ፍኖተ-አማራ ሚዲያ (Finote Amhara Media)
Открыть в Telegram
የተመሠረተው የአማራን ሕዝብ ለማንቃት፣ ለማደራጀት እና ለማስተባበር ነው። የአማራ ሕዝብን ✅ ፖለቲካዊ ✅ ማህበራዊ ✅ ኢኮኖሚያዊ ታሪካዊ ጥያቄዎችን ለማሰማት እና የአማራን ሕዝብ በማንቃት ሰፊውን ሕዝብ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ይሰራል። ወደዱም ጠሉም የኃላ ታሪካችን በእኛ እጅ ይፃፋል። አማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ ( አፋብን)
Больше4 387
Подписчики
+124 часа
+757 дней
+1 40730 дней
Архив постов
ፍትህና እኩልነት: እስልምና በሰው ልጆች መካከል ዘር፣ ቀለም፣ ወይም ደረጃ ሳይለይ እኩልነትና ፍትህን ያስተምራል።
መልካም ስነምግባር: እውነት መናገር፣ ታማኝነት፣ ጎረቤትን መርዳት፣ ወላጆችን ማክበር፣ ርኅራኄና ይቅርታ ማድረግን ያበረታታል።
ሰላማዊ አብሮ መኖር: ከሌሎች እምነት ተከታዮች ጋር በመቻቻልና በመከባበር መኖርን ያስተምራል።
ክብር እና ንፅህና: አካላዊ፣ ስነምግባራዊ እና መንፈሳዊ ንፅህናን ትልቅ ቦታ ይሰጣል።
እነዚህ የእስልምና
---የድሮን አሰሳ
በእግረኛው ሀይል የማይተማመነው አገዛዙ ፋኖ በተቆጣጠረባቸው ቦታዎች ከፍተኛ የሆነ የድሮን አሰሳ እያደረገ ይገኛል
አሁን 7:00 ሰዓት ላይ ሰከላ ዙሪያ ባሉ አካባቢዎች- ጣሊያ፣ ሱርባ፣ጉደራ፣ጅግሪታ፣አጉት ፣ አሽፋና ፈልቃ አካባቢዎች የድሮን አሰሳ ስላለ ጥንቃቄ ይደረግ!
ቻናላችን ሸር ጆይን አድርጉ ቤተሰብ
https://t.me/httpsuYkZrGfSZrNjNjFk
+1
በእውነት ሁሉም ነገር ዘመዴ እንዳለው ነው መፍትሄው መነጋገር መደረጀት እንቢ አልታረድም ብሎ መታጋል ነው ከለበለዚያ እየመጣ ካለው ነገር እንዳልሰማ እንዳላየ የሆነው ብለው አፋቸውን ዘግተው የተቀመጡ ኦርቶዶክስዊያም ይሁን ሙስሊም ቢሆኑ ከዚህ ስይፍ አያመልጡም። ስለዚህ ኢትዮጵያውያን የሆነ ሁሉ ወይም መደራጀት ወይም ከዚህ የፋኖን ትግል በመደገፍ ወደ ፊት መራመድ ብቻ ነው የሚያዋጣው ዴቭ ነኝ ከትግል ሚዳ
የአይሻ አህመድ አጥንት እሾ ሆኖ ይውጋኝ አማራ ያሸንፋል።
ቻናላችን ሸር ጆይን አድርጉ ቤተሰብ
https://t.me/httpsuYkZrGfSZrNjNjFk
+6
👉ፊታውራሲው ግዮን ብርጌድ አብሪ ኮከቦች‼️
======
➡️እነዚህ የግዮን ብርጌድ አብሪ ኮከቦች ለአማራ ህዝብ ኩራቶች የለውጥ ተምሳሌቶች ፊታውራሪው ግዮን ብርጌድን በስራ አስፈጻሚነት፣በሀብት አሰባሳቢነት፣በተለያዬ የአመራርነት ደረጃ ፣በተለያዩ ንዑስ ኮሚቴነት ለአለፉት ዘጠኝ ወራት ሲያገለግሉ ፣ሲታገሉ፣ሲያታግሉ የነበሩና ግዮን ብርጌድ በአለም አደባባይ ከፍ ብሎ እንዲዘመርለት ያደረጉ ትንታግ አመራሮች ናቸው።
