ru
Feedback

Не попадитесь на канал ботавода! Telemetrio находит и помечает такие каналы 👉 Хотите видеть метку — оформите подписку

Yekatit 12 Hospital for Community

Yekatit 12 Hospital for Community

Открыть в Telegram
4 272
Подписчики
+724 часа
+777 дней
+32030 дней
Архив постов
photo content
+9

ወርቃማው ሰኞ፦ የጡት ካንሰር ግንዛቤን ለማሳደግ ሳይንሳዊ ውይይትና የምርመራ ጥሪ ቀረበ በየካቲት 12 ሆስፒታል ሜዲካል ኮሌጅ የሚካሄደው ሳምንታዊው የወርቃማው ሰኞ የዕውቀትና የልምድ ልውውጥ መድረክ፣ የጡት ካንሰር ግንዛቤን በማሳደግና ቀድሞ የምርመራ አስፈላጊነትን በማጉላት ተካሂዷል። በመርሃ ግብሩ ላይ የየካቲት 12 ሆስፒታል ሜዲካል ኮሌጅ ዋና ፕሮቮስት ዶክተር አበበ ታደሰ፣ የሕክምና አገልግሎት አሰጣጥ ኃላፊ ዶክተር መአዛ ሮሪሳ፣ የአካዳሚክና ምርምር ምክትል ፕሮቮስት ዶክተር ዱቤ ጃራ፣ የሜዲካል ኮሌጁ ዲንና የጡት እና ኢንዶክራይን ሰብስፔሻሊስት ዶክተር ወንድወሰን አምታታው፣ የክፍል ኃላፊዎች፣ የቡድን መሪዎችና ሌሎች የተቋሙ ሠራተኞች ተሳትፈዋል። የመክፈቻ ንግግሩን ያደረጉት ዶክተር ዱቤ ጃራ፣ ተሳታፊዎችን በደህና መጡ በማለት ከተቀበሉ በኋላ፣ ወርቃማው ሰኞ እንደዚህ ያሉ የውይይት፣ የመማማርና የዕውቀት ልውውጥ መድረኮችን በማመቻቸት ለተቋሙ የሙያ እድገትና የተቀጣይ ትምህርት አስፈላጊ ሚና እየተወጣ መሆኑን አድንቀዋል። በመቀጠልም የዕለቱ አቅራቢ የሆኑት ዶክተር ወንድወሰን አምታታው፣ ስለ ጡት ካንሰር በሳይንሳዊ መረጃዎች የተደገፈና በፓወርፖይንት ስላይዶች የታገዘ ሰፊ ማብራሪያ ሰጥተዋል። በገለጻቸውም የጡት ካንሰርን በተመለከተ የሳይንሳዊ ዕውቀትን ማሳደግና በተገቢው ጊዜ ምርመራ ማድረግ ያለውን ጠቀሜታ አብራርተዋል። በተጨማሪም፣ የጡት ካንሰር ግንዛቤ ማስጨበጫ ወርን አስመልክቶ፣ የሚመለከታቸው የተቋሙ ሠራተኞችና ተገልጋዮች በየካቲት 12 ሆስፒታል ሜዲካል ኮሌጅ የሚሰጠውን የምርመራ አገልግሎት እንዲጠቀሙ ጥሪ ቀርቧል። በመቀጠልም ዶክተር ጽዮን ዘብድዮስ፣ ምርመራው የሚመለከታቸው አካላት ከጥቅምት 16 እስከ 30 ድረስ የጡትና የማኅጸን በር ካንሰር ምርመራ እንዲያደርጉ አሳስበዋል። በመዝጊያ ንግግራቸው የሆስፒታሉ ዋና ፕሮቮስት ዶክተር አበበ ታደሰ፣ ዶክተር ወንድወሰን አምታታው ያቀረቡትን ሳይንሳዊና ጥልቅ ገለጻ አድንቀዋል። በተጨማሪም ለመድረኩ የተገኙትን ተሳታፊዎች አመስግነው፣ ምርመራው የሚመለከታቸው ሁሉ በወቅቱ ምርመራ በማድረግ ለጤናቸው ቅድሚያ እንዲሰጡ አሳስበዋል። የዕለቱ ወርቃማው ሰኞ በሳይንሳዊ ዕውቀት ልውውጥ፣ በግንዛቤ ማሳደግና በቀድሞ ምርመራ አስፈላጊነት ላይ በተደረገ ማሳሰቢያ ተጠናቋል። 📍 የካቲት 12 ሆስፒታል ሜዲካል ኮሌጅ ኮሚኒኬሽን 📅 ጥቅምት 16/2019 ዓ.ም 📍 📌 Follow Us on Social Media 👉 Facebook: https://www.facebook.com/profile.php?id=100063650457050 👉 Telegram: Join Our Channel https://t.me/Y12HMCC 👉 Follow us on tiktok https://vm.tiktok.com/ZMHWJyPGKQmQp-dftjE 🔖 #Y12HMC 💛✨ #Yekatit12HospitalMedicalCollege #GoldenMonday #BreastCancerAwareness #EarlyDetection #HealthResearch

