ፍኖተ- አማራ ሚዲያ (Finote- Amhara ) Midea
Открыть в Telegram
የተመሠረተው የአማራን ሕዝብ ለማንቃት፣ ለማደራጀት እና ለማስተባበር ነው። የአማራ ሕዝብን ✅ ፖለቲካዊ ✅ ማህበራዊ ✅ ኢኮኖሚያዊ ታሪካዊ ጥያቄዎችን ለማሰማት እና የአማራን ሕዝብ በማንቃት ሰፊውን ሕዝብ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ይሰራል። ወደዱም ጠሉም የኃላ ታሪካችን በእኛ እጅ ይፃፋል። አማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ ( አፋብን)
Больше4 039
Подписчики
+6824 часа
+3957 дней
+1 39230 дней
Архив постов
የአገዛዙን የክፋትና የተንኮል እጆች እየተከታተሉ ለህዝብ ማድረስና እንዲጠነቀቅ ማድረግ ያስፈልጋል!
ፋሽስቱ አገዛዝ ብልፅግና ቆቦ ከተማና አካባቢው ላይ ከነ ጌታቸው ረዳ ታጣቂዎች የተመለመሉ ጥቂት ሃይሎች አስገብቶ ንፁሃን ላይ ጥቃት እንዲፈፅሙ በማድረግ ''ህወሓት አጠቃችሁ'' የሚል ተለምዷዊውን ተራና ርካሽ ፕሮፓጋንዳ ለመስራት ዝግጅት ማድረጋቸውንና ተልዕኮ መውሰዳቸውን ውስጥ አርበኞች መረጃ አድርሰውናል::
ጀምበር የጠለቀችበት ፋሽስቱ የብልፅግና አገዛዝ ለፖለቲካ ትርፍና ለስልጣኑ ሲል ዛሬም እንደ ትላንቱ ንፁሃን አማራዎችን ከማስጨፍጨፍ ወደኋላ አይልምና መላው ህዝባችን አስፈላጊውን ጥንቃቄ ሁሉ እንዲወስድ መልክታችንን እናስተላልፋለን!
መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልውና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል!
ህልዉናችን በተባበረ ክንዳችን!
የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ (አፋብን) ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ
ጥር 21/5/2018 ዓ.ም
74ኛ ክ/ጦር በደፈጣ በግዶ እና መጣያ መገንጠያ ላይ ጠላት ተረፍርፏል ።
➺➺➺➺➺➺➺➺➺➺➺➺➺➺➺➺
ጥር 20/2018 ዓ.ም
መነሻውን ደብረወርቅ እና ፈለገብርሃን አድርጎ መጠያ እንቅስቃሴ ሲያደርግ መረጃው የደረሰው ፋኖ ደያጠባ፣ጎል ውቅማ እና መጠያ መገንጠያ ላይ ደፈጣ በመጣል እልህ አስጨራሽ ውጊያ በማካሄድ 14 ሙት እና ከ11በላይ ጠላት ቁስለኛ በማድረግ አሳፍሮ መመለስ ተችሏል።
ቁስለኞችን ይዞ ወደ ፈለገብርሃን ከተማ በመገዝ ላይ እያለ በቦንብ ጥቃት የተፈፀመ ሲሆን ከ5 በላይ መከላከያ እና ምኒሻ በማቁሰል ምሽታቸውን የሃዘን ካባ በማልበስ በሃፍረት እንዲከናነቡ ማድረግ ተችሏል።
ጥር 21/2018 ዓ.ም
አዲስ ትውልድ፣አዲስ አስተሳሰብ፣አዲስ ተስፋ
የአፋብን የቴዎድሮስ ዕዝ 201ኛ ኮር ህዝብ ግንኘነት
የአፋብን ደቡብ አማራ ቀጠና አሳምነው ዕዝ ዓፄ ዘርዓ ያዕቆብ ፩ ኮር ናደው ክፍለ ጦር ህዝባዊ ውይይት መድረክ አደረገ!!
