ru
Feedback

Не попадитесь на канал ботавода! Telemetrio находит и помечает такие каналы 👉 Хотите видеть метку — оформите подписку 👈

የገ/ጉ/ወ/ወ/የመ/ኮ/ጉ/ጽ/ቤት

የገ/ጉ/ወ/ወ/የመ/ኮ/ጉ/ጽ/ቤት

Открыть в Telegram
925
Подписчики
Нет данных24 часа
+37 дней
+730 дней
Архив постов
ህዳር 4/2018 ዓ.ም በጉራጌ ዞን በገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ በዘር ከተሸፈነው 13 ሺህ 8 መቶ 89 ሄክታር መሬት ማሳ 795 ሺህ 426 ኩንታል ምርት እንደሚጠበቅ ተገለጸ። ፨፨፨፨፨///፨፨፨፨፨ በጉራጌ ዞን በገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ በዘር ከተሸፈነው 13ሺህ 8 መቶ 89 ሄክታር መሬት ማሳ 795 ሺህ 426 ኩንታል ምርት እንደሚጠበቅ ተገለጸ። የገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ሚፍታ ሁሴን እንዳሉት በግብርና ዘርፍ የአርሶአደሩ ምርትና ምርታማነት ለማሳደግ በርካታ ስራዎች እየተሰራ እንደሆነ ተናግረዋል። በወረዳው በበልግ በመኽርና በመስኖ ልማት የተለያዩ ሰብሎች በሰፊው የሚለማ እንደሆነም አመላክተው በመኽር 13 ሺህ 889 ሄክታር መሬት በገብስ ፣በስንዴ፣ አተር ባቄላና ሌሎችም ሰብሎች ማልማት ተችሏል ብለዋል። ቀደም ሲል የማይለሙ የነበሩ ማሳዎች ለማልማት ታቅዶ እየተሰራ እንደሆነም ያብራሩት ሀላፊው በአርሶአደርና በተቋማት ደረጃና የተለያዩ የሴቶችና የወጣቶች አደረጃጀት በመፍጠር በተሰራ ስራ በተጨባጭ ውጤት እየታየ እንደሆነም ተናግረዋል። በሁሉም ቀበሌዎች ሰፋፊ መሬቶች በኩታገጠም እየለማ ሲሆን ምርቶች ወደ ተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች በመላክና የገበያ ትስስር ተፈጥሮላቸው እየሸጡ ተጠቃሚነታቸው እየተሰጋገጠ እንደሆነም አስረድተዋል። በተቋማት ደረጃ በተለይም በትምህርት ተቋማቶች አካባቢ ከዚህ በፊት ሰፋፊ ማሳዎች በዛፍ ተይዘው የነበረና ዛፎችን በማንሳት ሰብል የማልማት ስራ እየተሰራና በዚህም በተጨባጭ ውጤት እየመጣ ነው ብለዋል። በግብርናው ዘርፍ የአርሶአደሩ ተጠቃሚነት ከጊዜ ወደ ጊዜ እያደገ መምጣቱም የተናገሩት አቶ ሚፍታ አሁን ላይ አርሷአደሩ በስፋት መሬቱን እያለማ ይገኛል ብለዋል። በአምና ደረጃ የግብአት ውስንነት በወረዳው ይስተዋል የነበረና ይህንንም ችግር ለመቅረፍ የዞኑ ግብርና መምሪያ በግብአት አቅርቦት ልዩ እገዛ እንዳደረገላቸውም