ግዮን ቤተ -መጽሐፍት (GYON LIBRARY)
Открыть в Telegram
በዚህ ቻናል የተለያየ ይዘት ያላቸው ልብ ወለዶች የፍልስፍና መጽሐፍቶች ሃይማኖታዊ መጽሐፍቶች ታሪኮች እና ሌሎችም መጽሐፍቶች ይለቀቁበታል ። ማንበብ ሙሉ ሠው ያደርጋል። @supergreatpower ከ #3000 በላይ መፅሐፍትን እዚህ ያገኛሉ። እናንብብ እንመራመር እንዋደድ እንስራ ሀገራችንን እንለውጥ !!!!! ግዮን ቤተ መጽሐፍት የአንባቢያን ምርጫ @gyonlibrary
Больше7 028
Подписчики
Нет данных24 часа
-227 дней
-5330 дней
Архив постов
በአለም ረጅሙ የማዕረግ ስም
"የተከበሩ የእድሜ ልክ ፕሬዝዳንት ፊልድ ማርሻል አል ሐጂ ፕሮፌሰር ዶክተር ኢዲ አሚን ዳዳ ቪሲ ዴኤስኦ ኤምሲ የምድር አራዊቶች እና የባህር አሳዎች ሁሉ ጌታ በአጠቃላይ የእንግሊዝ ና የስኮትላንድ ኢምፔሪያሊዝም በአፍሪካና በኡጋንዳ ድል አድራጊ።"
እንግዲህ ይህ ሁሉ አጭር መጣጥፍ ወይም ድርሰት ሳይሆን የቀድሞ የኡጋንዳ አምባገነን መሪ መጠሪያ ነው ።
ኤዲያሚን ዳዳ አፈሩን ገለባ ያድርግለትና በእነዚህ ሁሉ የማረግ ስሞች ያለማጓደል እንዲጠራ በመመርያ ሳይቀር ደንግጎ ነበር።
ኤድያሚን ዳዳ ታሪክ በአምባገነንታቸውና በጭካኝነታቸው በግንባር ቀደምትነት ከፈረጃቸው "ምርጥ አምባገነኖች" አንዱ ነበር።
የዚህ ሁሉ ስም ባለቤት ኢዲ አሚን ዳዳ የተማረው እስከ 4ተኛ ክፍል ነበር!
Promotion ‼
መድሃኒት እና የህክምና መገልገያዎችን ማስመጣት ፈልገው አማካሪ ከፈለጉ እኛን ማግኘት ይችላሉ ።
በተጨማሪም internal sales and external sales ከፈለጉም እኛ ጋ ማግኘት ይችላሉ ‼
በውስጥ ያውሩን ‼
@Pharmaconsultant_ethiopia
ለዐቢይ ቀመር 7519 ÷ 532 =14 14ቱ ዐቢይ ቀመር 7448 ሆኖ 71 ይቀራል 71÷19=3 ቀሪ 14
አዋጅ '' ወለእመ ተርፈከአሐደ አዕትት ለዘመን - አንድ ለዘመኑ ስጥ” አንዱን ለዘመን ስንሰጥ 13 ይቀራ ስለተ ጀመረ ተቆጠረ ስላልተፈጸመ ታተተ የ 20019 ዓመተ ምህረት ወንበር 13 ነው መጥቅዕ = 7 ተረፈ ዘመን ቁጥረ ሌሊት ሥፍረ ሌሊት ማለት ነው።
አበቅቴን ለማግኘት፦ ጥንተ አበቅቴ ከወንበር ጋር ማባዛት ከ30 ከበለጠ - በ30 መግደፍ አበቅቴ = 13+11= አበቅቴ=11×13=143÷30=4 ቀሪ=23 አበቅቴ የሚጠቅመን ሌሊቱን ለማግኘት ነው። ሌሊት = ዕለት + አበቅቴ + ሕፀጽ ሕፀጽ - ጉድለት ማለት ነው። ጨረቃ ከፀሐይ የምታጐድለው ማለት ነው።
የዓመቱ ሕፀጽ፦ የመስከረምና የጥቅምት = 1 የሕዳርና የታህሣሥ= 1 ከላይኛው ጋር = 2 የጥርና የየካቲት = 3 የመጋቢትና የሚያዚያ =4 የግንቦትና የሰኔ = 5 የሐምሌና የነሐሴ = 6 ጳጉሜ ወር ስለማትሞላ 6 ነው።
የመስከረም 1/2019 ዓም ሌሊት፦ ዕለት + አበቅቴ + ሕፀጽ 1 + 23+ 1 = 25 መጥቅዕ 7
➡️መጥቅዕ=19×12=247÷30=8 ቀሪ=7 መጥቅዕ ማለት ደወል ማለት ነው ደወል ሲመታ የራቁ ይቀርባሉ፣ የተበተኑ ይሰበሰባሉ። ይህም መጥቅዕ በዓላትና አጽዋማትን ይሰበስባል።
የዘመኑን መጥቅዕና አበቅቴን ለማግኘት ጥንተ መጥቅዕን እና ጥንተ አበቅቴን ከወንበር ጋር ማባዛት ከ 30 ከበለጠ ለ 30 ማካፈል ነው
አበቅቴ=11×13=143÷30=4 ቀሪ=23
መጥቅዕ=
➡️መጥቅዕ=19×12=247÷30=8 ቀሪ=7
መባጃ ሐመር
መባጃ ሐመር=8+7=15
ባጀ - ቆየ ፣ ሰነበተ
ሐመር - መርከብ
በዓላትና አጽዋማት የሚያሰነብት ስለሆነ መባጃ ሐመር ተብሏል።
መባጃ ሐመርን ለማግኘት፦ መጥቅዕና በዓለ መጥቅዕ የዋለበትን የዕለት ተውሳክ መደመር ነው። ከ 30 ከበለጠ በ 30 መግደፍ
በዓለ መጥቅዕ መቼ ይውላል?
