ru
Feedback

Не попадитесь на канал ботавода! Telemetrio находит и помечает такие каналы 👉 Хотите видеть метку — оформите подписку

Bureau of Labor and Skills-Dire Dawa

Bureau of Labor and Skills-Dire Dawa

Открыть в Telegram
1 318
Подписчики
+324 часа
+207 дней
+15030 дней
Архив постов
ለእስልምና እምነት ተከታዮች በሙሉ፥ እንኳን ለ1501ኛው የነቢዩ መሀመድ (ሰ.ዐ.ወ) የልደት በዓል 'መውሊድ' በሰላም አደረሳችሁ። #መልካም በዓል!
ለእስልምና እምነት ተከታዮች በሙሉ፥ እንኳን ለ1501ኛው የነቢዩ መሀመድ (ሰ.ዐ.ወ) የልደት በዓል 'መውሊድ' በሰላም አደረሳችሁ። #መልካም በዓል!

የድሬዳዋ አስተዳደር የሙያ ብቃት ምዘናና ማረጋገጫ ማዕከል በICT መሠረተ ልማት አቅሙን እያሳደገ ነው 540,873 ሺህ የአሜሪካን ዶላር የሚገመት የቁሳቁስ ድጋፍ በሁለት ዙር ተገኘ ድሬዳዋ፣ ነሐሴ 16/2018 ዓ.ም. — የቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ሥልጠና ጥራትን በማረጋገጥ የሙያ ብቃት ምዘናና ማረጋገጫ ሥርዓቱን ለማዘመን የድሬዳዋ አስተዳደር የሙያ ብቃት ምዘናና ማረጋገጫ ማዕከል በICT መሠረተ ልማት አቅሙን ለማጠናከር የሚያስችል የቁሳቁስ ድጋፍ ከሥራና ክህሎት ሚኒስቴር ማግኘቱ ተገለጸ። የድጋፉ ጠቅላላ ዋጋ 540.873 ሺህ የአሜሪካን ዶላር ሲሆን፣ በሁለት ዙር የተገኘው ይህ የቁሳቁስ ድጋፍ የማዕከሉን የICT መሠረተ ልማት በማጠናከር የሙያ ብቃት ምዘናና ማረጋገጫ አገልግሎቶችን በዘመናዊ፣ ቀልጣፋና የተረጋገጠ አሠራር ለማከናወን የሚያግዝ መሆኑ ተጠቁሟል። የድሬዳዋ አስተዳደር ሥራና ክህሎት ቢሮ የሙያ ብቃት ምዘናና ማረጋገጫ ማዕከል ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ አሚን አብዱላሂ እንዳስታወቁት፣ የተገኘው ድጋፍ ማዕከሉ የሚሰጠውን የሙያ ብቃት ምዘናና ማረጋገጫ አገልግሎት በተሻለ ደረጃ እንዲያከናውን ከፍተኛ አቅም የሚፈጥር ነው። በተለይም የICT መሠረተ ልማት መጠናከር የምዘና ሂደቶችን የበለጠ ተደራሽ፣ ፍትሐዊ፣ ቀልጣፋና ተአማኒ እንዲሆኑ ከማድረጉም በላይ፣ የምዘና ውጤቶችን በተገቢው መንገድ ለመመዝገብ፣ ለማስተዳደርና ለማረጋገጥ የሚያስችል የቴክኖሎጂ አቅም ይፈጥራል። ይህም በአስተዳደሩ የሙያ ሥልጠና ጥራትን ከማሻሻል አንፃር ብቁ የሰው ኃይል እንዲዘጋጅ፣ ተመራቂዎች ያገኙት የሙያ ብቃት በተጨባጭ እንዲረጋገጥና የሥራ ገበያው የሚፈልገውን የብቃት ደረጃ ያሟላ የሰው ኃይል ለማፍራት ወሳኝ ሚና ይኖረዋል። የተገኘው ድጋፍ በተጨማሪም በድሬዳዋ የሙያ ብቃት ምዘናና ማረጋገጫ ሥርዓትን ከዘመናዊ የቴክኖሎጂ አሠራሮች ጋር በማስማማት፣ የምዘና አገልግሎቱን በተቀናጀ መልኩ ለማስኬድ እና በክህሎት ልማት ዘርፍ የሚታየውን የጥራት ፍላጎት ለመመለስ የሚያስችል መሠረት እንደሚጥል ተገልጿል። በመሆኑም የድሬዳዋ አስተዳደር የሙያ ብቃት ምዘናና ማረጋገጫ ማዕከል ከዚህ ድጋፍ በመነሳት የቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ሥልጠና ጥራትን በማረጋገጥ፣ የተመዛኙን የሙያ ብቃት በተጨባጭ በመመዘን እና የሥራ ገበያውን ፍላጎት የሚያሟላ ብቁ የሰው ኃይል ለማፍራት ያለውን ሚና የበለጠ እንዲያጠናክር ይጠበቃል። የሥራና ክህሎት ቢሮ የህዝብ ግንኙነት ድሬዳዋ | ነሐሴ 16/2018 ዓ.ም.

