1 318
Подписчики
+324 часа
+207 дней
+15030 дней
Архив постов
🛍 የአዲስ ዓመት በዓል ባዛር በድሬዳዋ ተከፈተ
የመጪውን አዲስ ዓመት በዓል አስመልክቶ በድሬዳዋ አስተዳደር ኢንዱስትሪና ኢንቨስትመንት ቢሮ የተዘጋጀው የበዓል ባዛር በይፋ ተከፍቷል።
በባዛሩ የድሬዳዋ አስተዳደር ሥራና ክህሎት ቢሮ የሚደግፋቸው ኢንተርፕራይዞች ተሳትፈው ያመረቷቸውን ምርቶች ለሸማቾች በማቅረብ ላይ ይገኛሉ።
በዚህ የበዓል የገበያ መድረክ ላይ የፋብሪካ ምርቶችን ጨምሮ ለአዲስ ዓመት በዓል የሚያስፈልጉ የተለያዩ ምርቶች በስፋት ለሽያጭ ቀርበዋል።
ባዛሩ አምራቾችን ከሸማቾች በቀጥታ በማገናኘት፣ ለኢንተርፕራይዞች የገበያ ዕድል በመፍጠር፣ የአካባቢ ምርቶችን በማስተዋወቅና የአምራቾችን የገበያ ተደራሽነት በማሳደግ ረገድ ጠቃሚ መድረክ መሆኑ ተገልጿል።
የአካባቢ ምርቶችን መግዛት የአምራቾችን ጥረት ከመደገፍ ባለፈ፣ የኢንተርፕራይዞችን የማምረት አቅም ለማጠናከር፣ የሥራ ዕድል ፈጠራን ለማበረታታትና የአካባቢውን ኢኮኖሚ ለማሳደግ የራሱን አስተዋፅዖ ያደርጋል።
📍 የባዛሩ ቦታ፦ የቀይ መስቀል ማኅበር ፊት ለፊት
📅 የሚቆየው፦ እስከ ጳጉሜ 4 ቀን 2018 ዓ.ም.
✨ በዓሉን በአካባቢ ምርት!
አምራቾቻችንን በመደገፍ ሥራን፣ ምርትንና ኢኮኖሚያዊ እድገትን እናበረታታ!
+2
ጳጉሜ 1 ... የእምርታ ቀን
Qaammee 1....Guyyaa omishtummaa
Baagumee 1 ... Maalinta wax-soo-saarka
Repost from Ethio-Italy Polytechnic College (Dire Dawa)
"በክህሎት የዳበረ ዜጋ ለሀገር እድገትና ኢኮኖሚያዊ ለውጥ"
በኮሌጁ ላለፉት ወራት ሲሰጥ የቆየው የክረምት የክህሎት ስልጠና ተጠናቀቀ::
#EIPC ነሃሴ 28.2018 ዓ.ም ድሬዳዋ
የኢትዮ-ጣሊያን ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ በክረምቱ "አንድ ሙያ ለአንድ ዜጋ" በሚል መሪ ቃል ለአስተድደሩ ወጣቶች ሲሰጥ የቆየውን የክህሎት ስልጠና በማጠናቀቅ የማጠቃለያና መርሃ-ግብር አካሂዷል::
በመድረኩ የክረምት የሙያ ስልጠናቸውን ተከታትለው ላጠናቀቁ ወጣቶች የእንኳን ደስ አላችሁ መልዕክት ያስተላለፉት የኮሌጁ የውጤት ተኮር ትምህርትና ስልጠና ሀላፊና ም/ል ዲን የሆኑት አቶ ኤሊያስ አህመድ ሲሆኑ ወጣቶች በክረምት የክህሎት ስልጠና ሂደት ውስጥ ስለ ቴክኒክና ሙያ ዘርፍ ያለውን ነባራዊ ሁኔታ የተረዱና በቂ ግንዛቤ ያገኙ በመሆኑ በቀጣይ ዘርፉን ምርጫቸው እንዲያደርጉ መደላድል የፈጠረ ስልጠና እንደነበርም ገልፀዋል::
