ru
Feedback

Не попадитесь на канал ботавода! Telemetrio находит и помечает такие каналы 👉 Хотите видеть метку — оформите подписку

Bureau of Labor and Skills-Dire Dawa

Bureau of Labor and Skills-Dire Dawa

Открыть в Telegram
1 328
Подписчики
+224 часа
+87 дней
+9530 дней
Архив постов
#ዜና| በኮሌጅ ውስጥ የሚገኙ ሴት ሰራተኞችን ቀጣይነት ባለው ስልጠና አቅማቸውን ማጎልበት እንደሚያስፈልግ ተገለጸ፡፡ ድሬዳዋ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ EASTRIP ፕሮጀክት በስርዓተ-ፆታ ላይ የተመሰረተ ጥ
+7
#ዜና| በኮሌጅ ውስጥ የሚገኙ ሴት ሰራተኞችን ቀጣይነት ባለው ስልጠና አቅማቸውን ማጎልበት እንደሚያስፈልግ ተገለጸ፡፡ ድሬዳዋ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ EASTRIP ፕሮጀክት በስርዓተ-ፆታ ላይ የተመሰረተ ጥቃትን እንዲሁም የህይወት ክህሎት እና ስራ ፈጠራ በተመለከተ የአቅም ግንባታ ስልጠና የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ከኮሌጁ እና ከሐረማያ ዩኒቨርሲቲ በተጋበዙ አሰልጣኞች ለሴቶች የአስተዳደር ሰራተኞች በዛሬው እለት መሰጠት ተጀመረ፡፡ በስልጠናው ላይ በመገኘት ስልጠናውን በንግግር የከፈቱት የኮሌጁ ም/ዲን ወ/ሮ ትግስት በዙ እንደ ገለጹት እንደሚታወቀው ሃገራችን ኢትዮጵያ አሁን ላለችብት እድገት እንዲሁም ቀጣይ ለምትደርስበት የእድገት ደረጃ ለመድረስ የሴቶች ተሳትፎ ወሳኝ ነዉ። ስለዚህ ሴቶችን በህይወት ክህሎት እንዲሁም በስራ ፈጠራ ላይ ማብቃት ያስፈልጋል ብለዋል፡፡ ምክትል ዲኗ አያይዘውም በስርአተ-ፆታ ላይ የተመሰረቱ ጥቃቶችን አብዛኛው ጊዜ ሴቶች እንዲሁም ህጻናት ላይ የሚደርስ እንደመሆኑ መጠን ሁሉም አካላት ሊቃወሙትና ሊታገሉት እንደሚገባ በስልጠናው ላይ ለተሳተፉ አካላት አስገንዝበዋል፡፡ በስልጠናው ላይ በኮሌጁ የሚገኙ ሴት አመራሮች፣ሴት ኬዝ ቲም አስተባባሪዎች እንዲሁም ሁሉም ሴት ሰራተኞች የተሳተፉ ሲሆን ስልጠናው ለ5 ቀን የሚቆይ ይሆናል፡፡ የኮሌጁ ኮምኒኬሽን የካቲት 5/2017 ዓ.ም ድሬዳዋ

