cookie

Мы используем файлы cookie для улучшения сервиса. Нажав кнопку «Принять все», вы соглашаетесь с использованием cookies.

avatar

Ministry of Revenues -Medium Taxpayers Branch No2

This is official Telegram Channel of Ministry of Revenues Medium Taxpayers Branch No 2. Join the channel.

Больше
Рекламные посты
3 939
Подписчики
+1824 часа
+807 дней
+34630 дней

Загрузка данных...

Прирост подписчиков

Загрузка данных...

ሕዝብ ለሀገሩ ሁለት ጊዜ ግብር ይከፍላል፤ በጦርነት ጊዜ የደም፣ በሰላም ጊዜ የገንዘብ ግብር ይከፍላል - አቶ ተመስገን ጥሩነህ (የኢፌዴሪ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር) ሰኔ 27/2016 ዓ.ም (የገቢዎች ሚኒስቴር) ከየካቲት 2015 ዓ.ም እስከ የካቲት 2016 ዓ.ም የተካሄደው <<ግብር፤ ለሀገር ክብር!>> የታክስና ጉምሩክ ህግ-ተገዥነት ንቅናቄ ማጠቃለያ እና አዲስ ንቅናቄ ማስጀመሪያ ፕሮግራም በአድዋ መታሰቢያ ሙዚየም አዳራሽ ተካሂዷል:: በዚሁ መድረክ የማጠቃለያ ንግግር እና የስራ አቅጣጫ የሠጡት የኢፌዴሪ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ተመስገን ጥሩነህ ሕዝብ ለሀገሩ ሁለት ጊዜ ግብር ይከፍላል፤ በጦርነት ጊዜ የደም፣ በሰላም ጊዜ የገንዘብ ግብር ይከፍላል ያሉ ሲሆን ከባዱን የደም ግብር ለምንወዳት ሀገራችን ለመክፈል ግንባራችንን የማናጥፍ እና የማንሰስት ብንሆንም ቀላሉን እና በሰላም ጊዜ የምንከፍለውን የገንዘብ ግብር የመክፈል ባህላችን ግን ደካማ ነው ብለዋል፡፡ በመሆኑም በደም የጠበቅናትን ሀገር በኢኮኖሚ ለማጽናት ከዚህ ችግር በፍጥነት መላቀቅ ይገባናል ሲሉ ገልጸዋል፡፡ ሙሉውን ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ፡- https://rb.gy/lskq0b
Показать все...
👍 2
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ (ዶ/ር) በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 36ኛ መደበኛ ስብሰባ ላይ ገቢን በተመለከተ ከተናገሩት (በገቢዎች ሚኒስቴር የመካከለኛ ግብር ከፋዮች ቁጥር 2 ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ሰኔ 27/2016 ዓ.ም አዲስ አበባ)፡- የአንድ መንግስት የልማት፣ የማህበራዊ ጉዳዮች ትልሞቹን የማሳኪያ የሀብት ምንጮች ሁለት ናቸው፡፡ አንደኛው ግብር ሲሆን ሁለተኛው ዜጎች ከሚቆጥቡት ገንዘብ ተበድሮ በልማታዊ መስኮች ላይ የሚያውለው ነው፡፡ ከግብር እና ከዜጎች ቁጠባ ውጪ ያሉ የመንግስታት የሀብት ምንጮች እርዳታና ብድር ያሉ ቋሚ የሀብት ምንጭ ተደርገው አይወሰዱም ከሁኔታዎች ጋር የሚቀያየሩ ናቸው፡፡የመንግስትን የልማት ትልም ለማሳካት ቋሚ የሀብት ምንጭ የሚሆነው ከግብር እና ዜጎች የሚያስቀምጡት ሀብት ነው፡፡ ይህንን ሀብት ወደ ልማት በማስገባት ሀገራት ሊለወጡም ሊቀየሩም ይቻላሉ፡፡ የእኛን ስራዎች መመዘን ያለብን እነዚህን ሁለት የሀብት ምንጮች ምን አስገኙ መንግስት እነዚህን ተጠቅሞ ምን ሰራ በሚለው ነው፡፡ ኢትዮጵያ ውስጥ የፌደራል መንግስት ከ64 ሺህ ግለሰቦች፣ ቡድኖች ወይም ኩባንያዎች ግብር ይሰበስባል፡፡ 64ሺህ ሰዎች ከፍለውት 120ሚሊዮን ህዝቦች ይጠይቁታል፡፡ 64ሺህ ሰዎች የሚከፍሉት ግብር ኢትዮጵያ አጠቃላይ ካላት ሀብት ጋር በእጅጉ ያነሰ በመሆኑ በምንፈልገውና በምናስበው ልክ በሁሉም መስክ ልማትን ውጤትአማ በሆነ መንገድ ለማምጣት እንቸገራለን፡፡ ምናልባት ግብር በበቂ ሁኔታ እስኪሰበሰብ እንደዚህ ቀደሙ በብድር ይሰራል እንዳይባል እዳ ያጎበጠው ኢኮኖሚ ስለሆነ ከለውጡ ጊዜ ጀምሮ ምንም ዓይነት የኮሜርሻል ብድር አንበደርም ብለን ባለፉት ስድስት አመታት አልተበደርንም፡፡ በአንፃሩ ኢትዮጵያ የነበረባት ዕዳ ወደ ልጆቻችን መሸጋገር የለበትም በሚል ፅኑ እምነት ዛሬ ኢትዮጵያ ያለባትን የውጪ ዕዳ ወደ17.5% ከጂዲፒ ዝቅ ብሏል ይህ ትልቅ ዕድል እና ትልቅ ዜና ነው፡፡ በዚህ በጀት ዓመት 529 ቢሊዮን ብር ለመሰብሰብ ታቅዶ 11 ወራት 466 ቢሊዮን ብር ወይም 96 በመቶ ተሰብስቧል፡፡ ካለፈው ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነጻጸር ከፍተኛ መሻሻል አለው፡፡ የተለጠጠ እቅድ ታቅዶ ወደስራ እንደመገባቱ አፈጻጸሙም በቀላል የሚታይ አይደለም፡፡ በእኛ ገቢ ውስጥ ያለው አንኳር ችግር 1ኛ ኮንትሮባንድ፤ ነው ኮንትሮባንድ አሁንም የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ ጋሬጣ የሆነ ጉዳይ ነው፡፡ 2ኛ ገቢ ስወራ ነው፤ ገቢን መክፈል ሲገባ የመሰወር ልምምዳችን በበቂ ደረጃ ገቢን ለመሰብሰብ እንዳንችል ጋሬጣ ሆኗል፡፡ 3ኛ የንግድ ማጭበርበር ነው፣ በተለይም በገቢና በወጪ ንግዶች የሚታየው የንግድ ማጭበርበር ኢትዮጵያ በቀላሉ ሰብስባ ልማቷን ለመመገብ የሚያስችል ሀብት ማመንጨት እየቻለች በነዚህ ዋና ዋና ምክንያች ከመንግስት የማስፈጸም ውስንነት ጋር ተያይዞ በበቂ ደረጃ ገቢን ለመሰብሰብ እንቅፋት ሆኗል፡፡ አፍሪካን ጨምሮ በርካታ ሀገራት ዜጎች ከፍተኛ የሆነ የግብር ጫና አለብን ብለው ነው የሚያነሱት የእኛ በተቃራኒው ከፍተኛ የታክስ ስወራ አለብን ነው ምንለው፡፡ በአፍሪካ ውስጥ ሞሮኮ 32%፣ ደቡብ አፍሪካ 24%፣ ኬንያ 15% ከጂዲፒአቸው ላይ ግብር የሚሰበሰቡ ሲሆን እኛ ከኬንያ በግማሽ አንሰን 7% ሚሆነውን ነው ከግብር የምንሰበስበው፡፡ በቀጣይ ወደ 10% እንኳን ብናሳድገው የተሻለ ልማት ለማምጣት ያስችለናል፡፡ ግብር ላይ አዋጆችን ጨምሮ በርካታ ማሻሻያዎች የምናደርገው ዜጎች የሚገባቸውን አግኝተው መንግስት የሚገባውን በታማኝነት የመክፈል ባህል፣ አሰራር ፣ ህግ እንዲዳብር ለማድረግ ነው ፡፡ ከተቋሙ አንፃር በርካታ ሪፎርሞች ተጀምረዋል፡፡ ተቋሙን የማዘመንና ኦቶሜት የማድረግ ስራዎች ተጠናክረው ይቀጥላሉ ፡፡ በትብብር መንፈስ በዚህ ዓመት የተሻለ ገቢ ለመሰብሰብ ጥረት ይደረጋል፡፡ ግብር÷ ለሀገር ክብር! ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ቴሌግራም፦ https://t.me/mormto2 ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/mto2infoo ኢሜል፡- [email protected] ዩትዩብ፡- https://www.youtube.com/@ministryofRevenues-MTO2 በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
Показать все...
Ministry of Revenues -Medium Taxpayers Branch No2

