cookie

Мы используем файлы cookie для улучшения сервиса. Нажав кнопку «Принять все», вы соглашаетесь с использованием cookies.

avatar

ፍልስፍና-ራስን መሆን

በዚህ Channel ምርጥ #የፍልስፍና_መፅሐፍቶችንና #የፍልስፍና_አስተሳሰቦችን #የስኬት ቁልፍ ሀሳቦችን እና #እና የተለያዩ የታላላቅ ሰዎች አባባሎችን ታገኛላችሁ.......

Больше
Рекламные посты
307
Подписчики
Нет данных24 часа
+67 дней
+930 дней

Загрузка данных...

Прирост подписчиков

Загрузка данных...

📚ርዕስ:- የቆሸሹ ሳቆች 📝ደራሲ:- አዘርግ ADAMU G 📜ዘውግ:- 70እውነታ 30ፈጠራ 📅ዓ.ም:- 2012 📖የገፅ ብዛት:- 212 👨አዘጋጅ:- ✨️ባቢ ✨️ 🔞🔞 SHARE and JOIN🙏 @ETHIO_PDF_BOOKS @ETHIOPDFBOOKS2 @ARTOFBOLLA777 @BHEREMETSHAFTOCH
Показать все...
የቆሸሹ ሳቆች በአዘርግ- @ETHIO_PDF_BOOKS.pdf27.39 MB
👍 2
🎋#ወደውስጥ_ተመልከት "ራስን መፈለግ፣ ራስን ማወቅና ራስን መሆን ትጋት ውስጥ የሚኖር ሰው፣ ስለሚያደርገው ሁሉ ሀላፊነት ይሰማዋል። ከራሱ አንፃር ብቻ ሳይሆን፣ የሌሎችንም ፍላጎት ለማሳካት ጭምር ያልማል።በአጭሩ ራሱን የሆነ ሰው ሃገሩን ይሆናል።" ወዳጄ ራሳቸውን ያልሆኑ ሰዎች ከአንተነትህ ሥርዓተ ስብዕና ሰበዝ እየመዘዙ ወይ ያደንቁሃል ወይ ይንቁሃል። ሚዛናቸው አንተነትህን በአንተነትህ ልክ ሳይሆን በፍላጎታቸው ማዕቀፍ ያደርጉትና ስትጎድልባቸው በነገር ያበጥሩሃል። ወደ ውስጥ መመልከት የጀመሩ እንደሆነ ግን ብዙ ሊደክሙለት የሚገባ ማንነት እንዳላቸው ይረዱታል። ወደ ውስጥ መመልከት መቻል ጸጋ ነው!!! : #ራስህን_ሁን
Показать все...
👏 2
☞ትልቅ ሐሳብ ትልቅነት ስላለን ብቻ አይደለም የሚመጣው። ሰው ሰው በመሆኑ ብቻ ያስባል። ዩኒቨርሲቲ ስለገባ አይደለም፤ በጣም ስለተማረም አይደለም ሐሳብ የሚያፈልቀው። ከችግር፣ ከተግዳሮት ጋር ሲላተም ከዛ ለመውጣት የማይቆፍረው ጉድጓድ የለም። አጣብቂኞች ሲበዙ፣ ማምለጫዎች ሲጠፉ ነው አዲስ ሐሳብ የሚፈልቀው። ኢትዮጵያ ውስጥ መብራት ባይኖር ማሰብ እንጀምር ነበር። አሁን መብራት ስላለህ ሞባይልህ ጋር መሸወጃ ጊዜ አለህ። ቻት እያደረገ የሚነጋበት እኮ ብዙ ነው። መጽሐፍ ብትሰጠው ግን በ10 ደቂቃ ውስጥ እንቅልፍ ይወስደዋል። ይሄ የመጣው በጣም በጥልቀት በተደጋጋሚ የተቀጠቀጠ ሐሳብ ስላለ ነው። ከዚህ በኋላ እኮ የ4ኛ ክፍል ተማሪ ፍቅር ይዞት "ውዴ..."