አዋጅ ፦ መጥቅዕ ከ14 በላይ ከሆነ በመስከረም ከ 14 በታች ከሆነ በጥቅምት (መጥቅዕ ሲበዛ ከመስከረም ንዛ መጥቅዕ ቢያንስ ከጥቅምት ዳስ) ይላል መርሐ ዕውር መጥቅዕ 7 ነው ስለዚህ መጥቅዕ በጥቅምት ይውላል በዓለ መጥቅዕ (በጥቅምት) ቅዳሜ ቀን ይውላል። የቅዳሜ ተውሳክ 8 +7=15
የዕለት ተውሳክ፦ ተውሳክ - ወሰከ - ጨመረ ጭማሪ ማለት ነው።
የቅዳሜ ተውሳክ = 8
የእሑድ = 7
የሰኞ = 6
የማክሰኞ = 5
የረቡዕ = 4
ሐሙስ = 3
ዓርብ = 2
ጥቅምት 7/2019/ዓ ም ቅዳሜ ቀን ይውላል (8= ተውሳክ) መባጃ ሐመር = መጥቅዕ + የዕለት ተውሳክ 8+ 7= 15 መባጃ ሐመር 15 ከበዓላትና አጽዋማት ተውሳክ ጋር በመደመር የየዘመኑንን በዓላትንና አጽዋማት ያስገኝልናል። የበዓላትና አጽዋማት ተውሳክ የሚውልበት
1ኛ. ጾመ ነነዌ ተውሳክ የላትም (0 ነው) ስለዚህ በመባጃ ሐመር ትወጣለች ዘንድሮ በዓለ መጥቅ 7 ስለሆነ በጥቅምት 7 ይውላል ጥቅምት 7 ደግሞ ቅዳሜ ቀን ይሆናል የቅዳሜ ተውሳክ 8 ነው መጥቅዕ ሲደመር የዕለት ተውሳክ እኩል ይሆናል መባጃ ሐመር በዓለ መጥቅዕ 7+8 =15 የዕለት ተውሳክ = 15 ጾመ ነነዌ የካቲት 15 ትገባለች።
የአጽዋማትና የበዓላት ተውሳክ
1ኛ ለጾመ ነነዌ ተውሳክ የላትም በመባጃ ሐመር ትወጣለች ብለናል
2ኛ. የዐቢይ ጾም ተውሳክ = 14+15 =29 የካቲት 29 ዐቢይ ጾም
3ኛ. የበዓለ ደብረ ዘይት = 11+15=26 ደብረ ዘይት መጋቢት 26
4ኛ. የበዓለ ሆሳዕና = 2+15=17 ሆሳዕና ሚያዝያ 17
5ኛ. የበዓለ ስቅለት = 7+15=22 ስቅለት ሚያዝያ 22
6ኛ. የበዓለ ትንሣኤ = 9+15=24 ትንሣኤ ሚያዝያ 24
7ኛ. የበዓለ ርክበ ካህናት = 3+15=18 ርክበ ካህናት ሚያዝያ 18
8ኛ. የበዓለ ዕርገት = 18+15 = 33 ቀሪው3 ዕርገት ግንቦት 3
9ኛ. የበዓለ ጰራቅሉጦስ = 28+15=43 ቀሪ 13 ጰራቅሉጦስ ግንቦት 13
10ኛ. ጾመ ሐዋርያት = 29+15=44 ጾመ ሐዋርያት ግንቦት 14
11ኛ. ጾመ ድኅነት = 1 ጾመ ድኅነት ግንቦት 16
ኢየዓርግና ኢይወርድ
ጾመ ነነዌ ከጥር 17 አትወርድም ከየካቲት 21 አትወጣም
ዓቢይ ጾም ከየካቲት 1 ወደ ታች አይወርድም ከመጋቢት 5 ወደ ላይ አይወጣም
ደብረዘይት ከየካቲት 28 ወደ ታች አይወርድም
ከሚያዝያ 2 ወደ ላይ አይወጣም
ሆሣዕና ከመጋቢት 19 ወደ ታች አይወርድም
ከሚያዝያ 23 ወደ ላይ አይወጣም
በዓለ ስቅለት ከመጋቢት 24 ወደ ታች አይወርድም
ከሚያዝያ 28 ወደ ላይ አይወጣም
በዓለ ትንሣኤ ከመጋቢት 26 ወደ ታች አይወርድም
ከሚያዝያ 30 ወደ ላይ አይወጣም
ርክበ ካህናት ከሚያዝያ 20 ወደ ታች አይወርድም
ከግንቦት 24 ወደ ላይ አይወጣም
በዓለ ዕርገት ከግንቦት 5 ወደ ታች አይወርድም
ከሰኔ 9 ወደ ላይ አይወጣም
በዓለ ጰራቅሊጦስ ከግንቦት 15 በታች አይወርድም
ከሰኔ 19 በላይ አይወጣም
ጾመ ሐዋርያት ከግንቦት 16 በታች አይወርድም
ከሰኔ 20 በላይ አይወጣም
ጾመ ድኅነት ከግንቦት 18 በታች አይወርድም
ከሰኔ 22 በላይ አይወጣም
ዓመተ ወንጌላውያኑን ለማግኘት ዓመተ ፍዳ + ዓመተ ምህረት
5500 + 2019= 7519 = ዓመተ ዓለም ዓመተ ዓለሙን ለ 4ቱ ወንጌላውያን በማካፈል
ቀሪው 1 ከሆነ ማቴዎስ
2 ከሆነ ማርቆስ
3 ከሆነ ሉቃስ
ዜሮ ወይም እኩል ከሆነ ዮሐንስ
7519 ÷ 4 = 1879 ደርሶ =3 ይቀራል ወንጌላዊው ሉቃስ ነው
2. መስከረም 1 (ዕለተ ቀመር) ዓመተ ዓለም + መጠነ ራብዒት = ለሰባቱ ዕለታት ማካፈል 7519+ 1879 =9,398 9398 ÷ 7= 1342 ደርሶ 4 ይቀራል። ቀሪ፦
