1 326
Подписчики
+224 часа
+87 дней
+9730 дней
Архив постов
"የአንድ ማዕከላትን አቅም ማጎልበትና ተልዕኳቸውን በሚጠበቀው ልክ እንዲፈጽሙ መከታተልና መደገፍ በቢሮው ትኩረት ተሰጥቶት እየተሰራ ነው"
አቶ ሮቤል ጌታቸው
የድሬዳዋ አስተዳደር ሥራና ክህሎት ቢሮ ኃላፊ
በዛሬው ዕለት በአስተዳደሩ ከተማና ገጠር የሚገኙ የአንድ ማዕከላትን ከሚያስተባብሩ አመራሮችና ባለሙያዎች ጋር በአጠቃላይ የሥራ ዕድል ፈጠራ አፈጻጸምና ቀጣይ ትግበራ ላይ ሰፊ ውይይት ተካሄደ፡፡
የድሬዳዋ አስተዳደር ሥራና ክህሎት ቢሮ የተሰጠውን ሀገራዊና አስተዳደራዊ ተልዕኮዎችን ወደ ተግባር ለውጦ ውጤት ለማምጣት የአንድ ማዕከላት ሚና ላቅ ያለ ሲሆን በተለይም ቢሮው በስራ ዕድል ፈጠራ የዜጎችን ስራ አጥነት ለመቀነስ በሚደረገው ሁሉን አቀፍ እርብርቦሽ የአንድ ማዕከላቱ በቀጥታ ከህብረተሰቡ ጋር በመገናኘት ምቹ ሁኔታዎች እንዲፈጠሩ ያስቻሉ መሆኑን አቶ ሮቤል ጌታቸው ተናግረዋል።
በተጨማሪም አንድ ማዕከላቱ እንደ አስተዳደር የሚሰጡ ተልዕኮዎችን በጋራ እና በተናጠል ተከፋፍለው የሚፈጽሙበት ሁኔታና አግባብነትን በተጠናከረ መልኩ ከማስቀጠልና የሚታዩ ክፍተቶችን በማረም የሚጠበቅባቸውን ኃላፊነት በብቃት እንዲወጡ ያሳሰቡ ሲሆን በቀጣይ በተለይ የገጠሩን ሥራ ዕድል ፈጠራ ከማጠናከር አኳያ አደረጃጀቱን የማጠናከርና የአቅም ግንባታ ስራዎች ትኩረት እንደተሰጣቸውና በተያያዘ በቀጣይ ቢሮው በድጋፍና ክትትል የሁሉንም አንድ ማዕከላት ውጤታማነት ማረጋገጥ የሚያስችል አቅጣጫ ማስቀመጡን ገልጸዋል፡፡
የሥራና ክህሎት ቢሮ ህዝብ ግንኙነት
መጋቢት 17/2017 ዓ.ም
ድሬዳዋ
"የአንድ ማዕከላትን አቅም ማጎልበትና ተልኳቸውን በሚጠበቀው ልክ እንዲጽሙ መከታተልና መደገፍ በቢሮው ትኩረት ተሰጥቶት እየተሰራ ነው"
አቶ ሮቤል ጌታቸው
የድሬዳዋ አስተዳደር ሥራና ክህሎት ቢሮ ኃላፊ
በዛሬው ዕለት በአስተዳደሩ ከተማና ገጠር የሚገኙ የአንድ ማዕከላትን ከሚያስተባብሩ አመራሮችና ባለሙያዎች ጋር በአጠቃላይ የሥራ ዕድል ፈጠራ አፈጻጸምና ቀጣይ ትግበራ ላይ ሰፊ ውይይት ተካሄደ፡፡
የድሬዳዋ አስተዳደር ሥራና ክህሎት ቢሮ የተሰጠውን ሀገራዊና አስተዳደራዊ ተልዕኮዎችን ወደ ተግባር ለውጦ ውጤት ለማምጣት የአንድ ማዕከላት ሚና ላቅ ያለ ሲሆን በተለይም ቢሮው በስራ ዕድል ፈጠራ የዜጎችን ስራ አጥነት ለመቀነስ በሚደረገው ሁሉን አቀፍ እርብርቦሽ የአንድ ማዕከላቱ በቀጥታ ከህብረተሰቡ ጋር በመገናኘት ምቹ ሁኔታዎች እንዲፈጠሩ ያስቻሉ መሆኑን አቶ ሮቤል ጌታቸው ተናግረዋል።
በተጨማሪም አንድ ማዕከላቱ እንደ አስተዳደር የሚሰጡ ተልዕኮዎችን በጋራ እና በተናጠል ተከፋፍለው የሚፈጽሙበት ሁኔታና አግባብነትን በተጠናከረ መልኩ ከማስቀጠልና የሚታዩ ክፍተቶችን በማረም የሚጠበቅባቸውን ኃላፊነት በብቃት እንዲወጡ ያሳሰቡ ሲሆን በቀጣይ በተለይ የገጠሩን ሥራ ዕድል ፈጠራ ከማጠናከር አኳያ አደረጃጀቱን የማጠናከርና የአቅም ግንባታ ስራዎች ትኩረት እንደተሰጣቸውና በተያያዘ በቀጣይ ቢሮው በድጋፍና ክትትል የሁሉንም አንድ ማዕከላት ውጤታማነት የሚያረጋገጥ አቅጣጫ ማስቀመጡን ገልጸዋል፡፡
