cookie

Мы используем файлы cookie для улучшения сервиса. Нажав кнопку «Принять все», вы соглашаетесь с использованием cookies.

avatar

ገፅ Art & promotion 🎭 ®£

ገፅ [ [ [ የተለያዩ የኪነጥበብ ስራዎች ጥቆማ፣ዜና፣አዝናኝና አስተመሪ ሥነ ፁሁፎች ምርጥ ምርጥ ግጥሞች ከተለያዩ ፕሮግራሞች ጋር የሚገኝበት ቻናል ። [ [ [ የገፅ ኪነጥበባት ይፉዊ #የtelegram ቻናል [ [ [ ለማስታወቂያ እና መሰል ነገሮች @Nazzrawi ያግኙን ። join share👇

Больше
Эфиопия5 987Амхарский5 781Категория не указана
Рекламные посты
948
Подписчики
Нет данных24 часа
-207 дноК
-6230 дноК

Загрузка данных...

Прирост подписчиков

Загрузка данных...

ዓለም ደህና ሰንብች """""" """""""" """"""""" ፈቅ ፈቅ ፈቀቅ እግሬን አነሳሁት ወደ ነገ መንገድ ከተሸከሙኝ ላይ ወርጄ ልራመድ ቀና ቀና ቀና በድንገት ተነሳሁ እንደቀመሰ ሬት የተሸከምኩትን ላወርደው ከመሬት መንገዴን ጨርቅ ያርገው እርግማኔ ይክሸፍ ትላንት ይበቃኛል ወደ ነገ ልለፍ ዛሬን ኖሬው ልለፍ ቻው ተሰናበቱኝ ሄድኩኝ ወደ ሰላም ከማልጠግብበት ቤት አልቀምስም አልበላም ሄድኩኝ ወደ ደስታ ራሴን አገለልኩ ከማይጠቅመኝ ቦታ ለምን ሸክም ልሁን ለምን ልንገላታ ልሂድ ወደ ሰላም ልሂድ ወደ እፎይታ ከራስ በሚያሻግር በጥዑም ዝምታ ዓለም ፅድቅ እና ኩነኔ ጥጋብ እና ጠኔ ሰላም እና ጠቡ ገሀድና ህቡዕ እስኪጣጣሙላት ታርቀው እስኪቆሙ ሳይሻል አይቀርም ወደ ራስ ተሻግረው ከራስ ጋር መጦሙ ምሽግ ሳይቆፍሩ ጫካ ሳይሸፍቱ ድንበር ሳያፈርሱ ሙግት ሳይሞግቱ ክልልን ሳይለቁ ከሀገር ሳይወጡም ከራስ ጋ በመሆን ይታለፋል ሁሉም ዓለም ሁካታዋን ባታቆም ሁነቷን ሀሰቷን ገላልጣ ብትሸፍን እውነቷን አልከራከርም አልፈልግም ሸንጎ ጩኸት አይበርደውም አውቆ የተኛን ሰው ዝምታን ደራርቦ ዝም ዝም ዝም ሳላዝን ሳልቆዝም ዝም ዝም ዝም ለሸክላ ስጋዬ ነፍሴን አላሲዝም አሜን ዓለም ይድላት ዝምታን ያድላት ትሸ 'ኝ በዝምታ ትቀበል በአርምሞ ጦር አይማዘዝም ሰው አፉን አጡሞ እኔ'ማ ሄጃለሁ አካሌን ገዝቼ ከብኩን እርምጃ አንደበት አቅቤ ሌላውን መተቻ ሄጃለሁኝ ብቻ ዓለም ደህና ሰንብች ተኝቼ እስክነቃ ነገ እስከምነሳ ልለይሽ ነው በቃ ዓለም ደህና እደሪ !!! #በረከት_ዘውዱ @getsarts @getsarts ሼር
Показать все...
Фото недоступноПоказать в Telegram
የዳናት ፕሮዳክሽን የተዋንያኖች መመዝገቢያ ቅፅ 1 ሙሉ ስም 2 እድሜ 3 ፆታ 4 አድራሻ /ሰፈር/ 5 ስልክ ቁጥር 6 ልዩ ተሰጥኦ 7 6 በደንብ የሚታይ ፎቶ ( audtion photo) ለበለጠ መረጃ @danat 321 @Danatproductions 0967093758
