ru
Feedback
ፍኖተ መጻሕፍት 📚FinoteBooks1623 ➮አድራሻ አዲስ አበባ ፒያሳ ገነተ ፅጌ ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተክርስቲያን ማኅበረ በኩር ሰንበቴ ፊት ለፊት ለበለጠ መረጃ ፦በ0913083816 ይደውሉ።

ፍኖተ መጻሕፍት 📚FinoteBooks1623 ➮አድራሻ አዲስ አበባ ፒያሳ ገነተ ፅጌ ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተክርስቲያን ማኅበረ በኩር ሰንበቴ ፊት ለፊት ለበለጠ መረጃ ፦በ0913083816 ይደውሉ።

Открыть в Telegram

📚ፍኖተ መጻሕፍት @finoteBooks1623 ለውድ አንባብያን በDHL እና በEMS እንዲኹም የDelivery አገልግሎት በመስጠት መጻሕፍትን ተደራሽ እናደርጋለን። [ እንደ መጻሕፍት ያለ መንገድ ከወዴት ይገኛል?] ይደውሉልን!📞፦0913083816 t.me/FinoteBooks1623

Больше
3 275
Подписчики
Нет данных24 часа
-207 дней
-5830 день
Архив постов
#በብዙዎች_እጅ_ዘንድ_ስላልገባው፥ #ግን_ደግሞ_እጅግ ግሩም የሆነ መጽሐፉ እንጠቁምዎት! የዮሐንስ ዘሰዋስው እና የነገረ ሃይማኖት መጻሕፍት አዘጋጅ የኾነው የመምህር ሳሙኤል ፍቃዱ ነው። ምጽአተ ክርስ
#በብዙዎች_እጅ_ዘንድ_ስላልገባው፥ #ግን_ደግሞ_እጅግ ግሩም የሆነ መጽሐፉ እንጠቁምዎት! የዮሐንስ ዘሰዋስው እና የነገረ ሃይማኖት መጻሕፍት አዘጋጅ የኾነው የመምህር ሳሙኤል ፍቃዱ ነው። ምጽአተ ክርስቶስ ይሰኛል። ይህ በ445+10 (455) ገጾችና በ11 ምዕራፎች የተዘጋጀው መጽሐፍ በውስጡ፦ ፩. ምጽአትን ስለ መረዳት ፪. ስለ ምጽአት መጽሐፍ ቅዱሳዊ ምሳሌዎች ፫. ስለ ምጽአት ቀን ምንነት ፬. ስለ ምጽአት ምልክቶች ፭. ምጽአትን አስመልክቶ ስለሚነገሩ አንዳንድ አስተምሮዎችና የቤተ ክርስቲያን ትምህርት ፮. በምጽአት ዋዜማ ስለሚታዩ ምልክቶች ፯. በምጽአት ጊዜ ስለሚኖር ታላቁ መከራና ስለ ሰባቱ ጽዋዎች ፰. በምጽአት ጊዜ ስለሚከናወኑ ሦስቱ ዐበይት ክስተቶች ፱. የሚመጣው ማን እንደ ኾነና ስለሚደረገው ፍርድ ፲. ስለ ምረረ ገሃነም ፲፩. ስለ መንግሥተ ሰማያት  ብዙ ዝርዝርና ርቱዕ የኾነውን ትምህርት የያዘ ነው። እርስዎም ይህን ብስል መጽሐፍ በማግኘት ስለ ኦርቶዶክሳዊ ምጽአት ያለዎትን ግንዛቤ ያዳብሩ። ከስሕተት ትምህርቶች ይጠበቁ፤ ሌሎችንም ይጠብቁ። ------------------------- በግዮን መጻሕፍት መደብር ዘወትር በልዩ ቅናሽ ያገኙታል። https://t.me/GhionBookStore1623

#ዜና_ድጋሚ_ኅትመት ምሥጢረ ምሥጢራትን እንደ ጎበኘኋት፡፡ ዘመኑ በመጻሕፍት አቅርቦት በኩል ምቹ ነውና ብዙ መጻሕፍትን የማንበብ እድል ገጥሞኛል። ምሥጢረ ምሥጢራት ግን እንደ ሥያሜዋ ከሌሎች ለየት ብ
#ዜና_ድጋሚ_ኅትመት ምሥጢረ ምሥጢራትን እንደ ጎበኘኋት፡፡ ዘመኑ በመጻሕፍት አቅርቦት በኩል ምቹ ነውና ብዙ መጻሕፍትን የማንበብ እድል ገጥሞኛል። ምሥጢረ ምሥጢራት ግን እንደ ሥያሜዋ ከሌሎች ለየት ብላ አግኝቻታለሁ፡ በምሥጢረ ሥላሴ ላይ ብቻ ትኩረት ማድረጓ አንድ ልዩ ነገር ሁኖ፣ ከዚያውም ዘንድ ወደ ባሕረ ምሥጢሩ ስባ ጎትታ የምታስገባና በጥሩ የሊቃውንት መቅዘፍያ እየቀዘፈች ብዙ ሰዎች ወደ አላዩት የምሥጢር ወደብ የምታደርስ፤ ከይዘት አንጻር ከተመዘነች በምጥቀትና በጥልቀት ለዘመናችን የመጀመሪያ የምትባል መጽሐፍ ናት፡፡ መጽሐፏን የምትመለከቱ ሁሉ፦ በትሐት ሰብእና፣ በንጹሕ ልቡና፤ በቅጥነተ ኅሊና ሁናችሁ እንድትመለከቷት ወንድማዊ ምክሬ ነው። መልካም ንባብ መምህር ኃይለ ማርያም ዘውዱ ዘቦሩ ሜዳ 👉ውድ አንባብያን ይኽን በመ/ር ገብረ መድኅን እንየው እና በመ/ር መዝገበ ቃል ገብረ ሕይወት ተዘጋጅቶ በሊቃውንት ሳይቀር ግሩምነቱ የተመሰከረለትን መጽሐፍ አንብበን ተጠቃሚ ለመኾን ጊዜ ባንሰጥ መልካም ነው እያልን መጽሐፉን #በግዮን_መጻሕፍት በልዩ ቅናሽ ያገኙታል። #📚 ግዮን መጻሕፍት ለውድ አንባብያን በDHL እና በEMS መጻሕፍትን ተደራሽ እናደርጋለን። ይደውሉልን !📞፦0913083816 https://t.me/GhionBookStore1623

