925
Подписчики
Нет данных24 часа
+47 дней
+930 дней
Архив постов
የሳምንቱ አበይት ዜናዎች
መስከረም 04/2018 ዓ.ም
👉🏼 የ12ኛ ክፍል ማጠናቀቂያ ፈተና ውጤት ነገ ይፋ ይሆናል።
፨፨፨፨፨///፨፨፨፨፨
👉🏼 ሰባቱ የጉባ ብስራቶች
፨፨፨፨፨///፨፨፨፨፨
👉🏼በጉራጌ ዞን ገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ የመማር ማስተማር ስራ የፊታችን ሰኞ በቀን 05/2018 ዓ.ም ትምህርት እንደሚጀመር የወረዳው ትምህርት ቤቶች ጽ/ቤት አስታወቀ።
፨፨፨፨፨///፨፨፨፨፨
👉🏼 በጉራጌ ዞን የገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ የ2018 በጀት ዓመት የወረዳው በጀት ብር 488 ሚሊዮን 688 ሺህ 793 ሆኖ መፅደቁ የወረዳው ፋይናንስ ጽ/ቤት ተገለጸ፡፡
፨፨፨፨፨///፨፨፨፨፨
👉🏼'ዲጂታል ኢትዮጵያን እውን ማድረግ'
👉🏼 በጉራጌ ዞን ገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ ቦኔ ቀበሌ በመኸር እየለሙ የሚገኙ ሰብሎች እና የመስኖ ቅድመ ዝግጅት በመደብ ደረጃ ያለበት ቁመና በምስል በከፊል፦
፨፨፨፨፨///፨፨፨፨፨
👉🏼 የታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ምረቃ ሥነ ሥርዓት በምስል፦
፨፨፨፨፨///፨፨፨፨፨
👉🏼 ታላቁ የኢትዮጽያ ህዳሴ ግድብ ግንባታ ተጠናቆ ለምረቃ መብቃቱ እንዳስደሰታቸው በጉራጌ ዞን የገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ የመሃል አምባ ከተማ ነዋሪዎች ገለፁ።
፨፨፨፨፨///፨፨፨፨፨
👉🏼የርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው(ዶ/ር) መልዕክት
፨፨፨፨፨///፨፨፨፨፨
👉🏼 ኢትዮጵያ ከሕዳሴ ግድብ ጋር የሚስተካከል የኒውክሌር ማበልጸጊያ በቅርቡ ትጀምራለች - ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)
፨፨፨፨፨///፨፨፨፨፨
👉🏼አፍሪካውያን የጋራ ትዕምርታቸው የሆነውን ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብን በጋራ መረቁ
#etv
፨፨፨፨፨///፨፨፨፨፨
👉🏼አንድም ህጻን በትምህርት ቁሳቁስ እጦት ከትምህርት ገበታ እንዳይቀር በክረምት በጎ ፍቃድ አገልግሎት የትምህርት መማሪያ ቁሳቁስ በማሰባሰብ ለ30 የተቸገሩ ህፃናት 20 ደርዘን ደብተርና 2 ፓኬት እስክሪብቶ ድጋፍ ማድረጉን
የገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ ወጣቶችና ስፖርት ጽ/ቤት ገለፀ።
፨፨፨፨፨///፨፨፨፨፨
👉🏼ጳጉሜ 3 የእምርታ ቀን " ሁለንተናዊ እምርታ ለኢትዮጵያ ከፍታ " በሚል መሪ ቃል በጉራጌ ዞን ገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ በፓናል ውይይትና በልዩ ልዩ መርሐግብሮች ተከበረ።
፨፨፨፨፨///፨፨፨፨፨
👉🏼በጉራጌ ዞን ገደባኖ ጉታዘር ወለኔ በጠይባ ቀበሌ በጠረጴዛማ እርከን በወጣቶች የለማ የስንዴ ማሳ በምስል፦
የ12ኛ ክፍል ማጠናቀቂያ ፈተና ውጤት ነገ ይፋ ይሆናል።
፨፨፨፨፨///፨፨፨፨፨
በ2017 የትምህርት ዘመን የተሰጠው የ12ኛ ክፍል ማጠናቀቂያ ፈተና ውጤት በነገው ዕለት ይፋ ይሆናል።