1 ከሆነ = ማክሰኞ
2 ከሆነ = ረቡዕ
3 ከሆነ = ሐሙስ
4 ከሆነ= ዓርብ
5 ከሆነ = ቅዳሜ
6 ከሆነ = እሁድ
0 ከሆነ = ሰኞ
በ2019 ዕለተ ሉቃስ ዓርብ ቀን ስለ መዋሉ በዚህ ይረጋገጣል
3. ዕለቱን ለማግኘት
ዕለት + አጽፈ ወርኅ + ጥንተ ዮን
መስከረም 30 + የመስከረም ዕጥፍ + ጥንተ ዮን
ጥንተ ዮን መስከረም 1 ረቡዕ ከዋለ = ጥንተ ዮን አንድ ነው።
ሐሙስ ከዋለ = 2
ዓርብ ከዋለ = 3
ቅዳሜ ከዋለ = 4
እሑድ ከዋለ = 6
ሰኞ ከዋለ = 7
ማክሰኞ ከዋለ = 8
መስከረም 1 ቀን ዓርብ ስለዋለ ጥንተ ዮን 3 ነው።
ዓመተ ዓለም ሲደመር መጠነ ራብዒት 7519+1879= 9398 ይህ ለ7ቱ ዕለታት ሲካፈል
9396 ፥ 7 = 1342 ደርሶ ቀሪው 4 ነው። ይህ ማለት 9397 - 7 × 1342 = 4 ይሆናል
6= ከሆነ እሁድ
0= ከሆነ ሰኞ
1=ከሆነ ማክሰኞ
2=ከሆነ ረቡዕ
3= ከሆነ ሐሙስ
4= ከሆነ ዓርብ
5= ከሆነ ቅዳሜ
ከቅዳሴም በኋላ በደመራው እሳት ውስጥ እየተመላለሰ ያጥን ጀመር። ልዕልተ ወይንንም ከምቅዋመ አንስት/ከሴቶች መቆሚያ/ አስጠርቶ “ስፍሒ አጽፈኪ - ልብስሺን ዘርጊ” በማለት ፍሕሙን እያነሳ በልብሷ ላይ ጨመረ እና እየዞረች ለሕዝቡ ሁሉ አሳየች። እርሷም ሆነ ልብሷ ምንም በእሳቱ አልተነኩም ነበር። ድሜጥሮስንም ምንድነው ይህ ነገር አባታችን ብለው ሲጠይቁት ለ48 ዓመት አብረው ሲኖሩ በግብረ መርዓት ወመርዓዊ/በተራክቦ/ እንደማይተዋወቁ ሲገልጥላቸው ሕዝቡ ሁሉ በመጸጸት አባ ሥረይ ለነ እያሉ ይቅርታ ጠየቁ። እርሱም “ይህድግ ይፍታሕ ያንጽሕ ወይቀድስ ወያስተሥሪሊቅ ሊቀ ካህናት ኢየሱስ ክርስቶስ ” ብሎ ናዝዟቸዋል ኑዛዜ በዚህ ጊዜ ተጀምሯል ። ይህም ቅዱስ አባት በመንበረ ጵጵስናው ሳለ አንድ ትልቅ ተምኔት ነበረው።
➡️ ጾመ ነነዌ ፣ ዐቢይ ጾም ፣ ጾመ ሐዋርያት ከሰኑይ፣
➡️ ደብረ ዘይት ፣ ሆሣዕና ፣ ትንሣኤ እና ጰራቅሊጦስ ከእሑድ፣
➡️ ርክበ ካህናት እና ጾመ ድኅነት ከረቡዕ፣
➡️ ዕርገት ከሐሙስ
➡️ ስቅለት ከዓርብ ባይወጣ እያለ ይመኝ ነበር።
ምክንያቱም እሊህ በዓላት ለመጀመርያ ጊዜ የዋሉት በእነዚህ ዕለታት ስለነበር ነው። እንዲህም እያለ ሲመኝ የታዘዘ መልአክ ወደርሱ መጥቶ በምኞት ብቻ እንደማይሆን ነግሮት ሱባኤ እንዲገባ ይነግረዋል። “ከሌሊቱ 23 ሱባኤ ግባ እና አበቅቴ ይሁንህ፤ ከቀኑ 7 ሱባኤ ግባ እና መጥቅዕ ይሁንህ” ብሎታል። ሌሊቱን አብዝቶ ቀኑን ማሳነሱ ለምንድነው ቢሉ ቀኑን የተጣላ ሲያስታርቅ፣ የታመመ ሲጠይቅ ሲያስተምር እንዲህ ባለው ሁሉ ግብር ስለሚያሳልፍ ነው።ሌሊት ግን ይህ ሁሉ የለበትምና ከዚህም ጥንተ አበቅቴ እና ጥንተ መጥቅዕ ይገኛሉ።
አዋጅ፦ ማንኛውም ቁጥር ከ30 ከበለጠ በ30/በዐውደ ወርኅ/ ይገደፍና ይተዋል ።
የቀኑን ስናሰላ አንድ ሱባኤ ማለት ሰባት ዕለት ነው። 7×7=49 ይህንም በ30 ስንገድፈው 1 ጊዜ ይደርስና 19 ይቀራል። ይህም ጥንተ መጥቅዕ ይባላል። ይህም መጥቅ ከዕለታት ከአጽዋማት እና ከበዓላት ተውሳክ ጋር ተደምሮ ከ30 ከበዛ ሰላሣውን ገድፎ ትርፉን እየያዙ ማውጫ ነው 23×7=161 ይህንም በ30 ስንገድፈው 5 ጊዜ ይደርስና 11 ይቀራል። ይህም ጥንተ አበቅቴ ይባላል። ሌሎች ቀመሮች ላይ ሌሊትን ለማውጣት እና የየዓመታቱን አበቅቴ ለማውጣት እንገለገልበታለን። ይህም በተለይም ካህናት ጸሎትን ለማሣረግ አሥርቆት የሚያደርጉበት ነው።
ባሕረ ሐሳብን ማን መማር አለበት?
