ru
Feedback

Не попадитесь на канал ботавода! Telemetrio находит и помечает такие каналы 👉 Хотите видеть метку — оформите подписку

Bureau of Labor and Skills-Dire Dawa

Bureau of Labor and Skills-Dire Dawa

Открыть в Telegram
1 329
Подписчики
+324 часа
+87 дней
+8330 дней
Архив постов
#ዜና በ2017 ዓ/ም ወደ ቴክኒክና ሙያ ኮሌጆች የሚገቡ ሰልጣኝ ተማሪዎችን ለመቀበል ዝግጅት መጠናቀቁንና ኮሌጆች መቀበል መጀመራቸውን የድሬዳዋ አስተዳደር የሥራና ክህሎት ቢሮ አስታወቀ፤ በሀገር አቀፍ ደረጃ የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ውጤት መለቀቅን ተከትሎ በ2017 ዓ/ም ወደ ቴክኒክና ሙያ ኮሌጆች የሚገቡ ሰልጣኝ ተማሪዎችን ለመቀበል ዝግጅት መጠናቀቁንና ኮሌጆች ምዝገባ መጀመራቸውን የድሬዳዋ አስተዳደር የሥራና ክህሎት ቢሮ ምክትል ኃላፊና የቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና ኤጀንሲ ኃላፊ ወ/ሮ ፈጡም ሙስጠፋ በዛሬው ዕለት ለሚዲያ አካላት በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ አስታውቀዋል፡፡ የድሬዳዋ አስተዳደር የሥራና ክህሎት ቢሮው አዳዲስ ሰልጣኝ ተማሪዎች ወደ ቴክኒክና ሙያ ኮሌጆች እንዲገቡ በማድረግ ረገድ ሰፊ ስራ መሰራቱን ገልጸዋል፡፡ በዚህም በአስተዳደሩ 6 የግል እና 2 የመንግስት ኮሌጆች ሰልጣኝ ተማሪዎችን ለመቀበል ሙሉ ዝግጅቶች የተጠናቀቁ ሲሆን ሰልጣኝ ተማሪዎች ከምዝገባ በፊት አዋጭ የትምህርት ዘርፎችን የመለየት በተለይም አስተዳደሩ የኢንዱስትሪ ማዕከል እንደመሆኑ መጠን ሀገር አቀፍ እና አለምቀፍን የሚያስተሳስሩ  የዲጂታላይዜሽን ስልጠናዎችን ጨምሮ ስለሚሰጥ ሰልጣኞች አውቅና እና ብቃት ካላው ኮሌጆች ጋር ተገናገኝተው ዘርፉን መምረጥ እንደሚገባም ነው ኃላፊዋ ያብራሩት፡፡   በተጨማሪም ከዚህ ቀደም በደረጃ 3 እና 4 ላይ ብቻ ትኩረት አድርጎ የመቀበል አዝማሚያዎች እንዳሉ አንስተው በተያዘው በጀት አመት ሁሉም የግል እና የመንግስት ኮሌጆች ደረጃ 1 እና 2 ተቀብለው ምዝገባ እንዲያካሂዱም ነው ያሳሰቡት፡፡ ኃላፊዋ አያይዘውም ቢሮው እንደ ከዚህ ቀደሙ በአስተዳደር ደረጃ በደማቁ የቴክኒክና ሙያ ስልጠና ሳምንት(TVT Week) ለማክበር በዝግጅት ላይ መሆናቸውንና የዘርፉን ገጽታ ለመገንባት የሚያስችሉ በተጨባጭ የተሰሩ ስራዎችን ህብረተሰቡ እንዲመለከታቸው የማስተዋወቅ እና ከሚመለከታቸው የባለድርሻ አካላት ጋር ያለውን ግንኙነት እንደሚያጠናክረው ኃላፊዋ ወ/ሮ ፈጡም ሙስጠፋ ጨምረው ገልጸዋል፡፡  በመሆኑም ሰልጣኝ ተማሪዎች የሥራ ዕድል ፈጠራን  በክህሎት በመታጀብ የተመቻቸውን ዕድል ወደ ቴክኒክና ሙያ ኮሌጆች በመምጣት እንዲጠቀሙ ጥሪ አቅርበዋል፡፡  ©️ DGC  ጥቅምት 20/2017

