ru
Feedback

Не попадитесь на канал ботавода! Telemetrio находит и помечает такие каналы 👉 Хотите видеть метку — оформите подписку 👈

የገ/ጉ/ወ/ወ/የመ/ኮ/ጉ/ጽ/ቤት

የገ/ጉ/ወ/ወ/የመ/ኮ/ጉ/ጽ/ቤት

Открыть в Telegram
925
Подписчики
Нет данных24 часа
+67 дней
+1130 дней
Архив постов
ህዳር 02/2018 ዓ.ም የሀሰተኛ መረጃ አይነቶች ፨፨፨፨፨///፨፨፨፨፨ 1. የምጸት መረጃዎች (Satire and Parody)፦ ምጸት አንድን ሃሳብ፣ ስራ ወይም ሰው አስቂኝ በሆነ መልኩ /ዘና እያደረገ/ የመተቸት ዘዴን ይገልጻል:: ፓረዲ / Parody / ደግሞ የአንድን ታዋቂ ሰው የአነጋገር ወይም የአጻጻፍ ዘይቤ በአስቂኝ መንግድ መኮረጅ ነው። እነዚህ መረጃዎች በዋናነት የምናባዊ ፈጠራ ይዘት ያላቸው እና ተገቢነት የሌላቸውን ስራዎችና ባህሪያት ለማጋለጥ ወይም ለመንቀፍ የሚጠቅሙ ቢሆኑም በግልጽ የምጸት መረጃዎች መሆናቸው ካልታወቀ በስተቀር ካለው የመረጃ መጥለቅለቅ ጋር ተዳምረው ሰዎችን የማሳሳት ወይም ግራ የማጋባት ሁኔታዎችን ይፈጥራሉ። 2. አሳሳች ይዘት (misleading content)፦ ከአንድ ጽሁፍ /ንግግር/ ላይ የተወሰነውን ክፍል ቆርጦ በማወጣት ሌላ ትርጉም እና ግንዛቤ እንዲያዝበት አድርጎ ማዘጋጀት ነው፡፡ ይህም በአንድ ጉዳይ ላይ የተዘጋጀውን ሙሉ ጽሁፉ በማንበብ /ሙሉ ንግግር በማድመጥ/ ከሚያዘው ግንዛቤ የተለየ እንዲሆን ስለሚያደርገው ሰዎችን የሚያሳስትና ተገቢ ያልሆነ አረዳድ እንዲኖራቸው የሚያደርግ ነው። 3. ከአውድ ውጭ የሚወሰድ መረጃ /out of context/፦ አውድ ነገሮችን ለመረዳት ከፍተኛ እድል ይሰጣል:: አንድን ሃሳብ ከቀረበበት ወይም ከተነገረበት ሁኔታ/አውድ/ ውጭ በመወስድ አሳሳች መልዕክት የመፍጠር ሂደት ነው:: በመሆኑም ሃሳቡ ከአውዱ ተነጥሎ ስለሚቀርብ በመጀመሪያ ከያዘው ትርጉም የተለየ ትርጉም ይኖረዋል። 4. ተመሳስሎ የሚዘጋጁ ይዘቶች / Imposter Content/፦ ይህ ታዋቂ የጥበብ ሰዎችን ባለስልጣናትን፣ ተቋማት፣ ጋዜጠኞችንና የመሳሰሉትን አካላት ስም፣ ምስል፣ የድርጅት ሎጎ የመሳሰሉትን በመጠቀም የተለያዩ አሳሳች ይዘቶችን የማዘጋጀት ሂደትን ይገልጻል:: በዚህም ምክንያት የተለያዩ አካላት ተመሳስለው የተከፈቱ ድረ-ገጾችን፣ የግልና የድርጅት የማህበራዊ ሚዲያዎችን ለማዘጋት ሲጥሩ /ሲጠይቁ/ ወይም የእነሱ እንዳልሆኑ ሲገልጹ ማየት የተለመደ ክስተት ነው። 5. የተቀነባበረ ይዘት /Manipulated Content/፦ እውነተኛ መረጃን /ምስልን/ በመጠቀም ለማጭበርበርና ለማታለል በሚያስችል መልኩ ይዘትን አቀነባብሮ ማቅረብ ነው። 6. ሃሰተኛ የፈጠራ ይዘት -/fabricated content/፦ ይህ ደግሞ ሙሉ በሙሉ ሃሰተኛ መረጃን /ይዘትን/ አዘጋጅቶ በማህበራዊ ሚዲያውና በተለያዩ ሃሰተኛ ድረ ድረ-ገጾች ላይ ማቅረብን ይገል ይገልጻል:: በመሆኑም የተለያዩ ጽሁፎች፣ ማስታዎቂያዎች የጽሁፍ-ለስሌዳዎች፣ አጫጭር ቪዲዮዎች በሃሰተኛ መረጃዎች ላይ ተመስርተው በማህበራዊ ሚዲያውና በተለያዩ ዩ ሃሰተኛ ድረ-ገጾች ላይ ሊለቀቁ ይችላሉ። EBC