#ዜና | የፀሀይ ታዳሸ ሀይልን ለወጣቶች የስራ አድል ፈጠራ ያለው አበርክቶት ከፍተኛ በመሆኑ ትኩረት ሊሰጠው ይገባል ተባለ። ADRA ኢትዮጵያ ግብረሰናይ ድርጅት 5.2 ኪሎ ዋት የሚያመነጭ የፀሀይ ሀይል ኤሌትሪክ መሳሪያ ለኢትዮ-ጣሊያን ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ ለገሠ። በ2001 ወደ ስራ የገባው የኢትዮ-ጣሊያን ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ ከደረጃ 1-5 በማንፋክቸሪንግ ኤሌክትሪክ አውቶ እና ሰርቬይንግን ጨምሮ በ9 የትምህርትና የስልጠና ዲፓርትመንቶች እያሰለጠነ ይገኛል። ኮሌጁ ADRA ኢትዮጵያ ከተባለ ግብረ ሰናይ ድርጀት ጋር በመተባበርና በፀሀይ የኤሌትሪከ ሀይል ማምረቻ ተከላ እና ጥገና ዙሪያ ወጣቶችን እያሰለጠነ ይገኛል። ለሁነቱ የተግባር መማሪያ የሚያስፈልግ 5.2 ኪሎ ዋት የሚያመነጨ የፀሀይ ሀይል ማመንጫ መሳርያ ለኮሌጁ ለግሶል። በኩነቱ ላይ የተገኙት የአስተዳደሩ ስራ ከህሎት አና ቴክኖሎጂ ቢሮ ምክትል አና የቴክኒክ ሞያ ኤጀንሲ ሀላፊ ወይዘሮ ፈጡም ሙስጠፋ በአስተዳደሩ ስራ አጥነትን ለመቅረፍ በሚደረገው ጥርት ወጣቶችን ስልጠናውን እንዲወስዱ እየተደረገ ይገኛሉ ብለዋል።በተለይም የገጠር ቀበሌዎችን የኤሌትሪክ ሀይል ተጠቃሚ ከማድረግ ጎን ለጎን ወጣቶችን በማደራጀት የስራ እድል ተጠቃሚ አንዲሆኑ ያደርጋል ሲሉ ገልፀዋል። የADRA ኢትዮጵያ የፕሮጀከት ዳይሬክተር ዶክተር ዘሪሁን ሀዋኖ በበኩላቸው ከኮሌጁ ጋር በመተባበር ባለፉት 2 አመታት 90 ወጣቶችን በዘርፉ ማሰልጠናቸውን ገልፀው እርዳታው ሰልጣኞች በዘረፉ በቂ እውቀት እንዲጨብጡ እንዲሁም የራሳቸውን ስራ እንዲፈጥሩ ያደረጋል ብለዋል። #DireTv አማርኛ የካቲት 4/2017

ለህጋዊና  ደህንነቱ የተረጋገጠ የውጭ ሀገር ሥራ ስምሪት ተጠቃሚ ለመሆን ምን ማድረግ እንዳለብዎ ያውቃሉ? ✅ ካሉበት ሆነው የእጅ ስልዎን በመጠቀም በኢትዮጵያ የሥራ ገበያ መረጃ ስርዓት (www. lmis.gov.et ) ላይ አስፈላጊውን ምዝገባ ያከናውኑ፣ ✅ የባለሙያ ድጋፍ ከፈለጉ አቅራቢያዎ በሚገኝ አንድ ማዕከል በመሄድ ምዝገባውን ማካሄድ ይችላሉ፣ ✅በግለሰቡ እንዲሞሉ የቀረቡ መረጃዎችን ሞልተው ሲያጠናቅቁ  8 ዲጅት ያለው ቁጥር መልዕክት በስልክዎ ይደርስዎታል፡፡ ✅ ቀጥሎ  የተላከልዎትን የባዮሜትሪክ ቁጥር ይዘው በአቅራቢያዎ ወደ ሚገኝ የአንድ ማዕከል አገልግሎት በመሄድ አሻራ መስጠት ይኖርብዎታል፣ ✅መረጃዎቹን ሰጥተው ሲያጠናቅቁ በስልክዎት አስር ዲጂት ያለው የሰራተኛ መለያ መታወቂያ ቁጥር የያዘ መልዕክት ይደርስዎታል፡፡ በዚህም በኢትዮጵያ የሥራ ገበያ መረጃ ስርዓት ምዝገባው ተጠናቀቀ ማለት ነው። ቀጣይ ሂደቶቹን ለማወቅና ተከታታይ ወቅታዊ መረጃ እንዲደርስዎ ገፃችንን ይከታተሉ። 📢ልብ ይበሉ ✅ ለእነዚህ አገልግሎቶች ምንም አይነት ክፍያ አይጠየቁም! ✅ተጨማሪ መረጃዎችን በአቅራቢያዎ ከሚገኙ የአንድ ማዕከል አገልግሎት መስጫ ጣቢያዎች ማግኘት ይችላሉ! #LegalOverseasEmployment #OverseasOpportunities  #ህጋዊአማራጭ  #ደህንነቱየተጠበቀሥራስምሪት  ለወቅታዊ ትኩስ የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር መረጃ ፡ የካቲት 4፤ 2017 በድረገጽ፡- http://mols.gov.et/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/MolsFDRE ቴሌግራም፦ https://t.me/fdre_mols