እነዚህ አመራሮች ሰለቸኝ ደከመኝ የማያወቁ፣ ስራ ቆጥረው ሰጥተው ስራ ቆጥረው የሚቀበሉ፤የተቀበሉትን ስራ ደግሞ በጠላት መሀል በእግራቸው 12 ሰአት ተጉዘው ሀብት የሚያሰባስቡ፣ሻለቆቻቸውን የሚደግፉ፣ማህበረሰባቸውን የግንዛቤ ፈጠራ የሚሰጡ ከሁሉም አካል ጋር እጅና ጓንት ሁነው የሚሰሩ የግዮን ብርጌድ አብሪ ኮከቦች የትግሉ ማርሽ ቀያሪ ናቸው።
👉በአለፉት ዘጠኝ ወራት ኮለኔል አባተ ከእነ ግብረ አበሮቹ እንዲደመሰስ፣ዲሽቃ እንዲማረክ እና በርካታ የጠላት ሀይል እንዲደመሰስ የትግል ሜዳውን ያመቻቹ የትግሉም መሀንዲስ ናቸው።
አንድነታችሁ ለሌላው አራያ ለትግሉ ብርሃን ነውና በዚሁ ቀጥሉበት‼️‼️
የቻለ አድማሱ
ቻናላችን ሸር ጆይን አድርጉ ቤተሰብ
https://t.me/httpsuYkZrGfSZrNjNjFk
• አሩሲ ኦሮሞ፣ ኦሮሚያ…¡¡
"…እናንት በራሳችሁ አባቶች የተካዳችሁ፣ ከእናንተ ወተቱንና ሥጋችሁን ለራሳቸው መጠጣትና መብላት እንጂ እናንተን ከአውሬ፣ ከነጣቂ የማያስጥሉ እረኛና አባት የሌላችሁ። የገዛ እንጀራችሁን በልተው መልሰው ተረከዛቸውን የሚያነሱባችሁ የእናት ጡት ነካሽ፣ አሳልፈው የሚሰጡ ይሁዳ ልጆችን የወለዳችሁ፣ የሀገሬው መንግሥት እንደ ጠላት፣ እንደ ታዳኝ አውሬ እንጂ እንደ ዜጋ የማያያችሁ፣ የማይቆጥራችሁ፣ የማያውቃችሁ፣ ፖሊስ፣ ሚሊሻ፣ ወታደር እንደዜጋ ቆጥሮ የማይጠብቃችሁ፣ ፍርድ ቤት ፍትሕ ማግኘት የተከለከላችሁ። የሀገሪቱ ሚዲያዎች፣ ጋዜጠኞች ሞታችሁን መዘገብ ባልተጻፈ ዐዋጅ የተከለከላችሁ፣ የሕዝብ ተወካይ ምክርቤት ስለ ጭፍጨፋችሁ ደንታ የሌለው የሆነባችሁ፣ ለምን ብሎ የሚጠይቅ ወታደር፣ የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ያጣችሁ፣ በአደባባይ መሰደብ፣ በአደባባይ መዋረድና መታረድ ዕጣ ፈንታችሁ፣ የ40 ቀን ዕድላችሁ ነው አምናችሁ ተቀበሉ የተባላችሁ። እንደ ቆሻሻ፣ እንደ ጥራጊ የተቆጠራችሁ፣ መጨፍጨፋችሁን፣ ሞታችሁን ጭምር መስቀል በጨበጡ፣ ቀድሰው ባቆረቧችሁ፣ ወንጌል ባስተማሯችሁ፣ ከእናንተው መቀነት ተፈትቶ በተሰበሰበ፣ በተለቀመ ሳንቲም ከርሳቸውን ሞልተው ልጆቻቸውን በሚያሳድጉ በራሳችሁ እረኞች አንደበት የተካዳችሁ፣ ሲያርዷችሁ የማትንፈራገጡ፣ የማትጮሁ፣ ላለመሞት እንኳ የማትሞክሩ፣ ድረሱልኝ ብትሉም የሚደርስላችሁ የሌለ፣ መሄጃ፣ መሸሺያ፣ መጠለያ፣ መጠጊያ፣ መደበቂያ ሥፍራ ያጣችሁ፣ በቀን በብርሃን ቀኑ የጨለመባችሁ፣ በምድር ላይ የሚታደጋችሁ ያጣችሁ፣ የመሞቻ፣ የመታረጃ ቀናችሁን በስጋት የምትጠባበቁ ሆይ…!
"…እንደምን አደራችሁ?
"…እንደምን አረፈዳችሁ?
"…እንደምን ዋላችሁ?
"…እንደምን አመሻችሁ?
ቻናላችን ሸር ጆይን አድርጉ ቤተሰብ
https://t.me/httpsuYkZrGfSZrNjNjFk
ቤተ ክርስቲያን ለራሷ ልጆች እና ለአማራ መገደያ የሚሆን የጥይት መግዣ እያቀበለች ነዉ።
ጉድ በል!!
የነ አቡነ ሳርዮስ (አርዮስ)
ግዜ ይሄን ይመስላል።
‹‹ሰው›› ከመሆን በላይ ምን አለ?