በየካቲት 12 ሆስፒታል ሜዲካል ኮሌጅ የማህፀን በር ጫፍ ቅድመ ካንሰር ምርመራ እና የጡት ቅድመ ካንሰር ምርመራ ከዛሬ ጀምሮ ማለትም 16/2/2019 ዓ.ም እስከ 20/2019 ዓ.ም እድሜያቸው 25-4
በየካቲት 12 ሆስፒታል ሜዲካል ኮሌጅ የማህፀን በር ጫፍ ቅድመ ካንሰር ምርመራ እና የጡት ቅድመ ካንሰር ምርመራ ከዛሬ ጀምሮ ማለትም 16/2/2019 ዓ.ም እስከ 20/2019 ዓ.ም እድሜያቸው 25-49 የሆናቹ የተቋማችን ሰራተኞች ተገልጋዮች በተቋማችን የካቲት 12 ሆስፒታል ሜዲካል ኮሌጅ የአገልግሎቱ ተጠቃሚ እንድትሆኑ በአክብሮት እንጠይቃችኋለን።

photo content
+6

አበበች ጎበና ሆስፒታል በIPC እና በታካሚዎች ደህንነት ዘርፍ ጥሩ አፈጻጸም ላሳየው ኒዮናታል ዋርድ እውቅና ሰጠ ጥቅምት 13/2019 ዓ.ም. በኢንፌክሽን መከላከልና ቁጥጥር (Infection Prevention and Control – IPC) እና በታካሚዎች ደህንነት (Patient Safety) ዘርፎች አበረታች አፈጻጸም ላሳዩ ክፍሎች የእውቅናና የሽልማት ሥነ-ሥርዓት ተካሂዷል። በዚሁ መርሃ ግብር በአበበች ጎበና የእናቶችና ሕፃናት ሆስፒታል የሚገኘው ኒዮናታል ዋርድ በሁለቱም ዘርፎች ባሳየው ጥሩ አፈጻጸም ሽልማት ተበርክቶለታል። የሽልማት ሥነ-ሥርዓቱን የከፈቱት የሆስፒታሉ የኒዮናታል ዲፓርትመንት ኃላፊ ዶ/ር ሰላማዊት አሰፋ ሲሆኑ፣ ኒዮናታል ዋርድ ለተለየ እንክብካቤ የሚፈልጉ አራስ ሕፃናትን የሚያገለግል በመሆኑ በሁሉም የአገልግሎት አሰጣጥ ሂደቶች ላይ ቅድሚያ ሊሰጠው እንደሚገባ አጽንኦት ሰጥተዋል። ዶ/ር ሰላማዊት እንደገለጹት፣ ኢንፌክሽንን መከላከልና መቆጣጠር እንዲሁም የታካሚዎችን ደህንነት ማረጋገጥ በጤና አገልግሎት ውስጥ ከፍተኛ ትኩረት ሊሰጣቸው የሚገቡ ተግባራት ናቸው። ኒዮናታል ዋርድም በእነዚህ ዘርፎች በየቀኑ የሚከናወኑ ተግባራትን በጥራት እያከናወነ እንደሚገኝ በመግለጽ፣ የተሻሉ አፈጻጸሞችን ማወቅ፣ ማበረታታትና እውቅና መስጠት ለቀጣይ ስኬት ወሳኝ መሆኑን አስረድተዋል። የሽልማት ሥነ-ሥርዓቱን የዘጉት የሆስፒታሉ የሕክምና ዳይሬክተር ዶ/ር አህመድ እባቡ ናቸው። ዶ/ር አህመድ እውቅና የሚሰጠው ጥሩ አፈጻጸም ያሳዩ ሠራተኞችንና ክፍሎችን ለማመስገን ብቻ ሳይሆን፣ ለቀጣይ ሥራ ተነሳሽነትን ለመፍጠርና የሥራ ባህልን ለማጠናከርም እንደሆነ ገልጸዋል። በተጨማሪም ሆስፒታሉ በኢንፌክሽን መከላከልና ቁጥጥር እንዲሁም በታካሚዎች ደህንነት ላይ ትኩረት ሰጥቶ እየሠራ መሆኑን በማስታወስ፣ ጥሩ አፈጻጸም ያሳዩ ዋርዶችን ማበረታታት ሌሎች ክፍሎች ከተሞክሮዎቻቸው እንዲማሩ፣ የተሻሉ አሠራሮችን እንዲቀስሙና በጋራ የጤና አገልግሎት ጥራትን እንዲያሻሽሉ እንደሚያግዝ አመልክተዋል። በመጨረሻም የኒዮናታል ዋርድ አስተባባሪ አቢይ፣ ለዋርዱ ሥራ እውቅና መሰጠቱ ታላቅ ደስታና ኩራት እንደፈጠረላቸው ገልጸዋል። ይህ ዓይነቱ እውቅና በቀጣይም በበለጠ ትጋት፣ ቁርጠኝነትና ኃላፊነት እንዲሠሩ ትልቅ ተነሳሽነት እንደሚፈጥርላቸው በመግለጽ፣ ለሰጣቸው እውቅና አመስግነዋል። ይህ የእውቅና መርሃ ግብር በIPC እና በታካሚዎች ደህንነት ዘርፎች የተሻሉ አሠራሮችን በማበረታታት፣ የጥራት ባህልን በማጠናከርና ለታካሚዎች ደህንነት የተሻለ የጤና አገልግሎት ለማረጋገጥ ያለውን የሆስፒታሉን ቁርጠኝነት የሚያሳይ ነው።