የአፋብን ደቡብ አማራ ቀጣና አሳምነው ዕዝ፣ አፄ ዘርያዕቆብ ፩ ኮር ናደው ክፍለ ጦር በሚያስተዳድሯቸው ቀጣናዎች ሰፊ ህዝባዊ ውይይት እያደረገ ይገኛል። በመሆኑም በአፋብን ደቡብ አማራ ቀጠና አሳምነው ዕዝ ሥር የሚገኙ ከፍተኛ የዕዝ የኮር እና የክፍለ ጦር አመራሮች በተገኙበት ከሞረትና ጅሩ ወረዳ ላም ዋሻ ቀበሌ ህዝብ ጋር ሰፊ ውይይት ተደርጓል።
በውይይቱም በተለያዩ ወቅታዊ ጉዳዮችና ለትግሉ ጠቃሚ በሆኑ አጀንዳዎች ላይ ያተኮረ ጥልቅ ምክክር የተደረገበት መድረክ ነበር። በተለይም የአማራ ህዝብ ሲናፍቀው የነበረውና አንድ ሁኑልኝ በማለት ሲያደርገው የነበረው ግፊት እውን መሆኑ የተበሰረበት መድረክ ሆኗል። የጋራ ጠላትን ለመመከት የሚያስችል አማራዊ የአንድነት ድርጅት መፈጠሩን ተከትሎ፣ የህዝቡን ደስታና ድጋፍ ተሳታፊዎቹ በተለያዩ ሃሳቦች ገልጸዋል።
ህዝቡም እንኳን አንድ ሆናችሁልን፤ ከአሁን በኋላ በሙሉ ልብና በ24 ሰዓት ከጎናችሁ ተሰልፈን ይህንን ቅዱስ ትግል ከዳር ለማድረስ እንሰራለን በማለት ደስታቸውንገልፀውልናል። በመጨረሻም በመድረኩ የፋኖ አሁናዊ የወታደራዊ አቋም ባለፈ፣ በህዝብና በአመራሩ መካከል የነበረውን የመተማመን ድልድይ ይበልጥ ያጠናከረ ነው። ድላችን በተባበረ ክንዳችን የሚበሰርበት በተግባር ደግሞ የሚፈታበት የመጀመሪያው ምዕራፍ የሚሆንበት ቀን ቅርብ ነው።
መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልውና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል!!,ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን
የአፋብን ደቡብ አማራ ቀጣና አሳምነው ዕዝ አፄ ዘርያዕቆብ ፩ ኮር ህዝብ ግንኙነት ኃላፊ
አርበኛ አማረ ታዘዘ
ጥረ 21/05/2018 ዓ.ም
የወረዳውን ዋና አስተዳዳሪን ጨምሮ የመከላከያ ከፍተኛ አመራሮች እርምጃ ተወሰደባቸው!
ጥር:-21/2018 ዓ/ም
በሰሜን ወሎ አስተዳደር ዞን ስር የላስታ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ የሆኑት ኢንጅነር ለዓለም ብርሐኑ እና ላሊበላ ከተማ ሰፍሮ የሚገኘው የብልፅግና ፓርቲ ተላላኪ የመከላከያ ሰራዊት ከፍተኛ አመራሮች ሆቴል አዘግተው አስረሽ ምችው በሚሉበት ጊዜ ላሊበላ ከተማ ላይ ሰርገው በገቡ ባልታወቁ ኃይሎች በደረሰባቸው የእጅ ቦምብ ጥቃት ከፍተኛ አመራሮቹ ከፍተኛ ጉዳት አስተናግደዋል።
ጉዳቱ የደረሰው ጥር 20/2018 ዓ/ም ከምሽቱ 4:30 ገደማ ላሊበላ ከተማ ለውዝ መገንጠያ ሀብትዬ መዝናኛ ካፌ ሲሆን በደረሰባቸው የእጅ ቦምብ ጥቃት አንድ ከፍተኛ የመከላከያ አመራር ወዲያውኑ ህይወቱ ሲያልፍ ተጨማሪ ሰባት የመከላከያ አመራሮችና አባላት ከባድ አካላዊ ጉዳት አስተናግደዋል።
የላስታ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ የሆኑት ኢንጅነር ለዓለም ብርሐኑም የጉዳቱ ሰለባ ሲሆኑ ጉዳቱ እንደደረሰ ወዲያውኑ ወደ ቅዱስ ላሊበላ ሆስፒታል የተወሰዱ ሲሆን የመተንፈሻ ሳንባቸው በከፍተኛ ሁኔታ እንደተጎዳና ሰው ሰራሽ መተንፈሻ ተሰርቶላቸው እንዳሉ፣ጀርባቸው በከፍተኛ ሁኔታ እንደደቀቀና ራሳቸውን ስተው ኮማ ውስጥ እንዳሉ አሁንም በሞትና በህይወት አፋፍ ላይ እንደሚገኙ በውስጥ መረጃዎቻችን በኩል ተረጋግጧል።
መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልውና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል ሲል የላስታ ጄኔራል አሳምነው ፅጌ ኮር ህዝብ ግንኙነት ኃላፊ ፋኖ መምህር ቢሆነኝ ቢያበይን መረጃውን አድርሷል!
ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን!!!
የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ (አፋብን)
ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ
ጥር:-21/2018 ዓ/ም
ቤተ-ክርስቲያን አገልጋዩ የሐይማኖት አባት በብልፅግና ሰራዊት በግፍ ተረሸኑ!
ጥር:-21/2018 ዓ/ም
በሰሜን ወሎ አስተዳደር ዞን ቡግና ወረዳ 09 ጉልሐ ቀበሌ ነዋሪ እና የጀርጀንቦይ መድሐኒአለም ቤተ-ክርስቲያን አገልጋይ የሆኑት የ58 አመት ዕድሜ ያላቸው መርጌታ ጌጡ በላይ የብልፅግና አገልጋይ በሆኑት መከላከያ ሰራዊት አባላት ጥር 20/2018 ዓ/ም ከቀኑ 11:00 ሰዓት ገደማ በግፍ ተረሽነዋል።
የቤተ-ክርስቲያኑ አገልጋይ አባት መርጌታ ጌጡ በላይ አይና እየሱስ ከተማ እህል በወፍጮ አስፈጭተው በመመለስ ላይ እንዳሉ እየሱስ ቤተ-ክርስቲያን ጫካ ውስጥ አራት ጥይት አከታትለው በመተኮስ እንደረሸኗቸው ታውቋል።
የተረሸኑበት ምክኒያትም ሰሞኑን ከፋኖ ኃይሎች ጋር አስታርቁን በሚል ሽፋን ከተመለመሉት የሐይማኖት አባቶች አንዱ ሲሆኑ ራሳችሁ ባጠፋችሁት ጥፋት፣መነኩሴን ለሚደፍር፣የቆሎ ተማሪን ለሚረሽን፣ቤተ-ክርስቲያንን ለሚያረክስ ስርዓት አልላክም በማለታቸው በቡግና ወረዳ ብልፅግና አመራሮች ሴራ ጠንሳሽነትና አስተባባሪነት በብርሃኑ ጁላ ሰራዊት ትዕዛዝ ፈፃሚነት የሐይማኖት አባቱ እንደተረሸኑ የውስጥ የመረጃ ምንጮቻችን አረጋግጠዋል።
መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልውና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል ሲል የላስታ ጄኔራል አሳምነው ፅጌ ኮር ህዝብ ግንኙነት ኃላፊ ፋኖ መምህር ቢሆነኝ ቢያበይን መረጃውን አድርሷል!
ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን!!!
የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ (አፋብን)
ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ
ጀግኖች ለአላማቸው ይሰዋሉ! ትግላቸውና አላማቸው ይቀጥላል!
ጥር 20/2018 ዓ/ም ጀግናው መኩሪያ ፈንቴ ለአላማውና የህልውና አደጋ ላይ ላለው ህዝቡ አንድያ ህይወቱን ለግሷል!