ፈላስፋ እና ደራሲው ካህሊል ጂብራን፡- ‹‹አንድ ሰው በውስጡ ሁለት ሰዎችን ነው፤ አንዱ በብርሃን ሲተኛ ሌላው በጨለማ ይነቃል›› አለ፡፡ በዛሬዋ ኢትዮጵያ የብዙዎች ማንነት እንዲሁ መስሏል። በብርሃን የሚተኛ ማንነት የሰው ስላም ይረብሸዋል፣ የሰው ፍቅር ያውከዋል፣ የሰው አንድነት ይበታትነዋል፣ የሰው መከባበር ዝቅ ያደርገዋል፣ የሰው ሳቅ ያስለቅስዋል፣ የሰው ዝምታ ያስጮኸዋል፡፡ እናም በብርሃን መተኛትን ይመርጣል።
በጨለማ ደግሞ ይነሳል፡- ስለጦርነት ይሰብካል፣ ስለብሔሩ ይፎክራል፣ ስለመንደሩ ይጮሃል፣ ስለዕልቂት ይተነብያል፡፡ በእሱ ዘንድ ‹‹ሰው›› የለም፡፡ ለእሱ ህያው የሚላቸው ነገሮች በደቦ የሚታሰቡበቱ ፓርቲው፣ ብሄሩ፣ እምነቱ ወይም ደግሞ ቡድኑ ናቸው፡፡ እነሱ መልካም የሚሉት መልካም፣ ክፉ የሚሉትንም ክፉ ብሎ እያስተጋባ ይቀጥላል፡፡ "ሰው መሆንን" ብቻ ይዘው የዕውቀት ጫፍ የረገጡት ለሰው ጥቅም በፈጠሩት ቴክኖሎጂ ሰውን ሲያክፋፋ፣ ሲያጥላላ፣ ሲሳደብና ሲራገም ውሎ ይገባል።
ዛሬ ሰውን ከሰው በሚያማርጥ እና በሚያበላልጥ የብሄር ማንነት፣ የፖለቲካ አቋም፣ የሀብት መጠን የሃይማኖት ፍልስፍና እና የፍትህ ትርጉም ተይዘን የሰዎችን ተፈጥሯዊ እኩልነት እስከመዘንጋት ደርሰናል።
ጠቢቡ ዲዮጋን በቀን ብርሃን ፋኖስ አብርቶ በገበያ ሥፍራ ሲዞር የተመለከቱት ምን እንደሚፈልግ ሲጠይቁት፡- ‹‹ሰው እየፈለግሁ ነው›› አላቸው። ሰው በሞላበት ሀገር ‹‹ሰው›› መፈለግ ግዴታ የሚሆንበት አንዳንድ ዘመን አለ፡፡ የዲዮጋን ዘመኗ አቴና የሰው ትርጉሙ እንጂ የሰው እውነቱ የጠፋባት መስላ ነበር። አንዱ በዘሩ፣ ሌላው በዕውቀቱ፣ ከፊሉ በዝናው፣ ግማሹ በሀብቱ፣ የቀረውም በሃይማኖቱ የማንነቱን ትርጉም እየገለጠ ‹‹ሰው›› መሆንን ወደ ትንሽነት ቀየረው᎓᎓ ሰው መሆን ለዘረኛውም፣ አዋቂ ነኝ ለሚለውም፣ በሀብቱ ለሚመካውም፣ በዝናው ለሚኮፈሰውም፣ በእምነቱ የፅድቅ አክሊል ለጨበጠውም ዋጋ ቢስ ነበር፡፡ ዲዮጋን ስዎችን በትዝብት ሲመለከት ሰው መሆናቸውን ረስተዋል፤ ለእነሱ የሰው ዋጋ መተመኛው ሆኖ የሚያለያያቸው፣ የሚያጋድላቸው በእሱ ዘንድ እጅግ የተዋረደ ቢሆንበት ተደነቀ፡፡ የሰው መሆንን ትልቅነት በዘነጉ ሰዎች መካከል ራሱን ቢያገኘው ‹‹ሰው›› ፍለጋ ወጣ፡፡ በሁሉም ላይ ከሚወጣው የቀኑ ብርሃን ይልቅ ዲዮጋን በፋኖሱ ጭላንጭል ‹‹ሰው›› እንደሚያገኝ አምኗል፡፡ እኔም አንዳንዴ ሰው ከመሆን ባሻገር በሌላ ተቀጥላ ስምና ማንነት የማያምን ‹‹ሰው›› (እንደ ዲዮጋን) መፈለግ ይናፍቀኛል፡፡
የእኛ ፖለቲካ ‹‹ሰው›› አያውቅም፡፡ በብሄር፣ በጎሳና፣ በቡድን እንድታስብ ለሚሻ ፖለቲካ ሰው ‹‹ምንም›› ነው፡፡ ግለሰባዊ እምነትና አስተሳሰብ ቦታ አይሰጠውም፡፡ አሻፈረኝ ብለህ እንደሰው ለሚገባህ ሥፍራ ብትቆም እንኳን በቡድን ሃሳብ ትጨፈለቃለህ፡፡