#ዜና በ2017 ዓ/ም ወደ ቴክኒክና ሙያ ኮሌጆች የሚገቡ ሰልጣኝ ተማሪዎችን ለመቀበል ዝግጅት መጠናቀቁንና ኮሌጆች መቀበል መጀመራቸውን የድሬዳዋ አስተዳደር የሥራና ክህሎት ቢሮ አስታወቀ፤ በሀገር አቀፍ ደረጃ የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ውጤት መለቀቅን ተከትሎ በ2017 ዓ/ም ወደ ቴክኒክና ሙያ ኮሌጆች የሚገቡ ሰልጣኝ ተማሪዎችን ለመቀበል ዝግጅት መጠናቀቁንና ኮሌጆች ምዝገባ መጀመራቸውን የድሬዳዋ አስተዳደር የሥራና ክህሎት ቢሮ ምክትል ሀላፊና የቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና ኤጀንሲ ኃላፊ ወ/ሮ ፈጡም ሙስጠፋ በዛሬው ዕለት ለሚዲያ አካላት በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ አስታውቀዋል፡፡ የድሬዳዋ አስተዳደር የሥራና ክህሎት ቢሮው አዳዲስ ሰልጣኝ ተማሪዎች ወደ ቴክኒክና ሙያ ኮሌጆች እንዲገቡ በማድረግ ረገድ ሰፊ ስራ መሰራቱን ገልጸዋል፡፡ በዚህም በአስተዳደሩ 6 የግል እና 2 የመንግስት ኮሌጆች ሰልጣኝ ተማሪዎችን ለመቀበል ሙሉ ዝግጅቶች የተጠናቀቁ ሲሆን ሰልጣኝ ተማሪዎች ከምዝገባ በፊት አዋጭ የትምህርት ዘርፎችን የመለየት በተለይም አስተዳደሩ የኢንዱስትሪ ማዕከል እንደመሆኑ መጠን ሀገር አቀፍ እና አለምቀፍን የሚያስተሳስሩ  የዲጂታላይዜሽን ስልጠናዎችን ጨምሮ ስለሚሰጥ ሰልጣኞች አውቅና እና ብቃት ካላው ኮሌጆች ጋር ተገናገኝተው ዘርፉን መምረጥ እንደሚገባም ነው ኃላፊዋ ያብራሩት፡፡   በተጨማሪም ከዚህ ቀደም በደረጃ 3 እና 4 ላይ ብቻ ትኩረት አድርጎ የመቀበል አዝማሚያዎች እንዳሉ አንስተው በተያዘው በጀት አመት ሁሉም የግል እና የመንግስት ኮሌጆች ደረጃ 1 እና 2 ተቀብለው ምዝገባ እንዲያካሂዱም ነው ያሳሰቡት፡፡ የቴ/ሙ/ት/ስ ሳምንት ሲከበርም በተለይም አጫጭር ስልጠናዎች ለስራ እድል ሰፊ እድሎችን ስለሚያመጣ ከነበረው ከአጫጭር ስልጠናዎች ውጪ በማኒፋክቸሪንግ ዘርፍ  ሌሎች ተጨማሪ ስልጠናዎችን ለመስጠት ሰፊ ስራ መሰራታቸውንም ኃላፊዋ ወ/ሮ ፈጡም ሙስጠፋ ጨምረው ገልጸዋል፡፡  በመሆኑም ሰልጣኝ ተማሪዎች የሥራ ዕድል ፈጠራን  በክህሎት በመታጀብ የተመቻቸውን ዕድል ወደ ተቋማቸው በመምጣት እንዲጠቀሙ ጥሪ አቅርበዋል፡፡  ©️ DGC  ጥቅምት 20/2017 ዓ.ም

