ru
Feedback

Не попадитесь на канал ботавода! Telemetrio находит и помечает такие каналы 👉 Хотите видеть метку — оформите подписку

Bureau of Labor and Skills-Dire Dawa

Bureau of Labor and Skills-Dire Dawa

Открыть в Telegram
1 326
Подписчики
+224 часа
+67 дней
+11030 дней
Архив постов
#ዜና|የድሬዳዋ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ የምርምር፣የቴክኖሎጂ እና ክህሎት ያላቸው ዜጎች መፍለቂያ ተቋም እንዲሆን እየተሰራ እንዳለ ተገለጸ፡፡ የድሬዳዋ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ብሩህ አእምሮዎች በክህሎት የበቁ እጆች በሚል መሪ ቃል በተዘጋጀው 4ተኛው የተግባር ተኮር ጥናትና ምርምር፣የቴክኖሎጂና የፈጠራ ስራ እንዲሁም የክህሎት ውድድር ላይ ተሳትፈው አመርቂ ውጤት ላስመዘገቡ መምህራንና ሰልጣኝ ተማሪዎች የእውቅና መርሃ ግብር አከናወነ፡፡ ኮሌጁን የምርምር፣የቴክኖሎጂ እና ክህሎት ያላቸው ዜጎች መፍለቂያ እንዲሆን እየተሰራ እንዳለ የገለጹት በመርሃ ግብሩ ላይ ተገኝተው ንግግር ያደረጉት የኮሌጁ ዲን አቶ ሰለሃዲን አብዱልሃሚድ ሲሆኑ አያይዘውም በከተማ አስተዳደሩ ለቴክኒክና ሙያ ትኩረት ተሰጥቶ ሁሉም ዜጎች ሙያቸውን እንዲያዳብሩና የስራ ፈጣሪ እንዲሆኑ በትጋት እየተሰራ ነው ይህ ተግባር ደግሞ ከግብ እንዲደርስ ኮሌጃችን ከመቼውም ጊዜ በላይ ትኩረት ሰጥቶ የሚሰራ ይሆናል ያሉ ሲሆን፡፡ በመጨረሻም ኮሌጁን ወክላችሁ በተወዳደራችሁበት መስክ አመርቂ ውጤት ላስመዘገባችሁ እና ከተማ አስተዳደሩን ወክላችሁ በአገር አቀፉ ውድድር ላይ ለምትሳተፉ በሙሉ መልካም እድል እንዲገጥማችሁ እመኛለሁ ብለዋል፡፡ በመቀጠል ንግግር ያደረጉት ደግሞ የኮሌጁ ም/ዲንና የውጤት ተኮር ትምህርትና ስልጠና ኃላፊ የሆኑት አቶ አብዱልፈታህ አፈንዲ ሲሆኑ ኮሌጁን ወክላችሁ ይህን አመርቂ ውጤት ላስመዘገባችሁ እና ይህ ውጤት እንዲመጣ ቀን ከሌት የሰራችሁ በሙሉ እንኳን ደስ አላችሁ ያሉ ሲሆን አያይዘውም ኮሌጁ ትምህርትና ስልጠናን ከመስጠት በዘለለ የቴክኖሎጂ እና የኢንተርፕራይዞች መፍለቂያ እንዲሆን ሁሉም ባለ ድርሻ አካላት የሚጠበቅባቸውን መስራት እንደሚገባቸው ተናግረዋል፡፡ ኮሌጁ በያዘው ራእይ መሰረት በኮሌጁ የሚሰለጥኑ እንዲሁም ድጋፍ የሚደረግላቸው ኢንተርፕራይዞች የፈጠራ ሃሳባቸውን ወደተግባር የሚለውጡበትን የኢንኩቤሽን ሴንተር አቋቁሞ ለሰልጣኞች እንዲሁም ለተለያዩ አካላቶች ድጋፍን እያደረገ ይገኛል ያሉት የኮሌጁ ም/ዲንና የኢ/ኤ/ቴ/ሽ ኃላፊ የሆኑት ወ/ሮ ትግስት በዙ ሲሆኑ አያይዘውም አሰልጣኞችም እንዲሁም ሰልጣኞች የሚኖርባቸውን የተለያዩ ክፍተቶችን ለመሙላት እየተሰራ እንዳለ ገልጸዋል፡፡ በእውቅና መርሃ ግብሩ ላይ በተግባር ተኮት ጥናትና ምርምር፣በቴክኖሎጂ እንዲሁም በክህሎት ውድደር አመርቂ ውጤት ላስመዘገቡ እንዲሁም ይህ ውጤት እንዲመጣ ለሰሩ ትምህርት ክፍሎች የእውቅና እና የምስጋና የምስክር ቀረቀት ተሰጥቷል፡፡ የኮሌጁ ኮምኒኬሽን ሚያዝያ 9/2017 ዓ.ም ድሬዳዋ