photo content
+1

የድሬዳዋ አስተዳደር ሥራና ክህሎት ቢሮ ለ250 ተማሪዎች የትምህርት መርጃ ቁሳቁስ ድጋፍ አደረገ ድሬዳዋ፣ ነሐሴ 16/2018 ዓ.ም. — የድሬዳዋ አስተዳደር ሥራና ክህሎት ቢሮ መጪውን የ2019 ዓ.ም. የትምህርት ዘመን በማስመልከት ለ250 ተማሪዎች የሚውል የትምህርት መርጃ ቁሳቁስ ድጋፍ አደረገ። ድጋፉ ተማሪዎች የትምህርት ዘመኑን በተሻለ ዝግጅት እንዲጀምሩና የትምህርት ተሳትፎአቸውን እንዲያጠናክሩ የሚያግዙ ደብተር፣ እስክሪብቶ፣ እርሳስና ሌሎች የትምህርት ቁሳቁሶችን ያካተተ ሲሆን፣ ጠቅላላ ዋጋውም ከ250,000 ብር በላይ ነው። የቢሮው ኃላፊ አቶ ሮቤል ጌታቸው በርክክቡ ወቅት ድጋፉን ለድሬዳዋ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ኃላፊ አቶ ሱልጣን አልዪ አስረክበዋል። ድጋፉ የቢሮው የማኅበራዊ ኃላፊነት ተሳትፎን ከማረጋገጥ ባለፈ፣ የተማሪዎችን የትምህርት ዕድል ለማጠናከርና የትምህርት ተደራሽነትን ለማሳደግ የቢሮው ቁርጠኝነት አካል መሆኑን አቶ ሮቤል ገልጸዋል። የቢሮውየሕዝብ ግንኙነት ነሐሴ 16/2018 ዓ.ም.

photo content
+3

የድሬዳዋ አስተዳደር ሥራና ክህሎት ቢሮ ለ250 ተማሪዎች የትምህርት መርጃ ቁሳቁስ ድጋፍ አደረገ ድሬዳዋ፣ ነሐሴ 16/2018 ዓ.ም. — የድሬዳዋ አስተዳደር ሥራና ክህሎት ቢሮ መጪውን የ2019 ዓ.ም. የትምህርት ዘመን በማስመልከት ለ250 ተማሪዎች የሚውል የትምህርት መርጃ ቁሳቁስ ድጋፍ አደረገ። ድጋፉ ተማሪዎች የትምህርት ዘመኑን በተሻለ ዝግጅት እንዲጀምሩና የትምህርት ተሳትፎአቸውን እንዲያጠናክሩ የሚያግዙ ደብተር፣ እስክሪብቶ፣ እርሳስና ሌሎች የትምህርት ቁሳቁሶችን ያካተተ ሲሆን፣ ጠቅላላ ዋጋውም ከ250,000 ብር በላይ ነው። የቢሮው ኃላፊ አቶ ሮቤል ጌታቸው በርክክቡ ወቅት ድጋፉን ለድሬዳዋ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ኃላፊ አቶ ሱልጣን አልዪ አስረክበዋል። ድጋፉ የቢሮው የማኅበራዊ ኃላፊነት ተሳትፎን ከማረጋገጥ ባለፈ፣ የተማሪዎችን የትምህርት ዕድል ለማጠናከርና የትምህርት ተደራሽነትን ለማሳደግ የቢሮው ቁርጠኝነት አካል መሆኑን አቶ ሮቤል ገልጸዋል። የቢሮውየሕዝብ ግንኙነት ነሐሴ 16/2018 ዓ.ም.

