃያየራችሁ የምትለብሱ፤በደም አይነታችሁ አመጋግባችሁን አስተካክላችሁ የምትመገቡ፤ ቤተሰቦቻችሁ ቢያንስ በየዕለቱ በስልክ እያገኛችሁ ደህንነታቸዉን የምታዉቁ ከልክ በላይ በተጋነነ መልኩ የፋኖን ትግል የምትወቅሱ እነ ሰማይ ቅርቡ የሆናችሁ ግለሰቦች ወደ ልቦናችሁ ትመለሱ ዘንድ ወንድማዊ ምክሬን ለግሳለሁ:: አማራ ጀምሮ ያልጨረሰዉ አንድም ነገር የለም!! አሸናፊነታችን አማራ ከሚለዉ ስማችን ነዉ!! አዲስ ትዉልድ፣አዲስ አስተሳሰብ፣አዲስ ተስፋ!! (ህዳር 13/03/18) ፋኖ ዘዉድአለም አዱኛ

#አብይ ዓህመድ እና ቡድኑ በአሁኑ ወቅት እየተወራጩ ይገኛሉ! #ፀረ-አማራዊ እገዛዙ ሃይል አማራ ክልል ውስጥ ጥፋት ለመፈፀም እየገባ በተቃርኖው ሽንፈት እያስተናገደ፣እየተማረከ እና ግብዓተ መሬቱን እ
+4
#አብይ ዓህመድ እና ቡድኑ በአሁኑ ወቅት እየተወራጩ ይገኛሉ! #ፀረ-አማራዊ እገዛዙ ሃይል አማራ ክልል ውስጥ ጥፋት ለመፈፀም እየገባ በተቃርኖው ሽንፈት እያስተናገደ፣እየተማረከ እና ግብዓተ መሬቱን እያፋጠነው ይገኛል። #ጎንደር፣ጎጃም፣ሽዋ እና ወሎ በግፍ እየገባ ያለው የጁላ ምስለኒ ሰራዊት በፋኖ ሃይል ክፉኛ ምት እየደረሰበት እየተወቀጠ እና ድባቅ እየተመታ ይገኛል።በወገን ሃይል በደረሰበት ጥቃት ጠላት ከፍተኛ የሆነ አካላዊ ፣ሞራላዊ እና ቁሳዊ ኪሳራ እያስተናገደ ይገኛል!! #ለአገዛዙ የፖለቲካ ክንፉ የሃሰት ፕሮፖጋንዳ ሽፋን ግብዓት እንዲሆን ተደርጎ የታቀደው የወሸታሞች ዕቅድ በህልውና ታጋዩ የፋኖ ሃይል ሙሉ ለሙሉ በሚባል ደረጃ ከሽፏል!!! #ሀገር አፍራሹ፣ጅምላ ጨፍጫፊው፣ተላላኪው፣ተስፋየለሹ፣አወዳሚው፣ወራሪው፣ተስፋፊው፣መንግስታዊ መዕከልነቱን የተነጠቀው፣ፀረ-ህዝባዊ…ባዶ ድስኩር ፍርስራሹ የአብይ ምስለ ስርዓት በሀገር ወዳድ ኢትዮዽያን ሃይሎች እና በግዙፉ የፋኖ ሃይል የጋራ ትብብር በአጭር ጊዜ ውስጥ ይደመሰሳል!! ስር ነቀል ተነቅሎ ይወድቃልም! ዕጣ ፈንታው ታሪክ ይሆናል። #ይህ የሚተገበር አይቀሬ ነባራዊ ሃቅ ነው። #ነፃነት በነፃ አይገኝም!! #ታሪክ አለን ታሪክም እንሰራለን! #ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን! 🔐አርበኛ በየነ አለማው

