cookie

Мы используем файлы cookie для улучшения сервиса. Нажав кнопку «Принять все», вы соглашаетесь с использованием cookies.

avatar

መዝሙር ዘምር ዘምር አለኝ

መንግስተ ሰማዐያት ቀርባለችና ንስሀ እንግባ

Больше
Рекламные посты
1 940
Подписчики
-124 часа
-187 дней
+8630 дней

Загрузка данных...

Прирост подписчиков

Загрузка данных...

✞ የልቤን ሁሉ ✞ የልቤን ሁሉ ለማን ለማክር  እመቤቴ ሆይ ካንቺ በቀር  ለደካማ ሰው መጠጊያ እኮ ነሽ  ሀዘን ጭንቀቴን የምረሳብሽ  ቅዱሳን አበው አንቺን መረጡ ፪ ከሲኦል አለም ስላመለጡ  ጻዲቅ በስራው ያኔ ሲድን ፪ እጠራሻለው ድንግል አንቺን  አዝ ====== የጭንቄ ደራሽ አክሊሌ ነሽ ፪ ቂም በቀል አያውቅ የዋህ ልብሽ  ልቤ ለፍቅርሽ ሰፊ ስፍራ አለው ፪ በአዘንኩኝ ሰአት እጠራሻለው  አዝ ====== ዋሴ ነሽ ለኔ ድንግል እናቴ ፪ ስምሽ ጠበቀኝ ከልጅነቴ  ሁል ጊዜ ለኔ በጎ አረግሽልኝ  ምን ልበል ላንቺ ቃላታም የለኝ  አዝ ====== ላዘንኩኝ ለኔ ደስታዬ ነሽ ፪ ያረጋጋሽኝ ፈጥነሽ ደርሰሽ  ስምሽ ኃጥአንን የሚቀድስ፪ ከሞት ወደ ህይወት የሚመልስ  አዝ ====== የመንገዴ ስንቅ የረሀቤ መርሻ ፪ ለታመመ ሰው ነሽ መፈወሻ  ለተማጸነሽ በስምሽ አምኖ ፪ ማን አፍሮ ያውቃል አንቺን ለምኖ  
Показать все...
5👏 1
በማህፀን ቅኔ በማህፀን ቅኔ ለማርያም ተሰማ በተራራማ ሃገር በኤፍሬም ከተማ ዮሐንስ ይናገር በረሃ ያደገው ድንግል ስትናገር ምን እንዳዘለለው /2/ የእናቱ ማህፀን የቅኔ ርስት ሆነች ድንግል የአምላክ እናት ፊቱ ስለቆመች በሃሴት ዘለለ ዘመረ በደስታ ከድንግል ሲወጣ ታላቁ ሰላምታ አዝማች... በድንግል ማህፀን ስላየ ጌታውን ከመወለድ ቀድሞ ሰማነው መዝሙሩን ትንቢቱ ሲፈፀም በሆዷ ሲነግስ ሰገደ ለአምላኩ የስድስት ወር ፅንስ አዝማች... ጀመረ ስብከቱን ገና ሳይወለድ ተፈጥሮ መች ቻለ ነብዩን ለማገድ አፉ ተከፈተ በታላቅ ምስጋና በእናቱ ማህፀን ድምጽን አሰማና አዝማች... የዮሐንስ እና ኤልሳቤጥ ገረማት ልጇ በማህፀን ቅኔ ሲቀኝባት ድምጿን ከፍ አደረገች አለም እንዲሰማ ሞላት መንፈስ ቅዱስ ለመዝሙር ለዜማ
Показать все...
👍 1
መዝሙር 108👏 "በቃለ ስብሀት" ዘማሪ አቤል መክብብ👏
Показать все...
👍 1 1
እዩና እመኑ ሰዎች እዩና እመኑ ሰዎች ድንጋዩ ተፈነቃቅሏል ኢየሱስ በኩለ ሌሊት በሀይሉ ሞትን ድል ነስቷል/2/ እልልታ ለዚህ ይገባል ግርግርታ ለዚህ ይገባል የሞት ሀይል ተዋርዷል ዛሬ ሲኦልም ተመሰቃቅሏል/2/ መላዕክቱ ነጭ ለብሰዉ ምስራቹን አበሰሩ ተነስቷል ኢየሱስ ብለው ለዓለም እዲናገሩ/2/ 👥@yemezmurgetemochet.me/KIDAN_MEHRET_ENATEbot @EthiopianOrthodoxTewahdoMezmurs