የክረምት "የአንድ ሙያ ለአንድ ዜጋ" ስልጠና ወጣቶች ባላቸው ዝንባሌና በመረጡት ሙያ ዘርፍ ሰልጥነው የሙያ ባለቤት ከመሆን በተጨማሪ ለቀጣይ መንገዳቸው መሰረት የጣሉበት ውጤታማ ስልጠና እንደነበር የገለፁት ደግሞ በኮሌጁ የቴክኖሎጂ ሽግግርና ኢንዱስትሪ ኤክስቴሽን አገልግሎት ሀላፊና ም/ል ዲን የሆኑት አቶ ተሾመ ሸዋዬ ሲሆኑ ለዚህ ስልጠና መሳካት የዲፓርትመንት ተጠሪዎች፣ አሰልጣኝ መምህራና አስተባባሪዎች ያለባቸውን ጫና ተቋቁመው የክረምት ስልጠናው በተሳካ ሁኔታ እንዲጠናቀቅ ያስቻሉ በመሆኑ ምስጋናም አቅረበዋል::
በእለቱ በተካሄደው ማጠቃለያ መድረክ በኮሌጁ ሲሰጥ የቆየውን የክረምት ክህሎት ስልጠና ተከታትለው በብቃት ላጠናቀቁ ወጣቶች በኮሌጁ ሀላፊዎች የእውቅና ሰርተፊኬት ተበርክቶላቸዋል::
በ2018ዓ.ም የክረምት ሙያ ስልጠና መርሃ ግብር በ7 ዲፓርትመንቶችና 11 የሙያ አይነቶች....
1, በኤሌትሪክ መስመር ዝርጋታ
2, በኤሌክትሪካል/ኤሌክትሮኒክስ
3, በምግብ ዝግጅት
4, በመሰረታዊ ኮምፕዩተር
5, በአውቶ ኤሌክትሪክ
6, በአውቶ መካኒክ
7, በጂፕሰም
8, በውድዎርክ
9, በኢንተርፕሩነርሺፕ
10, በግራፊክስ ዲዛይን
11, በቪዲዮ ኤዲቲንግ...... ለ155 ወንድ እና ለ139 ሴት በድምሩ ለ294 ሰልጣኝ ወጣቶችን በኮሌጁ በማሰልጠን የክህሎት ባለቤት ማድረግም ተችሏል::
ተጨማሪ መረጃዎችን በሚከተሉት አማራጮች ያግኙ፡-
በፌስቡክ -https://www.facebook.com/share/19wDiZAD7x/?mibextid=wwXIfr
በቴሌግራም -https://t.me/EIPC2001
በቲክቶክ -https://www.tiktok.com/@ethioitaly2001?_t=ZM-90MxIrBN8qe&_r=1
በዌብሳይት - https://ethioitalypolytechniccollege.com/
የድሬዳዋ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ዘመኑን የሚመጥን እና በሙያ ክህሎቱ ብቁ የሆነ ዜጋን ከማፍራት ባሻገር ወጣቶችን ከስራ ፈላጊነት ወደ ስራ ፈጣሪነት ለማሸጋገር በመስራት ላይ እንደሚገኝ አስታወቀ።
©️ DireTv
ድሬዳዋ በሥራና ክህሎት ዘርፍ ላስመዘገበችው ውጤት የዋንጫ ተሸላሚ ሆነች፤
የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር ከሰኞ ነሐሴ 25 ቀን 2018 ዓ.ም. ጀምሮ ለአራት ተከታታይ ቀናት ሲያካሂድ የቆየው የአምስት ዓመታት የልማት ጉዞ የምክክር መድረክ ለዘርፉ ዕድገት አስተዋጽዖ ላበረከቱ ተጠሪ ተቋማት፣ የክልል አስፈጻሚ አካላት፣ ስኪል ኢትዮጵያና ኢንተርፕራይዞች ዕውቅና በመስጠት ተጠናቋል።
