1 321
Подписчики
+224 часа
+87 дней
+15130 дней
Архив постов
Repost from Dire Dawa Polytechnic College
+9
የበጀት፣ ኢኮኖሚ ንግድና የኢንዱስትሪ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ የኮሌጁን መደበኛ ፣ በኮሌጁ በሚገኙ ፕሮጀክቶች የ2018 በጀት ዓመት የ6 ወር የእቅድ አፈጻጸም ግምገማ በድሬዳዋ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ አከናወነ፡፡
የኮሌጁን መደበኛ ፣በኮሌጁ በሚገኙ ፕሮጀክቶች የ2018 በጀት ዓመት የ6ወር የእቅድ አፈጻጸም ከዝግጅት ምእራፍ አንስቶ እስከ ግማሽ በጀት አመቱ ማጠቃለያ ድረስ በከፍተኛ ትጋትና የሁሉም ተሳትፎ በጋራ በማካተት እየሰራ እንዳለ የተገለጸ ሲሆን ፡፡ በተጨማሪም ኮሌጁ በ ቴክኒክና ሙያ አዲሱ እሳቤ አንጻር ከእቅዱ ጋር በማስተሳሰር እየሠራ እንደሚገኝ ለቋሚ ኮሚቴው ገለጻ ተደርጓል።የከተማው አስተዳደር ለኮሌጁ የሰጠውን ሃላፊነት ኮሌጁ ተቀብሎ ከእቅዱ ጋር በማስተሳሰር ያለምንም እንከን እየሰራንም እንዳለ የተብራራ ሲሆን።
የቋሚ ኮሚቴው አባላት እንዳሉት ኮሌጁ በመደበኛ እንዲሁም በኮሌጁ ባሉ ፕሮጀክቶች አፈጻጸም ከእቅዱ አንጻር አመርቂ ውጤት የታየበት ነው ያሉ ሲሆን አያይዘውም ተቋሙን ሞዴል እንዲሆን የሚሰራው ስራ ተጠናክሮ መቀጠል አለበት የተገኙ ልምዶችና ውጤቶች ለሌሎች ተቋማት የማካፈል ስራዎች ተጠናክሮ ሊቀጥል ይገባል ብለዋል፡፡በተለይ የገጠሩን ማህበረሰብ ለመጥቀም እየተሰራ ያለው ቴኖሎጂዎችን የማፍራትና የማሸጋገሩ ስራ እንዲሁም ትምህርትና ስልጠናዎችን ፕሮጀክት ተኮር እንዲሆኑ በተጨማሪም የኮሪደር ልማቱ ላይ ያለው አመርቂ ውጤት ተጠናክሮ ሊቀጥል ይገባል ብለዋል፡፡በመጨረሻም ልኡክ ቡድኑ በኮሌጁ እየተሰሩ ያሉ ስራዎችን ተዘዋውረው የጎበኙ ሲሆን የመስክ ምልከታውንና ሪፖርቱን መሰረት በማድረግ የተለያዩ ገንቢ አስተያየቶችን ሰጥተዋል፡፡
የኮሌጁ ኮምኒኬሽን
ጥር 4/2018 ዓ.ም ድሬዳዋ
+8
በክቡር ዳንኤል ተሬሳ የተመራው የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር የድጋፍና ክትትል ቡድን በጅግጅጋ የመግቢያ ውይይት ማድረግ ጀመረ፡፡
መድረኩ በቀጣይ በዘርፉ ታቅደው እየተከናወኑ የሚገኙ ተግባራት የሚገኙበትን ሁኔታ በአካል በማየት ጠንካራ ሥራዎች በመለየት ወደሁሉም እንዲሰፉ የማድረግ እና ክፍተቶች ካሉ ደግሞ የማገዝ ሥራ ለመስራት መግባባት የሚፈጠርበት ይሆናል፡፡
ድጋፍና ክትትሉ ዛሬ በይፋ ሲጀመር በጅግጅጋ ከተማ የሶማሌ ክልልን ጨምሮ የሀረሪ ክልል እና የድሬዳዋ አስተዳደር የዘርፉ አመራሮች በተገኙበት የአፈጻጸም ሪፖርት ቀርቦ የመግቢያ ውይይት በመደረግ ላይ ይገኛል፡፡
Repost from Dire Dawa Polytechnic College
+3
ኢንዱስትሪዎች ጥራቱን የጠበቀ ምርት እንዲያመርቱ የስራ ቦታቸው ምቹ ሊሆኑ ይገባል ተባለ፡፡
የድሬዳዋ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ በተለያዩ ኢንዱስትሪዎች ሲሰጥ የነበረውን የአራቱን ኢንዱስትሪ ኤክስቴንሽን የድጋፍ ማእቀፎች ስልጠናና ትግበራ ስራ በማስቀጠል ኡሚ ዱቄት ፋብሪካ ለሚገኙ ሰራተኞች በካይዘን አተገባበር ላይና የካይዘን ክህሎት ላይ ትኩረቱን ያደረገ ስልጠና ሰጠ፡፡