Показать все...
01:41
Видео недоступноПоказать в Telegram
አልናፍቅሽም ''''''''''''''''''''''''''''''''''''  ማለት ነው """""""""""""""'''''''''''''''''''''''''''''''''''''                  ደህና ነህ ይሉኛል አዎን ናፍቃኛለች አሞኛል በጠና አንድ ጊዜ መጥታ እንደምንም ባያት እሆን ነበር ደህና አለህ ወይ ይሉኛል እኔማ ከሌለሽ  ከመኖር የት አለው አንቺ ግን ታድለሽ...አልናፍቅሽም  ማለት ነው ዘመን እንደ ጥምጣም ከህይወት አንገት ላይ      ታስሮ ተተብትቦ ቀን እንደ መስታወት አንቺን እያሳየኝ ናፍቀሽኛል አቦ እሄዳለሁ መንገድ እሻለሁኝ ጥጋት.............ከናፍቆት መሸም ሺ ሀገር ታምሶ መፍትሄ ላይገኝ.......አንድ አንቺን ለመርም አንቺስ እንደምን ነሽ ይሄድልሻል ወይ ? ይገፋል ሰአቱ ልክ ነው....አንቺጋ የጊዜ ስርዐቱ ........ያውልሽ እኔ ጋ ዘመን እንደ ዳዊት አንቺን ተነቅሶ ሲደግም ከረመ ጊዜዬን ናፈቅሽው መሄዱን አቆመ ያውልሽ እኔ ጋ መዐልቱ ጨልሞ ፀሀይን ልሞቃት እነሳለሁ ሱብሂ  ሀዘን ዘለቀበት በከፈትኩት ልቤ አንቺ እንድትገቢ አላሳዝንሽም የትዝታሽ ዝናብ ዶፍ እያዘነበ የናፍቆት በረዶ የፍቅርሽ ቤት ፈርሶ.............ልቤ ላይ ተንዶ ..............ሊገለኝ ናፍቆትሽ ሲነድለኝ ጉልበቴን ሲያዝለኝ ለመውጣት ስዳክር የትዝታን ዳገት አቅሜ እስከቻለው አንቺ ግን ታድለሽ   አልናፍቅሽም ማለት ነው ስሚ'ማ ምን ልልሽ ነበረ...........እንትን ሰው ዛሬ ላይ ሲቆም   ይረሳል ትላንትን ግን አንዳንዴም ሳስብ ልክ ነሽ እላለው አንቺ ግን ታድለሽ ረስተሽኛል ማለት ነው #በረከትዘውዱ @getsarts @getsarts @getsarts ቤተሰቦች ሟር ሟር
Показать все...
ይታይሻል አይደል እዚያ ማዶ ጋራ ይታይሻል አይደል አንድ ሴት ተክዛ እኔን የምትመስል እንባዋ ይወርዳል ድምፅ ግን የላትም እሷን የሚረዳት ማንም የለም ምንም እና..... የለበሰችውን ቀሚስ ቆሜ ስመለከት አረንጓዴ ቢጫ ቀይ ቀለም አለበት ምንድነው ትርጉሙ የምታለቅስበት ምን ይሆን ምክንያቱ በቀለም ሸብርቃ የምትታይበት በርከክ አልኩኝና አጠገቧ ስደርስ አይኖቿን አየሁኝ ደም እንባ ሲያለቅስ የኔ እህት ለምን ታለቅሻለሽ? ምንድነው ትርጉሙ ይህን ልብስ መልበስሽ? እሷም አንዲህ አለች ነፍረቅረቅ እያለች አረንጓዴ ማለት ልምላሜ ነው ብላ መተንተን ጀመረች... ቢጫ ማለት ደግሞ ተስፋዬ ነው ብላ ማውራቷን ቀጠለች... ቀይ ማለትማ ለኔ የተሰውልኝ የልጆቼ ደም ነው ብላ ደመደመች እና ለምን ታለቅሻለሽ?