የትምህርት ሚኒስቴር ለፋና ሚዲያ ኮርፖሬሽን እንዳስታወቀው፤ የፈተና ውጤቱን አስመልክቶ በነገው ዕለት ከ10 ሰዓት ጀምሮ ለመገናኛ ብዙሃን ማብራሪያ ይሰጣል።
የ2017 የትምህርት ዘመን የ12ኛ ክፍል ማጠናቀቂያ ፈተና ከሰኔ 23 እስከ ሐምሌ 8 ቀን 2017 ዓ.ም በሀገር አቀፍ ደረጃ መሰጠቱ ይታወሳል።
በተፈጥሮ ሳይንስና በማህበራዊ ሳይንስ በአጠቃላይ 608 ሺህ 742 ተማሪዎች ተመዝግበው 581 ሺህ 905 ተማሪዎች ፈተናውን ወስደዋል።
ከተፈታኞቹ መካከል 134 ሺህ 828 ተማሪዎች በበይነ መረብ የተፈተኑ ሲሆን፤ ቀሪዎቹ ተማሪዎች ደግሞ በወረቀት ተፈትነዋል።
ፈተናው በሁሉም ክልሎችና ከተማ አስተዳደሮች በተቋቋሙ 216 የመፈተኛ ማዕከላት በበይነ መረብ በአራት ዙር እንዲሁም በወረቀት በሁለት ዙር መሰጠቱ የሚታወስ መሆኑን ኤፍ ኤም ሲ ዘግቧል።
ሰባቱ የጉባ ብስራቶች 🔥
****
በሚቀጥሉት አምስት እና ስድስት ዓመታት የሚተገበሩ ሰባቱ ግዙፍ ፕሮጀክቶች፤
✅የኒውክሌር ማበልጸጊያ
✅የጋዝ ፋብሪካ ማስመረቅ
✅የነዳጅ ማጣሪያ እውን ማድረግ
✅በአፍሪካ ግዙፉ አየር ማረፊያ
✅2ኛውን የጋዝ ፋብሪካ ግንባታ ማስጀመር
✅የማዳበሪያ ፋብሪካ ግንባታ ማስጀመር
✅1.5 ሚሊዮን ቤቶች በመላው ሀገሪቱ ማስጀመር
እነዚህ ፕሮጀክቶች ከ30 ቢሊዮን ዶላር በላይ የሚፈልጉ ናቸው።
#ebcdotstream #ሜጋፕሮጀክቶች
መስከረም 02/2018 ዓ.ም
በጉራጌ ዞን ገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ የመማር ማስተማር ስራ የፊታችን ሰኞ በቀን 05/2018 ዓ.ም ትምህርት እንደሚጀመር የወረዳው ትምህርት ቤቶች ጽ/ቤት አስታወቀ።
፨፨፨፨፨///፨፨፨፨፨
የወረዳው ትምህት ቤቶች ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ አለማየው ኬኔ ጉዳዩን አስመልከተው እንደገለጹት የትምህርት ጥራት ለማረጋገጥ የመማር ማስተማር ስራ በአግባቡ በተቀመጠው የጊዜ ሰሌዳ መጀመሩ ወሳኝ መሆኑን አስታውቀዋል።
የ2018 የትምህርት ዘመን የተማሪዎች ምዝገባ ከነኀሴ 12/2017 ዓ.ም ጀምሮ እስከ ጳጉሜ 05/2017 ድረስ ሲካሄድ መቆየቱን ጠቁመው ቅድመ መደበኛ ተማሪ 6350 እና መደበኛ ተማሪዎች ከ1ኛ እስከ 12ኛ ክፍል 25 ሺህ 6 መቶ 45 መመዝገቡን አቶ አለማየው ገልጸዋል።
የፊታችን ሰኞ ማለትም መስከረም 5 የ2018 የትምህርት ዘመን በወረዳው በሚገኙ በሁሉም ትምህርት ቤቶች የመማር ማስተማር ስራ የሚጀምር ሲሆን የቅድመ ዝግጅት ተግባራት በመሆኑ ወላጆች ተማሪ ልጆቻቸውን በእለቱ ወደ ትምህርት ቤት መላክ እንዳለባቸው አስገንዝበዋል።
በመጨረሻም አቶ አለማየው ባስተላለፉት መልዕክት
የትምህርት ብክነት ከአንድ ክፍለ ጊዜ የሚጀምር በመሆኑ ሁሉም ባለድርሻ አካላት የትምህርት ብክነት እንዳይኖር የበኩላቸውን እንዲወጡ አሳስበዋል።
ጳጉሜ 05/2017 ዓ.ም
በጉራጌ ዞን የገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ የ2018 በጀት ዓመት የወረዳው በጀት ብር 488 ሚሊዮን 688 ሺህ 793 ሆኖ መፅደቁ የወረዳው ፋይናንስ ጽ/ቤት ተገለጸ፡፡
፨፨፨፨፨///፨፨፨፨፨
ይህ የተገለጸው የወረዳው ፋይናንስ ጽ/ቤት የ2018 በጀት ዓመት ለወረዳው የካቢኔ አካላት በማቅረብ ባጸደቀበት ወቅት ነው፡፡
በዚህ ወቅትም የገ/ጉ/ወ/ወረዳ ፋይናንስ ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ አ/ዋሃብ ኸሊል የበጀት የ2018 ዓ/ም የተጠቃለለ በጀት አቅርበዋል፡፡