ምናምን እያለ የፍቅር ቋንቋ ሲያወጣ ልትሰማው ትችላለህ። ምን ያህል የትውልድ ክፍተት እንዳለ እኮ የሚገርም ነው። ሌላው ቀርቶ "ያ ትውልድ" በምትለውና በዛሬው ትውልድ መሃል ያለው ልዩነትኮ በአያትና በልጅ መሐል ያለ ነው የሚመስለው። በፍጥነት ነው ለውጡ። : ✍#ቡርሐን_አዲስ✍
Показать все...
እኔ የምፈራው. . . "ምን አለኝ?" ከሚል ጥያቄ ይልቅ "ሰው ምን ይላል?!" በሚል ስጋት ተውርሮ ሕልምን ማጨናገፍ! አድገው ጽጌረዳ ሳይሆኑ በለጋነት መርገፍ! ዓለም በፈጠረችው ሕግጋት ታስሮ የራስን ዓለም ሳይፈጥሩ ማለፍ! #እኔ_የምፈራው. . . ደስታዬን በሰዎች ላይ መገንባት! ከሰው ሲስማሙ ጮቤ መርገጥ፣ሰው አለኝ ብሎ ደረትን መንፋት! ሰው የጠፋ ቀን ማንነትን ፈልጎ ማጣት፣እውነትን መካድ፣መንገድ አልባ ሆኖ ከንፋስ ጋ መጥፋት! . #እኔ_የምፈራው. . . በሚተኩኝ ሰዎች ዙሪያ ማንዣበብ! "አይተኬ ነኝ" ብለው ሲደነቁ ከርመው፣ ከታች ተወርውሮ አፈር ድሜ መብላት፣እንደ ዘበት. .. እንደ ዋዛ ተዘንግተው መና ሆኖ መቅረት! . #እኔ_የምፈራው. . . ባልተፈጠሩበት መስክ ዕድሜን ማሟጠጥ! የሚወዱትን ሰውተው፣የኔ በማይሉት መስክ ላይ ያለ ሰበብ መረገጥ! በሕሊና ጩኸት፣በፀፀት ረመጥ እየታቀጠሉ በሞት ሽረት ህመም ዕድሜ-ዘመን መራወጥ! . #እኔ_የምፈራው. . . በሰው እጅ መውደቅ! እኔ የምፈራው. . ፍርሃቴን ብቻ እየቆጠርኩ፣ፍርሃቴን ብቻ እየፈራሁ፣!ፍርሃቴን ብቻ እየተመንኩ መኖር!
Показать все...
#ስለፍቅር ከኦሾ❤❤ 💚ተጨልፎ ከማያልቀው ከኦሾ እይታዎች የተወሰነ ስለፍቅር ከተናገረው ወደናንተ እንበትነው ዘንድ የተገባ ሆኖ አገኝነው። " ፍቅር ማለት በምትወደው ሰው ነፍስ ውስጥ ራስህን መግደል ነው። ፍቅር ማለት ሞት ነው ፤ የሚቻልህን ያህል ጥልቅ በሆነ ሞት ውስጥ ትገባለህ ፤ የምትሞተውም በምትወዳት ሴት ነፍስ ውስጥ ነው ። ዕለት ዕለት ወደ ጥልቅ የነፍሷም ቦታ ትወሰዳለህ ፤ ፍቅር ወደምታፈቅራት ሴት የነፍስ ቦታ የምታደርገው ዘላለማዊ ጉዞ ነው ። ጉዞውም ማቆሚያ የለውም ። አንዲትን ሴት ስታፈቅራት በአንተ ሕይወት ውስጥ ከአንተ በላይ ዋጋ አላት ። ፍቅር ማለት ያለምንም ቅድመ ሁኔታ መማረክ ማለት ነው ። ምክንያቱም አንዳች ቅድሙ ሁኔታ የምታስቀምጥለት ከሆነ ከምታፈቅረው ሰው በላይ ለራስህ ዋጋ ሰጥተሃል ፡ማለት ነው ። ራስህን ዋነኛው ጉዳይ አድርገህ በፍቅር ውስጥ ስትመለከት ተፈቃሪዋ መጠቀሚያህ ሆነች ፤ የፍላጎትህ ማርኪያ አደረግሃት፤ በሌሎች ዘንድ መደነቂያህ ሆነች...