የእኛ እምነት ‹‹ሰው›› አያውቅም፡፡ ዛሬ በኢትዮጵያ የአማኝ እንጂ የእምነት ተቋማት ችግር የለም። የእኛ አማኝ በጥላቻ፣ በነቀፌታ እና በራስ ፍቅር የተጠመደ ነው፡፡ ለእኛ ሀገር አማኝ ‹ሰው›› መሆንህ ብቻ አይበቃውም፡፡ እሱ የሚያምነውን ማመን፣ እሱ የሚከተለውን መከተል፣ የእሱን ቋንቋ መናገር ካልቻልክ ‹‹ሰው›› ብቻ ብትሆን ምን ያደርግለታል? የቱንም ያህል ጥሩ እና በጎ አድራጊ ሰው ልትሆን ትችላለህ፤ እንደምትከተለው ሃይማኖት የሰማይ ዋጋህን በየጓዳቸው ይወስኑልሃል እንጂ በአንተ አይቀኑም። በአደባባይ ደግሞ ‹‹ተቻችሎ የመኖር ባህል›› ይሉታል፡፡ ሰውን እንደ ‹‹ሰው›› በእኩል የሚመለከት እምነት ቢኖረንማ ተቻችሎ መኖር ቀድሞውንም ባልተደሰኮረ ነበር።
በመጨረሻም እንዲህ _ እላለሁ፡- ‹‹ማንንም _ ሰው ጌታው እንዲሆን የማይፈቅድ እና እሱም የማንም ሰው ጌታ መሆን የማይሻ በእርግጥ እሱ ታላቅ ሰው ነው››፡፡ ለዚህም ፋኖነት የአማራ የነፃነት ምልክት ነው ዴቭ
+3
ጀኔራል ተፈራ ማሞ የቀድሞው የአማራ ክልል ልዩ ሃይል አዛዥ የአሁኑ የአፋብሃ ማዕከላዊ ኮማንድ አባል ጀኔራሉን በአማራ ልዩ ሃይል እያለን በቅርብ ከሚያውቁት ሰዎች መካከል አንዱ ነኝ እንደ አባት እና እንደ ልጅ እንመካከርም ነበር ጀኔራል እንደ እምታውቁት ግልፅ የዋህ እና ቅን ሰው ነው በውጊያ አንቱታን ያተረፍ እንደ ሀገር ታዋቂ ከሆኑ የጦር ሜዳ ተሸላሚ ጀግኖች መካከል አንዱ ተፊ ነው
ጀኔራል አስራ አምስት ቦታ የጥይት ምት አለበት ያልወጣም ጥይት አለበት ወደ ውጭ ወጥቶ ለመታከም ሲጠይቅ እንኳን መንግስት ነኝ በሚለው ሃይል ተክልክሏል በተለይ በቅዝቃዜ ስዓት ህመም ሊኖረው ይችላል ነገር ግን ጀኔራል ህመሙን ተቋቁሞ ሁሉን ነገር እርግፍ አድርጎ ትቶ ከሞትኩም ክብር ያለው ሞት ልሙት ብሎ በእዚህ እድሜው ከወጣቶቹ እኩል እየተጓዘ ወታደራዊ ልምድን እያስተማረ ወታደራዊ አመራሮችን እየገነባ እዚህ ደረጃ ደርሷል
ጀኔራል የሁላችንም አባት የአማራ ህዝብ የቁርጥ ቀን ልጅ ነው ።
ሰው ማለት ሰው በጠፋ ጊዜ ሰው ሆኖ መገኘት ነው ይህን ደግሞ ጀኔራል በተግባር የህዝብ ልጅ መሆኑን አስመስክሯል ስሙን በታሪክ መዛግብት ላይ አስፍሯል ልብ በሉ ጀኔራሉ በዚህ እድሜው እየታገለ እያታገለ ስመለከት ለእኔ ትልቅ ተስፋ ነው እሱን አይቶ የወደነት ወኔ የማይሰማው ወጣት ወንድነቱን ተሰልቧል የሚል አቋም አለኝ።
ጀኔራል ተፈራ ማሞ የእኛ የፋኖዎች ኩራት ፈጣሪ የደከምክበትን የትግልህን ፍሬ ለማየት ያብቃህ።
በትግል ላይ ፦ አላማ ፣እምነት፤ ተስፋ እና ፅናት ሊኖርህ ይገባል ልክ እንደ ጀኔራል ተፈራ!!
የአርበኛ ጌትነት መሳፍንትን መስዋዕትነት አስመልክቶ ከአርበኛ ደሳለኝ ሲያስብሸዋ የተላለፈ መልዕክት!