ከ1,800 በላይ ወጣቶችን ከሥራ ዓለም ጋር ለማስተሳሰር፤ የብቃት የወጣቶች የሥራ ላይ ልምምድ ፕሮጀክት 4ኛ ዙር ወደ ትግበራ መግባቱ ተገለጸ፤ ድሬዳዋ፣ ነሐሴ 14/2018 ዓ.ም. — ከፌዴራል ሥራና ክህሎት ሚኒስቴር ጋር በትብብር እና በዓለም ባንክ ድጋፍ በድሬዳዋ አስተዳደር እየተተገበረ የሚገኘው የብቃት የወጣቶች የሥራ ላይ ልምምድ ፕሮጀክት 4ኛ ዙር በሥራ ፈጣሪዎችና በድርጅት ባለቤቶች ትብብር ወጣቶችን ከተግባራዊ የሥራ ዓለም ጋር ለማስተሳሰር ያለመ ውይይት ተካሂዷል። የውይይቱ ዋና ዓላማ በፕሮጀክቱ ስር የታቀፉ ወጣቶች የሥራ ላይ ልምምድ በማግኘት የሙያ ብቃታቸውን እንዲያሳድጉ፣ የሥራ ልምድ እንዲያካብቱ እና በቀጣይ በሥራ ዓለም ውስጥ ተወዳዳሪና ምርታማ ሠራተኛ እንዲሆኑ ከድርጅት ባለቤቶች ጋር የተጠናከረ ትስስር መፍጠር ነው። በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የድሬዳዋ ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ኃላፊ ክቡር አቶ ኢብራሂም ዩሱፍ በውይይቱ ወቅት ፕሮጀክቱ አሁን ላይ ለ4ኛ ዙር እየተተገበረ መሆኑን ጠቁመው፣ በቀደሙት ሦስት ዙሮች በርካታ ወጣቶች የሥራ ላይ ልምምድ በማግኘት ከሥራ አጥነት ወደ ሥራ ዓለም መሸጋገር መቻላቸውን ገልጸዋል። ኃላፊው አክለውም፣ በ4ኛው ዙር ከ1,800 በላይ ወጣቶች የሕይወት ክህሎት ሥልጠና ወስደው ወደ ተግባራዊ የሥራ ላይ ልምምድ ለመሰማራት ዝግጁ መሆናቸው ለአስተዳደሩ የሚያበረክተው ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ጠቀሜታ የላቀ መሆኑን ጠቅሰዋል።
“የዛሬ ወጣት የነገ ሠራተኛ ብቻ ሳይሆን የነገ ሥራ ፈጣሪ ነው። ስለዚህ የሥራ ላይ ልምምዱ ወጣቶችን ከሥራ ዕድል ጋር ብቻ ሳይሆን ከተግባራዊ ብቃት፣ ከሙያ ልምድና ከሥራ ዓለም ባህል ጋር የሚያስተዋውቅ ወሳኝ የሰው ኃይል ልማት መሣሪያ ነው።”
የድሬዳዋ አስተዳደር ሥራና ክህሎት ቢሮ ኃላፊ ክቡር አቶ ሮቤል ጌታቸው በበኩላቸው ወጣቶቹ በተለያዩ ድርጅቶች የሥራ ላይ ልምምድ በሚያካሂዱበት ወቅት የሚያገኙትን ልምድ ወደ ዘላቂ የሥራ ዕድል ለመቀየር የድርጅት ባለቤቶች ሚና ከፍተኛ መሆኑን አስገንዝበዋል። በተለይም ወጣቶቹ በልምምድ ወቅት የሚያሳዩትን ትጋት፣ የሥራ ሥነ-ምግባር፣ ተግባቦት፣ የቡድን ሥራ አቅምና የሙያ ብቃት በመመዘን በድርጅታቸው ውስጥ የቅጥር ዕድል እንዲያገኙ ወይም ያገኙትን ልምድ ተጠቅመው በሌሎች ተቋማት የሥራ ዕድል እንዲያገኙ የሚያግዝ ሥርዓት መፍጠር እንደሚገባ ጠቁመዋል። የድርጅት ባለቤቶች ተሳትፎ ወሳኝ ነው! የወጣቶችን የሥራ ላይ ልምምድ ወደ ተጨባጭ የሥራ ዕድል ለመቀየር የግሉ ዘርፍ ተሳትፎ ወሳኝ መሆኑ በመድረኩ ተገልጿል። የድርጅት ባለቤቶች ወጣቶችን በሥራ ቦታቸው በመቀበል የተግባር ልምድ እንዲያገኙ፣ ከልምድ ባለሙያዎች እንዲማሩ እና የሥራ ዓለምን በተግባር እንዲያውቁ የማስቻል ኃላፊነት አለባቸው። ይህም በአስተዳደሩ የሚታየውን የሥራ አጥነት ቁጥር በተጨባጭ ለመቀነስ፣ የወጣቶችን የሥራ ተወዳዳሪነት ለማሳደግ እና በአሠሪዎችና በሥራ ፈላጊዎች መካከል ያለውን የብቃት ክፍተት ለማጥበብ አስተዋጽኦ ያደርጋል። ከልምምድ ወደ ቅጥር፣ ከቅጥር ወደ ምርታማነት! በውይይቱ ወቅት ወጣቶች ወደ ድርጅቶች ሲሄዱ ምን ዓይነት የሥራ ሥነ-ምግባር ሊከተሉ እንደሚገባቸው፣ ከድርጅቶች ምን እንደሚጠበቅ፣ በልምምድ ወቅት ሊከተሉ ስለሚገባቸው ሂደቶች እና ፕሮጀክቱ ያለውን አጠቃላይ ፋይዳ የሚያብራራ ጽሑፍ ቀርቦ ሰፊ ውይይት ተካሂዷል። በመጨረሻም የድሬዳዋ አስተዳደር ሥራና ክህሎት ቢሮ በአራቱም ዙሮች የወጣቶች የሥራ ላይ ልምምድ ፕሮጀክት በሚተገበርበት ወቅት በራቸውን በመክፈት ወጣቶች የተግባር ሥራ ልምድ እንዲያገኙ ላደረጉ የድርጅት ባለቤቶችና ባለሀብቶች ምስጋና አቅርቧል። የ4ኛው ዙር የብቃት የወጣቶች የሥራ ላይ ልምምድ ፕሮጀክት ትልቁ ግብ ወጣቶችን ማሰልጠን ብቻ ሳይሆን፣ ብቃታቸውን ወደ ሥራ፣ ሥራን ወደ ገቢ፣ ገቢን ወደ ራስን መቻል እና ራስን መቻልን ወደ ዘላቂ የኢኮኖሚ ተሳትፎ መቀየር ነው። የድሬዳዋ አስተዳደር ሥራና ክህሎት ቢሮ ነሐሴ 14/2018 ዓ.ም.

