ru
Feedback
ሰዋስው ☘☘☘☘

ሰዋስው ☘☘☘☘

Открыть в Telegram

በሰዋስወ ብርሀን ቅዱስ ዻውሎስ ገዳም እና ለተለያዩ ቤተክርስቲያን ለክብረ በአላት ማውጫ ። በተጨማሪም-ዋዜማ ሥርዓተ ማኅሌት - መዝሙራት ስንክሳር - የየእለቱን ምስባክ ቅኔያት ጥያቄዎች እንዲሁም የወቅታዊ ነገር መወያያ በተጨማሪም @eotcww ብለው ይቀላቀሉን ለወዳጅ ዘመድዎ share#Share#Share# ያድርጉ።

Больше
1 161
Подписчики
Нет данных24 часа
Нет данных7 дней
Нет данных30 дней
Архив постов
photo content

❤ "በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። ❤ ❤ መጋቢት ፳፭ (25) ቀን። ❤ እንኳን ከሰባ ሁለቱ አርድእት ለአንዱ ጌታችንም በአገረ ናይን የመበለቲቱን ልጅ በአስነሣው ጊዜ አይቶ ከአይሁድነት በኢየሱስ ክርስቶስ አምኖ ለተከተለው ለከበረና ለተመሰገነ ለሐዋርያ ለቅዱስ አንሲፎሮስ ለዕረፍት በዓልና ለዘመነ ሐጋይ(በጋ) መውጫ በሰላም አደረሰን። + + + ❤ ሐዋርያ ቅዱስ አንሲፎሮስ፦ ይህም ከእስራኤል ልጆች ከብንያም ነገድ ነው። ወላጆቹም የኦሪትን ሕግ የሚጠብቁ ናቸው። እርሱም ሥራዎቹን በአየ ጊዜ ትምህርቶቹንም በሰማ ጊዜ ጌታችንን ተከተለው። ❤ ድንቅ የሆኑ ተአምራቶችን እየተመለከተ ጥቂት ቀን ተቀመጠ ጌታችንም በአገረ ናይን የመበለቲቱን ልጅ በአስነሣው ጊዜ ከዚያ ነበር። ይህን አይቶ ወዲያውኑ አመነ ሌላ ምልክት አልሻም ብልጭ ብልጭ ሲል የነበረ የአይሁድ የሕግ ፋናን ትቶ ወደ እውነተኛ ፀሐይ ወደ ጌታ ኢየሱስ ቀርቦ ደመ መዝሙሩ ሆነው እንጂ። ❤ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከዐረገ በኋላ በጽዮን አዳራሽ አጽናኝ መንፈስ ቅዱስ በወረደ ጊዜ ከሐዋርያት ጋራ የመንፈስ ቅዱሳን ጸጋ ተቀብሎ የሐዋርያትንም በመከተል በብዙ አገሮች አስተማረ። ❤ ሐዋርያትም በአገረ አቴና ኤጲስቆጶስ አድርገው ሾሙት በውስጥዋም ወንጌልን በመስበክ ብዙዎችን አሳመነ የክርስትና ጥምቀትንም አጠመቃቸው በትምህርቱና በምክሩ ዕውቀት እንዲያድርባቸው አደረጋቸው በትምህርቱም ከደዌ ሥጋ ከደዌ ነፍስ ፈወሳቸው። ❤ ተጋድሎውንም በፈጸመ ጊዜ መጋቢት25 በሰላም ዐረፈ። በድል አድራጊነትም የክብር አክሊል ተቀበለ። መላ ዘመኑ ሰባ ዓመት ነው። በአይሁድ ሕግ ሃያ ዘጠኝ ዓመት በክርስትና ሕግ አርባ አንድ ዓመት ኖረ። ❤ እንሆ የከበረ ሐዋርያ ቅዱስ ጳውሎስም በመልእክቶቹ አስታውሶታል ሰላምታም አቅርቦለታል። ከሐዋርያ ቅዱስ አንሲፎሮስ በጸሎቱ የምትገኝ በረከቱ ከእኛ ጋራ ለዘላለሙ ትኑር አሜን። ምንጭ፦ የመጋቢት25 ስንክሳር። + + + ❤ "ሰላም ለአንሲፎሮስ እግዚአብሔር ዘጸውዖ። ምስለ ሐዋርያት በጽዮን መንፈስ ቅዱስ ይቅብዖ። ለወልደ መበለት ምውት በሀገረ ናይን ጊዜ አንሥኦ። መንክሮ ነጺሮ ወትምህርተ ቃሉ ሰሚዖ። ለወልደ ማርያም አብደረ ከመ ይኩን ረድኦ"። ሊቁ አርከ ሥሉስ (አርኬ) የመጋቢት 25። @sigewe https://t.me/eotcw

photo content
+2

❤ "በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። ❤ ❤ እንኳን ለቢይ ጾም ስድስተኛ ሳምንት ለገብር ኄር እግዚአብሔር አምላክ በሰላምና በጤና አደረሰን። + + + ❤ የገብር ኄር መዝሙር፦ "መኑ ውእቱ ገብር ኄር ወምዕመን ዘይረክቦ እግዚኡ በምግባረ ሠናይ ወይሠይሞ ዲበ ኵሉ ንዋዩ ካዕበ ይቤሎ እግዚአብሔር ገብር ኄር ወምዕመን ዘበውኁድ ምዕመነ ኮንከ ዲበ ብዙኅ እሠይመከ ባዕ ውስተ ፍሥሓሁ ለእግዚእከ"። ትርጉም፦ በመልካም ሥራ ጌታው ያገኘው በጎ ታማኝ አገልጋይ ማነው? በንብረቱ ላይ ሁሉ የሚሾመው ታማኝ በጎ አገልጋይ ማነው? ዳግመኛም እግዚአብሔር አንተ በጎ ታማኝ አገልጋይ በጥቂቱ ታምነሃልና በብዙ እሾምሃለሁ፤ ወደ ጌታህ ደስታ ግባ አለው። + + + ❤ ገብር ኄር፦ ማለት ቸር አገልጋይ ማለት ነው። ገብር ኄር ተብሎ በወንጌል የሚነገረው ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርሰቶስ በመዋዕለ ሥጋዌው ሲያስተምር ካስተማረቸው ትምህርት አንዱ ነው። እንዲህ ሲል ይጀምራል፦ ወደ ሌላ ሀገር የሚሄድ ሰው ባሮቹን ጠርቶ ገንዘብ እንደሰጣቸው እንዲሁ ይሆናል ። ❤ ለእያንዳዱም እንደያቅማቸው ለአንዱ አምስት መክሊት፤ ለአንዱም ሁለት መክሊት፤ ለአንዱም አንድ መክሊት አድርጎ ሰጣቸውእና ወደ ሌላ ሀገር ወዲያው ሄደ። አምስት የተቀበለውም ነግዶ ሠርቶ አምስት ሌላ መክሊት አተረፈ፤ ሁለት የተቀበለውም እንደዛው ሁለት መክሊት አተረፈ፤ አንድ የተቀበለው ግን ምድር ቆፍሮ የጌታውን ገንዘብ ቀበረ ። ❤ ከብዙ ዘመን በኀላ የእኒዚያ ባሮቾ ጌታ መጥቶ ተቆጣጣረቸው የሰጠዋችሁስ ገንዘብ አላቸው ። ባለአምስቱም፤ "ጌታ ሆይ አምስት መክሊት ሰጥተኸኝ ነበር ይኸው ሌላ አምስት መክሊት አትሪፊያለው" ብሎ መክሊቱን አስረከበ ጌታውም "አንተ መልካም ተማኝ ባሪያ በጥቂቱ የታመንክ በብዙ እሾምሃለው ወደ ጌታህ ደስታ ግባ" አለው። ሁለተኛውም "ጌታ ሆይ ሁለት መክሊት ሰጥተኸኝ ነበር ሌላ ሁለት አተረፍኩ" ብሎ መክሊቱን አስረከበ ጌታውም "አንተ መልካም ታማኝ ባሪያ በጥቂቱ የታመንክ በብዙ እሾምሃለው ወደ ጌታህ ደስታ ግባ" አለው። ባለአንዱም መክሊት ወደ ጌታው ቀረበ እንዲህም አለ "አንተ ካልዘራኅበት የምታጭድ ካልበተንክበት የምትሰበሰብ ጨካኝ ሰው መሆንክን አውቃለሁ ፈርቼም የሰጠኸኝን መክሊት ቀበርኩት እነሆ መክልቲህን" ብሎ ምንም ሳያተርፍ ሰጠው። ጌታውም "አንተ ክፉ እና ኀኬተኛ ባሪያ እኔ ካልዘራውበት የማጭድ ካልበተንኩት የምሰበስብ መሆኔን ታውቃለህን? ስለዚህ ገንዘቤን ለለዋጮች አደራ ልትሰጠው በተገባህ ነበረ እኔም መጥቼ ከትርፉ ጋር መጥቼ እወስድ ነበር ፣ ስለዚህ መክሊቱን ውሰዱበት አስር ላለውም ጨምሩለት ላለው ይሰጠዋል ( ይጨመርልታል ) ለሌለው ያለውም ያለው ይወሰድበታል የማይጠቅመውንም ባሪያ በውጭ ወዳለው ጨለማ አውጡት በዚያ ልቅሶና ጥርስ ማፋጨት ይሆናል" አለው። ❤ መክሊት የተባለ ጸጋ ስጦታ ሲሆን እግዚአብሔር ለእያንዳንዳችን የተለያየ ስጦታ ሰጥቶናል፡፡ በተሰጠንም ስጦታ ልናገለግልበት ያስፈልጋል፡፡ በተጨማሪ መክሊት ቃለ እግዚአብሔር ነው፡፡ የሰማናትን ቃለ እግዚአብሔር ለሌላው ማሰማት ይገባናል ፡፡ ከእኛ የሚጠበቀው ማሰማቱ ብቻ ነው፡፡ በልቦናው አድሮ ሥራ የሚሠራ እግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ ነው፡፡ ❤ ወዳጆቼ ስንቶቻችን የተሰጠንን መክሊት ቀብረን ይሆን? ይህ ሰው በመፍራት እና ጌታውን ባለማመን የተሰጠውን መክሊት ቀበረ ዛሬም እኮ እኛ ከክርስቶስ የተሰጠንን ፍቅር እና አንድነት ቀብረነዋል ዛሬም እኮ ሃይማኖታችንን በፍርሃት ባለመመስከር ቀብረነዋል ዛሬም እኮ እኛ ከፈጣሪ ያገኘነውን በጎነት ደግነት ቀብረነዋል በዘመናችን ከፈጣሪ የተቀበል ናቸው ፤መክሊት ተቀብረው እኮ ነው ሰላም የጠፋው ሰው እንደ በግ የሚታረደው!። ❤ ወዳጆቼ ማነው መክሊቱን ያልቀበረ አምስት ተሰጥቶት አምስት ያተረፈ ሁለት ተሰጥቶት ሁለት ያተረፈ ይኖር ይሆን ጌታው ሲመጣ "መልካም ታማኝ ባሪያ በጥቂቱ የታመንክ በብዙ እሾምሀለው ወደ ጌታህ ደስታ ግባ የሚባል ማን ይሆን? ሁላችንም የቀበርነውን መክሊት አለ አውጥተን እናትርፍበት ካህኑ እንደ ክህነቱ መምህሩ እንደ መምህርነቱ ዘማሪው እንደ ዘማሪነቱ ምዕመኑ እንደ አማኝነቱ ሁሉም መክሊቱን ከቀበረበት አወጥቶ በተሰጠው መክሊት ልክ ያትርፍበት አለበለዚያ የመክሊቱ ባለቤት ሲመጣ መልሳችን ምን ሊሆን? ፈርቼህ በምድር ቀበረሁት የሰጠኸኝ መክሊት ይኸው ውሰድ ይኽንን ከማለት ፈጣሪ ይሰውረን! አሜን። + + + + የገብር ኄር ዓራራይ ዜማ፦ ሃሌ ሉያ "ኩኑ እንከ ከመ አግብርት ኄራን ወከመ አግብርተ ክርስቶስ ምዕመናን እለ ይጸንሑ እግዚኦሙ እስከ የዐቱ እምከብካብ ዘበሰማያት ያከብርዋ ለሰንበት"። ትርጉም፡- እንግዲህ እንደቸሮች ባለምዋሎች ሁኑ እንደየክርስቶስ አገልጋዮ ምእመናን ጌታቸውን ደጅ ለሳማያዊው ሠርግ እስኪከፍት ሰንበትን ያከብሯታል። ሊቁ ቅዱስ ያሬድ በጾመ ድጓው ላይ። + + + ❤ የዕለቱ ምስባክ፦ "ከመ እንግር ፈቃደከ መከርኩ አምላኪየ። ወሕግከኒ በማእከለ ከርሥየ። ዜኖኩ ጽድቀከ በማኅበረ ዓቢይ"። መዝ 39፥8-9። የሚነበቡት መልዕክታት 2ኛ ጢሞ 2፥1-16፣ 1ኛ ጴጥ 5፥1-12 እና የሐዋ ሥራ 1፥6-9። የሚነበበው ወንጌል ማቴ 25፥14-31። የሚቀደሰው ቅዳሴ የቅዱስ ባስልዮስ ቅዳሴ ነው። መልካም የጾም ጊዜና በዓል ለሁላችንም ይሁንልን። https://t.me/eotcw