ኮሌጁ በተያዘው በጀት አመት ሊሰራቸው ካቀዳቸው ስራዎች መካከል አንዱና ዋንኛው ኢንዱስትሪዎች የተሸለ ምርት እንዲያመርቱ የሚያስችላቸውን አቅም የመገንባትና የካይዘን ፍልስፍና አተገባበር ላይ በቂ ግንዛቤ በመፍጠር ኢንዱስትሪዎች ምርታቸውን ያለምንም ብክነት ለገበያ እንዲያቀርቡ ማስቻል ነው፡፡
በዛሬው እለት የተጀመረው የካይዘን ትግበራ የመጀመሪያ ምእራፍ ስራ ከዚህ ቀደም በተለያዩ አነስተኛ፣መካከለኛና ከፍተኛ ኢንዱስትሪዎች ላይ ተከታታይነት ያለው የካይዘንና ሂሰብ መዝገብ አያያዝ ስልጠናዎች የተሰሩ ሲሆን በተጨማሪም ኢንዱስትሪዎቹ ያለባቸውን ክፍተት ለመሙላት ተከታታይነት ያለው የዳሰሳ ጥናት የተደረገ ሲሆን በተገኘው ግብአት መሰረት ኮሌጁ በተረከባቸው ኢንዱስትሪዎች ላይ አራቱን የድጋፍ ማእቀፎች የሚተገብር ይሆናል፡፡በዚህም ስራ ላይ የኮሌጁ መምህራን ከኢንዱስትሪው ባለሙያዎች ጋር በጋራ በመሆን የሚተገበር ሲሆን በቀጣይም በኢንዱስትሪው ውስጥ የሚኖሩ የቴክኖሎጂ ችግሮችን፣የስፔርፓር ችግሮችን እንዲሁም የክህሎት ችግሮችን ተከታታይነት ያለው ስራዎችን በመስራት የሚፈታ ይሆናል፡፡
የኮሌጁ ኮምኒኬሽን
ጥር 1/2018 ዓ.ም ድሬዳዋ
የድሬዳዋ አስተዳደር ሥራና ክህሎት ቢሮ በኢንተርፕራይዝ ልማት ስራዎች የ2018 በጀት አመት የመጀመሪያ ስድስት ወራት አፈጻጸም
✍️ በግማሽ ዓመቱ ውስጥ አዳዲስ ኢንተርፕራይዞችን እንዲደራጁ በማድረግ ሂደት በሦስቱም ዘርፎች ማለትም በግብርና 1113 አባላት ያላቸው 118 ኢንተርፕራይዞች፣ በኢንድስትሪ 791 አባላት ያላቸው 107 ኢንተርፕራየዞች እንዲሁም በአገልግሎት ዘርፍ 2069 አባላት ያሏቸው 190 ኢንተርፕራይዞችን በአጠቃላይ በሦስቱም ዘርፎች 3973 አባላትን ያቀፉ 415 ኢንተርፕራይዞችን ማደራጀት ተችሏል፡፡ ይህም በዕቅድ ከተያዘው 750 አዳዲስ ኢንተርፕራይዞችን ከማደራጀት አንፃር የ55.3 በመቶ አፈፃፀም አለው፡፡
✍️ ለኢንተርፕራይዞች የሚሰጡ መንግስታዊ ድጋፎችን በማጠናከር ከአንዱ የእድገት ደረጃ ወደ ቀጣይ የእድገት ደረጃ እንዲሸጋገሩ የማድረግ ስራም ሲከናወን የቆየ ሲሆን በዚህም መሰረት 312 ኢንተርፕራይዞች ሽግግር እንዲያደርጉ ማድረግ ተችሏል፡፡ ይህም በዕቅድ ተይዞ ከነበረው የ320 ኢንተርፕራይዞች የደረጃ እድገት ሽግግር አንፃር የ97.5 በመቶ አፈፃፀም አለው፡፡ ከዚህ በተጨማሪም 77 ኢንተርፕራይዞች ቅድመ ሞዴል ማድረግ ተችሏል፡፡ ይህም በግማሽ ዓመቱ 87 ኢንተርፕራይዞችን ቅድመ ሞዴል ለማድረግ ከተያዘው ዕቀድ አንፃር የ88.5 በመቶ የተመዘገበበት ነው፡፡
✍️ 377 ኢንተርፕራይዞች የ72,807,737 ብር የገበያ ትስስር እንዲፈጠርላቸው ማድረግ ተችሏል፡፡ ይህም የገበያ ትስስር ተጠቃሚ ለማድረግ ከታቀደው 218 የኢንተርፕራይዞች መጠን እንዲሁም ከትስስሩ የገንዘብ መጠን አንፃር በሁለቱም ከ100 ፐርሰንት በላይ አፈፃፀም የተመዘገበበት ነው፡፡
✍️ ኢንተርፕራይዞች የፋይናንስ አቅማቸውን እንዲያጠናክሩ በማድረግ ሂደት 180 ሚሊዮን ብር እንዲቆጥቡ ለማድረግ ታቅዶ 324.61 ሚሊዮን ብር ማስቆጠብ ተችሏል ይሕም ከ100 ፐርሰንት በላይ አፈፃፀም የተመዘገበበት ሆኗል፡፡