#Oduu gammachiisaa!!! Warra barnota fi leenjii digrii barbaaddan hundaaf! Inistiitiyuutii Leenjii Teeknikaa fi Ogummaa Federaalaa Rippabiliika Dimookiraatawaa Itiyoophiyaa, Mooraa Saatalaayitii Kolleejjii Pooliteeknikii Dire dawaa bara barnootaa 2017tti dabalataan leenjii idilee digrii tokkoffaa sagantaa galgalaa (extension) fi sagantaa dhuma torbee (weekend) Leenjiiwwan Idilee: 1. Automotive Teeknooloojii 2. Construction Teeknooloojii 3. Electrical Electronics Teeknooloojii 4. Garment Teeknooloojii 5. Manufacturing Teeknooloojiidhaan. Qophii leenjii fi galmee iyyattoota ulaagaa galmee guutan xumuruu isaa, gammachuu guddaadhaan isin beeksifna

🌍ደህንነቱ የተረጋገጠ የውጭ ሀገር ሥራ ስምሪት፣ ለሁለንተናዊ ተጠቃሚነት🌍 የውጭ ሀገር ሥራ ስምሪት የዜጎችን መብት፣ ደህንነትና ተጠቃሚነት ባረጋገጠ መልኩ ተግባረዊ እየተደረገነው፡፡ በዚህም ባለፉት ሦስት ዓመታት በርካታ ዜጎችን ተጠቃሚ ማድረግ ተችሏል፡፡ በሥራ ስምሪቱ ዙሪያ ተጨማሪ ግልጽነት ለመፍጠር፣ ዜጎች ህጋዊ ባልሆኑ አማራጮች ላልተፈለገ ወጪና እንግልት እንዳይዳረጉ ከዛሬ ጀምሮ በማህበራዊ ትስስር ገጾቻችን ተከታታይ መረጃዎችን እናጋራለን፡፡ 📌ምን ምን ጉዳዮች ተካተዋል? ✅ ቁልፍ መስፈርቶ፦ በሥራ ስምሪቱ ተጠቃሚ ለመሆን ማሟላት ስላለብዎ ጉዳዮች፣ ✅ ዋና ዋና ሂደቶች፦ ህጋዊ የሥራ ስምሪት ተጠቃሚ ለመሆን መከተል      ያለብዎት ሂደት፣ ✅ ስለስልጠና ማዕከላትና ክፍያ ስርዓት፦ የትኛው ስልጠናና የሥልጠና     ማዕከል ክፍያ ይጠይቃል? ✅ የኤጀንሲዎች ዝርዝርና ህጋዊ ሥራ ስምሪት የሚካሄድባቸው፦ ህጋዊ ስራ ስምሪት ላይ ፍቃድ ያላቸው ኤጀንሲዎችና መዳረሻ ሀገራት፣ ✅ለሰለጠኑና በከፊል ለሰለጠኑ ባለሙያዎች ያሉ ዕድሎች፦ በተለያየ ደረጃ የሚገኙ ባለሙያዎች በሥምሪቱ ያላቸው እድልና መከተል ያለባቸው ቅደም          ተከተል፣ ✅ስኬታማ ታሪኮች፦ የህጋዊ ስራ ስምሪት ፋይዳዎች እና ስኬታማ ታሪኮች፣ ✅የርቀት የሥራ ዕድል፦ ካሉበት ሆነው ተጨማሪ ገቢ ማግኘት ስለሚችሉበት የርቀት ሥራዎች፣ ✅ጥያቄና መልስ፦ በሥምሪቱ ላይ ለሚነሱ ጥያቄዎች ምላሽ ይሰጣል፣ 📢 የእርስዎ ሚና የማይተካ ነው!📢 ✅ ይህንን መረጃ በማጋራት ዜጎቻችን በህገወጦች አማላይ ማስታወቂያ ተታለው ላልተፈለገ ወጪና እንግልት ብቻ ሳይሆን ለከፋ አደጋ እንዳይጋለጡ የበኩልዎን ይወጡ!🚨 ✅ በሥራ ስምሪቱ ላይ ማንኛውንም ጥያቄ ካልዎት ያድርሱን፣ 📟ይከታተሉን! 🎯 ወቅታዊ መረጃዎችን ያግኙ! ለወዳጅ ለጓገኛዎ ያጋሩ! ስለ ውጭ ሀገር ሥራ ስምሪት ማንኛውም ጥያቄ ካለዎት ይላኩልን! 🎯 በውጭ ሀገር የሥራ ስምሪት ተጠቃሚ ለመሆን ፍላጎት ካልዎት ህጋዊና  ደህንነቱ የተረጋገጠ የውጭ ሀገር ሥራ ስምሪትን ብቻ ይጠቀሙ፣ ሌሎችም     እንዲጠቀሙ ያበረታቱ፣ እራሰዎንና ሌሎችንም ከአደጋ ይጠብቁ!  

