cookie

Мы используем файлы cookie для улучшения сервиса. Нажав кнопку «Принять все», вы соглашаетесь с использованием cookies.

avatar

Abu hatim Abduselam Aselefiy

ትክክለኛው እስላማዊ አስተምህሮ ከቁርአንና ከሐዲስ ከደጋግ ቀደምቶች አረዳድ ከታማኝ ዑለሞች ንግግር የሚሰራጭበት ቻናል ነው።

Больше
Рекламные посты
1 305
Подписчики
-424 часа
+177 дней
+4330 дней

Загрузка данных...

Прирост подписчиков

Загрузка данных...

👉 ከተውሒድ ዳዒነት ወደ ባህል አስተዋዋቂነት ዝቅጠት በ30 የእንቅልፍ ክኒን ደንዝዘው ከሱፍይ ሙሪድ የባሱት በፊት ወደ ተውሒድ እየተጣሩ ሽርክን በዝርዝር ያስጠነቅቁ የነበሩ የነሲሓ ዱዓቶች ከዝቅታቸው የተነሳ የዳዕዋው ብርሀን ጠፍቶባቸው ወደ ባህል አስተዋዋቂነት ተሸጋግረዋል ። አምና አንዱ ዳዒያቸው በዒደል አድሓ የጉራጌን ባህል ሲያስተዋውቅ ነበር ። ዘንድሮ ደግሞ ሌላኛው የስልጤ ባህል አስተዋውቆላቸዋል ። በጣም የሚገርመው የውመንነሕር የእርድ ቀን በጉራጌም በስልጤም ከዑድሒያ እርድ ጋር በተገናኘ ሽርክ ተንሰራፍቶ ነው ያለው ። በአብዛኛው ማህበረሰቡ በሬ ወይም ወይፈን ነው የሚያርደው ። የሚታረደው ከብት ለእርድ ሲቀርብ አብዛኛው ቦታ ሁሉም ተሰብስበው ሽማግሌዎች የከብቱን ሻኛ እያሻሹ ዱዓእ ያደርጋሉ ። ዱዓኡ አላህን በመለመን ብቻ ቢሆን ኖሮ በዛ መልኩ መደረጉ ቢዳዓ ነው እንል ነበር ። ነገር ግን የሚለመነው በየአካባቢው የሚታመንበት ሸይኽ ወይም ወልይ ነው ። እንዲህ አይነት ሙንከር በስፋት በተንሰራፋበት ሀገር ላይ ነው የነሲሓ ዳዒዮች ባጀት ተመድቦላቸው ባህል የሚያስተዋዉቁት ። የዘንድሮ አስተዋዋቂ እንሰት ወደ ቆጮነት እንዴት እንደሚቀየርና አዘገጃጀቱን ነበር ያስተዋወቀላቸው ።‼ ከወረዱ አይቀር መዝቀጥ እንዲህ ነው ። ቁርኣንና ሐዲስ ለትውልድ አደርሳለሁ ወደ ተውሒድ እጣራለሁ ከሽርክ አስጠነቅቃለሁ የሚል አካል ገጠር ገብቶ ስለቆጮ አዘገጃጀት ለከተማው ማህበረሰብ በዒድ ቀን መዝናኛ ብሎ ያቀርባል ? ይህ ነው የሰለፎችን መንገድ የመተው መጨረሻው ። https://t.me/bahruteka
Показать все...
ባህሩ ተካ - Bahiru Teka

السلام عليكم ورحمة الله وبركاته قناة رسمية لمحاضرات ودروس الأستاذ بحرو تكا (أبو عبيدة) الدعوة السلفية በአላህ ፈቃድ በዚህ ቻናል የአማርኛ ትምህርቶችን እንዲሁም አጫጭር የአረብኛና የአማርኛ ፁሁፎችን እንለቃለን ከዚህ ቻናል ውጪ ከሌላ ቦታ ተወስደው ለሚለቀቁ ኦዲዮዎች እውቅና አልሰጥም