በጉባኤ ቤት ከመጻሕፍት ጉባኤ ጋር በአንድነት የሚሰጥ ትምህርት ነው። በዚህም ካህን የሆነ ሁሉ በበረሀ ጥላ ሥር እንዳለች ምንጭ የሚያረካ እንዲሆን መማር አለበት። ምክንያቱም በዓላትን እና አጽዋማትን አውጥቶ ለልጆቹ መንገር አለበት እና ነው። ምእመናንም ቢሆኑ በተለያየ ምክንያት ከሀገር የሚወጡበት አጋጣሚ ስለሚኖር በባዕድ ሀገር ሁነው በዓላትን በአግባቡ ለማክበር እና አጽዋማትን ለመጾም ማወቅ ያስፈልጋቸዋል።
ጥንታት ሦስት ናቸው
የኢትዮጵያ የዘመን አቆጣጠር የሚጀምረው ከጥንታት ነው።
➡️ ጥንትነቱም ከፍጥረተ ዓለም፣
➡️ ከፍጥረተ ፀሐይ፣
➡️ ከፍጥረተ ጨረቃ እና ክዋክብት ነው።
ዓለም የተፈጠረበት ዕለተ እሁድ ጥንተ ዕለት ይባላል። እንዲህም መባሉ ፍጥረታት መፈጠር የጀመሩበት ዕለት በመሆኑ ነው። አዝርዕት ዕጽዋት እና አትክልት የተፈጠሩበት ዕለተ ሠሉስ ደግሞ ጥንተ ቀመር ይባላል። ቁጥር የተጀመረበት እለት ስለሆነ ነው። ፀሐይ ጨረቃ እና ክዋክብት የተፈጠሩበት ዕለተ ረቡዕም ጥንተ ዖን/ዮን/ በመባል ይታወቃል። ዖን ማለትም ብርሃን ማለት ነው። በመጽሐፍ “ዖን ይእቲ ስማ ለፀሐይ” እንዲል የእስክንድርያ 12ኛ ሊቀ ጳጳስ (ፓትርያርክ) የነበረው ቅዱስ ድሜጥሮስ
ከ180-222 ዓ.ም ድረስ ለ 42 ዓመት ሊቀ ጳጳስ ነበር ይላል ታሪኩ ሊቀጳጳስ ከመሆኑ በፊት መስተገብረ ምድር (ገበሬ)ነበር ሞፈር አርቆ፣ በአጭር ታጥቆ የሚሰራ ትጉህ ገበሬ ነበር ከልዕልተ ወይን (የቤተክርስቲያን ለቃውንት የሚጠሯት ስም) ጋር አጋብተዋቸው ነበር። ቤተ ክርስቲያን አራት ጉባዔ ቤቶች አሏት
ብሉይ ኪዳን
ሐዲስ ኪዳን
መጽሐፈ መነኮሳት (ማር ይስሐቅ፣ ፈልክስዩስ)
ሊቃውንት (ሃይማኖተ አበው |ቄርሎስ | መጽሐፈ ቅዳሴ| አክሲማሮስ )
አምስተኛ ጉባዔ ተደርጐ በሁለት መንገድ ይሰጣል። (አቡካኻር) ባሕረ ሀሳብ ተብሎ አቡካኻር (ወልደ አቤል ሄሬም) የተባለ መነኩሴ ሲሆን ባሕረ ሐሳብን ጨምሮ ሌሎች የሥነ ጸሐይ፣ ጨረቃና ከዋክብት ሊቅ ነው። ባሕረ ሀሳብም አብሮ ተገልጾለታል። ከድሜጥሮስ በተጨማሪ ባሕረ ሀሳብን ለማወቅ የተመኙ ሊቃውንት
አንደኛ ሰዒድ ወልደ ጰጥሪቅ
ሁለተኛ መሀቡብ ወልደ መንጋ
ሦስተኛ ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ
አራተኛ ኤጲፋንዮስ ዘመንፈስ ቅዱስ
አምስተኛ ጊዮርጊስ ወልደ አሚድ
ስድስተኛ ማርቆስ ወልደ ቀምበር
ሰባተኛ ዮሐንስ ወልደ አቤልሔሬም (አቡካክር) … እና ሌሎችም
የቅዱስ ድሜጥሮስ ምኞት እንዲህ መልአከ እግዚአብሔር ከገለጠለት በኋላ ቀምሮ አስቀምጦታል በሱባኤ አወጋጅቶታል
23 ሱባዔ ማለት
1 ሱባዔ = 7 ቀናት
23 ሱባዔ = 161 ቀናት
አዋጅ ፦ ማንኛውም ቁጥር ከ30 ከበዛ በ30 ግደፈው ወይም ለ30 አካፍለው ቀሪውን መያዝ ነው 161 ÷ 30 = 5 ደርሶ ወይም በአምስት ሰላሣ ገድፎ 11 ይቀራል 11 ጥንተ አበቅቴ ይባላል።
ሰባት ሱባዔ ማለት፦ 1 ሱባዔ = 7 7 ሱባዔ = 7× 7= 49 በ 30 ስንገድፈው (49÷30) =1 ደርሶ 19 ይቀራል 19 ጥንተ መጥቅዕ ይባላል። መጥቅዕና አበቅቴ ተደምረው ከ 30 አይበልጡም ፣ ከ 30 አያንሱም አዋጅ “አበቅቴ ወመጥቅዕ ክልዔሆሙ ኢየዓርጉ እም 30 ወኢይወርዱ እም 30 ወትረ ይከውኑ 30 ” ይላል
አዕዋዳት
አዕዋድ ዖደ ከሚል የግዕዝ ቃል የተገኘ ነው ትርጉሙም ዞረ ማለት ሲሆን በየጊዜው እየዞረ የሚመጣ ማለት ነው። ዓመተ ዓለም የሚሠፈሩበት ሰባት አዕዋዳት አሉ። እነሱም፦