ዜና_መጽሐፍ አዲስ መጽሐፍ በገቢያ ላይ …በአድሜ ዘመኑ ሌላው ቀርቶ የዚህን ጫካ ወለል ምን እንደሌለው፣ ምን እንዳለው እንኳን አይቶት የማያውቅ፤ ጨርሶ ስለኛ የማወቅ ፍላጎት የሌለው እኮ ነው፡፡ ንሥ
ዜና_መጽሐፍ አዲስ መጽሐፍ በገቢያ ላይ …በአድሜ ዘመኑ ሌላው ቀርቶ የዚህን ጫካ ወለል ምን እንደሌለው፣ ምን እንዳለው እንኳን አይቶት የማያውቅ፤ ጨርሶ ስለኛ የማወቅ ፍላጎት የሌለው እኮ ነው፡፡ ንሥር እኮ በእኛ ላይ የሚኖር፣ ከእኛ ጋር ግን የሌለ፤ ለእኛ ቅርብ የሆነ፡ ከእኛ ግን ሩቅ የሆነ ፍጥረት መሆኑን አታውቅምን?…..! “…..እንደምታውቁት ተፈጥሯችን ከአንድ ቦታ ተተክለን እንድንኖር ያስገድደናል፡፡ ይህ ውብ ተፈጥሯችን ግን የተለየ ጸጋ ነበር፡፡ ፈጣሪ ከአንድ ቦታ ተተክለን እንድንኖር አድርጎ ሲፈጥረን ትልቁ ምሥጢር ችግር መፍታት እንጅ ችግርን መሸሽ ተፈጥሯችን እንዳልሆነ ሲያጠይቅ ነበር…. እኛ እንደ እንስሳት ችግር በመጣ ጊዜ እየፈረጠጥን ከአንዱ ወደ አንዱ ልንሄድ አይገባንም፤ አያስፈልገንምም…….' “መቸም እኛ ዕፅዋት … ነፋስ በነፈሰ ቁጥር መወዛወዛችን የነበረና ያለ ነው፣ ወደፊትም የሚኖር ነው…. ዕፅዋት ልብ በሉ! የምንወዛወዘው ከነፋስ ጋር አላስፈላጊ ግብግብ ላለመግጠም እና ትንሽ አወዛውዞን አልፎ እንዲሄድ እንጅ ከሥራችን እንዲነቅለን አይደለም፡፡' '…..ታምሚያለሁ ብሎ ያላመነ መድኃኒት አይሻም፤ በህመም ያልተሰቃየም በፈውስ አይደሰትም! ጤነኛ ነኝ ብሎ የሚያስብ ባለ መድኃኒት ይፈልጋልን? አዋቂ ነኝ የሚልስ መካሪ ይሻል?.......' በግዮን መጻሕፍት መደብር የተለያዩ መጽሐፎችን ዘወትር በልዩ ቅናሽ ያገኛሉ። ይደውሉ ፦በ0913083816 https://t.me/GhionBookStore1623

#ምርጡን_ከተመረጡት_ተማር ከነህሚያ 👉 ጸሎትን ከማርያም 👉 አክብሮትን ከማርታ 👉 ዝቅ ማለትን ከጳውሎስ 👉 ማስተማርን ከዳንኤል 👉 መታዘዝን ተማር የተሸለሙትን ትሸለማለህ!!! #የጽድቅ_መንገ
#ምርጡን_ከተመረጡት_ተማር ከነህሚያ 👉 ጸሎትን ከማርያም 👉 አክብሮትን ከማርታ 👉 ዝቅ ማለትን ከጳውሎስ 👉 ማስተማርን ከዳንኤል 👉 መታዘዝን ተማር የተሸለሙትን ትሸለማለህ!!! #የጽድቅ_መንገድ መጽሐፍ #ሕይወት_እና_ክርስትና መጽሐፍ ሁለቱም የአቡነ ሺኖዳ ሳልሳዊ አዲስ መጽሐፍት በግዮን መጻሐፍት ዘወትር በልዩ ቅናሽ ይገኛሉ። ለበለጠ መረጃ፦ በ0913083816ይደውሉ። https://t.me/GhionBookStore1623

#ፈጣሪ ለዳንኤል የአንበሶችን አፍ ከዘጋ ለሙሴ ቀይ ባህርን ከከፈለ ለኢያሱ ጸሐይን ካቆመ ለጴጥሮስ እስር ቤትን ከከፈተ ለሳራ ልጅን ከሰጠ አላዛርን ከሞት ካስነሳ ላንተም የማያስብበት ምክንያት የለም
#ፈጣሪ ለዳንኤል የአንበሶችን አፍ ከዘጋ ለሙሴ ቀይ ባህርን ከከፈለ ለኢያሱ ጸሐይን ካቆመ ለጴጥሮስ እስር ቤትን ከከፈተ ለሳራ ልጅን ከሰጠ አላዛርን ከሞት ካስነሳ ላንተም የማያስብበት ምክንያት የለም!! ብቻ አንተ በእሱ እመንበት!!? #ወንድሜ_ሆይ_ለነፍስህ_ቤት_ስራላት https://t.me/GhionBookStore1623

#ለነፍስ_አይጠቅምም! ስለ እሳት ማሰብ ገላን እንደማያሞቀው ሁሉ፣ ተግባራዊ ፍቅር የሌለበት እምነትም ለነፍስ አይጠቅምም! የአቡነ ሺኖዳ ሳልሳዊ፣ የቅዱስ ዮሐንስ አዲስ ምርጥ ምርጥ መንፈሳዊ መጽሐፍት
#ለነፍስ_አይጠቅምም! ስለ እሳት ማሰብ ገላን እንደማያሞቀው ሁሉ፣ ተግባራዊ ፍቅር የሌለበት እምነትም ለነፍስ አይጠቅምም! የአቡነ ሺኖዳ ሳልሳዊ፣ የቅዱስ ዮሐንስ አዲስ ምርጥ ምርጥ መንፈሳዊ መጽሐፍት በገበያ ላይ ፦ 👇🎀👇 👉 #ጠይቁ_ይመለስላችኋል 4ተኛ ዕትም 👉 #ሰይጣንን_አስርቡት 2ተኛ ዕትም 👉 #የነፍስ_ምግብ 2ተኛ ዕትም 👉 #እስከማዕዜኑ 3ተኛ ዕትም ሁሉም መጽሐፍት በመጻሐፍት መደብራችን ዘወትር በልዩ ቅናሽ ይገኛሉ። https://t.me/GhionBookStore1623