Announcement: Extension of application call for post-basic degree programs
+1
Announcement: Extension of application call for post-basic degree programs

List of postgraduate applicants for Written exam.pdf8.12 MB

photo content
+2

ልሳን ዘየካቲት የደኅንነት ሥርዓቱን ለማጠናከር የሰርቪላንስ ካሜራ ቁጥጥር ሥልጠና ተሰጠ የካቲት 12 ሆስፒታል ሜዲካል ኮሌጅ ጥቅምት 10/2019 ዓ.ም የየካቲት 12 ሆስፒታል ሜዲካል ኮሌጅ የደኅንነት ሥርዓቱን ለማጠናከር እና የተቋሙን ንብረት ለመጠበቅ የሚያስችል የሰርቪላንስ ካሜራ ቁጥጥር ሥልጠና ተሰጠ ሆስፒታሉ ከኢትዮ ቴሌኮም ጋር በገባው ውል መሠረት ለተቋሙ ደኅንነት የሚያገለግሉ ወደ 80 የሚጠጉ የተለያዩ ሦስት ዓይነት የውስጥና የውጭ ሰርቪላንስ ካሜራዎችን ከNVR /Network Video Recorder/ ሥርዓት ጋር ማስገጠሙ ይታወቃል ይህንኑ ዘመናዊ የደኅንነት መሣሪያ በብቃት መቆጣጠርና መጠቀም እንዲቻል ለአምስት የካሜራ ቁጥጥር ባለሙያዎች በኢትዮ ቴሌኮም ባለሙያዎች የቲዎሪና የተግባር /Theory and Practical/ ሥልጠና በትላንትናው ዕለት በ9/2/2019 ዓ.ም ተሰጥቷል ሥልጠናውም የካሜራዎቹን አጠቃቀም፣ የክትትል ሥርዓቱን አሠራርና የቁጥጥር አቅምን ለማሳደግ ያለመ ነው በቅርበት ያገኘናቸው የአይቲ ክፍል አስተባባሪ አቶ በቃቢል በፈቃዱ እንደገለጹት፣ የአይቲ ክፍሉ ከሲስተሙ መሠረተ ልማት ጋር ተያይዞ የራሱ የሆነ ወሳኝ ሚና አለው በተቋሙ ውስጥ ከሠራተኞችና ከተማሪዎች በተጨማሪ አስታማሚዎች፣ ጠያቂዎችና የተለያዩ አገልግሎቶችን ለማግኘት የሚመጡ ሰዎች የሚገኙ በመሆኑ፣ የሰዎችንና የንብረትን ደኅንነት ለማረጋገጥ የተሟላ ቁጥጥር ማድረግ እንደሚያስፈልግ አስገንዝበዋል አቶ በቃቢል አክለውም፣ የተቋሙን ንብረት ከመጥፋትና ከሌሎች የደኅንነት ችግሮች ለመጠበቅ፣ ዘመናዊውን የክትትል መሣሪያ በአግባቡ መጠቀምና የሚመለከታቸው አካላት በቅንጅት አስፈላጊውን ክትትል ማድረግ እንደሚገባ ጠቁመዋል በአጠቃላይ፣ የሰርቪላንስ ካሜራ ቁጥጥር ሥልጠናው የሆስፒታሉን የደኅንነት አቅም ከማጠናከር ባሻገር፣ የሠራተኞችን፣ የተገልጋዮችንና የተቋሙን ንብረት ጥበቃ ለማሻሻል አስፈላጊ አስተዋጽኦ ያበረክታል 📍 የካቲት 12 ሆስፒታል ሜዲካል ኮሌጅ ኮሙኒኬሽን 📌 Follow Us on Social Media 👉 Facebook: https://www.facebook.com/profile.php?id=100063650457050 👉 Telegram: Join Our Channel https://t.me/Y12HMCC 👉 Follow us on tiktok https://vm.tiktok.com/ZMHWJyPGKQmQp-dftjE 🔖 #Y12HMC 💛