በመድረኩ የአምስት ዓመቱ የልማት ጉዞ ዋና ዋና ውጤቶች፣ ተሞክሮዎች፣ ተግዳሮቶችና ቀጣይ የሥራ አቅጣጫዎች በስፋት የተገመገሙ ሲሆን፣ ለዘርፉ ዕድገት የላቀ አስተዋጽዖ ያበረከቱ ተቋማትና ባለድርሻ አካላትም ዕውቅና ተሰጥቷቸዋል።
በዚህ የዕውቅናና የሽልማት መርሐ ግብር የድሬዳዋ አስተዳደር ሥራና ክህሎት ቢሮ በዘርፉ ባስመዘገበው ውጤት የዋንጫ ተሸላሚ ሆኗል።
የተገኘው ዋንጫ በአምስት ዓመቱ የልማት ጉዞ የተመዘገቡ ውጤቶችን ከማመስገን ባለፈ፣ በድሬዳዋ የሥራና ክህሎት ዘርፍ ለተከናወኑ የተቋማዊ ለውጥ፣ የክህሎት ልማት፣ የሥራ ዕድል ፈጠራና የሥራ ዓለም ትስስር ሥራዎች የተሰጠ ዕውቅና መሆኑ ተገልጿል።
የድሬዳዋ አስተዳደር ሥራና ክህሎት ቢሮ ኃላፊ አቶ ሮቤል ጌታቸው የተገኘውን ውጤት እንደ ተቋማዊ ስኬት በመቀበል፣ የተጀመሩ የለውጥ ሥራዎችን በማጠናከርና የተሻለ ውጤት በማስመዝገብ ለቀጣይ የልማት ዘመን በበለጠ ቁርጠኝነት ለመሥራት የሚያነሳሳ መሆኑን ተናግረዋል።
የሥራና ክህሎት ቢሮ ሕዝብ ግንኙነት
ነሐሴ 28 ቀን 2018 ዓ.ም | አዲስ አበባ
Repost from Dire Dawa Polytechnic College
+5
የድሬዳዋ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ በክረምቱ በጎ ፍቃድ አገልግሎት መርሃ ግብር የተለያዩ እቅዶችን በማዘጋጀትየተለያዩ የበጎ አድራጎት ስራዎችን እያከናወነ ይገኛል፡፡
በዘንድሮ የክረምት በጎ ፍቃድ መርሃ ግብር ላይ የደም ልገሳ፣የማእድ ማጋራት፣የችግኝ ተከላ እንዲሁም የአቅመ ደካማ ቤቶችን የመስራት ተግባር እያከናወነ ይገኛል፡፡
በዛሬው እለትም የኮሌጁ አመራሮች የትምህርት ክፍል ተጠሪዎች አሰልጣኝ መምህራኖችና አስተዳደር ሰራተኞች እንዲሁም ሰልጣኝ ተማሪዎች በጋራ በመሆን የደም ልገሳ መርሃ ግብር ያከናወኑ ሲሆን በቀጣይም በርካታ ዩኒት ደም ከሰልጣኞች እንዲሁም ከኮሌጁ ሰራተኞች ለማሰብ መታቀዱን ለማወቅ ተችሏል፡፡
የድሬዳዋ አስተዳደር ሥራና ክህሎት ቢሮ የ2018 ዓ.ም የክረምት በጎ ፍቃድ አገልግሎት መርሃ ግብርን በይፋ ከዚህ ቀደም ማስጀመሩ የሚታወስ ነው፡፡የድሬዳዋ አስተዳደር እንዲሁም የሥራና ክህሎት ቢሮ በሚያዘጋጁት የተለያዩ የክረምት በጎ አድራጎት መርሃ ግብሮች ላይ ኮሌጁ ከማህበረሰቡ የተጣለበት ሃላፊነት ዜጋ ተኮር ስራዎችን እየሰራ እየተወጣ ይገኛል፡፡
የኮሌጁ ኮምኒኬሽን
ነሀሴ 28/2018 ዓ.ም ድሬዳዋ
የቴክኒክና ሙያ ሥልጠናን ለገጠሩ ማህበረሰብ በፍትሃዊና ተደራሽ መልኩ ለማድረስ በ2019 የሥልጠና ዘመን ተንቀሳቃሽ የቴክኒክና ሙያ ሥልጠና ለመተግበር መዘጋጀቱ ተገለጸ።
ተንቀሳቃሽ ሥልጠናው ‹‹ቴክኒክና ሙያ ሥልጠና ለገጠሩ ማህበረሰብ ፍትሃዊ ተጠቃሚነት›› በሚል መሪ ቃል የሚተገበር ሲሆን፣ ዓላማውም በገጠር የሚኖሩ ማህበረሰቦች ከቴክኒክና ሙያ ሥልጠና ፍትሃዊ ተጠቃሚ እንዲሆኑ በማስቻል የምርትና ምርታማነት አቅማቸውን ማሳደግ ነው።