ዓውደ ዕለት ከሰኞ - እሁድ
ዓውደ ወርኅ በፀሐይ 30 ቀናት፤ በጨረቃ 29ና 30
ዓውደ ዓመት- በፀሐይ 365 ቀናት 6 ሰዓት (15 ኬክሮስ) በጨረቃ 354 ከ 22 ኬክሮስ
ዓውደ አበቅቴ (ንዑስ ቀመር) = 19 ዓመት
ዓውደ ፀሐይ = 28 ዓመት
ዓውደ ማኅተም (ማዕከላዊ ቀመር) = 76 ዓመት
ዓውደ ዐቢይ ቀመር (ዐቢይ ቀመር) = 53 (ወንበር 13)
የዘመኑን አበቅቴንና መጥቅዕ የሚያስገኝ ነው።
ወንበር ለማግኘት ቀድመን ዓመተ ዓለሙን ማውጣት 5500 ዓመተ ፍዳ፣ ዓመተ ኩነኔ የሰው ልጅ ከገነት ወጥቶ ከፈጣሪው ጋር ተጣልቶ በመከራ በጭንቅ ይኖር ነበረና 2019 ዓመተ ምህረት ዓመተ ሥጋዌ (ዓ/ምሕረት) (ለምን ዓመተ ምህረት ተባለ?) አዳም የበደለውን በደል ለመካስ በምህረት በይቅርታ ስላዳነው የምህረት ዘመን ስለሆነ ዓመተ ምህረት ተብሏል 5500+2019 =7519 ይህንን በሶስቱ ቀመሮች እንቀምረዋለን።
ዐቢይ ቀመር ፣ 532 ማዕከላዊ ቀመር ፣76 ንዑስ ቀመር፣ 19
1ኛ. ለዐቢይ ቀመር 7519 ÷ 532 =14 14ቱ ዐቢይ ቀመር 7448 ሆኖ 71 ይቀራል
2ኛ. ለማዕከላዊ ቀመር 7519÷76=98 ደርሶ ቀሪ 13
3ኛ. ለንዑስ ቀመር (19) 7519÷19=395 ቀሪ 14
ወይም በቀጥታ ለዐቢይ ቀመር ተካፍሎ 14 ዐቢይ ቀመር ደርሶ (71) ሰባ አንዱን ለንዑስ ቀመር አካፍሎ ቀሪውን ይዞ ከቀሪው አንዱን ለዘመን ሰጥቶ ቀሪውን ወንበር ማለት ለምሳሌ
ባሕረ ሐሳብ ማለት ምን ማለት ነው
ባሕረ ሓሳብ ማለት ከሁለት ጥምር ቃላት የተገኘ ሕብረ ቃል ሲሆን ትርጉሙም፤ባሕር ማለት ዘመን ማለት ነው። “በመዳልው ደለወ ዓለመ ወበመሥፈርት ሰፈራ ለባሕር” እንዲል። ሐሳብ ማለት ደግሞ ቁጥር ማለት ነው። ቅዱስ ዳዊት በመዝሙሩ “ብፁዓን እለ ተኀድገ ሎሙ ኃጢአቶሙ ወእለ ኢሐሰበ ሎሙ ኲሎ ጌጋዮሙ - ኃጢአታቸው የተተወላቸው በደላቸውንም ያልቆጠረባቸው ንዑዳን ናቸው ” /መዝ 31÷1/በማለት እንደተናገረው ሐሳብ ማለት ቁጥር የሚል ትርጉም ይይዛል።
ባሕረ ሐሳብን ማን ደረሰው
ባሕረ ሀሳብን ለማወቅ ብዙ አበው የተመኙ እና የደከሙ ቢሆንም የተገለጸው ግን ለእስክንድርያ 12ኛ ሊቀ ጳጳስ ለነበረው ለቅዱስ ድሜጥሮስ ነበር። እርሱም ልክ እንደ ቅዱስ ሕርያቆስ የቤተክርስቲያን ዕውቀት ያልነበረውነው ዳሩ ግን መስተገብረ ምድር /ገበሬ/ ነበር። የርሱ አባት እና አጎቱ በዘመነ ሰማዕታት ከኢየሩሳሌም ተሰደው ከባዕድ ሀገር ይኖሩ ነበር። የድሜጥሮስ አባት እንደራኒቆስ ሲባል አጎቱ ደግሞ አስተራኒቆስ ይባላል። ለአስተራኒቆስም ልዕልተ ወይን የተባለች መልከ መልካም ልጅ ነበረችው። የዕረፍቱ ጊዜ ሲደርስም /በዚያ ስፍራ ከእነርሱ በቀር ሌላው ሁሉ አሕዛብ ነበርና/ “ልጄን ለአሕዛብ እንዳትድራት ብሎት ሞተ”።
ሁለቱም ለአቅመ አዳም ወሔዋን ሲደርሱ እንደራኒቆስ የወንድሙን አደራ በማስታወስ “ለአሕዛብ አጋብቼ ሕንፃ ሃይማኖት ከሚፈርስ ሕንፃ ሥጋ ቢፈርስ ይሻላል” በማለት ልዕልተ ወይንን እና ቅዱስ ድሜጥሮስን ያጋቧቸዋል። በሠርጋቸውም ዕለት ማታ ሥርዓተ መርዓት ወመርዓዊ እንዲፈጽሙ ከጫጉላ ሲተዉአቸው እነርሱ ግን የወንድማማች ልጆች ስለሆኑ ሩካቤ ለመፈጸም ባለመፈለጋቸው በሐዘን ተውጠው ያለቅሱ ጀመር።
ልዕልተ ወይንም ወንድሜድሜጥሮስን “ ይህን የሠራኸው እኔን ንቀህ ነው ወይስ ተዛምዷችንን” አለችው። እርሱም እህቴ የአባቴን ፈቃድ ለመፈጸም እንጂ አንቺንም ሆነ ተዘምዷችንን ንቄ አይደለም አላት ከዚህ በኋላ ፈቃድሽ ከሆነ ብንለያይ አንቺን ለሌላ አህዛባዊ እኔንም ለሌላ አህዛባዊት ያጋቡናል ተስማምተን ንጽህ ጠብቀን ባልና ሚስት መስለን እንኑር መከኑ ሰነፉ ይሉናል እንጂ በዚህ የሚጠረጥረን የለም አላት በዚህ ሐሳብ ተስማምተው በሩካቤ ሳይተዋወቁ 48 ዓመት ተቀመጡ ። በንጽሕናም ሲኖሩ መልአከ እግዚአብሔር አንድ ክንፉን ለልዕልተ ወይን አንድ ክንፉን ለድሜጥሮስ አልብሷቸው ይተኙ እና ጠዋት በርግብ አምሳል በመስኮት ሲወጣ ይታያቸው ነበር። እንዲህም ባለ የንጽህና ጉዞ 48 ዓመታትን አብረው ከኖሩ በኋላ የእስክንድርያው 11ኛ ሊቀ ጳጳስ ዮልያኖስ የእረፍቱ ጊዜ ደርሶ ነበር እና ከርሱ ቀጥሎ የሚሾመው ማን እንደሆነ ለመንገር ሕዝቡን በቤተክርስቲያን ጠራ።
ቅዱስ ድሜጥሮስም ድኮ ታጥቆ ሞፈር አርቆ የሚኖር ነበረና ወደእርሻው በገባ ግዜ ያለ ጊዜዋ የደረሰች የወይን ፍሬ አገኘ ይህ ለሊቀ ጳጳሱ ይገባል እንጂ ለኛ አይገባም ብሎ ወደ ቤቱ ሔደ ለልዕልተ ወይን ሰጣት ልዕልተ ወይንም ይህ ለሊቀ ጳጳሱ ይገባል እንጂ ለኛ አይገባም ብላ በመሶበ ወርቅ አድርጋ ሰጠችው ለሊቀ ጳጳሱ ይዞ ሄደ ሊቀ ጳጳሱም በሰጠው ጊዜ ከርሱ ቀጥሎ እንደሚሾም በሱባኤ ስለተገለጠለት ቅብዓ ሜሮን ቀብቶ ሥርዓተ ጵጵስናን ፈጽሞለታል ብለው ይናገራሉ መተርጉማን ። ይህ ሲሆን ግን ቅዱስ ድሜጥሮስ አላወቀም ነበር።
ከጥቂት ቀናትም በኋላ ሊቀ ጳጳሱ ሲያርፍ ከርሱ ቀጥሎ ሊቀ ጳጳስ የሚሆነው ቅዱስ ድሜጥሮስ እንደሆነ ነግሯቸው ነበርና መንበር ብቻውን አያድርም በማለት ሂደው በመንበረ ማርቆስ ላይ ሊቀ ጳጳስ እንደሚሆን ነገሩት። እርሱ ግን “እኔ በአንድ በኩል ያልተማርኩ ገበሬ ነኝ፣ በዚያውም ላይ ሕጋዊ ነኝ። እንዴት ንጹሁ በነበረበት እኔ ሕጋዊው
ጻድቁ በነበረበት እኔ ኃጥኡ የተማረ በነበረበት እኔ መሐይሙ እንዴት ይሆናል አይሆንም አላቸው አይሆንም ቢላቸው እነርሱ ግን አባታችን ግብር ገብቶ ሱባዔ ይዞ ነግሮናል ብለው ግድ አሉት አስቀመጡትም። በሀገራችሁ ሊቀ ጳጳስ ሲሾም ምን አድርጎ ይሾማል አላቸው አላውቅም አልከን እንጂ አንቀጸ አባግዕን አንብቦ ተርጉሞ ይሾማል አላቸው ወዲያው መንፈስ ቅዱስ ገልጦለት አንቀጸ አባግዕን አንብቦ ተርጉሞ በዮልያኖስ ፈንታ ተሾመ ለድሜጥሮስም ቅዳሴ እና መጻሕፍት ተገልጠውለት ሕዝቡን ያስተምራቸው ጀመር። ከንጽሕናውም የተነሳ የሕዝቡ ሁሉ ኃጢአት ይታየው ነበር እና በቅዳሴ ጊዜም ሕዝቡ ሊቆርቡ ሲቀርቡ አንተ በቅተሀል ተቀበል አንተ ንስሐ ግባ እያለ ይመልሳቸው ጀመር። ሕዝቡም “እርሱ ሚስቱን አቅፎ እየተኛ በንጹሁ በዮልያኖስ ፈንታ በመንበረ ማርቆስ ላይ ብናስቀምጠው ጭራሽ ይከለክለን ጀመር በማለት በሐሜት የሚጎዱ ሆነ በዚህ ጊዜም መልአከ እግዚአብሔር ተገልጾለት ሕዝቡ በሐሜት ስለተጎዳ ኢትፍቅድ አድህኖ ርዕስከ ራስህን ማዳንን አትፍቀድ አላ ክሥት ዘሀሎ ማዕከሌከ ወማዕከለ ብእሲትከ አለው በልዕልተ ወይንና በርሱ መካከል ያለውን ንጽሕናቸውን እንዲገልጽላቸው ይነግረዋል። ድሜጥሮስም ሕዝቡ ሁሉ እንጨት እንዲያመጡ ነግሯቸው አንድ አንድ ሸክም ዕንጨት እየያዙ መጡ ያንን እንደ ደመራ አስደምሮ ቅዳሴ ገባ።
የዶ/ር የሮም ተማፅኖ!😭 "ልጄ ፀጋዘአብን አድኑልኝ"