photo content
+9

በአስተዳደሩ ከዛሬ ጀምሮ ለሚቀጥለው አንድ ወር 232 የቴክኒክና ሙያ አሰልጣኝ መምህራን የሙያ ብቃት ምዘና እንደሚወስዱ ተገለጸ፤ በድሬዳዋ አስተዳደር የሚገኙ በሁለቱ የመንግስት ፖሊቴክኒክ ኮሌጆች አዲስ በተከለሰው የሙያ ደረጃና የሆልስቲክ ምዘና አሰጣጥ ስርዓት የሙያ ምዘና በመውሰድ ላይ እንደሚገኙ የሥራና ክህሎት ቢሮ የአሰልጣኝ ልማትና ተቋማት ጥራት ቁጥጥር ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ታሪኩ ለገሰ አስታወቁ፤ አቶ ታሪኩ አክለው ከዚህ ቀደም ቴክኒክና ሙያ ዘርፉ ከኢንዱስትሪው ጋር በመተባበር የማሰልጠኛ ሙያ ደረጃዎችን(Occupational Standards) የከለሰ ሲሆን በተከለሰው የሙያ ደረጃ መሰረት አሰልጣኝ መምህራንን በተለያዩ ሥርዓቶች በማብቃት ተከታታይነት ያለው የአቅም ግንባታ ስልጠናዎችና የትምህርት ደረጃቸውን በማሻሻል እንዲበቁ መደረጉን አስታውሰዋል፡፡ በአስተዳደሩ 232 የቴክኒክና ሙያ አሰልጣኝ መምህራን የሙያ ብቃት ማረጋገጫ ምዘና በ12 ዘርፎች በ23 ሙያዎች(Occupation) መውሰድ መጀመራቸውንና ምዘናውም በሚቀጥለው አንድ ወር ውስጥ የሚጠናቀቅ መሆኑን  በቢሮው የሙያ ብቃት ምዘናና ማረጋገጫ ማዕከል የሙያ ብቃት ምዘና ቡድን መሪ የሆኑት አቶ መኳንንት ዘውዴ ተናግረዋል፤ የሥራና ክህሎት ቢሮ ህዝብ ግንኙነት ሚያዝያ 7/2017 ዓ.ም ድሬዳዋ