Показать все...
8👏 1
✞ሆሣዕና✞ ሆሣዕና በአርያም ሆሣዕና በአርያም ሆሣዕና በአርያም ሆሣዕና ሆሣዕና ሆሣዕና ለወልደ ዳዊት ህፃናቱ ሁሉ ድንጋዮች ሳይቀሩ ለዘመሩለት ሆሣዕና ለወልደ ዳዊት በእግዚአብሔር ስም የሚመጣ እርሱ የተባረከ ነው ቅዱስ ነው መንፈሱ ሰላምን የሚሰብክ የሚናገር ፍቅርን በአህያ ውርንጫ መጥቷል ንጉሣችን አዝ= = = = = ዘንባባውን ይዘው ህፃን አዛውንቱ ልብሳቸውን ሳይቀር አንጥፈው በፊቱ ሆሳሣና ብለው ዘመሩ በእልልታ ግባ ንጉሣችን የሠራዊት ጌታ አዝ= = = = = ዘመንን ለሰጠን እንዘምርለት የምስጋናን መስዋዕት በፊቱ እንሰዋለት እንኳን እኛን ቀርቶ ድንጋይ ያናግራል ከሚጠቡ አንደበት ምስጋናን ይወስዳል አዝ= = = = = መድሃኒት ለሰው ልጅ ስለተገለጠ የመርገም ጨርቃችን ስለተወጠ ሰላም በሰማያት ሆነ በምድር ክብርና ምስጋና ለእርሱ ለእግዚአብሔር አዝ= = = = = እኛ ለክርስቶስ እናስፈልጋለን ቅዱሳኑን ልኮ መፈታትን ይስጠን በትህትና ወድቀን በልባችን ይግባ እንደ ህፃናቱ እንያዝ ዘንባባ መዝሙር ዲያቆን ቀዳሜጸጋ ዮሐንስ የዮሐንስ ወንጌል ፲፪፥፲፫ መዝ ፰፥፪
Показать все...
✝️✝️✝️2አንችን ብቻ ቤተልሔም✝️✝️ ✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️ አንቺን ብቻ ቤተልሔም አንቺን ብቻ በዚያ ግርግም ዮሀንስነ በገሊላ በኤፍራታ አላየንም አንቺን ብቻ ቀራንዮ አንቺን በኮረብታ ዮሴፍንም አላየንም ሊጣስትራ ጎልጎታ አዝ... ገና በማለዳ በናዝሬቷ መቅደስ ገብርኤል በስራት ይዞ ከገሊላ ሲደርስ ያን ዜና ስሰሚ ደነገጥሽ በብርቱ አንቺ ብቻ ነበርሽ ብላቴናይቱ አዝ.... ሕፃኑን ስትወልጅ ግርግም የነበሩ የሉም በመከራው ቀራንዮን ፈሩ በልደቱ እንጂ የታሉ በሞቱ አብረሹ ነበርሽ አንቺ ብቻ እናቱ አዝ... የግብፅ በረሀ አብረውሽ የወጡ በቀያፋ ግቢ እንደምን አልመጡ እርሱ ለሚገረፍ እነሱ እያፈሩ አንቺን ብቻ ትተው በመንደር ነበሩ አዝ.. ሐሙስ ዕለት ፋሲካን ሲበሉ ያመሹ አርብ ዕለት ተነሥተው ከቶ ወዴት ሸሹ ቃል ገብተው ነበር ላይክዱት መሀላ ድንግል ካንቺ በቀር ማን ነበር ሌላ አዝ... በሠላሳ ዘመን በሥጋ ወራቱ መች ነበሩ ከቶ ደቀመዛሙርቱ የእጆቹን ታምራት ቀን ከሌሊት እያየሽ በቃሉ በርታት ፊት አንቺ ነበርሽ አዝ... ቤተልሄም ያሉ ቀራንዮ የሉም ቀራንዮም ያሉ ግርግም አልነበሩም በሆነበት ዘመን በመስቀል ሞቱ አብረሹ ነበርሽ አንቺ ብቻ እናቱ
Показать все...
👍 4
#እርሱ_ነው_ቀን_የሚይወጣ ከዳን እስከ ቤርሳቤህ ዛሬ ሞልቷል ምስጋናህ ተነሳ ልቤ ዘምር ለጌታ ለእግዚአብሔር 3 አዝ።።።።።።።።።።።።።። በገና ተነስ እንዚራ ማዳኑን እንድናወራ ብትቀርቡ ብትከተሉ ሁላችው ሆሳህና በሉ 2 አዝ።።።።።።።።።።።።። እግዚአብሔር ዘመን ከሰጠ ይዘምር የተለወጠ እልልታ ይሁን ለስሙ ለዋጀን በወርቅ ደሙ 2 አዝ።።።።።።።።።።።።።።።።። የክብሬ የቤቴ ጌታ የነፍሴ ባለውለታ ኤፉድ ነው በፍታ ነው ልብሴ ዘማሪ ነኝ ለንጉሴ 2 አዝ።።።።።።።።።።።።።።።።። ሰገነት ላይ የወጣችው ዝምታን የመረጣችው ከአፋችው ወረት አይውጣ እሱ ነው ቀን የሚያወጣ 2 አዝ።።።።።።።።።።።።።።።