photo content

#በመካከላችን የቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና ዘርፍ ከሚመራበት መርሆች መካከል አካታችነት አንዱ ሲሆን በዚህም አካል ጉዳተኞች በመሰልጠንም ሆነ በማሰልጠን ሂደት ውስጥ እንዲሳተፉና ተጠቃሚነታቸው እንዲረጋገጥ ያደርጋል። የማነ ግርማ ይባላል በድሬዳዋ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ 13 አመታትን ያስቆጠረ የስራ ላይ ቆይታ አለው ወደ ስራ አለም ከመቀላቀሉ አስቀድሞ በፈርኒቸር ሜኪንግ በደረጃ 1 እና 2 እዚያው በኮሌጁ የሰለጠነ ሲሆን ስልጠናውን እንዳጠናቀቀም ኮሌጁ በወርክሾፕ ቴክኒሺያንነት የስራ ዕድል አመቻችቶለታል በተጨማሪም በደረጃ 3 እና 4 በኢትዮ ጣሊያን ፖሊቴክኒክ ስልጠናውን ተከታትሎ አጠናቋል። የዚህ ሳምንት የሥራና ክህሎት ቤተሰብ እንግዳችን ብርቱና በኮሌጁ ውስጥ የሚሰሩ ልዩ ልዩ ቴክኖሎጂዎችና የእንጨት ስራዎች ላይ በግንባር ቀደምነት የምናገኘው በስራውም ታታሪና ታዛዥ እንደሆነ የኮሌጁ ዲኖችና አብረውት የሚሰሩ አሰልጣኝ መምህራን ይመሰክራሉ፤ የማነ መስማት የተሳነው ሲሆን ከሰዎች ጋር ለመግባባት የማይቸግረው ጥሩ ተግባቢና በኮሌጁ ውስጥ ለአዲስ ገቢ ሰልጣኞች የምልክት ቋንቋ ስልጠና ድጋፍ እንደሚያደርግ ማወቅ ችለናል። ክህሎትና ሥራ ለሁሉም ከሁሉም በሁሉም!