አርበኛ መኩሪያ ፈንቴ የመጀመሪያ ዲግሪውን በመቀሌ ዩኒቨርስቲ የተመረቀ ሲሆን፤ሁለተኛ ድግሪውን በወልድያ ዩኒቨርስቲ ተመርቋል:: በ2013 ዓ/ም የአማራ ፋኖ ንቅናቄንና ምስረታዎችን በመቀላቀል የአርበኝነቱን ህይዎት ያኔ ጀመረ። የአርበኝነት ጅማሮው ከአምስት አመታቶች በላይ በጫካና በዱር ያሳለፈ በፅናትና በታማኝነት ለአማራ ህዝብ የቆመ ነበር።
አርበኛ መኩሪያ የደጋው መብረቅ ኮር ህዝብ አደረጃጀት መምሪያ እና በሚኒሊክ ዕዝ ማህበራዊ ዘርፍ ም/ሃላፊ ነበር። አርበኛው ከአዋጊነት እስከ ተዋጊነት የተዋጣለት መሪም ነበር። ጥር 20/2018 ዓ/ም ከማለዳው12:00 ሰዓት እስከ ቀኑ 7:00 ሰዓት በዘለቀው አውደ ውጊያ በርካታ የፋሽስቱን ሰራዊት ዶግ አመድ በማድረግ፤በርካታዎችን ምርኮኛና ቁስለኛም በማድረግ ጀግናው ፊት ለፊት ከጥላት ጋር አንገት ለአገት ተናንቆ በጀግንነት ተሰውቷል።
አርበኛ መኩሪያ ፈንቴ ከአማራ ህዝብ በፊት እኔ እሞታለሁ ብሎ ደረቱን ለጥላት የሰጠ የቁርጥ ቀን አርበኛ ነበር። ቀኝአዝማች ተበጀ ወርቁ ክፍለ ጦርን ከጓዶቹ ጋር በመመስረትና ለአማራ ህዝብ የነፃነት ሀይል አድርጎ በመገባት ትልቅ ሚና ነበረው። አርበኛው አንድያ ህይዎቱን ለአማራ ህዝብ በአውደ ውጊያ ሜዳ ላይ የሰጠ ሲሆን የአርበኞች መሰዋዕትነት የአማራ ፋኖ ትግል መራር ዋጋ የሚከፈልበት ህያው ዋጋ መሆኑ ሲሆን ለዚህ ትልቅ የታሪክ ህያው ምስክር ሆኖ አርበኛ መኩሪያ ፈንቴ ለአላማውና ለህዝቡ ተሰውቷል።
#ኑረን ለምናገለግለው ሞተን ለምናሻግረው ህዝባችን ምንስ የማንሆንለት ይኖራልና!
መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልውና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል!
ህልዉናችን በተባበረ ክንዳችን!
የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ (አፋብን) ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ!
ጥር 21/5/2018 ዓ.ም
+1
ምስራቅ በለሳ በበላይ ዘለቀ ዕዝ ቁጥጥር ስር ገብታለች!
ምስራቅ በለሳ!✊
ምስራቅ በለሳ ላይ የነበረው የጠላት ኃይል ሙሉ ለሙሉ ለቆ በመውጣቱ አፋብን ቀጠናውን ገቢ አርጓል።
አርበኛ አታለል ሰጠኝ እና አርበኛ ብርሀኑ ነጋ ምስራቅ በለሳ ወረዳ አስተዳደር ፅ/ቤትን ያለምንም የተኩስ ልውውጥ ተቆጣጥረዋል። የአንድነት ዋጋው ይህ ነው። ከዚህ በኋላ የአማራ አንገቱ አንድ ነው። አናጥለህ የምታጠቃው አማራ የለም።
ድል ለአማራ ፋኖ !✊
ለአማራ ክልል መንግሥት የቀረበው ግልፅ ምርጫ
ፋኖን እየወጋህ ትቀጥላለህ ወይስ አፍጥጦ ከመጣው የድሮ አለቃህ ጋር ትዋጋለህ?
የእኛ እምነት የወረሙማው አገዛዝ እስካለ ድረስ ራያ፣ ወልቃይት ፣ መተከል...የአማራ ሊሆኑ ይቅርና አዲስ አበባ ለመግባትም የከፋ ፈተናና መከራ ሆኖ ይቀጥላል። ባህርዳር ወይም ጎንደር የሚኖርን አማራ መስበራቸውን በአደባባይ መለፈፍ ምኞታቸው፣ ወሎ (ቤተአማራን) መጠቅለል ያልሞተ ቅዥታቸው ሆኖም ይቀጥላል። የሆነው ሆነና ለእኛ አንድና ግልፅ አማራጭ ይታየናል።
የክልሉ መንግሥት ፋኖን ለመውጋት በተለያዩ ጊዜያት ያሰለጠናቸውን "አድማ መከላከል" ሲል የሚጠራቸውን ኃይሎች ከሚሊሽያው ጋር በማቀናጀት፣ ከተለያዩ ቦታዎች ሰባስቦ "ዕርስት መከላከል" ሲል ያዝምታቸው። ፋኖዎቻችንም ይህ ኃይል ወደ ወልቃይትና ራያ በሚያመራበት ወቅት ምንም አይነት ውጊያ ባለመክፈት ትብብር ማሳየት። እዚህ ጋር ለክልሉ አገዛዝ የቀረበው ግልፅ ምርጫ "የአማራን ፋኖ እየወጋህ ትቀጥላለህ? ወይስ ታሪካዊ ጠላቴ ከምትለው ትህነግ ጋር ትዋጋለህ?" የሚል ነው።
የአማራ ህዝብ የታሪካዊ ዕርስቶች እና ሌሎች ህልውናና በዘለቄታው የሚያረጋግጡ ጥያቄዎች የሚመለሱት፣ በኦህዴድ አገዛዝ መገርሰስ ላይ የተመሰረተ ነው" ብለው የሚያምኑት ሌሎች ኃይሎች ደግሞ የእራሳቸውን አማራጭ ይዘው ይቀጥላሉ።
የአማራ ህዝብ ማወቅ ያለበት ራያ አካባቢ ያለው ነባራዊ ሁኔታና እውነታ!