ብዬ ጥያቄ ሰነዘረኩ እሷ:ልጆቼ ቢጣሉ ከራሳቸው ጋራ ሚሰማኝ የለኝም ብጣራ ብጣራ የኔ ነሽ አያሉ ሰላም ይነሱኛል ብርቆቹ ልጆቼን ከኔ ይነጥቁኛል ውስጤ ይቃጠላል ድምፅም ይሰማኛል የጥይት እሩምታ በሰው ላይ ይወርዳል የልጆቼ ጩኸት ልቤን አውኮኛል የድሮ ኢትዮጵያን መምሰል አቅቶኛል አንዳንዶቹ ደግሞ ያጠባውን ጡቴን ደግመው ደጋግመው ዛሬም ሰውነቴን ንክስ ያረጉኛል ህመም ይሰማኛል መልአኩ ገብርኤል ኸረ እንዴት ይሻላል? ብላ አወራችኝ እኔም በእንባ ረጠብኩ በደረሰው ድርጊት እጅጉን አዘንኩ እናቴ ኢትዮጵያ እያልኩኝ ጠራኋት እንባዎቿ ጠፉ ሳይታሰብ በቅስፈት እናቴ ነው ያልከው ብላ አቀፈችኝ በጉንጮቿ ስማ ፍቅርን ሰጠችኝ ሀገሬ እዛ ማዶ ጋራ ይታይሻል አይደል አንቺን የሚጠብቅ ወዲህ ወዲያ የሚል ያ ማለት እኔ ነኝ ሰራዊት ሚመስል @getsarts @getsarts 🙏🙏share
Показать все...
Фото недоступноПоказать в Telegram
ሳይታይ🤷‍♀ አለ ማይነገር ልብ ላይ የሚቀር ሳይታይ እውነታው ከልብ የሚታሰር ተደፋፍኖ ሚኖር መቼም ማይሰማ ታፍኖ የሚቆይ በትግስት በአላማ ጥንካሬን አዝሎ ጥበብን ተክኖ ይኖራል ሳይፈራ በልቡ አፍኖ ነገራትን አይቶ አርቆ መርምሮ በዝምታ ይኖራል ሕሊናን አዳብሮ አላዋቂ ይመስላል ለሚያየው ሩቅ ሆኖ ዝምታ ቅኔውን በመርሳት አጋኖ ዝም ስንላቸው ሞኝ ምንመስላቸው አሉ በሂወታችን ቦታ ምንሰጣቸው ይኑሩም ዘላለም እነርሱ ባሰቡን በሞኝነት አይተው ሳያውቁ እውኑን ሳይረዱ ቀርተው ሚዛን ሚደፋውን ቅኔ መሆኑንም ከቶም ሳይገባቸው ዝምታን ያዩታል ሞኝነት መስሏቸው እንኑርላቸ በዝምታ ጊታር በቄኔያችን ምስጢር በታጋሹ ጥበብ ከላይ በተቸረን እ ው ነ ት እኖራለን አላዋቄ መምሰል አንችልበታለን በ፦ቃልኪዳን ሲሳይ @getsarts @getsarts @getsarts
Показать все...
ሽንቁር በድቅድቅ ጨለማ በጥቁር ሰማይ ስር ብርሀን ምታስገባ አለች አንዲት ሽንቁር በደምፀ(አቡጊዳ) በታመቀ ምድር በእኔነት መንፈስ እጅግ ለተጎዳ የኛነትን ንፋስ የሚያናፍስልን አለ አንድ ቀዳዳ እረግ እረግ ታፍነን የለም ወይ በእኔነት ማዕረግ ማዕረግ ነው ማዕረግ ነው ግድ የለም አንዲህ ሚያላቅሰን ሠይጣን ያሣከለን ከሠውነት አንሠን ቁጥቋጦ ያረገን ከዋርካነት ንዶን ብቻዬን ለግሌ ሚያስብለን አባዜ ሠውነትን ሚያስክድ የሠይጣን ኑዛዜ አብረን ቁጭ ብለናል የስልካችን ብርሀን ፊታችን ላይ በርቷል ውስጣችን ጨልሟል ወርቃችንን ትተን መዳብን ፍለጋ እሩቅ ተጉዘናል ታድያ ከዚህ ወዲያ ማዕረግ ኬት ይገኛል በሠይጣኒዝም ኮርስ ማስትሬት ይዘናል ግን ግን ደግሞ ይነጋል አይቀርም ጨልሞ የጦቢያ ፋኖስ ልባችን ላይ ከትሞ በድቅድቅ ጨለማ በጥቁር ሰማይ ስር ብርሀን ምታስገባ አለች አንዲት ሽንቁር ሽንቁር ናት ለሌው ኢምንት ምናምቴ ከአድማስ ትሰፋለች ለኔና ለአያቴ ሽንቁር ናት ለነሱ ሽንቁር ናት ለነዚያ ለኔ ግን ምሉዕ ነች የንጋትን ጮራ የብርሀን ማያ ጨለማ ይሏታል ጥቁሮች ይሉናል