አስታውሰዋል። የገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ ግብርና ልማት ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ከድር መርጋ እንዳሉት በወረዳው በሰብል ምርት ላይ የአርሶአደሩ ምርትና ምርታማነት ለማሳደግ በትኩረት እየተሰራ ይገኛል። በዘንድሮ አመት የማሳ ሽፋን ከ1035 ሄክታር በላይ የጨመረበት አግባብ መኖሩም ተናግረው የማሳ ሽፋኑ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረና የአርሶአደሩ ሜካናይዜሽን የመጠቀም ባህሉ እያደገ እንደሆነ አስረድተዋል። በዘር ከተሸፈነው 13ሺህ 8 መቶ 89 ሄክታር መሬት ማሳ 795 ሺህ 426 ኩንታል ምርት እንደሚጠበቅ ያመላከቱት ሀላፊው በወረዳው የሚገኙ 80 ፐርሰንት የሚሆኑ አርሶአደሮች በመኽር ወቅት በስፋት የሚያለሙ እንደሆነም ተናግረው በዘር ከተሸፈነው ማሳ 34 ፐርሰንቱ በስንዴ ዘር መሸፈኑና ቀሪው መሬት በገብስ ፣በጥራጥሬና በሌሎችም ሰብሎች የተሸፈነ እንደሆነም አመላክተዋል። ከወልቂጤ ግብርና ምርምር ማዕከል ጋር በጋራ በመሆን የተሻሻሉ ስንዴ ዝርያ በተለያዩ በቀሌዎች በመዝራት ውጤት አመት የመጣ እንደሆነም አስረድተዋል። በወረዳው በአንዳንድ ቀበሌዎች ያነጋገርናቸው አርሶ አደሮች እንደሚሉት ማሳቸው በኩታ ገጠም በማልማታቸው የተሻለ ምርት እንደሚያገኙና ምርትና ምርታማነታቸው እንደሚጨምርም አስረድተዋል።

ህዳር 04/2018 ዓ.ም የኢንጌ እና ወለጋዲሴ ማዘጋጃ ቤቶች የሊዝ ጨረታ ማስታወቂያ  የወለጋዲሴ ማዘጋጃ ቤት  የሊዝ የመሬት ጨረታ  ይመለከታል 1.የንግድ ብዛት 7 የጨረታ ሰነድ መግዥያ ዋጋ 600 የሊዝ መናሻ ዋጋ 570 2.የመኖራያ  ብዛት 14 የጨረታ ሰነድ መግዥያ ዋጋ 500 የሊዝ መናሻ ዋጋ 107.5   ሲሆን $.ጨረታው የሚጀመርበት በቀን 01/ 03/2018 ዓ.ም $.ጨረታው የሚዘጋበት /የሚያልቅበት በቀን 12/03/2018 ዓ.ም እስከ 11:00 ሰዓት ነው። $.የጨረታው አሸናፊ የሚለይበት 15/03/2018 ዓ.ም መሆኑን እናሳውቃለን!!! የኢንጌ ማዘጋጃ  የከተማ መሬት የሊዝ ጨረታ ማስታወቂያ   ማዘጋጃ ቤቱ 22  እጣዎች የመኖሪያ ቦታ ያዘጋጀ ሲሆን የጨረታ ሰነድ የሚሸጥበት ጊዜ 02/03/18 እስከ15/03/2018 ቢሮ ቁጥር 02 በመምጣት የማይመለስ 500 ይዘው በመቅረብ በስራ ሰዓት መግዛት የሚቻል መሆኑን እያሰወቅን የጨረታ ሳጥን የሚታሸገው በቀን 15/03/18 ከቀኑ 11:30 ሲሆን የጨረታ ሳጥን የሚከፈተው 16/03/2018 ከጠዋቱ 3:00 መሆኑን እናሳውቃለን!!! ለበለጠ መረጃ ከዚህ በታች ያለው መረጃ  ይመልከቱ፦