በጉራጌ ዞን ገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ የተቀናጀ የግብርና ልማት አሁናዊ ሁኔታ በምስል በጥቂቱ፦

ጥቅምት 30/2018 ዓ.ም የአመራሩ ቁርጠኝነት፣ በፈጠራ፣ ፍጥነትና ጥራት መስራት ለሁለንተናዊ ብልጽግና መረጋገጥ ወሳኝ ነው - ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር) ፨፨፨፨፨///፨፨፨፨፨ "በመደመር መንግሥት እይታ፣ የዘርፎች እምርታ" በሚል መሪ ሃሳብ ለብልጽግና ፓርቲ ከፍተኛ አመራሮች ሲሰጥ የቆየው ስልጠና ተጠናቅቋል። የአመራሩ ቁርጠኝነት፣ በፈጠራ፣ ፍጥነትና ጥራት መስራት ለሁለንተናዊ ብልጽግና መረጋገጥ አስፈላጊ ነው አሉ የብልጽግና ፓርቲ ፕሬዚዳንትና የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)፡፡ የብልጽግና ፓርቲ ፕሬዚዳንትና የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በመደመር መንግሥት ላይ የማጠቃለያ ስልጠና ሰጥተዋል። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር) በዚህ ወቅት እንዳሉት የአመራሩ ቁርጠኝነት፣ በፈጠራ፣ በፍጥነትና በጥራት መስራት ለሁለንተናዊ ብልጽግና መረጋገጥ አስፈላጊ ነው። በስልጠና መርሐ ግብሩ የመደመር መንግሥት ጽንሰ ሀሳብ፣ መንገድ እና መዳረሻ ግቦቹን በስፋት መዳሰሳቸው ተመላክቷል፡፡ በዚህም በመደመር መንግሥት መርሕ የሚመራው ፓርቲው አመራሮች በፈጠራና በፍጥነት በብዛት ሥራዎችን ማከናወን እንደሚጠበቅባቸው አንስተዋል፡፡ የሕዝቡን ሁለንተናዊ ጥያቄ ከመመለስ በላይ የሀገሪቱን ራዕይ ለማሳካት እና ሁለንተናዊ ብልጽግናን ለማረጋገጥ በሚረዳ መንገድ መምራት እንዳለባቸው አስገንዝበዋል፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ትኩረት የሚሹ ግቦችን በየፈርጁ በመለየት አቅጣጫ ማስቀመጣቸውንም የፓርቲው መረጃ ያመላክታል፡፡ ፋይዳ፣ 5 ሚሊየን ኮደሮች፣ የተጀመሩ የኮሪደር ልማት ሥራዎች፣ የገበታ ለትውልድ ፕሮጀክቶች፣ የምርጫ ምቹነትና የሲቪል ሰርቪስ ሪፎርም አጀንዳዎችን መቶ በመቶ ለማሳካት መትጋት እንደሚገባ ጠቅሰዋል፡፡ መደመር ትውልድን ወደ ብልጽግና የሚያደርስ መንገድ ነው ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር) የመደመር መንግሥት ለሀገር ብልጽግና ባለአደራ መሆኑን አውስተዋል፡፡ በፈጠራና በፍጥነት ጥራትና ብዛትን እውን ማድረግ እንደሚገባ ጠቁመው በብዝሃ ዘርፍ ትስስር ወደ ስልጣኔ ሽግግር ማምጣት እንደሚገባ አስገንዝበዋል፡፡ የሀሳብ ሉዓላዊነት የብልጽግና መሰረት መሆኑን የጠቀሱት ጠቅላይ ሚኒስትሩ ሁሉም የፓርቲው አመራር በዚህ አግባብ በመትጋት ሁለንተናዊ ብልጽግና ማረጋገጥ አለበት ነው ያሉት፡፡ የፓርቲው ከፍተኛ አመራሮች ባለፉት 11 ቀናት በስልጠና፣ በውይይትና በመስክ ጉብኝት እንዲሁም በማጠቃለያ ገለጻ ያገኟቸውን እውቀትና ልምዶች በዕቅድ በማካተት ወደ ሥራ እንዲቀይሩ አጽንኦት ሰጥተዋል፡፡ የኢትዮጵያን ሁለንተናዊ ብልጽግና እውን ለማድረግ በሚደረገው ጥረት ውስጥ የድርሻቸውን እንዲወጡም አሳስበዋል። (ኤፍ ኤም ሲ)