የሥራና ክህሎት ቢሮ ህዝብ ግንኙነት
መጋቢት 17/2017 ዓ.ም
ድሬዳዋ
Repost from Ethio-Italy Polytechnic College (Dire Dawa)
በኢትዮ-ጣሊያን ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ EASE ፕሮጀክት ለኮሌጁ የድጋፍ ሰጪ ሰራተኞች ሲሰጥ የቆየው የ3ኛዙር የአቅም ግንባታ ስልጠና ተጠናቀቀ::
የኢትዮ-ጣሊያን ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ
ከድሬዳዋ ስራ አመራር ኢንስቲትዩት ጋር በጋራ ለመስራት በገባው ውል መሰረት ለ3ኛ ዙር ለኮሌጁ የፅዳትና ጥበቃ ሰራተኞች ለተከታታይ 3 ቀናት ሲሰጥ የቆየው የአቅም ግንባታ ስልጠና በዛሬው እለት ተጠናቋል::
ለ3 ተከታታይ ቀናት የተሰጠውን ስልጠና በአግባቡ ተከታትለው ላጠናቀቁ ሰልጣኞች ምስጋና ያቀረቡት የድሬዳዋ ስራ አመራር ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር አቶ አወቀ ለገሰ አክለውም ኮሌጁ ሰራተኞች በስራ ገበታቸው ላይ የሚሰጡት አገልግሎት እንዲሻሻል በማቀድ ይህንና መሰል ስልጠናዎችን እንዲወስዱ ማመቻቸቱ የሚበረታታ ነውም ብለዋል::
በዚህ 3ኛ ዙር ስልጠና ላይ የተካፈሉ ሰልጣኞች የወሰዱትን ስልጠና በተግባር ላይ ማዋል የሚጠበቅባቸው መሆኑን የገለፁት የኮሌጁ ዲን አቶ ታደለ አሰፋ አክለውም በቀጣይ በሚፈጠርላቸው መሰል የአቅም ግንባታ ስልጠናዎች ላይ በንቃት በመሳተፍ አቅማቸውን እንዲገነቡና በተመደቡበት የስራ ዘርፍ የተሻለ አገልግሎት በመስጠት ለተቋሙ ራዕይና ስኬት የድርሻቸውን እንዲወጡም ጠይቀዋል::
ሰልጣኞች ከዚህ ስልጠና በኃላ በስራ ገበታችሁ ላይ ያመጣውን ለውጥ በተግባር እንድታሳዩ ያስፈልጋል ያሉት የኮሌጁ የኢንዱስትሪ ኤክስቴንሽንና ቴክኖሎጂ ሽግግር ስራ ሂደት ም/ዲን አቶ ተሾመ ሸዋዬ ሲሆኑ አክለውም በመሰል ስልጠናዎች የሚመዘገቡ ውጤቶችን በድጋፍና ክትትል እናረጋግጣለንም ብለዋል::
የ3ኛው ዙር ስልጠና ቀደም ብለው ከተሰጡት የ1ኛና 2ኛ ዙር ስልጠናዎች በተለያየ ምክንያት ዘግይቶ እንደተሰጠ ያስታወሱት የEASE ፕሮጀክት ዋና አስተባባሪ የሆኑት ኢንጂነር ፋሲል ማዘንጊያ ሲሆኑ አክለውም ይህ ስልጠና ማስጀመርያ መሆኑንና ኮሌጁ ከኢንስቲትዩቱ ጋር በቅንጅት ለመስራት ባደረገው ስምምነት መሰረት አስፈላጊ የሆኑ የአቅም ግንባታ ስልጠናዎች በቀጣይ እንደሚዘጋጁም ገልፀዋል::
የማጠቃለያ መርሃ-ግብሩ ላይ ስልጠናውን በአግባቡ ተከታትለው ላጠናቀቁ ሰልጣኞችም ከእለቱ ክብር እንግዶች የምስክር ወረቀት ተበርክቶላቸዋል::
የኢትዮ-ጣሊያን ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ ኮምኒኬሽን