photo content

❤ "በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። ❤ + + + ❤ "ሰላም ለፅንሰትከ ወለልደትከ እምከርሥ። አመ እሥራ ወረቡዑ ለወርኀ ታኅሣሥ። ተክለ ሃይማኖት በኵሉ ወበውስተ ኵሉ ውዱስ። ናሁ ወጠንኩ ወእቤ ለስብሐቲከ ሐዲስ በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ"። ትርጉም፦ ተክለ ሃይማኖት ሆይ፤ አስቀድሞ በማኅፀን ለተፀነሰከው ፅንሰትህና በታኅሣሥ ሃያ አራት ቀን ለተኸለድክበት መወለድህ ሰላም እላለሁ። ቅዱስ አባት፤ ሁሉ በሁሉ የተመሰገንህ ነህና እኔም በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ ብዬ እነሆ አዲስ ምስጋናን እጀምራለሁ። መልክአ አቡነ ተክለ ሃይማኖት።

photo content
+1

እንቢ ማለቱ ነው፡፡ ይህን ሥልጣን ቀድሞ ለሐዋርያት ሰጥቻቸው ነበር፡፡ ከሐዋርያትም ሹመትን የተቀበለ ጳጳሱ ትሾምና ትሽር፣ ትተክልና ትነቅል ዘንድ ሥልጣንን ሰጠህ፡፡ ይህንንም ያደረኩልህ የጳጳሱን ቃል በመናቅ አይደለም፡፡ የፍቅሬን ጽናት ባንተ እገልጽ ዘንድ ነው እንጂ፡፡ ሐዋርያት ወዳልደረሱበት ሕዝብ በመምህርነት እልክህ ዘንድ በሚካኤል ቃል አዲስ ስም አወጣሁልህ፡፡ አንተም በማናቸውም ሥራ ከእነርሱ አታንስም፣ ሐዲስ ሐዋርያ አድርጌሃለሁና፡፡ ሰውን ሁሉ በእኔ ስም እያስተማርክ ታሳምን ዘንድ፣ ሚካኤልም ባሰብከው ሥራ ሁሉ ረዳት ይሁንህ፣ ሁል ጊዜ ካንተ አይለይም፤ በምትሄድበትም ጎዳና ሁሉ እርሱ መሪ ይሁንህ፤ እኔም ባለ ዘመንህ ሁሉ አልለይህም" ካላቸው በኋላ ሰላምታ ሰጥቷቸው ዐረገ፡፡ ❤ ብፁዕ አባታችንም እጅ ነሥተው ለእኔ ለኀጥኡ የማይገባኝ ሲሆን ይህን ሁሉ ጸጋ የጠኸኝ ስምህ በሰማይ በምድር የተመሰገነ ይሁን" አሉ፡፡ ከዚያች ቀን ጀምሮ ሀብተ ኃይልን የተመሉ ሆኑ፡፡ ወደቤታቸው ተመልሰው ያላቸውን ሀብት ንብረት ሁሉ ለቤተ ክርስቲያን፣ ለድኆችና ለጦም አዳሪዎች ሰጥተው ጨረሱ፡፡ ከዚያም "አቤቱ ጌታዬ ኢየሱስ ክርስቶስ ሆይ! የመንግሥተ ሰማያትን በር ትከፍትልኝ ዘንድ እነሆ ቤቴን እንደተከፈተ ተውኩልህ" ብለው ቤታቸውን እንደተከፈተ ትተው ወንጌልን ለማስተማር ወጡ፡፡ ጻድቁ አባታችን በሀገራችን ኢትዮጵያ እየተዘዋወሩ ሕዝቡን ከኃጢአት ወደ ገቢረ ጽድቅ፣ ከክህደት ወደ ኃይማኖት ስለመለሱት በዚህም የተነሣ ለኢትዮጵያውያን ብርሃን ተብለዋል፡፡ ከአባታችን ከአቡነ ተክለሃይማኖት እግዚአብሔር አምላክ ረድኤትና በረከትን ያሳትፈን። ምንጭ፦ መዝገበ ቅዱሳን። ❤ በየቀኑ ይህን ቴሌግራም ላይ ማግት ከፈለጉ ከታች ያለውን ሊንክ ተጭነው ይቀላቀሉ። @sigewe https://t.me/eotcw

