ru
Feedback
The Ethiopian Evangelical Church Mekane Yesus - EECMY

The Ethiopian Evangelical Church Mekane Yesus - EECMY

Открыть в Telegram

The Ethiopian Evangelical Church Mekane Yesus (EECMY) is a national Lutheran church with more than 10 million members.

Больше
3 318
Подписчики
+224 часа
+277 дней
+10230 день
Архив постов
የኢ/ወ/ቤ/ክ መካነ ኢየሱስ - የሴቶች አገልግሎት የስራ ሂደት የፀሎትና የወንጌል አገልግሎት ንቅናቄ መርሃ ግብር በዋና ጽሕፈት ቤት ዛሬ አካሂዷል። በመርሃ ግብሩም ላይ ከማኀበራነ ምዕመናን የመጡ ሴት መሪዎች እና ቄሶች ተገኝተዋል። በማጠቃለያውም ሴት መሪዎቹ የሴቶችን የፀሎትና የወንጌል አገልግሎት በየማኀበራነ ምዕመናቸው ለመቀቀስቀስ እና ከማህበረ ምዕመናን እስከ ሀገር አቀፍ የሚካሄድ የፀሎት አገልግሎት ለመዘርጋት ወስነዋል። * * * * * * * EECMY - Women Ministry Department conducted prayer and mission mobilization program today at the central office main Hall. On the program women leaders and pastors from different congratulations of the Central Ethiopia Synod has attended. When finalizing the program, the leader agreed to revive women’s prayer and mission ministry in their individual congregations, and devise a prayer ministry that stretch from congregations to the nation level.

የኢትዮጵያን ወንጌላዊት ቤተ ክርስቲያን መካነ ኢየሱስ ፕሬዚዳንት ቄስ ዶ/ር ዮናስ ይገዙ ዛሬ ከሰዓት በኋላ ጋምቤላ ሲደርሱ በምዕመናን ደማቅ አቀባበል የተደረገላቸው! * * * * * * * The Ethiopian Evangelical Church Mekane President, Rev Dr Yonas Yigezu, received a warm welcome from believers when they arrived at Gambela this afternoon!