photo content
+4

ልሳን ዘየካቲት ደኅንነቱን የጠበቀ ጉዞ፥ኃላፊነት የተሞላበት ሹፌር ለራስ፣ ለተቋምና ለሕዝብ ደኅንነት የተደረገ የሹፌሮች የሙያ ሥልጠና የካቲት 12 ሆስፒታል ሜዲካል ኮሌጅ ጥቅምት 7/2019 ዓ.ም ዕለተ ቅዳሜ ሹፌሮች በሥራቸው የሚጠበቅባቸውን ኃላፊነት በተገቢው እንዲወጡ፣ የሥራ ሂደታቸውንና የተቋሙን መዋቅር ጠብቀው እንዲሠሩ፣ የትራፊክ አደጋን በመከላከል የራሳቸውን፣ የተሳፋሪዎችንና የሕዝብን ደኅንነት እንዲጠብቁ ያለመ የሥራ ላይ ሥልጠና ተካሄደ ሥልጠናው ሹፌሮች በየዕለቱ የሚያከናውኑትን ተግባር በተሻለ ግንዛቤ፣ በሙያዊ ብቃትና በኃላፊነት እንዲፈጽሙ ለማገዝ ያለመ ሲሆን፥ በፕሮጀክተር በተደገፉ ምስሎችና ማብራሪያዎች የተለያዩ የሥራ ሁኔታዎችና የአደጋ መከላከያ ዘዴዎች ቀርበዋል 🎯 የሥልጠናው ዋና ዋና ዓላማዎች ሥልጠናው በዋናነት፦ ሹፌሮች የተቋሙን መዋቅር፣ የሥራ ሂደትና የሪፖርት አሰጣጥ ሥርዓት ጠብቀው እንዲሠሩ፤ የዕለቱን ሥራ በቅድመ ዝግጅትና በተገቢ የጊዜ አጠቃቀም እንዲጀምሩ፤ ተሽከርካሪዎችን በየዕለቱ ከማሽከርከራቸው በፊት በመመርመር የቴክኒክ ብልሽትና የአደጋ ምክንያቶችን ቀድመው እንዲለዩ፤ የትራፊክ ሕጎችን በማክበር በጥንቃቄና በሙያዊ ሥነ-ምግባር እንዲያሽከረክሩ፤ ራሳቸውን፣ ተሳፋሪዎችንና ሌሎች የመንገድ ተጠቃሚዎችን ከአደጋ እንዲጠብቁ፤ የተሰጣቸውን ኃላፊነት በታማኝነት፣ በተጠያቂነትና በትብብር እንዲወጡ ማስቻል ነው የአንድ ሹፌር የቀን የመጀመሪያ ሥራው ምንድን ነው? በሥልጠናው አጽንዖት ከተሰጣቸው ጉዳዮች መካከል አንዱ ሹፌሮች የዕለቱን ሥራ እንዴት መጀመር እንዳለባቸው ነው አንድ ሹፌር የቀኑን ሥራ ሲጀምር፦ በሰዓቱ በሥራ ቦታ መገኘት፤  የተመደበለትን የዕለቱን ተግባር ከኃላፊው ማረጋገጥ፤  የተሽከርካሪውን ጎማ፣ ፍሬን፣ መብራት፣ መሪ፣ የፈሳሽ መጠኖችና ሌሎች የደኅንነት ክፍሎችን መፈተሽ፤ የተሽከርካሪውን ሰነዶችና አስፈላጊ የደኅንነት መሣሪያዎች ማረጋገጥ፤  ማንኛውም ብልሽት ወይም የደኅንነት ችግር ሲያጋጥም ለሚመለከተው ኃላፊ ማሳወቅ የተሽከርካሪ ቅድመ ምርመራ የጊዜ ማባከን ሳይሆን ሕይወትን የሚታደግ የደኅንነት ባህል ነው ራስንና ሕዝብን ከአደጋ መጠበቅ በሥልጠናው ሹፌሮች ሲያሽከረክሩ የትራፊክ ሕጎችን ማክበር፣ በተፈቀደው ፍጥነት መጓዝ፣ የመንገድና የአየር ሁኔታን