photo content
+9

photo content
+9

የኢትዮ-ጣሊያን ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ የ2017 በጀት አመት የተቋሙን የ6ወር አፈፃፀም እና የEASE ፕሮጀክትን እስካሁን ተደረሰበትን አፈፃፀም ሪፖርት ለኮሌጁ ማህበረሰብ ቀርቦ ውይይት ተካሄደ:: መድረኩን በንግግር ያስጀመሩት የኮሌጁ ዲን አቶ ታደለ አሰፋ በንግግራቸውም እንደ ተቋም ከዚህ አመት ጀምሮ በርካታ ዘርፈብዙ ስራዎችን ለማከናወን የአጭርና የረጅም ጊዜ እቅዶችን በመንደፍ ወደተግበራ መገባቱን አስታውሰው ይህ ውጤታማ እንዲሆንም የኮሌጁን ማህበረሰብ የነቃ ተሳትፎን ከመቼው ጊዜ በላይ የሚጠይቅ ወቅት በመሆኑ ሁሉም አካል በዚህ አግባብ ተነሳሽነት በማሳይት ተልኮን መፈፅም እንደሚገባም ገልፀዋል:: በእለቱ በተካሄደው መድረክ የኮሌጁን የ2017 በጀት አመት የ6ወር አፈፃፀም ያቀረቡት የኮሌጁ የእቅድና በጀት ስራ ክፍል ሀላፊ አቶ አለማየሁ ብርሃኑ ሲሆኑ በቀረበው ሪፖርትም ኮሌጁ የበጀት አመቱን ትግበራን ከጀመረበት የዝግጁነት ምዕራፍ ወቅት አንስቶ በ6ወር ውስጥ የነበረውን አጠቃላይ ንቅስቃሴ በዝርዝር ያቀረቡ ሲሆን አክለውም ኮሌጁ እስከ በጀት አመቱ መጠናቀቂያ ድረስ ለትግበራ በእቅድ የያዛቸውን ተግባራት ለመድረኩ ተሳታፊዎች አመላክተዋል:: በመቀጠል የEASE ፕሮጀክት ወደ ትግበራ ከገባበት ጊዜ አንስቶ የተከናወኑ ስራዎችን አፈፃፀም ሪፖርት በEASE ፕሮጀክት የሞኒተሪንግና ኢቫሉዌሽን አስተባባሪ ኢንጂነር ህይወት እሸቱ አማካኝነት ለተሳታፊዎች የቀረበ ሲሆን በቀረበው አፈፃፀምም የፕሮጀክቱን ባለሙያዎች ከማዋቀርና የኢንዱስትሪ አድቫይዘሪንግ ቦርድ ከማቋቋም አንስቶ የፕሮጀክቱ አመራሮችንና ባለሙያዎችን በልምድ ልውውጥና ስልጠናዎች የማብቃት እንዲሁም 65 ለሚሆኑ የተቋሙ አገልግሎት ሰጪ ሰራተኞች የአቅም ግንባታ ስልጠና እንዲወስዱ ማድረግ መቻሉም ተገልፇል:: በተጨማሪም በቀረበው ሪፖርት በአስተዳደሩ ለሚገኙ የሚዲያ ባለሙያዎች እና የአንደኛና ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት አመራሮችና ተማሪዎች ስለ ዘርፉ ያለውን የተዛባ አመለካከት መቀየር የሚያስችል የግንዛቤ ማስጨበጫ መድረክ መካሄዱም በሪፖርቱ ከቀረቡት ነጥቦች የሚጠቀሱ ናቸው:: በመጨረሻም የEASE ፕሮጀክት የቀጣይ ስድስት ወራት እቅድ በፕሮጀክቱ አስተባባሪ ኢንጂነር ፋሲል ማዘንጊያ አማካኝነት ለተሳታፊዎች የቀረበ ሲሆን በዚህም በቀጣይ ዘርፈ ብዙ ተግባራትን ለመፈፀም በእቅዱ ላይ የተመላከት ሲሆን ከነዚህም ውስጥ በተቋሙ የሪኢኖቬሽን ስራዎች ፣ የአሰልጥኞች ስልጠና፣ የኢንተርፕሩነርሺፕ ስልጠናዎች፣ የሴቶችን መደገፍና ማብቃት እንዲሁ የተለያዩ የአቅም ግንባታ ስልጠዎችን ተግባራዊ ለማድረግ መያዙ ከብዙ ጥቂቱ መሆኑን በቀረበው እቅድ ተመላክቷል:: የመድረኩ ተሳታፊዎች በቀረበው የአፈፃፀም ሪፖርትና የቀጣይ እቅድን መነሻ በማድረግ ለቀጣይ ትግባራት ውጤታማነት የሚረዱ ገንቢ እስተያየቶችና ምክረ ሃሳቦች በስፋት አንስተው ውይይት ተደርጎበት መድረኩ ፍፃሜውን አጊኝቷል:: የኢትዮ-ጣሊያን ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ ኮሚኒኬሽን የካቲት 1/2017 ዓ.ም

የኢትዮ-ጣሊያን ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ የ2017 በጀት አመት የመደበኛ ስራ 6ወር አፈፃፀምና የEASE ፕሮጀክት የሩብ አመት አፈጻጸምን ለኮሌጁ የቦርድ አባላት አቀረበ፡፡ የተቋሙን የስራ አፈፃፀም ሪፖርት እንዲሁም የEASE ፕሮጀክት አፈጻጸም በኮሌጁ ዲን አቶ ታደለ አሰፋ አማካኝነት ለቦርዱ የቀረበ ሲሆኑ በዚህም ኮሌጁ ከዝግጅት ምእራፍ ጀምሮ በ6ወሩ ውስጥ የነበረውን የእቅድ አፈፃፀምና የተሰሩ ስራዎችን እንዲሁም የተገኙ ውጤቶችን የገለፁ ሲሆን አያይዘውም በቀጣይ በተቋሙ ሊሰሩ በእቅድ የተያዙ ስራዎችን ለቦርድ አባላት አቅርበዋል፡: በመድረኩ የቀረበውን ሪፖርት መነሻ በማድረግም የቦርድ አባላቱ ሀሳብ አስተያየታቸውን የሰጡ ሲሆን በተጨማሪም ኮሌጁ በቀጣይ በሚኖረው እንቅስቃሴ ላይ ምክረ-ሃሳባቸውን አስቀምጠዋል:: በመጨረሻም የኮሌጁ ቦርድ ሰብሳቢ እንዲሁም የንግድ፣ ኢንዱስትሪና ኢንቨስትመንት ቢሮ ኃላፊና የድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ አቶ ሀርቢ ቡህ በኮሌጁ እቅድ አፈፃፀም እንዲሁም በፕሮጀክቱ ትግበራ አፈጻጸም ላይ ማጠቃለያ እና የቀጣይ ስራ አቅጣጫና መመሪያም ሰጥተዋል፡፡ የኢትዮ-ጣሊያን ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ ኮሚኒኬሽን ጥር 30/2017 ዓ.ም

ከአመታት በኋላ ህዳሴ የሆነለት ፕሮጀክት… “ፕሮጀክቱ በአጭር ጊዜ ውስጥ የቅድመ ዝግጅት ስራውን በማጠናቀቅ ተመርቆ ሙሉ ለሙሉ ወደ ስራ የሚገባ ይሆናል” አቶ ሮቤል ጌታቸው የድሬዳዋ አስተዳደር ሥራና ክህሎት ቢሮ ኃላፊ መንግስት ኢንዱስትሪዎችን ለመደገፍና ሊያግዙ የሚችሉ የተርን ኪ ፕሮጀክቶች በአገሪቱ የተለያዩ ቦታዎች ማቋቋሙ የሚታስ ነው፤ ከነዚህም ውስጥ በድሬዳዋ የሚገኘው ፕሮጀክት አንዱ ሲሆን ምርቶችን እያመረተ ለፋብሪካዎች ግብአት እንዲያቀርብ ታልሞ የተመሰረተ ቢሆንም ባለፉት ዘጠኝ አመታት ግንባታው ተጠናቆና ማሽኖቹ ተሟልተው ወደ ስራ መግባት ሳይችል ለታለመለት አላማም ሳይውል በተለያዩ ምክንያቶች ያለምንም ስራ አስተዳደሩንና ነዋሪውን እንደታሰበው ሳይጠቅም ቆይቷል፡፡ ይሁንና የድሬዳዋ አስተዳደር ክቡር ከንቲባ ከድር ጁሃር በሰጡት አቅጣጫ ማሽኖቹ ወደ ስራ ገብተው የስራ እድል ሚፈጥሩበት፣ የፋብሪካ ግብዓቶችን የሚያቀርቡበት እንዲሁም የቴክኒክና ሙያ ሰልጣኞች የተግባር ስልጠና የሚያገኙበት ለማድረግ ፕሮጀክቱ ወደ ድሬዳዋ አስተዳደር ሥራና ክህሎት ቢሮ ስር መጥቶ በስሩ ወደ ሚገኘው የድሬዳዋ ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ ተላልፎ ውጤት አምጪ ስራዎችን ለመስራት እንቅስቃሴዎች የተደረጉ መሆኑንና ሙሉ ለሙሉ ወደ ስራ ለማስገባት የተከናወኑ ስራዎችን በምን ሁኔታ ላይ እንደሚገኙ የመስክ ምልከታ መደረጉን የቢሮው ኃላፊ አቶ ሮቤል ጌታቸው ተናግረዋል፡፡ የድሬዳዋ ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ ዲን አቶ ሳላህዲን አብዱልሃሚድ በበኩላቸው የተርን ኪ ፕሮጀክት ለአስተዳደሩ ነዋሪ ከስልጠና በላይ የሚታሰበውን የቴክኒክና ሙያ ዘርፍ እሳቤን ተጨባጭ ለማድረግ አጋዥ ሆኖ ተገኝቷል፤ በዚህም ሰልጣኞች በተግባር ልምምድ የሚያደርጉበትና የስራ እድል እንዲፈጠርላቸው የሚያመቻች ሲሆን በአጠቃላይ ትምህርትና ስልጠናውን፣ የኢንዱስትሪ ኤክስቴንሽንና ቴክኖሎጂ ሽግግር ስራዎችን በተሻለ አቅም ለመምራት የሚያስችል ይሆናል ብለዋል፡፡ በኮሌጁ የማኑፋክቸሪንግ ዲፓርትመንት ኃላፊና አሰልጣኝ መምህር የሆነው ዮሐንስ ተካ እንደገለጹት በኮሌጅ ለሚሰጠው ትምህርትና ስልጠና ፕሮጀክቱ አጋዥነት በቀጥታ የትምህርትና ስልጠና ጥራትን ከመጨመር አኳያ ሰልጣኞች ተግባራዊ የሆነ ልምድ እንዲያካብቱ የሚያግዝ መሆኑ ከኮሌጅ አጠናቀው ሲወጡ በራሳቸውም ሆነ በኢንዱስትሪዎች ላይ ተሰማርተው ሲሰሩ በክህሎት የበቁ እንደሚያደርጋቸው ገልጸዋል፡፡ የሥራና ክህሎት ቢሮ ህዝብ ግንኙነት ጥር 30/2017 ዓ.ም ድሬዳዋ