ህዳር 04/2018 ዓ.ም የጉራጌ ዞን አስተዳደር ወቅታዊ የንቅናቄ ተግባራት አፈፃፀም በወልቂጤ ከተማ እየተገመገመ ይገኛል። ፨፨፨፨፨///፨፨፨፨፨ የጉራጌ ዞን ዋና አስተዳዳሪ ክቡር አቶ ላጫ ጋሩማ በተገኙበት ወቅታዊ የልማትና ሌሎች የንቅናቄ ስራዎች ላይ ትኩረት ያደረገ የውይይት መድረክ እየተገመገመ ይገኛል። በግብርና ፣በከተማ ልማት ኮንስትራክሽን፣ በገቢ፣ በአንድ ከተማ የአንድ ፕሮጀክት ኢኒሼቲቭ፣በገጠርና በከተማ የኮሪደር ልማትና በሌሎችም በወቅታዊ ስራዎች ላይ እየተሰሩ ያሉ ስራዎች ይበልጥ ለማጠናከር መሆኑን ተገልጿል። አሁን እየተሰራ ያለው የበጋ የመስኖ ስራችን ይበልጥ ማጠናከርና የደረሱ ሰብሎችን በወቅቱ መሰብሰብ እንደሚገባም በመድሩኩ ተመላክቷል። በመድረኩም የጉራጌ ዞን ዋና አስተዳዳሪ ክቡር አቶ ላጫ ጋሩማ፣የጉራጌ ዞን ዋና የመንግስት ተጠሪ አቶ አለማየሁ ገ/መስቀል፣የጉራጌ ዞን ምክትል አስተዳዳሪና ግብርና መምሪያ ኃላፊ አቶ አበራ ወንድሙ ጨምሮ የዞን መምሪያ የስራ ኃላፊዎች፣ የወረዳ ዋና አስተዳዳሪዎችና ከንቲባዎች ጨምሮ የሚመለከታቸው የጽ/ቤት ኃላፊዎች በመድረኩ እየተሳተፉ ይገኛል። መረጃው የጉራጌ ዞን ኮሚኒኬሽን መምሪያ ነው።

ህዳር 03/2018 ዓ.ም የመልካም አስተዳደር ችግሮችን በመቅረፍ የህብረተሰቡን ሁለንተናዊ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ እየሰራ መሆኑን የገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ አስተዳደር ፅ/ቤት አስታወቀ። ፨፨፨፨፨///፨፨፨፨፨ ፅ/ቤቱ የ2018 ዓ/ም የመጀመሪያ ሩብ ዓመት ዕቅድ አፈፃፀም የዜጎች ቻርተር እና የህዝብ ክንፍ መድረክ ዛሬ አካሂዶ ውሏል። በመድረኩ የፅ/ቤቱ ልማት ዕቅድ ባለሙያ አቶ መንሱር ብርሃኑ የ2018 ዓ/ም የመጀመሪያ ሩብ ዓመት ዕቅድ አፈፃፀም ሪፖርት አቅርበዋል። በውይይቱ ከተነሱት ሃሳብና አስተያየቶች መካከል ተቋሙ እያከናወናቸው ያሉ የልማትና መልካም አስተዳደር ስራዎች አበረታች ደረጃ ላይ መገኘታቸውን ጠቅሰው በአንፃሩ ኢንቨስትመንት ከማበረታታት ረገድ ሰፊ ስራ መሰራት እንዳለበት፣ ቅሬታዎችን ተቀብሎ ከመፍታት ረገድ ያለው አፈፃፀም የሚበረታታ ቢሆንም ፈጣን ምላሽ ከመስጠት አኳያ ያለው ክፍተት መታረም እንደሚገባው ያነሱት ተሳታፊዎቹ የመብራት እና የውሃ አገልግሎት መቆራረጥ እልባት ሊሰጠው እንደሚገባ፣ ጠንካራ የፕሮጀክቶች አፈፃፀም ክትትልና ቁጥጥር ስራን ጨምሮ ችግር ፈቺ የሆነ ወጥ የተቋማት ድጋፍና ክትትል ማድረግ እንደሚያሻ ተሳታፊዎች አንስተዋል። ለተነሱ ጥያቄዎችና አስተያየቶች ምላሽና ማብራሪያ የሰጡት የወረዳው አስተዳደር ፅ/ቤት ምክትል ኃላፊ አቶ ጅላሉዲን መሀመድ ከመድረክ ተሳታፊዎች የተሰጡ ግብዓቶችን በመውሰድ የቀጣይ የዕቅድ አካል ተደርጎ እንደሚሰራ ጠቅሰው መንግስት ኢንቨስትመንት ከማበረታታት ረገድ አፅንኦት ሰጥቶ እየሰራ መሆኑን በማንሳት ዘርፉንም ለማጎልበት ምቹ ሁኔታ ከመፍጠር አንስቶ አስፈላጊው ሁሉ ጥረት እየተደረገ ስለመሆኑ አብራርተዋል። አክለውም የሚነሱ ቅሬታዎች ፈጣን ምላሽ ለመስጠት የተጀመረው ርብርብ ተጠናክሮ የሚቀጥል መሆኑን በማንሳት በየደረጃው የሚገኙ አካላት እገዛ መጎልበት እንዳለበት አስገንዝበዋል።

ህዳር 03/2018 ዓ.ም ዓላማ ተኮር የህዝብ ግንኝነት በሚል መሪ ቃል በጉራጌ ዞን ገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ ብ/ፓርቲ ከባለድርሻ አካላት የውይይት መድረክ ተካሄዷል። ፨፨፨፨፨///፨፨፨፨፨ በመድረኩ የተገኙት የወረዳው ብ/ፓ/ቅ/ፅ/ቤት ኃላፊ አቶ አብድረሂም ርዳ እንደገለጹት ሚዲያ ለበጎ ስራ በመጠቀም ገዢ ትርክቶች ላይ ትኩረት በማድረግ የህዝቡ ሰላምና አንድነት ያጠናከረ በፓርቲ መሪነት የተከናወኑ የመንግስት ልማቶች እውነተኛና የተናበበ መረጃ ለህዝብ ተደራሽ መደረግ እንዳለበት ተናግረዋል። የውይይት መድረክ ሰነድ ያቀረቡት የወረዳው የመንግስት ረዳት ተጠሪና የፓለቲካና አቅም ግንባታ ዘርፍ ኃላፊ አቶ ሚፍታ አረቦ እንዳሉት ዓላማ ተኮር የህዝብ ግንኝነት ስራዎች በማጠናከር ሚዲያን ለበጎ ተግባር መጠቀም እንደሚገባ አስገንዝብዋል። ሌላው የተለያዩ የሚዲያ አማራጮችን በማስፋትና ተከታይ ቁጥር በማብዛት እውነተኛ መረጃ ለህዝቡ ተደራሽ ለማድረግ ሁሉም ባለድርሻ አካላት የድርሻቸውን ሊወጣ እንደሚገባም ተመላክቷል። መረጃው የወረዳው ብ/ፓ/ቅ/ፅ/ቤት ነው።

ህዳር 02/2018 ዓ.ም በጉራጌ ዞን ገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ እየተገነባ ያለው ከሼሽት ማዴ- አዳዘር ት/ት ቤት ባለው መንገድ ላይ የዳገት ቆረጣ ስራ እና የጠጠር ምርት ስራዎችን አስመልክቶ ከወረዳው ተወላጅ ባለሃብቶችና አመራሮች ጋር የመስክ ምልከታ በዛሬዉ ዕለት ተካሄደ። ፨፨፨፨፨///፨፨፨፨፨ በሳይት ምልከታውም በቀጣይ ተግባራዊ በሚደረጉ የትግበራ ምዕራፍ ላይ ማለትም ቀሪ የስትራክቸር እና ጠጠር ንጣፍ ስራዎች ላይ ውይይትና ምክክር በማድረግ የጋራ መግባባት ላይ መድረስ ተችሏል። በምልከታው ላይ የተገኙት የገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ሚፍታ ሁሴን እንደገለጹት መንገድ ለአንድ ህብረተሰብ ሁለንተናዊ ልማት የአንበሳዉን ድርሻ ይጫወታል። ከዚህ ረገድ በዘርፉ በተከናወኑ መጠነ-ሰፊ ስራዎች አበረታች የመንገድ መሰረተ-ልማት ዝርጋታ ማከናወን የተቻለ ቢሆንም በአንጻሩ መንግስት ተደራሽ ባልሆነባቸው የልማት