https://telegram.me/bahruteka

Фото недоступноПоказать в Telegram
السلام عليكم ورحمة الله وبركاته የክረምት ኮርስ  ምዝገባ ማስታወቂያ መድራሳችን አል-ኢስላሕ እንደተለመደው ልጆች የእረፍት ጊዜያቸውን ስለዲናቸው በማወቅና እና በመማር እንዲያሳልፉ የ (2) የሁለት ወር የክረምት ኮርስ ስላዘጋጅ ልጆች የእድሉ ተጠቃሚ እንዲሆኑና ኢስላማዊ ግዴታውን ለመወጣት ዝግጅቱን አጠናቆ ይጥብቃችኋል፡፡ እነሆ ከዚህ በታች የተዘረዘረውን መስፈርት የምታሟሉ ተማሪዎች መመዝገብ ትችለችሁ ቅድመ ስፈርት 1.      ቁርአን ማንበብ የሚችል/ትችል 2.     ኪታብ መቅራት የጀመረ/ረች 3.     እድሜ ከ10 አመት በላይ 4.     መልካም ስነ-ምግባር ያላው/ላት 5.     የተቀመጠውን ክፍያ መክፍል የሚችል/ትችል 6.     ከጠዋቱ 2፡30 እስከ 9፡30 መቆየት የሚችል/ትችል   የምዝገባ ጊዜ እና ሰአት :-  ከሰኔ 19 እስከ 28, 2016 ከጠዋቱ 3:00 - 12:00 ትምህርቱ የሚሰጠው፡- ከሐምሌ 1, 2016 ጀምሮ የሚሰጠው የትምህርት አይነት :- 1.     ቁርአን 2.     አቂዳ 3.     ሐዲስ 4.     ፊቅህ   ማሳሰቢያ፡- 1.     ከላይ የተጠቀሰውን መስፈርት የሚያለማሉ ተማሪዎች ወላጆች በአካል በመቅረብ ወይም  በተቀመጠው አድራሻ በመደወል ማስመዝገብ ይችላሉ:: 2.     ትምህርቱ የሚሰጠው እስከ 9፡30 ስለሆነ ለምሳ መውጣት ስለማይቻል ተማሪዎች ምሳ ይዘው መምጣት ይኖርባቸዋል፡፡    ለበለጠ መረጃ፡ በስልክ ቁጥር፡ 09-51-51-83-83 በመድረሳው ቴሌግራም ቻናል፡ https://t.me/medresetulislah
Показать все...
Фото недоступноПоказать в Telegram
السلام عليكم ورحمة الله وبركاته አስደሳች ዜና የወንድ ተመላላሽ ቁርአን ሒፍዝ ምዝገባ ማስታወቂያ እነሆ መድራሳችን አል-ኢስላሕ  ባለፉት አመታት ለሴቶች ብቻ ሲሰጥ ነበረው ተመላላሽ ቁርአን ሒፍዝ  ወደ ወንዶች በማሰፋት በአላህ ፍቃድ ልጆች በቁርአን እና በዲናቸው ብቁ ሆነው ዲናቸው በእውቀት የተማሰረተ እንዲሆን የእውቀት መሰረት በሆነው  ቁርአን አንፆ ሊያወጣ ዝግጅቱ አጠናቆ ይጠብቃችኃል፡፡ ከዚህ በታች የተዘረዘረውን መስፈርት የምታሟሉ ተማሪዎች መመዝገብ የምትችሉ መሆኑን ያሳውቃል፡፡ ቅድመ ስፈርት 1.      ቁርአን ማንበብ የሚችል ወይም የጨረሰ 2.     እድሜ ከ13 አመት በላይ 3.     መልካም ስነ-ምግባር ያላው 4.     የተቀመጠውን ክፍያ መክፍል የሚችል 5.     ከጠዋቱ 2፡30 እስከ 9፡30 መቆየት ትችል 6.     ቁርአኑ ሐፍዞ ጨርሶ እስኪወጣ ድረስ በተጠቀሰው ሰአት አመቱ በሙሉ መቀጠል የሚችል   የምዝገባ ጊዜ እና ሰአት :-  ከሰኔ 22 እስከ 30, 2016 ከጠዋቱ 3:00 - 12:00   ማሳሰቢያ፡- 1.    ከላይ የተጠቀሰውን መስፈርት የሚያሟሉ ተማሪዎች ወላጆቻቸው በአካል በመቅረብ ማስመዝገብ ይችላሉ፡፡ 2.    ለምሳ መውጣት ስለማይቻል ተማሪዎች ምሳ ይዘው መምጣት ይኖርባቸዋል፡፡  3.    የሰነ-ምግባር ችግር ያለበት ተማሪ መቀጠል እንደማይችል ከወዲሁ ለማሳወቅ እንወዳለን፡፡   የምንቀበለው ውስን ተማሪ ስለሆነ ኮታው ከሞላ ስለማንቀበል በተቀመጠው ጊዜ ያስመዝግቡ!!!     ለበለጠ መረጃ፡ በስልክ ቁጥር፡ 09-51-51-83-83 በመድረሳው ቴሌግራም ቻናል፡  https://t.me/medresetulislah
Показать все...
🔸 አል-ፈታዋ በወልቂጤ 🔊 “መንሀጅ ነክ እና ቤተሰብ ጋር በተያያዘ የተጠየቁ ጥያቄዎች” 🎙በሸይኽ አቡ ዐብዲል ሀሊም ዐብዱል ሀሚድ አል-ለተሚይ (ሐፊዘሁላህ) https://t.me/abdulham/2295
Показать все...
አል’ፈታዋ_በወልቂጤ_ዳሩል’ሁዳ_የሸይኽ_ሙባረክ_አል_ወልቂጢይ_መድረሳ.mp312.40 MB
ሰምንተዊ የቁሪአን ተፊስር ልጀምር ነዉ ገባ        ገባ              ገባ                 በሉ https://t.me/abuhatimaselefiy
Показать все...
Abu hatim Abduselam Aselefiy

ትክክለኛው እስላማዊ አስተምህሮ ከቁርአንና ከሐዲስ ከደጋግ ቀደምቶች አረዳድ ከታማኝ ዑለሞች ንግግር የሚሰራጭበት ቻናል ነው።

👍 6
ዳዕዋ ዳዕዋ ዳዕዋ 📢 ‼️ አስላሙ አለይኩም ወረህመቱላሂ ወበረካትሁ ውድና የተከበራችሁ የሱና እአህቶችና ወንድሞች በያላችሁበት ቦታ ሁናችሁ ያአላህ እዝነቱና በረከቱ አይለየን አይለያችሁ በሱናም ላይ አላህ ያፅናን ያፅናችሁ እንኳን ለ (1445) ኢደል አድሃ በአል በሰላም አደረሰን አደረሳችሁ እነሆ አስደሳች ዜና ይዘን ዘልቀናል የፊታችን እሁድ ማለትም ሰኔ ቀን /16/2016/ታላቅ የዳዕዋ ዝግጅት ስላለን በተባለው ቦታ በጧት በመገኝት የዳዕዋው ተቋዳሽ ትሆኑ ዘንድ ታድማችኋል 🔄ብርቅየ ተጋባዥ እንግዶቻችነን ስናሳውቃችሁ በታላቅ ደስታ ነው ↘️1 ሸይኽ ሙሐመድ ሃያት ከሃራ ↘️2 ሸይኽ ሁሴን ከረም     ከሃራ ↘️3 ሸይኽ ሙሃመድ ሲራጅ ከሃሮ ↘️4 ሸይኽ ሁሴን አባስ  ከጉራ    ወርቄ ↘️5 ኡስታዝ ኑራድስ           ከሃራ ↘️6 ኡስታዝ ኑረድን            ከመርሳ ↘️7 ኡስታዝ አብዱረህማን  ከመርሳ የሚጠቀሱትና የሚዳሰሱት እርዕሶች በሰአቱ በቦታው ላይ የሚነገሩ ሲሆን ጥሪውን አስታውሱ እንዳትረሱ 👁‍🗨የዳዕዋው ባታ አጆሜዳ ሲሆን ከጃራ ከፍ ያለች ከድሌሮቃ ዝቅ ብላ የምትገኝ የገጠር አድስ ከተማ ናት  ወረዳ ሃብሩ ቀበሌ ( 024) በድጋሜ አጆ ሜዳ 🕑 የሚጀመርበት ሰአት ከጧቱ ሁለት 2:00 ሰአት ጀምሮ እስከ 10:00 ሰአት ድረስ የዘልቃል የኦናይን ስርጭትም ስለሚኖረን ሳትርቁ ጠብቁን 🕌 መስጅደ ፉርቃን አጆ ሜዳ ሰኔ/ቀን/16/2016/1445/ዓ/ሂ https://t.me/hussenhas
Показать все...
አቡ አዒሻ العلم نور

የዚህ ቻናል ዋና አላማ ሱናን ማንገስ ሽርክን ማርከስ ነው!! የሱና መሻይኮችና የሱና ዳዒዎች የሚላክበት የዳዕዋ የደርስ ሴንተር ቻናል ነው ሐሳብ አስተያትን ያለምንም ጥበት እንቀበላለን ቅድሚያ ለተውሂድ በተግባር