የድሬዳዋ አስተዳደር የሥራና ክህሎት ቢሮ በማስተር ካርድ ፋውንዴሽን ስር የሚገኙ የተለያዩ ፕሮግራሞችን ከሚያስተባብሩ በአስተዳደሩ ከሚገኙ የፕሮግራም አስተባባሪዎች ጋር በሥራ ፈጠራና ክህሎት ልማት ላይ ያተኮረ ውይይት አካሂዷል፤ በመድረኩ የሥራና ክህሎት ቢሮ ም/ኃላፊ ወ/ሮ ፈጡም ሙስጠፋ ቢሮው ከተቋቋመ ጊዜ ጀምሮ ባለፉት ሦስት ዓመታት የተከናወኑ አበይት ተግባራትና የተገኙ ውጤቶች ላይ የአጋር አካላት ሚና ቀላል የማይባል መሆኑንና በቀጣይም ተቀራርቦ እና በየጊዜው ስራዎችን እየገመገሙ መሄድ አስፈላጊ በመሆኑ የዛሬው መድረክ መዘጋጀቱን ገልጸዋል፡፡ በአስተዳደሩ ከተማና ገጠር ፍትሃዊ ተደራሽነትን ለማረጋገጥ የአጋር አካላት ድጋፍ ወሳኝ መሆኑን የገለፁት የሥራ ዕድል ፈጠራ እና የአንድ ማዕከል ማስተባበሪያ ዳይሬክቶሬት አቶ ሰኢድ አሊ በማስተር ካርድ ፋውንዴሽን እየተተገበሩ የሚገኙ ፕሮግራሞችን ከዘርፉ እሳቤ ጋር የተቀናጀ እንዲሆኑ ለማስቻል ብሎም ጠንካራ ትብብር ለመፍጠር በትኩረት ይሰራል ብለዋል፡፡ በማስተር ካርድ ፋውንዴሽን ስር የሚገኙ የተለያዩ ፕሮግራሞች ሲኖሩ በዛሬው ዕለት ስራዎቻቸውን ለቢሮው አቅርበው የተገመገሙት የመስራት ስራ ፈጣሪዎች ፕሮግራም፣ ሳፊ ፕሮግራም፣ መስመር ፕሮግራም እና ሲድ ፕሮግራም ናቸው፡፡ የመስራት ስራ ፈጣሪዎች ፕሮግራም : 5 ዓመት የሚቆይ ፕሮግራም ሲሆን፣ 100 ጊግ ሞዴል ያላቸውን ቢዝነሶችን መርጦ ሁለ ገብ ድጋፍ ይሰጣል፤ ሳፊ ፕሮግራም ፋይናንሻል ቴክኖሎጂ ላይ የሚሰራ ሲሆን መደበኛ እና ኢ-መደበኛ ብድሮችን ያቀርባሉ በተለይ ለኢ-መደበኛ ተበዳሪዎች በመታወቂያ ብቻ ብድሮችን ከእጅ ንክኪ ነጻ የሆነ በAI ታግዘው ብድሮችን ያመቻቻሉ፤በዚህም በዋናነት 80% ሴቶች፣ 10% ለአካል ጉዳተኞች እና 10% ለተፈናቃዮች ትኩረት አድርጎ ይሰራል፤ መስመር ፕሮግራም የብድር አገልገሎት ሴቶችና ወጣት ሥራ ፈጣሪዎችን ለማበረታታትና ሥራቸውን ለማስፋፋት የብድር አገልገሎት ይሰጣል አገልገሎቱ በአስተዳደራችን የሚገኙ በተለይም በወጣት ሴቶች የሚመሩ የጥቃቅን፣ አነስተኛና መካከለኛ ኢንተርፕራይዞችን በመጠነኛ ዋስትናና በአነስተኛ የወለድ መጠን እንዲሁም የሸሪአ መርህን የተከተለ ከወለድ ነጻ የብድር አገልገሎት ተጠቃሚ በማድረግ ላይ ይገኛል፡፡ ሲድ ፕሮግራም እንደ ኢትዮጵያ ለአንድ ሚሊዮን ወጣቶች እና ሴቶች የሥራ ዕድል ለመፍጠር ይፈልጋል፡፡ አንድ መቶ የቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና ኮሌጆችን በማጎልበት ለውጥ አምጭ የንግድ ሞዴሎችን በማስተዋወቅ፣ የንግድ መፈልፈያ ማዕከላትን በማቋቋምና ወደ ስራ በማስገባት እንዲሁም ፍላጎትን መሰረት ያደረጉ ልማቶችን በማጎልበት የወጣቶች የስራ እድል ፈጠራን ለመደገፍ በማለም የሚተገበር ነው፡፡ የሥራና ክህሎት ቢሮ ህዝብ ግንኙነት ጥቅምት 18/2017 ዓ.ም ድሬዳዋ