መጋቢት17/2017 ዓ.ም
"ብሩህ አዕምሮዎች በክህሎት የበቁ ዜጎች" በሚል መሪ ሃሳብ የድሬዳዋ አስተዳደር ሥራና ክህሎት ቢሮ የቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና ኤጀንሲ የኢንደስትሪ ኤክስቴንሽንና የቴክኖሎጂ ሽግግር ዳይሬክቶሬት አዘጋጅነት የሚካሄደው የ2017 ዓ.ም የክህሎት ውድድር በክላስተር ደረጃ መካሄድ ጀመረ።
በዛሬው ዕለት በድሬዳዋ ፖሊቴክኒክ እና በኢትዮ ጣሊያን ፖሊቴክኒክ ኮሌጆች በጋርመንት፣ ዉድ ወርክ፣ ኤሌክትሪክ፣ ሆቴል እና ቱሪዝም፣ ኮንስትራክሽን፣ አውቶሞቲቭ፣ ማኑፋክቸሪንግ እና በአይሲቲ ላይ ሰልጣኝ ተማሪዎች በአስተዳደር ደረጃ ለሚካሄደው ውድድር ኮሌጃቸውን ወክለው ለመሳተፍ ከየዘርፉ በተመረጡ ዳኞች ፊት ክህሎታቸውን በመጠቀም ስራዎቻቸውን በማቅረብ ላይ ይገኛሉ።
በዚህም በክላስተርና በአስተዳደር ያለውን ውድድር በበላይነት የሚያጠናቅቁ ተወዳዳሪዎች ኮሌጆቹን እንዲሁም አስተዳደሩን በመወከል በአገር አቀፍ ደረጃ በሚካሄደው የክህሎት ውድድር የሚሳተፉ እንደሚሆን በዳይሬክቶሬቱ የቴክኒካል ክህሎት አቅም ግንባታ ቡድን መሪ ወ/ሮ አለምጸሃይ ጌታቸው ገልጸዋል።
የሥራና ክህሎት ቢሮ ህዝብ ግንኙነት
መጋቢት 16/2017 ዓ.ም
ድሬዳዋ
በአካታች የሥራ ዕድል ፈጠራና በከተማ ሴፍቲኔት ፕሮግራም ዙሪያ ያተኮረ አውደ ጥናት ላይ የድሬዳዋ አስተዳደር ተሞክሮ ቀረበ፤
የኢትዮጵያ ከተሞች የትብብር መድረክ ከኔዘርላንድ የከተሞች ትብብር መድረክ (VNGI) “ዊ አር ኤብል” ከተሰኘው ፕሮግራም ጋር በመተባበር የአካል ጉዳተኞች በከተማ ሴፍቲኔት ፕሮጀክቶች አካታችነትና ተጠቃሚነት፣ በከተሞች የአፈጻጸም ተሞክሮ ፣ ያጋጠሙ ችግሮችና ዘላቂ መፍትሄዎች ዙሪያ ላይ ያተኮረ የአንድ ቀን የልምድ ልውውጥ አውደጥናት በአዳማ ከተማ አካሂዷል፡፡
በዚህም መድረክ ላይ የድሬዳዋ አስተዳደርን ተሞክሮ የአስተዳደሩ ሥራና ክህሎት ቢሮ ኃላፊ አቶ ሮቤል ጌታቸው ያቀረቡ ሲሆን በአጠቃላይ አካታች የሆነ የሥራ ዕድል ፈጠራ ተደራሽነትና ጥራትን ከማረጋገጥ አኳያ እንደማሳያም ከቢሮው ጀምሮ በተመሳሳይ ተቋማት በቅጥር እንዲሁም ተደራጅተው ሥራ እንዲፈጥሩ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር ተቀራርቦ በመስራት የአካል ጉዳተኞች አካታችነትና ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ አስቻይ የሆኑ የተሰሩ ሁሉ አቀፍ ስራዎች መኖራቸውን አብራርተዋል፡፡
በተያያዘ “ዊ አር ኤብል” ፕሮግራም ከሌሎች መሰል ድርጅቶች ጋር በመተባበር የኢትዮጵያ ከተሞችን የምግብ ዋስትናቸውን እንዲያረጋግጡና ከተሞች የልማት ስራዎቻቸውን በሚያከናውኑበት ወቅት ለአካል ጉዳተኞች ልዩ ትኩረት እንዲሰጡ እንዲሁም ለነዋሪዎቻቸው ደግሞ የስራ ዕድል እንዲፈጥሩ በርካታ ስራዎችን እያከናወነ እንደሚገኝ በዚህ አውደጥናት ተጠቅሷል፡፡