እኔ ዶ/ር የሮም ጌታቸው እባላለሁ።ህመምተኞችን የመርዳት እና የህይወት ተስፋ የመስጠት ሙያ ውስጥ ብኖርም፣ የገዛ ልጄ ፀጋዘአብ "Ewing's Sarcoma" በተባለ አደገኛ የአጥንት ካንሰር ሲሰቃይ መመልከት ግን አቅም አሳጥቶኛል። የ3 ዓመት ከ6 ወር ህፃን፣ ገና መኖር ያልጀመረ ህይወት፣ በካንሰር ህመም ምክንያት ከበሬ ቆሞ እርዳታን ይጠይቃል።
እስካሁን ያደረግነው የኬሞቴራፒ ህክምና በሽታውን ሊገታው አልቻለም። ሀኪሞቹ የልጄን ህይወት ለመታደግ በአስቸኳይ ወደ ውጭ ሀገር ተወስዶ የቀዶ ጥገና ህክምና እንዲያገኝ ወስነዋል። ነገር ግን ለዚህ ህክምና የሚጠየቀው 3.5 ሚሊየን የኢትዮጵያ ብር የኔን የህይወት ዘመን ጉልበት እና አቅም የሚበልጥ ነው።
ለልጄ ህይወት መታደግ ዛሬ የእናንተ የደጋግ ኢትዮጵያውያን እጅ ያስፈልገኛል። የኔ የህክምና እውቀት ዛሬ ለልጄ ምንም ሊፈይድለት አልቻለም፤ የእናንተ ግን የልጄን ህይወት ሊታደግ ይችላል።
በአንድ አባት እሮሮ እማፀናችኋለሁ፤ ፀጋዘአብን ህይወት ለመታደግ የምትችሉትን ያህል ተባበሩኝ። ትንሹ ፀጋዘአብ በፈገግታ እንዲያድግ፣ እናንተ የህይወት ምክንያት ሁኑት። ለልግስናዎ የሚከተሉትን አማራጮች ይጠቀሙ።
Yerom Getachew Bekele
CBE - 1000149557982
Abay Bank - 2091011011819814
Awash Bank - 013201344371300
Tele Birr: +251910119336
ከተለያዩ imports ተመጣጣኝ ዋጋ ያላቸው መድሃኒቶች እና የህክምና እቃዎች በየሰአቱ የሚለቀቁበት ቻናል ነው ።
ቤተሰብ እንዲሆኑ ተጋብዘዋል ︎‼
👇👇👇👇👇👇👇
https://t.me/wholesalerg
💖 🍒 💖
ከትንሣኤ እሁድ በኋላ ያሉ ዕለታት ስያሜ
በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሀዱ አምላክ አሜን፡፡
✞ ሰኞ- ማዕዶት ይባላል፡-
💛
ማዕዶት ማለት መሻገር፣ ማለፍ ማለት ነው፡፡ በዚህ ዕለት በፋሲካችን በክርስቶስ ትንሣኤ ከድቅድቅ ጨለማ ወደ ሚደነቅ ብርሃን፣ ከሞት ወደ ሕይወት፣ ከሲኦል ወደ ገነት፣ ከሃሳር ወደ ክብር መሻገራችንን እናስባለን፡፡
✞ ማክሰኞ- ቶማስ ይባላል፡-
💛
በዚህ ዕለት ቶማስ ጌታን አይቶ ማመኑ፤ "ጌታዬና አምላኬ" ብሎ መመስከሩ ይዘከራል፡፡ ዮሐ.፳፥፳፯-፳፱
✞ ረቡዕ- አልአዛር ይባላል፡-
💛
በዚህ ዕለት ትንሣኤና ሕይወት የሆነው ጌታችን አምላካችን ኢየሱስ ክርስቶስ አልአዛርን ከሞት እንዳስነሳው እናስባለን፡፡ ክርስቶስ የሞትን ስልጣን የሻረ የሕይወት ራስ ፤ የመቃብርን ሥርዓት ያጠፋ ትንሣኤ፡ በድልም ያረገ ንጉሥና የባህርይ አምላክ መሆኑን እንመሰክራለን፡፡
✞ ሐሙስ- አዳም ሐሙስ ይባላል፡-
💛
በዚህ ዕለት ለአዳም የተሰጠው ተስፋ እና የተገባለት ኪዳን እንደተፈጸመ አዳምና ልጆቹ ነጻ እንደወጣን እናስባለን፡፡
✞ አርብ- ቅድስት ቤተክርስቲያን ይባላል፡-
💛
በዚህ ዕለት ቤተክርስቲያን በክርስቶስ ሞትና ትንሣኤ ስለመመስረቷ ይሰበካል፡፡ ክርስቶስ ስለ እርሷ ራሱን አሳልፎ ሰጥቶ ቤዛ ሆኖ በደሙ አንጽቶ በትንሣኤው ድል ሰጥቶ እንዳከበራት ይነገራል፡፡
✞ ቅዳሜ- ቅዱሳት አንስት ይባላል፡-
💛
በዚህ ዕለት ቅዱሳት አንስት የክርስቶስን አካል ሽቶ ለመቀባት ጨለማ አቋርጠው ወደ መቃብር መምጣታቸውና ትንሣኤውንም ቀድመው ማየታቸው ይሰበካል፡፡
✞ እሁድ- ዳግም ትንሣኤ ይባላል፡-
💛
በዚህ ዕለት ክርስቶስ ለሦስተኛ ጊዜ ለደቀ መዛሙርቱ ተገልጦ ሰላምን መስበኩ እና ሥልጣንን መስጠቱ ይሰበካል፡፡
💛
ወስብሐት ለእግዚአብሔር
ወለወላዲቱ ድንግል
ወለመስቀሉ ክቡር አሜን፡
ይህንን ያውቃሉ?