ከአመታት በኋላ ህዳሴ የሆነለት ፕሮጀክት… “ፕሮጀክቱ በአጭር ጊዜ ውስጥ የቅድመ ዝግጅት ስራውን በማጠናቀቅ ተመርቆ ሙሉ ለሙሉ ወደ ስራ የሚገባ ይሆናል” አቶ ሮቤል ጌታቸው የድሬዳዋ አስተዳደር ሥራና ክህሎት ቢሮ ኃላፊ መንግስት ኢንዱስትሪዎችን ለመደገፍና ሊያግዙ የሚችሉ የተርን ኪ ፕሮጀክቶች በአገሪቱ የተለያዩ ቦታዎች ማቋቋሙ የሚታስ ነው፤ ከነዚህም ውስጥ በድሬዳዋ የሚገኘው ፕሮጀክት አንዱ ሲሆን ምርቶችን እያመረተ ለፋብሪካዎች ግብአት እንዲያቀርብ ታልሞ የተመሰረተ ቢሆንም ባለፉት ዘጠኝ አመታት ግንባታው ተጠናቆና ማሽኖቹ ተሟልተው ወደ ስራ መግባት ሳይችል ለታለመለት አላማም ሳይውል በተለያዩ ምክንያቶች ያለምንም ስራ አስተዳደሩንና ነዋሪውን እንደታሰበው ሳይጠቅም ቆይቷል፡፡ ይሁንና የድሬዳዋ አስተዳደር ክቡር ከንቲባ ከድር ጁሃር በሰጡት አቅጣጫ ማሽኖቹ ወደ ስራ ገብተው የስራ እድል ሚፈጥሩበት፣ የፋብሪካ ግብዓቶችን የሚያቀርቡበት እንዲሁም የቴክኒክና ሙያ ሰልጣኞች የተግባር ስልጠና የሚያገኙበት ለማድረግ ፕሮጀክቱ ወደ ድሬዳዋ አስተዳደር ሥራና ክህሎት ቢሮ ስር መጥቶ በስሩ ወደ ሚገኘው የድሬዳዋ ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ ተላልፎ ውጤት አምጪ ስራዎችን ለመስራት እንቅስቃሴዎች የተደረጉ መሆኑንና ሙሉ ለሙሉ ወደ ስራ ለማስገባት የተከናወኑ ስራዎችን በምን ሁኔታ ላይ እንደሚገኙ የመስክ ምልከታ መደረጉን የቢሮው ኃላፊ አቶ ሮቤል ጌታቸው ተናግረዋል፡፡ የድሬዳዋ ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ ዲን አቶ ሳላህዲን በበኩላቸው የተርን ኪ ፕሮጀክት ለአስተዳደሩ ነዋሪ ከስልጠና በላይ የሚታሰበውን የቴክኒክና ሙያ ዘርፍ እሳቤን ተጨባጭ ለማድረግ አጋዥ ሆኖ ተገኝቷል፤ በዚህም ሰልጣኞች በተግባር ልምምድ የሚያደርጉበትና የስራ እድል እንዲፈጠርላቸው የሚያመቻች ሲሆን በአጠቃላይ ትምህርትና ስልጠናውን፣ የኢንዱስትሪ ኤክስቴንሽንና ቴክኖሎጂ ሽግግር ስራዎችን በተሻለ አቅም ለመምራት የሚያስችል ይሆናል ብለዋል፡፡ በኮሌጁ የማኑፋክቸሪንግ ዲፓርትመንት ኃላፊና አሰልጣኝ መምህር የሆነው ዮሐንስ ተካ እንደገለጹት በኮሌጅ ለሚሰጠው ትምህርትና ስልጠና ፕሮጀክቱ አጋዥነት በቀጥታ የትምህርትና ስልጠና ጥራትን ከመጨመር አኳያ ሰልጣኞች ተግባራዊ የሆነ ልምድ እንዲያካብቱ የሚያግዝ መሆኑ ከኮሌጅ አጠናቀው ሲወጡ በራሳቸውም ሆነ በኢንዱስትሪዎች ላይ ተሰማርተው ሲሰሩ በክህሎት የበቁ እንደሚያደርጋቸው ገልጸዋል፡፡ የሥራና ክህሎት ቢሮ ህዝብ ግንኙነት ጥር 30/2017 ዓ.ም ድሬዳዋ