አላማጣ ከተማ ራያ አላማጣ እና ኮረም ዙሪያ የነበረው የፋሽስቱ አገዛዝ ብልፅግና መከላከያ ሰራዊት እና ፌደራል ፖሊስ ያለ ምንም የጥይት ተኩስ ጥር 21/2018 ዓ.ም አካባቢውን ለቆ ወጥቷል::
ፋሽስቱ የብልፅግና አገዛዝ ሚያዚያ 2016 ዓ.ም ራያ ላይ የነበረውን መዋቅር በሴራ አፍርሶ አካባቢውን አሳልፎ በመስጠት በኋላም የተወሰነ ሃይሉን የተለያዩ ቦታዎች ላይ በማስፈር አካባቢውን ከትግራይ ሃይሎች ጋር ይዞ መቆየቱ የሚታወቅ ነው::
ፋሽስቱ አገዛዝ ብልፅግና በተጠቀሱት የራያ አካባቢዎች ከሚያዚያ 2016 ዓ.ም ጀምሮ ከትግራይ ሃይሎች ጋር በጋራ ሰፍሮ ይኖር የነበረውን ሰራዊቱን ጥር 21/2018 ዓ.ም ያለ ምንም የጥይት ተኩስ ለቆ እንዲወጣ አድርጎ ቦታውን ሙሉ ለሙሉ ለትግራይ ሃይሎች አስረክቧል::
ከዚህ ጋር ተያይዞም አገዛዙ በዚህ መንገድ ለቆና አስረክቦ የወጣውን የራያ አካባቢዎች የሃሰት ፕሮፓጋንዳና ሴራ ሊሰራበት እንደተዘጋጀ መረጃው አለን:: ይህንን ካሁን በፊት እንዳደረገውና አሁንም እንደሚያደርግ ግን ለህዝብ የተደበቀ አይደለም::
ብልፅግና ይዞት የነበረውን የራያ መሬት በዚህ መንገድ ያስረከበ መሆኑ እየታወቀ ነገር ግን በክልሉ በሁሉም አካባቢዎች ህዝብ ላይ የተለመደ ፀረ ፋኖ የውሸት ፕሮፓጋንዳውን በመስራትና አዲስ የውጊያ አጀንዳ በመፍጠር ብሎም በፀረ-ህዝብና አገር አፍራሽ ሚዲያዎቹ በማስተጋባት ለአማራው ከእልቂት በስተቀር አንዳች መፍትሄ ወደሌለው ጦርነት በማስገባት እድሜውን ለማራዘም እየሰራ ይገኛል::
ከዚህ ጋር ተያይዞም ከደቡብ ወሎ ዞን የተለያዩ ወረዳዎች በሚሊሻ ስም የሰበሰበውን የአማራ ገበሬ እና አድማ ብተና ቀድሞ ወልድያ እና ራያ ቆቦ ዙሪያ ያሰፈረ ሲሆን ከሰሜን ወሎ ሚሊሻ ጋር በማድረግ በቀጣይ ከትግራይ ሃይሎች ጋር ሊያደርገው ባሰበው ጦርነት ከፊት ሊማግዳቸው ዝግጅቱን ጨርሷል::
*ማስታወሻ፦ አገዛዙ ባሁኑ ሰዓት ሰሜን ወሎ ዞን ባሉ ወረዳዎች የግል ታጣቂዎችን ሳይቀር ለጥር 22/2018 ዓ.ም አስቸኳይ ስብሰባ እየጠራ ይገኛል::
እየሆነ ያለው እውነታ ይሄው ነው::
ጥር 21/2018 ዓ.ም
👉 ከታች ባለው የቴሌግራም ሊንክ ቶሎ ቀጥታውን ከግንባር መረጃዎችን እንዲደርሳችሁ ጆይን በማድርግ ይወዳጁን።
https://www.facebook.com/profile.php?id=61586538705973
https://t.me/httpsuYkZrGfSZrNjNjFk
የአማራ ህዝብ ማወቅ ያለበት ራያ አካባቢ ያለው ነባራዊ ሁኔታና እውነታ!