❤ "በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። ❤ ❤ መጋቢት ፳፫ (24) ቀን። ❤ እንኳን እንኳን ለታላቁ አባት ለሐዲስ ሐዋርያ ለኢትዮጵያ ብርሃኗ ለሆኑት ለአቡነ ተክለ ሃይማኖት ለፅንሰታቸው በዓል በሰላም አደረሰን። + + + ❤ አቡነ ተክለ ሃይማኖት (ፅንሰታቸው)፦ እግዚአብሔር አምላካችን ለኢትዮጵያ ሐዲስ ሐዋርያ አድርጎ የመረጣቸው ጻድቁ አባታችን ተክለ ሃይማኖት በሊቀ መላእክት በቅዱስ ሚካኤል አብሳሪነት ከአባታቸው ከካህኑ ጸጋ ዘአብና ከእናታቸው ከቅድስት እግዚእ ኀረያ መጋቢት 24 ቀን ተፀንሰው ታኅሣሥ 24 ቀን 1197 ዓ.ም ተወለዱ፡፡ ጻድቁ በተወለዱ በሦስተኛው ቀን ከእናታቸው ዕቅፍ ወርደው "አሐዱ አብ ቅዱስ አሐዱ ወልድ ቅዱስ አሐዱ ውእቱ መንፈስ ቅዱስ" ማለትም "አንዱ አብ ቅዱስ ነው አንዱ ወልድ ቅዱስ ነው አንዱ መንፈስ ቅዱስ ቅዱስ ነው" በማለት የፈጠራቸውን አምላክ አመስግነውታል፡፡ ወላጆቻቸውም ስማቸውን ፍሥሐ ጽዮን አሏቸው፡፡ ይኸውም የጽዮን ተድላዋ ደስታዋ ማለት ነው፡፡ የወላጆቻቸው የቀድሞ ስማቸው ዘርዐ ዮሐንስና ሣራ ይባል ነበር፡፡ ❤ ቅዱሳን አባቶቻችን እነ አቡነ ተክለ ሃይማኖትና እነ አቡነ ዜና ማርቆስ ሌሎቹም እነ አቡነ ሳሙኤል ዘወገግ፣ አቡነ ሕፃን ሞዐ፣ አቡነ አኖሪዮስ (ትልቁ)፣ አቡነ ገላውዲዮስ፣ አቡነ ማትያስ ዘፈጠጋርና አቡነ ቀውስጦስ ዘመሐግል የትውልዳቸው መሠረት ኢያሱ ለሌዋውያን ክፍል ትሆን ዘንድ ከለያት ከኢየሩሳሌም ነው፡፡ ስማቸውን የጠቀስኳቸው እነዚህ ቅዱሳን አባቶቻችን የወንድማማቾች ልጆች ሲሆኑ ከአዳም ጀምሮ 61ኛ ትውልድ ናቸው፡፡ ይኸውም እንዴት ነው ቢሉ ትውልዱ ከአዳም ጀምሮ በካህኑ አሮን በኩል የሆነውና የሌዋዊያን ሊቀ ካህን የነበረው የሳዶቅ ልጅ አዛርያስ በንጉሥ ሰሎሞን ዘመን ከታቦተ ጽዮንና ከብዙ ሌዋዊያን ካህናት ጋር ሊቀ ካህን ሆኖ ከኢየሩሳሌም ወደ ኢትዮጵያ መጥቶ አክሱም ተቀምጦ ኖረ፡፡ የኦሪትንም ሕግ እየዞረ ለኢትዮጵያ ሰዎች አስተማረ:: ትውልዱም በአብርሃ ወአጽብሓና በአባ ሰላማ ዘመን እስከነበረው እንበረም የሚባለው ጻድቅ ድረስ ደረሰ፡፡ የእንበረምም ትውልድ ደገኛው ሕይወት ብነ በጽዮን ድረስ ደረሰ፡፡ ሕይወት ብነ በጽዮንም የደማስቆ ምድር ከሚሏት ከወለቃ ሀገር የመኰንን ልጅ የሆነችውን ወለተ ሳውልን አግብቶ አበይድላን ወለደ፡፡ አበ ይድላም በንጉሡ ድልዓዥን ዘመነ መንግሥት ለ150 ካህናት አለቃ ሆኖ በወለቃ ሀገር የክርስቶስን የወንጌል ሕግ እያስተማረ ብዙዎችን አጠመቀ፡፡ እስከ ሸዋ ምድር ድረስ እያስተማረ መጥቶ በሸዋ ምድር ተቀመጠ፡፡ ብዙ አብያተ ክርስቲያናትንም አሳነጸ፡፡ እጅግ አስደናቂ ተአምራትንም ያደርግ ነበር፡፡ "በሸዋ ጽላልሽ ተቀምጦ ሲያስተምርም በአንዲት ቀን እስከ ሁለት መቶ ሺህ ሕዝብ ያጠምቅ ነበር" በማለት ገድለ አቡነ ተክለ ሃይማኖት ይመሰክርለታል፡፡ ❤ አበይድላ በመጨረሻ በፈቃደ እግዚአብሔር ከሸዋ ጽላልሽ ምድረ ዞረሬ ሚስት አግቶ ሀበነ እግዚእን ወለደ፤ ሀበነ እግዚእም በኩረ ጽዮንን ወለደ፤ በኩረ ጽዮንም ሕዝበ ቀድስን ወለደ፤ እርሱም ነገደ እግዚእ የተባለ ነው፡፡ ሕዝበ ቀድስም ብርሃነ መስቀልን ወለደ፤ እርሱም ዐቃቢነ እግዚእ የተባለ ነው፡፡ ብርሃነ መስቀልም ሕይወት ብነን ወለደ፤ እርሱም ሴትን ወለደ፡፡ ሴትም ወረደ ምሕረትን ወለደ፡፡ ወረደ ምሕረትም ዘካርያስን ወለደ፡፡ ዘካርያስም የእነ አቡነ ተክለ ሃይማኖት አባት የሆኑ 6 ወንድማማች ልጆችን ወለደ፡፡ እነርሱም እንድርያስ፣ አርከሌድስ፣ ዘርዐ አብርሃም፣ ዘርዐ ዮሐንስ ወይም ጸጋ ዘአብ፣ ቀሲስ ዮሐንስና ቀሲስ ዮናስ ናቸው:: እንድርያስም ሳሙኤል ዘወገግን ወለደ፤ አርከሌድስም ሕፃን ሞዐን ወለደ፤ ዘርዐ አብርሃምም ታላቁን አኖርዮስን ወለደ፤ ዘርዐ ዮሐንስ ወይም ጸጋ ዘአብም ተክለ ሃይማኖትን ወለደ፤ ቀሲስ ዮሐንስም ዜና ማርቆስን ወለደ፣ ቀሲስ ዮናስ ደግሞ የፈጠጋሩን ማትያስንና ገላውዲዮስን ወለዳቸው፡፡ ገላውዲዮስም የመሐግሉ ቀውስጦስን ወለደ፡፡ እነዚህ ደጋግ ቅዱሳን በእናታቸውም በኩል እንዲሁ በዝምድና የተሳሰሩ ናቸው፡፡ ማቴዎስ የተባለው ደገኛ ክርስቲያን የሸዋ ገዥ የነበረ ሲሆን አንድ ወንድ ልጅ መድኃኒነ እግዚእንና ሦስት ሴቶች ልጆችን ወለደ፡፡ ሶስቱ ሴቶች ልጆችም እምነ ጽዮን፣ ትቤ ጽዮንና ክርስቶስ ዘመዳ ይባላሉ፡፡ ሦስቱ እኅትማማቾችም ደጋጎቹን አባቶቻችንን ወለዱልን፡፡ እምነ ጽዮን የእነ ዜና ማርቆስን እናት ማርያም ዘመዳንና ወለደች፡፡ ትቤ ጽዮንም ሕፃን ሞዐን ወለደች፡፡ ክርስቶስ ዘመዳ ደግሞ ታላቁን አኖሬዎስን ወለደች፡፡ የፈጠጋሩ ገዥ መድኃኒነ እግዚእ ደግሞ የተክለ ሃይማኖትን እናት እግዚእ ኀረያን ወይም በሌላ ስሟ ሣራን ወለደ፡፡ ❤ አቡነ ተክለ ሃይማኖት ከልጅነታቸው ጀምሮ በወላጅ አባታቸው በካህኑ ቅዱስ ጸጋ ዘአብ ግብረ ዲቁናን ሥርዓተ ቤተ ክርስቲያንን ሲያጠኑ ቆይተው በ15 እና በ22 ዓመታቸው ከእስክንድርያው ሊቀ ጳጳስ ከአቡነ ቄርሎስ (ጌርሎስ) ዲቁናንና ቅስናን ተቀብለዋል፡፡ ብፁዕ ወቅዱስ አባታችን ቅድስት ቤተክርስቲያንን በወጣትነት ዕድሜያቸው ያገለግሉ እንደነበር በዚህ ይታወቀል፡፡ ❤ ከዕለታት በአንዱ ቀን አባታችን ከጓደኞቻቸው ጋር ለአደን ወደ ዱር ሄደው ሳለ ሊቀ መላእክት ቅዱስ ሚካኤል ተገልጦ ታያቸው፡፡ ቅዱስ አባታችንም "እንደዚህ ባለ ገናንነት የማይህ ጌታዬ ማነህ?" ባሉት ጊዜ ቅዱስ ሚካኤል "ዘወትር የምጠብቅህ ካንተ የማልለይ እናትህንና አባትህንም ስላንተ ከውኃ ስጥመትና ከምርኮ ያዳንኳቸው እኔ ሚካኤል ነኝ፡፡ ከእንግዲህ አውሬ አዳኝ አትሁን፤ ሰውን ወደ እግዚአብሔር ለመመለስ ሰውን በትምህርት የምታድን ሁን እንጂ፡፡ እነሆ እግዚአብሔር ጽኑዕ ሥልጣን ሰጥቶሃልና፤ ሙት ታስነሣለህ፤ ድውያንን ትፈውሳለህ፤ አጋንንትም አንተን በመፍራት ይሸሻሉ፡፡ ስምህ ፍሥሐ ጽዮን አይሁን፤ ተክለ ሃይማኖት ይሁን እንጂ፡፡ ትርጓሜውም ተክለ አብ፥ ተክለ ወልድ፥ ተክለ መንፈስ ቅዱስ ማለት ነው" አላቸው፡፡ ❤ ቅዱስ ሚካኤል ይህን ሲነግራቸው ጌታችን በሥጋ ከደቀ መዛሙርቱ ጋር እንደነበር ሆኖ መልከ መልካም ጎልማሳ መስሎ ታያቸው፡፡ ጌታችንም "ወዳጄ እንዴት ሰነበትክ? ቸር አለህን?" አላቸው፡፡ አቡነ ተክለ ሃይማኖትም "ጌታዬ ሆይ አንተ ማነህ?" ብለው ሲጠይቁት ጌታችንም "እኔ የዓለም መድኃኒት ኢየሱስ ነኝ፤ በናትህ ማኅፀን ፈጥሬህ ያከበርኩህ እኔ ነኝ፡፡ በተወለድክ በሦስተኛው ቀን አሐዱ አብ ቅዱስ አሐዱ ወልድ ቅዱስ አሐዱ ውእቱ መንፈስ ቅዱስ ብለህ ታመሰግነኝ ዘንድ የምስጋና ሀብት ያሳደርኩብህ እኔ ነኝ፡፡ በርሃብ ዘመን በቤት የሚያሻው ምግብ ሁሉ ቅቤው፣ የስንዴው ዱቄት በእናት በአባትህ ቤት ይመላ ዘንድ በእጅህ ሀብተ በረከት ያሳደርኩብህ እኔ ነኝ፡፡ ያንን ሰው አንተን በተጣላ ጊዜ በነፋስ አውታር የሰቀለኩት በመዓት ጨንገር የገረፍኩት እኔ ነኝ፡፡ ውኃ ጠምቶህ በለመንከኝ ጊዜ ከደረቅ መሬት የጣፈጠ ውኃ ያመነጨሁልህ እኔ ነኝ፡፡ ከልጅነትህ ጀምሮ እስከ ዛሬ ድረስ ብዙ ተአምራት እያደረግሁ በአንተ እጅ የታመሙትን ያዳንኳቸው እኔ ነኝ፡፡ ወደፊትም አደርግልሃለሁ" አላቸው፡፡ ይህንን ብሎ በእጆቹ ባረካቸውና "ንሣእ መንፈስ ቅዱስ" ብሎ የሹመትን ሀብት አሳደረባቸው፡፡ ዳግመኛም "በምድር ያሰርከው በሰማይ የታሰረ ይሁን፤ በምድርም የፈታኸው በሰማይ የተፈታ ይሁን፤ አንተን የሰማ እኔን መስማቱ ነው፤ የላከኝ አባቴንም መስማቱ ነው፡፡ አንተን እንቢ ያለ እኔን እንቢ ማለቱ ነው፡፡ የላከኝ አባቴንም

❤ "በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። ❤ + + + ❤ "ሰላም ለዳንኤል ነቢይ ሠናይ ውርዙት ምሉአ መንፈስ ማእማረ ኅቡኣት ዘተወድየ ውስተ ግበ አናብስት"። ትርጉም፦ በአንበሶች ጒድጓድ ውስጥ የተጣለ የተሰወሩትን ለሚያውቅ መንፈስ ቅዱስን ለተመላና መልካም ጐልማሳነት ላለው ለነቢዩ ለዳንኤል ሰላምታ ይገባል። ሊቁ አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ በተአምኆ ቅዱሳን ላይ። https://t.me/eotcw