Показать все...
1
✞ ምስጋናዬን ✞ ምስጋናዬን ላምላኬ አቀርባለው በማደሪያው ገብቼ ሠግድለታለው ኤልሻዳይ ነው ጌታ ሁሉን ቻይ ይፈፀማል አምናለሁ የልቤን ጉዳይ(2) ዘንባባዬን ይዤ እደህፃናቱ ሆሣና ልበለው ሠግጄ በፈቱ ምንም ባዶብሆን እውቀት ቢጎድለኝ ለሥሙ ልዘምር ከልካይም የለኝ(2)          አዝ= = = = = አምላኬ በፈትህ ቃል አለብኝ እኔ ቋንቋዬ መዝሙር ነው ያንተ እደመሆኔ ባሚናዳ ደጃፍ በቅድመ ታቦቱ ያየክብርህ ውደር ጠራኝ ማህሌቱ (2)          አዝ= = = = = የህይወት ትርጉሜ አንተነህ ደሥታዬ ስምህን ማገልገል ክብሬነው ሥራዬ ለታመነው ጌታ ምስክር የሆኑ ከብረው ተመለሱ ለበረከት ሆኑ(2)          አዝ= = = = = መነሻዬ አንተነህ ጉልበቴና ክብሬ መድረሻዬም አንተ መደምደሚያ ቅጥሬ በፂሆን ተራራ ስትገለጥ ያኔ ነጩን ልብሥ አልብሠህ አስነሳኸኝ ለቅኔ (2)                     መዝሙር በ    ሊቀ መዘምራን ዲያቆን ቴድሮስ ዮሴፍ ╭══•|❀:✧๑♡๑✧❀|: ══╮   
Показать все...
3👍 1
✞ሆሳዕና✞ ሆሳዕና በአርያም ሆሳዕና ሆሳዕና ብለን እናቅርብ ምስጋና ሆሳዕና በሉ - - - ሆሳዕና ለወልደ አምላክ - - - ሆሳዕና ትህትናን አሳየን - - - ሆሳዕና ስሙ ይባረክ - - - ሆሳዕና አዝ= = = = = ሆሳዕና በሉ - - - ሆሳዕና ለሰማይ ንጉስ - - - ሆሳዕና ግርማ ለብሶ መጣ - - - ሆሳዕና እኛን ሊቀድስ - - - ሆሳዕና አዝ= = = = = ሆሳዕና በሉ - - - ሆሳዕና ለወልደ ዳዊት - - - ሆሳዕና ነብያት በትንቢት - - - ሆሳዕና ለተናገሩለት - - - ሆሳዕና ሐዋርያት በወንጌል - - - ሆሳዕና ለሰበኩለት - - - ሆሳዕና አዝ= = = = = ሆሳዕና በሉ - - - ሆሳዕና ለአምላከ ምህረት - - - ሆሳዕና ተወልዶ ከድንግል - - - ሆሳዕና እንደ ህጻናት - - - ሆሳዕና እረኞች በዋሻ - - - ሆሳዕና የሰገዱለት - - - ሆሳዕና የአዳም ልጆች ሁሉ - - - ሆሳዕና ደግሞም መላእክት - - - ሆሳዕና ═•|❀:✧๑♡๑✧❀|: ═
Показать все...
✞የዘመን ፍፃሜ✞ የዘመን ፍፃሜ እስከዚህ የሌለህ ዘላለም የምትኖር (፫)ፍጹም አምላክነህ 🌿ሆሳዕና (፫) በአርያም🌿 ቡሩክ ሆሳዕና አምላከ እስራኤል ተቀምጦ መጣ (፫) በአህያ ግልገል አዝ= = = = = 🌿 ትንሹም ትልቁም በአንድነት ዘመሩ አመሰገኑት (፫) ሆሳዕና እያሉ 🌿 አዝ= = = = = በጣም ደስ ይበልሽ እልል በይጽዮን ንጉሥሽ መጣልሽ (፫) ሊሆንሽ መድኅን 🌿 🌿 ╭══•|❀:✧๑♡๑✧❀|: ══╮
Показать все...