photo content
+6

የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር በሚሰጠው የውጭ ሀገር የሥራ ስምሪት ህጋዊ ፈቃድ ያላቸው የውጭ ሀገር ሥራና ሠራተኛ አገናኝ ኤጀንሲዎች ዝርዝር። ህጋዊ አማራጮችን ብቻ በመጠቀም ደህንነቱ የተረጋገጠ የውጭ ሀገር ሥራ ስምሪት ተጠቃሚ ይሁኑ! ለወቅታዊ ትኩስ የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር መረጃ ፡ ጥቅምት 16፤ 2017 በድረገጽ፡- http://mols.gov.et/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/MolsFDRE ቴሌግራም፦ https://t.me/fdre_mols ዋትስአፕ፡- https://whatsapp.com/channel/0029VakCgcYIyPtTbPZtDW1y ቲክቶክ:- tiktok.com/@mols_official ሊንክዲን፡- https://www.linkedin.com/.../ministry-of-labor-skill-fdre/

"ማህበራዊ መስተጋብሩ ጠንካራ የሆነ ተቋም ተልዕኮውን ከግብ ለማድረስ የሚያደርገው ጉዞ ቀልጣፋና ውጤታማ ይሆናል" አቶ ሮቤል ጌታቸው የድሬዳዋ አስተዳደር የሥራና ክህሎት ቢሮ ኃላፊ በዛሬው ዕለት የድሬዳዋ አስተዳደር የሥራና ክህሎት ቢሮ የመረዳጃ ዕድር ይፋዊ ምስረታ እና የሸራ ምርቃት መርሃግብር ተካሄደ። በዚህ መርሃግብር ላይ የተገኙት የቢሮው ኃላፊ አቶ ሮቤል ጌታቸው አመራሩ እና ሠራተኛው በደስታና በሃዘን የሚገጥማቸውን የህይወት ገጠመኞች በመረዳዳትና በመደጋገፍ የሚያደርጉት መተጋገዝ በቀጥታ በመንግስታዊ ተልዕኮ መፈጸም ላይ አዎንታዊ ተጽዕኖ እንዳለው ገልጸው ቢሮውም ይህን መስተጋብር የሚያጠናክር ድጋፍ ማድረጉን እንደሚቀጥል ተናግረዋል። የመረዳጃ ዕድር ኮሚቴ ተወካዮች በበኩላቸው የቢሮው ኃላፊ አቶ ሮቤል ጌታቸው እና ማኔጅመንታቸው ዕድሩን የሚያጠናክሩ የተለያዩ ድጋፎችን ስላደረጉላቸው በተለይም ዋና ነገር የሆነውን ሸራ እንዲገዛ ከፍ ያለውን አስተዋጽኦ ስላበረከቱ አመሥግነዋል። የሥራና ክህሎት ቢሮ ህዝብ ግንኙነት ጥቅምት 16/2017 ዓ.ም ድሬዳዋ