አርበኝነት በደም የሚወረስ የታሪክ ስንቃችን ነው። አርበኝነት ፈሪዎች የማይደርሱበት የጎበዞች መንበር ነው። አርበኝነት ከራስ በላይ ለአገርና ለህዝብ፤ ለታራክና ማንነት የሚዋደቁ የተመረጡ ዋጋ የሚከፍሉበት ህያው የታሪክ ገፃችን ነው።
እኛ አማራ ነን ስንል። ከአገር ሰሪው ታላቁ የአማራ ህዝብ አብራክ ስለወጣን ብቻ ሳይሆን እነዚያ ጥቁር ሰው መሆኑን በክንዳቸው ለዓለም ያስተማሩት አርበኞች የግብር ልጆች መሆናችንን በተግባር በማሳየት ነው።
አርበኝነት የትውልድ ቅብብል ውጤት ነው ስንል በእኛ ዘመን ከፊት ምሳሌ የምናደርገው የትግል አባታችን አርበኛ መሳፍንት ተስፉ ነው።
አባታችን የፕሮፌሰር አሥራት ወልደየስን አደራ በብረት ትግል ከተቀበሉ ቀዳሚ አርበኞች አንዱ ናቸው።
የአማራ ህዝብ የተቃጣበትን መዋቅራዊ ጥቃት ለመመከት የሀሳብ ትግል ያደረጉት፣ አንቂያችን አደራጃችን ፕሮፌሰር አሥራት የትግል ራዕያቸው በዘመናቸው ባይሳካም። ከሀሳብ ትግል ወደ ነፍጥ ትግል የገባው አማራ የፕሮፌሰር አሥራትን አደራ በመቀበል ነው።
ታላቁ አርበኛ መሳፍንት ተስፉ በአማራዊ ብሄርተኝነት፣ "አማራ ነኝ" ብለው ቀድመው ነፍጥ ካነሱት አንዱና ቀዳሚው ናቸው።
ከ 30 ዓመታት በላይ አማራ ነኝ ብለው በመታገል ለኛ ትውልድ የሞራልም የተግባር መምህር ሆነውናል።
በዚህ ሳይወሰኑ መላ ቤተሰባቸውን በአማራ የኀልውና ትግል ላይ አሰልፈው፣ ታሪክ በወርቃማ ቀለም የሚፅፈው ገድል እየሰሩ ነው።
የአማራ ህዝብን የታሪክ እጥፋት በሚወስነው በዚህ የትግል ታሪክ መላ ቤተሰቡ በትግል ሜዳ ተሰልፎ በሚከፍለው ዋጋ፣ አርበኛ ጌትነት መሳፍንት መስዋዕት መሆኑን የሰማሁት በከባድ ሐዘን ነው።
ለኛ ለታጋዮች ሞት ለአማራ ህዝብ ህልውና መረጋገጥ የምንከፈለው የመጨረሻው ስጦታችን ቢሆንም፣ አርበኛ ጌትነት ዕድሜው ለትግል ከደረሰበት ጊዜ ጀምሮ ያለእረፍት ከአባቱ ጎን ተሰልፎ የከፈለው ዋጋና ከዚህም በላይ የሚጠበቅበት ታጋይ መሆኑን ስናስብ ህልፈቱ ከባድ ሐዘን ፈጥሮብናል።
ቢሆንም በዚህ መራር ዋጋ እየተከፈለበት ባለ ትግል የ አርበኛ ጌትነት መሳፍንት እና ሌሎች ሰማዕታት የትግል አደራ ከግብ ለማድረስ የትግል ቃል ኪዳናችንን እናድሳለን።
ትግላችን እስከቀራኒዮ ነውና በእኛ መስዋዕትነት ታላቁን የአማራ ህዝብ ለዘላቂ ድል እናበቃዋለን።
በመጨረሻም ለድርጅታችን አፋብኃ የበላይ ጠባቂ አርበኛ መሳፍንት ተስፉ፣ ቤተሰቦቹ፣ እና መላው የትግል ጓዶቹ ልባዊ መጽናናትን እመኛለሁ።
ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን
የአፋብኃ ማዕከላዊ ኮማንድ አባል አሳምነው ዕዝ ሰብሳቢ አርበኛ ደሳለኝ ሲያስብሸዋ
ህዳር 3 ቀን 2018 ዓ.ም
+1
..............የአደረጃጀት ዜና !! ...........
በአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል ( አፋብኃ ) የቴዎድሮስ ዕዝ የ102ኛ ኮር የ33ኛ ክፍለጦር ምስረታ ተጠናቋል ።
በአፋብኃ ቴዎድሮስ ዕዝ የመልሶ ማደራጀት እና የመዋቅር ማሻሻል ተግባራት መካከል አንዱ የሆነው የኮር አደረጃጀት እና የክፍለጦር መልሶ ማደራጀት ይገኝበታል ።
ክፍለጦሩ በአምስት ሻለቃ የተዋቀረ ሲሆን ለቀጣይ የህልውና ትግል ዝግጁ መሆናቸውን የክፍለጦሩ ፣ የሻለቃ አመራሮች እና አባላት አረጋግጠዋል ።
የክፍለጦር መልሶ ማደራጀት ስራው በአርበኛ እሸቱ ጌትነት እና በአርበኛ እስቲበል አለሙ አስተባባሪነት ተጠናቋል ።
አዲስ ትውልድ አዲስ አስተሳሰብ አዲስ ተስፋ !!