❤ እግዚአብሔር መልአኩን ወደ ዕንባቆም ላከው እርሱም በኢየሩሳሌም ውስጥ ለአጫጅዎች ምሳ ተሸክሞ ሲሔድ በራስ ጠጉሩ ተሸከመው። ወስዶም ዳንኤል በአለበት ጒድጓድ ውስጥ አኖረው ዳንኤልም ተመግቦ እግዚአብሔርን አመሰገነው በዕንባቆምም ቃል ተረጋጋ በዚያችም ሰዓት እግዚአብሔር የላከው መልአክ ወደ አገሩ ወደ ኢየሩሳሌም መልሶ አደረሰው። ❤ በሰባተኛዪቱ ቀንም ስለ ዳንኤል እያለቀሰ ንጉሡ ወደ ጒድጓዱ መጣ ዳንኤል ሙቶ አንበሶች የበሉት መስሎት ነበርና። ወደ ጒድጓዱም ሲመለከት ዳንኤልን አየው አንበሶችም እንደ ድመቶች እግሮቹን እየላሱ ከእግሮቹ በታች እጥፍጥፍ ብለው ተኝተው ነበር። ንጉሡም "እግሮቹን እስከሚልሱ እንደ ድመቶች አንበሶችን ያገረመለትና ያስገዛለት የዳንኤል አምላክ ታላቅ ነው ብሎ ከፍ ባለ ድምፅ ጮኸ"። ❤ በዚያን ጊዜ ዳንኤልን ከጒድጓድ እንዲያወጡት እነዚያንም የዳንኤልን ጠላቶች ይዘው ለአንበሶች ወደ ጒድጓድ እንዲጥሏቸው ንጉሥ አዘዘ ወዲያው እነዚያ አንበሶች በንጉሡ ፊት በሏቸው። ❤ ዳንኤልም የእስራኤል ልጆች ወደ ኢየሩሳሌም እስከ ሚመለሱበት ጊዜ በባቢሎን ኖረ እርሷም ሰባ ዘመን ናት ከዚያም በኋላ መጋቢት23 በሰላም በፍቅር ዐረፈ። ከቅዱስ ዳንኤል በጸሎቱ የምትገኝ በረቱ ከእኛ ጋራ ለዘላለሙ ትኑር አሜን። + + + ❤ በዚች ቀን በጌታችን ላይ ሊመክሩ የአይሁድ ማኅበር በቀያፋ ቤት ተሰበሰቡ። ይቅርታውና ቸርነቱ ከእኛ ጋር ለዘላለሙ ይኑር አሜን። ምንጭ፦ የመጋቢት 23 ስንክሳር። + + + ❤ "ሰላም ዳንኤል እንተ ፈከረ በቃሉ። ሕልመ ንጉሥ ሥውረ እንዘ ትርጓሜ ያተሉ። ተዘኪሮሙ ረድኤተ ዘተውህበቶ እምላዕሉ። ሶበ በጸሎት አምላክ ዳንኤል ይብሉ። እምአፈ አናብስት ድኅኑ ሰማዕታት ኵሉ"። ሊቁ አርከ ሥሉስ (አርኬ) የመጋቢት 23። + + + ❤ የዕለቱ ምስባክ፦ "ወገሠፀ ነገሥተ በእንቲአሆሙ። ወኢትግሥሡ መሲሐንየ። ወኢታሕስሙ ዲበ ነቢያትየ"። መዝ 104፥14-15። የሚነበቡት መልዕክታት ዕብ 11፥32-ፍ.ም፣ 2ኛ ጴጥ 1፥19-ፍ.ም እና የሐዋ ሥራ 7፥51-55። የሚነበበው ወንጌል ማቴ 21፥18-23። የሚቀደሰው ቅዳሴ የእመቤታች የማርያም ቅዳሴ ነው። መልካም የጾም ጊዜና በዓል። ለሁላችንም ይሁንልን። ❤ በየቀኑ ይህን ቴሌግራም ላይ ማግት ከፈለጉ ከታች ያለውን ሊንክ ተጭነው ይቀላቀሉ። @sigewe https://t.me/eotcw

❤ "በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። ❤ ❤ መጋቢት ፳፫ (23) ቀን። ❤ እንኳን ከአራቱ ዐበይት ነቢያት ለአንዱ የዮናኪር ሴት ልጁ ለወለደችው ለታላቁ ነቢይ ለቅዱስ ዳንኤል ለዕረፍት በዓል መታሰቢያ በዓል በሰላም አደረሰን። + + + ❤ ነቢዩ ቅዱስ ዳንኤል፦ ናብከደነጾርም ኤየሩሳሌምን በወራራት ጊዜ አባታቸው ዮናኪር አናንያን አዛርያና ሚሳኤልን ሦስቱን ልጆቹን የልጁን ልጅ ዳንኤልንም ወሰዳቸው ከእርሳቸውም ጋር ከእስራኤል ልጆች ብዙ ሰዎች ተማረኩ። ይህም ዮናኪር የንጉሡ የኢዮአቄም ልጅ ነው። ❤ ኢሳይያስ ለሕዝቅያስ ንጉሥ ትንቢት እንደተናገረ የቤተ መንግሥቱንና የቤተ እግዚአብሔርን እቃ ሁሉ ናብከደጾር ወደ ባቢሎን ወደሰደ። ❤ ይህ ዳንኤል በእድሜው ታናሽ ነበር ፍጽም የሆነ ታላቅ ተጋድሎ ተጋደለ የእግዚአብሔር መንፈስ አድሮበት በባቢሎን አገር ትንቢት ሲናገር ኖረ። ❤ ምርኮ በሆነ በአራተኛው ዓመት ናቡከደነፆር የምታስፈራ ራእይ አየ ከእቅልፉም በነቃ ጊዜ ያች ህልም እረሳት በባቢሎን የሚኖሩትን ሁሉ ጥበበኞች ሰበሰባቸው ከርሳቸውም ያች ራእይ ትርጓሜዋን እንዲነግሩ ፈለገ እነርሱ ግን ያች ራእይ ትርጓሜዋን ሊያውቋት አልቻሉም የባቢሎንን ጥበበኞች ሁሉ እርሱንና ባልጀሮቹን ሠለስቱ ደቂቅን ይገድሏቸው ዘንድ ንጉሥ አዘዘ። ❤ ዳንኤልም ይህን ነገር ሰምቶ የዘበኞቹን አለቃ "ስለምን እዲህ ያለ ትዕዛዝ ከንጉሥ ዘንድ ታዘዘን" ብሎ ጠየቀው እርሱም "ንጉሥ ስላያት ራእይ ነው። የባቢሎንና የግብጽ ጠቢባን ሁሉ እርሷን ራእይ ትርጓሜዋን ሊነግሩት አልተቻላቸውምና" ብሎ መለሰለት ዳንኤልም የዘበኞቹን አለቃ "እኔ ለንጉሥ ህልሙን እንደምነግረውና ፍችው እንደምተረጉምለት ስለእኔ ንገረው እሊህንም ተዋቸው" አለ። ❤ ከዚህ በኋላ ዳንኤል ወደ እግዚአብሔር ጸለየ ባልጀሮቹ ሠለስቱ ደቂቅም ከእርሱ ጋር የንጉሡን ህልም ፍችዋንም ሊገልጥላቸው ዘንድ በአንድነት ማለዱ እግዚአብሔርም ገለጠላቸው ዳንኤልም ወደ ንጉሥ ገብቶ ህልሙንና ፍቺዋን ነገረው ከእርሱ በኋላ ስሚነሱ ነገሥታት ከእያንዳንዳቸው የሚሆነውን ገለጠለት የዳንኤልም ቃል ናቡከደነፆርን ደስ አሰኘው በፊቱ ሰገደ ብዙ እጅ መንሻ ሰጠው ታላቅ ክብርንም ሰጥቶ በባቢሎን ጠጢባን ሁሉ ላይ አለቃ አድርጎ ሾመው። ❤ ከዚህም በኋላ ናቡከደነፆር ሌላ ህልም አየ ያንንም ተረጎመለት እንዲህም ብሎ አስረዳው "ስለታበይክ እግዚአብሔር ከሰው መካከል አውጥቶ ከአራዊት ጋራ በዱር ሰባት ዓመት ያኖር ዘንድ አለው እንደ እንስሳ ሣር ትበላለህ ከሰባት ዓመትም በኋላ ወደ መንግሥትህ ይመልስሃል" በማለት ይህም ተፈጸመበት። ❤ ናቡከደነፆር ከሞተ በኋላ መልአክ በግድግዳ ላይ የጻፉቱን ለልጁ ለብልጣሶር ተረጐመለት በቤተ እግዚአብሔር እቃ በጠጣ ጊዜ ጽሑፍ የተቀጠረ የተመጠነ የተመዘነ እንደሆነ ትርጓሜውን ዙፋኑን መግሥቱን እግዚአብሔር ለሌላ የሰጠው መሆኑን ገለጠለት እዲህም አለው "ቢመዝንህ ጎደሎ ሁነህ አገኘህ መንግሥትህም ለፋርስ አሳልፎ ሰጠ" ትንቢቱም ተፈጸመች። ❤ እግዚአብሔርም እስከ ዓለም ፍጻሜ የሚነግሡቱን ነገሥታት በራእይ አሳየው የሐሳዊ መሲሕንም መገለጥ አሳየው። ❤ ከዚህ በኋላ እግዚአብሔርነቱን ክቡር ልዕልናውን ጌትነቱን አሳየው። የክብር ባለቤት ክርስቶስን ወደ ዓለም መምጣቱን ትንቢት ተናገረ ሱባኤዎችም ወሰነ እነዚያ ሱባኤዎችም በተፈጸሙ ጊዜ የክብር ባለቤት ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ መጣ። ክርስቶስ ይመጣል ይገድሉታልም በኢየሩሳሌም መዳኞዋ ይሆናታል ብሎ ትንቢት እንደተናገረ የክብር ባለቤት ከሆነ ከጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ ስቅለት በኋላ ኢየሩሳሌም እንደምትጠፋ ቤተ መቅደስ እንደሚፈርስ የተናገረው ትንቢት ሁሉ ተፈጸመ። ❤ በባቢሎን አገርም ቤል የሚባል ጣዖት ነበር ምግቡም ሁል ጊዜ ዐሥራ ሁለት ጫን በሚፈጅ ቻል፣ ዐሥራ ሁለት መስፈርያ ስንዴ፣ አርባ በግ፣ ሰባት ፊቀን የወይን ጠጅ እያወጣጡ ይሰጡተት ነበር። ንጉሡም ሁል ጊዜ ይሰግድለታል ቤል ጣዖትም ከንጉሡ ቤት የሚሰጡትን የሚበላና የሚጠጣ ይመስለው ነበር። ንጉሡም ዳንኤልን "ለቤል የማትሰግድ ለምድን ነው?" አለው ዳንኤልም ንጉሡን "እኔስ ሰማይንና ምድርን ለፈጠረ ፍጥረቱንም ሁሉ በሕያውነት ለሚያኖር አምላክ እንጂ የሰው እጅ ለሠራው ጣዖት አልሰግድም" አለው። ንጉሡም "ቤል ሕያው ያልሆነ ይመሰግሃልን? በየነጋታው እንዲበላ እንዲጠጣ አታይምን" አለው። ዳንኤልም በንጉሡ ሳቀበት "ንጉሥ ሆይ ይበላል ይጠጣል እያሉ አያታሉህ ይህ ውስጡ ጭቃ ላይ ናስ ነው ምንም ምን አይበላም አይጠጣም" አለው። ንጉሡም ተቆጣ የጣዖቱንም ካህናት ጠራቸው "እውነት ነውን ቤል አምላክ አይበላም አይጠጣም" አላቸው።"ሁል ጊዜ የምንሰጠውን በእውነት ይበላል ይጠጣል" አሉት። ❤ ከዚህም በኋላ በመሸ ጊዜ ከጣዖቱ ዘንድ መብሉንና መጠጡን ሁሉ ንጉሡ እየተመለከተ ካህናቱ አስቀምጠው ወጡ የጣዖቱ ካህናትም ከወጡ በኋላ ዳንኤል አመድ አምጡ ብሎ አዘዘ። አመጡለትም ንጉሡም ከእዛ ሆኖ እያየ ከጣዖቱ ቤት ውስጥ ነሰነሰው ንጉሡም በቁልፉ ከዳንኤል ጋራ በአንድነት ቈለፉት አተሙትም ወደ ማደሪያቸውም ሔዱ። የጣዖቱ ካህናት ግን ከምድር በታች ውስጥ ለውስጥ መግቢያ ቀዳዳ ነበራቸው ከሚስቶቻቸው ከልጆቻቸው ጋራ በሌሊት በዚያ ገብተው በሉ ጠጡ በመጡበትም ተመለሱ። ❤ በማግስቱም ንጉሡ መጥቶ የጣዖቱን ቤት ከፈተ ራሱ ከአኖረው መብሎች ምንም አላገኘም ንጉሡም "ቤል ሆይ ፈጣሪዬ ዳንኤልን ያሳፈርከው አንተ ገናና ነህ" ብሎ ጮኸ። ዳንኤልም ሳቀ ለንጉሡም ወንዶችና የሴቶችን የልጆችንም ፍለጋቸውን በአመድ ላይ አሳየው ንጉሡም የጣዖቱን ካህናት ይዞ መረመራቸው እነርሱም ውስጥ ለውስጥ ተሠውረው የሚገቡበትንና የሚወጡበትን ለንጉሥ አሳዩት። ያን ጊዜ ንጉሥ ተቆጥቶ የጣዖቱን ካህናት ከሚስቶቻቸውና ከልጆቻቸው ጋራ ገደላቸው ጣዖቱንም ለዳንኤል ሰጠው ዳንኤልም ሰበረው ምኵራቡንም አፈረሰ። ❤ ከዚህ በኋላ ደግሞ የባቢሎን ሰዎች የሚያመልኩትና የሚሰገዱለት ታላቅ ዘንዶ ነበር ንጉሡም ዳንኤልን "ይህንንስ አምላክ አይደለም ትለዋለህን እነሆ ሕያው ነው ይባላል ይጠጣል ናስ ነው ትለው ዘንድ አትችልምና ስገድለት እንጂ" አለው። ዳንኤልም ለንጉሡ እንዲህ ብሎ መለሰለት "እኔስ በሕያውነት ከሚኖር ከእግዚአብሔር በቀር ለሌላ አልሰግድም ግን ያለ ሰይፍና ያለ በትር ይህን ከይሲ እገድለው ዘንድ አሰናብተኝ" አለው። ንጉሥም "አሰናበትኩህ" አለው። ❤ ዳንኤልም ጠጉርና አደሮ ማር ወስዶ እንደ እንቁላልም አድበልብሎ በእሳት አጋለው በሞራም ጠቅልሎ ለከይሲው አጐለሰው በዋጠውም ጊዜ ሆዱ ተሰንጥቆ ሞተ ዳንኤልም "የባቢሎን ሰዎች ሆይ አምላካችሁን ተመልከቱ" አላቸው። የባቢሎን ሰዎች በሰሙ ጊዜ እጅግ ተቆጡ ወደ ንጉሡም ተሰብስበው "አይሁዳዊ ዳንኤል ነግሦአልን እነሆ ቤልን ሰበረው ካህናቶቹንም ገደላቸው። ከዚያም ደግሞ ዘንዶውን ገደለው አሁን እርሱን ዳንኤልን እንድንገድለው ካልሰጠህን አንተን ቤተ ሰብህን እንገድላለን" አሉት። ❤ ንጉሡንም እጅግ አስጨነቁት ጊዜ ስለ ዳንኤል አዘነ ግን ዳንኤልን ሰጣቸው እነርሱም ለአንበሶች ጒድጓድ ውስጥ ጣሉት በዚያም ሰባት ቀን ኖረ። ከረኀብ ጽናትም የተነሣ እንዲበሉት በሌላ ጊዜ የሚሰጧቸውን በእነዚያ ቀኖች ምንም ምን አልሰጧቸውም ነበር።