✍️ ኢንተርፕራይዞችን የብድር አገልግሎት ተጠቃሚ እንዲሆኑ ከማድረግ አንፃር 2750 አባላት ያሏቸውን 2000 ኢንተርፕራይዞች የ205 ሚሊዮን ብር ብድር ተጠቃሚ ለማድረግ ታቅዶ 2749 አባላት ላሏቸው 1943 ኢንተርፕራይዞች የ310,532,293 ብር ብድር ተጠቃሚ ማድረግ ተችሏል፡፡ በዚህም ለማሰራጨት ከታቀደው የብድር ገንዘብ መጠን አንፃር ከ100 ፐርሰንት በላይ፣ ከብድር ተጠቃሚ አንቀሳቃሾች አንፃር የ100 ፐርሰንት እንዲሁም የብድር ተጠቃሚ ለማድረግ ከታቀደው የኢንተርፕራይዞች ቁጥር አንፃር ደግሞ የ97 በመቶ አፈፃፀም ሊመዘገብ ችሏል፡፡
✍️ ለኢንተርፕራይዞች ከተሰራጨ ብድር ውስጥ ከዘመኑ እና ከውዝፍ ብድሮች ከ150.5 ሚሊዮን ብር በላይ ለማስመለስ ታቅዶ ከውዝፍ ብድር 4,968,929 ብር እንዲሁም ከዘመኑ ብድር 175,292,009 በድምሩ 180,260,938 ብር ተመላሽ እንዲሆን ማድረግ ተችሏል፡፡ ይምህ ከዕቅድ አንፃር ከ100 ፐርሰንት አፈፃፀም የተመዘገበበት ነው፡፡
✍️ ለኢንተርፕራይዞች ከሚሰጥ የኦዲትና የሂሳብ አያያዝ ዝርጋታ አገልግሎቶች አንፃር ለ532 ኢንተርፕራይዞች የሂሳብ መዝገብ አያያዝ ስርዓት የመዘርጋት እና ለ446 ኢንተርፕራይዞች ደግሞ የኦዲት አገልግሎቶችን የመስጠት ስራ ተከናውኗል፡፡ በአጠቃላይ ከሂሳብ መዝገብ አያያዝ ስርዓት ዝርጋታ አንፃር በዕቅድ ተይዞ ከነበረው 475 አንፃር ከ100 ፐርሰንት በላይ አፈፃፀም የተመዘገበበት ሲሆን የኦዲት አገልግሎትን ለኢንተርፕራይዞች ከመስጠት አንፃር በዕቅድ ከተያዘው የ500 ኢንተርፕራይዞች መጠን የ89.2 በመቶ አፈፃፀም እንዲመዘገብ ለማድረግ ተችሏል፡፡
የድሬዳዋ አስተዳደር ሥራና ክህሎት ቢሮ በሥራ ዕድል ፈጠራ ስራዎች የ2018 በጀት አመት የመጀመሪያ ስድስት ወራት ምን አከናወነ?
✍️ 54 ኢንተርፕራይዞች በኢትዮጵያ የስራ ገበያ መረጃ አስተዳደር ስርዓት (ELMIS) ፕላትፎርም ላይ ተመዝግበዋል፣
✍️ ስራ ፈላጊ ዜጎችን በኢትዮጵያ የስራ ገበያ መረጃ ስርዓት መተግበሪያ (Ethiopia Labor Market Information System) ላይ ከመመዝገብ አኳያ ወንድ 3218 ሴት 4208 በድምሩ 7436 ለመመዝገብ ተችሏል፡፡ ይህም በበጀት ዓመቱ የመጀመሪያው ግማሽ ዓመት ለመመዝገብ ከታቀደው 11,227 የስራ አጥ ምዝገባ መጠን አንፃር የ66.14 በመቶ አፈፃፀም የተመዘገበበት ሆኗል፡፡
✍️ በጠቅላላው ስድስት ወራት ውስጥ በከተማ በነበረ የሥራ ዕድል ፈጠራ በሦስቱም ዘርፎች ማለትም በግብርና ለ172 ዜጎች (2.3%)፤ በኢንድስትሪ ለ3183 ዜጎች (42%) እንዲሁም በአገልግሎት ለ4223 ዜጎች (55.7%) በድምሩ 7,578 ዜጎች (ወንድ 4380፤ ሴት 3198) የሥራ ዕድል መፍጠር ተችሏል፡፡ ይህም ሦስቱም ዘርፎች በዕቅድ ተይዞ ከነበረው 8241 የስራ ዕድል ፈጠራ አንፃር የ92 በመቶ አፈፃፀም ያለው ነው፡፡
✍️ በጠቅላላው በስድስት ወራት ውስጥ በገጠር በነበረ የሥራ ዕድል ፈጠራ በሦስቱም ዘርፎች ማለትም በግብርና ለ1010 ዜጎች (59.23%)፤ በኢንድስትሪ ለ155 ዜጎች (9.1%) እንዲሁም በአገልግሎት ለ540 ዜጎች (31.7%) በድምሩ 1705 ዜጎች (ወንድ 915፤ ሴት 790) የሥራ ዕድል መፍጠር ተችሏል፡፡ ይህም በሦስቱም ዘርፎች በዕቅድ ተይዞ ከነበረው 2707 የስራ ዕድል ፈጠራ አንፃር የ63 በመቶ አፈፃፀም ያለው ነው፡፡