መገምገም፣ ከሌሎች ተሽከርካሪዎች ተገቢውን ርቀት መጠበቅና ለእግረኞች ቅድሚያ መስጠት ያለው ጠቀሜታ ተገልጿል በተጨማሪም በማሽከርከር ጊዜ ሞባይል ስልክን አለመጠቀም፣ ከድካምና ከእንቅልፍ ማጣት ጋር አለማሽከርከር፣ በአልኮል ወይም በአደንዛዥ ዕፅ ተጽዕኖ ሥር ሆኖ ተሽከርካሪ አለመንዳት እና በድንገተኛ ሁኔታዎች በተረጋጋ ሁኔታ ምላሽ መስጠት የሹፌር የዕለት ተዕለት ኃላፊነቶች መሆናቸው ተጠቁሟል የሹፌር ሙያ መኪናን ከአንድ ቦታ ወደ ሌላ ማድረስ ብቻ ሳይሆን፣ ሕይወትን በኃላፊነት መጠበቅም ነው የሠልጣኞች አስተያየት በሥልጠናው የተሳተፉ ሹፌሮች በተዘጋጀላቸው የሥራ ላይ ሥልጠና ደስተኛ መሆናቸውን ገልጸዋል እንደ አስተያየታቸውም፣ እንዲህ ያሉ አጫጭርና ተከታታይ ሥልጠናዎች የሙያ ክህሎታቸውን ለማሳደግ፣ በሥራ ላይ የሚያጋጥሟቸውን ችግሮች በተሻለ ሁኔታ ለመፍታትና ከአደጋ የጸዳ አገልግሎት ለመስጠት ከፍተኛ ጠቀሜታ አላቸው ሠልጣኞቹም ይህ ተግባር አስፈላጊና ጠቃሚ መሆኑን በመግለጽ፣ ተመሳሳይ ሥልጠናዎች በተደጋጋሚ ቢሰጡና የሙያ እውቀታቸውን የሚያሳድጉ ውይይቶች ቢቀጥሉ ያላቸውን ፍላጎት አሳይተዋል ቀጣይ ትኩረት፦ በየዕለቱ መማር፣ በየዕለቱ መጠንቀቅ! የሹፌሮች የሥራ ላይ ሥልጠና በአንድ ቀን የሚያበቃ ተግባር ሳይሆን፣ በተከታታይ በሚሰጡ አጫጭር ሥልጠናዎች፣ በልምድ ልውውጥና በተግባር ላይ በተመሠረቱ ውይይቶች መጠናከር ያለበት ሂደት ነው። በዚህም ሹፌሮች የተቋሙን መዋቅርና የሥራ ሥርዓት በማክበር፣ የተሰጣቸውን ኃላፊነት በታማኝነት በመወጣትና ለሕዝብ ደኅንነት ቅድሚያ በመስጠት የተሻለ የሥራ አፈጻጸም እንዲያሳዩ ይጠበቃል ደኅንነት ምርጫ አይደለም፤ ኃላፊነት ነው ሲሉም የንብረት አስተዳደር ጠቅላላ አገልግሎት ዳይሬክተር  የሆኑት አቶ ናትናኤል ታደሠ ተደምጠዋል በጥንቃቄ እናሽከርክር፤ ሕይወትን እንጠብቅ! ሠናይ ቀን! 📍 የካቲት 12 ሆስፒታል ሜዲካል ኮሌጅ ኮሚኒኬሽን 📌 Follow Us on Social Media 👉 Facebook: https://www.facebook.com/profile.php?id=100063650457050 👉 Telegram: Join Our Channel https://t.me/Y12HMCC 👉 Follow us on tiktok https://vm.tiktok.com/ZMHWJyPGKQmQp-dftjE 🔖 #Y12HMC 💛✨