ጥቅምት 30/2018 ዓ.ም በገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ ወጣቶችና ስፖርት ጽ/ቤት አዘጋጅነት የሚካሄዳው የበጋ ወራት የውስጥ ለውስጥ የእግር ኳስ ጨዋታ ውድድር በዛሬው እለት ተጀመረ። ፨፨፨፨፨///፨፨፨፨፨ በመክፈቻ ጫወታ መከዞ ከ ኮንበል የተገናኙ ሲሆን መከዞ እግር ኳስ ቡድን 2ለ0 በሆነ ውጤት በማሸነፍ የመጀመሪያውን 3 ነጥብ ማግኘት ችሏል። የማሸነፊያ ጎሎችን ሳዲቅ ናስር እና ኑርሀሠን ረሻድ አስቆጥረዋል። በገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ ወጣቶችና ስፖርት ጽ/ቤት አዘጋጅነት የሚካሄዳው የበጋ ወራት የውስጥ ለውስጥ የእግር ኳስ ጨዋታ ውድድር ቅዳሜና እሁድ ቀጥሎ የሚካሄድ ይሆናል።

የሳምንቱ አበይት ዜናዎች ጥቅምት 30/2018 ዓ.ም 👉🏼‎ በጉራጌ ዞን ገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ በከተማ እናገጠር የተያዙ የኮሪደር ልማት ስራዎች ለመተግበር የሚደረገውን ጥረት በየደረጃው የሚገኙ አካላት ማገዝ እንደሚጠበቅባቸው ተገለፀ። ፨፨፨፨፨///፨፨፨፨፨ 👉🏼‎በገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ ያለውን ሰላምና ጸጥታ በዘላቂነት ለማስጠበቅ የሚደረገውን ጥረት በየደረጃው የሚገኙ ባለድርሻዎች ተቀናጅቶ በመስራት ዘርፉን ውጤታማ ማድረግ   እንደሚጠበቅባቸው ተገለጸ። ፨፨፨፨፨///፨፨፨፨፨ 👉🏼‎የሴቶች ልማት ህብረት ውጤታማ ስራዎችን ይበልጥ በመጠናከር የሴቶችና ህፃናትን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ እንደሚሠራ በጉራጌ ዞን የገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ ሴቶችና ህፃናት ጉዳይ ጽህፈት አስታወቀ። ፨፨፨፨፨///፨፨፨፨፨ 👉🏼‎የገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ ወጣቶችና ስፖርት ፅ/ቤት አማካኝነት የ2018 ዓ.ም የበጋ እግር ኳስ የውስጥ ለውስጥ ውድድር ለመጀመር የእጣ ድልድል ስነ ስርዓት እንዲሁም የውድድሩ መመሪያ እና ደንብ ላይ ውይይት አካሄደ። ፨፨፨፨፨///፨፨፨፨፨ 👉🏼‎የተጀመረውን የሚዲያና ኮሚኒኬሽን ስራ አጠናክሮ በማስቀጠል የህብረተሰቡን የልማትና መልካም አስተዳደር ተጠቃሚነት ማሳደግ እንደሚገባ ተጠየቀ። ፨፨፨፨፨///፨፨፨፨፨ 👉🏼‎በጉራጌ ዞን የገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ የመሃል አምባ ኮንስትራክሽንና ኢንዱስትሪያል ኮሌጅ በ2018 ዓ.