ኦሮራ ከተማ ከምክር ቤት አባል
አት–ላርጅ
የህዝብ መግለጫ
እኔ እንደ ማህበረሰብ አባል እና እንደ ተመራማሪ የሕዝብ ውሳኔ ባለሥልጣን ከኢትዮጵያ የሚመጡትን አሳዛኝ ዘገባዎች በጣም ተጨንቄ እንዳለሁ እገልጻለሁ። በአርሲ ዞን ያሉ የኦርቶዶክስ ክርስቲያኖች ብዙ ሰዎች መግደል እና ተሰደደት እየተጋጠማቸው ነው። ሰዎችን በሃይማኖታቸው ወይም በብሔራዊነታቸው ምክንያት መታለል ተቀባይነት የለውም። ሰብአዊነት ከጥ hatred በፊት መቅደም አለበት። ክብር፣ ታማኝነት እና የሰብአዊ መብቶች ጥበቃ በማንኛውም መልኩ መተው የለባቸውም።
ይህንን ወቅታዊ ጉዳይ ለመጠቆም እና በኢትዮጵያና ኤርትራ መካከል የሚጨምሩ እብድ ግጭቶችን ለመጠንቀቅ በቀጥታ የትራምፕ የተለይቶ የተመረጠ አማካሪ እንደ ተገናኝሁት እገልጻለሁ። ዲፕሎማሲ መጀመር አለበት — ጦርነት አይደለም።
ሕይወት በአደጋ ሲደርስ መተላለፍ አይቻልም። ዓለም አቀፍ ማህበረሰብ ይህን ከተጨማሪ አደጋ ለመከላከል እና የተጎዳውን የዕውቅና ህዝብ ለመጠበቅ አሁን መውሰድ አለበት። ለሰላም፣ ለፍትሕ እና ለሁሉም ሰው የሕይወት ክብር መቆም አለብን።
አምሳሉ ካሳው
ኦሮራ ከተማ ከምክር ቤት አባል አት–ላርጅ
ጊዜያዊ አስተዳደሮች እና ህዝባዊ ውይይቶች አጠናክረው ቀጥለዋል!
አፋብኃ ቴዎድሮስ ዕዝ ይፋ ባደረገው አዲስ መዋቅር መሰረት በ 201ኛ ኮር 74ኛ ክፍለ ጦር እና በስሩ ባሉት የወረዳ ጊዜያዊ መስተዳድሮች የድርጅታችንን ቁመና ፣ አዲሱን መዋቅር በማስረዳት የማደራጀት ስራወች እየተሰሩ ናቸው።
ዛሬ በቀን 29/02/2018 ዓ/ም በአፋብኃ ምዕራብ አማራ ቀጠና እነብሴ ሳር ምድር ወረዳ ጊዜያዊ አስተዳደር ውስጥ የሚገኙ ነባርና በቅርቡ ከጠላት ነፃ የወጡ ቀበሌዎችን ማለትም እነጀረር (012) እና ደብረ መዳኒት (020) ቀበሌዎች ውይይት የተካሄደ ሲሆን፦
➢ የቀበሌ መዋቅር የሌላቸውን አዋቅረናል፣ ➢የድርጅታችን ወቅታዊ ቁመና በማስረዳት
➢ በወል መሬትና ሌሎች መሰረተ ልማቶች ዙሪያ የሚነሱ ጉዳዮችን የመጨረሻ እልባት በመስጠት፤ ማህበረሰቡም አጥቶት የነበረውን ነፃነቱን በማግኘቱ ደስታውን ገልፆ ይህንን ነፃነት ለማፅናት የትኛውንም ድጋፍ እንደሚያደርግና መስዋዕትነት ለመክፈል ዝግጁ እንደሆነ በሙሉ ድምፅ የመግባባት ስራ ተሰርቷል።
የእነብሴ ሳር ምድር ወረዳ ጊዜያዊ አስተዳደር ሚዲያና ኮምኒኬሽን ሀላፊ መረጃውን አደርሰውናል
ፋኖ ሐብታሙ የሱፍ
የቴድዎሮስ እዝ 201ኛ ኮር ህዝብ ግንኙነት
ህዳር 02/2018 ዓ.ም
ሰበር ዜና!
የአፋብኃ ምዕራብ አማራ ቀጠና ቴዎድሮስ 206ኛ ኮር የ14ኛ ክፍለ ጦር አካል የሆኑት የቀስተ ደመና ሻለቃ ፋኖዎች በጡት ቆራጩ የብልጽግና ሠራዊት ላይ እርምጃ ወሰደ።
የአፋብኃ ምዕራብ አማራ ቀጠና ቴዎድሮስ 206ኛ ኮር የ14ኛ ክፍለ ጦር አካል የሆኑት የቀስተ ደመና ሻለቃ ፋኖዎች የግዳድ ተብሎ በሚጠራ ቦታ ላይ ታላቅ ውጊያን በማድረግ በጡት ቆራጩ የብልጽግና ሠራዊት ላይ ድልን ተቀዳጅተዋል።
ከቅዳምን ተነስቶ ወደ ደብረ ኤልያስ ወረዳ ለመሻገር ያሰበውን ኃይል ለመቀበል ከደብረ ኤልያስ ከተማ ተነስቶ የመጣውን ጠላት ጀግኖቹ የቀስተ ደመና ሻለቃ ፋኖዎች የግዳድ ቀበሌ ላይ በመጠበቅ ከፍተኛ ጥቃት በመፈጸም በርካታ የጠላት ኃይልን ደምስሰዋል።
በውጊያወም 06 የጠላት ኃይል የተደመሰሰ ሲሆን 11 ያህሉ ከባድ ቁስለኛ ሆኗል።
የመጣው ጠላትም ሙትና ቁስለኛው ተሸክሞ ወደ መጣበት ተመልሷል።
ፋኖ ዘመን ባሳዝነው
የቴዎድሮስ ዕዝ 206ኛ ኮር 14ኛ ክፍለ ጦር ሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ
💪ሰበር መረጃ💪
ከወልድያ በቅርብ ርቀት አማየ ሚጫ ተብሎ በሚጠራው አከባቢ ላይ በተፈፀመ ደፈጣ ጥቃት አንድ ኦራል ሙሉ የአገዛዙ ወታደር ሙትና ቁስለኛ ተደርጓል!