photo content

photo content

photo content
+7

በአበበች ጎበና እናቶችና ሕፃናት ሆስፒታል የወርቃማው ሰኞ ፕሮግራም ተካሄደ በአበበች ጎበና እናቶችና ሕፃናት ሆስፒታል የወርቃማው ሰኞ (Golden Monday) ፕሮግራም ተካሄደ። ፕሮግራሙ በእናቶች ጤና ዙሪያ ያለውን ግንዛቤ ለማሳደግ፣ ልምድና ዕውቀትን ለመለዋወጥ እንዲሁም የጤና ባለሙያዎችን የሙያ አቅም ለማጠናከር ያለመ የመማማርያ መድረክ ነበር። ፕሮግራሙን በይፋ የከፈቱት ዶ/ር ብርሃኑ ከበደ፣ የፌቶ-ማተርናል ሰብ-ስፔሻሊስት እና የተቋሙ የፌቶ-ማተርናል ትምህርት ክፍል ኃላፊ ናቸው። በመቀጠል ዶ/ር ኦልያድ ለሜሳ የወርቃማው ሰኞ ፕሮግራምን አስመልክቶ የተለያዩ የእናቶች ጤና ጉዳዮችን የሚዳስሱ የኬዝ ሴናሪዮዎችን በማቅረብ ተሳታፊዎች በጉዳዮቹ ላይ እንዲወያዩ፣ ልምዳቸውን እንዲለዋወጡና ከተግባራዊ ሁኔታዎች እንዲማሩ ዕድል ፈጥረዋል። ይህም በእናቶች ጤና አገልግሎት አሰጣጥ ዙሪያ የጋራ ግንዛቤን ለማጎልበት አስተዋጽኦ አድርጓል። በፕሮግራሙ መጨረሻ የአበበች ጎበና እናቶችና ሕፃናት ሆስፒታል ኃላፊ ዶ/ር ወገኔ አሰፋ የወርቃማው ሰኞ ፕሮግራምን አስመልክቶ ለተቋሙ ሠራተኞች መልዕክት አስተላልፈዋል። በእናቶች ጤና ዘርፍ የሚሰጠውን አገልግሎት በዕውቀት፣ በሙያዊ ትብብርና በተከታታይ ትምህርት ማጠናከር ያለውን አስፈላጊነት የሚያጎላ መልዕክት አስተላልፈዋል። የወርቃማው ሰኞ ፕሮግራም የጤና ባለሙያዎች በእናቶች ጤና ላይ ያላቸውን ዕውቀት እንዲያጎለብቱ፣ በሙያዊ ልምድ እንዲለዋወጡና ለእናቶች የሚሰጠውን የጤና አገልግሎት ጥራት እንዲያሻሽሉ የሚያግዝ የትምህርትና የልምድ ልውውጥ መድረክ ነው።