❤ እግዚአብሔር መልአኩን ወደ ዕንባቆም ላከው እርሱም በኢየሩሳሌም ውስጥ ለአጫጅዎች ምሳ ተሸክሞ ሲሔድ በራስ ጠጉሩ ተሸከመው። ወስዶም ዳንኤል በአለበት ጒድጓድ ውስጥ አኖረው ዳንኤልም ተመግቦ እግዚአብሔርን አመሰገነው በዕንባቆምም ቃል ተረጋጋ በዚያችም ሰዓት እግዚአብሔር የላከው መልአክ ወደ አገሩ ወደ ኢየሩሳሌም መልሶ አደረሰው። ❤ በሰባተኛዪቱ ቀንም ስለ ዳንኤል እያለቀሰ ንጉሡ ወደ ጒድጓዱ መጣ ዳንኤል ሙቶ አንበሶች የበሉት መስሎት ነበርና። ወደ ጒድጓዱም ሲመለከት ዳንኤልን አየው አንበሶችም እንደ ድመቶች እግሮቹን እየላሱ ከእግሮቹ በታች እጥፍጥፍ ብለው ተኝተው ነበር። ንጉሡም "እግሮቹን እስከሚልሱ እንደ ድመቶች አንበሶችን ያገረመለትና ያስገዛለት የዳንኤል አምላክ ታላቅ ነው ብሎ ከፍ ባለ ድምፅ ጮኸ"። ❤ በዚያን ጊዜ ዳንኤልን ከጒድጓድ እንዲያወጡት እነዚያንም የዳንኤልን ጠላቶች ይዘው ለአንበሶች ወደ ጒድጓድ እንዲጥሏቸው ንጉሥ አዘዘ ወዲያው እነዚያ አንበሶች በንጉሡ ፊት በሏቸው። ❤ ዳንኤልም የእስራኤል ልጆች ወደ ኢየሩሳሌም እስከ ሚመለሱበት ጊዜ በባቢሎን ኖረ እርሷም ሰባ ዘመን ናት ከዚያም በኋላ መጋቢት23 በሰላም በፍቅር ዐረፈ። ከቅዱስ ዳንኤል በጸሎቱ የምትገኝ በረቱ ከእኛ ጋራ ለዘላለሙ ትኑር አሜን። + + + ❤ በዚች ቀን በጌታችን ላይ ሊመክሩ የአይሁድ ማኅበር በቀያፋ ቤት ተሰበሰቡ። ይቅርታውና ቸርነቱ ከእኛ ጋር ለዘላለሙ ይኑር አሜን። ምንጭ፦ የመጋቢት 23 ስንክሳር። + + + ❤ "ሰላም ዳንኤል እንተ ፈከረ በቃሉ። ሕልመ ንጉሥ ሥውረ እንዘ ትርጓሜ ያተሉ። ተዘኪሮሙ ረድኤተ ዘተውህበቶ እምላዕሉ። ሶበ በጸሎት አምላክ ዳንኤል ይብሉ። እምአፈ አናብስት ድኅኑ ሰማዕታት ኵሉ"። ሊቁ አርከ ሥሉስ (አርኬ) የመጋቢት 23። + + + ❤ የዕለቱ ምስባክ፦ "ወገሠፀ ነገሥተ በእንቲአሆሙ። ወኢትግሥሡ መሲሐንየ። ወኢታሕስሙ ዲበ ነቢያትየ"። መዝ 104፥14-15። የሚነበቡት መልዕክታት ዕብ 11፥32-ፍ.ም፣ 2ኛ ጴጥ 1፥19-ፍ.ም እና የሐዋ ሥራ 7፥51-55። የሚነበበው ወንጌል ማቴ 21፥18-23። የሚቀደሰው ቅዳሴ የእመቤታች የማርያም ቅዳሴ ነው። መልካም የጾም ጊዜና በዓል። ለሁላችንም ይሁንልን። ❤ በየቀኑ ይህን ቴሌግራም ላይ ማግት ከፈለጉ ከታች ያለውን ሊንክ ተጭነው ይቀላቀሉ። @sigewe https://t.me/eotcw