መነሻውም መድረሻውም አንተ ሆነሃል ። : #OSHO/ኦሾ/
Показать все...
#ተደጋጋሚ ነገሮች በሙሉ ፀረ-ህይወት ናቸው! ከመደንዘዝና ከመሰልቸት ወጥታችሁ ህያው መሆን ከፈለጋችሁ #ስሜታችሁን ከልማድ አፅዷቸው።ልማዶች ከመደንዘዘ መሠረታዊ መንስኤዎች መሀል አንዱ ናቸው።አዲስ የተግባር መንገዶችን ፈልጉ፣አዲስ የፍቅር መንገዶችን ፍጠሩ።ሰዎች በጣም ስለሚፈሩ ቋሚ ልማድ አላቸው።ፍቅር ሲሰሩ እንኳን በአንድ አይነት መንገድ ነው።እናንተ ግን አዲስ የስሜት መንገዶች ፈልጉ።ተደጋጋሚ ነገር አትፈፅሙ።ተደጋጋሚ ነገሮች በሙሉ ፀረ-ህይወት ናቸው።ተደጋጋሚ ነገሮች የሞት አገልጋዮች ናቸው።ሁልጊዜ መፍጠር ትችላላችሁ ፈጠራዎች ወሰን የላቸውም በትንሽ ለውጥ ብዙ ልትጠቀሙ ትችላላችሁ ። * #ኦሾ/osho/
Показать все...
እንድታስታውሱ የምመክራቹሁ:- በህይወት እንድትኖሩ እና ህይወት ምን እንደሆነች ለማወቅ እንድትሞክሩ ነው። በሕይወት መኖራችሁ በጣም ውድ ነገር መሆኑ አስታውሱ ። ህይወትን አክብሩ ። ከህይወት የበለጠ የተቀደሰ ፣ ከሕይወት የበለጠ መለኰታዊ የሆነ ነገር የለም ። #ህይወታችሁን አክብሩ ። ህይወታችሁን በማክበርም የሌሎችን ህይወት ማክበር ትጀምራላችሁ ። ዋናው ምክንያት ህይወትን ካከበራችሁ አበባን እንኳን መቅጠፍ ይከብዳችኃል። አበባው ያስደስታችኃል ፣ ትወዱታላችሁ ፣ትዳስሱታላችሁ፣ታሸቱታላችሁ ነገር ግን አበባውን መቅጠፍ ልክ እንደ እናንተ ህይወት ያለውን አካል ማጥፋት እና ማሰቃየት ነው። : ➣Osho/ኦሾ ➣ኃይማኖትን መመርመ
Показать все...
ግትር መሆን ጅልነት ነው ። በብዙ አቅጣጫ መንቀሳቀስ ደግሞ #ብልህነት ነው ። ብልህነት ሁል ጊዜም እንደ ጅረት መፍሰስ ሲሆን ብልህ አለመሆን እንደ በረዶ ተጋግሮ መቅረት ነው ። ነገ የገዛ ራሱን አጋጣሚዎች ይዞ ይመጣልና የትላንቱን ሃሳቦቻችሁን የሙጥኝ ይዛችሁ ለመዝለቅ መሞከር እንደ በረዶ ረግታችሁ መቅረትን ያስከትላል ።በብልህነት ተንቀሳቀሱ ። #ኦሾ ህያውነት 3
Показать все...