አዲስ መጽሐፍ በገቢያ ላይ ዶ/ር ዓለማየሁ ዋሴ እመጓ፣ ዝጎራ፣ መርበብት፣ ሚተራሊዮን፣ ሰበዝ እና ችቦ በተሰኙ ተወዳጅ መጻሕፍት የሚታወቅ ደራሲ ነው። አኹን ደግሞ ሰባተኛ መጽሐፋቸውን ፍካሬ በሚል እ
አዲስ መጽሐፍ በገቢያ ላይ ዶ/ር ዓለማየሁ ዋሴ እመጓ፣ ዝጎራ፣ መርበብት፣ ሚተራሊዮን፣ ሰበዝ እና ችቦ በተሰኙ ተወዳጅ መጻሕፍት የሚታወቅ ደራሲ ነው። አኹን ደግሞ ሰባተኛ መጽሐፋቸውን ፍካሬ በሚል እነሆ ብለውናል በመደብራችን ዘወትር በልዩ ቅናሽ ያገኙታል። ይደውሉልን ፦በ0913083816 https://t.me/GhionBookStore1623

አዲስ መጽሐፍ በገቢያ ላይ ዶ/ር ዓለማየሁ ዋሴ እመጓ፣ ዝጎራ፣ መርበብት፣ ሚተራሊዮን፣ ሰበዝ እና ችቦ በተሰኙ ተወዳጅ መጻሕፍት የሚታወቅ ደራሲ ነው። አኹን ደግሞ ሰባተኛ መጽሐፋቸውን ፍካሬ በሚል እ
አዲስ መጽሐፍ በገቢያ ላይ ዶ/ር ዓለማየሁ ዋሴ እመጓ፣ ዝጎራ፣ መርበብት፣ ሚተራሊዮን፣ ሰበዝ እና ችቦ በተሰኙ ተወዳጅ መጻሕፍት የሚታወቅ ደራሲ ነው። አኹን ደግሞ ሰባተኛ መጽሐፋቸውን ፍካሬ በሚል እነሆ ብለውና በመደብር ዘወትር በልዩ ቅናሽ ያገኙታል። ለበለጠ መረጃ መደወል በ0913083816

💧ዜና_መጽሐፍ 【አዲስ መጽሐፍ በገበያ ላይ】 📖ትምህርተ እግዚአብሔር ➮ይህ “ትምህርተ እግዚአብሔር ዘኦርቶዶክስ"በሚል ርእስ በመ/ር_ምስጢሩ_ታየ የተዘጋጀው መጽሐፍ፣ ስለ #እግዚአብሔር አምላክነትና
💧ዜና_መጽሐፍ  【አዲስ መጽሐፍ በገበያ ላይ】 📖ትምህርተ እግዚአብሔር ይህ “ትምህርተ እግዚአብሔር ዘኦርቶዶክስ"በሚል ርእስ በመ/ር_ምስጢሩ_ታየ የተዘጋጀው መጽሐፍ፣ ስለ #እግዚአብሔር አምላክነትና እሠራር እንዲሁም ስለ ሌሎች መሰል ጉዳዮች ልናውቃቻው የሚገቡ መሠረታዊ ሐሳቦችን የያዘ መጽሐፍ ነው። የሚያነሣቸውን ሐሳቦችም ኦርቶዶክሳዊ በሆነ ይዘትና ውበት ባለው የሥነ-ጽሑፍ ለዛ የሚያብራራ ጥሩ መጽሐፍ ነው። መ/ር_ምስጢሩ_ታየ ይህን መጽሐፍ ጽፈው ስላበረከቱልን ከልብ እያመሰገንኩ፣ ይህን መጽሐፍ ብታነቡ ትጠቀሙበታላችሁና ጊዜ ሰጥታችሁ ታነቡት ዘንድ በአክብሮት እጋብዛለሁ።   #ዲ/ን_ያረጋል_አበጋዝ 👉ውድ አንባብያን ይኽን በመ/ር ምስጢሩ ታየ ተዘጋጅቶ በሊቃውንት ሳይቀር ግሩምነቱ የተመሰከረለትን መጽሐፍ አንብበን ተጠቃሚ ለመኾን ጊዜ ባንሰጥ መልካም ነው እያልን መጽሐፉን #በግዮን_መጻሕፍት በልዩ ቅናሽ ያገኙታል። #📚 ግዮን መጻሕፍት ለውድ አንባብያን  በDHL እና በEMS መጻሕፍትን ተደራሽ እናደርጋለን። ይደውሉልን !📞፦0913083816 https://t.me/GhionBookStore1623