በዚህ መሠረት ለበጀት ዓመቱ ጠቅላላ በጀት ብር 488 ሚሊዮን 688 ሺህ 793 በጀት የጸደቀ ሲሆን ከዚህ ውስጥም ለመደበኛ እና ማዘጋጃ ቤቶች የጸደቀ በጀት ብር 449 ሚሊዮን 153 ሺህ 018 ለደመወዝ 229 ሚሊዮን 220 ሺህ 344 ፣ ለስራ ማስኬጂያ 80 ሚሊዮን 278 ሺህ 473 እና ላደሩና አዳዲስ ካፒታል ፕሮጀክቶ 139 ሚሊዮን 654 ሺህ 199 ሆኖ የጸደቀ ሲሆን በተጨማሪም የትምህርት ቤቶች የውስጥ ገቢ 17 ሚሊዮን 547 ሺህ 184 ብር እንዲሁም ለጤና ተቋማት የውስጥ ገቢ 21 ሚሊዮን 988 ሺህ 591 ብር ሆኖ መጽደቁን ገልጸዋል፡፡
አቶ አ/ወሃብ አክለውም ውስን የሆነውን የመንግስት በጀት በአግባቡ በመጠቀም፣በመቆጣጠርና በመከታተል በጀቱ ለታለመለት ዓላማ እንዲውል በማድረግ የህዝቡን የልማት ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ
እንደሚሰራ አስተውቀዋል። በተጨማሪም በወረዳው ያለው የልማት ጥያቄ ሰፊ በመሆኑ በመንግስት በጀት ብቻ መሸፈን ስለማይቻል የህዝቡ እና የተወላጅ ባለሀብቶች ድጋፍ እና ርብርብ እንደሚያስፈልግ ገልፀዋል።
የገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ሚፍታ ሁሴን በማጠቃለያቸው እንዳሉት የወረዳውን የውስጥ ገቢ አሟጦ መሰብሰብ እንደሚገባ በመግለጽ ለካፒታል ፕሮጀክት ቅድሚያ መስጠት እንደሚያስፈልግ ጠቅሰው በተያዘለት ጊዜ በማጠናቀቅ ህብረተሠቡን ማስጠቀም እንደሚገባ አሳስበዋል።
በመጨረሻም አቶ ሚፍታ እንዳሉት በጀትን ለታለመለት ዓላማ በማዋል የተጀመረውን የብልጽግና ጉዞ በተጨባጭ ውጤቶች ማረጋገጥ እንደሚገባ አስገንዝበዋል።
ጳጉሜ 05/2017 ዓ.ም
የገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ሚፍታ ሁሴን ለ2018 ዓ.ም አዲስ አመት አስመልክተው የእንኳን አደረሳቹ መልክት አስተላለፉ።
፨፨፨፨፨///፨፨፨፨፨
የገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ሚፍታ ሁሴን ለመላው የወረዳችንና ለሃገራችን ህዝብ እንኳን ለአዲሱ አመት በሰላምና በጤና አደረሳችሁ በማለት መልካም ምኞታቸውን ገልፀዋል።
የዘንድሮ አዲሱ ዓመት ለየት የሚያደርገው የዘመናት ቁጭት የነበረው የህዳሴ ግድባችን ተጠናቆ በተመረቀበት ማግስት የምናከብረው አዲስ አመት በመሆኑ እጅግ ድርብ ደስታን የሚፈጥርም ነው ብለዋል።
አቶ ሚፍታ በመልዕክታቸው መጪው አዲስ አመት ብሩህ ተስፋ የምናይበት እንዲሁም በወረዳችን በሁሉም መስክ የተያዙ የልማትና የመልካም አስተዳደር ስራዎች ውጤቶችን የምናስመዘግብበት በአጠቃላይ የሀገራችን ብሎም የወረዳችን ከፍታ የምናረጋግጥበት እንዲሆን ምኞታቸውን ገልፀዋል።
በመጨረሻም ዋና አስተዳዳሪው እንዳሉት አዲሱ አመት የሠላም ፣የጤና ፣የብልፅግና፣ የፍቅርና የሀገረችን ህዝቦች አብሮነት ደምቆ የሚታይበት ዓመት እንዲሆን በመመኘት ለወረዳው ነዋሪዎችና ለመላው ኢትዮጵያዊያን የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።
ጳጉሜ 04/2017 ዓ.ም
በጉራጌ ዞን ገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ የቦኔ ቀበሌ በመኸር እየለሙ የሚገኙ ሰብሎች እና የመስኖ ቅድመ ዝግጅት በመደብ ደረጃ ያለበት ቁመና በምስል በከፊል፦