የደቡብ ወሎ ዞን ተፈናቃዮች ለከፍተኛ የምግብ እጥረት ተጋልጠናል አሉ! በደቡብ ወሎ ዞን ሐይቅ እና ዉጫሌ ከተሞች አቅራቢያ የተጠለሉ ተፈናቃዮች ለከፍተኛ የምግብ እጥረት ተጋልጠናል አሉ ። ተፈናቃዮቹ እንዳሉት እስከ ሰባት ወራት ልዩነት ይቀርብ የነበረው አነስተኛ መጠን ያለው ምግብ አሁን እስከ መቋረጥ ደርሷል ። በደቡብ ወሎ ዞን ሐይቅ እና ዉጫሌ ከተሞች አቅራቢያ የተጠለሉ ተፈናቃዮች ለከፍተኛ የምግብ እጥረት ተጋልጠናል አሉ ። ተፈናቃዮቹ እንዳሉት እስከ ሰባት ወራት ልዩነት ይቀርብ የነበረው አነስተኛ መጠን ያለው ምግብ አሁን እስከ መቋረጥ ደርሷል ። በሂደት ቆይቶም ቢሆን የሚቀርበው ምግብ የተበላሸ መሆኑ ወደ ከተማ በመውሰድ ለእንስሳት መኖነት ለመሸጥ እስከ መገደድ እንዳደረሳቸውም ተናግረዋል። የዉጫሌ ወረዳ የምግብ ዋስትና ባልደረባ የተፈናቃዮቹን አቤቱታ አረጋግጠው ከአምስት ወራት በኋላ አሁን መጠነኛ ድጋፍ ማድረግ መጀመራቸውን ተናግረዋል።  ስማቸውን የማንጠቅስ ተፈናቃይ ከምስራቅ ወለጋ ተፈናቅለው ሐይቅ አካባቢ ከሰፈሩ ጥቂት ዓመታት ተቆጥረዋል። ለወትሮ ለወራት እየዘገየ ይመጣ የነበረውየምግብ ርዳታበመቋረጡ ለከፋ ችግር መዳረጋቸውን ለዶቼ ቬለ ተናግረዋል። «ኸረ ምን አለን ብለህ ነው ? በጣም ችግረኛ ነን ። ምንም ነገር የለንም ፤ የሚሰጠንም በቆሎ ነበር፤ በአራት ወር በሦስት ወር ፣ ያንንም ደግሞ የበሰበሰ የነቀዘ፣ 2001 ዓም 2002 [የተመረተ] ነው በቆሎው ፤ በዚያ ላይ ምንም ነገር የለንም መሬት ነው የምንተኛው ፣ በጣም ችግር ላይ ወድቀናል።»  እዚያው ሐይቅ እንደሚኖሩ የነገሩን ሌላው ተፈናቃይ በአስከፊ ሁኔታ ውስጥ መኖራቸውን ቢያረጋግጥም ርዳታ ይመጣልናል የሚል ተስፋ ግን እንደሰነቁ ነው። «ምን እናደርጋለን ? ችግር በችግር ሆነናል ። እኛ እንኳ መቼም ችግሩ ይፈታልና ፣መቼም ይህ ሁሉ ጉልበተኛ ሠርቶ ይበላል የሚል ተስፋ ነበረን ፣ የርዳታው እንኳ የሚያረካ አይደለም አልሃምዲሊላህ ተኝቶ ማደሩም አንድ ነገር ነው። » ከኦሮሚያ ፣ ከትግራይ እና ከአፋር ክልሎች በተለያዩ አጋጣሚዎች በተቀሰቀሱ ግጭቶች ከቤት ንብረታቸው የተፈናቀሉ በሺህዎች የሚቆጠሩ ተፈናቃዮች በደቡብ ወሎ ዞን በተለያዩ የመጠለያ ጣቢያዎች ተጠልለው እንደሚገኙ ጣቢያችን ሲዘግብ ቆይቷል።  ስማቸውን የማንጠቅስ  አንድ የአፋር ክልል አዳይቱ ተፈናቃይ በአምባሰል ወረዳ ከደረሱ አሁን አምስት ዓመታት ማስቆጠራቸውን ይናገራሉ ። የሰብአዊ ርዳታ እና መጠለያ ፍለጋ አስቸጋሪ ዓመታት ማሳለፋቸውን የገለጹት ተፈናቃዩ አሁን ከሱዳን ጭምር ወደ አካባቢው በርካታ ተፈናቃዮች እየደረሱ መሆናቸው ችግሮቹን እያወሳሰበው እንደሚገኝ ነው የገለጹት ። «በዚያው እኔ በመጣሁበት 2013 ግን ከትግራይ ብዙ ማኅበረሰብ መጣ ፣ ከዚያ ከአፋርም ከኦሮሚያም መጣ ፣ አሁን እየጨመረ እየጨመረ ነው የመጣው። ከዚያ አሁን ደግሞ ከሱዳንም መጥተዋል። በጣም ብዙ ማኅበረሰብ ነው ከሱዳን የመጣው አሁን ።»  