Ethiopian Higher Education Institutions Muslim Students' Union
Открыть в Telegram
This is the official Channel of Ethiopian Higher Education Institutions Muslim Students' Union.
Больше4 434
Подписчики
-424 часа
-167 дней
-9130 дней
Архив постов
አንዱ የሌላውን መብት ማክበሩ ግዴታው ነው!
@EHEMSU
+1
ከኦዳ ቡልቱም ጀመዓዎች ትንሽ ብንማር!
ባለፈው አመት ሚያዚያ ወር ላይ ነበር አብርሐም የተባለ የሪሜዲያል ተማሪ በቲክቶክ ብቅ ብሎ የቁርዓን ክብርን የሚነካ ለ4 ደቂቃ የዘለቀ ንግግር ያደረገው:: ሆኖም በመቅፀብት ጀመዓው በግቢም በከተማም ባሉ ተቋማት ዘንድ ከሰሰ:: ክሱንም ሳይሰለቹ ተከታተሉ:: በመጨረሻም ተማሪው በፖሊስ ቁጥጥር ስር ውሎ ለ2 አመታት ያክል ከትምህርት እንዲታገድ ሆነ::
አሁንስ የነቢ ክብርን ለማስመለስ እኔ ብሎ ሀላፊነት የሚወስደውና መሬት ላይ ያለውን ትግል የሚመራው ማን ነው?
@MohammadamminKassaw
+1
በ1998 ዓ.ል በአዲስ አበባ: ከሚሴ እና ሐዋሳ የነቢ ክብርን ለመንካት የሞከሩ አካላትንና የቁርዓን ክብርን የተዳፈሩ አካላትን አስመልክቶ በወቅቱ የነበሩ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ሙስሊም ተማሪዎች ጥያቄያቸውን ለጠቅላይ ሚኒስቴር መለስ ዜናዊ ያደረሱበት ደብዳቤ ነው::
አሁንስ የነቢን ክብር መነካት አስመልክቶ የሙስሊሙ መሪ ተቋም የሙስሊሙን ጥያቄ ለማን አቀረበ?!
@MohammadamminKassaw
"ኒቃብ መልበሴ አጠነከረኝ እንጅ አዕምሮዬን አልሸፈነውም!" - የዋንጫ ባለቤቷ ዚክራ ሰዒድ
ከወሎ ዩኒቨርሲቲ በ2 ዋንጫ እና የወርቅ ሜዳሌያ የተመረቀችው ታታሪዋ ዚክራ ሰዒድ ከሐሩን ሚዲያ ጋር በነበራት ቆይታ "ኒቃብ መልበሴ ለትምህርት አግዞኛል እንጅ አዕምሮዬን አልሸፈነውም!" ብላለች::
📌ሙሉ ፕሮግራሙ በሀሩን ሚዲያ ልዩ ዝግጅት በኢፍጣር ሰዓት ይለቀቃል!
+9
"በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የራስ ገዝነት ጉዞ ዙሪያ ጥያቄ አለዎት?" በሚል መነሻ የማህበረሰቡን ቅሬታ ለዩኒቨርሲቲው ለማድረስ ሐሳብ እያሰባሰበ መሆኑን የገለፀው ቲክቫህ Magazine ካወጣው ማስታዎቂያ ቡሃላ ህብረታችንን ጨምሮ ብዙ ሙስሊም ተማሪዎች እና የሰብዓዊ መብት ተቆርቋርዎች ዩኒቨርሲቲው ባወጣው ጨቋኝ መመሪያ ዙሪያ ቅሬታቸውን ልከዋል::
•••••••••••••••••••••••••••••••••••••••
እንደሚታወቀው አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ከሕግም ከሞራልም ውጭ ሆኖ ኒቃብ እና የጀመዓ ሶላትን የሚከለክል መመሪያ አውጥቷል!
••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••
ለምን እንዳወጣ ጥያቄ አለንና ጥያቄያችንን ሁላችሁም ልታቀርቡ ይገባል:: የጥያቄ ሳምፕል ከላይ ተያይዟል:: ጥያቄዎችን ለማቅረብ @tikvahmagbot ይጠቀሙ።
የላካችሁበትን Screenshot አድርጉና @Aaumuslimstudentsunion1 ላኩልን::
መብት በትግል እንጅ በልመና አይገኝም!
ነፃነት በነፃ አይገኝም!
የሙስሊም ተማሪዎች የመብት ጥያቄ የዚህ ትውልድ አደራ ነው!
@aaumsu
የሙስሊም ተማሪዎች የመብት ጥያቄዎች በዚህ ትውልድ ሊቋጩ የሚገቡ የትላንት አደራዎች ናቸው!
https://t.me/EHEMSU
Breaking!
የአርባምንጭ ዩኒቨርሲቲ ሙስሊም ተማሪዎች ህብረት ተመሰረተ!
•••••••••••••••••••••••••••••••••••••
አርባምንጭ:- ረመዳን 9/9/1446
•••••••••••••••••••••••••••••••••••••
በአርባንጭ ዩኒቨርሲቲ የሚገኙ የካምፓስ አሚሮች አባያ በሚገኘው መስጂደልአንሷር ባደረጉት ጥልቅ ውይይት የአርባምንጭ ዩኒቨርሲቲ ሙስሊም ተማሪዎች ህብረትን መስርተዋል:: ህብረቱ ሲመሰረት የMain campus: ኩልፎ ካምፓስ: ነጭ ሳር ካምፓስ: አባያ ካምፓስ እና ጫሞ ካምፓስ አሚሮች የተገኙ ሲሆን የህብረቱን ከፍተኛ አመራሮች መርጠዋል:: በዚህም መሠረት:-
1) ወንድም ኡሳማ አሊ ••• ፕሬዚዳንት (ከMain campus)
2) ነቢል ሙሐመድ ••• ምክትል ፕሬዚዳንት (ከነጭ ሳር ካምፓስ)
3) ኸይሩ ጀማል ••• ፀሐፊ (ከጫሞ ካምፓስ)
ተደርገው ተመርጠዋል:: አላህ ለተማሪው በተሻለ ሁኔታ የሚያገለግሉበትን ብርታት ይሰጣቸው ዘንድ ዱዓችን ነው::
https://t.me/EHEMSU
ጁምዓ ሶላት ሁሉም ሙስሊም በመስጂድ ተገኝቶ ይሰግደው ዘንድ ከአላህ ግዴታ የተደረገ ነው!
