925
Подписчики
Нет данных24 часа
+47 дней
+930 дней
Архив постов
“ዛሬ፣ የኛ የሆነውን ቀይ ባሕርን መልሶ ለመጠየቅ የሚሰጋ፣ የሚጠራጠር ትውልድ መፈጠሩ የሥነ-ልቦና ስብራት አካል ነው። ‘አንችልም’ ብሎ ነው የሚያስበው፤ እኔ ላረጋግጥላችሁ እወዳለሁ፣ ኢትዮጵያ ትችላለች!”
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)
#Ethiopia #PMAbiy #RedSea #accesstothesea
መስከረም 08/2017 ዓ.ም
በጉራጌ ዞን ገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ የክረምት በጎ ፍቃድ አገልግሎት ተጠናክሮ ቀጥሏል።
፨፨፨፨፨///፨፨፨፨፨
የወረዳው ሴቶችና ህፃናት ጉዳይ እና ወጣቶችና ስፖርት ጽ/ቤት በጋራ በመሆን ከ70 ሺህ ብር በላይ የሚገመት የትምህርት ቁሳቁስ፣ የአልባሳት እና የንፅህና መጠበቂያ በዛሬው በጋራ ድጋፍ ማድረጋቸውን ገለጹ።
በእለቱ 76 ለሆኑ ህፃናት 62 ደርዘን ደብተር፣ 4 ፓኬት እስኪሪብቶ፣ 7 ዩኒፎርም እንዲሁም ለአረጋውያን የተለያዩ አልባሳት፣ፍሬ ሳሙና፣12 ኪሎ ግራም ሩዝ ድጋፍ የተደረገ ሲሆን የድጋፉ ምንጩ በጎ ፍቃደኛ ህብረተሰብ ክፍሎች እና በወረዳው የሚገኙ ሴክተር መስሪያ ቤቶች በማስተባበር እንደሆነ ተመላክቷል።
የወረዳው ብልጽግና ፓርቲ ጽ/ቤት ኃላፊ እና የበጎ ፍቃድ አብይ ኮሚቴ ሰብሰቢ የሆኑት አቶ አ/ረሂም ርዳ ተገኝተዋል።
ዜና ሹመት
የገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ ብልጽግና ጽህፈት ቤት በዛሬው ዕለት አዲስ የአመራር መዋቅር የተቀላቀሉ አመራሮችን ጨምሮ በሽግሽግ በካቢኔና በምክትል ማዕረግ አደራጅቷል።
በዚህም መሰረት፦
በካቢኔ ደረጃ
1. አቶ ተማም አደም የከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ጽ/ቤት ኃላፊ
2. አቶ አ/ጀሊል ቱሉ ውሃና ማዕድን ጽ/ቤት ኃላፊ
3. አቶ ፍሪስ ከማል ፐብሊክ ሰርቪስና የሠው ሃብት ልማት ጽ/ቤት ኃላፊ
4. አቶ ሙባሪክ ሠይፉ ጤና ጥበቃ ጽ/ቤት ኃላፊ
5. አቶ አብድልበር አብራር የአስተዳደር ጽ/ቤት ኃላፊ
6. አቶ ረመዳን ከድር የገቢዎች ጽ/ቤት ኃላፊ
በምክትል ደረጃ
1፡ወይሪት አጃኢባት ወራቄ ፐብሊክ ሰርቪስ ጽ/ቤት ምክትል ኃላፊ
2፡አቶ ሚፍታ ድሬሳ ከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ጽ/ቤት ምክትል ኃላፊ
3፡አቶ ሙደሲር ንጉሴ የውሃና ማዕድን ጽ/ቤት ምክትል ኃላፊ
4፡አቶ አ/ፈታ አማን የወጣቶች ክንፍ ኃላፊ
5፡አቶ አለማር ሃቢብ የወጣቶች ክንፍ ምክትል ኃላፊ
6፡ወይዘሪት ዘይነብ አብራር የሴቶች ክንፍ ምክትል ኃላፊ
7፡አቶ ሚፍታ መቻል የጤና ጥበቃ ጽ/ቤት ምክትል ኃላፊ
8፡ወ/ሮ መኪያ ነጋሽ በግብርና ጽ/ቤት የአደጋ ስጋት ስራ አመራር ዘርፍ ኃላፊ
9፡አቶ ጀማል ለሜሳ የብልጽግና ፓርቲ ጽ/ቤት የሀብት ልማት ዘር ኃላፊ
10፡አቶ ሀሚድ ባሃሩ የአደረጃጀት ዘርፍ ምክትል ኃላፊ
11፡አቶ መባሪክ ሀቢብ ኮንበል መዘጋጃ ቤት ስራስኪያጅ