መስኮች ላይ የባለሀብቱ ሚና ቀላል የሚባል እንዳልሆነ ገልጸዋል። የወረዳው ተወላጆች ከመንግስት ጎን በመሰለፍ የሚከናወኑ ሁለንተናዊ የልማት ስራዎች ለማገዝ እያደረጉት ያለውን ጥረት መንግስት እውቅና የሚሰጠው ስለመሆኑ ጠቅሰው ለስራው መሳካት መንግስት አስፈላጊውን እገዛ እንደሚያደርግ ገልጸዋል። አንዳንድ ተወላጆች በሰጡት አስተያየት በወረዳው በተመለከቱት የመንገድ መሰረተ-ልማት ዝርጋታ መደሰታቸውን ጠቅሰው በቀጣይ ተፈጻሚ የሚደረጉትን ከሼሽት ማዴ-  አዳዘር ት/ት ቤት የ7 ኪ/ሜትር ቀሪ የስትራክቸር እና ጠጠር ንጠፋ ስራዎች ባጠረ ጊዜ ለማጠናቀቅ አበክረው እንደሚሰሩ ገልጸዋል። የወረዳው የመንግስት ረዳት ተጠሪ አቶ ሚፍታ አረቦ በበኩላቸው የብልጽግና መንግስት በሁሉም መስኮች እያከናወናቸው ያሉ ዜጋ ተኮር የልማትና መልካም አስተዳደር ስራዎች ህብረተሰቡን በተጨባጭ ተጠቃሚ ማድረግ መቻሉን ገልጸዋል። አክለውም ተወላጆች በአንድነትና በቅንጅት ለአካባቢያቸው ልማትና ብልጽግና መረጋገጥ እያደረጉት ያለው ጥረት ተደናቂ፣ ሌሎችንም የሚያነሳሳ መሆኑን በማንሳት ባጠረ ጊዜ ወደ ስራ መግባት እንደሚገባ አስገንዝበዋል። የወረዳው ትራንስፖርትና መንገድ ልማት ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ አሸብር ርጋ ስራውን አስመልክቶ አጠቃላይ ማብራሪያ የሰጡ ሲሆን ተወላጅ ባለሀብቶች በዚህ መልኩ የህብረተሰቡን የመንገድ ችግር በመገንዘብ ችግሩን ለመፍታትና ያሳደጋቸውን ህብረተሰብ ለማገዝ እያደረጉት ያለውን ርብርብ አድንቀው ጽ/ቤታቸው አስፈላጊውን ሁሉ እንደሚያደርግ በመግለጽ ተወላጆች እያበረከቱት ላለው አስተዋጽኦ ምስጋናቸውን አቅርበዋል። ዘገባው የገ/ጉ/ወ/ወ/የመ/ኮ/ጉ/ጽ/ቤት ነው።

ህዳር 02/2018 ዓ.ም የዜጎችን ሁለንተናዊ ተሳትፎና ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ የስራ ዕድል ፈጠራ ስራን ውጤታማ ማድረግ እንደሚገባ ተገለጸ። ፨፨፨፨፨///፨፨፨፨፨ በጉራጌ ዞን የገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ ስራ ዕድል ፈጠረና ኢንተርፕራይዝ ልማት ጽ/ቤት የንቅናቄና የስራ እድል ፈጠራ ምክር ቤት የ2018 ዓ.ም የ4 ወራት አፈፃፀም መድረክ ተካሄደ። የወረዳው ስራ ዕድል ፈጠረና ኢንተርፕራይዝ ልማት ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ጅላሉ ወራቄ ለንቅናቄ የተዘጋጀውን የ2018 ዓ.