👍 2
🚫 እህቶችን መሰረት ያደረገ የሿሿ ጥቃት ሿሿ ማለት የሚታወቀው በአንድ ሚኒ ባስ ታክሲ ላይ ከስብእና የወጡ ሴቶች የሽማግሌ ቀላሎችና ወሮበላ ወጣቶች ተሰባስበው የሶስት ሰው ቦታ ከፊት ከመሀልና ኋላ ክፍት አድርገው ከተሳፋሪ ውስጥ የሚፈልጉትን ሲያገኙ አንድ ሰው ብቻ ብለው ያስገባሉ ። በክብር ቦታ የተለቀቀለት በማስመሰል የሚፈልጉት ቦታ እንዲቀመጥ ይደረጋል ። ያ ቦታ ማለት የተዋጣለት ፈታሽ የተዘጋጀበት ቦታ ነው ። ፈታሹ ስራውን ሲጀምር ውስጥ ያለው የውርጋጦች ስብስብ ረብሻ ይፈጥራል ። ሹፌሩ መኪናውን የሚገለብጠው ይመስላል ። በዚህ መሀል ግራ በመጋባት ምን እንደተፈጠረ ሳይገባው በፍተሻው የተራቆተው እንግዳ ተሳፋሪ እንዲወርድ ይደረጋል ። ወደራሱ ሳይመለስ ግራ እንደተጋባ ቆሞ ታክሲውን ያያል ። ታክሲው ትቶት ይፈተለካል ። ወደራሱ ሲመለስና ኪሱን ሲፈትሽ ተራቁቷል ። ለመደወል ስልክ የለም ለመሳፈር ሳንቲም የለም ። የዚህን ጊዜ ነው የድራማው ሚስጢር የሚገባው ። ይህ ነው ከዚህ በፊት በሿሿ የሚታወቀው ። የአሁኑ ሿሿ የረቀቀና ከውጭ የመጡ ወይም የውጭ ሀገር እድል ያገኙ እህቶችን መሰረት ያደረገ ነው ። በአብዛኛው የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አካባቢና እንዲሁም ኤምባሲዎች አካባቢ ነው የወጥመዱ አካባቢዮች ። ይህን በድራማ መልኩ የሚሰራ ትእይንተ ዘረፋ የሚያካሄዱ ዋልጌዎች በተቀናጀ መልኩ ስፍራ ስፍራቸውን ይይዛሉ ። በቅርብ ርቀት ቦታና የስራ ድርሻ ይመዳደባሉ ። የተንጣለለ ጊቢ ተከራይተው ለእኩይ ተግባራቸው ያዘጋጃሉ ። በአብዛኛው ሒጃብ የለበሱ ሴቶችና ፂም ያስረዘሙ ሱሪ ያሳጠሩ ኮፍያ ያጠለቁ የሙስሊም ገፀባህሪ ተደርገው የተዘጋጁ የድራማው ተሳታፊ ይሆናሉ ። በዚህም በቀላሉ የሙስሊም እህቶችን ዐይን ይስባሉ ። ከቀረጥ ነፃ ወረቀት ውክልና ሰጥተው ለማረጋገጥ ወደ ውጪ ጉዳይ የሚሄዱ , የጋብቻ ወይም የልደት አሊያም የትምህርት ማስረጃ ለማረጋገጥም ወደዚያ የሚያመሩ እህቶች በተለይ ከተማውን የማያውቁ ከሆኑ ቶሎ ይታወቃሉ ። ወዲያው በእነዚያ በተዘረጋ ሰንሰለት አቀባበል ይደረግላቸዋል ። ሙስሊሞች ከሆኑ በባለ ሒጃቧ ወዴት ነው ? ተብለው ይጠየቃሉ ያለ ምንም መጠራጠር ለምን ጉዳይ ወዴት መሄድ እንደሚፈልጉ ይናገራሉ ። እኔም ወደዛው ነኝ አብረን እንሄዳለን ይባላሉ ። ጉዞ ይጀመራል ። ከደቂቃ በኋላ መኪና ይዞ የቆመ የሰንሰለቱ ተዋናይ ጋር ይደርሳሉ ። ባለ ሂጃቧ ውጪ ጉዳይ በየት በኩል ነበር የሚያስገባው ? ብላ ትጠይቃለች ። ተዋናዩም ግቡ ላድርሳችሁ ይላል ። ወደ ትወናው ቢሮ ጊቢ አድርሶ ያው ብሎ አውርዶ ይሄዳል ። በድራማው የተመለመሉ የወንድና ሴት ጥበቃዎች የት ነበር ብለው ይጠይቃሉ ይነገራቸዋል ። እዚህ ጋር የሚሰራውን ድራማ ለመረዳት ወደ ተለያዩ በጣም ጥብቅ የሆኑ የመንግስት ተቋማት ሲገባ ያለውን ሁኔታ ላስታውሳችሁ ። እንደ ሰላም ሚኒስቴር ፣ ደህንነትና መረጃ ፣ ኤር ፖርትና የመሳሰሉ ቦታዎች ሲገባ አንድ ሰው ወንድም ይሁን ሴት ወደ ውስጥ ለማለፍ ፍተሻ አልፎ ነው የሚገባው ። ፍተሻው ጋር ኤክስሬ ማሽን አለ ። ማንም ሰው በእጁም በኪሱም የያዘውን ማንኛውንም ብረት ነክ ነገር እንደ ሰአት ፣ ቁልፍ ጌጣጌጥ ፣ ቀበቶም ጭምር አውጥቶ በማሽኑ እንዲያልፍ አድርጎ ራሱም በሌላ ፈታሽ ማሽን አልፎ ይሄድና ያ በማሽን እንዲያልፍ ያደረገውን ንብረቱን ይወስዳል ። ከዚህ በኋላ ወደ መስሪያ ቤቱ ቢሮ ያመራል ። ይህ ታዲያ እነዚህ ድራማ ሰሪዮች እንዴት እንደሚጠቀሙበት እንይ : – ይህች ድራማ የሚሰራባት ምስኪን እህት በእነዚህ ተልእኮ በተሰጣቸው ሴት ፈታሾች ምንም ብረት ነክ ነገር ይዞ መግባት አይፈቀድም ስለዚህ ሰአት ፣ ሞባይል ፣ ጌጣ ጌጦችን በሙሉ አውጥተሽ በቦርሳሽ ውስጥ አድርጊ ትባላለች ። ምስኪኗ እህትም የተባሉትን በሙሉ በቦርሳው ውስጥ ያለውን ብርም ጭምር ታስረክባለች ። ምናልባት ፓስፖርትና የሚረጋገጠው ወረቀት ቦርሳው ውስጥ ካለ በፓስፖርቱ ውስጥ መቶ ብር ተደርጎ ይሰጣታል ። ወደ ተባለው ቢሮ ስትገባ ማንም የለም ትንሽ ቆዪ ይመጣሉ ትባላለች ። ይሁን እንጂ የሚመጣ የለም ለመጠየቅ ስትወጣ ዘበኛው ተቀይሮ ሌላ ነው ። ስትጠይቀው ቢሮ ገና ሰው ያልገባበት ባዶ ነው ። የምን የውጪ ጉዳይ ነው እንዲህ የሚብል ነገር አላቅም ይላል ። ‼ ኤምባሲ ከሆነ ድራማ ሰሪዮቹ በታክሲ ወደ ኤንባሲ የመጡ እህቶችን አዛኝ መስለው ኤምባሲው ከዚህ ለቋል ተብለን ነው ኑ ወደ አዲሱ ቢሮ አብረን እንሄዳለን በማለት የተለመደውን ድራማ ይሰራሉ ። ሴቶችን መሰረት ያደረገው ሿሿ ይህን ይመስላልና እህቶች ራሳችሁን ጠብቁ ። ወጪ ለመቀነስ ብላችሁ በታክሲ ከመሳፈር በሚታወቁ ታማኝ ራይዶች ሄዳችሁ ጉዳያችሁን ፈፅማችሁ በሰላም ተመልሳችሁ ተመጣጣኝ ዋጋ ብትከፍሉ ከአስደንጋጭ ዘረፋ ትድናላችሁና ለማንኛውም ተጠንቀቁ ። http://t.me/bahruteka
Показать все...
ባህሩ ተካ - Bahiru Teka