ስንክሳር ገድላት ወግጻዌ: ❤ "በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። ❤ ❤ መጋቢት ፳፫ (23) ቀን። ❤ እንኳን ከአራቱ ዐበይት ነቢያት ለአንዱ የዮናኪር ሴት ልጁ ለወለደችው ለታላቁ ነቢይ ለቅዱስ ዳንኤል ለዕረፍት በዓል መታሰቢያ በዓል በሰላም አደረሰን። + + + ❤ ነቢዩ ቅዱስ ዳንኤል፦ ናብከደነጾርም ኤየሩሳሌምን በወራራት ጊዜ አባታቸው ዮናኪር አናንያን አዛርያና ሚሳኤልን ሦስቱን ልጆቹን የልጁን ልጅ ዳንኤልንም ወሰዳቸው ከእርሳቸውም ጋር ከእስራኤል ልጆች ብዙ ሰዎች ተማረኩ። ይህም ዮናኪር የንጉሡ የኢዮአቄም ልጅ ነው። ❤ ኢሳይያስ ለሕዝቅያስ ንጉሥ ትንቢት እንደተናገረ የቤተ መንግሥቱንና የቤተ እግዚአብሔርን እቃ ሁሉ ናብከደጾር ወደ ባቢሎን ወደሰደ። ❤ ይህ ዳንኤል በእድሜው ታናሽ ነበር ፍጽም የሆነ ታላቅ ተጋድሎ ተጋደለ የእግዚአብሔር መንፈስ አድሮበት በባቢሎን አገር ትንቢት ሲናገር ኖረ። ❤ ምርኮ በሆነ በአራተኛው ዓመት ናቡከደነፆር የምታስፈራ ራእይ አየ ከእቅልፉም በነቃ ጊዜ ያች ህልም እረሳት በባቢሎን የሚኖሩትን ሁሉ ጥበበኞች ሰበሰባቸው ከርሳቸውም ያች ራእይ ትርጓሜዋን እንዲነግሩ ፈለገ እነርሱ ግን ያች ራእይ ትርጓሜዋን ሊያውቋት አልቻሉም የባቢሎንን ጥበበኞች ሁሉ እርሱንና ባልጀሮቹን ሠለስቱ ደቂቅን ይገድሏቸው ዘንድ ንጉሥ አዘዘ። ❤ ዳንኤልም ይህን ነገር ሰምቶ የዘበኞቹን አለቃ "ስለምን እዲህ ያለ ትዕዛዝ ከንጉሥ ዘንድ ታዘዘን" ብሎ ጠየቀው እርሱም "ንጉሥ ስላያት ራእይ ነው። የባቢሎንና የግብጽ ጠቢባን ሁሉ እርሷን ራእይ ትርጓሜዋን ሊነግሩት አልተቻላቸውምና" ብሎ መለሰለት ዳንኤልም የዘበኞቹን አለቃ "እኔ ለንጉሥ ህልሙን እንደምነግረውና ፍችው እንደምተረጉምለት ስለእኔ ንገረው እሊህንም ተዋቸው" አለ። ❤ ከዚህ በኋላ ዳንኤል ወደ እግዚአብሔር ጸለየ ባልጀሮቹ ሠለስቱ ደቂቅም ከእርሱ ጋር የንጉሡን ህልም ፍችዋንም ሊገልጥላቸው ዘንድ በአንድነት ማለዱ እግዚአብሔርም ገለጠላቸው ዳንኤልም ወደ ንጉሥ ገብቶ ህልሙንና ፍቺዋን ነገረው ከእርሱ በኋላ ስሚነሱ ነገሥታት ከእያንዳንዳቸው የሚሆነውን ገለጠለት የዳንኤልም ቃል ናቡከደነፆርን ደስ አሰኘው በፊቱ ሰገደ ብዙ እጅ መንሻ ሰጠው ታላቅ ክብርንም ሰጥቶ በባቢሎን ጠጢባን ሁሉ ላይ አለቃ አድርጎ ሾመው። ❤ ከዚህም በኋላ ናቡከደነፆር ሌላ ህልም አየ ያንንም ተረጎመለት እንዲህም ብሎ አስረዳው "ስለታበይክ እግዚአብሔር ከሰው መካከል አውጥቶ ከአራዊት ጋራ በዱር ሰባት ዓመት ያኖር ዘንድ አለው እንደ እንስሳ ሣር ትበላለህ ከሰባት ዓመትም በኋላ ወደ መንግሥትህ ይመልስሃል" በማለት ይህም ተፈጸመበት። ❤ ናቡከደነፆር ከሞተ በኋላ መልአክ በግድግዳ ላይ የጻፉቱን ለልጁ ለብልጣሶር ተረጐመለት በቤተ እግዚአብሔር እቃ በጠጣ ጊዜ ጽሑፍ የተቀጠረ የተመጠነ የተመዘነ እንደሆነ ትርጓሜውን ዙፋኑን መግሥቱን እግዚአብሔር ለሌላ የሰጠው መሆኑን ገለጠለት እዲህም አለው "ቢመዝንህ ጎደሎ ሁነህ አገኘህ መንግሥትህም ለፋርስ አሳልፎ ሰጠ" ትንቢቱም ተፈጸመች። ❤ እግዚአብሔርም እስከ ዓለም ፍጻሜ የሚነግሡቱን ነገሥታት በራእይ አሳየው የሐሳዊ መሲሕንም መገለጥ አሳየው። ❤ ከዚህ በኋላ እግዚአብሔርነቱን ክቡር ልዕልናውን ጌትነቱን አሳየው። የክብር ባለቤት ክርስቶስን ወደ ዓለም መምጣቱን ትንቢት ተናገረ ሱባኤዎችም ወሰነ እነዚያ ሱባኤዎችም በተፈጸሙ ጊዜ የክብር ባለቤት ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ መጣ። ክርስቶስ ይመጣል ይገድሉታልም በኢየሩሳሌም መዳኞዋ ይሆናታል ብሎ ትንቢት እንደተናገረ የክብር ባለቤት ከሆነ ከጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ ስቅለት በኋላ ኢየሩሳሌም እንደምትጠፋ ቤተ መቅደስ እንደሚፈርስ የተናገረው ትንቢት ሁሉ ተፈጸመ። ❤ በባቢሎን አገርም ቤል የሚባል ጣዖት ነበር ምግቡም ሁል ጊዜ ዐሥራ ሁለት ጫን በሚፈጅ ቻል፣ ዐሥራ ሁለት መስፈርያ ስንዴ፣ አርባ በግ፣ ሰባት ፊቀን የወይን ጠጅ እያወጣጡ ይሰጡተት ነበር። ንጉሡም ሁል ጊዜ ይሰግድለታል ቤል ጣዖትም ከንጉሡ ቤት የሚሰጡትን የሚበላና የሚጠጣ ይመስለው ነበር። ንጉሡም ዳንኤልን "ለቤል የማትሰግድ ለምድን ነው?" አለው ዳንኤልም ንጉሡን "እኔስ ሰማይንና ምድርን ለፈጠረ ፍጥረቱንም ሁሉ በሕያውነት ለሚያኖር አምላክ እንጂ የሰው እጅ ለሠራው ጣዖት አልሰግድም" አለው። ንጉሡም "ቤል ሕያው ያልሆነ ይመሰግሃልን? በየነጋታው እንዲበላ እንዲጠጣ አታይምን" አለው። ዳንኤልም በንጉሡ ሳቀበት "ንጉሥ ሆይ ይበላል ይጠጣል እያሉ አያታሉህ ይህ ውስጡ ጭቃ ላይ ናስ ነው ምንም ምን አይበላም አይጠጣም" አለው። ንጉሡም ተቆጣ የጣዖቱንም ካህናት ጠራቸው "እውነት ነውን ቤል አምላክ አይበላም አይጠጣም" አላቸው።"ሁል ጊዜ የምንሰጠውን በእውነት ይበላል ይጠጣል" አሉት። ❤ ከዚህም በኋላ በመሸ ጊዜ ከጣዖቱ ዘንድ መብሉንና መጠጡን ሁሉ ንጉሡ እየተመለከተ ካህናቱ አስቀምጠው ወጡ የጣዖቱ ካህናትም ከወጡ በኋላ ዳንኤል አመድ አምጡ ብሎ አዘዘ። አመጡለትም ንጉሡም ከእዛ ሆኖ እያየ ከጣዖቱ ቤት ውስጥ ነሰነሰው ንጉሡም በቁልፉ ከዳንኤል ጋራ በአንድነት ቈለፉት አተሙትም ወደ ማደሪያቸውም ሔዱ። የጣዖቱ ካህናት ግን ከምድር በታች ውስጥ ለውስጥ መግቢያ ቀዳዳ ነበራቸው ከሚስቶቻቸው ከልጆቻቸው ጋራ በሌሊት በዚያ ገብተው በሉ ጠጡ በመጡበትም ተመለሱ። ❤ በማግስቱም ንጉሡ መጥቶ የጣዖቱን ቤት ከፈተ ራሱ ከአኖረው መብሎች ምንም አላገኘም ንጉሡም "ቤል ሆይ ፈጣሪዬ ዳንኤልን ያሳፈርከው አንተ ገናና ነህ" ብሎ ጮኸ። ዳንኤልም ሳቀ ለንጉሡም ወንዶችና የሴቶችን የልጆችንም ፍለጋቸውን በአመድ ላይ አሳየው ንጉሡም የጣዖቱን ካህናት ይዞ መረመራቸው እነርሱም ውስጥ ለውስጥ ተሠውረው የሚገቡበትንና የሚወጡበትን ለንጉሥ አሳዩት። ያን ጊዜ ንጉሥ ተቆጥቶ የጣዖቱን ካህናት ከሚስቶቻቸውና ከልጆቻቸው ጋራ ገደላቸው ጣዖቱንም ለዳንኤል ሰጠው ዳንኤልም ሰበረው ምኵራቡንም አፈረሰ። ❤ ከዚህ በኋላ ደግሞ የባቢሎን ሰዎች የሚያመልኩትና የሚሰገዱለት ታላቅ ዘንዶ ነበር ንጉሡም ዳንኤልን "ይህንንስ አምላክ አይደለም ትለዋለህን እነሆ ሕያው ነው ይባላል ይጠጣል ናስ ነው ትለው ዘንድ አትችልምና ስገድለት እንጂ" አለው። ዳንኤልም ለንጉሡ እንዲህ ብሎ መለሰለት "እኔስ በሕያውነት ከሚኖር ከእግዚአብሔር በቀር ለሌላ አልሰግድም ግን ያለ ሰይፍና ያለ በትር ይህን ከይሲ እገድለው ዘንድ አሰናብተኝ" አለው። ንጉሥም "አሰናበትኩህ" አለው። ❤ ዳንኤልም ጠጉርና አደሮ ማር ወስዶ እንደ እንቁላልም አድበልብሎ በእሳት አጋለው በሞራም ጠቅልሎ ለከይሲው አጐለሰው በዋጠውም ጊዜ ሆዱ ተሰንጥቆ ሞተ ዳንኤልም "የባቢሎን ሰዎች ሆይ አምላካችሁን ተመልከቱ" አላቸው። የባቢሎን ሰዎች በሰሙ ጊዜ እጅግ ተቆጡ ወደ ንጉሡም ተሰብስበው "አይሁዳዊ ዳንኤል ነግሦአልን እነሆ ቤልን ሰበረው ካህናቶቹንም ገደላቸው። ከዚያም ደግሞ ዘንዶውን ገደለው አሁን እርሱን ዳንኤልን እንድንገድለው ካልሰጠህን አንተን ቤተ ሰብህን እንገድላለን" አሉት። ❤ ንጉሡንም እጅግ አስጨነቁት ጊዜ ስለ ዳንኤል አዘነ ግን ዳንኤልን ሰጣቸው እነርሱም ለአንበሶች ጒድጓድ ውስጥ ጣሉት በዚያም ሰባት ቀን ኖረ። ከረኀብ ጽናትም የተነሣ እንዲበሉት በሌላ ጊዜ የሚሰጧቸውን በእነዚያ ቀኖች ምንም ምን አልሰጧቸውም ነበር።