FINAL_RESULT_of_MD_accepted_list_for_2026_2027_Academic_Year_for.pdf4.34 MB

ለየካቲት 12 ሆስፒታል ሜዲካል ኮሌጅ የሕክምና ዶክተሬት (MD) ትምህርት ተወዳድራችሁ ለተመረጣችሁ ተማሪዎች በሙሉ 🎉 እንኳን ደስ አላችሁ! የመግቢያ ፈተናውንና አጠቃላይ የምደባ ሂደቱን ላጠናቀቃችሁ ተወዳዳሪዎች በሙሉ፣ ውጤታችሁን እና ተጨማሪ መረጃዎችን በሚከተለው የቴሌግራም ቻናል ማየት ትችላላችሁ። 📲 የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ። 👇👇 🔗 https://t.me/Y12HMCC 🎓 የምዝገባ ቀን ጥቅምት 20-21/2019                                                                                                                                                           🎓 የትምህርት መጀመሪያ ቀን፦ ጥቅምት 23/2019 ዓ.ም. 📋 ለምዝገባ ስትመጡ ማሟላት ያለባችሁ መስፈርቶች፦ 1️⃣ አራት (4) የፓስፖርት መጠን ፎቶግራፎች። 2️⃣ በሥራ ላይ የነበራችሁ ተወዳዳሪዎች የሥራ መልቀቂያ ደብዳቤ። 3️⃣ የትምህርት ማስረጃዎች ዋናው እና ፎቶኮፒውን፦ የ8ኛ ክፍል የሚኒስትሪ ውጤት የ11ኛ እና የ12ኛ ክፍል ትራንስክሪፕት የ12ኛ ክፍል ማጠናቀቂያ ውጤት የዲግሪ ማስረጃ እና የተማሪ ቅጂ (Student Copy) ⚠️ ማሳሰቢያ፦ ቅሬታ ያላችሁ ተወዳዳሪዎች በጥቅምት 9 እና 10/2019 ዓ.ም. በሬጅስትራር ቢሮ በአካል በመቅረብ ቅሬታችሁን ማቅረብ እና ውጤታችሁን ማየት ትችላላችሁ። 🙏 ለተመረጣችሁ ተማሪዎች በሙሉ መልካም የትምህርት ዘመን እንመኛለን! የየካቲት 12 ሆስፒታል ሜዲካል ኮሌጅ #Yekatit12HospitalMedicalCollege #MDAdmission #Registration #MedicalEducation

Scan_16_Oct_2023.pdf5.69 MB

📢 ለየካቲት 12 ሆስፒታል ሜዲካል ኮሌጅ የሕክምና ዶክተሬት (MD) ትምህርት ተወዳድራችሁ ለተመረጣችሁ ተማሪዎች በሙሉ 🎉 እንኳን ደስ አላችሁ! የመግቢያ ፈተናውንና አጠቃላይ የምደባ ሂደቱን ላጠናቀቃችሁ ተወዳዳሪዎች በሙሉ፣ ውጤታችሁን እና ተጨማሪ መረጃዎችን በሚከተለው የቴሌግራም ቻናል ማየት ትችላላችሁ። 📲 የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ። 👇👇 🔗 https://t.me/Y12HMCC 🎓 የትምህርት መጀመሪያ ቀን፦ ጥቅምት 29/2019 ዓ.ም. 📋 ለምዝገባ ስትመጡ ማሟላት ያለባችሁ መስፈርቶች፦ 1️⃣ አራት (4) የፓስፖርት መጠን ፎቶግራፎች። 2️⃣ በሥራ ላይ የነበራችሁ ተወዳዳሪዎች የሥራ መልቀቂያ ደብዳቤ። 3️⃣ የትምህርት ማስረጃዎች ዋናው እና ፎቶኮፒውን፦ የ8ኛ ክፍል የሚኒስትሪ ውጤት የ11ኛ እና የ12ኛ ክፍል ትራንስክሪፕት የ12ኛ ክፍል ማጠናቀቂያ ውጤት የዲግሪ ማስረጃ እና የተማሪ ቅጂ (Student Copy) ⚠️ ማሳሰቢያ፦ ቅሬታ ያላችሁ ተወዳዳሪዎች በጥቅምት 19 እና 20/2019 ዓ.ም. በሬጅስትራር ቢሮ በአካል በመቅረብ ቅሬታችሁን ማቅረብ ትችላላችሁ። 🙏 ለተመረጣችሁ ተማሪዎች በሙሉ መልካም የትምህርት ዘመን እንመኛለን! የየካቲት 12 ሆስፒታል ሜዲካል ኮሌጅ #Yekatit12HospitalMedicalCollege #MDAdmission #Registration #MedicalEducation

photo content