السلام عليكم ورحمة الله وبركاته قناة رسمية لمحاضرات ودروس الأستاذ بحرو تكا (أبو عبيدة) الدعوة السلفية በአላህ ፈቃድ በዚህ ቻናል የአማርኛ ትምህርቶችን እንዲሁም አጫጭር የአረብኛና የአማርኛ ፁሁፎችን እንለቃለን ከዚህ ቻናል ውጪ ከሌላ ቦታ ተወስደው ለሚለቀቁ ኦዲዮዎች እውቅና አልሰጥም

https://telegram.me/bahruteka

👍 2
ሰምንተዊ የቁሪአን ተፊስር ልጀምር ነዉ ገባ        ገባ              ገባ                 በሉ https://t.me/abuhatimaselefiy
Показать все...
Abu hatim Abduselam Aselefiy

ትክክለኛው እስላማዊ አስተምህሮ ከቁርአንና ከሐዲስ ከደጋግ ቀደምቶች አረዳድ ከታማኝ ዑለሞች ንግግር የሚሰራጭበት ቻናል ነው።

ሰምንተዊ የቁሪአን ተፊስር ልጀምር ነዉ ገባ        ገባ              ገባ                 በሉ https://t.me/abuhatimaselefiy
Показать все...
Abu hatim Abduselam Aselefiy