ቁጣ ድል አይንሣህ ወንድምህን ከሚገባው ይልቅ ለማክበር ሰውነትህን አትጋት። ባገኘህውም ጊዜ እጁን እግሩን ሳመው፤ በጎ አድርግለት አክብረህ ወደህ እየው፡፡ ሥራው ባይደለ ሥራ አመስግነው፣ ከአንተም በ
ቁጣ ድል አይንሣህ ወንድምህን ከሚገባው ይልቅ ለማክበር ሰውነትህን አትጋት። ባገኘህውም ጊዜ እጁን እግሩን ሳመው፤ በጎ አድርግለት አክብረህ ወደህ እየው፡፡ ሥራው ባይደለ ሥራ አመስግነው፣ ከአንተም በተለየ ጊዜ የእሱን ነገር ተናገር፡፡ ከበጎ ሥራው ወገን መናገር በሚቻልህ ገንዘብ በጎ በጎ አድርግለት፡፡ በጎ ነገር በመናገርህ ወደ በጎ ሥራ ትስበዋለህ ታነቃቀዋለህ፡፡ አንተ ባመሰገንከው ምስጋና፣ አንተ ባከበርከው ክብር የተነሣ ያፍር ዘንድ እንዳመሰገንከው ያልሆነ እንደሆነ ያፍራል፤ እንዲህ የሆነ እንደሆነ ዘርአ ትሩፋትን ትዘራበታለህ፡፡ ነፍስህ ከለመደችው ባልንጀራህን ከማክበር የተነሣ በጎ ነገርን መውደድ በልቡናህ ይቀርጻል፡፡ ፍጹም ትሕትናን ገንዘብ ታደርጋለህ ሳትጥር ብዙ ሥራ ትሠራልህ፡፡ የምታከብረው በጎውን ሰው ብቻ አይደለም ነውር ያለበትም ቢሆን አክብረው እንጂ፡፡ እንዲህ የሆነ እንደሆነ አንተ ካከበርከው ክብር የተነሣ አፍሮ ካንተ ድኅነትን ያገኛል። ገንዘብህ የምትሆን ይህችን ጥበብ ለሁሉ አድርጋት፤ ጥበብም የተባለች ሰውን ማክበር ለሰው ማዘን መራራት ናት። አንዱንስ እንኳን አትቈጣ፣ ተቈጥተህ አታሳዝነው፣ ቍጣ ድል አይንሳህ፡፡ ስለ ሃይማኖትም ቢሆን፣ ሥራው ክፉ ስለሆነም ቢሆን ሰው እንዳታማ ተጠበቅ እንጂ አትፍረድበት፡፡ በልዕልና ፊት አይቶ ሳያዳላ የሚፈርድ ዳኛ ክርስቶስ አለንና፡፡ ወደ በጎ ሥራም ልትመልሰውም ብትወድ እዘንለት፤ እያለቀስህ የለዘበ ነገር ንገረው፤ በቍጣ አትናደድበት፤ ጸብ ያለህ ይመስለዋል ፍቅር ውስጣዊ ቍጣን አይሻምና። #ማር_ይስሀቅ

#ራእየ ዮሐንስ « በዮሐንስ ራእይ የሚገኙ ምስጢራት እንደ ቃላቱ የበዙ ናቸው፡፡ እያንዳንዱ ቃል ጥልቅ የሆነ ምስጢር በውስጡ አዝሏል፡፡ ይህም ስለ መጽሐፉ ልንሰጠው ከሚገባው የከበሬታ ስፍራ ትንሹ ነ
#ራእየ ዮሐንስ « በዮሐንስ ራእይ የሚገኙ ምስጢራት እንደ ቃላቱ የበዙ ናቸው፡፡ እያንዳንዱ ቃል ጥልቅ የሆነ ምስጢር በውስጡ አዝሏል፡፡ ይህም ስለ መጽሐፉ ልንሰጠው ከሚገባው የከበሬታ ስፍራ ትንሹ ነው፡፡ እያንዳንዱ ቃል የያዘው ምስጢር እጅግ ብዙ በመሆኑ ለእርሱ የሚኖረን ምስጋና ከሚገባው በታች ነው፡፡ እኔ ለምረዳውም ሆነ ለማልረዳው ለእያንዳንዱ ቃል ምስጋና አቀርባለሁ፡፡›› #ቅዱስ ሄሮኒመስ ‹‹ እኔ ከማስበው በላይ ብዙ ሐሳቦችን አምቆ የያዘ ቢሆንም በብዙ መልኩ ታላላቅ ምስጢሮችን መያዙን ተረድቻለሁ፡፡ ለመረዳት ያለኝ አቅም ትንሽ ቢሆንም ከቃላቱ ባሻገር ጥልቅ ምስጢር መያዙን ግን አምናለሁ። እኔ በምረዳው ያህል ዐረፍተ ነገሮችን ለመተርጎም ወይንም ይህ ነው ብዬ ለመናገር አልችልም፤ በየዋሕነት እና በእምነት እንዲሁ እቀበለዋለሁ እንጂ፡፡ ለአእምሮ የተደላደለ እና ተስማሚ ሆኖልኛል፤ እናም ያልተረዳሁትን ነገር አልቃወመውም፤ አደንቃለሁ እንጂ።›› #የእስክንድርያ ፓትርያርክ ዲዮናስዮስ ◍ይኽ እጅግ ተፈላጊ መጽሐፍ ሀርድ ከቨር ሲኾን የተወሰኑ ቅጂዎች ብቻ የቀሩት በመኾኑ እንዳያመልጥዎ እነኾ ጋብዘንዎታል።   ✥••┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈••✥ #📚 ግዮን መጻሕፍት ለውድ አንባብያን  በDHL እና በEMS መጻሕፍትን ተደራሽ እናደርጋለን። ይደውሉልን !📞፦0913083816 https://t.me/GhionBookStore1623