በአካባቢው የተፈናቃዮች እና ስደተኞች መጨናነቅ ራሱን የቻለ መጠለያ ጣቢያ እንዳይኖር አድርጓል የሚሉት ተፈናቃይ ፣ተፈናቃዮች የኃይማኖት ተቋማትን ጨምሮ በተበታተነ ሁኔታ ውስጥ መገኘታቸው የሰብአዊ ርዳታ ለማግኘት የሚያደርጉትን ጥረት ተስፋ አስቆራጭ እንዳደረገባቸው  ነው የተናገሩት። «በቃ ምንም መፍትሔ የለንም አሁን ፣ ብዙ ነገር ጠይቀናል ፣ መጠለያ ካምፕ ጠይቀናል ፣ ተደራጅተን ጊዜያዊ ኮንቴይነር እንኳ እንዲሰጠን ጠይቀናል ፣ መልስ ግን የለንም ። ተፈናቃዩ አሁን በሳባትም በስምንትም ወር የምትመጣውን ርዳታ እየጠበቀ መኖር ሆኗል። ተስፋ የለንም አሁን።» በደቡብ ወሎ ዞን ውስጥ ለሚገኙ ተፈናቃዮች የሰብአዊ ርዳታ በወቅቱ ለምን ማድረስ እንዳልተቻለ ለመጠየቅ  በዞኑ አደጋ መከላከልና ምግብ ዋስትና ፕሮግራም ማስተባበሪያ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ አሊ ሰይድ የእጅ ስልክ ላይ በተደጋሚ ብንደውልም ስልካቸው ዝግ ነው ። የክልሉ አደጋ ስጋት ሥራ አመራር ኮሚሽን  ኃላፊን ምላሽ ለማካተት ያደረግነ ውም ጥረት የኮሚሽነሩ ዲያቆን ተስፋው ስልክ ባለመነሳቱ ሳይሰምርልን ቀርቷል። ነገር ግን ስማቸው እንዳያጠቀስ የጠየቁን የውጫሌ ወረዳ የምግብ ዋስትና ጽ/ቤት አንድ ባልደረባ በተፈናቃዮች የቀረበውን አቤቱታ አረጋግጠው ርዳታው ከደረሳቸው አሁን በአምስተኛው ወር ለማድረስ ጥረት እያደረጉ መሆናቸውን ተናግረዋል።  ለችግሩ መንግስት ትኩረት አለመስጠቱ ነገሮች እንዲወሳሰቡ ማድረጋቸውን የሚናገሩት ባልደረባው ከተፈናቃዮች የተበላሸ ምግብ እየቀረበ ነው ለሚለው ወቀሳም ማረጋገጫ ሰጥተዋል።  «ያው የትኩረት ማነስ ነው ። መንግስት ትኩረት ሰጥቶ እየደገፋቸው አይደለም። ይህም ደግሞ የሚሰጠው ጥራቱን የጠበቀም ይሄን ያህል አይደለም፤  በቆሎ በአራትም በአምስትም ወር ነው የሚሰጣቸው።»  ከላይ የሚመጣው ብዙም መፍትሄ እየሰጣቸው እንዳልሆነ የገለጹት የአደጋ መከላከል ባለሞያው ለጊዜው እንደ መፍትሔ የወሰዱት የአካባውን ማኅበረሰብ በማስተባበር አካባቢያዊ መፍትሄ በማበጀት ላይ እያተኮሩ መሆናቸውን ገልጸዋል።  Via:- DW

መተከል መተከል ቡለን ወረዳ በኩጂ የሚባል ቦታ ኦነግ ሸኔ በሚል የዳቦ ስም የጅምላ ግድያ ተፈጽሟል። እዚህ ቦታ ላይ ከአምስት አመት በፊት ጅምላ ግድያ ተፈጽሞ የሰው ልጅ እንደ ቆሻሻ በዶዘር ታፍሶ