✍️ ከ9283 የሥራ ዕድል ውስጥ የሴቶች ድርሻ 3988 ሲሆን ይህም የ43 በመቶ ድርሻ ያለው ነው፡፡ ከዕቅድ አንፃር ደግሞ የ73 በመቶ አፈፃፀም አለው፡፡
✍️ ከ9283 የሥራ ዕድል ውስጥ አጠቃላይ የወጣቶች መጠን 6366 ሲሆን ይሕም ከጠቅላላው የሥራ ዕድል ተጠቃሚዎች ውስጥ የ68.6 በመቶ ድርሻ ያለው ነው፡፡ ከዕቅድ አንፃር የ72.7 በመቶ አፈፃፀም አለው፡፡
✍️ ለ41 አካል ጉዳተኛ ዜጎች የሥራ ዕድል እንዲፈጠርላቸው ተደርጓል፡፡ ይህም በዕቅድ ከተያዘው የ77 አካል ጉዳተኞች የስራ ዕድል ተጠቃሚነት አንፃር የ53 በመቶ አፈፃፀም ያለው ነው፡፡
✍️ ከ973 ብቃት የወጣቶች የሥራ ላይ ልምምድ ካደረጉት ውስጥ ወንድ 245 ሴት 631 በድምሩ 876 ተጨማሪ የኮምፒውተር ክህሎት ስልጠና የወሰዱ ናቸው፡፡
✍️ በብቃት የወጣቶች የሥራ ላይ ልምምድ ፕሮጀክት ከ973 ሰልጣኞች ውስጥ ከ27 ሰልጣኞች ማቋረጥ በስተቀር ቀሪዎቹ 946 ወጣቶች የስራ ትስስር ተፈጥሮላቸዋል፡፡
✍️ ቢሮው ከቆላማ አካባቢዎች የኑሮ ማሻሻያ ፕሮጀክት(LLRP) ጋር በመተባበር ለ15 በአስተዳደሩ ገጠር ለሚገኙ ኢንተርፕራይዞች ወንድ 46 ሴት 146 በድምሩ ለ192 ዜጎች ለእያንዳንዱ ኢንተርፕራይዝ 500,000 ሺህ ብር በድምሩ 7.5 ሚሊዮን ብር ድጋፍ ተደርጎ ወደ ስራ እንዲገቡ ማድረግ ተችሏል።
✍️ ቢሮው ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ጋር በትብብር የሚሰራ ግራንድ ግሩፕ ኢንተርፕራይዝ ጋር በመቀናጀት በኢ-መኒ ዲጂታል ፋይናንስ በሁሉም ወረዳዎች 40 ኢንተርፕራይዞች በአጠቃላይ 200 ዜጎችን ወደ ስራ ለመግባት ዝግጁ ሆነው ተደራጅተዋል።
በድሬዳዋ አስተዳደር ከተለያዩ ቢሮዎችና ከሚመለከታቸው አካላት የተወጣጣ የሱፐርቪዥን ቡድን የአስተዳደሩን ሥራና ክህሎት ቢሮ እና በስሩ የሚገኙ ኮሌጆችን የ2018 በጀት የመጀመሪያ ግማሽ አመት የዕቅድ አፈጻጸም ገመገመ፤
በቢሮው እንዲሁም በድሬዳዋ እና በኢትዮ ጣሊያን ፖሊቴክኒክ ኮሌጆች የተከናወነ የ2018 በጀት አመት የመጀመሪያ ስድስት ወራት የስራ አፈጻጸም ቀርቦም ሰፊ ውይይት ተካሂዶበታል።
በመጨረሻም የሱፐርቪዥን ቡድን አባላቱ የቀረበው ሪፖርት አቀራረቡንና የተከናወኑ ስራዎችን አድንቀው በቀጣይ ሊተኮርባቸውና ሊስተካከሉ የሚገባቸውን ጉዳዮች ሀሳብና አስተያየቶች አክለው አቅጣጫ ሰጥተዋል።
የሥራና ክህሎት ቢሮ ህዝብ ግንኙነት
ታህሳስ 28/2018 ዓ.ም
ድሬዳዋ
ለክርስትና እምነት ተከታዮች በሙሉ እንኳን ለጌታችንና ለመድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የልደት በዓል በሰላም አደረሰን፤ አደረሳችሁ፤
*
በክርስትና እምነት አስተምህሮ የልደት በዓል ኢየሱስ ክርስቶስ ዓለምን ለማዳን ሲል ከሰማየ ሰማያት ወርዶ በከብቶች በረት ከእናቱ ቅድስት ድንግል ማርያም የተወለደበት ታላቅ የትኅትና፣ የፍቅር እና የይቅርታ በዓል ነው፡፡
እኛም የጌታችንን ልደት ስናከብር እርስ በእርሳችኝ ይቅርታ በመጠያየቅ፤ እዝነትና ምኅረትን በማድረግ፣ የተቸገሩትን በመርዳት እና ለሀገራችን ሁለንተናዊ ሰላምና ብልፅግና በጎውን በማድረግ ይሁን!