photo content
+9

የወጣት ሥራ ፈጣሪነት ለብልጽግናችን ስኬት   “የወጣት ሥራ ፈጣሪነት ለብልጽግናችን ስኬት” በሚል መሪ ሃሳብ፣ ለድሬዳዋ አስተዳደር ሥራና ክህሎት ቢሮ ብልፅግና ህብረት የወጣቶች ክንፍ አመራሮችና አባላት የአቅም ግንባታ ስልጠና መድረክ ተካሄደ።   ስልጠናው ወጣቶችን በሥራ ፈጠራ፣ በክህሎት ልማት፣ በአመራርና በኢኮኖሚ ተሳትፎ ለማብቃት ያለመ ሲሆን፣ የወጣቶችን አጠቃላይ ፈጠራ በተለይም የሥራ ፈጠራ አቅምን ወደ ተጨባጭ የሥራና የሀብት ፈጠራ ዕድል ለመቀየር ትኩረት ተሰጥቶበታል።   በመድረኩ የወጣቶችን አቅም ማጎልበትና የሥራ ፈጠራ ባህልን ማስፋት ለድሬዳዋ የኢኮኖሚ እድገትና ለብልጽግና ጉዞ ወሳኝ መሆኑ ተገልጿል።   [የድሬዳዋ አስተዳደር ሥራና ክህሎት ቢሮ]፣ ነሐሴ 13/2018 ዓ.ም.