በድሬዳዋ አስተዳደር ሥራና ክህሎት ቢሮ የተዘጋጀ የሞዴል ኢንተርፕራይዞች ኤግዚቢሽንና ባዛር ተጀመረ። ከዛሬ ጀምሮ እስከ ሚያዚያ 10/2017 ዓ.ም ድረስ በኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማህበር ድሬዳዋ ቅርንጫፍ ፊት ለፊት የሚገኘው ቦታ ላይ የሚካሄደውን ይህን ኤግዚቢሽን እና ባዛር የቢሮው አመራሮች በተገኙበት በይፋ ተከፍቷል። በዚህም ኤግዚቢሽንና ባዛር ላይ ሞዴል ኢንተርፕራይዞች ምርትና አገልግሎቶቻቸውን ይዘው የሚቀርቡ ሲሆን ወቅቱም በዓል ሰሞን እንደመሆኑ በቦታው በመገኘት የአስተዳደሩ ነዋሪ ሞዴል ኢንተርፕራይዞችን በማበረታታት ተጠቃሚ እንዲሆን የድሬዳዋ አስተዳደር ሥራና ክህሎት ቢሮ ኃላፊ አቶ ሮቤል ጌታቸው መልዕክት አስተላልፈዋል። የቢሮው ኃላፊ አክለው ኢንተርፕራይዞች የሚገጥማቸውን የገበያ ተደራሸነትን ለመቅረፍ በሥራና ክህሎት ሚኒስቴር በሚመራው የኢትዮጵያ ሥራ ገበያ መረጃ ስርአት(E-LMIS) ተግባራዊ የሆነው  መተግበሪያና ድህረገፅ ላይ በሰፊው እንዲመዘገቡ እየተደረገ መሆኑና ኢንተርፕራይዞች  ምርታቸውን ለሀገር ውስጥም ሆነ ለውጭ ሀገራት  ኦንላይን በማስተዋወቅ የሚሸጡበትና ክፍያ የሚቀበሉበት ዕድል መመቻቸቱን ተናግረዋል፡፡ በቢሮው የሥራ ዕድል ፈጠራ እና አንድ ማዕከል ማስተባበሪያ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ሰኢድ አሊ በበኩላቸው በቢሮው ለኢንተርፕራዞች ከሚሰጡ የድጋፍ ማዕቀፎች አንዱ የገበያ ትስስር ሲሆን ኤግዚቢሽንና ባዛር ወሳኝ ሚና አለው በመሆኑም ኢንተርፕራይዞች ያመረቱትን ምርት ይዘው የሚቀርቡበት ገበያተኛውም በሚፈልገው ልክ ተገበያይቶ የሚወጣበት መድረክ መፍጠሪያ ዘዴ አንዱ ይህ በመሆኑ እንዲሁም  ያለውን የኑሮ ውድነት ለማረጋጋትም ከፍተኛ ሚና ይኖረዋል ብለዋል። የሥራና ክህሎት ቢሮ ህዝብ ግንኙነት ሚያዚያ 6/2017 ዓ.ም ድሬዳዋ