This is official Telegram Channel of Ministry of Revenues Medium Taxpayers Branch No 2. Join the channel.

👍 3
Фото недоступноПоказать в Telegram
የግብር፤ ለሀገር ክብር የንቅናቄ ፕሮግራም ማጠቃለያ እና አዲስ ንቅናቄ ማስጀመሪያ ፕሮግራም እየተካሄደ ይገኛል ሰኔ 27/2016 ዓ.ም (የገቢዎች ሚኒስቴር) ከየካቲት 2015 ዓ.ም እስከ የካቲት 2016 ዓ.ም የተካሄደው <<ግብር፤ ለሀገር ክብር!>> የታክስና ጉምሩክ ህግ-ተገዥነት ንቅናቄ ማጠቃለያ እና አዲስ ንቅናቄ ማስጀመሪያ ፕሮግራም የኢፌዴሪ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ተመስገን ጥሩነህ በተገኙበት በአድዋ መታሰቢያ ሙዚየም አዳራሽ እየተካሄደ ይገኛል:: በዚሁ መድረክ የገቢዎች ሚኒስትር ወ/ሮ ዓይናለም ንጉሴ ባለፈው አንድ አመት የታክስ እና ጉምሩክ ህግ-ተገዥነት ንቅናቄ መርሃ ግብር በፌደራል ደረጃ የተጀመረ ቢሆንም ክልሎች እና ከተማ አስተዳደሮችም አጀንዳውን በመቀበል በየደረጃው ካሉ የማህበረሰብ ክፍሎች ከኃይማኖት አባቶች አባገዳዎች እና ኡጋዞች ጋር ውጤታማ ምክክር በማድረግ የንቅናቄውን ዓላማ ለማሳካት የበኩላቸውን ኃላፊነት መወጣት ችለዋል፤ በርካታ ኩነቶችም ተከናውነዋል ብለዋል፡፡ መላ ኢትዮጵያዊያን በድህነት ውስጥ ያለች ሃገር ለትውልድ ከማስረከብ የኢኮኖሚ ሉአላዊነት ያላት ሃገር ለትውልድ ለማስረከብ ከወሰንን በዘርፈ ብዙ ችግሮችም ውስጥ ሆነን ከአላማችን አይናችንን ሳንነቅል ከሰራን የራሳችንን አዲስ የታሪክ ምዕራፍ መጻፍ እችላለን፡፡ በመሆኑም ይህንን አዲስ ምዕራፍ በመንግስት፤ በግሉ ዘርፍና በመላው ህዝባችን ትብብር እውን በማድረግ እና የኢኮኖሚ ሉአላዊነታችንን በማረጋገጥ የራሳችንን ደማቅ ታሪክ መጻፍ ይኖርብናል ሲሉ መልእክታቸውን አስተላልፈዋል፡፡ በተጨማሪም የታክስ እና ቀረጥ ህግ ተገዥነት ንቅናቄው መርሃ ግብር ስኬታማ እንዲሆን ኃላፊነታችሁን የተወጣችሁ የታክስና ጉምሩክ አምባሰደሮቻችን፣ በየደረጃው ያላችሁ የፌደራል የክልልና የከተማ አስተዳደር የስራ ኃላፊዎች እና ባለሞያዎች በራሴና በሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ስም ላቅ ያለ ክብር እና ምስጋና ይድረሳችሁ ብለዋል፡፡
Показать все...