የአስተምህሮ እና የምዕመናን ጥበቃ ስልጠና ተሰጠ × × × × “አስተምህሮ እና የምዕመናን ጥበቃ” በሚል አርዕስት በአዲስ አበባ እና ሸገር ከተሞች ለሚገኙ አፋን ኦሮሞ ተናጋሪ የአዲስ አበባ እና ማዕከላዊ ኢትዮጵያ ሲኖዶስ ማኅበራነ ምዕመናን ቄሶች፣ ወንጌላዊያን እና የቤተ ክርስቲያን ሽማግሌዎች ከጥር 14–15/2016 ዓ.ም ጉለሌ በሚገኘው የፊንፊኔ ኦሮሞ ማህበረ ምዕመናን ለሁለት ቀናት ስልጠና ተሰጥቷል። የቤተ ክርስቲያኒቱም ምክትል ፕሬዚዳንት ቄስ ዶ/ር ታሪኩ ቶሎሳ በስልጠናው ላይ በመገኘት ለአገልጋዮች ቃለ እግዚአብሔር አስተምረው፣ ሰላምታ በማቅረብ የቤተ ክርስቲያኒቱን መልዕክት አስተላልፈዋል። በስልጠናው ተሳታፊ የሆኑትም አገልጋዮች በነበራቸው ውይይት ጊዜ በከፍተኛ የትምህርት ተቋማት እና በየደረጃው የሚገኙ የክርስቲያን ተማሪ ህብረቶች ለስህተት ትምህርት እና ልምምዶች ተጋላጭ ስለሆኑ ማኅበራነ ምዕመናኑ ልዩ ትኩረት ሰጥተው መስራት በሚችሉባቸው ስልቶች ዙሪያ መክረዋል። “የስህተት ትምህርት በመጽሐፍ ቅዱስ ብርሐን ሲፈተሽ” በሚል ርዕስ በቤተ ክርስቲያኒቱ የወንጌል ተልዕኮና ቲኦሎጂ ዲፓርትመንት የተዘጋጀ መጽሐፍ ለስልጠናው ተሳታፊዎች እንዲቀርብ ተደርጓል። Leenjiin "Barsiisaafi Eegumsa Amantootaa" irratti Xiyyeeffatu Kenname × × × × Mata duree "barsiisaa fi eegumsa amantootaa" jedhu irratti Luboota, H/Wangeelaa, Jaarsolii fi tajaajiltoota Oromoo Waldoota Amantootaa Magaalaa Finfinnee fi Shaggar keessa jiraniif Sinoodosii Giddu Galeessa Itiyoophiyaa fi Sinoodosii Addis Ababaa irraa kan waltti qabamaniif leenjiin guyyaa lamaa (Amajjii 14 fi 15, bara 2016) Gullalleetti kan argamu Waldaa Amantoota Oromoo Finfinneetti kennameeraaf. Itti A/Pirezedaantii Waldatti Lubni Dr. Taarikuu Tolosaa leenjii kana irratti argamuudhaan tajaajiltoota kana dubbii Waaqayyoo barsiisanii, nagaa gaafachuudhaan ergaa Waldaa Kiristiyaanaa dabarsaniiru. Tajaajiltootni lernjicha irratti hirmaatan yeroo maree isaanii keessatti haala yeroo Ammaa barattootni sadarkaa ol-aanaa irratti baratan keessa jiranii fi tokkummaa barattoota Kiristiyaanaa Oromoo barsiisa sobaa fi shakkallii hin barbaachifnee saaxilamaa waan jiraniif Waldaan Amantootaa xiyyeeffannaa godhanii akka irratti hojjetan, tajaajila mucaalii fi karaa ittiin dargaggootaa jabeessuudanda'an bu'uura godhatanii akka hojjetan irratti maree bal'aa geggeessaniiru. "Barsiisni sobaa ifaa Wangeelaatiin Yeroo Sakkatta'amu" mata duree jedhu irratti Dippaariimentiin Ergaa Wangeelaa fi Ti'ooloojii Waldatti leenjicha qopheessee hirmaattotaaf dhiyeessera. Doctrine and believers' retention training was given × × × × Under the title of “Doctrine and believers retention” a two days fruitful training was given for Afaan Oromo speaking congregations Pastors, Evangelists and Elders within the Addis Ababa and Central Ethiopia Synod from January 23-24, 2024 at Finfine Oromo Congregation. The church’s vice president, Rev Dr Tariku Tolessa, conveyed the church’s message after sharing the word of God with participants. During discussion times, the ministers consulted on the possible strategies to counter false teachings that are entertained and practiced in the higher educational institution, christian students' fellowships. A book that was prepared by the Department of Mission and Theology, under the title "False Teaching examined under the Light of Scripture," was also made available.