ም የነባርና አዳዲስ ሰልጣኞች ቅበላ ማሳካት ላይ  ያተኮረ የውይይት መድረክ ከባለድርሻ አካላት ጋር ተካሄደ። ፨፨፨፨፨///፨፨፨፨፨ 👉🏼‎የሴቶችና ህጻናትን ሁለንተናዊ ተሳትፎና ተጠቃሚነታቸውን ለማረጋገጥ የሚደረገውን ጥረት በየደረጃው የሚገኙ ባለድርሻ አካላት ማገዝ እንደሚጠበቅባቸው የገ/ጉ/ወ/ወረዳ ሴቶችና ህጻናት ጉዳይ ጽህፈት ቤት አስታወቀ። ፨፨፨፨፨///፨፨፨፨፨ 👉🏼‎የሴቶችን የማሀበራዊ ሚዲያ አጠቃቀም ግንዛቤ በማሳደግ ሁለንተናዊ ተሳትፎ እና ተጠቃሚነትን ማረጋገጥ እንደሚገባ በጉራጌ ዞን የገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ ሴቶች ክንፍ ጽህፈት ቤት አስታወቀ። ፨፨፨፨፨///፨፨፨፨፨ 👉🏼‎ወጣቶች ሚዲያን ለበጎ አላማ በማዋል ለተጀመረው ሁለንተናዊ እድገትና ልማት የበኩላቸውን ሚና መወጣት እንደሚገባቸው በጉራጌ ዞን የገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ ብልፅግና ፓርቲ ፅ/ቤት ገለጸ።

ጥቅምት 28/2018 ዓ.ም በጉራጌ ዞን ገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ በከተማ እና ገጠር የተያዙ የኮሪደር ልማት ስራዎች ለመተግበር የሚደረገውን ጥረት በየደረጃው የሚገኙ አካላት ማገዝ እንደሚጠበቅባቸው ተገለፀ። ፨፨፨፨፨///፨፨፨፨፨ የወረዳው ባህል ቱሪዝም እና ከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ጽ/ቤቶች የኮሪደር ልማት የንቅናቄ መድረክ ዛሬ ከባለድርሻ አካላት ጋር አካሂደዋል። የወረዳው ባህል ቱሪዝም ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ሄኖክ ጉልላት እና የወረዳው ከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ተማም አደም የ2018 ዓ/ም የገጠር እና የከተማ ኮሪደር ልማት ዕቅድ አቅርበው ውይይት ተደርጓል። የገ/ጉ/ወ/ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ሚፍታ ሁሴን እንደ ሀገር የተጀመረው የኮሪደር ልማት ስራ ተጠናክሮ መቀጠሉን ገልጸዋል። በወረዳ ደረጃ አባቶቻችን ጠብቀው ያቆዩልንን የገጠር ኮሪደር ልማት ወይም የውርዘነ ዛሬ ላይ እንደምቹ አጋጣሚ በመጠቀም ባህላዊ ይዘቱን ለተለያዩ ግልጋሎቶች ሲውል የቆየውን የውርዘነ ዳግም ለህብረተባችን ልማት ማዋል እንደሚገባ በመግለፅ በአንፃሩ በከተማ ኮሪደር ልማት ዘርፍ መሰረታውያን የሆኑትን የእግረኛ መንገድ ማስፋት፣ የውሃ አካላትና አረንጓዴ ልማትን ጨምሮ ህዝባዊ ኩነቶች ማስኬጃ ቦታዎች ማልማት የትኩረት አቅጣጫ ተደርጎ እየተሰራ መሆኑን ጠቅሰው በመስኩ የተያዙ የኮሪደር ልማት ስራዎች ለመተግበር የሚደረገውን ጥረት በየደረጃው የሚገኙ አካላት ማገዝ እንደሚጠበቅባቸው አስገንዝበዋል። የወረዳው የመንግስት ዋና ተጠሪ አቶ አ/ረሂም ርዳ በበኩላቸው የጠፍውን የውርዘነ በተደራጀ መልኩ እንዲመለስ መስራት እንደሚያስፈልግ ጠቁመው ተግባሩን ሁሉም ማህበራዊ መሰረቶች የሚሳተፉ ስለመሆኑ በማንሳት በከተማም ሆነ በገጠር የተያዘውን የኮሪደር ልማት ውጥን ውጤታማነት በመደጋገፍና በመቀናጀት የድርሻችንን ልንወጣ ይገባል ሲሉ አመላክተዋል። አንዳንድ ተሳታፊዎች በሰጡት አስተያየት ልማቱ ሁለንተናዊ ብልጽግናችንን ባጠረ ጊዜ የሚያረጋግጥ ስለመሆኑ ጠቅሰው ለተግባራዊነቱ የሚጠበቅባቸውን እንደሚወጡ ገልጸዋል።