❤ "በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። ❤ ❤ መጋቢት ፳፫ (23) ቀን። ❤ እንኳን ከአቡነ ተክለ ሃይማኖት በኋላ ለደብረ ሊባኖስ ሦስተኛ መምህር (እጨጌ) ለሆኑት የአቡነ ፊሊጶስ ፍልሰተ ዐፅማቸው በክብር ተከናወነ በዓል በሰላምአደረሰን። + + + ❤ አቡነ ፊሊጶስ ዘደብረ ሊባኖስ፦ በተወለዱ በ15 አመታቸው በምናኔ ወደ ደብረ ሊባኖስ ገቡ፡፡ ከብዙ ጊዜ አገልግሎትም በኋላ በአቡነ ተክለሃይማኖት እጅ መንኩሰው ከእርሳቸውም ዕረፍት በኋላ ሦስተኛ አበምኔት ሆነው አገልግለዋል፡፡ በኢትዮጵያ ከተወለዱት የመጀመሪያ ፓትርያርክ ሆነዋል፡፡ አባታቸው ቅዱስ ተክለሃይማኖትም በመንፈቀ ኢትዮጵያ ጳጳስ ሆነው ነበር፡፡ በመጀመሪያ የአቡነ ፊሊጶስን የጽድቅ ሕይወትና ሹመታቸውን በተመለከተ በአቡነ ተክለ ሃይማኖት ገድልና በራሳቸው በአቡነ ፊሊጶስ ገድል ላይ የተጻፈውን እንመልከት፡- "ክቡር አባታችን አቡነ ተክለሃይማኖት ከዚህ ዓለም ተለይቶ የሚሄድበት ጊዜ ሲደርስ "ከአንተ በኋላ አንተን ተክቶ በዙፋንህ የሚቀመጥ ማነው?" አሉት፡፡ እርሱም "ብዙ ዘመን አይኖርም እንጂ ኤልሳዕ በእኔ ተተክቶ ይቀመጥ" አለ፡፡ ስለ ፊሊጶስ ግን አላነሳም፣ ኤልሳዕ ካረፈ በኋላ በእርሱ ተተክቶ አባት ይሆን ዘንድ ጌታችን የተሸለመ ፊሊጶስን እንደመረጠው ስም አጠራሩ ለልጅ ልጅ ዘመን እንደሚጸና ያውቅ ነበርና ስለዚህ "አልሳዕ በእኔ ተተክቶ አባት ይሁናችሁ" አለ፡፡ ክቡር አባታችንም በታላቅ ክብር ዐረፈ፡፡ ❤ አንድ ቀን አንድ ዲያቆን ዐረፈና ሬሳውን ገንዘው አጠቡት፣ ይቀብሩትም ዘንድ አስክሬኑን ይዘው ሲሄዱ በአልጋ ላይ ሳለ አስክሬኑ ተንቀሳቀሰ፡፡ የተሸከሙትም ደንግጠው መሬት ላይ አስቀመጡትና ከመግነዙ ፈቱት፡፡ እርሱም ተነሥቶ ሦስት ጊዜ ተነፈሰ፡፡ ወንድሞችም "ምን እያልክ ነው?፣ ወዴትስ ነበርክ?" አሉት፡፡ ያ የከበረና የተመረጠ ዲያቆንም ‹ክቡር አባታችን ተክለሃይማኖት "ኤልሳዕ ወደኔ ይምጣ፣ ፊሊጶስ ስለ እኔ ተሹሞ በወንበሬ ይቀመጥ እርሱ ለብዙዎች አሕዛብ አባት ይሆናልና የክርስቶስንም መንጋ በጽድቅና በቅን ይጠብቃል" ብሎኛል› ብሎ ይህን ተናግሮ ተመልሶ ዐረፈ፡፡ ወንድሞችም ኤልሳዕ እንደልማዱ ጎኑን ሳያሳርፍ በወንበር ላይ እንደተደገፈ በሞት ማረፉን አላወቁም ነበር"፡፡ ❤ ወደ ጻድቁ የልጅነት ገድላቸው እንመለስና አቡነ ፊሊጶስ በእግዚአብሔር ተመርጠው የመንፈስ ቅዱስም ማደሪያ ሆነዋልና ገና በሕፃንነታቸው በተወለዱባት ሰላሌ ክፍለ ሀገር ዝማ በምትባል ልዩ ቦታ ውስጥ ሰይጣን በጠንቋይ ላይ አድሮ በነደደ በእሳት ውስጥ በመግባትና የተለያዩ ተአምራትን በማድረግ በአካባቢው ራሱን ያስመልክ የነበረን ሰይጣን በእሳት ውስጥ እንዳለ በስመ ሥላሴ አማትበውበት አመድ አድርገውታል፡፡ በዚህ በአቡነ ፊሊጶስ ድንቅ ተአምር የጠንቋዩ ቤተሰቦችና የአካባቢው ሰዎችም አምነው ሊጠመቁ ችለዋል፡፡ ይህንንም ያደረገው ገና ሕፃን ሳለ ነው፡፡ መልአከ እግዚአብሔር ተገልጦለት የትውልድ መንደሩን ትቶ ወደ ግራርያ ሀገር ደብረ አስቦ ሄዶ ቅዱስ ተክለሃይማኖትን እንዲያገኝ በነገረው መሠረት አንድ ቀን ያህል ተጉዞ ተክለሃይማኖትን አገኛቸውና ባርከውት ከመነኰሳት ጋር እንዲያርፍ አደረጉት፡፡ ሦስት ዓመት እነርሱን በመልካም ሥራ ፍጹም ሆኖ ሲያገለግላቸው ከቆየ በኋላ "ሁሉም በአንድነት አሁን ልብሰ ምንኩስና ይገባዋል" አሉ፡፡ ቅዱስ አባታችን ተክለሃይማኖትም የምንኵስናን ሥራ የሚያሠራ ቅድስናን ሰጠው፡፡ ❤ በሌላም ጊዜ ቅስናን ይቀበል ዘንድ ወደ ጳጳሱ ዘንድ ላኩት፡፡ አቡነ ፊሊጶስ በንጉሥ አምደ ፅዮን ዘመነ መንግሥት ሥጋቸው አልቆ አጥንታቸው እስኪቀር ድረስ ሲገረፉ ደማቸው እሳት ሆኖ ገራፊዎቻቸውን ያሳደደ ቅዱስና ጻዲቅ አባት ናቸው፡፡ ንጉሥ አምደ ጽዮን በክፉ ጠንቋዮች ምክር ተታሎ ‹‹ያልወለደችህን የአባትህን ሚስት ብታገባ መንግሥትህ ትፀናለች›› ብለው ክፉ ምክርን መክረውት የእንጀራ እናቱን አገባትና ንግሥት አደረጋት፡፡ አቡነ ፊሊጶስም ይህን ሲሰሙ ነቢዩ ኤልያስ ንጉሡ አክአብንና አልዛቤልን በድፍረት እንደገሠጻቸው እርሳቸውም በቀጥታ ሄደው ንጉሡን ዘልፈው ገሠጹት፡፡ ወደ ንጉሡም ከመሄዳቸውም በፊት በዚህ ምክንያት ሰማዕት እንደሚሆኑ አውቀውት ነበርና ልጆቻቸውን ተሰናብተውና የሚተካቸውን ሰው ነግረዋቸው ነው የሄዱት፡፡ ንጉሡ አምደ ጽዮንም አጥንታቸው እስኪቀር ድረስ አስገረፋቸው፡፡ ደቀ መዛሙርቶቻቸውም መሬት ላይ እየተቆረሰ የወደቀውን ሥጋቸውን እያነሱ ለበረከት ወሰዱት፡፡ ደማቸውም እንደ እሳት ሆኖ ገራፊዎቻቸውን ያቃጥላቸው ነበር፡፡ 300 አንስራ ውኃ አምጥተው ከደሙ በወጣው እሳት ላይ ቢያፈሱትም የውኃው ብዛት እሳቱን ማጥፋት አልቻለም፡፡ ንጉሡም በፍርሃት ከዙፋኑ ላይ ወርዶ ሸሸ፡፡ ❤ የንጉሡ ጭፍሮች ግን በጋለ ማረሻ ጀርባና ግንባራቸውን ደረታቸውንም ተኮሷቸው፡፡ ኃፍረታቸውንም እንዳይሸፍኑ እጆቻቸውን ወደ ኋላ አስረው ራቁታቸውንም በከተማው ሁሉ ሲያዞሯቸው ዋሉ፡፡ ማታም ንጉሡ "ታስረው ለኖሩ ኃይለኛ ውሾች ስጡት" ብሎ በማዘዝ ውሾቹ እንዲቦጫጭቋቸው ቢያደርጉም ውሾቹ ግን ከእግራቸው ስር ሰግደዋል፣ እርሳቸውም በእግራቸው ባረኳቸው፡፡ አማካሪዎቹም ንጉሡን ‹‹ከዚህ መነኩሴ ጋር ምን አጨቃጨቀህ በግዞት አርቀህ ስደደው ብለው›› ብለው መክረውት "እስከ ቆርቆራ አገር አውጥታችሁ ወደ ትግሬ አገር ውሰዱት" ብሎ አዘዘ፡፡ እርሳቸውም ንጉሡን ከ3 ዓመት በኋላ ትሞታለህ ብለው ትንቢት ነገረውት በወታደሮች ተወሰዱ፡፡ በግርፋት ብዛት የተቆረሰ ሥጋቸው ድውያንን ይፈውስ ነበር፡፡ ❤ ደማቸውም አስረው የሚወስዷቸውን የአንዱን ወታደር አንድ ስውር ዐይኑን ፈወሰለትና ወታደሮቹም አምነው ከእርሳቸው ጋር በዚያው ተሰደው መከራን ተቀብለዋል፡፡ እሳቸው በትግራይ ታላላቅ ተአምራትን እያደረጉ ሲያስተምሩ በትንቢታቸው መሠረትም ንጉሡ ከሦስት ዓመት በኋላ ሞተና ልጁ ነገሠ፡፡ ልጁም አባታችንን ከስደት መለሳቸውና ከተክለሃይማኖት መቃብር ደብረ አስቦ ገቡ፡፡ የነገሠውንም ልጅ አንድ ክፉ ሰው "ከአንድ በላይ ማግባት ትችላለህ፣ በገና ወቅትም ረቡዕና አርብን መጾም ተገቢ አይደለም" ብሎ ስለመከረው ጳጳሱን ወደ ሀገራቸው ግብፅ እንዲሰደዱ ሲያደርግ አቡነ ፊሊጶስን ደግሞ "ረቡዕና አርብን በጠዋት ካልቀደስክ" ብሎ ወደ ደራ ተሰደው እንዲሄዱ አደረገ፡፡ አባታችን በአጠቃላይ አምስት ጊዜ ተሰደው በትግራይ፣ በደራ፣ በዝዋይ ባሕረ ደሴት፣ በዳሞት ገማስቄ እና በወለቃ በስደት ቆይተዋል፡፡ ጳጳሱን አባ ሰላማን በአቃሊት ቅበረኝ ብለዋቸው በቃሬዛ አድርጎ ከጌርጌሳ ወደ አቃሊት ወሰዷቸው፤ እዚያም ሐምሌ 28 ቀን በሰላም ዐረፉ፡፡ ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስም ሰባት አክሊላት አቀዳጅቷቸዋል፡፡ዐፅማቸውም ከተቀበረ ከ140 ዓመት በኋላ በመጋቢት 23 ቀን ወደ ደብረ ሊባኖስ በክብር መጥቶ ዐርፏል፡፡ ከአቡነ ፊሊጶስ እግዚአብሔር አምላክ ረድኤትና በረከትን ያሳትፈን። ምንጭ፦ ከገድላት አንደበት። https://t.me/eotcw