የሚስዮን ቀን ጥር (2).png2.87 MB

የሚስዮን ቀን ጥር (2).png3.05 MB

የኢ/ወ/ቤ/ክ/መ/ኢየሱስ በደቡብ ኢትዮጵያ የሮቦት ሲኖዶስ በገረሴ ዙርያ ወረዳ በተፈጥሮ አደጋ ጉዳት ለደረሰባቸው አርሶ አደሮች ድጋፍ አደረገ። ** የኢ/ወ/ቤ/ክ/መ/ኢየሱስ በደቡብ ኢትዮጵያ የሮቦት ስኖዶስ ፕረዝዳንት ቄስ ከተማ ካምሌ እና ዋና ፀሐፊ ቄስ ደመቀ ጩራቀ በገረሴ ዙርያ ወረዳ ግብርና ልማት ጽ/ቤት ተገኝተው ለገረሴ ዙርያ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ካሳሁን ካማ በተፈጥሮ አደጋ ጉዳት ለደረሰባቸው 28 አባወራ አርሶ አደሮች ድጋፍ አደርጓል። አቶ ካሳሁን ካማ ስረከቡ እንደተናገሩት ስኖዶሱ ገና የተመሠረተ ለጋ ስኖዶስ እንደመሆኑ ድጋፍ አልጠየቅንም። ነገር ግን ፈጣሪ አሳስቦአቸው ይህንን በጎ ተግባር ድጋፍ ስላደረጉ በፈጣሪና በወረዳው ህዝብ ስም አመሰግናለሁ ብለዋል። ለድሃ የሰጠ ለእግዚአብሔር ያበድራል እንደሚባለው የስኖዶሱ መልካም ተግባር እኛ እርስ በርሳችን እንድንረዳዳና እንድንደጋገፍ መልካም ተሞክሮ ነው ብሏል። ስኖዶሱ በዚህ ብቻ ሳይሆን ለበርካታ መታከም ለማይችሉ የማህበረሰብ ጤና መድህን ፈንድ በመግዛት እንደዚሁም ለተቸገሩት በመርዳት ከማህበረሰቡ ጎን የቆመ ስለሆነ ለቀጣይ በማናቸውም ሁኔታ ከስኖዶሱ ጎን በመቆም የወረዳው መንግስት ተደጋግፈው እንደሚሠሩ ተናግሯል። ዶ/ር ቦርሴ ቦታ የገረሴ ዙርያ ወረዳ ግብርና ልማት ጽ/ቤት ኃላፊ በበኩላቸው የገረሴ ዙርያ ወረዳ የመሬት አቀማመጥ ወጣ ገባ በመሆኑ ለተፈጥሮ አደጋ ተጋላጭ በመሆኑ በርካታ አርሶ አደሮችን ለጉዳት እየተዳረጉ መሆኑን ተናግሯል። ባለፈው ወቅቱን ባልጠበቀ ዝናብ አኳያ በተፈጥሮ ናዳ አደጋ የደረሰባቸው ከጋርባንሳ ሦሮጌ፣ ከጋርባንሳ ካርቼ፣ ከመሌ ጋጉሌ እና ካምኣለ ባርኤ ኦሮ ቀበሌ ለመጡ 28 አባወራ አርሶ አደር ቤተሰቦች 14 ኩንታል የምግብ እህል ስኖዶሱ ድጋፍ ማድረጋቸውን በመግለጽ አመስግኗል። በወረዳው በተፈጥሮ አደጋ እና አየር መዛባት ምክንያት ለችግር የተጋለጡ በርካታ አርሶ አደሮች መኖራቸውን ኃላፊው ተናግረው ስኖዶሱ ከወንጌል ሥራ ጎን ለጎን በመንግሥት ልሸፈኑ ያልቻሉ በርካታ የልማት ሥራዎችን ከጎናችን ሆነው እንዲደግፉ ስሉ ጥሪ አቅርቧል። የኢ/ወ/ቤ/ክ/መ/ኢየሱስ በደቡብ ኢትዮጵያ የሮቦት ስኖዶስ ፕረዚዳንት ቄስ ከተማ ካምሌ በበኩላቸው ስኖዶሱ አድስ ነው፣ ቀጣይ ከወረዳ፣ ከዞንና ከክልሉ መንግሰት ጋር አብረን ለመሥራት ዕቅድ አለን ብሏል። እስከአሁን ባለን ሂደት ከወረዳም ይሁን ከቀበሌ መንግስት ለእኛ ሥራ እንቅፋት የሆነ ነገር የለም በማለት ቀጣይ አብረን ተባብረን ለመሥራት እግዚአብሔር እንዲረዳን እንለምናለን ስሉ አስታወቋል። ገረሴ፣ ጥር 8/2016 ዓ.ም(የገረሴ ዙሪያ ወረዳ መንግስት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት) መረጃውን ከየገረሴ ዙርያ ወረዳ ኮሙኒኬሽን የፌስቡክ ገፅ አገኘነው።