photo content
+9

“በቴክኒክና ሙያ ዘርፍ የአሰልጣኝ መምህራንን ምዘና ማካሄዳችን ለቀጣይ የለውጥ ጉዞ ውጤታማነት ዝግጁ የሚያደርገን ይሆናል”  ወ/ሮ ፈጡም ሙስጠፋ የድሬዳዋ አስተዳደር ሥራና ክህሎት ቢሮ የቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና ኤጀንሲ ዳይሬክተር እና የቢሮው ም/ ኃላፊ ኃላፊዋ በዛሬው ዕለት በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ በአገር አቀፍ ደረጃ እየተካሄደ የሚገኘውን የአሰልጣኝ መምህራን ምዘና በድሬዳዋ አስተዳደር ደረጃ ለማስጀመር ቅድመ ዝግጅት መጠናቀቁን አስታውቀዋል፤  የምዘናው ዋና አላማም አሰልጣኝ መምህራኑን ከአዲሱ የዘርፉ ፖሊሲ ጋር የማስተዋወቅና የማብቃት እንዲሁም የዘርፉን የስልጠና ጥራት ከመጠበቅ አኳያ ምዘናው ሚናው ላቅ ያለ እንደሚሆን አስታውቀዋል፡፡ በአስተዳደር ደረጃ በዚህም ምዘና የማያልፍ የቴክኒክና ሙያ አሰልጣኝ የማይኖር መሆኑን እና የሚመዝኑ መዛኞችም ከዚህ ቀደም የነበሩት ሳይሆን በአዲስ መልክ ከኢንዱስትሪ እና ከድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ የፈሩ መሆናቸውና በቢሮው የሙያ ብቃት ምዘናና ማረጋገጫ ማዕከል በኩል ለአዳዲስ እጩ መዛኞች ስልጠና መሰጠቱ ተገልጻል፤ በዚህም በሁለቱ የመንግስት ኮሌጆችና በድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ የምዘና ማዕከላት ምዘናው የሚካሄድ ሲሆን በአጠቃላይ ሁሉም አሰልጣኝ መምህራን በምዘናው የሚያልፉ ሲሆን በመጀመሪያው ዙር በሁለቱ የመንግስት ኮሌጆች የሚያሰለጥኑ አሰልጣኝ መምህራን ይመዘናሉ በቀጣይ ደግሞ የግል የቴክኒክና ሙያ ስልጠና ኮሌጅ ላይ የሚያሰለጥኑ አሰልጣኝ መምህራን በተመሳሳይ የሚመዘኑ ይሆናል፡፡ በዋናነት ይህ ምዘና የሚካሄደው አሰልጣኝ መምህሩ ከዚህ ቀደም በምዘና ስርዓት ያላለፈ ሆኖ ሳይሆን የዘርፉ ፖሊሲ በመቀየሩ ከጊዜው ጋር የተናበበ አቅም ለመፍጠር ታስቦ የሚከናወን ሲሆን በሌቭል የነበረው የምዘና ስርአት አካሄድም በሆልስቲክ ተተክቶ የሚመዘኑ ሲሆን በመጀመሪያው ዙር ምዘና ብቁ ሆነው ያልተገኙ አሰልጣኝ መምህራን ክፍተታቸውን በመለየትና እስከ ፌደራል ቴክኒክና ሙያ ኢንስቲትዩት ድረስ በመላክ አቅማቸው የሚገነባ ይሆናል፤ ይህም በመጪው 2018 ዓ.ም ለሚደረገው የሰልጣኝ ተማሪዎች ቅበላ ቅድመ ዝግጅት አካል ሆኖ የሚሰራበት ነው፡፡ ወ/ሮ ፈጡም ሙስጠፋ በመግለጫው ማጠቃለያ እንደገለጹት አስተዳደሩ የኢንዱስትሪ ማዕከል እንደመሆኑ መጠን ከፍተኛ የሆና በቴክኒክና ሙያ የበቃ የሰው ሃይል ፍላጎት በመኖሩ ይሄንንም ለማሟላት አሰልጣኝ መምህሩን መመዘንና ማብቃት ትኩረት እንደተሰጠው ጠቅሰው በአጠቃላይ በድሬዳዋ አስተዳደር የሚገኘው የቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና ዘርፍ የኢንዱስትሪዎችን አቅም ከመገንባትና አስፈላጊ የሙያዊም ሆነ የቴክኖሎጂ ድጋፍ እያደረገ እንደሚገኝና ከዚህ በተጨማሪም በአጠቃላይ ትምህርት ላይ የሚገኙ ተማሪዎችንም ተደራሽ ያደረገ የተለያዩ ስራወች እየተሰሩ መሆኑን አንስተው ለዚህ ሁሉ ዋና እና መሰረቱ የአሰልጣኝ መምህራኑ መብቃት በመሆኑ ከነገ ሚያዚያ 7/2017 ዓ.ም ጀምሮ ምዘናው የሚካሄድ መሆኑን ገልጸዋል፡፡ የሥራና ክህሎት ቢሮ ህዝብ ግንኙነት ሚያዝያ 6/2017 ዓ.ም ድሬዳዋ