የድሬዳዋ አስተዳደር ሥራና ክህሎት ቢሮ የቴክኒክና ሙያ ሥልጠና ኤጀንሲ ከግብርና፣ ውሃ፣ ማዕድንና ኢነርጂ ቢሮ የግብርናና ተፈጥሮ ሀብት ልማት ጽ/ቤት ጋር በመተባበር ሥልጠናውን በድሬዳዋ በሚገኙ ሁለት ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጆች አማካኝነት ለማስፈጸም አቅጣጫ ተይዟል።
በዚህም በግብርና፣ ከግብርና ውጪ በሆኑ ዘርፎች እና በገጠር ቴክኖሎጂ ልማት ላይ ያተኮሩ ሥልጠናዎችን ወደ ገጠር ማህበረሰቡ በማድረስ፣ በሥራ ላይ ያሉና ከዋና ሥራቸው ውጪ በሆኑ የሥልጠና ዘርፎች ለመሳተፍ ፍላጎት ያላቸውን 4,000 አርሶ አርብቶ አደሮች በማብቃት ምርትና ምርታማነትን ማሻሻል ታስቧል።
ይህንንም አስመልክቶ በተዘጋጀው የውይይት መድረክ የገጠሩ ማህበረሰብ ችግሮችን ደረጃ በደረጃ ለመፍታት ሥልጠናን ከተግባራዊ ቴክኖሎጂ ጋር ማጣመር እና የሥልጠና ይዘትን ከአካባቢው ትክክለኛ ፍላጎትና የገበያ አቅጣጫ ጋር ማስማማት ወሳኝ መሆኑ ተገልጿል።
በዚህም ሥልጠና በኮሌጅ ግቢ ብቻ የሚሰጥ አለመሆኑን የሚያረጋግጥ ሲሆን አሰልጣኞችና የሥልጠና ግብዓቶች ወደ ገጠር የሥልጠና ቦታዎች በመንቀሳቀስ ማህበረሰቡ በሚገኝበት አካባቢ ሥልጠና እንዲያገኝ የሚያስችል አተገባበር ይከተላል።
የአተገባበሩ ዋና ዋና እርምጃዎች
* የገበያ ተኮር አጫጭር ሥልጠና ፍላጎት ዳሰሳ ማካሄድ፤
* ተገቢ የሥልጠና ቦታዎችን ማመቻቸትና ለሥልጠና የሚስማማ ጥበቃ ማድረግ፤
* አሰልጣኞችንና የሥልጠና ግብዓቶችን ከኮሌጆች ወደ ገጠር ማንቀሳቀስ፤
* ለማህበረሰቡ በቂ ግንዛቤ መፍጠር፤
* ሰልጣኞችን መመልመልና በፍላጎታቸው መሠረት ወደ ሥልጠና ማቅረብ፤
* አንገብጋቢ የልማት ችግሮችን በመለየት በሥልጠናና በቴክኖሎጂ አማራጮች መፍትሔ ማመቻቸት፤
* ተግባራዊ ሥልጠና መስጠት፤
* የሥልጠና ተጠቃሚዎችን በድጋፍና በክትትል ማጠናከር፤
* የሙያ ብቃት ምዘና ማከናወን።
በመሆኑም ተንቀሳቃሽ የቴክኒክና ሙያ ሥልጠናው የሥልጠና አገልግሎትን ከከተማ ወደ ገጠር በማስፋፋት የተደራሽነት ክፍተትን ለማጥበብ፣ የገጠር ማህበረሰብን በተግባራዊ ክህሎት ለማብቃት እና ሥልጠናን ከአካባቢያዊ የልማት ችግሮች ጋር በማስተሳሰር ዘላቂ የኢኮኖሚና የኑሮ ለውጥ ለማምጣት የሚያግዝ ተግባራዊ የክህሎት ልማት አቅጣጫ መሆኑ በቢሮው የሰልጣኝ ልማትና የተቋማት አቅም ግንባታ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ጀማል አደን ተጠቁሟል።
“ሥልጠና ወደ ማህበረሰቡ፤ ክህሎት ወደ ምርት፤ ሙያ ወደ ልማት!”