ጥቅምት 28/2018 ዓ.ም የጉራጌ ዞን ምክር ቤት ቋሚ ኮሚቴ አባላት በገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ በገደባኖ ክላስተር ከህዝቡ ጋር በልማትና መልካም አስተዳደር ዙሪያ በዛሬው እለት ውይይት ማድረጋቸው ተገለጸ። ፨፨፨፨፨///፨፨፨፨፨ በመድረኩ የገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ የጤና እና ትምህርት ጽ/ቤት ኃላፊዎች የአፈጻጸም ሪፖርት ለውይይቱ ታዳሚዎች አቅርበዋል። በጉራጌ ዞን ምክር ቤት የማህበራዊ ዘርፍ ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ ወይዘሮ ጥሩነሽ ምኑታ በህዝብ ውይይቱ ላይ የክላስተሩ ህዝብ ከመንግስት ጋር በመቀናጀት በመሠረተ ልማት በጤና በትምህርት እና በሌሎችም የልማት ዘርፎች እያደረገ ያለው ተሳትፎ አጠናክሮ ማስቀጠል እንደሚገባው በመግለፅ ህዝቡ የሚያንሳቸው ጥያቄዎች ከየአካባቢው ማህበረሰብ ጋር በመቀናጀት ደረጃ በደረጃ ምላሽ እንዲያገኙ ትኩረት ተሰጥቶ ይሰራል ብለዋል። የውይይቱ ተሳታፊ የገደባኖ ክላስተር ነዋሪዎች በክላስተሩ የተከናወኑ ተግባራት ከማስፋት ጎን ለጎን ህዝብ የሚያነሳቸው የልማት የመልካም አስተዳደር በተለይም የመብራት የመንገድ የጤና አገልግሎቶች አቅርቦት እና ተደራሽነት ጥያቄዎች ምላሽ እንዲሰጣቸው ጠይቀዋል። በህዝብ መድረኩ ለተነሱ ጥያቄዎች የወረዳው ጤና ጥበቃ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ሙባሪክ ሰይፉ እና የወረዳው ትምህርት ጽ/ቤት ም/ኃላፊ አቶ አህመዲን ሰኢድ ምላሽና ማብራሪያ ሰጥተዋል። በህዝብ መድረኩ በጉራጌ ዞን ምክር ቤት የማህበራዊ ዘርፍ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ ወ/ሮ ጥሩነሽ ምኑታ የገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ ምክር ቤት ምክትል አፈ ጉባኤ አቶ ጫሉ ከድር ፣ የወረዳው ጤና ፅህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ሙባረክ ሰይፉ የወረዳው ትምህርት ፅህፈት ቤት ም/ኃላፊ አቶ አህመዲን ሰኢድን ጨምሮ የዞንና የወረዳው ባለድርሻ አካላት እንዲሁም የገደባኖ ክላስተር ህዝብ በመድረኩ ላይ ተሳትፈዋል።