photo content

የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያው ለሥራ ዕድል ፈጠራ ከፍተኛ አስተዋጽኦ አበርክቷል - ወ/ሮ ሙፈሪሃት ካሚል በበጀት ዓመቱ ዘጠኝ ወራት በማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያው የተመዘገበው ስኬት ለሥራ ዕድል ፈጠራ ከፍተኛ አስተዋጽኦ አበርክቷል ሲሉ የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ሙፈሪሃት ካሚል ገለፁ፡ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በተገኙበት የ2017 በጀት ዓመት ያለፉት 9 ወራት አፈጻጸም ግምገማ ተካሂዷል፡፡ የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር የአፈፃፀም ሪፖርትን ያቀረቡት ወ/ሮ ሙፈሪሃት ካሚል÷ባለፉት 9 ወራት እንደ ሀገር በርካታ ስኬቶች መመዝገባቸውን ጠቅሰው፤ በሚኒስቴሩም ዘርፈ ብዙ ሥራዎች ተከናውነዋል ብለዋል፡ በእያንዳንዱ ዘርፍ እድገት ሲመዘገብ በቀጥታ ከሥራ እድል ፈጠራ ጋር እንደሚገናኝ ገልፀው÷እንደ ሀገር የተከናወነው የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያ ለዘርፉ ከፍተኛ አስተዋፅኦ ማድረጉን አንስተዋል፡፡ ባለፉት 9 ወራት ለ3 ነጥብ 4 ሚሊየን በላይ ዜጎች የሥራ እድል መፈጠሩን የጠቀሱት ሚኒስትሯ÷የግብርና፣ የኢንዱስትሪ እና የአገልግሎት ዘርፎች ከፍተኛውን ድርሻ እንደሚይዙ አስረድተዋል፡፡ የዲጂታል ሥራን በማጠናከር 344 ሺህ ለሚሆኑ ዜጎች የውጭ ሀገር ሥራ እድል መፍጠሩን ጠቁመው÷ በኮደርስ ኢንሼቲቭ 45 ሺህ ዜጎችን የዲጅታል ሥራዎች ተጠቃሚ ማድረግ መቻሉን አመላክተዋል፡፡ በተጨማሪም ከ1 ነጥብ 2 ሚሊየን በላይ ለሚሆኑ ዜጎችን የሥራ እድል ፈጠራ ስልጠናዎችን በመስጠት በአካባቢያቸው ያለውን ፀጋ እንዲመለከቱ ማድረግ መቻሉን አስገንዝበዋል፡፡ በልምድ ሲሰሩ ለነበሩ ሙያ ፈጣሪዎች ሚኒስቴሩ እውቅና መስጠት መጀመሩን እና በበጀት ዓመቱ መጨረሻ 80 ሺህ የልምድ ባለሙያዎችን እውቅና ለመስጠት መታቀዱን ገልጸዋል፡፡ ኢትዮጵያ ውስጥ ያለው የሥራ ፍላጎት ከፍተኛ መሆኑን የገለፁት ሚኒስትሯ÷የሥራ እድልን በመፈጠር ረገድ ከመንግስት በተጨማሪ ባለሃብቶችና ባለድሻ አካላት የበኩላቸውን እንዲወጡ አሳስበዋል፡፡ ሚያዝያ 6፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ)

photo content

ለጥንቃቄ! ካናዳን ጨምሮ በተለያዩ የአውሮፓ ሀገራት ለሥራ ዜጎችን እንልካለን፡፡ ለዚህም ከሚመለከታቸው አካላት ፍቃድ አግኝተናል በሚል በተለያዩ የማህበራዊ ትስስር ገጾች ህገ-ወጥ ማስታወቂያዎችን በማ
ለጥንቃቄ! ካናዳን ጨምሮ በተለያዩ የአውሮፓ ሀገራት ለሥራ ዜጎችን እንልካለን፡፡ ለዚህም ከሚመለከታቸው አካላት ፍቃድ አግኝተናል በሚል በተለያዩ የማህበራዊ ትስስር ገጾች ህገ-ወጥ ማስታወቂያዎችን በማሰራጫት ህብረተሰቡን ላላስፈላጊ ወጪና እንግልት እየዳረጉ በመሆኑ መሰል የማጭበርበር ተግባር እየፈፀሙ የሚገኙ አካላትን በህግ ተጠያቂ ለማድረግ ሚኒስቴር መስሪያ ቤታችን በትኩረት እየሰራ ይገኛል፡፡ በውጭ ሀገር ስራ ስምሪቱ የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር ወደ አውሮፓና አሜሪካ ዜጎችን ለሥራ ለማሰማራት ለየትኛውም አካል የሰጠው ውክልና የሌለ መሆኑን እየገለጽን ዜጎቻችን በስምሪቱ ተጠቃሚ ለመሆን ህጋዊ አማራጮችን ብቻ በመጠቀም ካላስፈላጊ ወጪ፣ እንግልትና ሌሎች አስከፊ አደጋዎች ራሳቸውን እንዲጠብቁ በጥብቅ እናሳስባለን፡፡ የሁለትየሽ ስምምነት በተፈረመባቸው መዳረሻ ሀገራት የሥራ ዕድል ማግኘት ከፈለጉ የሚከተለውን ማስፈንጠሪያ (lmis.gov.et) በመጠቀም የኢትዮጵያ የሥራ ገበያ መረጃ ስርዓት ላይ በመመዝገብ ደህንነቱ የተረጋገጠ የውጭ ሀገር ሥራ ስምሪት ተጠቃሚ ይሁኑ፡፡ ለወቅታዊ ትኩስ የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር መረጃ ፡ ሚያዝያ 5፤ 2017 በድረገጽ፡- http://mols.gov.et/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/MolsFDRE ቴሌግራም፦ https://t.me/fdre_mols ዋትስአፕ፡- https://whatsapp.com/channel/0029VakCgcYIyPtTbPZtDW1y ቲክቶክ:- tiktok.com/@mols_official ሊንክዲን፡- https://www.linkedin.com/.../ministry-of-labor-skill-fdre/m