photo content
+6

የሥራ እድል ፈጠራን ለማሳደግ የሥራ ማዕከላት አፈጻጸም ላይ ውይይት ተካሄደ   ቢሮው የሥራ እድል ፈጠራን ለማሳደግና የሥራ ፈላጊዎችን ከተፈጠሩ የሥራ እድሎች ጋር በተሻለ ሁኔታ ለማገናኘት ከሥራ ማዕከል አመራሮችና ባለሙያዎች ጋር ውይይት አካሄደ።   በውይይቱ የሥራ ማዕከላት የሥራ ፈላጊዎችን ከአሰሪዎች ጋር በማገናኘት፣ የሥራ ገበያ መረጃን በማደራጀትና ተገቢውን የሥራ እድል ለተገቢው የሰው ኃይል በማቅረብ የሚኖራቸው ሚና በዝርዝር ተነስቷል።   በተለይም የሥራ ፈላጊዎችን ፍላጎትና ችሎታ በትክክል መለየት፣ የሥራ ገበያውን ፍላጎት በወቅቱ መረዳት፣ አሰሪዎችን በበቂ ሁኔታ ማሳተፍ እና የሥራ ማዕከላትን አገልግሎት በመረጃና በቴክኖሎጂ የተደገፈ ማድረግ እንደሚገባ ተጠቁሟል።   የሥራ እድል ፈጠራ ቁጥርን ከመጨመር ባለፈ ዘላቂ፣ ምርታማና ከሥራ ገበያው ፍላጎት ጋር የተጣጣመ የሥራ እድል ማስፋፋት እንደሚጠይቅም በውይይቱ ተመላክቷል። በዚህም የግሉ ዘርፍ፣ የሥራ ፈጠራ ተቋማትና የክህሎት ልማት ተቋማት በቅንጅት መሥራታቸው የሥራ ገበያውን ውጤታማነት ለማሳደግ ወሳኝ መሆኑ ተገልጿል።   የሥራ ማዕከል አመራሮችና ባለሙያዎችም በተግባር የሚያጋጥሟቸውን ችግሮች፣ ያሉ አቅሞችና በቀጣይ ሊሻሻሉ የሚገቡ የአሠራር ጉዳዮችን በማንሳት ለውይይቱ ግብዓት አቅርበዋል።   በመጨረሻም የሥራ ማዕከላትን አቅም በማጠናከር፣ የሥራ ገበያ መረጃን በተሻለ ሁኔታ በመጠቀምና ተቋማዊ ቅንጅትን በማሳደግ የሥራ ፈላጊዎችን ወደ ተጨባጭና ዘላቂ የሥራ እድል የሚያሸጋግር ውጤት-ተኮር አሠራር ለመገንባት አቅጣጫ ተቀምጧል።   [የድሬዳዋ አስተዳደር ሥራና ክህሎት ቢሮ]፣ ነሐሴ 12/2018 ዓ.ም.

