cookie

Мы используем файлы cookie для улучшения сервиса. Нажав кнопку «Принять все», вы соглашаетесь с использованием cookies.

avatar

Addis Mohammed & Associates Law firm👩‍⚖

ማንኛውም የህግ መረጃዎች እና ጉዳዮች የሚዳሰሱበት፣ ሀገራችን ላይ የሚፈጠሩ አሳዛኝና አስደንጋጭ ወንጀሎችን እንዲሁም ቀላል የሚመስሉ ጉዳዮች ላይ የኢትዮጵያ ህጎች ምን ይላሉ የሚሉትን የምናይበት ቻናል ነው። ማንኛውንም የህግ ጥያቄዎች በዚህ ይመለሳሉ

Больше
Рекламные посты
774
Подписчики
Нет данных24 часа
Нет данных7 дней
+730 дней

Загрузка данных...

Прирост подписчиков

Загрузка данных...

የመኖርያ ቤት ኪራይ ቁጥጥር እና ኣስተዳደር ኣዋጅ ቁ.1320/2016 የተካተቱ ዋና ዋና ነጥቦች እና የአዋጁ አስፈላጊነት በሀገራችን አሁን ባለው ሁኔታ የመኖሪያ ቤት ኪራይ ዋጋ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየናረ እና በዜጎች ኑሮ ላይ ከፍተኛ ጫና እየፈጠረ በመሆኑ፣ የመኖሪያ ቤት አቅርቦት አንገብጋቢ እና መሰረታዊ የመብት ጉዳይ እንደመሆኑ መንግስት የመኖሪያ ቤት አቅርቦትን ለማሟላት እያደረገ ካለው ጥረት ጎን ለጎን እየናረ ያለውን የቤት ኪራይ ዋጋ የማህበረሰቡን አቅም ያገናዘበ እና ተመጣጣኝ እንዲሆን በከተሞች ያለውን የመኖሪያ ቤት ኪራይ ዋጋ ንረት በአግባቡ መቆጣጠርና ማስተዳደር በማስፈለጉ አዋጁን ማውጣት አስፈላጊ ሆኗል። በተጨማሪም የመኖሪያ ቤት ቁጥጥር እና አስተዳደር ግልፅነት፣ ተጠያቂነት ያለው እና የአከራዮችን እና ተከራዮችን ጥቅም እና መሰረታዊ መብቶች ሚዛን በጠበቀ መልኩ ለማስተናገድ የሚያስችል የህግ ማዕቀፍ አስፈላጊ በመሆኑ አዋጁ ወጥቷል። ⭐️ የአዋጁ የተፈፃሚነት ወሰን ይህ አዋጅ ተፈፃሚ የሚሆነው ከአንድ ክፍል ጀምሮ ለመኖሪያ አገልግሎት የተከራየና ገንዘብ የሚከፈልበትን ማንኛውም ቤት ላይ ሲሆን በሆቴል፣ ሪዞርት፣ የእንግዳ ማረፊያ እና ሌሎች በንግድ ፈቃድ መሰረት በሚከራዩ ቤቶች ላይ ተፈፃሚ አይሆንም፡፡ ⭐️ ስለመኖሪያ ቤት ኪራይ ውል ማንኛውም የመኖሪያ ቤት ውል በፅሁፍ የሚደረግ ሆኖ በወረዳ ቤቶች አስተዳደር ፅ/ቤት መረጋገጥ እና መመዝገብ አለበት፡፡ የኪራይ ክፍያውም በባንክ ወይም በሌላ ህጋዊ በሆነ የኤሌክትሮኒክ ዘዴ ብቻ የሚፈፀም ይሆናል። የአከራይ እና ተከራይ ውሉን ከሰኔ 1/2016 ዓ/ም ጀምሮ በአቃቂ ቃሊቲ ክ/ከተማ ሁሉም ወረዳዎች ፅ/ቤቱ የማረጋገጥና የመመዝገብ ስራውን ጀምሯል፡፡ ይህ የመኖሪያ ቤት ኪራይ ውል አከራይና ተከራይ በተፈራረሙ 30 ቀናት ውስጥ የማረጋገጥ እና እንዲመዘገብ የማድረግ ግዴታ አለባቸው። ማንኛውም ያልተረጋገጠ እና ያልተመዘገበ የመኖሪያ ቤት ኪራይ ውል እንዳልተደረገ ይቆጠራል። የማረጋገጥ እና የምዝገባ ግዴታን ያለመወጣት በአከራይ ወይም በተከራይ ላይ በተቆጣጣሪው አካል እስከ ሶስት ወር የሚደርስ በውሉ ላይ የተጠቀሰውን ገንዘብ ያስቀጣል፡፡ ይህ አዋጅ ከመውጣቱ በፊት በፅሁፍ የተደረገ የኪራይ ውል ካልሆነ በስተቀር የመኖሪያ ቤት ኪራይ የውል ዘመን ከሁለት ዓመት ሊያንስ አይችልም። እንዲሁም ማንኛውም የመኖሪያ ቤት ውል ሲገባ አከራይ ከተከራይ ላይ ሊጠይቅ የሚችለው ቅድሚያ ክፍያ ከ2 ወር የቤቱ የኪራይ ዋጋ ሊበልጥ አይችልም። በዚህ የውል ዘመን ውስጥ ተከራይን ከቤት ማስወጣትም ሆነ በአዋጁ ከሚፈቀደው አግባብ ውጭ የቤት ኪራይ ዋጋ መጨመር አይቻልም፡፡ ⭐️የመኖሪያ ቤት ኪራይ ዋጋ የኪራይ ውል ላይ ያለው የቤት ኪራይ ዋጋ የቤቱ የኪራይ ዋጋ እንደሆነ ተደርጎ ይወሰዳል እንጂ አዲስ የሚወጣ የቤት ኪራይ ዋጋ አሁን ላይ የለም። አከራይ ለነባር ተከራይ ወይም ለአዲስ ተከራይ በሚያከራየው የመኖሪያ ቤት ላይ ቀደሞ በነበረው ኪራይ ላይ የኪራይ ዋጋ ጭማሪ ማድረግ የሚችለው የአዲስ አበባ ቤቶች አስተዳደር ቢሮ በአመት አንድ ጊዜ በሰኔ ወር ነባራዊ የኢኮኖሚ ሁኔታ እና ሌሎች አግባብነት ያላቸውን ጉዳዮች ከግምት በማስገባት ሊወስን የሚችለው የመኖሪያ ቤት ኪራይ ጭማሬ መሰረት በማድረግ ብቻ ነው። አዲስ የተገነባ ወይም ለመጀመሪያ ጊዜ ለኪራይ የቀረበ የመኖሪያ ቤት በሚከራይበት ጊዜ የቤቱ የኪራይ ዋጋ በአከራይና በተከራይ ስምምነት የሚወሰን ይሆናል። ነገር ግን አከራይ ቀደም ሲል ሲከራይ የቆየ የመኖሪያ ቤት ወይም ግንባታው ሙሉ በሙሉ የተጠናቀቀ አዲስ ቤት ያለአገልግሎት ከስድስት ወር በላይ እንዲቀመጥ ካደረገ ቤቱ ቢከራይ ሊከፍል ይችል የነበረውን የመኖሪያ ቤት ኪራይ ገቢ ግብር ተሰልቶ እንዲከፍል ይደረጋል፡፡ ⭐️የመኖሪያ ቤት ኪራይ ውል ስለሚቋረጥበት ሁኔታ 1. የመኖሪያ ቤት ኪራይ ውል የኪራይ ዘመኑ ሳይጠናቀቅ በአከራዩና ተከራዩ ስምምነት፣ 2. ተከራይ ቤቱን መልቀቅ ሲፈልግ የሁለት ወር የቅድሚያ ማስታወቂያ በመስጠት 3. የአንድ ቤት ባለቤትነት በውርስ፣ በሽያጭ፣ በዕዳ ወይም በሌላ ማናቸውም ህጋዊ ምክንያት ለሌላ ወገን ከተላለፈ የመኖሪያ ቤት ኪራይ ውሉ ሊቋረጥ የሚችለው ቤቱ ከተላለፈበት ጊዜ ጀምሮ የ6 ወር ማስጠንቀቂያ ለተከራዩ በመስጠት ነው። ⭐️የመኖሪያ ቤት ኪራይ ውል ያለ ማስጠንቀቂያ የሚቋረጥባቸው ሁኔታዎች 1. የቤት ኪራይ በውሉ በተመለከተው የመክፈያ ጊዜ ለመጀመሪያ ጊዜ ከሆነ ከ15 ቀን ካሳለፈ 2. ለሁለተኛ ጊዜ ከሆነ 7 ቀን ካሳለፈ፣ 3. ቤቱን ያለአከራዩ ፈቃድ ከመኖሪያነት ውጪ ወይም ለንግድ ስራ የሚጠቀምበት ከሆነ፣ 4. የአካባቢውን ሰላምና ፀጥታ በተደጋጋሚ የሚያውክ ከሆነ 5. በቤቱ ውስጥ የወንጀል ተግባር የሚፈፅም ወይም ቤቱን ለወንጀል መፈፀሚያነት የሚጠቀምበት ከሆነ፣ 6. አስቦ ወይም በቸልተኝነት በቤቱ ላይ ጉልህ ጉዳት ያደረሰ እንደሆነ ወይም በሌላ ተመሳሳይ ምክንያት ከተፈጠረ ተከራይ የውል ጊዜው ከመጠናቀቁ በፊት ቤቱን እንዲለቅ በህግ ሊገደድ ይችላል። ⭐️በውል ምዝገባ ወቅት ስ ለሚቀርቡ ሰነዶች 1. በህግ አግባብ የተዘጋጀ የመኖሪያ ቤት ኪራይ ውል ሰነድ፤ 2. የአከራይና ተከራይ ማንነታቸውን የሚገልፅ መታወቂያ ወይም ተመጣጣኝ ሰነድ ኦሪጅናልና ኮፒ (የመኖሪያ ቤት ኪራይ ውሉ የሚመዘገበው በወኪል ከሆነ ሕጋዊ ውክልና የሁለት ምስክሮች የታደሰ መታወቂያ ኦሪጅናልና ኮፒ) 3. አከራይ የመኖሪያ ቤቱን ለማከራየት የሚያስችል መብት እንዳለው የሚያሳይ ህጋዊ ሰነድ ኦሪጅናልና ኮፒ ይዞ መቅረብ አለበት፡፡ በማንኛውም ምክንያት የተሻሻለ ውል በ30 ቀናት መመዝገብና መረጋገጥ አለበት፡፡ ⭐️የተከለከሉ ተግባራት እና ጥቆማ የ ሚቀርብባቸው ጉዳዮች 1. የተመዘገበ ውል ሳይኖር የመኖሪያ ቤት ማከራየት፤ 2. የመኖሪያ ቤት ኪራይ ውል ሳያስመዘግቡ መከራየትና ማከራየት ወይም በአዋጁ የተቀመጠው የጊዜ ገደብ አሳልፎ ማስመዝገብ፤ 3. በተመዘገው ውል ላይ ከተቀመጠው የመኖሪያ ቤት ኪራይ ዋጋ በላይ ክፍያ መፈጸም 4. በአዋጁ ከተፈቀደው ውጪ የዋጋ ጭማሪ ማድረግ ወይም ከ2 ወር በላይ የቅድመ ክፍያ እንዲፈጸም ማስገደድ፤      5. በአዋጁ ከተፈቀደው ውጪ የቤት ኪራይ ዘመን ውል ማቋረጥ፤ 6. በአዋጁ ለአከራይ የተሰጠውን ማበረታቻ ያለአግባብ ለመጠቀም ሀሰተኛ መረጃ ወይም ማስረጃ ማቅረብ፤ 7. መኖሪያ ቤቱ ከመኖሪያነት ዓላማ ውጪ አገልግሎት ወይም ለወንጀል መፈጻሚያነት ወይም ለወንጀል ተግባር ላይ እየዋለ ከሆነ፤ 8. አዋጁ ከሚፈቅደው ውጪ የውል ዘመን ሳይጠናቀቅ ከቤት ማስወጣት፤ 9. በአዋጁ የተቀመጠውን የማስታወቂያ ወይም የማስጠንቀቂ ጊዜ ሳይሰጥ ውል ማቋረጥ፤ 10. በባንክ ወይም በሌላ ሕጋዊ የሆነ የኤሌክትሮኒክስ መንገድ የመኖሪያ ቤት ኪራይ ክፍያ አለመፈጸም፤ 11. ቀደም ሲል ሲከራይ የቆየ የመኖሪያ ቤት ወይም ግንባታው ሙሉ ለሙሉ የተጠናቀቀ አዲስ መኖሪያ ቤት ያለአገልግሎት እንዲቀመጥ ማድረግ፣ ⭐️ስለ ቁጥጥር፡ ጽህፈት ቤቱ ቁጥጥር የሚያደርገው ለቁጥጥር በተመደበ ባለሙያ ይሆናል፤ ተቆጣጣሪ ባለሙያው በመንግሥት የሥራ ሰዓት ተቆጣጣሪ መሆኑን የሚገልጽ መታወቂያ በመያዝ የቁጥጥር ተግባሩን ይፈጽማል፤ የቁጥጥር ሥራ የሚከናወነው በተናጠል በአንድ ባለሙያ ሳይሆን በቡድን ከአንድ በላይ ተቆጣጣሪዎች በመሆን ነው፡፡
Показать все...
👍 3 1
#ህግን_በአዲስ_እይታ  ወንጀል ምንድን ነው ? ክፍል ሁለት ጠበቃ አዲስ መሀመድ ከ ኢዘዲን ፈድሉ  ጋር ግሩም ቆይታ አድርገዋል እነሆ ክፍል አንድን ከላይ ያለውን ማስፈንጠሪያ በመጫን ይመልከቱ በወንጀል ዙሪያ ያለዎትን ግንዛቤ ያዳብሩ። subscribe, like እና share በማድረግ የቻናላችን ቤተሰብ መሆን አይርሱ
Показать все...
👍 4
Показать все...
ህግን በአዲስ እይታ || ወንጀል ምንድን ነው? || ክፍል ሁለት || አዲስ መሀመድና ኢዘዲን ፈድሉ || አቃቢ ህግ ሆነው ካሳለፉት ኢዘዲን ጋር ያደረጉት ቆይታ

