cookie

Мы используем файлы cookie для улучшения сервиса. Нажав кнопку «Принять все», вы соглашаетесь с использованием cookies.

avatar

#ሥነ_ፀሑፎች 🤔

አኔ ፡ማለት፡እኛ፡እኛ፡ማለት፡አንድ:ፅኑ:ገፅ፡ነን ።

Больше
Страна не указанаЯзык не указанКатегория не указана
Рекламные посты
291
Подписчики
Нет данных24 часа
Нет данных7 дней
Нет данных30 дней

Загрузка данных...

Прирост подписчиков

Загрузка данных...

​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​━━━━━━━━━━━━━━━━ እኔ አንተን ስወድህ እኔ አንተን ስወድህ ልክ እንደ ገጣሚ ጨረቃ ታደሚ አንቺ ኮከብ ስሚ ምድር ሆዬ አድምጪ ፍቅሬን አረጋግጪ። ቅጠል ሁሉ ብዕር ብራናዬ ባህር ቢሆኑም አይበቁኝ ፍቅሬን ለመመስከር። ብዬ አልልህም.......... ጨረቃ ታድማ በፍፁም አይታወቅም ምድርም ስታደምጥ ታይቶ አይታወቅም። ቅጠሉም ባህሩም ላንተ ፍቅር ብሎ ስላንተ አይፅፍም ይህ ሁሉ ዉሸት ነዉ ተደርጎ አያዉቅም። ወይም........ ልክ እንደ ደራሲ ወይም እንዳዝማሪ ደረቱ ሠፊ ነዉ ኩራቱ ገዳይ ነዉ ቁመቱ ሎጋ ነዉ ሺ ዉን ይዘርራል ያሳሳቁ ነገር እንደምን ይወራል ወንዳ ወንዱነቱን ሀገር ሁሉ አዉቆታል። እያልኩ በፍፁም አላወድስህም በዉዳሴ ከንቱ አልሸነግልህም በሚያልፍ በሚጠፋ ቃል አልደልልህም። እኔ አንተን ስወድህ ስልጣኑን አምልኮ ህዝቡን ለማሳመን እንደሚዳክረዉ አንድ ባለስልጣን አንተ የኔ ከሆንክ ችግር ተሠናበትክ ልማትን አበሰርክ ርሀብ የሚባል ከሀገር አባረርክ። እኔን ከመረጥከኝ ለምለም ነዉ ሀገሩ ጥጋብ ነዉ መንደሩ ሠላም ነዉ ብሄሩ ህብረት ነዉ መዝሙሩ እዉቀት ጤና ፍቅር ድሎት ነዉ ድምሩ። እያልኩ ባዶ ተስፋ ዉዴ አልሰጥህም ችግር የሌለበት ህይወት ታይቶ አያቅም። እኔ አንተን ስወድህ ፍቅሩን ለመመስከር እንደሚማልደዉ እንደ ደቀ መዝሙር። ሠላም ለአስናንከ ሠላም ለከናፍርከ ሠላም ለሳቅከ ሠላም ለጉርናኤከ እያልኩ አላወድስህም እኔ አንተን ስወድህ እንዲህ አላረቅህም። ብቻ.............. እኔ አንተን ስወድህ በቃልም ያልሆነ ተነግሮ በማያዉቅ ፍፁም በተለየ በማንም ታስቦ ባልተተነበየ እኔ አንተን ስወድህ እራሴን ሆኜ ነዉ ምናልባት ምናልባት ትቼህ እየሄድኩ ነዉ። #በትዝታ_ወልዴ እንደተፃፈ ✍ #መልካም_ቀን_ተመኘሁ 🙏🙏 SHARE @artmilitarys SHARE @artmilitarys #yegtm_hywet
Показать все...
ልጅነት የለሰለሰ መሬት ፣ ወጣትነት የአዝመራ ዘመን ፣ ሽምግልና ደግሞ የአጨዳ ዘመን መሆኑን አስተውል ። በሽምግልናህ የምታጭደው የወጣትነትህን አዝመራ ነውና ዛሬ ለምትዘራው ዘር ተጠንቀቅ! መልካም ቀን ተመኘሁ ። #ከመፃሕፍት_ጥግ
Показать все...
#ይሆን_ሁለገብ_የአርት_ቻናል #ካልተቀላቀልክ_እንዳያልፍህ ። #ውብ ስነፅሁፎች ከሁሉም ቦታ #የጥያቄና መልስ ውድድር ከእውነተኛ ሽልማት ጋር #የተለያዩ ጠቃሚና አስፈላጊ ንግግሮች ውይይቶች ያሉበት #መፅሐፍት በpdf የአርት ዜና ጥቆማ አስተማሪና አዝናኝ ምርጥ ቻናል #join ብቻ በል ታተርፋለህ። @artmilitarys #join @artmilitarys #join @artmilitarys #join
Показать все...