መልካም ገና!!
አቶ ሮቤል ጌታቸው
የድሬዳዋ አስተዳደር ሥራና ክህሎት ቢሮ ኃላፊ
+1
ለክርስትና እምነት ተከታዮች በሙሉ እንኳን ለጌታችንና ለመድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የልደት በዓል በሰላም አደረሰን፤ አደረሳችሁ፤
*
በክርስትና እምነት አስተምህሮ የልደት በዓል ኢየሱስ ክርስቶስ ዓለምን ለማዳን ሲል ከሰማየ ሰማያት ወርዶ በከብቶች በረት ከእናቱ ቅድስት ድንግል ማርያም የተወለደበት ታላቅ የትኅትና፣ የፍቅር እና የይቅርታ በዓል ነው፡፡
እኛም የጌታችንን ልደት ስናከብር እርስ በእርሳችኝ ይቅርታ በመጠያየቅ፤ እዝነትና ምኅረትን በማድረግ፣ የተቸገሩትን በመርዳት እና ለሀገራችን ሁለንተናዊ ሰላምና ብልፅግና በጎውን በማድረግ ይሁን!
መልካም ገና!!
አቶ ሮቤል ጌታቸው
የድሬዳዋ አስተዳደር ሥራና ክህሎት ቢሮ ኃላፊ
Repost from Ethio-Italy Polytechnic College (Dire Dawa)
በገጠር ክላስተሮች የMobile Trainingን በስፋት በማዳረስ ወጣቶች በአካባቢያቸው ያለውን ሰፊ የስራ እድል ተጠቃሚ እንዲሆኑ በትኩረት እየተሰራ መሆኑ ተገለፀ::
በድሬደዋ አስተዳደር ከሚገኙ የገጠር ክላስተሮች እና የገጠር ስራ እድል ፈጠራ ተወካዮች እንዲሁም ከስልጠና ክፍል ተጠሪዎች ጋር የአጫጭር ስልጠና ማዕቀፍን በተመለከት የውይይት መድረክ በኮሌጁ ተካሂዷል።
በገጠር ክላስተሮች ያለው የተፈጥሮ ፀጋ በመገንዘብ በአካባቢው የሚገኙ ወጣቶችን ተጠቃሚ የሚያደርጉ ተግባራትን ማከናወን ያስፈልጋል ያሉት የስራና ክህሎት ቢሮ ም/ል ሀላፊ የሆኑት ወ/ሮ ፈጡም ሙስጠፋ ሲሆኑ አክለውም የMobile Training ትግበራን በስፋትና በጥራት ተደራሽ ለማድረግ በሚኖረው ሂደት ክላስተሮችና የገጠር ስራ እድል ፈጠራ አስተባባሪዎች የሚያስፈልጉ መሰረተ ልማቶችን በማመቻቸት የስልጠናዎችን ውጤታማነት ማረጋገጥ እንደሚገባ ገልፀዋል::
በኮሌጁ የMobile Training ሊሰጥባቸው በሚያስችሉ ዲፓርትመንቶች ላይ የተለዩ የሙያ መስኮች መኖራቸውን የገለፁት የኮሌጁ ም/ል ዲን እና የውጤት ተኮር ትምህርትና ስልጠና ሂደት ሀላፊ አቶ ኤሊያስ አህመድ ሲሆኑ አክለውም በቀጣይ ከገጠር ክላስተር አስተባባሪዎችና ከሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ጋር በመቀናጀት ነባራዊ ሁኔታ ላይ መነሻ ያደረገ የፍላጎት ዳሰሳ ጥናት በማካሄድ በተለያዩ ዘርፎች ስልጠናዎች እንደሚሰጡም አመላክተዋል::