(መጋቢት16፣ 2017 ዓ.ም፣ አዳማ)
Repost from Ethio-Italy Polytechnic College (Dire Dawa)
#ዜና | ከኮሌጆች ጋር በጋራ መስራት እና ተመሳሳይ አቅም መገንባት የኢንዱስትሪውን የሰው ኃይል ፍላጎት ከማሟላት ባሻገር የስራ እድል በመፍጠር በኩል ትልቅ አስተዋጽኦ እንደሚ ያደረግ ተገለፀ ::
የኢትዮ -ጣሊያን ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ ከምዕራብ እና ምስራቅ አጎራባች ክልሎች ከተውጣጡ የኮሌጅ አመራሮች ጋር የልምድ ልውውጥ እና በጋራ ለመስራት
የሚስችላቸውን የስምምነት ሰነድ ተፈራርሟል ።
በወቅቱ የስራና ክህሎት ቢሮ ምክትል ኃላፊ እና የቴክኒክና ሞያ ኤጀንሲ ዋና ዳሬክተር ወ/ሮ ፈጡም ሙስጠፋ ኮሌጁ ከኢትዮጵያ የተሰማሚነት ድርጅት
የጥራት ደረጃ እውቅና ( ISO) ያገኘና ትልቅ አቅም የሚፈጥር ኮሌጅ መሆኑን ጠቅሰው ይሄ አቅም ድሬዳዋ ላይ ብቻ ተወስኖ እንዳይቀር ከሌሎች አጎራባች ክልሎች
የቴክኒክ እና ሞያ ኮሌጅ አመራሮች ጋር በጋራ በመስራት በቴክኒክም በክህሎትም ተመሳሳይ አቅም
በመገንባት የኢንዲስትሪውን የሰው ኃይል ፍላጎት ከማሟላት ባሻገር የስራ እድል በመፍጠር በኩል ትልቅ አስተዋጽኦ እንደሚያደረግ ነው የገለፁት።
ወ/ሮ ፈጡም አያይዘውም በየአካባቢያችን ያለውን ሀብት እንዴት መጠቀም እንዳለብን ጭምር የጋራ እውቀት አቅም እንዲኖረን የሚያደርግ የልምድ ልውውጥ
ነዉ ብለዋል። ይህ የተሞክሮ ልውውጥ በዛሬ ብቻም አያበቃም ይቀጥላልም ነው ያሉት ::
የኢትዮ ጣሊያን ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ ዲን አቶ ታደለ አሰፋ በአለም ባንክ በተገኘ የገንዘብ ድጋፍ ኮሌጁ
( EASE)ኘሮጀክትን በመተግበር ላይ እንደሚገኝ ገልጸው ፕሮጀክቱ በተለዩ ስምንት (8) የትኩረት አቅጣጫዎች ላይ ይሰራል ብለዋል። ይህም የዛሬው የመጀመሪያው ዙር የድሬዳዋ አጎራባች ክልሎች የቴክኒክ እና ሞያ ኮሌጅ አመራሮች ጋር ያደረግነው የልምድ ለውውጥ እና በጋራ ለመስራት የተስማማንበት መድረክ አንዱ የፕሮጀክቱ ትግበራ አካል ነው ብለዋል ::
አያይዘውም ፕሮጀክቱ በቴክኒክም በክህሎትም ጥራት ያለው መምህር በመፍጠር ገበያው የሚፈልገውን
የሰው ኃይል በማቅረብ በኢንዱስትሪዎች ላይ የሚታየውን የሞያተኛ የብቃት ችግር ለመቅረፍ ብሎም
የስራ አጥ ቁጥርን ለመቀነስ የሚረዳ ፕሮጀክት ነው ብለዋል፡ :
ከአጎራባች ክልሎች የመጡት የቴክኒክ እና ሞያ ኮሌጅ ዲኖች በበኩላቸው የወሰድነው የልምድ ልውውጥ በየኮሌጃችን ለመተግበር የሚያስችል ተሞክሮ ቀስመናል ያሉ ሲሆን በተከታታይነትም ለመስራት የሚያስችለንን ስምምነት ላይ ደርሰናል ነው ያሉት ::
ኮሌጁ በቀጣይ በጋራ ለመስራት በሚያስችላቸው ጉዳዮችላይ የስምምነት ሰነድ ተፈራርሟል :: በመጨረሻም ከአጎራባች ክልሎች የመጡት እንግዶች
ኮሌጁን ተዘዋውረው ጎብኝተዋል።
#Dire tv አማርኛ መጋቢት 13/2047