ምስራቅ አማራ ኮር 2 ዞብል አምባ ክፍለጦር 6ኛ ሻለቃ ከመርጦ ወደ ወልድያ ከተማ ይጓዝ የነበረ የአገዛዙ ሰራዊት ላይ አማየ ሚጫ በሚባል ቀጠና ደፈጣ በመያዝ በፈፀሙበት ጥቅት ኦራል ላይ የነበረውን ሙሉ ለሙሉ ሙትና ቁስለኛ በማድረግ እንዲሁም በእግር ይጓዝ የነበረውን ከሙትና ቁስለኛ የተረፈውን ብትንትኑን በማውጣት ከባድ ሰብዓዊ ኪሳራ በማድረስ ታላቅ ጀብድ ፈፅመዋል ሲል የዕዙ ሕዝብ ግንኙነት መምሪያ ለመረብ ሚዲያ በላከው መረጃ አስታውቋል።
በቀጣይም የፋሽስቱ ብልፅግና አገዛዝ ሰራዊት ላይ የሚወሰደው እርምጃ በደፈጣ ጥቃት ረፍት በመንስስትና በማዋከብ እንዲማረር በማድረግ ሲያመች በመደበኛ ውጊያ በመደምሰስና በመማረክ ብሎም በማስኮብለል አገዛዙን የማፈራረሱ ስራ ተጠናክሮ ይቀጥላል ነው ያለው ዕዙ በሕዝብ ግንኙነት መምሪያው በኩል ለጣቢያችን በላከው መረጃ።
https://t.me/httpsuYkZrGfSZrNjNjFk
ሰበር ቲሊሊ ዘንገና ብርጌድ‼️
#ቲሊሊ_ላይ_ሁለት_ባስ_ምልምል_ሰራዊት_ጭቃ_ሁኗል💪
በአፋብኃ ምራብ አማራ ቀጠና ቴዎድሮስ ዕዝ ጎጃም አገው ምድር ክፍለ ጦር ቲሊሊ ዘንገና ብርጌድ አማካኝነት ከአዲስ አበባ ወደ ባህር ዳር ይቀንቀሳቀስ በነበረ ከ30 ባስ በላይ አዲስ ተመራቂ የመከላከያ ሰራዊት ላይ በተወሰደ የደፈጣ ጥቃት ሁለት መሉ ባስ ሰራዊት ከጥቅም ውጭ ሁኗል።
ዛሬ ህዳር 2/2018 ዓ.ም ከቀኑ 9:00 ላይ ከቲሊሊ ከተማ አቅራቢያ በቲሊሊ ዘንገና ብርጌድ ነበልባሎች በተደረገው ተኩስ በወራሪዉ ሰራዊት ላይ ከፍተኛ የሆነ ሰብዊና ቁሳዊ ኪሳራ ደርሶበታል።
በተወሰደዉ እርምጃ ሁለቱ ባስ መሉ በሙሉ ከጥቅም ዉጭ ሲሆን ከዉስጥ የነበሩ ሙሉ የመከላከያ ሰራዊቶችም እስከወዲያኛው ተወግደዋል።
ጡት ቁሩጥ አማራን አጥፋ ተብሎ በግዳጅ ታፍሶ ሰልጥኖ የሚላከዉ ሀይል ካሰበበት ሳይደርስ በነበልባሎቹ አንገቱ እየተቀላ የአሞራ ቀለብ እየሆነ ይገኛል።
ጠላት ምንም እንኳን ከቲሊሊ ቡሬ ያለዉን መንገድ ሙሉ በሙሉ አጅቦ ለማሳለፍ ዉጠራ ቢያደርግ እንከን የለሾቹ የቲሊሊ ዘንገና ብርጌድ ነበልባሎች ተስቦ በመግባት አጃቢ ቱልቱላዎችን ጨምሮ ሁሉቱን ባስ ሙሉ ሰራዊት አስወግደዉታል።
ቲሊሊ ዘንገና ብርጌድ ለተከታታይ ሁለት ቀናት እያደረገ ባለዉ ጥቃት ያለምንም ጉዳት የጠላትን ቅስም በመስበር ከፍተኛ ድል ተቀዳጅቷል።
ይህ በእንዲህ እንዳለ የተወናበደዉ ሀይል በመንገድ ያገኘው ሰው ሁሉ በተኩስ እያባረረ በቅርቡ የተገኘውን እየረሸነ ይገኛል። ትናንት ባደረሰው የንፁሃን ጥቃት ከአምስቶቹ ውስጥ ሶስቶቹ ህክምና ከገቡ በኋላ ህይወታቸው አልፏል።
"ፋኖዎቹ ከመቱን ንፁሃኑን የቲሊሊ ህዝብ እንረሽናለን" በማለት በይፋ እያስፈራሩ የቆዩት ሆድ አደር አድማ ብተና ትናንትናም ዛሬም ጥቃት በተሰነዘረባቸዉ ቁጥር የንፁሃንን ህይወት መቅጠፍ ቀጥለዋል።
ስለሆነም መሸነፉን ያረጋገጠው መጠጊያ የለሽ ቡድን ይዞ የመዉደቅ አላማ ስለያዘ ተኩስ በተከፈተበት አጋጣሚ ህዝቡ እራሱን እንዲጠብቅ እያልነ የወጣንለትን የህልውና ትግል ከግብ ሳናደርስ የማናፈገፍግ የቁርጥ ቀን ልጆች ነንና፤ጥቃቱን አጠናክረን የጠላትን አከርካሪ እየለየን መምታት የምንቀጥል ይሆናል‼
ላናሸንፍ የጀመርነው ትግል የለም፤ድላችን ቅርብ ነዉ💪💪
ይቀጥላል ገና.........