የሥራና ክህሎት ቢሮ ህዝብ ግንኙነት
ነሐሴ 27 ቀን 2018 ዓ.ም | ድሬዳዋ
የድሬዳዋ አስተዳደር ሥራና ክህሎት ቢሮ የ‹‹ብቃት›› የወጣቶች የሥራ ላይ ልምምድ 4ኛ ዙር አተገባበርን በተሳካና በተቀናጀ መልኩ ለማስፈጸም ያለመ የግንዛቤ ማስጨበጫ መድረክ አካሄደ።
መድረኩ የተዘጋጀው በ4ኛ ዙር የወጣቶች የሥራ ላይ ልምምድ ፕሮግራም አፈጻጸም ላይ የሚሳተፉ የተለያዩ ኮሚቴ አባላትና ባለድርሻ አካላት ስለፕሮግራሙ ዓላማ፣ አፈጻጸምና የተሳትፎ ሚና የጋራ ግንዛቤ እንዲይዙ ለማስቻል ነው።
በመድረኩ የ4ኛ ዙር የሥራ ላይ ልምምድ አተገባበር ሂደት፣ የተሳታፊዎችና የባለድርሻ አካላት ሚናና ኃላፊነት፣ የአፈጻጸም ቅንጅትና ክትትል ጉዳዮች ላይ ውይይትና ግንዛቤ ማስጨበጫ ተካሂዷል።
የወጣቶችን የሥራ ዓለም ተሞክሮ ለማሳደግ፣ የተግባር ክህሎታቸውን ለማጎልበትና ከሥራ ዓለም ጋር ያላቸውን ትስስር ለማጠናከር የሥራ ላይ ልምምድ ፕሮግራም የሚኖረው ሚና ከፍተኛ መሆኑ በመድረኩ ተጠቁሟል።
በተለይም የፕሮግራሙ ውጤታማነት በአንድ ተቋም ብቻ የሚረጋገጥ ሳይሆን፣ የተለያዩ ኮሚቴዎችና ባለድርሻ አካላት በጋራ አቅጣጫ፣ በግልጽ ኃላፊነትና በተቀናጀ አፈጻጸም መሥራታቸው ወሳኝ መሆኑን የቢሮው ም/ኃላፊ እና የቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና ኤጀንሲ ኃላፊ ወ/ሮ ፈጡም ሙስጠፋ ገልጸዋል።
በመድረኩ ተሳታፊዎች ጥያቄዎችን አንስተው ምላሽ የተሰጠባቸው ሲሆን የተካሄደው የጋራ ግንዛቤ ማስጨበጫና ውይይት የ4ኛ ዙር የ‹‹ብቃት›› የወጣቶች የሥራ ላይ ልምምድ አፈጻጸምን ይበልጥ ተቀናጅቶ፣ ተጠያቂነት ባለውና ውጤት ተኮር በሆነ መልኩ ለማስፈጸም መሠረት ያስቀምጣል።
የወጣቶች የሥራ ላይ ልምምድ፤ ከሥራ ፈላጊነት ወደ ሥራ ዓለም የሚያሻግር የብቃት ድልድይ!