መተከል መተከል ቡለን ወረዳ በኩጂ የሚባል ቦታ ኦነግ ሸኔ በሚል የዳቦ ስም የጅምላ ግድያ  ተፈጽሟል። እዚህ ቦታ ላይ ከአምስት አመት በፊት ጅምላ ግድያ ተፈጽሞ የሰው ልጅ እንደ ቆሻሻ በዶዘር ታፍሶ የተቀበረበት አካባቢ ነው። ዝርዝር ጉዳዩን አጣርተን እንቀርባለን ።

ሽርጥ ለባሽ ኮማንዶዎቹ ባካሄዱት የመደበኛ ውጊያና የሽምቅ ጥቃት ታላቅ ድል መቀዳጀታቸው ታወቀ! በሀብሩ ወረዳ ጊራና ከተማና ጎራርባ ቀበሌ ውስጥ በነበሩ የጠላት ወታደሮች ላይ በተደረገ ማጥቃት በርካታ ወታደሮች ተገድለዋል። በአፋብኃ ምኒልክ ዕዝ ምስራቅ አማራ ኮር1 የባለሽርጡ ክ/ጦር አሃዶች በሀብሩ ወረዳ ጊራና ከተማና በጎራርባ ቀበሌ ላይ በነበሩ የፀረ አማራው ብልፅግና ቡድን ተላላኪ ወታደሮች ላይ ትናንት ህዳር 12/2018 ዓ/ም ከረፋድ ጀምሮ እስከ አመሻሹ ባካሄዱት የመደበኛ ውጊያና የሽምቅ ጥቃት ታላቅ ድል መቀዳጀታቸውን ዕዙ በሕዝብ ግንኙነት መምሪያው በኩል ለመረብ ሚዲያ በላከው መረጃ አስታውቋል። "ሽርጥ ለባሽ ኮማንዶ" በሚል ቅፅል ስም የሚታወቁት ተወርዋሪ ጀግኖቹ፡ በጊራና ከተማ በሚሊሻ ካምፕ ላይ በፈፀሙት የተጠና ሽምቅ ጥቃት፡ ከ10 በላይ ሆድ አደር ሚሊሾች ሲገደሉ በርካቶች ቆስለዋል ነው ያለው ዕዙ ለጣቢያችን በላከው መረጃ! በዚህ ደፈጣ ጥቃት ወታደራዊ ካምፑ ከጥቅም ውጭ ሲደረግ ቁጥራቸው በውል ያልታወቀ በርካቶች ቆስለው ለሕክምና ወደ ጊራናና መርሣ መወሰዳቸው ተገልጿል። ጊራና ላይ በተፈፀመው ደፈጣ ጥቃት ሙትና ቁስለኛ ከመሆን የተረፉት ወደ ጎራርባ በመሸሽ ላይ እንዳሉ ድጋሚ የእሳት ውርጅብኝ ወርዶባቸዋል። የፋኖ አባላቱ ከደፈጣ ጥቃቱ በኋላ እግር በእግር በመከታተል ከጊራና ወደ ጎራርባ እየተንቀሳቀሱ የነበሩ የጠላት ወታደሮችን 360° በመክበብ እስከ አመሻሽ ድረስ በአፈሙዝ አለንጋ ሲገርፏቸው አምሽተዋል። በየሄደበት፣ በየደረሰበት በጅምላ መገደልና ማማ'ረክ እጣ ፈንታው የሆነው የአፀያፊው ብልፅግና ቡድን አገልጋይ ወታደሩ፡ በትናንትናው እለትም በጊራና ቀጠና የሞት ፅዋን ሲጎነጭ ውሏል። ፀረ አማራው አገዛዝ ከተገደሉበት ወታደሮቹ በተጨማሪ በውጊያው የቆሰሉትን በበርካታ ተሽከርካሪዎች ጭኖ ወደ ጊራና እና መርሣ ጤና ጣቢያዎች ሲያጓጉዝ ማምሸቱን ምኒልክ ዕዝ በሕዝብ ግንኙነት መምሪያው በኩል ለመረብ ሚዲያ በላከው መረጃ አስታውቋል። መረበኞች ነን መረጃ አጥማጆች!