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ (ዶ/ር) በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 36ኛ መደበኛ ስብሰባ ላይ ገቢን በተመለከተ ከተናገሩት (በገቢዎች ሚኒስቴር የመካከለኛ ግብር ከፋዮች ቁጥር 2 ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ሰኔ 27/2016 ዓ.ም አዲስ አበባ)፡- የአንድ መንግስት የልማት፣ የማህበራዊ ጉዳዮች ትልሞቹን የማሳኪያ የሀብት ምንጮች ሁለት ናቸው፡፡ አንደኛው ግብር ሲሆን ሁለተኛው ዜጎች ከሚቆጥቡት ገንዘብ ተበድሮ በልማታዊ መስኮች ላይ የሚያውለው ነው፡፡ ከግብር እና ከዜጎች ቁጠባ ውጪ ያሉ የመንግስታት የሀብት ምንጮች እርዳታና ብድር ያሉ ቋሚ የሀብት ምንጭ ተደርገው አይወሰዱም ከሁኔታዎች ጋር የሚቀያየሩ ናቸው፡፡የመንግስትን የልማት ትልም ለማሳካት ቋሚ የሀብት ምንጭ የሚሆነው ከግብር እና ዜጎች የሚያስቀምጡት ሀብት ነው፡፡ ይህንን ሀብት ወደ ልማት በማስገባት ሀገራት ሊለወጡም ሊቀየሩም ይቻላሉ፡፡ የእኛን ስራዎች መመዘን ያለብን እነዚህን ሁለት የሀብት ምንጮች ምን አስገኙ መንግስት እነዚህን ተጠቅሞ ምን ሰራ በሚለው ነው፡፡ ኢትዮጵያ ውስጥ የፌደራል መንግስት ከ64 ሺህ ግለሰቦች፣ ቡድኖች ወይም ኩባንያዎች ግብር ይሰበስባል፡፡ 64ሺህ ሰዎች ከፍለውት 120ሚሊዮን ህዝቦች ይጠይቁታል፡፡ 64ሺህ ሰዎች የሚከፍሉት ግብር ኢትዮጵያ አጠቃላይ ካላት ሀብት ጋር በእጅጉ ያነሰ በመሆኑ በምንፈልገውና በምናስበው ልክ በሁሉም መስክ ልማትን ውጤትአማ በሆነ መንገድ ለማምጣት እንቸገራለን፡፡ ምናልባት ግብር በበቂ ሁኔታ እስኪሰበሰብ እንደዚህ ቀደሙ በብድር ይሰራል እንዳይባል እዳ ያጎበጠው ኢኮኖሚ ስለሆነ ከለውጡ ጊዜ ጀምሮ ምንም ዓይነት የኮሜርሻል ብድር አንበደርም ብለን ባለፉት ስድስት አመታት አልተበደርንም፡፡ በአንፃሩ ኢትዮጵያ የነበረባት ዕዳ ወደ ልጆቻችን መሸጋገር የለበትም በሚል ፅኑ እምነት ዛሬ ኢትዮጵያ ያለባትን የውጪ ዕዳ ወደ17.5% ከጂዲፒ ዝቅ ብሏል ይህ ትልቅ ዕድል እና ትልቅ ዜና ነው፡፡ በዚህ በጀት ዓመት 529 ቢሊዮን ብር ለመሰብሰብ ታቅዶ 11 ወራት 466 ቢሊዮን ብር ወይም 96 በመቶ ተሰብስቧል፡፡ ካለፈው ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነጻጸር ከፍተኛ መሻሻል አለው፡፡ የተለጠጠ እቅድ ታቅዶ ወደስራ እንደመገባቱ አፈጻጸሙም በቀላል የሚታይ አይደለም፡፡ በእኛ ገቢ ውስጥ ያለው አንኳር ችግር 1ኛ ኮንትሮባንድ፤ ነው ኮንትሮባንድ አሁንም የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ ጋሬጣ የሆነ ጉዳይ ነው፡፡ 2ኛ ገቢ ስወራ ነው፤ ገቢን መክፈል ሲገባ የመሰወር ልምምዳችን በበቂ ደረጃ ገቢን ለመሰብሰብ እንዳንችል ጋሬጣ ሆኗል፡፡ 3ኛ የንግድ ማጭበርበር ነው፣ በተለይም በገቢና በወጪ ንግዶች የሚታየው የንግድ ማጭበርበር ኢትዮጵያ በቀላሉ ሰብስባ ልማቷን ለመመገብ የሚያስችል ሀብት ማመንጨት እየቻለች በነዚህ ዋና ዋና ምክንያች ከመንግስት የማስፈጸም ውስንነት ጋር ተያይዞ በበቂ ደረጃ ገቢን ለመሰብሰብ እንቅፋት ሆኗል፡፡ አፍሪካን ጨምሮ በርካታ ሀገራት ዜጎች ከፍተኛ የሆነ የግብር ጫና አለብን ብለው ነው የሚያነሱት የእኛ በተቃራኒው ከፍተኛ የታክስ ስወራ አለብን ነው ምንለው፡፡ በአፍሪካ ውስጥ ሞሮኮ 32%፣ ደቡብ አፍሪካ 24%፣ ኬንያ 15% ከጂዲፒአቸው ላይ ግብር የሚሰበሰቡ ሲሆን እኛ ከኬንያ በግማሽ አንሰን 7% ሚሆነውን ነው ከግብር የምንሰበስበው፡፡ በቀጣይ ወደ 10% እንኳን ብናሳድገው የተሻለ ልማት ለማምጣት ያስችለናል፡፡ ግብር ላይ አዋጆችን ጨምሮ በርካታ ማሻሻያዎች የምናደርገው ዜጎች የሚገባቸውን አግኝተው መንግስት የሚገባውን በታማኝነት የመክፈል ባህል፣ አሰራር ፣ ህግ እንዲዳብር ለማድረግ ነው ፡፡ ከተቋሙ አንፃር በርካታ ሪፎርሞች ተጀምረዋል፡፡ ተቋሙን የማዘመንና ኦቶሜት የማድረግ ስራዎች ተጠናክረው ይቀጥላሉ ፡፡ በትብብር መንፈስ በዚህ ዓመት የተሻለ ገቢ ለመሰብሰብ ጥረት ይደረጋል፡፡ ግብር÷ ለሀገር ክብር! ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ቴሌግራም፦ https://t.me/mormto2 ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/mto2infoo ኢሜል፡- [email protected] ዩትዩብ፡- https://www.youtube.com/@ministryofRevenues-MTO2 በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
Показать все...
Ministry of Revenues -Medium Taxpayers Branch No2

This is official Telegram Channel of Ministry of Revenues Medium Taxpayers Branch No 2. Join the channel.

Фото недоступноПоказать в Telegram
ከየካቲት 2015 ዓ.ም እስከ የካቲት 2016 ዓ.ም የተካሄደው የታክስና ጉምሩክ ህግ-ተገዥነት ንቅናቄ ማጠቃለያ እና አዲስ ንቅናቄ ማስጀመሪያ ፕሮግራም አሁን እየተካሄደ ይገኛል ሰኔ 27/2016 ዓ.ም (የገቢዎች ሚኒስቴር)
Показать все...
Фото недоступноПоказать в Telegram
2
Фото недоступноПоказать в Telegram
👍 3
Выберите другой тариф

Ваш текущий тарифный план позволяет посмотреть аналитику только 5 каналов. Чтобы получить больше, выберите другой план.