ግጥም
Открыть в Telegram
በዚህ ቻናል በጣም ምርጥ እና መንፈስን የሚያድሱ ግጥሞች ፣ ተከታታይ ታሪኮች ፣ የኦንላይን ቢዝነስ ቲፖች ይቀርቡበታል መርጣችሁ አብራችሁን ስላላችሁ እናመሰግናለን Buy Ads https://telega.io/c/gitm_post ADMIN 👉 @Big_jor
Больше4 815
Подписчики
+1324 часа
+617 дней
+23730 день
Архив постов
4 815
እባክሽ አንች እርግብ ነይ ተላኪኝማ
ሚስጥሬን ደብቀሽ ሌላ ሰው ሳይሰማ
ባደግኩበት ምድር በተወለድኩበት
አኩኩሉ አባሮሽ በተጫወትንበት
ለነበሩ ልጆች እኔ ለማውቃቸው
ለሁሉም ንገሪ እንደምወዳቸው
አደራ የኔ ውድ መልዕክቴን ስጫቸው
እነዳንረሳሳ ደግመሽ ንገሪያቸው
ዛሬ እንጀራ ሆኖ ምንም ብንራራቅ
ብዙ ትዝታ አለን እርቆ የማይርቅ
@gitm_post
♡ ㅤ ❍ㅤ ⌲
ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢʰᵃʳᵉ
4 815
#ትለያለሽ_እማ
ፍትህ በምድር ካለ ሰውም ካስተዋለ
መልካም እየሰራ መልካም ጋር ከዋለ
ንፁህ ፍቅር የት ነው እንዲያው ከተባለ
እውነተኛ አፍቃሪ እንዳንቺ ማን አለ
አያልቅ አይጎልብሽ የፍቅር አውድማ
የመልካም ሞዴል ነሽ የጥሩነት አርማ
ምንም ብትከፊ ውስጥሽ አያውቅም ቅር
አንች ነሽ ሚዛኗ የእውነተኛ ፍቅር
አያልፍ ወረት የለው ሁሌም የሚጠማ
የርህራሄ ምንጭ የመውደድ ቄጠማ
በፍትህ ፍርድ ላይ ብትቀመጭማ
ፍቅርሽ የትም የለም ትለያለሽ እማ
@gitm_post
♡ ㅤ ❍ㅤ ⌲
ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢʰᵃʳᵉ
4 815
ላንቺ ተገዝቼ አፍቅሬሽ የኖርኩኝ
ደስታሽን ስፈልግ ደስታዬን ያጣሁኝ
ሂድ ስትይ የምሄድ ቁም ስትይ የምቆም
ስከተልሽ ብውል ስዞር እማልደክም
እኔ እኮ እንደዚህ ነኝ...
ባልዋልሽበት ቦታ ዓይኔ የሚስልሽ
የእኔ ብትሆኝ እያልኩ ሁሌ የማስብሽ
ሳይሽ የምረካ ሳጣሽ ግን የምነድ
አመድ አፋሽ ሆኜ ባንች ባልወደድ
ምንም ባልልሽም አንድ እርምጃ ባልሄድ
ተውኩት በቃኝ እያልኩ አፍቅሬሽ ይመመኝ
እንዳሻሽ ያረግሽኝ እኔኮ ባሪያሽ ነኝ
ከእንግዲህስ ወዲያ....
ለተገፋው ልቤ ለተንሰፈሰፈው
ለገፋሽው ቀልቤ ባዶ ላስቀረሽው
ካሳም አልጠይቅሽ እሽ የሚል ምላሽ
ቅመሽው አልልም ባንቺ ይድረስብሽ
ግን ግን ቅሬታ አለኝ የምፀልይልሽ
የእኔ ዓይነት አፍቃሪ መቼም እንዳይሰጥሽ
@gitm_post
♡ ㅤ ❍ㅤ ⌲
ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢʰᵃʳᵉ
Уже доступно! Исследование Telegram 2025 — ключевые инсайты года 