የአፋብሃ ሜጀር ጄኔራል ውባንተ አባተ 1ኛ ኮር ጉና ክፍለ ጦር ስማዳ ሃገረ ቢዘን ብርጌድ ስማዳ ጉጦ ቀበሌ በተጠና ኦፕሬሽን 1ሚኒሻ በቁጥጥር ስር አዋለ።
የአፋብሃ ሜጀር ጄኔራል ውባንተ አባተ 1ኛ ኮር ጉና ክፍለ ጦር ስማዳ ሃገረ ቢዘን ብርጌድ ስማዳ ጉጦ ቀበሌ በተጠና ኦፕሬሽን 1ሚኒሻ በቁጥጥር ስር አዋለ።

102ኛ ኮር 11ኛ ክፍለጦር እና 33ኛ ክፍለጦር ጠላትን በልኩ ሲያናግሩት ውለዋል። በዛሬው እለት በቀን 13,03,2018 ዓ.ም ጠላት መነሻውን ጎንጅ፣አዴትና ጭስ አባይ መዳረሻውን ይልማና ዴንሳ ወረዳ አንጋርና ሰቀላ ቀበሌ በማድረግ በሶስት አቅጣጫ በሌሊት እንቅስቃሴ ያደረገ ሲሆን የ11ኛ ክፍለጦር ቃኝና መሀንዲስ ከሌሎች ሻለቃዎች እና የ22ኛ ክፍለጦር አካል የሆነቸው ጣናው መብረቅ ሻለቃ ጋር ጥምረት በመፍጠር ፣እንደ አንድ ልብ መካሪ እንደ አንድ ቃል ተናገሪ በመሆን ቀድሞ በደረሳቸው መረጃ መሰረት ቅድመ ዝግጅት በማድረግ በወሰዱት የአፀፋ እርምጃ አንጋርና ሰቀላል ላይ ሲወቁት ውለዋል። የጠላትን ሀይል ሙትና ቁስለኛ በማድረግ ሲገርፉት የዋሉ ሲሆን የፉኖን ክንድ መቋቋም ያቃተው የአገዛዙ ቡድን ከአዴት ተጨማሪ ሀይልና ዙ23 በማስመጣት በሁለት አይሱዙ ኮድ B13272isuzu እና A22480isuzu ሙትና ቁስለኛውን ይዞ የተመለሰ ሲሆን ከዚህ ጋር በተያያዘ ዜና ለአማራ ህዝብ የመረረ ጥላቻ ያለው የኦህዴድ መራሹ ቡድን አግታ ከተማ ላይ 1.አቶ ንግሩ ምትኩ 2.ወጣት ተሸራሽ ሽቤ የተባሉትን ንፁሀን ግለሰቦች በግፍ ሲረሽን በተጨማሪም የአብይ አህመድ የጭ*ን ገረ*ድና ዙፋን አስጠባቂ አድማ ብተና ባህርዳር ዙሪያ ወረዳ የግንድ ሎሚ ቀበሌ ላይ አቶ ታዘብ ወንዲፍራው የተባለን የንፁሀን መኖሪያ ቤትን አቃጥሏል። በተመሳሳይ ጠጠር ማርያም ላይ 33ኛ ክፍለጦር ጠላትን አይቀጡ ቅጣት ቀጠው ሙትና ቁስለኛ አድርገውታል። የደረሰበትን ምት መቋቋም ያቃተው አረመኔ ሰራዊት በሰብል ስብሰባ ላይ የነበሩ አርሶአደሮችን በአሰቃቂ ሁኔታ ገሏል። ሁሉም አማራ ይህን አረመኔአዊ አገዛዝ ለማስወገድ የበኩሉን ሊወጣ ይገባል። አማረ ጌታቸው አፋብኃ ምዕራብ አማራ ቀጠና ቴዎድሮስ ዕዝ 102ኛ ኮር የ11ኛ ክፍለ ጦር ህዝብ ግንኙት ኃላፊ