251920298841 For more information Telegram:

https://t.me/addismohlawfirm

Website :

https://addisassolawfirm.com

tik tok:tiktok.com/@tbqaaddis youtube:

https://youtube.com/@tebqaaddis?si=0QqR9G2JXTyJfoIh

Facebook :Addis Mohammed and Associates Law Firm Instgram:

https://www.instagram.com/tebqaaddis?igsh=c3czYWN3dzYxeDd1

👍 2
Фото недоступноПоказать в Telegram
በንብረት ማስመለስ ረቂቅ አዋጅ ላይ ከጋዜጠኞች ለቀረቡ ጥያቄዎች የፍትሕ ሚኒስትሩ ምላሽ https://www.fanabc.com/archives/251343
Показать все...
Фото недоступноПоказать в Telegram
👍 5
Фото недоступноПоказать в Telegram
👍 3
Фото недоступноПоказать в Telegram
Фото недоступноПоказать в Telegram
#ህግን_በአዲስ_እይታ  ወንጀል ምንድን ነው ? ጠበቃ አዲስ መሀመድ ከ ኢዘዲን ፈድሉ ጋር ግሩም ቆይታ አድርገዋል እነሆ ክፍል አንድን ከላይ ያለውን ማስፈንጠሪያ በመጫን ይመልከቱ በወንጀል ዙሪያ ያለዎትን ግንዛቤ ያዳብሩ። subscribe, like እና share በማድረግ የቻናላችን ቤተሰብ መሆን አይርሱ
Показать все...
Показать все...
ህግን በአዲስ እይታ || ወንጀል ምንድን ነው? || አዲስ መሀመድና ኢዘዲን ፈድሉ || አቃቢ ህግ ሆነው ካሳለፉት ኢዘዲን ጋር ያደረጉት ቆይታ

251920298841 For more information Telegram:

https://t.me/addismohlawfirm

Website :

https://addisassolawfirm.com

tik tok:tiktok.com/@tbqaaddis youtube:

https://youtube.com/@tebqaaddis?si=0QqR9G2JXTyJfoIh

Facebook :Addis Mohammed and Associates Law Firm Instgram:

https://www.instagram.com/tebqaaddis?igsh=c3czYWN3dzYxeDd1

Выберите другой тариф

Ваш текущий тарифный план позволяет посмотреть аналитику только 5 каналов. Чтобы получить больше, выберите другой план.