ም የ4 ወራት አፈፃፀም ሠነድ አቅርበዋል። የወረዳው ዋና አስተዳዳሪ አቶ ሚፍታ ሁሴን ዘላቂና አስተማማኝ የስራ ዕድል በመፍጠር የዜጎች ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነት በማሳደግ በሀገር ኢኮኖሚ ውስጥ ዘላቂ ብልፅግና ለማረጋገጥ ሚናው የጎላ መሆኑ ተናግረዋል። የስራ ዕድል ፈጠራ የዜጎች የኑሮ ደረጃ በማሻሻል ድህነትን ለመቀነስ ፍትሀዊ ዕድገት ለማረጋገጥ ሚናው ከፍተኛ መሆኑን አቶ ሚፍታ ሁሴን ገልጸዋል። በወረዳው በስራ ዕድል ፈጠራ ላይ የሚታዩ ችግሮችን በመፍታት ዘላቂ የሆነ የወጣቶችን ተጠቃሚነት ለማሳደግ በትኩረት እንደሚሰራ ገልጸዋል። የወረዳውብልጽግና ፓርቲ ጽ/ቤት ኃላፊና የመንግስት ዋና ተጠሪ አቶ አ/ረሂም ርዳ በበኩላቸው የስራ ዕድል ፈጠራ በሁሉም መልኩ የሚያበረክተው አስተዋጽኦ የጎላ መሆኑን ጠቅሠው የቤተሰብ ብልፅግናን ለማምጣት ደግሞ ለዜጎች የስራ ዕድል መፍጠር ቀዳሚ ጉዳይ መሆኑን አብራርተዋል። መንግስት የወጣቶች መሰረታዊ ጥያቄ የሆነውን የስራ እድል አማራጮችን ለማመቻቸት በቁርጠኝነት መስረት ይገባል ያሉት አቶ አ/ረሂም ርዳ በየደረጃው የሚገኙ የአመራር አካላት ለጉዳዩ ትኩረት እንዲሰጥ አሳስበዋል። የወረዳው ስራ ዕድል ፈጠረና ኢንተርፕራይዝ ልማት ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ጅላሉ ወራቄ በበኩላቸው በበጀት ዓመቱ የስራ እድል ለመፍጠር ከእቅድ ጀምሮ በልዩ ትኩረት እየተሰራ መሆኑን የተናገሩት ኃላፊው ለወጣቶች ግብዓት በማመቻቸት እንዲሁም ፋይናንስ በመደገፍ ለማስጠቀም እየተሰራ ሲሆን ቀደም ሲል የተሰራጨ ብድር ወደ ኦሞ ባንክ ከማስገባት አንፃር ትኩረት ሊሰጠው እንደሚገባ አሳስበዋል። ስራ አጥ ከመለየትና ኢንተርፕራይዞች ክህሎት መር አጫጭር ስልጠና በቴክኒክና ሙያ ተቋማት እንዲሰለጥኑ ከማድረግ አንጻር ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት አስታውቀዋል። በመጨረም ከመድረኩ የተገኙ ግብዓቶችን ወስደው የእቅድ አካል በማድረግ እንደሚሰሩ አቶ ጅላሉ አስታውቀዋል።

ህዳር 02/2018 ዓ.ም ህዝቡ ለሚጠይቀው የልማትና የመልካም አስተዳደር ጥያቄዎች በተገቢው ምላሽ ለመስጠት የገቢ አሰባሰብ ስራችን ላይ በትኩረት መስራት እንደሚገባ በጉራጌ ዞን ገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ ገቢዎች ጽ/ቤት አስታወቀ። ፨፨፨፨፨///፨፨፨፨፨ ገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ ገቢዎች ጽ/ቤት የገጠር መሬት መጠቀሚያ ክፍያ እና የግብርና ስራ ገቢ ግብር አሰባሰብ ዙርያ ባለድርሻ አካላት በተገኙበት የንቅናቄ መድረክ በዛሬው እለት አካሂዷል። በወረዳው በ2018 በጀት አመት በአዲሱ የገጠር መሬት መጠቀሚያ ክፍያና የግብርና ስራ ገቢ ግብር ከ39 ሚሊየን ብር በላይ ለመሰብሰብ መታቀዱን ተጠቁሟል። የንቅናቄ መድረኩን የመሩት የወረዳው ዋና አስተዳዳሪ አቶ ሚፍታ ሁሴን የህብረተሰቡን የልማት ጥያቄ በተቻለ መጠን ምላሽ ለመስጠትና አገልግሎት አሰጣጡን ለማስቀጠል ወረዳው የሚያመነጨው የገቢ አማራጭ አቅምን አሟጦ ገቢን መሠብሠብ ያስፈልጋል ብለዋል። የወረዳችን የገቢ አቅም ለማሳደግ በገጠር መሬት ዘርፍ የታቀደውን እቅድ በተያዘለት የጊዜ ገደብ ለመሰብሰብ በሚደረገው ጥረት ሁሉም በቅንጅትና በቁርጠኝነት መስራት እንዳለባቸውም ዋና አስተዳዳሪው ገልጸው በሁሉም የቀበሌ አርሶአደሮች ግብራቸውን እስከ ታህሳስ 30 ቀን 2018 ዓ.ም ድረስ ማጠናቀቅ እንደሚገባቸው አሳስበዋል። የወረዳው ዋና የመንግስት ተጠሪና የብልጽግና ፓርቲ ጽ/ቤት ኃላፊ የሆኑት አቶ አ/ረሂም ርዳ በመድረኩ እንዳሉት ግብር የልማት ሁሉ መሰረት መሆኑን ጠቁመው ግብርን በፍትሐዊነት መክፈል ክብርም የዜግነት ግዴታም ጭምር መሆኑን አብራርቷል። ለህዝቡ ተገቢውን አገልግሎት ለመስጠትና የመሰረተ ልማት ጥያቄዎች ደረጃ በደረጃ ለመመለስ ገቢ አሰባሰብ ስርዓት ማጠናከር እንደሚገባ ጠቅሠው የሚሰበሰበው ገቢ ለትምህርት፣ለጤና ለመንገድ እና ለሌሎች የመሰረተ ልማት ስራዎች የሚውል ስለመሆኑ አቶ አ/ረሂም ርዳ አክለው ገልጸዋል። የገቢ አሰባሰብ ስራዎች በአደረጃጀት በመምራትና እንደ ወረዳ በተመሳሳይ ቀን በማወጅና በአጭር ጊዜ ገቢውን ለመሰብሰብ የሚሠራ እንደሆነ አስገንዝበዋል። የወረዳው ገቢዎች ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ረመዳን ከድር የ2018 ዓ.ም የገጠር መሬት መጠቀሚያ ክፍያ እና የግብርና ስራ ገቢ ግብር አሰባሰብ ያለፈው አመት አፈጻጸምና የዘንድሮ የ2018 በጀት አመት ሰነድ ባቀረቡበት ወቅት እንደተናገሩት የግብር አሰባሰቡና አከፋፈል ስርዓቱ የተሟላና ሚዛናዊ ለማድረግ የገጠር መሬት መጠቀሚያ ክፍያና የግብርና ስራ ገቢ ግብር አዋጅ ቁጥር 27/2016 መሠረት በማድረግ ግብር በወቅቱ ተጠናቆ መሰብሰብ እንዳለበት አስታውቀዋል። በአዲሱ የገጠር መሬት መጠቀሚያ ክፍያና የግብርና ስራ ገቢ ግብር በወረዳው ከ39 ሚሊየን ብር በላይ ለመሰብሰብ መታቀዱን አቶ ረመዳን ከድር አስገንዝበዋል። ከውይይቱ ተሳታፊዎች መካከል አንዳንዶቹ በሰጡት አስተያየት የግብር አሰባሰብ ስራዎች በንቅናቄና በአደረጃጀት በመስራት በዘንድሮ አመት የተሻለ አፈፃፀም ለማስመዝገብ በትኩረት እንደሚሰሩ በቁርጠኝነት ተናግረዋል። በንቅናቄ መድረኩ ላይ የወረዳና የቀበሌ አመራሮች እንዲሁም ባለድርሻ አካላት ተሳትፈዋል። በመጨረሻም በ2017 በጀት አመት የተሻለ አፈጻጸም ላስመዘገቡ ቀበሌዎች የእውቅናና የምስክር ሠርተፍኬት ተበርክቷላቸዋል።