ብልፅግና "እረ አሳታሪቂስ የለም ወይ" የሚለውን የድምፃዊ አብነት አጎናፍርን ሙዚቃ እያንጎራጎረ ነው። ዐብይ አህመድ፡ አማልዱኝ፡ አስታርቁኝ በሚል ሽማግሌዎችን መርጧ ልኳል። ነገር ግን..."ባልዘፈን
ብልፅግና "እረ አሳታሪቂስ የለም ወይ" የሚለውን የድምፃዊ አብነት አጎናፍርን ሙዚቃ እያንጎራጎረ ነው። ዐብይ አህመድ፡ አማልዱኝ፡ አስታርቁኝ በሚል ሽማግሌዎችን መርጧ ልኳል። ነገር ግን..."ባልዘፈንሽ ባልዘፈንሽ፡ ከዘፈንሽ ባላፈርሽ" የሚል ምላሽ ነው የተሰጠው።

102ኛ ኮር 11ኛ ክፍለጦር እና 33ኛ ክፍለጦር  ጠላትን በልኩ ሲያናግሩት ውለዋል።   በዛሬው እለት በቀን  13,03,2018 ዓ.ም ጠላት መነሻውን ጎንጅ፣አዴትና ጭስ አባይ መዳረሻውን ይልማና ዴንሳ ወረዳ አንጋርና ሰቀላ ቀበሌ በማድረግ   በሶስት አቅጣጫ  በሌሊት እንቅስቃሴ ያደረገ ሲሆን የ11ኛ ክፍለጦር  ቃኝና መሀንዲስ  ከሌሎች ሻለቃዎች እና  የ22ኛ ክፍለጦር አካል የሆነቸው ጣናው መብረቅ ሻለቃ  ጋር ጥምረት በመፍጠር ፣እንደ አንድ ልብ መካሪ እንደ አንድ ቃል ተናገሪ በመሆን  ቀድሞ በደረሳቸው መረጃ መሰረት ቅድመ ዝግጅት በማድረግ በወሰዱት የአፀፋ እርምጃ አንጋርና ሰቀላል ላይ ሲወቁት ውለዋል። የጠላትን ሀይል ሙትና ቁስለኛ በማድረግ ሲገርፉት የዋሉ ሲሆን የፉኖን ክንድ መቋቋም ያቃተው የአገዛዙ ቡድን ከአዴት ተጨማሪ ሀይልና ዙ23 በማስመጣት በሁለት አይሱዙ ኮድ  B13272isuzu እና A22480isuzu ሙትና ቁስለኛውን  ይዞ የተመለሰ ሲሆን ከዚህ ጋር በተያያዘ ዜና ለአማራ ህዝብ የመረረ ጥላቻ ያለው የኦህዴድ መራሹ ቡድን አግታ ከተማ ላይ 1.አቶ ንግሩ ምትኩ 2.ወጣት ተሸራሽ ሽቤ የተባሉትን ንፁሀን ግለሰቦች በግፍ ሲረሽን በተጨማሪም የአብይ አህመድ የጭ*ን ገረ*ድና ዙፋን አስጠባቂ አድማ ብተና ባህርዳር ዙሪያ ወረዳ የግንድ ሎሚ ቀበሌ ላይ አቶ ታዘብ ወንዲፍራው የተባለን የንፁሀን መኖሪያ ቤትን አቃጥሏል። በተመሳሳይ ጠጠር ማርያም ላይ 33ኛ ክፍለጦር  ጠላትን  አይቀጡ ቅጣት ቀጠው ሙትና ቁስለኛ አድርገውታል። የደረሰበትን ምት መቋቋም ያቃተው አረመኔ ሰራዊት በሰብል ስብሰባ ላይ የነበሩ  አርሶአደሮችን   በአሰቃቂ ሁኔታ ገሏል። ሁሉም አማራ ይህን አረመኔአዊ አገዛዝ ለማስወገድ የበኩሉን ሊወጣ ይገባል። አማረ ጌታቸው አፋብኃ ምዕራብ አማራ ቀጠና ቴዎድሮስ ዕዝ 102ኛ ኮር የ11ኛ ክፍለ ጦር ህዝብ ግንኙት ኃላፊ