photo content
+2

የድሬዳዋ አስተዳደር ሥራና ክህሎት ቢሮ የሙያ ብቃት ምዘናና ማረጋገጫ ማዕከል ለአዳዲስ እጩ መዛኞች ስልጠና አዘጋጀ፤ ይህም ስልጠና በቀጣይ ሳምንት ለሚጀመረው አጠቃላይ የቴክኒክና ሙያ ስልጠና አሰልጣኝ መምህራንን በምዘና ለማሳለፍ ከፌደራል የተሰጠውን አቅጣጫ ወደ ተግባር ለማስገባት በድሬዳዋ ዩኒቨርስቲ የሚገኙ ከሁለተኛ ዲግሪ እና ከዚያ በላይ ያላቸውን መምህራን የእጩ መዛኝነት ስልጠና እንዲወስዱ ተደርጓል። ከዚሁ ጎን ለጎን ማዕከሉ አገልግሎት አሰጣጡን ቀልጣፋ ለማድረግ እንዲያስችለው ቀጣይነት ያለውና የማይቋረጥ የሪፎርም ስራዎችን በመስራት ላይ የሚገኝ ሲሆን በዋናነት ከዩኒቨርሲቲው የተመረጡ መዛኞችን በማፍራት ምዘና እና መዛኝነትን በሚገባ ተረድተው ተመዛኙን በፍጹም ስነምግባር እንዲመዝኑ የሚያስችላቸው እንደሚሆን የማዕከሉ ዋና ዳይሬክተር አቶ አሚን አብዱላሂ ገልጸዋል፡፡ ዳይሬክተሩ አክለውም ምዘና ያለ ብቁ መዛኝ የማይታሰብ መሆኑንና ከዚህም በላይ በብዛትም ሆነ በጥራት እንዲፈሩ የማድረጉ ስራ በተመሳሳይ ከተቋማት ጋር በትብብር እየተሰራ የሚገኝ መሆኑንና ከምዘና ጋር ተያይዞ ከተገልጋይ የሚነሱ ጥያቄዎችን ከሚመልሱ ተግባራት አንዱና ዋነኛው አዳዲስ መዛኞችን ማፍራትና ማብቃት እንደመሆኑ ቀጣይነት እንደሚኖረው ተናግረዋል፡፡ የሥራና ክህሎት ቢሮ ህዝብ ግንኙነት ሚያዝያ 4/2017 ዓ.ም ድሬዳዋ