12፡አቶ ሀቢብ ናስር የጎራ መዘጋጃ ቤት ስራስኪያጅ
መስከረም 06/2017 ዓ.ም
የህዳሴ ግድባችን የሉዓላዊነት መገለጫችን ነዉ ሲሉ በጉራጌ ዞን የገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ ነዋሪዎች ገለፁ።
፨፨፨፨፨///፨፨፨፨፨
በወረዳው ታላቁ የህዳሴ ግድብ ግንባታ መጠናቀቁን አስመልክቶ ህዝባዊ የድጋፍ ሠልፍ በዛሬው ዕለት ተካሂዷል።
በህዝባዊ የድጋፍ ሠልፍ ላይ የተገኙት የገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ሚፍታ ሁሴን የእንኳን ደስ ያላችሁ መልዕክት ያስተላለፉ ሲሆን የህዳሴው ግድብ ዳግማዊ ዓድዋ ድል ነው ብለዋል።
በዚህ ታሪካዊ ግድብ ሁሉም ኢትዮጵያዊ አሻራውን በማሳረፍ አብሮነታችንና አንድነታችን በተባበረ ክንድ በማሳየት ለአለም ምስክር መሆን ችለናል ሲሉ ገልጸዋል።
የህዳሴው ግድብ የኢትዮጵያ ብቻ ሳይሆን የአፍሪካ ኩራት ጭምር ነዉ ያሉት ዋና አስተዳዳሪዉ ግድቡን መገደብ ብቻ ሳይሆን የነጻነት፣ የሉዓላዊነት፣ የመስዋዕትነት፣ የቆራጥነት፣ የአብሮነት፣ የመተጋገዝ እና ህብረ ብሄራዊ አንድነታችን መገለጫ ነዉ ሲሉም አስታውቀዋል።
አቶ ሚፍታ ሁሴን አክለውም በአባይ መጠቀሚያ ጊዜ ላይ ደርሰናል ቀጥሎም የቀይ ባህር ጀምረናል ቀይ ባህር ጥንትም የኛ ነው አሁንም ወደነበረበት ይመለሳል ብለዋል።
የወረዳው ብልፅግና ፓርቲ ፅህፈት ቤት ኃላፊና የመንግስት ዋና ተጠሪ አቶ አ/ረሂም ርዳ በበኩላቸው በፓርቲያችን እሳቤ መሰረት ተናግረን ያላደረግነው፣ ቃል ገብተን ያልፈፀምነው፣ ጀምረን ያልጨረስነው ምንም ነገር የለም።
እኛ ኢትዮጵያን መቻል ምን እንደሆነ ለመላው ዓለም አቀፍ ማህበረሰብ ያሳየንበት የድል ችቦ ነው ሲሉ የገለፁት አ/ረሂም ርዳ "ከቃል እስከ ባህል" ስኬቶቻችንን ያጸናንበት የማንሰራራት ዘመን ጅማሮ የታላቁ ህዳሴ ግድባችን ሪቫን ቆርጠን ያሳየንበት፣ የሚያወሩ፣ የሚነቅፉ፣ የሚተቹ ከተቀመጡበት ወንበር ሳይነሱ ተአምር ለአለም ያሳየንበት ነው ብለዋል። በመተባበር፣ በመተጋገዝና በመደጋገፍ እውነታ ላይ ቆመን፣ አንድ ሆነን የህዝባችንን ብሎም የሀገራችንን ሁለንተናዊ ብልፅግና እናረጋግጣለንም ሲሉ አስታውቀዋል።
አንዳንድ የድጋፍ ሰልፉ ተሳታፊዎች በሰጡት አስተያየት የታላቁ ህዳሴ ግድብ ተጠናቆ ለምረቃ መብቃት በመቻሉና ሃይል ማመንጨት መጀመሩ ከፍተኛ ደስታን እንደፈጠረባቸዉ ገልጸዋል። አክለዉም የህዳሴ ግድባችን የሉዓላዊነት መገለጫችን ነው ያሉት ነዋሪዎቹ በቀጣይ ዘመናት በሚከናወኑ የልማትና መልካም አስተዳደር ስራዎች ላይ ከመንግስት ጎን በመሠለፍ የሚጠበቅባቸውን ለመወጣት አበክረው እንደሚሰሩም አስተያየታቸውን ሠጥተዋል።
ዘገባውየገ/ጉ/ወ/ወ/የመ/ኮ/ጉ/ጽ/ቤት ነው።
መስከረም 06/2018 ዓ.ም
"በህብረት ችለናል" በሚል መሪ ቃል በጉራጌ ዞን ገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ምረቃት አስመልክቶ የድጋፍ ሰልፍ አያካሄዱ ይገኛል።
፨፨፨፨፨///፨፨፨፨፨፨
በሰልፍ ላይ የወረዳው አመራሮች እንዲሁም የሀገር ሽማግሌዎች እና የሀይማኖት አባቶች፣የመንግስት ሠራተኞች እና የተለያዩ አካላት ተገኝተዋል።