የሥራና ክህሎት ቢሮ ህዝብ ግንኙነት
ነሐሴ 25 ቀን 2018 ዓ.ም | ድሬዳዋ
“አዲሱን የዘርፉን ዕሳቤ ተግባራዊ በማድረግ ለተቋማዊ ውጤታማነት መሠረት መጣል ችለናል።”
— አቶ ሮቤል ጌታቸው፣ የድሬዳዋ አስተዳደር ሥራና ክህሎት ቢሮ ኃላፊ
አቶ ሮቤል ባለፉት አምስት አመታት በዘርፉ አስተዳደሩ ላይ የተሰሩ ስራዎችን በሥራና ክህሎት ሚንስቴር በተዘጋጀው የአምስት አመት የልማት ጉዞ ቅኝት የፓናል ውይይት ላይ ፓናሊስት ሆነው ቀርበው በሰፊው አብራርተዋል።
በዚህም የሥራና ክህሎት ዘርፍ የፖሊሲና የተቋማዊ ዕሳቤ ለውጦችን ከሰነድ ወደ ተግባር፣ ከአሠራር ወደ ውጤት በመተርጎም የተሻለ ተቋማዊ አቅም ለመገንባት እየተሠራ እንደሆነ፤
የድሬዳዋ ሥራና ክህሎት ቢሮ ይህንን የለውጥ አቅጣጫ በተግባር በመተርጎም፣ የአደረጃጀት ወጥነትን በማረጋገጥ፣ ዘመናዊና ቀልጣፋ አሠራሮችን በመዘርጋት፣ የሕግ ማዕቀፎችን በማሻሻል፣ የቴክኖሎጂ አጠቃቀምን በማስፋፋትና የሰው ሀብት አቅምን በማጎልበት የተቋማዊ ለውጥ ሥራዎችን እያጠናከረ እንደሚገኝ፤
እነዚህ ለውጦች የሥራ ሂደቶችን በተቀናጀ መልኩ ለመምራት፣ የተቋማትን ተጠያቂነትና ቅንጅት ለማሳደግ፣ የሰው ኃይልን አቅም ለማሳደግና ለተገልጋዮች የተሻለ አገልግሎት ለማቅረብ ጠንካራ መሠረት እንደሚፈጥሩ፤
በአምስት ዓመቱ የዘርፉ የልማት ጉዞ የተገኙ ልምዶችን በመገምገምና ቀጣይ አቅጣጫዎችን በመለየት፣ የተጀመሩ ለውጦችን የበለጠ ማጠናከር የዘርፉን ተቋማዊ አቅምና ውጤታማነት ወደ ቀጣይ ደረጃ ለማሸጋገር ወሳኝ ነው ብለዋል።
“ለውጥ የሚለካው በዕሳቤ ብቻ ሳይሆን፣ በተግባር በሚመዘገብ ውጤት ነው።”
የሥራና ክህሎት ቢሮ ህዝብ ግንኙነት
ነሐሴ 27/2018 ዓ.ም አዲስ አበባ
+4
የድሬዳዋ አስተዳደር ሥራና ክህሎት ቢሮ የአሰሪና ሠራተኛ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ መሐመድ ኢብራሂም በዳይሬክቶሬቱ ሥር ከሚገኙ የቡድን መሪዎች ጋር የ2019 በጀት ዓመት የሥራ ዕቅድ ስምምነት ተፈራረሙ።
የዕቅድ ስምምነቱ የዳይሬክቶሬቱን የ2019 ዓ.ም. የሥራ አቅጣጫ በግልጽ በማስቀመጥ፣ ተጠያቂነትን፣ ተግባራዊ አፈጻጸምንና ውጤታማነትን ለማጠናከር ያለመ ነው።
የሥራና ክህሎት ቢሮ ህዝብ ግንኙነት
ነሐሴ 25 ቀን 2018 ዓ.ም. | ድሬዳዋ