የEASE ፕሮጀክት የሩብ አመት አፈፃፀም ሪፖርትና የቀጣይ ሩብ አመት እቅድ ለባለድርሻ አካላት ቀርቦ ውይይት ተካሄደ:: የኢትዮ-ጣሊያን ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ በEASE ፕሮጀክት የተከናወኑ ያለፉት 3ወራት የትግበራ አፈፃፀም ሪፖርትና የቀጣዩን 3ወራት እቅድ ለኮሌጁ ኢንዱስትሪ አድቫይዘሪንግ ቦርድ በዛሬው እለት አቅርቦ በመድረኩ ውይይት ተደርጎበታል:: መድረኩን በንግግር ያስጀመሩት የኮሌጁ የውጤት ተኮር ትምህርትና ስልጠና ም/ዲን አቶ ኤሊያስ አህመድ በንግግራቸው እንደገልፁት ፕሮጀክቱ በየሩብ አመቱ ሪፖርቱን ሲያቀርብ በዋነኛነት የደረሰበትን አፈፃፀም ደረጃ ለባለድርሻ አካላት ግልፅ ከማድረግም በተጨማሪ ለቀጣይ ትግበራዎች ግብዓት የሚሆኑ ምክረ-ሃሳቦችን ከመድረኩ ለማግኘት በማሰብ ጭምር መሆኑንም ገልፀዋል:: የፕሮጀክቱን ያለፈው ሩብ አመት አፈፃፀም ሪፖርት በEASE ፕሮጀክት ዋና ኮርድኔተር ኢንጂነር ፋሲል ማዘንጊያ አማካኝነት ለተሳታፊዎች የቀረበ ሲሆን በቀረበው አፈፃፀም ሪፖርትም በሩብ አመቱ ሊሰሩ የታቀዱ በርካታ ተግባራት መከናወናቸው ተገልፇል:: በዚህም.... የፕሮጀክቱን አዲስ ቢሮ ከማደራጀት አንስቶ -የGender & Inclucsive guidline ማዘጋጀት -የአሰልጣኞችን የውጭ ስልጠና የማመቻቸት -የDigitalization ስራዎች የማስፋፋት -ከተለያዩ የፌደራል ተቋማት እና ከ14 አጎራባች ቴክኒክና ሙያዎች ጋር አብሮ ለመስራት የመግባቢያ ስምምነት ውል የመፈራረም -የተልያዩ የአቅም ግንባታ ስልጠናዎች -የHigh school ተማሪዎች ላይ ግንዛቤ የመፍጠር ስራዎች በሩብ አመቱ ከተከናወኑት ተግባራቶች ውስጥ እንደሚጠቀሱም ተገልፇል:: መድረኩ ቀጥሎም በEASE ፕሮጀክት በቀጣይ 3ወራት በኮሌጁ የሚከናወኑ ተግባራት እቅድ ለተሳታፊዎች የቀረበ ሲሆን የመድረኩ ተሳታፊዎች በቀረበው የፕሮጀክቱ አፈፃፀምና የቀጣይ ትግበራ እቅድን መነሻ በማድረግ ለፕሮጀክቱ ውጤታማነት የሚረዱ ምክረ ሃሳቦችን በስፋት አንስተው ውይይት ተደርጎበታል:: በመጨረሻም በEASE ፕሮጀክት የትኩረት ዘርፎች ተብለው በተለዩት ዲፓርትመንትቶች ላይ ጊዜው የደረሰበትን የስልጠና ማቴሪያሎች ለማሟላት በዲፓርትመንቶቹ የሚገኙ አሰልጣኝ መምህራንን በማቀናጀት እየተዘጋጀ ሚገኘው የማቴሪያል ልይታ(Specification) ለኢንዱስትሪ አድቫይዘሪንግ ቦርዱ የቀረበ ሲሆን የቦርዱ አባላትም ካላቸው ልምድ አኳያ በማቴሪያል ዝርዝሩ ላይ ሊካተቱ ይገባል ያሏቸውን እንዲሁም ማስተካከያ ሚያስፈልጋቸውን ጉዳዮች ምክረ-ሀሳብ እንዲሰጡበት የተደረገ ሲሆን የማቴሪያል ዝርዝሩን ሚያዘጋጁት መምህራንም ከመመድረኩ የተሰጠውን ግብረ-መልስ በማካተት በቀጣይ በሚኖረው መድረክ የሚያቀርቡም ይሆናል:: የኢትዮ-ጣሊያን ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ ኮሚኒኬሽን ሚያዚያ 4/2017 ዓ.ም