አላማጣ ከተማ ራያ አላማጣ እና ኮረም ዙሪያ የነበረው የፋሽስቱ አገዛዝ ብልፅግና መከላከያ ሰራዊት እና ፌደራል ፖሊስ ያለ ምንም የጥይት ተኩስ ጥር 21/2018 ዓ.ም አካባቢውን ለቆ ወጥቷል::
ፋሽስቱ የብልፅግና አገዛዝ ሚያዚያ 2016 ዓ.ም ራያ ላይ የነበረውን መዋቅር በሴራ አፍርሶ አካባቢውን አሳልፎ በመስጠት በኋላም የተወሰነ ሃይሉን የተለያዩ ቦታዎች ላይ በማስፈር አካባቢውን ከትግራይ ሃይሎች ጋር ይዞ መቆየቱ የሚታወቅ ነው::
ፋሽስቱ አገዛዝ ብልፅግና በተጠቀሱት የራያ አካባቢዎች ከሚያዚያ 2016 ዓ.ም ጀምሮ ከትግራይ ሃይሎች ጋር በጋራ ሰፍሮ ይኖር የነበረውን ሰራዊቱን ጥር 21/2018 ዓ.ም ያለ ምንም የጥይት ተኩስ ለቆ እንዲወጣ አድርጎ ቦታውን ሙሉ ለሙሉ ለትግራይ ሃይሎች አስረክቧል::
ከዚህ ጋር ተያይዞም አገዛዙ በዚህ መንገድ ለቆና አስረክቦ የወጣውን የራያ አካባቢዎች የሃሰት ፕሮፓጋንዳና ሴራ ሊሰራበት እንደተዘጋጀ መረጃው አለን:: ይህንን ካሁን በፊት እንዳደረገውና አሁንም እንደሚያደርግ ግን ለህዝብ የተደበቀ አይደለም::
ብልፅግና ይዞት የነበረውን የራያ መሬት በዚህ መንገድ ያስረከበ መሆኑ እየታወቀ ነገር ግን በክልሉ በሁሉም አካባቢዎች ህዝብ ላይ የተለመደ ፀረ ፋኖ የውሸት ፕሮፓጋንዳውን በመስራትና አዲስ የውጊያ አጀንዳ በመፍጠር ብሎም በፀረ-ህዝብና አገር አፍራሽ ሚዲያዎቹ በማስተጋባት ለአማራው ከእልቂት በስተቀር አንዳች መፍትሄ ወደሌለው ጦርነት በማስገባት እድሜውን ለማራዘም እየሰራ ይገኛል::
ከዚህ ጋር ተያይዞም ከደቡብ ወሎ ዞን የተለያዩ ወረዳዎች በሚሊሻ ስም የሰበሰበውን የአማራ ገበሬ እና አድማ ብተና ቀድሞ ወልድያ እና ራያ ቆቦ ዙሪያ ያሰፈረ ሲሆን ከሰሜን ወሎ ሚሊሻ ጋር በማድረግ በቀጣይ ከትግራይ ሃይሎች ጋር ሊያደርገው ባሰበው ጦርነት ከፊት ሊማግዳቸው ዝግጅቱን ጨርሷል::
*ማስታወሻ፦ አገዛዙ ባሁኑ ሰዓት ሰሜን ወሎ ዞን ባሉ ወረዳዎች የግል ታጣቂዎችን ሳይቀር ለጥር 22/2018 ዓ.ም አስቸኳይ ስብሰባ እየጠራ ይገኛል::
እየሆነ ያለው እውነታ ይሄው ነው::
ጥር 21/2018 ዓ.ም
ትኩረታችን ዋናው ጠላታችን ላይ ብቻ ይሁን!!