ትክክለኛው እስላማዊ አስተምህሮ ከቁርአንና ከሐዲስ ከደጋግ ቀደምቶች አረዳድ ከታማኝ ዑለሞች ንግግር የሚሰራጭበት ቻናል ነው።

🔥 1
🔷 የነብዩላሂ ኢብራሂም ታሪክ ክፍል ሰባትና የመጨረሻው ነብዩላሂ ኢስማኢል ከአደን ሲመለሱ የመጣ ሰው ነበር ወይ ብለው ጠየቅዋት ። አው ብላ የሆነውን ነገረቻቸው ። ምን አለሽ አሉዋት ባለቤትሽ ሲመጣ የቤትህን መቃን አጥብቀው ጥሩ መቃን ነው በይው ብሎኛል አለችው ። እሳቸውም እሱ አባቴ ነው መቃኗ አንቺ ነሽ በደንብ ያዛት ማለቱ ነው አሉዋት ።    ነብዩላሂ ኢብራሂም ለሶስተኛ ጊዜ ቤተሰባቸውን ለማየት ወደ መካ መጡ ። ነብዩላሂ ኢስማኢል ቀስት እየሰሩ አገኟቸው ። ሁለቱም ተያዩ አባት በልጁ ላይ ልጅም በአባቱ ላይ እንደሚያደርገው ተቃቅፈው ተሳሳሙ ። ነብዩላሂ ኢብራሂም ካዕባን ከልጃቸው እስማኢል ጋር ሆነው መሰረቱን ከፍ አድርገው እንዲገነቡ አላህ ያዘዛቸው መሆኑን ነገሯቸው ። ነብዩላሂ ኢስማኢልም በጣም ተደሰቱ ። ካዕባንም መገንባት ጀመሩ ። ይህን ክስተትና ከግንባታው ጋር የተገናኙ ሁለቱም ያደረጓቸው ዱዓኦችን አላህ በላሚቷ ምእራፍ ከ25 – 30ኛው አንቀፅ ላይ እንዲህ ብሎ ይነግረናል : – وَإِذْ جَعَلْنَا الْبَيْتَ مَثَابَةً لِّلنَّاسِ وَأَمْنًا وَاتَّخِذُوا مِن مَّقَامِ إِبْرَاهِيمَ مُصَلًّى ۖ وَعَهِدْنَا إِلَىٰ إِبْرَاهِيمَ وَإِسْمَاعِيلَ أَن طَهِّرَا بَيْتِيَ لِلطَّائِفِينَ وَالْعَاكِفِينَ وَالرُّكَّعِ السُّجُودِ ቤቱንም ለሰዎች መመለሻና ጸጥተኛ ባደረግን ጊዜ (አስታውስ) ፡፡ ከኢብራሂምም መቆሚያ መስገጃን አድርጉ ፡፡ ወደ ኢብራሂምና ወደ ኢስማዒልም ቤቴን ለዘዋሪዎቹና ለተቀማጮቹም ለአጎንባሾች ሰጋጆቹም አጥሩ ስንል ቃል ኪዳን ያዝን ፡፡ وَإِذْ قَالَ إِبْرَاهِيمُ رَبِّ اجْعَلْ هَٰذَا بَلَدًا آمِنًا وَارْزُقْ أَهْلَهُ مِنَ الثَّمَرَاتِ مَنْ آمَنَ مِنْهُم بِاللَّهِ وَالْيَوْمِ الْآخِرِ ۖ قَالَ وَمَن كَفَرَ فَأُمَتِّعُهُ قَلِيلًا ثُمَّ أَضْطَرُّهُ إِلَىٰ عَذَابِ النَّارِ ۖ وَبِئْسَ الْمَصِيرُ ኢብራሂም ባለ ጊዜ (አስታውስ) ፡፡ ጌታዬ ሆይ! ይህንን ጸጥተኛ አገር አድርግ፡፡ ቤተሰቦቹንም ከነሱ በአላህና በመጨረሻው ቀን ያመነውን ሰው ከፍሬዎች ስጠው ፡፡ (አላህም) የካደውንም ሰው፤ (እሰጠዋለሁ) ፡፡ ጥቂትም እጠቅመዋለሁ፤ ከዚያም ወደ እሳት ቅጣት አስጠጋዋለሁ፤ ምን ትከፋም መመለሻ! (አለ) ፡፡ وَإِذْ يَرْفَعُ إِبْرَاهِيمُ الْقَوَاعِدَ مِنَ الْبَيْتِ وَإِسْمَاعِيلُ رَبَّنَا تَقَبَّلْ مِنَّا ۖ إِنَّكَ أَنتَ السَّمِيعُ الْعَلِيمُ ኢብራሂምና ኢስማኢልም «ጌታችን ሆይ! ከእኛ ተቀበል፡፡ አንተ ሰሚውና ዐዋቂው አንተ ነህና» የሚሉ ሲኾኑ ከቤቱ መሠረቶቹን ከፍ ባደረጉ ጊዜ (አስታውስ) ፡፡ رَبَّنَا وَاجْعَلْنَا مُسْلِمَيْنِ لَكَ وَمِن ذُرِّيَّتِنَا أُمَّةً مُّسْلِمَةً لَّكَ وَأَرِنَا مَنَاسِكَنَا وَتُبْ عَلَيْنَا ۖ إِنَّكَ أَنتَ التَّوَّابُ الرَّحِيمُ «ጌታችን ሆይ! ላነተ ታዛዦችም አድርገን ፡፡ ከዘሮቻችንም ላንተ ታዛዦች ሕዝቦችን (አድርግ) ፡፡ ሕግጋታችንንም አሳየን፤ (አሳውቀን) ፡፡ በኛም ላይ ተመለስን፤ አንተ ጸጸትን ተቀባዩ ሩኅሩኅ አንተ ብቻ ነህና ፡፡» رَبَّنَا وَابْعَثْ فِيهِمْ رَسُولًا مِّنْهُمْ يَتْلُو عَلَيْهِمْ آيَاتِكَ وَيُعَلِّمُهُمُ الْكِتَابَ وَالْحِكْمَةَ وَيُزَكِّيهِمْ ۚ إِنَّكَ أَنتَ الْعَزِيزُ الْحَكِيمُ «ጌታችን ሆይ! በውስጣቸውም ከነሱው የኾነን መልክተኛ በነርሱ ላይ አንቀጾችህን የሚያነብላቸውን መጽሐፍንና ጥበብንም የሚያስተምራቸውን (ከክህደት) የሚያጠራቸውንም ላክ፤ አንተ አሸናፊው ጥበበኛው አንተ ብቻ ነህና» (የሚሉም ሲኾኑ) ፡፡ وَمَن يَرْغَبُ عَن مِّلَّةِ إِبْرَاهِيمَ إِلَّا مَن سَفِهَ نَفْسَهُ ۚ وَلَقَدِ اصْطَفَيْنَاهُ فِي الدُّنْيَا ۖ وَإِنَّهُ فِي الْآخِرَةِ لَمِنَ الصَّالِحِينَ ከኢብራሂምም ሕግጋት ነፍሱን ያቄለ ሰው ካልኾነ በስተቀር የሚያፈገፍግ ማነው? (የለም)፤ በቅርቢቱም ዓለም በእርግጥ መረጥነው ፡፡ በመጨረሻይቱም ዓለም እርሱ ከመልካሞቹ ነው ፡፡ አላህ ለነብዩላሂ ኢብራሂም የካዕባን ቦታ አመላክቷቸው ከገቡ በኋላ ካዕባን ገንብተው ጨረሱ ። አላህም ለሐጅ ጥሪ እንዲያደርጉ አዘዛቸው ። እሳቸውም ጌታዬ ሆይ እንዴት አሰማለሁ አሉ ። አላህ አንተ ተጣራ እኔ አሰማለሁ አላቸው ። ተጣሩም ። አላህ ጥሪው እንዲሰሙ ካደረጋቸው ነፍሶች ውስጥ በዛን ጊዜ የነበሩና የቻሉ እንዲመጡ አደረጋቸው ። ነብዩላሂ ኢብራሂምም የመጡትን የሐጅን ስርኣት አስተማሯቸው ። እነዚያ ስርኣቶች ናቸው ሐጅ ላይ የሚከናወኑት ። ይህ ክስተት በሐጅ ምእራፍ ላይ በሰፊው ተብራርቷል ። ከዛውስጥ 26ኛውና 27ኛውን አንቀፅ ቀጥሎ እንመልከት : – وَإِذْ بَوَّأْنَا لِإِبْرَاهِيمَ مَكَانَ الْبَيْتِ أَن لَّا تُشْرِكْ بِي شَيْئًا وَطَهِّرْ بَيْتِيَ لِلطَّائِفِينَ وَالْقَائِمِينَ وَالرُّكَّعِ السُّجُودِ ለኢብራሂምም የቤቱን (የካዕባን) ስፍራ መመለሻ ባደረግንለት ጊዜ «በእኔ ምንንም አታጋራ፣ ቤቴንም ለሚዞሩትና ለሚቆሙበት ለሚያጎነብሱትና በግንባራቸውም ለሚደፉት ንጹሕ አድርግላቸው» (ባልነው ጊዜ አስታውስ) ፡፡ وَأَذِّن فِي النَّاسِ بِالْحَجِّ يَأْتُوكَ رِجَالًا وَعَلَىٰ كُلِّ ضَامِرٍ يَأْتِينَ مِن كُلِّ فَجٍّ عَمِيقٍ (አልነውም) ፡- በሰዎችም ውስጥ በሐጅ ትዕዛዝ ጥራ ፡፡ እግረኞች ከየሩቅ መንገድ በሚመጡ ከሲታ ግመሎችም ሁሉ ላይ ሆነው ይመጡሃልና ፡፡ ከዚህ በኋላ ነብዩላሂ ኢብራሂም መካ ላይ ተረጋግተው መኖር ጀመሩ ። የኢስሐቅን ልጅ ነብዩላሂ የዕቆብን ካዩ በኋላ ወደ አኼራ ሄዱ ። የነብዩላሂ ኢብራሂም አጭር የህይወት ታሪክ በዚህ ተፈፀመ ። ክፍል አንድን ለማግኘት የሚከተለውን ሊንክ ይጫኑ 👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇 https://t.me/bahruteka/5019 ክፍል ሁለት 👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇 https://t.me/bahruteka/5022 ክፍል ሶስት 👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇 https://t.me/bahruteka/5026 ክፍል አራት 👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇 https://t.me/bahruteka/5033 ክፍል አምስት 👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇 https://t.me/bahruteka/5034 ክፍል ስድስትን 👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇 https://t.me/bahruteka/5037 http://t.me/bahruteka
Показать все...
ባህሩ ተካ - Bahiru Teka