ጥቅምት 27/2018 ዓ.ም በገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ ያለውን ሰላምና ጸጥታ በዘላቂነት ለማስጠበቅ የሚደረገውን ጥረት በየደረጃው የሚገኙ ባለድርሻዎች ተቀናጅቶ በመስራት ዘርፉን ውጤታማ ማድረግ እንደሚጠበቅባቸው ተገለጸ። ፨፨፨፨፨///፨፨፨፨፨ ይህ የተገለጸው የገ/ጉ/ወ/ወረዳ ሰላምና ጸጥታ ጽ/ቤት፣ የወረዳው ፖሊስና ሚሊሻ ጽ/ቤቶች የ2018 ዓ/ም ዕቅድ አፈጻጸም ግምገማ እና የጋራ የሶስትዮሽ የውይይት መድረክ በዛሬው ዕለት ባካሄዱበት ወቅት ነው። በመድረኩም የወረዳው ወሳኝ ኩነት ምክር ቤት የ2018 ዓ/ም 1ኛ ሩብ ዓመት ዕቅድ አፈጻጸም እና የ2018 ዓ/ም ዕቅድ ዙሪያ ከባለ ድርሻ አካላት ጋር ውይይት ተደርጓል። የወረዳው ሰላምና ጸጥታ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ሙሰማ በድሩ የ2018 አመት የሶስትዮሽ የጋራ ዕቅድ እንዲሁም የጽ/ቤቱ ልማት ዕቅድ ባለሙያ ብሩክ አባቤ የበጀት ዓመቱን የመጀመሪያ 1ኛ ሩብ ዓመት አፈጻጸም ሪፖርት አቅርበዋል። ከተነሱ ሃሳብና አስተያየቶች መካከል የቀበሌ ወሰን ግጭት ሙሉ በሙሉ ለማስወገድ አጽንኦት ተሰጥቶት መሰራት እንዳለበት፣ የጸጥታ ችግር ሊሆኑ የሚችሉ ጉዳዮች ላይ በትብብር አቅዶ መስራት እንደሚያስፈልግ ያነሱት ተሳታፊዎቹ ፖሊስ የወንጀል መከላከል ስራ ላይ በትኩረት መስራት እንደሚኖርበት፣ የሚሊሻ አገልግሎት አሰጣጥ መሻሻል እንዳለበትና ሚሊሻ ሃይሉን በግብዓት መደገፍ እንደሚያስፈልግ ተሳታፊዎች አንስተዋል። በተያያዘም የወሳኝ ኩነት ምዝገባ አፈጻጸም መጎልበት እንደሚጠበቅበት የገለጹት የመድረኩ ተሳታፊዎች የባለድርሻዎች ቅንጅታዊ አሰራር ተጠናክሮ መቀጠል እንደሚጠበቅበት ጠይቀዋል። የገ/ጉ/ወ/ወረዳ ሰላምና ጸጥታ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ሙሰማ በድሩ በማጠቃለያቸው በሶስቱ ተቋማት የተነሱ ግብዓቶች ተወስዶ የዕቅድ አካል ተደርጎ እንደሚሰራ ገልጸዋል። አክለውም ባለድርሻዎች ተቀናጅቶ በመንቀሳቀስ በዘርፉ የሚሰሩ ስራዎችን ውጤታማ ለማድረግ የሚደረገውን ርብርብ ማገዝ እንደሚጠበቅባቸው አስገንዝበዋል። የወረዳ ሚሊሻ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ አብዲሳ በበኩላቸው የቀበሌ አመራሩ ሰላምና ጸጥታን ለማረጋገጥ የሚደረገውን ጥረት በተገቢው ማገዝ እንደሚጠበቅበት ጠቁመው ከሚሊሻ አገልግሎት አሰጣጥ መጓደል እና ተደራሽነት ጋር በተያያዘ የሚስተዋሉ ጉድለቶችን ለመፍታት እንደሚሰራ አስታውቀዋል። ዘገባው የገ/ጉ/ወ/ወ/የመ/ኮ/ጉ/ጽ/ቤት ነው።