በመድረኩ የኢትዮ-ጣሊያን ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ በአጫጭር ስልጠና ማዕቀፍ በMobile Training በገጠር ክላስተሮች ላይ ያከናወናቸው ተግባራትና ያለውን መልካም ተሞክሮ በኢ/ር ህይወት እሸቱ አማካኝነት ለተሳታፊዎች ገለፃ የተደረ ሲሆን በስልጠናው የተመዘገቡ ውጤቶችን ጨምሮ ያጋጠሙ ተግዳሮቶችም ቀርበው በቀጣይ ስልጠናዎች በሚሰጡበት አግባብ ላይም ውይይት ተካሂዷል::
የኢትዮ-ጣሊያን ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ
ታህሳስ 28/2018 ዓ.ም
ድሬዳዋ
የድሬዳዋ አስተዳደር ሥራና ክህሎት ቢሮ የቴክኒክና ሙያ ኤጀንሲ የኢንዱስትሪ ኤክስቴንሽንና ቴክኖሎጂ ሽግግር ዳይሬክቶሬት በ33 ነባርና አዲስ ኢንተርፕራይዞች ላይ ከሁለቱ የመንግስት ኮሌጆች በተወጣጡ አሰልጣኝ መምህራን የካይዘን ትግበራ ጀመረ፡፡
በዚህም ለኢንተርፕራይዞች ሠራተኞች የጥራትና ምርታማነት ማሻሻያ (ካይዘን) ትግበራ ስልጠና/ድጋፍ በመስጠት ማብቃት እና የመስሪያ/ ማምረቻ ወርክሾፖችን በካይዘን እንዲደራጁ በማድረግ ኮሌጆች ከኢንተርፕራይዞች ጋር የሚኖራቸዉን የስራ ትስስር ለማጠናከርና የኢንተርፕራይዞችን ሠራተኞች መሰረታዊ የካይዘን እዉቀትና ክህሎትን በኢንተርፕራይዙ ማምረቻ/የስራ ቦታ በመተግበር ደረጃዉን የጠበቀ ማምረቻ ቦታ ለመፍጠር እና በአጠቃላይ የከይዘን ፍልስፍናን በመተግበር የአሰልጣኝ መምህራኑን አቅም በመገንባት የኢንተርፕራይዞችን አላስፈላጊ ብክነቶችን በማስወገድ ምርትና ምርታማነትን ለማሻሻል አቅም የሚፈጥር ትግበራ ይሆናል፡፡
ዳይሬክቶሬቱ ከኮሌጆች ጋር በመሆን የኢንዱስትሪ ኤክስቴንሽን አገልግሎት ድጋፍ በመስጠት በአስተዳደሩ ጉልህ ስራዎችን እየሰራ ሲሆን በተለይም በ4ቱ የድጋፍ ማእቀፎች የጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞችን የምርትና ምራታማነት በማሻሻልና ብቁ የሆነ የሰዉ ሐይል በማፍራትና የሥራ እድል እንዲፈጥሩ ለማድረግ ድጋፍ እየሰጠ ይገኛል፤ በዚህም በአስተዳደሩ ዘጠኙም ወረዳዎች ለሚገኙ የኢንዱስትሪ ኤክስቴንሽን አገልግሎት ድጋፍ ለሚደረግላቸው ኢንተርፕራይዞች የድርጊት መርሀ ግብር በማዘጋጀት ወደ ትግበራ መገባቱን የቢሮው ም/ኃላፊና የኤጀንሲው ኃላፊ ወ/ሮ ፈጡም ሙስጠፋ ገልጸዋል፡፡
የሥራና ክህሎት ቢሮ ህዝብ ግንኙነት
ታህሳስ 28/2018 ዓ.ም
ድሬዳዋ
Repost from Ministry of Labor and Skills - Ethiopia
🇪🇹የኢትዮጵያ የሥራ ገበያ መረጃ ስርዓት፣ ለላቀ ተጠቃሚነት!
👉 የኢትዮጵያ የሥራ ገበያ መረጃ ስርዓት (ELMIS) በኢትዮጵያውያን በልጽጎ ለኢትዮጵያውያን የቀረበ ግዙፍ እና ሁሉን አቀፍ የዲጂታል መረጃ ስርዓት ነው፣
👉የሀገራችንን የሰው ኃይል መረጃ አያያዝና አስተዳደርን በእጅጉ የሚያዘምን እና ሥራን ከሠራተኛ ጋር በቀለለ፣ ፈጣን እና ፍትሃዊ በሆነ መንገድ ማገናኘት ያስችላል፣
🔑ቁልፍ ፋይዳዎች
✅የሥራ ስምሪት ሥራን ማዘመን፦ የሀገር ውስጥና የውጭ ሀገር ሥራ ስምሪትን እንዲሁም የርቀት ሥራዎችን በአንድ ላይ አጣምሮ አገልግሎት ጊዜውን በዋጀ መልኩ መስጠትና ማግኘት ያስችላል፣
✅ፍትሃዊ ተደራሽነት፦ ስርዓቱ በሰው ሰራሽ አስተውሎት የታገዘ እና ከሰው ንክኪ ነፃ እንዲሆን ተደርጎ የበለፀገ በመሆኑ፣ ለሁሉም ኢትዮጵያዊ በእኩል አገልግሎት መስጠት ያስችላል፣
✅መረጃ ላይ የተመሰረተ ውሳኔ፦ የትምህርትና ስልጠና ዘርፍ ከሀገራዊ የልማት ፍላጎት ጋር እንዲጣጣም ወሳኝ የመረጃ ምንጭ ሆኖ ያገለግላል፣
🚪23+ የዕድል በሮች በአንድ ጣሪያ ስር
የኢትዮጵያ የሥራ ገበያ መረጃ ስርዓት አንድ ስርዓት ቢሆንም፣ በውስጡ ከ23 በላይ ንዑስ አገልግሎቶች አሉት። አብዛኞቹ አገልግሎቶች ለዜጎች በነፃ የቀረቡ ናቸው።
🧭የኢትዮጵያ የሥራ ገበያ ዋና ዋና ንዑስ አገልግሎቶች በጥቂቱ
✅የሥራ ስምሪት፦ የሀገር ውስጥ፣ የውጭ ሀገር እና የርቀት (Remote) ሥራ ዕድሎችን ማግኘት አስችላል፣
✅የሰው ኃይል አስተዳደር፦ የተቋማት የሰው ሃይል አስተዳደርና አቅም ግንባታ ሥራዎችን ለማሣለጥ ሁነኛ መሳሪያ ሆኖ ያገለግላል፣
✅የሙያ ብቃት ማረጋገጫ፦ የሙያ ብቃት ምዘናና እውቅና እና የሳይኮሜትሪክ ምዘና መስጠት ያስችላል፣
✅የብድር አገልግሎት፦ ከፋይናንስ ተቋማት ጋር በቅርበት በመስራትና በሳይኮሜትሪ ምዘና በመታገዝ ያለ ማስያዣ የብድር አቅርቦት ለማመቻቸት የቅድመ ዝግጅት ሥራዎች ተጠናቀዋል፣
✅የውጭ ሀገር ባለሙያዎች የሥራ ፈቃድ እና እድሳት፦ በሀገር ውስጥ ባለሙያዎች ለማይሸፈኑ የሙያ መስኮች የውጭ ሀገር ባለሙያዎች ፍቃድና እድሳት ጋር የተያያዙ አገልግሎቶችን በተቀላጠፈ አግባብ መስጠት ያስችላል፣
✅የዲጂታል ኢንተርፕራይዝ ምስረታና የዲጂታል ግብይት፦ ስርዓቱ በበይነ መረብ የማደራጀት ሥራ ከመስራቱ ባሻጋር ኢንተርፕራይዞች ምርትና አገልግሎታቸውን ማስተዋወቅና መሸጥ የሚያስችላቸውን ዕድል ይዟል፣
✅ ክፍት የሥራ ቦታ ማስታወቂያ፦ ስርዓቱ ከተለያዩ የማስታወቂያ ድርጅቶች ጋር የተሳሰረ በመሆኑ ባልዎት የትምህርት ማስረጃና የሥራ ልምድ ማስታወቂያዎች በቀላሉ እንዲደርስዎ ያስችላል፣
📊በስርዓቱ የተከናወኑ ዋና ዋና ሥራዎች
ስርዓቱ ተጠናቆ ወደ ሥራ ከገባበት እለት ጀምሮ ባለፉት አራት ዓመታት ከ3.5 ሚሊዮን በላይ ዜጎች በስርዓቱ ተመዝግበዋል። ከዚህ ውስጥ፡-
✍️ከአንድ ሚሊዮን በላይ ዜጎች የውጭ ሀገር የሥራ ስምሪት ተጠቃሚ መሆን ችለዋል፣
✍️በርካታ ዜጎችም በሀገር ውስጥና በርቀት የሥራ ዕድሎች ተጠቃሚ ሆነዋል፣
🏢የተቋማት ተሳትፎ
👉 የኢትዮጵያ ስታስቲክስ አገልግሎት: 45 ሺህ የግብርና ናሙና ቆጠራ ባለሙያዎችን ስርዓቱን ተጠቅሞ በመመልመልና በመቅጠር ፈር ቀዳጅ ነው፣
👉 የሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን፣ ሚድሮክ ኢትዮጵያ እና ኦቪድን ጨምሮ በርካታ ተቋማት ብቁና ተወዳዳሪ ባለሙያዎችን መልምሎ ለተቋማቸው ለመቅጠር ስርዓቱን እየተጠቀሙበት ይገኛል፣
🚪 የዕድሉን በር ቁልፍ በእጅዎ ያስገቡ!
✍️ከሥራ ዕድል አኳያ ስርዓቱ ለሁሉም ክልሎች እኩል ዕድል የሚሰጥ ነው፡፡ ለየትኛውም ክልልና አካባቢ የተሰጠ ኮታ የለም፡፡
✍️በየትኛውም አካባቢም ሆነ የትምህርት ደረጃ ሁሉም እኩል እድል አለው፡፡ ይህም ማለት በስርዓቱ ላይ መመዝገብ ማለት የሀገር ውስጥ፣ የውጭ ሀገር ሥራ ስምሪት፣ የርቀት ሥራን ጨምሮ ሌሎች በርካታ ዕድሎችን በቀላሉ ለማግኘት የሚያስችል ቁልፍ በእጁ ማስገባት ማለት ነው።
📝እንዴት መመዝገብ ይቻላል?