#ማኅበረ_ሥላሴ_ገዳምና_ጻድቁ_ዐምደ_ሥላሴ ፨ ታቦቱ_ሥላሴ፥ ፨ ጻድቁ_ዐምደ_ሥላሴ፥ ፨ የገዳሙ ስም ማኅበረ ሥላሴ፡፡ ፨ በየቀኑ በሁሉም ቤክ በቅዳሴ ላይ ስሙ የሚነሳው ገናናው ገዳም (ብዙዎች ግን የማያውቁት)፡፡ ፨ እንኳን ሰዉ ከብቱ ሥርዐት ያለው ድንቅናዕፁብ ገዳም፡፡ ፨ ገዳሙን ያጠፉ አውሮፕላኖችን በጸሎት የከሰከሱ አባቶች የሚገኙበት የበርካታ ትምህቶችና የጥበብ ማዕክል፤ …. ኢትዮጵያውያን ሁሉ ቢያንስ አንዴ ሊያዩት የሚገባ ዕፁብ ድንቅ የኾነ ገዳም!!!፡፡ ፨ በዚህች በየካቲት 27 እለት ወላዴ አእላፍ ቅዱሳን ወመነኰሳት (ለአቡነ ክፍለ ማርያም፥ ለአቡነ ገብረ ክርስቶስ ዘቋራ፥ ለ፯ቱ ዘሥላሴ በመባል ለሚጠሩ ቅዱሳን፣ ለዐርከ ሥሉስ /የአርኬና የመልክአ ቊርባን ደራሲ/፤ ….) የኾኑትና ፤ ጽድቃቸውና ቃልኪዳናቸው እንደ ምድር አሸዋ የበዛው፥ እንደ ሰማይ ከዋክብት ለመቊጠር የሚያስቸግረው ጻድቁ ዐምደ ሥላሴ ዘማኅበረ ሥላሴ ልደታቸውም እረፍታቸውም ነው፡፡ - እኒህ ጻድቅ የተወለዱት በጎጃም(ሸዋም የሚሉ አሉ) ሲኾን፤ የተወለዱትም ሆነ 104ዓመታት ከኖሩ በኋላ ያረፉበት ቀን በመድኀኔ ዓለም ወርኀዊ በዓል በየካቲት 27 ነው፡፡ - ጻድቁ በተለያዩ ገዳማት በአርድእትነትና ሥርዐተ አበው በማጥናትና በመተግበር ከቆዩ በኋላ፤ ምንኩስናን ከአቡነ ተንሥአ ክርስቶስ ዘትግራይ ተቀብለዋል፤ ኋላም ወደ ታላቁ ገዳም ገዳመ ዋሊ (ገዳመ ዋልድባ) ገብተው ከቆዩ በኋላ ወደ ገዳመ አስቄጥስ በመሄድ ለ18 ዓመታት ከቆዩ በኋላ በስተመጨረሻ ምናኔያቸውን በማኅበረ ሥላሴ አድርገዋል፡፡ * በ1616ዓ.ም. ሱስንዮስ 8,000 ክርስቲያኖችን የካቶሊክን ካልተቀበላችሁ ብሎ ጠዳ ላይ በሰየፈ ጊዜ ሳይፈሩና ሳይፍሩ ለሃይማኖታቸው ከተከራከሩና ጠበቃ ከኾኑት መካከል ግንባር ቀደሙ ናቸው፡፡ (ሌሎችም ቅድስት ወለተ ጴጥሮስ፣ እኅተ ጴጥሮስ፣ ፍቅርተ ጴጥሮስ፣ ሐራ ድንግል ምዕመነ ድንግል አብረው ይጠቀሳሉ)፡፡ እነዚህም ቅዱሳን ሐዘናቸውን ወደ ፈጣሪያቸው በማድረሳቸው ሱስንዮስ ምላሱ ተጎልጉሎ ወጣ (ተቀሰፈ)፡፡ -  የሱስንዮስ ልጅ ፋሲልም አባቴን ይፈውሱልኝ ብሎ መልእክትን ላከ፤ ጻድቁ ዐምደ ሥላሴና አባ ምዕመነ ድንግል ዘጩጊ ማርያም ተገኝተው ካቶሊክነቱን ከተወ እሺ ብለው 3ት ሱባኤ ጸልየው ፈወሱት፤ ሱስንዮስም ንሥሐ ገብቶ ቅዱስ ቊርባንን ተቀበለ፡፡ በሰኔ 21 1624ዓ.ም. ‹‹የእስክንድርያ ሃይማኖት ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ይመለስ፥ የሮም ካቶሊክ ሃይማኖት ይፍለስ፥ ልጄ ፋሲል ይንገሥ›› ብለው አዋጅ ነገሩ፤ ልጃቸው ፋሲልንም ጻድቁ ዐምደ ሥላሴ ቅብዓ መንግሥት (አፈዋተ መንግሥት) ቀብተው አነገሡት፤ ንጉሡም ለገዳሙ የእርሻ መሬት የሚሆን ጣቁሳ ላይ 44ት ጉልት ጐለተ፥ የገዳሙንም ስም ‹‹ማኅበረ ሥላሴ›› ብሎ ሰየመው፡፡ - ታላቁ ማኅበረ ሥላሴ ገዳም ቀድሞም ከእርሳቸው በፊት የነበረ ቢኾንም፤ በተለያዩ ዘመናት በጠላት የጠፋ ስለነበረ ዳግመኛ ያስፋፉትና እንደ መሶብ ያስባረኩት ናቸው፤ - ከወለዷቸው አንዱ ዐርከ ሥሉስ ከደረሳቸው አንዱ በኾነው በመልክአ ቊርባን ላይ፤ ‹‹ሰላም ለክሙ ጻድቃነ ዛቲ ዕለት ኵልክሙ፤ ዕድ ወአንስት በበአስማቲክሙ፡፡ ቅዱሳነ ሰማይ ወምድር ማኅበረ ሥላሴ አንትሙ፤ ዝክሩነ በጸሎትክሙ በእንተ ማርያም እሙ፤ ተማኅጸነ ለክርስቶስ ሥጋሁ ወደሙ፡፡ በማለት የደረሱለት ሲኾን፤ በዚህም በየቀኑ በቅዳሴ ላይ ከቊርባን በፊት የማኅበሩን ስም የማይጠራ ቤተ ክርስቲያን የለም፡፡ ፨ ብፁዕ አባ አቡነ ዓምደ ሥላሴ ንብረቱ ገዳም ውስተ ሀቌሁ ቅንአቱ ዘአዲም ያስተጋብእ ጽድቀ ዘእምኵሎሙ ቅዱሳን በጾም ወበጸሎት ሀለወ በክብር ወበሰላም፡፡ /መሐረነ አብ/ /#ዋልድባ_ዋሊ_ገጽ/ #የማኅበረ_ሥላሴ_ገዳም፤ (#የሺዎች_ማኅበር)፤ ፨ ምቅዋመ ሥላሴ፡፡ ፨ስለ ገዳሙ አጠቃላይ ሁኔታ፤ *ገዳሙ የሚገኘው በሀገራችን በመተማ በረሃ ደቡባዊ ክፍል፥ ከጎንደር በስተምዕራብ አቅጣጫ (132 ኪ.ሜ. ርቀት ላይ) ሲሆን፤ ከአ.አ. 901ኪ.ሜ. ርቀት ላይ፤ ከደረቅ ዐባይ ቀበሌ በ4ት ሰዓት የእግር ጕዞ ይገኛል፡፡ የጣቁሳ የቋራና የሱዳን በረሓማው አከባቢዎችም ያዋስኑታል፡፡ *ከፀሐዩ ሐሩር ማየልና ከቆላነቱ የተነሣ ‹‹በደንጊያው ላይ ተልባ ያስቆላል›› እየተባለ የሚነገርለት ነው፡፡ የተለያዩ ዕፅዋትና አራዊት የሚገኙበትም ሲሆን ቦታው በብሔራዊ ደረጃ ጥብቅ ደን ነው፡፡ * የገዳሙ ይዞታ ከ19ሺህ 186 ሄክታር በላይ የሚሸፍን ሲሆን፤ በቦታ ስፋት የሚመስለው ዋልድባ (ዋሊ) ብቻ ነው፡፡ በዚህም ከሃገራችን ገዳማት 2ቱ ታላላቅ ገዳማት እጅግ በጣም ሰፋፊ ይዞታ ያላቸው ገዳማት ናቸው፡፡ * ገዳሙ በ፪ት ትላልቅ ወንዞች (በገንዳ ውኃና ሸንፋ ወንዝ) የተከበበ ነው፡፡ *ገዳሙ በሚገኝበት በረሃ ውስጥ 4ት ተራሮች(አምባዎች) ይገኛሉ፡፡ እነርሱም፤ ድባ(የማኅበረ ሥላሴ ገዳም ያለበት)፣ ከርከመች፣ ኩክቢና ጎርማስ ይባላሉ፡፡ *ገዳሙን በርቀት ሆነው የሚያዋስኑት ታላላቅ ገዳማትም፤ በሰሜን አቅጣጫ ደምጫ፥ በደቡብ ጋንጫ(ዋታሆ አቦ) ናቸው፡፡ *በገዳሙና በአካባቢው ከሚገኙት የተለያዩ ዕጽዋት መካከል (ሰርኪን፥ ሲና፥ የዕጣን ዛፍ/ዋልያ/፥ መቀር፥ ወርካ፥ ክርክራ፥ ሽመል) እና ሌሎችም ልዩ ልዩ ዕጽዋት የሚገኙበት ሲኾን፤ ከዱር አራዊት መካከልም (አንበሳ፥ ነብር፥ አጋዘን፥ ቶራ/ሚዳቋ/፥ ድኩላ፥ አሳማ፥ ጉሬዛ፥ ዝንጀሮ፥ ቀይ ጦጣ፥ የተለያዩ የእባብና የዘንዶ ዝርያዎች) ይገኙበታል፡፡