በእነማይ ወረዳ ሕዝባዊ ውይይቶች ተካሄዱ‼️ ህዳር 13/2018 ዓ.ም የአፋብኃ ቴወድሮስ ዕዝ 201ኛ ኮር አመራሮች እና የእነማይ ወረዳ ጊ/መንግስት በእነማይ ወረዳ መሌ ግማ ደብረገነት እና ዲማ ዙሪያ ቀበሌ ከማህበረሰቡ ጋር ሰፊ ውይይት ተካሂዶዋል። የህዝቡን ፍላጎት መሰረት ያደረገ የመዋቅር መሪወችን ማስመረጥ ተችሏል። 🔹የቀበሌ አስተዳደር 🔹የቀበሌ ም/አስተዳዳሪ 🔹የቀበሌ አስተዳደር ፀጥታ ዘርፍ 🔹 የቀበሌ ማህበራዊ ፍትህ አገልግሎት 🔹የቀበሌ ወጣት አደረጃጀት 🔹የቀበሌ ችግር ፈቺ የሀገር ሽማግሌዎችን ተዋቅረዋል። የ201ኛ ኮር አመራሮች የአረመኔው ሰራዊት በአማራ ህዝብ ላይ እያካሄደ ያለውን ዘር ተኮር ጭፍጨፋ እና ድርጅቱ ያለበትን ወቅታዊ ቁመና በተመለከተ ለማህበረሰቡ ሰፊ የፖለቲካ ግንዛቤ ሰጥተዋል። አዲስ ትውልድ፣አዲስ አስተሳሰብ፣አዲስ ተስፋ! ህዳር 13/2018 ዓ.ም ቴወድሮስ ዕዝ 201ኛ ኮር 64ኛ ክፍለ ጦር ሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ

አርሲ፡ አሳዛኝ መረጃ‼️ በሺርካ ወረዳ ጋዶ ጉና ከሚባለው ከተማ በግምት ከ10 ኪ.ሜ ራቅ ብሎ በሚገኝ ስፍራ በትናንትናው ዕለት አርብ ለቅዳሜ አጥቢያ በምስራቅ አርሲዋ ሺርካ ወረዳ ኦርቶዶክሳውያን የ
አርሲ፡ አሳዛኝ መረጃ‼️ በሺርካ ወረዳ ጋዶ ጉና ከሚባለው ከተማ በግምት ከ10 ኪ.ሜ ራቅ ብሎ በሚገኝ ስፍራ በትናንትናው ዕለት አርብ ለቅዳሜ አጥቢያ በምስራቅ አርሲዋ ሺርካ ወረዳ ኦርቶዶክሳውያን የአንድ ቤተሰብ አባላት ተገድለዋል ሲሉ አንድ ስማቸው እንዳንይጠቀስ የፈለጉ ግለሰብ መረጃውን ለከሰም ሚዲያ አድርሰዋል ። ...የሟቾች ስም፦ ➤ አቶ ባትሪ ካሳ ➤ አቶ ሰሎሞን ካሳ    ሌላው፤ ለጊዜው ስሙ ያልታወቀ ሦስተኛ ሟች እና ቆስለው የተረፉ ይገኛሉ.... ። ነፍስ ይማር ! 😭 💔

የአማራ ብሶት እና ሰቆቃ ያንገበገበዉ ፲ አለቃ ገብሬ 1 ስናይፐር፣ 1 ብሬን ፣ 1 ጥቁር ክላሽንኮቭ፣ 250 የክላሽ ጥይት እስከ ትጥቁ፣ 150 የብሬን ጥይት፣ 03 ቦንብ ብቻዉን ይዞ በአሁኑ የአደረ