👉 የነብዩላሂ ኢብራሂም ታሪክ ክፍል አንድ የነብዩላሂ ኢብራሂም ታሪክ ቁርኣን ላይ ቱክረት ከተሰጣቸው የነብያት ታሪክ ውስጥ በግንባር ቀደምትነት ይመደባል ። ታሪካቸው ቁርኣን ውስጥ በ17 ምእራፍ ወደ 69 ጊዜ ተጠቅሷል ። ይህ የሚያሳየው ታሪካቸው ምን ያክል አስፈላጊና ቁም ነገር አዘል መሆኑ ነው ። ነብዩላሂ ኢብራሂም ዒራቅ ውስጥ ባቢል በሚባል ቦታ በጣኦት አምላኪ ማህበረሰብ ውስጥ ተወለዱ ። ከህብረተሰቡ ውስጥ ኮከብ የሚያመልክ ፣ ጨረቃ የሚያመልክና ፀሀይ የሚያመልክ እንዲሁም ከእንጨት የተሰራ ጣኦት የሚያመልክ ነበር ። አባታቸው ኣዘር ከእንጨት ጣኦት እየሰራ ይሸጥ ነበር ። እሳቸው በልጅነታቸው እርሻ ይሰሩ ነበር ። አባታቸው ጣኦት እያዞሩ እንዲሸጡላቸው ሲያዙዋቸው ተቀብለው መሬት ለመሬት እየጎተቱ የማይጠቅምና የማይጎዳ የሚገዛ እያሉ ያዞሩ ነበር ። በዚህም ምክንያት ማንም የሚገዛ ስለማያገኙ ይዘውት ይመለሳሉ ። እድሜያቸው 13 አመት ሲሞላቸው ፈጣሪዬ ማን ነው ብለው ማሰብ ጀመሩ ። ቤተሰቦቻቸውና ማህበረሰቡ በሚያመልኩት ነገር ደስተኛ አልነበሩም ። ለብቻቸው ሲሆኑ ማን ነው የፈጠረኝ እያሉ ይብሰለሰላሉ ። በዚህ ስሜት ውስጥ ሆነው ከቤት ወጥተው ወደ ሰማይ በሚያዩበት ጊዜ የተከሰተውን አላህ ሲነግረን በአል አንዓም ምእራፍ ከ75 – 79 ድረስ እንዲህ ይለናል : – وَكَذَٰلِكَ نُرِي إِبْرَاهِيمَ مَلَكُوتَ السَّمَاوَاتِ وَالْأَرْضِ وَلِيَكُونَ مِنَ الْمُوقِنِينَ እንደዚሁም ኢብራሂምን (እንዲያውቅና) ከአረጋጋጮቹም ይኾን ዘንድ የሰማያትንና የምድርን መለኮት አሳየነው ፡፡ فَلَمَّا جَنَّ عَلَيْهِ اللَّيْلُ رَأَىٰ كَوْكَبًا ۖ قَالَ هَٰذَا رَبِّي…

👍 1
Выберите другой тариф

Ваш текущий тарифный план позволяет посмотреть аналитику только 5 каналов. Чтобы получить больше, выберите другой план.