ህዳር 1/2018 ዓ.ም ላሊበላ የተከሰተው ምንድን ነው?
ሎሌው አረጋ ከበደና ስብስቡ በላሊበላ በተፈፀመባቸው ያልጠበቁት ከባድ ጥቃት ያሰቡትን ሳያሳኩ ወደ ምሽጋቸው ባህርዳር ተመልሰዋል::
ከኦሮሚያ ብልፅግና ጋር በመተባበር የአማራ ህዝብ ላይ ዘር ማጥፋት እየፈፀመ ያለው አረጋ ከበደና ስብስቡ ከፍተኛ ጭንቀት ላይ ያለው አለቃቸው አብይ አህመድ የሰጣቸውን ተልዕኮ ይዘው ወደ ሰሜን ወሎ ዞን ላሊበላ ከተማ የተጓዙ ሲሆን ትናትና ህዳር 1/2018 ዓ.ም ረፋድ ላሊበላ አየር መንገድ ከደረሰ በኋላ ጥቃት ተፈፅሞበታል::
አቶ አረጋ ከበደ እና የክልሉ ልዑካን ጥቃቱ የተፈፀመባቸው በምኒልክ ዕዝ ላስታ ጀኔራል አሳምነው ፅጌ ኮር ተከዜ ክፍለ ጦር 3ኛ ሻለቃና የክፍለ ጦሩ ሜካናይዝድ በጋራ በመሆን ህዳር 1/2018 ዓ.ም ከጧቱ 2:30 እስከ ረፋዱ 3:30 ድረስ በወሰዱት እርምጃ ነው::
ጥቃቱ የክልሉ ፕሬዝዳንት ነኝ የሚሉት አረጋ ከበደ እና ግብረ አበሮቹ ከባህርዳር ኤርፖርት በመነሳት ላሊበላ አለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ደርሰው ወደ ላሊበላ ከተማ በማቅናት ላይ እያሉ ሹምሽሃ አየር ማረፊያ አጠገብ ልዩ ስሙ በርታ በተባለ ቦታ ድንገተኛና የተጠና ልዩ የሽምቅ ኦፕሬሽን ነው::
በዚህም ሎሌዎቹ አቶ አረጋ ከበደና ግብረአበሮቹ ከአምላካቸው አብይ አህመድ የተሰጣቸውን ተልዕኮ ሳይፈፅሙ በከባድ ፍርሃትና ድንጋጤ ውስጥ ሆነው ወደ ባህርዳር ተመልሰዋል:: በጥቃቱ ከአስር በላይ ቀይ ቦኔት ለባሽ አጃቢዎቻቸው የተደመሰሱ ሲሆን የተወሰኑ ቁስለኞችም ነበሩ::
መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልውና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል!
ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን!
አፋብኃ ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ
ህዳር 2/2018 ዓ.ም
ቀጠናን ለማጥናት በኤርትራና በአፋር አካቢቢ ቅኝት ስታደርግ የነበረችው የአብይ አህመድ ድሮን በኤርትራ መንግስት ተጠልፋ መከስከሷ ታውቋል።
የምስራቅ አፍሪካን ቀንድ የትርምስ ማዕከል ለማድረግ በየ አቅጣጫው ጦርነትን የቀሰቀሰው አብይ አህመድ ቀይ ባህርን ለማስመለስ አደርገዋለው ላለው ዘመቻ መልከዓምድርን ስታጠና የነበረችው ድሮን የኤርትራን ድንበር ጥሳ በመግባት ቅኝት ላይ እያለች በደረሰባት ጥቃት በድንበር አካባቢ ተከስክሳለች። የድሮኗን ክስካሽ በአረመኔው ሰራዊት ማስለቀማቸው ከአካባቢው የወጣ መረጃ አመላክቷል።