የአማራ ብሶት እና ሰቆቃ ያንገበገበዉ ፲ አለቃ ገብሬ 1 ስናይፐር፣ 1 ብሬን ፣ 1 ጥቁር ክላሽንኮቭ፣ 250 የክላሽ ጥይት እስከ ትጥቁ፣ 150 የብሬን ጥይት፣ 03 ቦንብ ብቻዉን ይዞ በአሁኑ የአደረጃጀት አጠራር አፋብኃ ምዕራብ አማራ ቀጠና ቴዎድሮስ ዕዝ 105ኛ ኮር 66ኛ ክ/ጦር 1ኛ ሻለቃን የተቀላቀለዉ ፲ አለቃ ገብሬ ከባድ ኦፕሬሽን እየሰራ የአብይ አህመድን ገረድ ሰራዊት እያንቀጠቀጠዉ ይገኛል። አማራነት እንዲህ ነው !! ናይሎ አማራ

የፋሽስቱ አገዛዝ ብልፅግና ሰራዊት ሁለት የቡድን መሳሪያ እና 29 ክላሽ በመያዝ ዞብል አምባ ክፍለጦርን ተቀላቀሉ‼️ ጀምበር የጠለቀችበት የብልፅግና አገዛዝ በርካታ ሰራዊቱ እየከዳውና እየፈረሰ ፋኖን
+1
የፋሽስቱ አገዛዝ ብልፅግና ሰራዊት ሁለት የቡድን መሳሪያ እና 29 ክላሽ በመያዝ ዞብል አምባ ክፍለጦርን ተቀላቀሉ‼️ ጀምበር የጠለቀችበት የብልፅግና አገዛዝ በርካታ ሰራዊቱ እየከዳውና እየፈረሰ ፋኖን እየተቀላቀለ ያለ ሲሆን አንድ ስናይፐር አንድ ብሬን እንዲሁም 29 ክላሽ የያዙ በአጠቃላይ 31 አባላቶቹ ኮብልለው ምኒልክ ዕዝ ምስራቅ አማራ ኮር 2 ዞብል አምባ ክፍለጦርን ተቀላቅለዋል:: በዚህም ሁለቱ የቡድን መሳሪያዎች ብሬን እና ስናይፐሩ እንዲሁም 26 ጥቁር ክላሽ እና 3 ስናይቶ ባጠቃላይ 29 ክላሽ ከተሟላ ትጥቅና ተተኳሽ ጋር ዞብል አምባ ክፍለጦር ገቢ ሆኗል:: የክፍለጦሩ እና የሻለቃ አመራሮችም አቀባበል አድርገውላቸዋል:: መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልውና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል! ሕልውናችን በተባበረ ክንዳችን! ©አፋብኃ ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ 13/ዐ3/2018 ዓ.ም

አሁናዊ መረጃ ከደቡብ አፍሪካ ፋሺስታዊው ጨፍጫፉው አራዊት ሰራዊት አብይ አህመድ በአማራላይ የሚያደርገውን የአማራን ዘር ጭፍጨፋ በመቃወም በደቡብ እፍሪካ የሚገኙ አማራዎች እንደዚህ በነቂስ ወተው በጂ
+3
አሁናዊ መረጃ ከደቡብ አፍሪካ ፋሺስታዊው ጨፍጫፉው አራዊት ሰራዊት አብይ አህመድ በአማራላይ የሚያደርገውን የአማራን ዘር ጭፍጨፋ በመቃወም በደቡብ እፍሪካ የሚገኙ አማራዎች እንደዚህ በነቂስ ወተው በጂ 20 ስብሰባ በሚደረግበት አዳራሽ ፊለፊት ተቃውማቸውን እየገለፁ ይገኛሉ