📖ፍትሐ ነገሥት ምን አለ? ፍትሐ ነገሥት በኢትዮጵያ በሕገ መንግሥትነት ጭምር ለዘመናት ያገለገለ ትልቅ ዋጋ ያለው መጽሐፍ ነው:: ፍትሕ መንፈሳዊና ፍትሕ ሥጋዊ በሚል የተከፈለው ይህ የቤተ ክርስቲያ
📖ፍትሐ ነገሥት ምን አለ? ፍትሐ ነገሥት በኢትዮጵያ በሕገ መንግሥትነት ጭምር ለዘመናት ያገለገለ ትልቅ ዋጋ ያለው መጽሐፍ ነው:: ፍትሕ መንፈሳዊና ፍትሕ ሥጋዊ በሚል የተከፈለው ይህ የቤተ ክርስቲያኒቱ ጥንታዊ ሀብት በሀገራችን ለሕግ ሙያ ፈር ቀዳጅ ሲሆን ዘመናዊው የሕግ ሙያ የሚፈለገውን የሕግ ትንታኔም ጭምር ቀድሞ በመረዳት የራሱ ትርጓሜ ቤት ያለው ጥልቅ የትምህርት ዘርፍ ነው:: በታሪክም የፍትሐ ነገሥት ሊቃውንት ነገሥታቱን በማማከርና በፍርድ ሒደትም ላይ በንቃት በመሳተፍ ሀገር ሲያስተዳድሩ ኑረዋል:: በዚህ የትርጓሜ ትምህርት ቤት ያለፉ ሊቃውንት ወደ ዘመናዊው የሕግ ትምህርት ዘርፍ ሲገቡም መምህራኖቻቸውን የሚቀድሙና የሕጉን አቅጣጫ ቀድመው የሚያስቡ እንደ እሳት የማይጨበጡ ተማሪዎች የሚሆኑት በትርጓሜ ቤቱ ሞረድነት የተሳለ ብሩሕ ሕሊና ስላላቸው ነው:: ◍ የፍትሐ ነገሥትን መንፈሳውያት አናቅጽ የተረጎሙበት ይህ መጽሐፋቸው ለማንኛውም አንባቢ በሚገባ አገላለጽ ከትርጓሜ ቤቱ ጥልቅ ትምህርት በተጨማሪ የራሳቸውን ብሩሕ አተያይና ማስተዋል የሚያሳዩ አስደናቂ ምሥጢራትንና ዘመንን የሚዋጁ መፍትሔዎችን በውብ ብርዕ አስቀምጠውልናል:: ረቂቁን በተመለከትሁ ጊዜ እንዲህ ዘመኑን የዋጀ ሥራ ከሊቃውንት ጎራ መፍለቁን አይቼ "ዘልብየ በጽሐ" (የልቤ ደረሰ) ብዬ ፈጣሪን እያመሰገንሁቀጣዩን ሥራቸውን በናፍቆት እየጠበቅን ፍትሐ ነገሥትን ከጥሩ ምንጭ እንጠጣ እላለኹ። ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ ©መጽሐፉን በግዮን መጻሕፍት  በልዩ ቅናሽ ያገኙታል። #📚 ግዮን መጻሕፍት ለውድ አንባብያን  በDHL እና በEMS መጻሕፍትን ተደራሽ እናደርጋለን። ይደውሉልን !📞፦0913083816 https://t.me/GhionBookStore1623