የዶሮ ወጥ እና "12ቱ ብልቶች" (The Symbolism of Doro Wat)
ይህ ደግሞ ለእኛ ለኢትዮጵያውያን በጣም ቅርብ የሆነ እውነታ ነው። በትንሳኤ በዓል የዶሮ ወጥ የማይሰራበት ቤት የለም። ነገር ግን የዶሮ ወጥ አዘገጃጀት ዝም ብሎ ለጥፍጥና ብቻ አይደለም፤ የራሱ ተምሳሌት አለው፦
• 12ቱ ብልቶች፦ ዶሮው በ12 ተቆራርጦ መሰራቱ የ12ቱ ሐዋርያት ተምሳሌት ነው።
• እንቁላሉ፦ በወጡ መሃል የሚቀመጠው እንቁላል ደግሞ የጌታችን ትንሳኤ ምልክት ነው።
• ስለዚህ ዶሮ ወጥ ስትበሉ፣ በሐዋርያት የተሰበከውንና በትንሳኤ የተገኘውን አዲስ ህይወት እያሰባችሁ ነው ማለት ነው።
የትንሳኤ ዕንቁላል (Easter Eggs) ምስጢር
ብዙ ሰዎች "ፋሲካና ዕንቁላል ምን አገናኛቸው?" ይላሉ። ዕንቁላል ለትንሳኤ በዓል ትልቅ ተምሳሌት አለው፦
• ዕንቁላል ከውጭ ሲታይ ዝም ያለ፣ የማይነቃነቅና የሞተ ይመስላል። ነገር ግን በውስጡ ህይወት አለው።
• ልክ ጊዜው ሲደርስ ጫጩቷ ያንን ጠንካራ ገለፈት (ሼል) ሰብራ ወጥታ አዲስ ህይወት እንደምትጀምር፣ ጌታችንም መቃብሩን ድል አድርጎ ተነስቷል።
• በጥንት ዘመን ዕንቁላልን ቀይ ይቀቡት የነበረው፣ በፈሰሰው ደም የተገኘውን አዲስ ህይወት ለመግለጽ ነበር።
ቤተሰብ በሁኔታዎች አለመመቻቸት ተቋርጦ የነበረው የፍቅር እስከ መቃብር ትረካ ክፍል አራት ነገ ይለቀቃል ።
ቻናሉ active እንዲሆን react አድርጉ ‼
በዚሁ አጋጣሚ ለውዷ እናቴ : ለእህቶቸ ለስራ ባልደረቦቸ እና ለወደፊቷ ሚስቴ😜 እና ለሴቶች በሙሉ እንኳን አደረሳችሁ ‼
እንኳን ለሴቶች ቀን አደረሳችሁ !!!
ዛሬ ብቻ ሳይሆን ቀሪ 364 ቀናቶችም የናንተ ናቸው እና ፈታ በሉ ‼
ሞክሩት !!
task መስራት እና refer ማድረግ ነው ።
https://t.me/PayneeX_bot?startapp=525016391
ሞክሩት !!
task መስራት እና refer ማድረግ ነው ።
https://t.me/PayneeX_bot?startapp=5250163910
Gmail ভাড়া দিন - ইনস্ট্যান্ট ইনকাম শুরু!
🔰 কিছু না বুঝলে আগে টিউটোরিয়াল দেখুন
এই ইউটিউব চ্যানেলে পুরো কাজের সমস্ত টিউটোরিয়াল আছে👇
https://youtube.com/channel/UCYuCyEebREjQzksgjbAf8GQ?si=PGl3GXs53zre7uj7
📩 Gmail ভাড়া দিন - ইনস্ট্যান্ট ইনকাম শুরু!
নতুন/পুরনো/ভেরিফাইড-যে কোনো Gmail ভাড়া দিতে পারবেন ✅
অ্যালগরিদমের মাধ্যমে অটোমেটিক ইনকাম শুরু হবে 💸
💰 মাত্র ৫০ টাকা হলেই উইথড্র!
🚀 শুরু করতে ক্লিক করুন👇
https://t.me/cookiesvara_bot?start=6685689621
#OnlineIncome #GmailRent #EarnMoney #Bangladesh