https://t.me/EHEMSU
ሶላት መስገድ ከአላህ በኩል የመጣ ግዴታ ነው!
https://t.me/EHEMSU
ኒቃብ መልበስ ከአላህ የመጣ ትዕዛዝ ነው!
https://t.me/EHEMSU
ሐረማያዎች እንዳሉት "ኒቃብ ኢትዮጵያዊ እሴት ነው!"
ሌላ የትግል ፍሬ ••• ከመቱ ዩኒቨርሲቲ ጀመዓዎች!
መቱዎች ከጁምዓ ሶላት ጋር ተያይዞ ከ5:30 እስከ 7:30 በሕግ እንደፀናው ትምህርት እንዳይኖር በተደጋጋሚ ሲጠይቁ እንደነበር ይታወቃል:: በአላህ ፈቃድ ብሎም በተማሪዎች ትግል ከዩኒቨርሲቲው ጋር ስምምነት ተደርሶ ተግባራዊ እንደተደረገ ጀመዓው አሳውቋል::
መብት በትግል እንጅ በልመና አይገኝም!
https://t.me/EHEMSU
ከሐረማያ ጀመዓዎች መግለጫ የተወሰደ:-
"የጅማ ዩኒቨርሲቲ ስልጣናቸውን ተማሪን ለመጨቆን በሚገለገሉ አግላይ አመራሮቹ ላይ ጥብቅ የሆነ እርምጃ በመውሰድ: ሙስሊም ሴት ተማሪዎችን በዚህ የልሕቀት ማዕከል ውስጥ ተካታች በማድረግ: ለሕዝብ የቆመ ተቋም እንደሆነ እንዲያስመሰክር እንጠይቃለን::"
እውነት ነው ••• ጥላቻው በርትቶ በሰከረ ሰዓት ተማሪን በድሎ ሲበርድለት ዝም ሊባል የሚገባ አካል ሊኖር አይገባም::
https://t.me/EHEMSU
ስለ ኒቃቢስቷ ዚክራ ሰዒድ ወርቃማ ስኬት ያልፃፈ የለም!
ኒቃብን በመመሪያ ደረጃ የከለከለው አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የቴሌግራም ቻናል AAU መረጃ እንኳ ስኬቷን ተማሩበት ብሏል::
እናማ:- የቻናሉ ፖስት "ኒቃብ የመማር ማስተማሩን ስርዓት ያስተጓጉላል!" በማለት በመመሪያ የከለከሉት የዩኒቨርሲቲው አመራሮች ያዩት ዘንድ ወደድን::
ጥላቻ ሊጋርደው ያልቻለ ስኬት !
ኡስታዝ አህመዲን አየር መንገዱ ለሚያዘጋጀው የኢፍጣር ፕሮግራም የግብዣ ጥሪ ሲቀርብላቸው እንደሚከተለው መለሱ:-
"እኛ ኢፍጣርም ሆነ ተምር አልቸገረንም። የጠሩኝን ሰዎች የሙስሊም ሴቶችን መብት አክብሩ ያኔ የኢፍጣር ጥሪያችሁ ትርጉም ይኖረዋል በላቸው። የሙስሊም ሠራተኞችን መብት እንዲያከብሩ የቀረበላቸው አቤቱታ ምንም ምላሽ ሳይሰጡ በዝምታ አልፈው ኑና አፍጥሩ ማለት ለኔ አይዋጥልኝ::"
ቆራጥነት እና ተምሳሌትነትን ያቀፈ ጥልቅ መልዕክት አለው!
መዳ ወላቡ ዩኒቨርሲቲ ጀመዓዎች መብታቸውን አስከብረዋል!
ዩኒቨርሲቲው ረመዳንን አስመልክቶ ሾርባ አለማዘጋጀቱን ተከትሎ በባሌ ሮቤ ከተማ ተቃውሞ ያሰሙት የመዳ ወላቡ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ተወካዮች የ ከግቢው አመራሮች ጋር በሙስሊም ተማሪዎች ጥያቄዎች ዙሪያ ለ3 ሰዓታት የዘለቀ ውይይት በዛሬው እለት አድርገው ነበር:: በውይይቱም ጠቅላላ የሆኑ ጥያቄዎች የቀረቡ ሲሆን ከዩኒቨርሲቲው ጋር በስምምነት ጨርሰዋል::
መብት በትግል እንጂ በልመና አይገኝም!
https://t.me/EHEMSU
የሐረማያ ጀመዓዎች ስለኒቃብ የሚከተለውን ብለዋል:-
"ኒቃብ ከአረብ ሀገራት የተወረሰ የተወረሰ ባህል አይደለም: የሐገራችን ግማሽ ማህበረሰብ የሆነው የህዝበ ሙስሊሙ ሃይማኖት አለምአቀፍ እንጅ የአረብ ብቻ አይደለምና:: ኒቃብ የአክራሪነት መገለጫ አይደለም: የመላው ኢትዮጵያዊ ሙስሊም መገለጫ እሴት ፅንፈኝነት አይሆንም::"
እውነት ነው!
https://t.me/EHEMSU