በቀደምት ጀግኖች አያቶቻችን ታላቅ ተጋድሎ እና መስዋዕትነት እንዲሁም በታላቁ ታሪክ የማይረሳው ንጉሳችን ዳግማዊ አጤ ምንሊክ እና በእቴጌ ጣይቱ ብጡል ብልህ አመራር እና አስተባባሪነት ለተቀዳጀነው አ
በቀደምት ጀግኖች አያቶቻችን ታላቅ ተጋድሎ እና መስዋዕትነት እንዲሁም በታላቁ ታሪክ የማይረሳው ንጉሳችን ዳግማዊ አጤ ምንሊክ እና በእቴጌ ጣይቱ ብጡል ብልህ አመራር እና አስተባባሪነት ለተቀዳጀነው አንፀባራቂው የ፻፳ ወ፱ኛው የአድዋ ድል በዓል እንኳን አደረሳችሁ የሚል መልዕክቴን ሳስተላልፍ በታላቅ ብሔራዊ ኩራት ነው:: ይህ በታሪክ ተመዝግቦ በየአመቱ የምንዘክረው አድዋ ላይ የተቀዳጀነው ድል የኢትዮጵያን ነፃነት ያስከበረ ብቻ ሳይሆን በአፍሪካ የቅኝ ግዛት ቀንበር ተጭኗቸው ሲሰቃዩ ለነበሩ አፍሪካዊያን ወንድም እና እህቶቻችን እንዲሁም በመላው አለም በጭቆና ውስጥ የነበሩትን ጥቁር ህዝቦች ቀና ብለው እንዲሄዱ እና ነፃ እንዲወጡ በወቅቱ ታላቅ መነቃቃትን የፈጠረ ገናና የጥቁር ህዝቦች ድል ነው። የዘንድሮውን የ፻፳ ወ፱ ኛው የአድዋ ድል በአል ስናከብር ሀገራችን ኢትዮጵያ ላለፉት ቀላል ለማይባሉ አመታት አንድነቷን አስጠብቃ ወደ ፊት እንዳትራመድ ሰቅዞ የያዛትን ተከታታይ የብሔር ፖለቲካ አዙሪት እንደ ሀገር እና እንደ ህዝብ ያስከፈለንን እና እያስከፈለን ያለውን ዋጋ ግምት ውስጥ በማስገባት ካለንበት ውስብስብ እና እጅግ ኋላቀር የዘር ፖለቲካ ለመውጣት ከመቼውም ጊዜ በላቀ አንድነታችንን አስተባብረን የህልውናችን መሰረት የሆነችው እናት ሀገራችንን ለማዳን በንቃት መቆም ይጠበቅብናል። ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር! ግዮን መጻሕፍት

📖ኰኲሐ ሃይማኖት 【ወጣት ተመልከት እንዳትሳሳት】 ✍️...በል ደኅና ኹን! አንተ፤ ዕውሩን ዐይናማ ነህ ቢሉት ዐይናማ ላይሆን፣ የተሰበረውንም ደኅና ነህ ቢሉት ደኅና ላይሆን፣ የንብላውን ሕግ እውነተ
📖ኰኲሐ ሃይማኖትወጣት ተመልከት እንዳትሳሳት】 ✍️...በል ደኅና ኹን! አንተ፤ ዕውሩን ዐይናማ ነህ ቢሉት ዐይናማ ላይሆን፣ የተሰበረውንም ደኅና ነህ ቢሉት ደኅና ላይሆን፣ የንብላውን ሕግ እውነተኛ ለማስመሰል በጻፍከው ስሕተት የምእመናንን ልቡና ይሆንን? አይሆንን? ከሚል ጥርጥር ላይ ስለጣልከው እኔም “ይነግረው ያጣ ያሙኝ አይመስለውም” እንደሚባለው ተረት ዝም ብንልህ ጥፋትህ እየቀጠልክ ስለሔድክ ለምእመናን ነገርህ እውነት ይመስላቸዋል በማለት “ገሥጽ ወተዛለፍ” ያለው ቃል እያጽናናኝ (፪ጢሞ. ፬÷፪) መልሱን ስጽፍልህ ያመላለሱ ዘዴ እያስገደደኝ በማደርገው ንግግር አንዳንድ ላይ “ባርክዎሙ ለእለ ይረግሙክሙ” የተባለው ትእዛዝ ሳይፈርስብኝ የቀረ አይመስለኝምና የሰውን መዳኑን እንጂ መጎዳቱን የማይወድ ቸሩ አምላክ ኹላችንንም ይቅር ብሎ በኢየሩሳሌም ሰማያዊት ያገናኝን፡፡ አሜን፡፡ [ከመጽሐፉ የውስጥ ገጾች የተወሰደ] 🫧መልአከ ብርሃን አድማሱ ጀንበሬ ሊቅ ረቂቅ የሃይማኖት አርበኛ መኾናቸው ዛሬም በመጻሕፍቶቻቸው፤ ሲወሳ፤ ሲመሰከር ፤ትውልድ ሲሻገር ይኖራል። በእቅበተ እምነት ዙሪያም ይኽ ነው የማይባል አሻራ አኑረውልናል ።ከድንቅና ዘመን ተሻጋሪ ስራዎቻቸው መካከል ለኘሮቴስታንቱ ዘመንፈስ ቅዱስ አብርሃ  ምላሽ የሰጡበት ኰኲሐ ሃይማኖት የተሰኘው መጽሐፋቸው በትህትና የተለበጠ በእውቀት የተጠረዘ መጽሐፍ መኾኑ መስካሪ የማያሻው እንዲኹም በዚኽ ዘመን ላለው የኑፋቄ ትምህርት እና ግርታ ውስጥ እየወደቀ ላለው ወጣት አይነተኛ መፍትሔ ይኽ መጽሐፍ እንደኾነ መገንዘብ አይከብድም። ©መጽሐፉን በግዮን መጻሕፍት  በልዩ ቅናሽ ያገኙታል። #📚 ግዮን መጻሕፍት ለውድ አንባብያን  በDHL እና በEMS መጻሕፍትን ተደራሽ እናደርጋለን። ይደውሉልን !📞፦0913083816 https://t.me/GhionBookStore1623

