ru
Feedback
Bashewam Primary & Junior School 1-8

Bashewam Primary & Junior School 1-8

Открыть в Telegram

Bashewam School Grade 1-8

Больше
2 781
Подписчики
+1524 часа
+287 дней
+8230 день
Архив постов
የሚመለከታችሁ ትምህርት ቤቶች በተላከላችሁ የሞዴል ጥያቄ መልስ መሠረት እንድታስተናግዱ ይሁን፡፡

የጥናት እቅድ አወጣጥ (ለተማሪዎች ሼር) 1. ለነገ ዝግጁ ሁኑ ሁሌም ዛሬ ለምነሰራው ብቻ ሳይሆን ነገ ለምንሰራው ስራ እቅድ በማውጣት ዝግጁ ልንሆን ይገባል! ለነገ ዝግጁ ሰትሆኑ ሰአታችሁን በአግባቡ ተጠቅማችሁ የቤት ስራችሁን በብቃት ወይንም በጊዜው ለማጠናቀቅ ይረዳችኃል! 2. የጥናት ቡድን ፍጠሩ ይህ የድሮ ዘዴ ሊመሰል ይችል ይሆናል! ነገር ግን አሁንም ቢሆን የጥናት ቡድን መፍጠር እጅግ በጣም ጠቃሚ ነው! እድሜ ለቴክኖሎጂ መሻሻል በሁላችንም ለማለት በሚያስደፍር መልኩ በምንጠቀምባቸው ስልኮች የሚገኙት እንደ ጎግል ፕላስ የመሰሉ ማህበራዊ ድረገፆች ከአስር በላይ ለሆኑ የጥናት ቡድኖች በቀጥታ የምስል እና የድምፅ ውይይት ለማድረገ ያስችላሉ! ስለሆነም በተለያዩ ቦታዎች ላይ ከሚገኙ የትምህርት አቻ ጓደኞች ጋር በአካልም ሆነ በተለያዩ የቴክኖሎጂ መገልገያዎች የጥናት ቡድኖች በመፍጠር እውቀትን እና ልምዶችን ልንጋራ ይገባል! 3. አንድ ነገር ለመስራት መደበኛ ልምድ ይኑራችሁ! – ከትምህርት ጋር የተገናኙ ስራዎችን ለመስራት እለታዊ የሆነ መደበኛ ጊዜ ስትመድቡ ሁሌም ቢሆን የሚሰጣችሁን የትምህርት ሀላፊነቶች እና የቤትስራዎች በአግባቡ እና በጊዜው ሰርቶ ለመጨረስ ይረዳችኃል! በአካባቢያችሁ ያሉ ሰዎችም ይህን ተረድተው ከአላማችሁ እንዳያሰናክሏችሁ አድርጉ! 4. ለጥናት ምቹ የሆነ ቦታ ያመቻቹ ! – ሁሌም ቢሆን የምታጠኑበት ስፍራ ምቾት ሊሰጣችሁና ትኩረት ለማድረግ የሚረዳችሁ ሊሆን ይገባል! 5. ሁሌም ቢሆን ተጠባባቂ እቅድ ይኑራችሁ – ብዙ ጊዜ ለትምህርት እና ለጥናት የምንገለገልባቸው እንደ ኮምፒውተር የመሳሰሉ መሳሪያዎች በማንጠብቃቸው ሰአቶች ሊበላሹ ብሎም ሊጠፉና ሊሰረቁ ይችላሉ! ስለዚህም አስፈላጊ የምንላቸውን ፋይሎች በተለያየ መልኩ በተጠባባቂነት ልንይዛቸው ይገባል! 6. የቀን መቁጠርያ አዘጋጁና ተጠቀሙ – በሁሉም የትምህርት ተቋማትና ደረጃዎች የአጭርና የረጅም ጊዜ የጥናት ስራዎች ይሰጣሉ! ታዲያ እንደ ርዝመታቸው እና እጥረታቸው ተማሪዎች በመዘናጋት ስራቸውን በአግባቡ ሳይወጡ ሲቀሩ ይስተዋላል! ይህን አስወግዶ ሀላፊነትን በአግባቡ ለመወጣት ከእለት ተእለት የትምህርት እና የጥናት እንቅስቀሴ ጀምሮ የረጅምና የአጭር ጊዜ ሀላፊነቶቻችንን በቀን መቁጠርያ አማካይነት እቅድ ልናወጣላቸው እና ልንተገብራቸው ይገባል! 7. የተደራጃችሁ ሁኑ በትምህርት ቆይታችሁ የምትገለገሉባቸውን መሳሪያዎች የትምህርት ሰአት የጥናት ሰአታችሁን የመዝናኛ ሰአታችሁን የገንዘብ አጠቃቀም እቅዳችሁን በመለየት ሁሉንም በስርአት በቦታውና በሰአቱ በመጠቀም የተደራጃችሁ ሁኑ! 8. አዎንታዊ አስተሳሰብን ያጎልብቱ ! የትምህርት ቤት ሕይወት ጠንካራ ስራን የሚፈልግና በጭንቀት ብሎም በመሰናክሎች የተመላ ነው! እነዚህን የሚገጥሙንን ጭንቀቶችና መሰናክሎች ተቋቁመን ስኬታማ ለመሆን ከምንመኛው የምረቃ በዓላችንም ለመድረስ አዎንታዊ አስተሳሰብን ልናጎለብት ይገባል! እንዴት አዎንታዊ አስተሳሰብን ማጎልበት እንደምንችል ኩሉ ኔትወርክ በቀጣይ ጠቃሚ ምክሮች ይዞላችሁ የሚመጣ ይሆናል! 9. እረፍት ውሰዱ ጥናት ከመጀመራችሁ በፊት ሆነ በጥናት መሀል አጭር የእረፍት ጊዜ መውሰድ ችግር እንደሌለው ልንረዳ ይገባል! ምክንያቱም የእረፍት ጊዜያቶች መንፈሳችሁን እንድታድሱ እና ወደጥናት ስትመለሱ ትኩረት አድርጋችሁ እንድትሰሩ ይረዳችኃል! 10. ዝርዝር የስራ እቅድ ወይንም check list ይኑራችሁ! – ብዙን ጊዜ የምንማራችሁ ትምህርቶች እለታዊ የሙከራ ስራ እና የቤት ስራዎች ይኖራቸዋል! በመሆኑም የሁሉንም የምንማራቸውን የትምህርት አይነቶች ሀላፊነቶች በአግባቡ ለመወጣት የስራ ዝርዝር በማዘጋጀት እቅድ ልናዘጋጅላቸው ይገባል! ይህም የስራ ሀላፊነታችንን በአግባቡ ለመወጣት ይረዳናል! ➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖

በፈተና ጊዜ የሚፈጠርን ጭንቀት ወይም ቴንሽንን ልንቆጣጠር የምንችልባቸው ዘዴዎች! ======================== 👉ፈተና የመፈተኛ ጊዜ ሲቃረብ ሁላችንም በመጠኑ መጨነቅ እና ከወትሮው ከፍ ባለ መጠን ውጥረት ውስጥ መግባታችን የተለመደ ነገር ነው::ይህን አይነቱን ከፍተኛ ውጥረት መቆጣጠር የምትችሉበትን መንገድ አንድ በአንድ እንመልከት፤ ከፈተና በፊት ማድረግ የሚገባን ዘዴዎች፤ ------------------------------------------------ ☝️ ፈተና ሲመጣ መጠነኛ ውጥረት እና ጭንቀት ተፈጥሮአዊ እና ሁሉም ተፈታኝ ተማሪ እንደሚያጋጥመው መረዳት። ☝️ ለፈተና ስንዘጋጅ አዎንታዊ እና በጎ ሀሳቦችን ማሰብ፡፡ 👌ፈተና ማለት ከዚህ ቀደም ከተማርነው ነገር የተረዳነውን እና የቀሰምነውን እውቀት የምንለካበት መመዘኛ እንጂ የኛ የህይወት ምዕራፍ ማብቂያ ወይም አጠቃላይ ችሎታችንን የሚያመላክት አይደለም ።  ☝️ማወቅ ያለብን አንድ ነገር ቢኖር መሳሳትን አለመፍራት እና ሁሌም ለማወቅ እና ራስን ለማሻሻል ዝግጅ መሆንን ነው ። እንዲሁም አሁን የምንፈተነው ፈተና እንዳሰብነው እንኳን ውጤቱ ባያስደስት ለቀጣይ ማስተካከል እና ማሻሻል እንደሚቻል ማመን። ☝️ ከጓደኞቻችን ጋር ያጠናነውን ነገር በጋራ ሆነን መጠያየቅ እና እርስ በርስ ያወቅነውን ነገር መለዋወጥ፡፡ ይህ ዘዴ ይበልጥ የማስታወስ ብቃታችንን እንደሚጨምር እና የተጠያየቅነው ነገር እንዳይረሳን ያረጋል ። ከዚህም በተጨማሪ የተሳሳትነውን ነገር ድጋሚ እንድንከልስ እና እርማት እንድናረግ ያግዘናል። ☝️ የፈተና ቀን ሲቃረብ እንደ ወትሮው ዘና ማለት እና በቂ እረፍትና በቂ እንቅልፍ  መተኛት ። ይህም ጭንቀትን ይቀንስልናል፣ እንዲሁም ተረጋግተን ያጠናነውን ነገር አስበን እንድንሰራ ይረዳናል።  ለተፈታኞች መልካም የፈተና ጊዜ!

photo content

photo content

photo content

photo content

photo content

photo content

photo content

photo content

photo content

photo content

ውድ የባሸዋም ትምህርት ቤት የተማሪ ወላጆች፡ በዛሬው ቀን በትምህርት ቤታችን የንባብ ቀን ለማክበር በተዘጋጀው ፕሮግራም ላይ ዶክተር መንግስቱ ታደሰ በተጋባዥነት የተገኙ ሲሆን ፡ ተማሪዎች እንዴት ማንበብ እንዳለባቸውና በክረምት ጊዜያቸው በንባብ እንዲያሳልፉ ስልጠና ሰጥተዋል። በፕሮግራሙ ላይ የተገኛችሁ የተማሪ ወላጆች እጅግ በጣም እናመሰግናለን።

ውድ የባሸዋም ትምህርት ቤት የተማሪ ወላጆች ሐሙስ እለት በቀን 08/10/15 ዓ.ም በትምህርት ቤታችን የአፀደ ህፃናት እና ከ1ኛ-4ኛ ክፍል ያሉት ተማሪዎች የንባብ ክህሎታቸው እንዲዳብር እና በክረምት ጊዜያቸው የተለያዩ መፅሐፍት እንዲያነቡ ለማነሳሳት ሲባል የንባብ ቀን የምናከብር ሲሆን በእለቱ መምጣት የምትችሉ የተማሪ ወላጆች 3:00 ሰዓት ላይ ትምህርት ቤት ተገኝታችሁ ፕሮግራሙን መታደም የምትችሉ መሆኑን እናሳውቃለን።