ሽማግሌዎች ሰውነታቸውን ያበረቱ ዘንድ መብል ሲፈልጉ በየመንገዱ ዳር ሞቱ፤ ያልሞቱትስ? ተስፋቸው ምንድርነው? በመሬት ላይ ተቀምጠዋል፣ የከፈለባቸው መጥቶ እስኪወስዳቸው እንደሚጠብቁ ከብቶች ሆነዋል፤ እንደተወጋ ሰው ጉልበቶቼ በዛሉ ጊዜ አይኔ በእንባ ደከመች አንጀቴም ታወከች። የማውቃቸው ጠፍተውኛል፣ ፊታቸው ከበርኖስ ይልቅ ጠቁሯል፣ ቁርበታቸው አጥንታቸው ላይ ተጣብቋል፣ ገርረው እንደ እንጨት ሆነዋል፤ አንድ የደከመ ድምፅ ወደ እኔ መጣ፤ “አንተ ልጅ ደፈር፣ ደፈር አትበል፣ ያመቸው ሰው ቀቅሎ እንዳይበላህ፤” ቀና ብዬ አየሁ። ይኼን የሚያደርግ እርሱ እራሱ፣ መካሪዬ እንደሆነ ገባኝ። @ዓለማየሁ ገላጋይ የተጠላው እንዳልተጠላ #መልከካም_ቀን_ይሁንልን ። SHARE @artmilitarys
Показать все...
ቤተሰቦች ሰው መሆን እንጂ መምሰል ሊያስጨንቀን አይገባም ። ጭንቅላት በሌላቸው ሰዎች መካከል ጉልበታችንን እንጠቀም ለመታገል ሳይሆን በዳዴ ለማለፍ ነገን ለማግኘት ዛሬን መስጠታችንን አንዘጋ ከ #Nazzrawi #ፀጥ_የለ_ሠናይ_አዳር_ይሁንልን SHARE @artmilitarys
Показать все...
ቅዠት - ዓለም እስኪደንቀን ድርስ ፣ እየታዘብነው ነው፣ የዚህን ዓለም ቅሌት፣ ይህን ዘመን ሙሉ ፣ በየዋህ ነፍስ እንጂ ፣ አልኖርንም በስሌት! ሁሉም ቀመርኛ ... ሁሉም ሂሳበኛ ባልለፋበት ጥበብ፣ ሕልምህን ይምሳል ፣ ጂኒ ምን ያውቅና ፣ 'ሰው' ከሠይጣን፣ ብሷል! #አስታወሰኝ_ረጋሳ #ወብ_ሰኞ_ተመኘሁ🙏🙏🙏 SHARE @artmilitarys SHARE @artmilitarys
Показать все...
አያሻም መደነቅ ┈┈┈•✦•┈┈┈ ማንኛውም ነገር ያለው በዚች ዓለም፣ ጊዜያዊ ነው እንጂ ቋሚ ነገር የለም፤ ተደንቆ ይናቃል፣ ተነስቶ ይወድቃል፤ ተናፍቆ ይረሳል፣ ከብሮ ይገሰሳል። መከላት መተካት ደንቡን ስለማይለቅ፣ ለመጣ ለሄደው አያሻም መደነቅ። ሰው እስካለ ድረስ እንዳይጎዳው ሀሳብ እንዳይጎዳው ጭንቀት፣ ቢያጤን ይጠቅመዋል ሂደትን በጥልቀት፤ ስለሚገኝ ዕውቀት ከትውፊት ከተግባር፣ ከንዝህላል ውድቀት ብልጥነት ነው መማር። SHARE @artmilitarys SHARE @artmilitarys ✍ ፀሐይ መልአኩ 📓 የስሜት ትኩሳት
Показать все...
"የትህትናም ሆነ የጉራ አላማ አንድ ይመስለኛል..... የሁለቱም አላማ የበላይነት ነው። "ልዩነቱ ጉረኛው የበላይነትን ተንጠራርቶ ይሸመጥጣል። ትሁቱ አጎንብሶ ይለቅማል። ምንጭ፦እንቅልፍ እና እድሜ ደራሲ፦ በዕውቀቱ ስዩም ?😳😔 #ethio_treca
Показать все...
ማንም ሰው ጫማውን እንጂ እግሩን መርጦ አይኖርም። ለመኖር እንበላለን ለመብላት እንሰራለን ለመስራት አቅማችንን(ስጦታችንን) እናውቃለን። ማንም ለመሞት አይኖርም ሞታችንን እያሰብን አንኖርም አማሟቱ ለማሳመር የሚኖር የለም ካለም አይሳካለትም ምክንያቱም እኛ በአምላክ እጅ ነን። ወደን እንዳልተወለደን ፈቅደን አንሞትም። ወደው ወደ አለም ያመጡን ወላጆቻችን ደስታቸው፤ ሳይፈልጉ ሲሸኙን ሀዘናቸው ነው። ይሄ ሚገርም አይደለም ለሞታችን አንድም ምክንያት ሳይኖር ሰው በመሰሉ ፍጡሮች ህይወትን ማጣት ህመሙ እያደር ይመረቅዛል 😥 #የዜግነትክብር #በቃ #ቀይአሻራ #አይዞሽ_ኢትዮጲያዬ #ኢትዮጲያዊነት_ለዘለዓለም_ይኑር 💚💛❤️
Показать все...
አዲሱና ትልቁ ቻናላችንን #ሼር_ሼር_join እያረግን ቤተሰብ እያፈራን ያለንን ምንም ነገር ለማካፈል @Nazzrawi እንጠቀም ቤተሰቦች መልካም አመሻሽ 😂😂🙏 #SHARE_&_JOIN http/t.me/artmilitarys http/t.me/artmilitarys
Показать все...
ገፅ all Art🎭 💃🎼

እኔ_ማለት_እኛ_እኛ_ማለት_ፅኑ_ገፅ_ነን።፲