📖ኰኲሐ ሃይማኖት 【ወጣት ተመልከት እንዳትሳሳት】 ✍️....በል ደኅና ኹን! አንተ፤ ዕውሩን ዐይናማ ነህ ቢሉት ዐይናማ ላይሆን፣ የተሰበረውንም ደኅና ነህ ቢሉት ደኅና ላይሆን፣ የንብላውን ሕግ እውነ
📖ኰኲሐ ሃይማኖትወጣት ተመልከት እንዳትሳሳት】 ✍️....በል ደኅና ኹን! አንተ፤ ዕውሩን ዐይናማ ነህ ቢሉት ዐይናማ ላይሆን፣ የተሰበረውንም ደኅና ነህ ቢሉት ደኅና ላይሆን፣ የንብላውን ሕግ እውነተኛ ለማስመሰል በጻፍከው ስሕተት የምእመናንን ልቡና ይሆንን? አይሆንን? ከሚል ጥርጥር ላይ ስለጣልከው እኔም “ይነግረው ያጣ ያሙኝ አይመስለውም” እንደሚባለው ተረት ዝም ብንልህ ጥፋትህ እየቀጠልክ ስለሔድክ ለምእመናን ነገርህ እውነት ይመስላቸዋል በማለት “ገሥጽ ወተዛለፍ” ያለው ቃል እያጽናናኝ (፪ጢሞ. ፬÷፪) መልሱን ስጽፍልህ ያመላለሱ ዘዴ እያስገደደኝ በማደርገው ንግግር አንዳንድ ላይ “ባርክዎሙ ለእለ ይረግሙክሙ” የተባለው ትእዛዝ ሳይፈርስብኝ የቀረ አይመስለኝምና የሰውን መዳኑን እንጂ መጎዳቱን የማይወድ ቸሩ አምላክ ኹላችንንም ይቅር ብሎ በኢየሩሳሌም ሰማያዊት ያገናኝን፡፡ አሜን፡፡ [ከመጽሐፉ የውስጥ ገጾች የተወሰደ] 🫧መልአከ ብርሃን አድማሱ ጀንበሬ ሊቅ ረቂቅ የሃይማኖት አርበኛ መኾናቸው ዛሬም በመጻሕፍቶቻቸው፤ ሲወሳ፤ ሲመሰከር ፤ትውልድ ሲሻገር ይኖራል። በእቅበተ እምነት ዙሪያም ይኽ ነው የማይባል አሻራ ያስቀመጡ መኾናቸው የአደደባባይ ምስርጢር መኾኑ አይረሴ ነው  ።ከድንቅና ዘመን ተሻጋሪ ስራዎቻቸው መካከል ለኘሮቴስታንቱ ዘመንፈስ ቅዱስ አብርሃ  ምላሽ የሰጡበት ኰኲሐ ሃይማኖት የተሰኘው መጽሐፋቸው በትህትና የተለበጠ በእውቀት የተጠረዘ መጽሐፍ መኾኑ መስካሪ አያሻውም ። ©መጽሐፉን በግዮን መጻሕፍት  በልዩ ቅናሽ ያገኙታል። #📚 ግዮን መጻሕፍት ለመላው ከሀገር ውጪ እና ሀገር ውስጥ ለምትገኙ አንባብያን  በDHL እና በEMS እንዲሁም የ Delivery አገልግሎት በመስጠት መጻሕፍትን ተደራሽ እናደርጋለን። ይደውሉልን !📞፦0913083816 https://t.me/GhionBookStore1623

💧ዜና መጽሐፍ 【አዲስ መጽሐፍ ገበያ ላይ】 📖ነገረ መላዕክት ቅዱሳን መላእክት በነገረ ድኅነት (በክርስትና) ከፍተኛ ሱታፌ ያላቸው የእግዚአብሔር ናቸው፡፡ ሰማያውያን ፍጥረቱ ስለተፈጥሮአቸው፧ አገል
💧ዜና መጽሐፍ 【አዲስ መጽሐፍ ገበያ ላይ】 📖ነገረ መላዕክት   ቅዱሳን መላእክት በነገረ ድኅነት (በክርስትና) ከፍተኛ ሱታፌ ያላቸው የእግዚአብሔር ናቸው፡፡ ሰማያውያን ፍጥረቱ ስለተፈጥሮአቸው፧ አገልግሎታቸው፧ _ ኃይላቸው፧ _ ቅድስናቸው፧ ምስጋናቸው፧ አማላጅነታቸው፥ ረዳትነታቸው፥ ወዘተ. . . በብሉይ ኪዳን፥ በሐዲስ ኪዳንም ሆነ በአዋልድ መጻሕፍት በብዙ ተጽፎ ይገኛል። ነገር ግን በዘመናችን ብዙ ትኩረት ካልተሰጣቸው ርዕሶች አንዱ "ነገረ መላእክት" ነው እላለሁ፡፡ ይህም ክፍተት ቁጥሩ ጥቂት የማይባል ሰው ስለጉዳዩ የመሰለውን እንዲያስተምር በር ሳይከፍት አልቀረም። ፈቃደ እግዚአብሔር ሁኖ እነሆ ይህንን ክፍተት ይሞላል ብዬ የማምንበት መጽሐፍ ተዘጋጅቷል። መጽሐፉ ስለ ንጹሐን መላእክት እና ተያያዥ ጉዳዮች በከፍተኛ ጥንቃቄና ማስተዋል ከመዘጋጀቱ ባሻገር፥ በየዘመናቱ እየተነሱ ለአማኞች ፈተና ለሆኑ ርዕሶች ኦርቶዶክሳዊ መልስን ይዟል። ከዚህ በፊት ባዘጋጇቸው መጻሕፍት ያልተዳሰሱ ይዘቶች ላይ ትኩረት እንደሚያደርጉ የተመለከትናቸው መምህር ዲበ ኵሉ ሰንደቄ፤ ንባብ ከሐተታ፡ ትርጓሜ ከምስጢር፧ ትምህርትንም ከእዝናት (ሞክር) አሰናስለው ይህንን የመሰለ መጽሐፍ ስለጻፉልን እያመሰገንኹ፧ አንብበን እንጠቀምበት ዘንድ በአክብሮት እጋብዛለሁ። መልካም ንባብ! [ዲያቆን ዮርዳኖስ አበበ] ታላቁን ጾም በንባብ ለማሳለፍ አይነተኛ ምርጫ እነኾ ፦በጣም በሚገርም ይዘት በልዩ አጻጻፍ በጥልቅ መረዳት እንዲኹም  ለማንበብ በሚያጓጓ ኹኔታ #መምህር ዲበኩሉ ሰንደቄ  ያዘጋጁልንን #ይኽን መጽሐፍ በግዮን መጻሕፍት በልዩ ቅናሽ ያገኙታል ። #📚 ግዮን መጻሕፍት ይደውሉልን !📞፦0913083816 https://t.me/GhionBookStore1623