ድሬ ፖሊስ lll ሚያዝያ 4 ቀን 2017 ዓም የድሬዳዋ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ እና የድሬዳዋ አስተዳደር ስራ እና ክህሎት ቢሮ በጋራ ለመስራት የሚያስችል የመግባቢያ ሰነድ ተፈራረሙ ።         በመርህ ግብሩ ላይ በድሬዳዋ ፖሊ ቴክኒክና ኮሌጅ አማካኝነት በሁለት ዙር መሰረታዊ የኮምፒውተር ስልጠና የወሰዱ የድሬዳዋ ፖሊስ አባላት እና አመራሮች የተመረቁ ሲሆን የአስተዳደሩ ክቡር ከንቲባ አቶ ከድር ጁሃር፣ የድሬዳዋ አስተዳደር ስራ እና ክህሎት ቢሮ ኃላፊው አቶ ሮቤል ጌታቸው እና የአስተዳደሩ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ ዋና አዛዥ ክቡር ኮሚሽነር አለሙ መግራ እንዲሁም የድሬዳዋ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ዲን አቶ ሰላዲን አብዱል ሀሚድና ሌሎች አስተዳደሩ እና የተቋሙ ከፍተኛ አመራሮች ተገኝተዋል ። በመድረኩ ላይ  በክብር እንግድነት በመገኘት መልዕክት ያስተላለፉት የድሬዳዋ አስተዳደር  ክቡር ከንቲባ አቶ ከድር ጁሃር እንደተናገሩት ድሬዳዋን ስማርት ሲት የማደረግ ጥረት በአስተዳደሩ ከፍተኛ ትኩረት ተሰጥቶ እየተሰራ መሆኑ ገልፀው ይህንንም ለማሳካት በቴክኖሎጂ የታገዘ የፖሊስ ሃይል ወሳኝ በመሆኑ ይህንን ባገናዘበ መልኩ ሁሉም የፖሊስ  አባላት መሰረታዊ የኮምፒውተር እውቀት እንዲኖር ለማስቻል ሁለቱ ተቋማት የጀመሩት ቅንጅታዊ ስራ የሚበረታታ እና የአስተዳደሩም አቅጣጫ ነው ብለዋል።       የድሬዳዋ አስተዳደር ስራ እና ክህሎት ቢሮ ኃላፊው አቶ ሮቤል ጌታቸው በበኩላቸው ባስተላለፉት መልዕክት ቢሮአቸው ከዚህ ቀደምም ከድሬዳዋ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ ጋር በቅርበት ሲሰራ መቆየቱን ገልጸው በቀጣይም በተፈራረሙት ስነድ መሠረት የተለያዩ ስልጠናዎችን በመስጠት የአባላቱን የቴክኖሎጂ አቅም ከማሳደግ ባለፈ ተቋሙን በተለያዩ የቴክኖሎጂ ግብአቶች ለመደገፍ በትኩረት ሰጥቶ ከሚሰራቸው ስራዎች መካከል አንዱ መሆኑን ተናግረዋል ።       ድሬዳዋ ፖሊስ ያስቀመጠው ራዕይ ጋር ለማደረስ በፍጥነት እየተጓዘ ነው ያሉት ክቡር ኮሚሽነር አለሙ መግራ ይህንን ዕውን ለማድረግ ከተለያዩ የትምህርት ተቋማት ጋር ለመስራት የሚያስችል ስነድ በመፈራረም ስራዎችን እየሰራ መሆኑን የገለፁት ሲሆን ከድሬዳዋ አስተዳደር ስራ እና ክህሎት ቢሮ ጋርም የተጀመረው የሁለቱ ተቋማት ጠንካራ ግንኙነት ይበልጥ ለማስቀጠል ስነድ መፈራረማቸውን ተናግረዋል ።      በተለይ የፖሊስ አባላቱን የቴክኖሎጂ አቅም ይበልጥ ለማሳደግ ከድሬዳዋ አስተዳደር ስራ እና ክህሎት ቢሮ ጋር የሚሰሩ ሰፊ ስራዎች መኖራቸውንም ክቡር ኮሚሽነር አለሙ መግራ ጨምሮ ተናግረዋል ። በመርሃ ግብሩ ላይ በሁለት ዙር የተሰጠው ስልጠና ላይ ከፍተኛ ውጤት ያስመዘገቡ የፖሊስ አባለት እና አሰልጣኞች እንድሁም ለተቋሙ እውቅና እና የምስክር ወረቀት ተሰጥቷቸዋል። ድሬዳዋ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