ዘላለማዊ ባርነትን በመለማመድ የህዝባችንን እጣ ፋንታ ለከፍተኛ ብሔራዊ የህልውና አደጋ የዳረገን የባንዳ ምልክቱ የአማራ ብልፅግና ዛሬም እንደ ወትሮው አድስ ማደናገሪያ ይዞ መጥቷል!!
የህልውና ትግላችን ዋና አጀንዳ የአማራን ህዝብ ህልውና ማረጋገጥ እንጅ በየሰፈሩ ሃይል ለመበተንና ከወጣንበት ዓላማ በተፃረረ ሁናቴ ህዝብን እያደናገሩ የአማራ ክልልን የቀውስ ቀጠና ማድረግ ተቀባይነት የለውም!!
አስከፊውን ፀረ -ህዝብ አገዛዝ በማስወገድ አድስ ስርዓት ለማንበር የጀመርነው ትግል ጠልፎ ለመጣል የሚደረገው ያልተገባ ትርክት መፍጠር ይበቃል!!
ዋናው ጠላታችን እያደረገ ያለውን አማራን ከፋፍሎ እና አደናግሮ የአማራ ፋኖ ትግልን መጥለፍ አይቻልም!!
አፋብን የሚመራበት የፓለቲካ ፕሮግራም እና የትግል መስመር የብልፅግናውን አገዛዝ በመገርሰስ በምትኩ አድስ ስርዓት ለመትከል እንጅ በየሰፈሩ እና በየግዛቱ ጠላት በሚሰራቸው አሉታዊ ፕሮፖጋንዳ የሚቀለበስ ትግል የለንም!!
ስለሆነም ድርጅታችን አፋብን ትኩረቱን ወደ ደቡብ ግንባር በማድረግ የአገዛዙን እስትንፋስ ለመቁረጥ የጀመረውን ዘመቻ አጠናክሮ ይቀጥላል!!
ከዚህ ባለፈ የቀጠናው ቀውስ ጠማቂ የአብይ አህመድ መንግስት ከሰሜን ሃይሎች ጋር የጀመረውን አድስ ውጊያ ምክንያት በማድረግ የአማራን ህዝብ እያደናገሩ መቀጠል ጊዜው አልፏል!!
የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ እንደ ድርጅት ሁለንተናዊ ትኩረቱን የጠላት ዋና የስበት ማዕከል የሆነውን የደቡብ ግንባር ዘመቻ አጠናክሮ በመቀጠል ፀረ ህዝብ አገዛዙን ላይመለስ መቅበር እንጅ በሀሰት ትርክት እና በጥቂት ጥቁር አማራዎች ተሳትፎ የሚመለስም የሚቀለበስም የህዝብ ትግል የለም!!
ግፋ በለው!!
ዝንታለም አማራ
ወይራው አማራ
ከሳንጃ ውግ እስከ ክላሽ ጨበጣ ውጊያና ቦምብ ውርወራ የደረሰው ከባዱ ትንቅንቅና የተሰበረው የጠላት ምሽግ‼️
በምስራቅ ዐምሓራ ቀጠና በተሁለ ድሬ ወረዳ ከሐይቅ ከተማ በቅርብ ርቀት ልዩ ስሙ ቆሎ ባቄላ ተብሎ በሚጠራው አከባቢ ላይ የሚገኘውና ከቦታ አቀማመጡ ጋር ተዳምሮ በመዘመናዊ መንገድ ተሰርቶ የነበረው የአገዛዙ ወታደራዊ ምሽግ በፋኖ ቦምብ ድርምስምሱ ወጥቷል።
በምሽጉ ውስጥ የነበሩ በርካታ ወታደሮች የእሳት እራት ሆነው ሲቀሩ፡ ሕይወታቸውን ለማትረፍ ሲሸሹ የነበሩ ቁጥራቸው በውል ያልታወቀ በርካቶች ደግሞ ገደል ገብተው አልቀዋል።
በአማራ ፋኖ ብሄራዊ ንቅናቄ ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒሊክ ዕዝ ልጅ እያሱ ኮር 24ኛ ክ/ጦር ጥር 19 ለጥር 20/2018 ዓ/ም አጥቢያ ሌሊት በፈፀሙት ታአምራዊ ኦፕሬሽን የጠላትን አከርካሪ በመስበር ታላቅ ድል መጎናፀፋቸውን የመረብ ሚዲያ የምስራቅ ዐምሓራ ቀጠና ዘጋቢዎች ለማረጋገጥ ችለዋል።