photo content
+4

photo content
+4

ለአስተዳደሩ ስራ አጥ ወጣቶች የህይወት ክህሎት ስልጠና ተሰጠ:: #EIPC ነሃሴ 12.2018 ዓ.ም ድሬዳዋ ኤስ.ኦ.ኤስ(SOS) አፍሪካን ቪሌጅ ድሬዳዋ ቅርንጫፍ ከኢትዮ-ጣሊያን ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ ጋር በመተባበር ከአስተዳደሩ ወረዳዎች ለተወጣጡ ስራ አጥ ወጣቶች የህይወት ክህሎት ስልጠና ተሰጥቷል:: ኤስ.ኦ.ኤስ(SOS) አፍሪካን ቪሌጅ ከአስተዳደሩ ወረዳዎች ለተወጣጡ ስራ አጥ ወጣቶች የተለያዩ የሙያ ስልጠዎችን በማሰልጠን ከስራ ጋር ለማስተሳሰር ያለመ ፕሮግራም በመንደፍ በኮሌጁ ስልጠና እየሰጠ የሚገኝ ሲሆን የህይወት ክህሎት ስልጠናውም የዚሁ መርሃ-ግብር አካል መሆኑም ተገልፇል:: ለተከታታይ ሶስት ቀናት በኢትዮ-ጣሊያን ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ ለስራ አጥ ወጣቶች የተሰጠው የህይወት ክህሎት ስልጠና በኮሌጁ አሰልጣኝ መምህራን አማካኝነት የተሰጠ ሲሆን በስልጠናውም ወጣቶች የቀጣይ ህይወታቸውን የመምራት ክህሎት፣ችግሮችን የመፍታት ክህሎት እንዲሁም የውሳኔ አሰጣጥ ክህሎቶችን የሚያዳብሩበት ስልጠና ያገኙበት እንደነበርም ተገልፇል:: ተጨማሪ መረጃዎችን በሚከተሉት አማራጮች ያግኙ፡- በፌስቡክ -https://www.facebook.com/share/19wDiZAD7x/?mibextid=wwXIfr በቴሌግራም -https://t.me/EIPC2001 በቲክቶክ -https://www.tiktok.com/@ethioitaly2001?_t=ZM-90MxIrBN8qe&_r=1 በዌብሳይት - https://ethioitalypolytechniccollege.com/

ተቋማት በተናበበና ወጥ እቅድ የካፒታል ፕሮጀክቶችን መፈጸማቸው የተሻለ ውጤት እንዲመዘገብ እንደሚያስችል ተገለጸ ​የድሬደዋ አስተዳደር የሴክተር ተቋማት የ2019 በጀት ዓመት የካፒታል ፕሮጀክቶች የቃል ኪዳን ሰነድ የፊርማ ሥነ-ሥርዓት ተካሄደ። ​በሥነ-ሥርዓቱ ላይ የተገኙት የድሬደዋ አስተዳደር ከንቲባ ክቡር አቶ ከድር ጁሃር፤ በአስተዳደሩ በየዓመቱ የሕዝቡን ተጠቃሚነት ማዕከል ያደረጉና ማህበራዊ ኢኮኖሚያዊ ፋይዳ ያላቸው የካፒታል ፕሮጀክቶች እንደሚተገበሩ ገልጸዋል። ​እነዚህ ፕሮጀክቶች በአግባቡ ሥራ ላይ ውለው የታለመላቸውን ዓላማ ማሳካት እንዲችሉ በጥብቅ የፕሮጀክት አስተዳደርና አፈጻጸም መመራት እንዳለባቸው ከንቲባው አሳስበዋል። ​አሁን የተፈጸመው የቃል ኪዳን ሰነድ፣ ተቋማት በበጀት ዓመቱ የሚያከናውኗቸውን የካፒታል ፕሮጀክቶች በውጤታማነት ለመፈጸም ቃል የሚገቡበት ከመሆኑም በላይ፤ በቀጣይም በሰነዱ መሠረት ተጠያቂነትና ኃላፊነትን የሚያሰፍን እንደሆነ ጠቁመዋል። ​በመጨረሻም ከዚህ ቀደም በፕሮጀክት አፈጻጸም ወቅት ከነበሩ ማነቆዎች ትምህርት በመውሰድ፣ አዳዲስና ነባር ፕሮጀክቶችን በጥራትና በተቀመጠላቸው ጊዜ ገደብ ማጠናቀቅ እንደሚገባ ከንቲባ አቶ ከድር ጁሃር የሥራ መመሪያ አስተላልፈዋል። ©️ DGC ነሐሴ 8/2018