1️⃣ በራስ መመዝገብ፦ lmis.gov.et የሚለውን ማስፈንጠሪያ በመጠቀም የእጅ ስልክዎን ጨምሮ መመዝገብ ይችላሉ፣
2️⃣ በሌሎች እርዳታ መመዝገብ፦ በአቅራቢያዎ ወደሚገኝ የአንድ ማዕከል አገልግሎት መስጫ ጣቢያዎች በመሄድ በማዕከሉ ባለሙያዎች እገዛ መመዝገብ ይቻላሉ፣
📌የመመዝገቢያ መስፈርት:
👉 ዕድሜ፦ ከ15-65 ዓመት
👉 የትምህርት ደረጃ፡ በየትኛውም የትምህርት ደረጃ ላይ ያለ ሰው መመዝገብ ይችላል
⚠️ማስታወሻ
✅ ስርዓቱ ይዞ የሚመጣውን ዕድሎች ሁሉ ለመጠቀም ግላዊ መረጃ፣ የትምህርት እና የሥራ ልምዶችን በአግባቡ ማያያዝዎን ልብ ይበሉ!
ታህሳስ 26/2018 ዓ.ም ፤ የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር
ለወቅታዊ ትኩስ የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር
Official Website: mols.gov.et
Facebook: https://web.facebook.com/MolsFDRE
Telegram: https://t.me/FDRE_MoLSofficial
TikTok: tiktok.com/@mols_official
Twitter / X: twitter.com/Jobs_ሚኒስቴር
WhatsApp: whatsapp.com/channel/0029VakCgcYIyPtTbPZtDW1y
መንግስት በጎዳና ሕይወት ኑሮዋችንን ከመምራት ታድጎናል ሲሉ በዐ2 እና 03 ወረዳ በክረምት በጎ ፈቃድ መኖሪያ ቤት ተሰርቶ የተሰጣቸው አረጋውያን ተናገሩ።
የድሬደዋ አስተዳደር የስራና ክህሎት ተጠሪ ተቋማት በክረምት በጎ ፈቃድ በ02 እና በ 03 ወረዳ ያስገነባቸው ሦስት የአቅመ አካማ ቤቶችን መርቆ አስረክቧል ።
ቤቶቹን መርቀው ያስረከቡት የስራና ክህሎት ቢሮ ኃላፊ አቶ ሮቤል ጌታቸው ፤ የብልፅግና ፓርቲ ድሬዳዋ ቅርጫፍ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ኢብራሂም ዩሱፍ እና የቢሮው ተጠሪ ተቋማት እንዲሁም የወረዳ አመራሮች ናቸው።
በወቅቱ የአስተዳደሩ የስራና ክህሎት ቢሮ ኃላፊ አቶ ሮቤል ጌታቸው እንደተናገሩት ተቋማቸው በ2017 ዓ.ም የክረምት በጎ ፈቃድ አገልግሎት ዛሬ መርቀው ያስረከቧቸውን ሦስት ቤቶች ጨምሮ ቢሮው ከተጠሪ ተቋማቱ ጋር ጠቅላላ ሰባት (7) ቤቶችን ገንብቶ ለአቅመ ደካማ እማወራዎች እና አባወራዎች ማከረከባቸውን ገልፀዋል።
ኃላፊው አያይዘውም ዛሬ በ02 እና 03 ወረዳ የተረከቡት ቤቶችም ጠቅላላ ከስምንት መቶ (800)ሺ ብር በላይ ወጪ የተደረገባቸው መሆኑን ገልፀዋል ።
ቤቶቹን የተረከቡት የ 03 ወረዳ ነዋሪ እማወራዎች ልጆቻቸውን የአገር ዳር ድንበር ለማስከበር ግዳጅ ልከው የተሰውባቸው እና በመኖሪያ ቤት እጦት በሰው በረንዳ ተጠግተው የሚኖሩ እና የጎዳና ሕይወት መምራት የጀመሩ መሆኑን አስታውሰው ዛሬ ግን መንግስት ይሄን ቤት ገንብቶ በመስጠቱ ኑራችንን በጎዳናና በሰው በረንዳ ከመምራት ታድጎናል ሲሉ ደስታቸውን ገልፀዋል።
ቤቶቹን ያሰሩት የስራ ክህሎት ቢሮ ተጠሪ ተቋማት የሆኑት የድሬዳዋ ፖሊቲክኒክ ኮሌጅ እና የኢትዮ ጣሊያን ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ የቤት ዕቃ እና የምግብ ግብዓት ለአረጋዊያኑ አጋርተዋል።
©️ DireTvአማርኛ |ታህሳስ 25 ፥ 2018 ዓ.ም | ድሬዳዋ