አዎ እኛ ጥቁር ነን ሁሉንም ችለናል ነጭማ ነጭ ነው ቶሎ ይመነችካል ካንድ ቀን ባሻገር መች ተለብሶ ያውቃል ጥቁሮች ነን እኛ ጨለማ ናት አሷ ልብሳችን ቡቱቱ ቤታችን ደሳሳ አርግጥ ነው አንክድም ሽንቁር ናት ለአለም የብርሀን መግቢያ ከዚች ሽንቁር ውጪ ሌላ መንገድ የለም ሽንቁር ነሽ ኢትዮጵያ ሽንቁር እናት አለም የተሸነቆርሽው አርጅተሽ አይደለም እንኳን ተሸነቆርሽ እንኳን ቀዳዳ ሆንሽ የኛነትን መንፈስ ታናፍሽኛለሽ በድቅድቅ ጨለማ በጥቁር ሰማይ ስር ብርሀን ምታስገባ አለች አንዲት ሽንቁር በታመቀ ምድር በእኔነት መንፈስ እጅግ ለተጎዳ የኛነትን ንፋስ የሚያናፍስልን አለ አንድ ቀዳዳ @getsarts @getsarts
Показать все...
በዚህ ጭጋግ በወረሰው በደፈረሰ ቀን የሰው ልጅ በሰው ልጅ በንቀት ዚመዘን ከመዛኙ ይልቅ ሚዛን የደፋነው እኔ እና አንቺ ነበርን እኔ እና አንቺ (3X) ማለት ባለም የተናቅን ስማችን ጥቁር ነው የተሰጠን ዋጋ ከውሻም በታች ነው ግና ውድ አለሜ እንደውሻ ታምነን እንደጥቁር ከርቤ የተከበርንበት የተፈራንበት አድዋ ምንለው ደማቅ ታሪክ አለ የምንባላበት ታዘቢ እንግዲ ጥቁር ዘር በሞላ አድዋ እያለ ዘላለም ያወራል ዘላለም ይኮራል የኛ ከንቱ ትውልድ በእጅ ያለ ወርቅ ሆኖበት ነገሩ በእምዬ ምንይልክ በእቴጌ ጣይቱ በአድዋ ይባላል ታዘብሽልኝ አይደል ተይ አትታዘቢ ይልቅ ጸልይለት ለዚህ የዘር ህሙም ለዚህ በሽተኛ ለአድዋ ድንበር ለሚያበጃጅለት ለዚህ መትፃጉእ ሰው ለዚህ ህመምተኛ እኔ ምልሽ ውዴ አደዋ በራሱ ድንበር አይደል እንዴ አዳምጪኝ አለሜ ብሶት ላፈነው ወንድ የሴት ልጅ ጆሮ ነው መደመጥ ነው ምሱ ከጭንቀት ማረፍያ መጠለያ ዳሱ አዳምጪኝ ግድ የለም ጆሮ ብቻ ስጭኝ ዝም ጭጭ ያልኩ እንደው ዳግም አታገኚኝ አለመሰማማት አለመስማማት ነው ለዚህ የዳረገን ካቻምና አምና ዘንድሮና ከርሞ በባዶ እግራችን ለነገሩ ብትሰሚኝም ባትሰሚኝም ዝም ብዬ አወራለው የማንባላበት የማንጣላበት አደዋ ሰራለው። ይልቀ ከጎኔ ሁኚ ነይ እንፈቃቀር ሚኒሊክስ ቢሆን ጣይቱ ባትኖር መች ያሸንፍ ነበር ✍️✍️✍️✍️በደምፀ @getsarts @getsarts @getsarts
Показать все...
😂😂ህይወትን ሳቅላት 😜😜😂 ታውቃለህ ወንድሜ ህይወትን በእድሜ ስተነትንልህ አትውቀሰኝ ምንመሰለህ ከሰማኸኝ እርህሴ ባይሰማም ስገጥምልህ እንዲናት በግጥም ሳቅባት ስትነቃባት በጭራሽ እንዳትሰማት ለችግር ስትሰጥህ ወንድልጅ ሁን እንዳታለቅስላት እግዚአብሔር ካንተጋ ነውና ተስፋህ ሲፈተን ጠንካራ ሁንና ከክፋት ከሀጥያት እራቅ በልና ጠብቅ ስኬትህን ደስተኛ ሁንና አንተ ከጠየከው በላይ ይደረግልሀል አምላክ ሰው አይደለም ቃሉን ይጠብቃል ስለዚህ ወንድሜ ጠብቀው በትእግስት ግድ የለም እመነኝ ህይወትን ሳቅላት 😜😂 📝 ከረቂቅ 📝📝🙏 @getsarts @getsarts @getsarts
Показать все...