በደቡብ ወሎ ዞን ተሁለደሬ ወረዳ ልዩ ቦታው ቆሎ ባቄላ ተብሎ በሚጠራው ቦታ በነበረው የአገዛዙ ወታደሮች ምሽግ ላይ ነው መብረቃዊው እርምጃ የተወሰደው።
ከቦታው መልካአ ምድራዊ አቀማመጥ ጋር ተዳምሮ በመዘመናዊ መንገድ ተሰርቶ የነበረው የአገዛዙ ወታደሮች የኮንክሪት ምሽግ ነው "ተናዳፊዎቹ" በሚል ቅፅል ስም የሚጠሩት በልጅ እያሱ ኮር ስር የ24 ክ/ጦር ፋኖዎች ትናንት አጥቢያ ለሊቱን የጥቃት ዶፍ አውርደውበት ድርምስምሱን ያወጡት።
የፋኖ አባላቱ የጥይት ካዝናቸውን እንዳነገቡና የብሬን ሸንሼናቸውን ልክ እንደመቀነት በወገባችው ደግድገው በደረታቸው እየተሳቡ በጠላት ምግሽ ተወርውረው በመግባት በቅድሚያ የምሽጉ ዋርድያዎችን በድምፅ አልባው ሳንጃ ካጋደሙ በኋላ በምሽጉ ውስጥ የነበሩ ወታደሮችን ጭዳ እንዳደረጓቸው የመረብ ሚዲያ የቀጠናው ዘጋቢ ጋዜጠኞች አረጋግጠዋል።
የሳንጃ ትንቅንቅን ጨምሮ የክላሽ ጨበጣ ውጊያው የተካሄደው በድቅድቅ ጨለማ በመሆኑ የተገደሉ የአገዛዙ ወታደሮች ቁጥር በውል ባይታወቅም ነገር ግን በርካቶች የአፈር ሲሳይ ሆነው ቀርተዋል።
በዚህ መብረቃዊ ኦፕሬሽን ከፋኖ ሳንጃና አፈሙዝ ለማምለጥ ሲሸሹ የነበሩ ቁጥራቸው በውል ያልታወቀ በርካቶች ደግሞ ገደል ገብተው መሞታቸው ነው የታወቀው።
የፋኖ አባላቱ፡ ጠላት አይደፈሬ በሚል ሲመካበት የነበረውን ምሽግ ሰዓታትን ባልፈጀ ውጊያ ድርምስምሱን በማውጣት በርካታ ወታደሮችን ከደመሰሱ በኋላ 15 ክላሽንኮቭ መሣሪያዎችን ከነ ተተኳሾቻቸው እንዲሁም ሌሎች ለትግሉ አስፈላጊ የሆኑ ወታደራዊ ግብአቶችን ከበርካታ ወታደሮች ጋር ማርከው በድል ታጅበው ቀጠናውን ለቀው መውጣታቸውን ነው ጣቢያችን መረብ ሚዲያ ለማረጋገጥ የቻለው።
ከሐይቅ ከተማ በውስን ኪሎሜትሮች እርቀት ቆሎ ባቄላ አከባቢ በነበረው ምሽግ ላይ ከእኩለ ለሊት ጀምሮ በፋኖ የተከፈተውን ጥብቅ እርምጃ የሰሙ በሐይቅ ከተማ የነበሩ የአገዛዙ ምንጣፍ ጎታች ካድሬዎች አንዳንዶች የለሊት ፒጃማ እንደለበሱ፡ አንዳንዶች ደግሞ በቁምጣና ፓንት ብቻ ሆነው በደረቅ ለሊት ወደ ደሴ ከተማ መሸሻቸው ነው የተነገረው።
በከተማዋ መኃል ሸሙሳ ተብሎ በሚጠራው ተራራማ ስፍራ ላይ ሰፍሮ የሚገኘው ቀሪው የአገዛዙ ኃይል፡ ባጠመደው ከባድ መሣሪያ ቆሎ ባቄላ ለነበሩ ጓዶቹ ሽፋን ሲሰጥ ያደረ ቢሆንም፡ ነገር ግን የአንድ ወታደርን ሕይወት ሳይታደግ "የአህያ ባል ከጅብ አያስጥልም" ሆኖ ቀርቷል።
21/ዐ5/2018 ዓ.ም