በዛሬው ዕለት በድሬዳዋ አስተዳደር የሥራና ክህሎት ቢሮ እንዲሁም በድሬዳዋ ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ በክረምት በጎ ፍቃድ ለአቅመ ደካሞች የተገነቡ ቤቶችን የድሬዳዋ አስተዳደር ክቡር ከንቲባ አቶ ከድር ጁሀር መርቀው ቁልፉን ለባለቤቶቹ አስረክበዋል፡፡ በዚህም በድሬዳዋ አስተዳደር የሥራና ክህሎት ቢሮ እና በድሬዳዋ ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ በእያንዳንዳቸው ከግማሽ ሚሊዮን ብር በላይ የወጣባቸው ሁለት ሁለት ቤቶች በድምሩ ከአንድ ሚልዮን ብር በላይ ወጪ የተደረገባቸው አራት የተገነቡ ቤቶች ተመርቀዋል:: ክቡር ከንቲባ አቶ ከድር ጁሀር ቤቶቹን መርቀው ቁልፉን ለባለቤቶቹ ባስረከቡበት ወቅት ቤቶቹን ለገነቡ ሁሉም ተቋማት አመስግነው፤  እርስ በእርስ እንደ ቤተሰብ በመረዳዳት የተሰሩ ቤቶች መሆናቸውን ገልፀዋል፤ በቀጣይም ይህ የመረዳዳት ባህል ተጠናክሮ መቀጠል ይገባዋል ሲሉ ከንቲባ ከድር መልእክታቸውን አስተላልፈዋል:: የድሬዳዋ አስተዳደር የሥራና ክህሎት ቢሮ ኃላፊ አቶ ሮቤል ጌታቸው በበኩላቸው በዛሬው ዕለት እንደ ድሬዳዋ አስተዳደር በተቋማት የተሰሩ የበጎ ፈቃድ ስራዎችን በዚህ ልክ መመልከት የሚያስደስት መሆኑን ጠቅሰው ቢሮው ኮሌጆችን አስተባብሮ የድርሻውን አሻራ ማሳረፉ እንዳስደሰታቸው ተናግረዋል። የሥራና ክህሎት ቢሮ ህዝብ ግንኙነት ጥቅምት 16/2017 ድሬዳዋ

የድሬዳዋ አስተዳደር የሥራና ክህሎት ቢሮ የቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና ኤጀንሲ የኢንዱስትሪ ኤክስቴንሽንና ቴክኖሎጂ ሽግግር ዳይሬክቶሬት በኦፊስ ካይዘን ትግበራ ዙሪያ ለቢሮው ሰራተኞች ስልጠና አዘጋጀ። በዚህም ስልጠናውን ከአስተዳደሩ የካይዘን ኢንስቲትዩት በመጡ ባለሙያ የተሰጠ ሲሆን በቢሮው የሚገኙ ዳይሬክቶሬቶችና ክፍሎች በቀጣይ የሚኖረውን ትግበራ ውጤት ሊያስገኝ በሚችል መልኩ እንዲከውኑ የሚያግዝ ይሆናል። ቢሮው ለሪፎርም ስራዎች ትኩረት ሰጥቶ ሲሰራ መቆየቱ የሚታወቅ ሲሆን እነዚህም ስራዎች የሆነ ጊዜ ብቻ ተግባር አለመሆኑ በሚያሳይ መልኩ የዚህ ትግበራ አካል የሆነው ኦፊስ ካይዘንን በሁሉም የቢሮው ዳይሬክቶሬቶችና ክፍሎች ላይ ተግባራዊ ማድረግ በተለየ መልኩ ቦታ ተሰጥቶታል። የሥራና ክህሎት ቢሮ ህዝብ ግንኙነት ጥቅምት 16/2017 ዓ.ም ድሬዳዋ

ሀገር አቀፍ የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ውጤት መለቀቅን ተከትሎ በየዓመቱ ወደ ቴክኒክና ሙያ ስልጠና ተቋማት ገብተው መሰልጠን ለሚፈልጉ የመግቢያ ነጥብ ተዘጋጅቷል፤ በዚህ መሰረት ከጥቅምት 12/2017 ዓ.ም እስከ ጥቅምት 30/2017 ዓ.ም ድረስ በድሬዳዋ አስተዳደር በሚገኙ የቴክኒክና ሙያ ማሰልጠኛ ተቋማት የአዲስ ሰልጣኞችን ቅበላ(ምዝገባ) የሚያደርጉ መሆኑን  እናሳውቃለን፡፡ የሥራና ክህሎት ቢሮ ህዝብ ግንኙነት ጥቅምት 15/2017 ዓ.ም ድሬዳዋ