photo content
+9

#ዜና የቢሾፍቱ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ የማኔጅምንት አባላት በድሬዳዋ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ የመስክ የስራ ጉብኝት አደረጉ፡፡ በመስክ ጉብኝቱ ላይ በመገኘት የእንኳን ደህና መጣችሁ ንግግር ያደረጉት እና ኮሌጁ
+5
#ዜና የቢሾፍቱ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ የማኔጅምንት አባላት በድሬዳዋ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ የመስክ የስራ ጉብኝት አደረጉ፡፡ በመስክ ጉብኝቱ ላይ በመገኘት የእንኳን ደህና መጣችሁ ንግግር ያደረጉት እና ኮሌጁን እንቅስቃሴ ያስጎበኙት የኮሌጁ ዲን አቶ ሰለሃዲን አብዱልሃሚድ ሲሆኑ በንግግራቸውም እንኳን ወደ ምስራቅ አፍሪካ የልህቀት ማእከል ወደ ሆነው የድሬዳዋ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ በደህና መጣችሁ ፡፡ ኮሌጁ በቀጣይ በተለያዩ የሞያ መስኮች የልህቀት ማእከል እንደመሆኑ መጠን ለድሬዳዋ ብሎም ለምስራቁ የሃገራችን ክፍል ከዛም አልፎ ለሃገራችን ብቁ የሆኑ በሙያ እንዲሁም በክህሎት የበለጸጉ ስራ ፈጣሪ የሆኑ ወጣቶችን እያፈራ ይገኛል ያሉ ሲሆን አያይዘውም በኮሌጁ እየተተገበሩ ያሉ ፕሮጀክቶች እንዲሁም መደበኛው ስራ ከ12ቱ የቴክኒክና ሙያ እሳቤዎች አንጻር የተቃኙ ናቸው ብለዋል፡፡ የመስክ ምልከታውን መሰረት በማድረግም የልኡካን ቡድኑ ጋር በነበረው የጋራ ውይይት ወቅት ልኡክ ቡድኑን የመሩት የቢሾፍቱ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ዲን አቶ ደበላ ተስፋ እንዳሉት አጠቃላይ የኮሌጁ እንቅስቃሴ እጅግ በጣም ጥሩ የሚባልና የልህቀት መአከል ግንባታ በከፍተኛ ፍጥነት ተከናውኖ ለሚፈለገው አላማ መዋል እንዲችል የድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር እየወሰደ ያለው ቁርጠኝነት ለሌሎች ከተሞች አራያ መሆን የሚችል ነው ብለዋል፡፡በኮሌጁ የሚገኙ የተለያዩ ትምህርት ክፍሎች ያላቸው አቅም ከሌሎች ኮሌጆች አንጻር ከድሬዳዋ አልፎ ለመላው ሃገራችን የሚበቃ ነው ብለዋል፡፡ በመስክ ጉብኝቱ ወቅት የድሬዳዋ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ እና የፕሮጀክቶ አፈጸጸም እንዲሁም የግንባታ ሂደቱን እስካሁን የደረሰበት ደረጃ በአቶ መሃመድአወል ጠሃ ገለጻ ተደርጓል፡፡ የኮሌጁ ኮምኒኬሽን ጥር 29/2017 ዓ.ም ድሬዳዋ