#ጨረቃናጸሃይአይወዳደሩም! የራስህን ሕይወት በፍፁም ከማንም ጋር አታወዳድር። ምክንያቱም ብሎ የሚያስቀምጥል ነገር  እራስህን ከሌሎች ጋር ስታወዳድር የምታገኘው ውጤት  ከዛ ሰው የተሻልክ ከሆንክ #ኩራት ሲሆን ከዛ ሰው የምታንስ ከሆነ ደግሞ #ቅናት  ነው የሚሆነው። ሁለቱም መጥፎ ውጤቶች ናቸው ። ጨረቃና ጸሃይ አይወዳደሩም ሁለቱም በጊዜያቸው ደምቀው ያበራሉ ። #ኦሾ
Показать все...
#ሰው ለምን ይስቃል? ዮጋ ንቃተ ሂሊናን ለሁለት ይከፍለዋል- እራሱን ያወቀና ያላወቀ። ነፍስ እያላቸው ነፍስ እንዳላቸው የማያውቁት ራሳቸውን ያላወቁ ናቸው። ይሁን እንጂ ራሳችንን ማወቅ የሚገባን እኛ እንኳን በብዙ መንገዶች እንደ እንስሳት፣ ዛፎችና ድንጋዮች ነን። ሰው የሆነው በጣም ጥቂቱ ክፍላችን ነው። በዚህም ሳብያ ሰው እጅግ በጣም እረፍት አልባ ነው። እንስሳት እረፍት አልባ አይደሉም፤ እራሱን የሚገድል እንስሳ የለም። አንድ እንስሳ እራሱን ያጠፋ ግዜ ዝርያዉን ከእንስሳነት ወደ ሰብዓዊ ፍጡርነት እየተቀየረ መሆኑን እወቁ። ራሱን የሚያጠፋ አንድም እንስሳ የለም። እራሱን እንዲያጠፋ የሚያነሳሳ ስጋት አይፈጠርበትም። ከሰው በቀር አንድም እንስሳ አይስቅም።መንገዳችሁ ላይ አንድ በሬ ሲስቅና ሲገለፍጥ ቢያጋጥማችሁ በዛ መንገድ አታልፉም። የትኛውም እንስሳ አይስቅም። ምክንያቱም ሃዘንተኛ ስላልሆነ ሃዘኑን የሚያስረሳው ሳቅ አያስፈልገውም። ሳቅ የሀዘንና የደስታ አልባነት መደበቅያ ነው። በአለማችን ደስታ እየጠፋ በመጣ ቁጥር የተለያዩ የመዝናኛ አይነቶች እየተፈጠሩ የመጡትም በዚህው ምክንያት ነው። ሲኒማ፣ ቲቪ፣ ሬድዮ፣ ዳንስ፣ ዘፈን ተፈጥረዋል። እነዚህ ሲሰለቹት ደግሞ ሰው ሌሎች አዳዲስ መዝናኛዎች እንዲመጡለት ይፈልጋል። በዚ ዘመን ሃምሳ በመቶ የዓለማችን ሃይል ለሰው ልጆች መዝናኛዎችን ለማቅረብ እየዋለ ይገኛል። በዚ ዘመን ሰውን ለማዝናናት የቻሉ ሁሉ በጣም ተፈላጊ ናቸው። የምትፈልጓቸው አልፍ ስለሚያዝናኗችሁ ነው። ስቃይ ስላላችሁ ትንሽ የሚያዝናናችሁ ሰው ስታገኙ በጣም አስፈልጊያችሁ ታደርጉታላችሁ። ሳቅ ከውስጥ ያለን ውጥረት መቀነሻ ነው። እንስሳ የማይስቀው ውጥረትና ስጋት ስለሌለበት ነው! #ባግዋን_ኦሾ
Показать все...
👍 2
Выберите другой тариф

Ваш текущий тарифный план позволяет посмотреть аналитику только 5 каналов. Чтобы получить больше, выберите другой план.