photo content
+1

❤ ከዚህም በኋላ ይህ መናፍቅ ቈስጠንጢኖስ ሞተ። ልጁ ሦስተኛው ቈስጠንጢኖስ ነገሠ ይህንንም አባት ከተሰደደበት ወደ መንበረ ጵጵስናው መለሰው አባቱ ያሳደዳቸው ኤጲስቆጶሳት ሁሉንም መለሳቸው። ይህም አባት የተረፈውን ዘመን በሰላምና በጸጥታ ኖረ። ❤ ታላቁ ቴዎዶስዮስም በነገሠ ጊዜ ስለ መቅዶንዮስ ስለ ሰባልዮስና ስለ አቡሊናርዮስ በቊስጥንጥንያ መቶ ሃምሳ ኤጲስቆጶሳትን አንድነት ጉባኤው ውሰጥ አንዱ እርሱ ነበር መናፍቃንም መመለስን እንቢ በአሉ ጊዜ ከወገኖቹ ጋር ረገማቸው አውግዞም ለያቸው። ❤ ሃይማኖትን ያቀኑ ሦስት መቶ ዐሥራ ስምንቱ በሠሩት በጸሎተ ሃይማኖት ላይ ለመንግሥቱም ፍጻሜ የለውም ከሚለው ቀጥሎ እንዲህ የሚል ጨመረ። "የባሕርይ ገዢ የሚሆን በሚያድን በመንፈስ ቅዱስ እናምናለን። ከአብ የተገኘ ከአብ ከወልድ ጋር እንስገድለት እናመሰግነውም በነቢያት አድሮ የተናገረ። ሐዋርያት ስብስበው አንድ በአደረጓት ከሁሉ በላይ በምትሆን ክብርት ንጽሕይት ጽንዕት ልዩ በምትሆን በአንዲት ቤተ ክርስቲያን እናምናለን። ኃጢአት በሚሠረይባቶ በአንዲት ጥምቀት እናምናለን። የሙታንንም መነሳት ተስፋ እናደርጋለን የሚመጣውንም የዘላለም ሕይወት"። ❤ ከዚህ በኋላ ይህ አባት በመንፈስ ቅዱስ ተቃኝቶ ብዙ ድርሳናትንና ተግሣጻትን ደረሰ። ሁለተኛም ስለ ጸሎት ሃይማኖትና ስለ ትርጓሜው ሌላ በውስጡ ዐሥራ ስምንት ያህል ድርሳን ያለው መጽሐፍ ደረሰ። እርሱም ጥበብን እውቀትን ሁሉ የተመላ እጅግ የሚጠቅም ነው። ❤ በጵጵስናውም መንበር ሠላሳ ሦስት ዓመት ከኖረ በኋላ መጋቢት 22 ቀን በሰላም ዐረፈ። በአባ ቄርሎስ በጸሎቱ የምትገኝ በረከቱ ከእኛ ጋር በዘላለም ትኑር አሜን። ምንጭ፦የመጋቢት22 ስንክሳር። + + + ❤ "ሰላም ለዕርገትከ ወለበዓትከ ማዕከላ። ኢየሱስ ክርስቶስ በተጽዕኖ ዕድግት ምስለ ዕዋላ። ኢየሩሳሌም አሜሃ ኢያእመረት መዋዕለ ሣህላ።ሀገርኒ ተሀውከት ኵላ። መኑ ውእቱ ኪያከ ብሂላ"። ሊቁ አርከ ሥሉስ (አርኬ) የመጋቢት 22። + + + ❤ የዕለቱ የማኅሌት ምስባክ፦ ኦ እግዚኦ አድኅንሶ። ኦ እግዚኦ ሠርኅሶ። ቡሩክ ዘይመጽእ በስመ እግዚአብሔር። መዝ 117፥20። የሚነበበው ወንጌል ማቴ 21፥6-12። + + + ❤ የዕለቱ ምስባክ፦ "እምአፈ ደቂቅ ወሕፃናት አስተዳሎከ ስብሐተ። በእንተ ጸላኢ። ከመ ትንሥቶ ለጸላኢ ወለገፋዒ"። መዝ 8፥2። የሚነበቡት መልዕክታት 1ቆሮ 4፥1-7፣ 2ኛ ዮሐ 1፥8-ፍ.ም እና የሐዋ ሥራ 5፥1-17። የሚነበበው ማቴ 21፥1-18። የሚቀደሰው ቅዳሴ የቅዱስ ቄርሎስ ወይም የቅዱስ ጎርጎርዮስ ዘኑሲስ ቅዳሴ ነው። መልካም የጾም ጊዜና በዓል። በሁላችንም ይሁንልን። https://t.me/eotcw

❤ "በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። ❤ ❤ መጋቢት ፳፪ (22) ቀን። ❤ እንኳን ለክብር ባለቤት ለጌታችን ለአምላካችን ለመድኃኒታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ ወደ ኢየሩሳሌም ከተማ ገብቶ ቤተ መቅደሱን በአህያ ግልገል ተቀምጦ በመዞር ሆሣዕና እያሉ እንዲያመሰግኑት ላደረገበት (ጥንት ሆሣዕና)ና ስለ መቅዶንዮስ ስለ ሰባልዮስና ስለ አቡሊናርዮስ በቊስጥንጥንያ መቶ ሃምሳ ኤጲስቆጶሳትን ከተሰበሰቡት አንድነት ጉባኤው ውሰጥ አንዱ ለሆነው ለኢየሩሳሌም ኤጲስቆጶስ ለአባ ቄርሎስ ለዕረፍት በዓል በሰላም አደረሰን። + + + ❤ ጥንት ሆሳዕና፦ ይህም ስርሱ እየአንዳንዳቸው በዘመናቸው ነቢያት የተናገሩት ትንቢት ይፈጸም ዘንድ ነው። ❤ ያዕቆብ በክርስቶስ ስለ ተመሰለው ስለ ልጁ "ይሁዳ አህያውን ዘይት ዕንጨት ላይ ያሥራል ውርንጫውንም በወይን አረገ" አለ። ዘካርያስም "ጽዮን ልጅ አትፍሪ እነሆ ንጉሥሽ በአህያ ግልገል ተቀምጦ ይመጣ" አለ። ❤ ኢሳይያስ "ንጉሥሽ ጻድቅ የዋህ የሆነ ይመጣል ዋጋውም ከእርሱ ጋራ ነው ሥራውም በፊቱ የተገለጠ ነው በአህያ ግልገልም ላይ ይቀመጣል" አለ። ❤ አብርሃምም የሰሌን ዝንጣፊ ይዞ መሠውያውን በዞረ ጊዜ "ይችን ዕለት ተድላ ደስታ የሚደረግባት የእግዚአብሔር በዓል" ብሎ ጠራት። ❤ ዳዊትም "ከሕፃናትና ከልጆች አንደበት ምስጋናን አዘጋጀህ" አለ። ሰሎሞንም "የሕፃናት አንደበታቸው የተቃናች ሆነች" አለ። ሁለተኛም "ልጆችና ሽማግሌዎች በኢየሩሳሌም ይጫወታሉ ምርጒዛቸውም መትከያዎችሽን አስፍተሽ ድንኳኖችሽን ዘርጊ" ያለም አለ። ❤ ይህንንም የትንቢት ነገር ለመፈጸም በከረ ወንጌል እንተጻፈ ጌታ በአህያዋና በውርንጭላዋ ላይ ተቀምጦ ወደ ኢየሩሳሌም ገባ። ወደ ኢየሩሳሌም ሊገባ በቀረበ ጊዜ የደብረ ዘይት አጠገብ ከምትሆን ቤተ ፋጌ ደረሰ ደብረ ዘይት ወደሚባል ቢታንያም በደረሰ ጊዜ ከደቀ መዛመቱን ሁለቱን ላከ። "ወደ ፊታችሁ ወዳለ አገር ሒዱ በገባችሁም ጊዜ ሰው ያልተቀመጠበት አህያ ግልገል ታገኛላችሁ ፈትታችሁ አምጡልኝ። ለምን ትፈቱታላችሁ የሚል ሰው ቢኖር ጌታው ይሻዋል" በሉ። የተላኩትም በሔዱ ጊዜ እንደነገራቸው አገኙ። የአህያውም ግልገል ፈቱ ጌቶቹም "ለምን ትፈቱታላችሁ" አሏቸው። "ጌታው ይሻዋል" አሉ። ወደ ጌታ ኢየሱስም ይዘውት ሔዱ ልብሳቸውንም በአህያው ግልገል ላይ ጐዘጐዙ ጌታችንም አስቀመጡት። ቅጠል ቆርጠው በመንገድ ላይ የጐዘጐዙ ብዙዎች ናቸው። ልብሳቸውንም በመንገድ ላይ ያነጠፋ አሉ። በፊትም በኋላ ይሔዱ የነበሩት "በእግዚአብሔር ስም የሚመጣ የተባረከ መድኃኒት ነው" ብለው አሰምተው ተናገሩ። "በእግዚአብሔር ስም የምትመጣ የአባታችን ዳዊት መንግሥትም የተባረከች ናት"። ❤ ጌታ ኢየሱስም ወደ ኢየሩሳሌም ቤተ መቅደስ ገባ ሕዝቡም ሁሉ አዩት በመሸም ጊዜ ከዐሥራ ሁለቱ ደቀመዛሙርት ጋር ወደ ቢታንያ ወጣ። በነጋውም ከቢታንያ በወጣ ጊዜ ተራበ። በሩቅም ቅጠል ያላትን በለስ አየ። በርሷ ፍሬ ያገኝ እንደሆነ ሊያይ ሔደ ወደርሷም በደረሰ ጊዜ ከቅጠል ብቻ በቀር ያገኘው የለም የበለስ ወራት አልነበረምና "ዘላለም ካንቺ ፍሬ የሚበላ አይኑር" አላት። ደቀ መዛሙርቱም ሰሙ። ❤ ወደ ኢየሩሳሌም ደርሶ ወደ ቤተ መቅደስ ገባ በምኵራቡም ግቢ የሚገበያዩትን ያስወጣ ጀመረ የለዋጮችንም ሰደቃቸውን ገለበጠ ርግብ የሚሸጡትንም ወንበራቸውን። ወደ ምኵራብ ለንግድ ገንዘብ ይዘው እንዳይገቡ ከለከለ። "ቤተ ለአሕዛብ ሁሉ የጸሎት ቤት ይሁን የሚል ጽሐፍ ያለ አይደለምን እናንተ ግን የሌቦችና የወንበዴዎች ዋሻ አደራጋችሁት" ብሎ አስተማራቸው። ❤ ቅዱስ ዮሐንስም እንዲህ አለ "አልዓዛርን ከሙታን ለይቶ ካስነሣው በኋላ። በነጋውም እሑድ ለበዓል የመጡ ሰዎች ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ወደ ኢየሩሳሌም እንዲመጣ በሰሙ ጊዜ። የሰሌን ዛፍ ዝንጣፊ ይዘው ከኢየሩሳሌም ፈጥነው ወጡ በእግዚአብሔር ስም የሚመጣ ከአርያም የተገኘ መድኃኒት የእስራኤል ንጉሥ የተባረከ ነው" እያሉ እየጮኹ ተቀበሉት። ❤ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የአህያ ግልገል አገኘ። ተቀመጠበትም እንደ ተጻፈ እንዲ ሲል። "የጽዮን ልጅ አትፍሪ እንሆ ንጉሥሽ በአህያ ግልገል ተቀምጦ ይመጣል"። አስቀድሞ ግን ደቀ መዛሙርቱ ይህን ነገር አላወቁም ነበር ጌታ ሳይሰቀል። ጌታ በተሰቀለ ጊዜ ይህ የተጻፈ ስለ እርሱ እንደሆነ ያን ጊዜ አወቁት እንጂ እንዲህም አደረጉለት። ❤ አልዓዛር አልዓዛር ብሎ ከሙታን ለይቶ እንዳስነሣው ባስነሣው ጊዜ ከእርሱ ጋር የነበሩ ሰዎች መሰከሩለት። ስለዚህም ሕዝቡ አመኑበት። ያደረገውን ተአምራት ሰምተወልና የሕፃናቱንም ምስጋና ደግሞ አልዓዛርን ማስነሣቱን። የካህናቱ አለቆችና ፈሪሳውያን ግን እርስ በርሳቸው "የምታገኙት ረብሕ ጥቅም እንደሌለ አታውቁምን እንሆ ሰው ሁሉ አመነበት" አሉ። ❤ ቅዱሳን ማቴዎስና ማርቆስ የሰሌንን ነገር አላወሱም ሌሎች ከእንጨቶች ቅጠሎችን እየቆረጡ በመንገድ ውስጥ ጐዘጐዙ አሉ እንጂ። ❤ ቅዱስ ሉቃስም ቅጠልን ወይም ሰሌንን አላወሳም ሲሒዱ ልብሳቸውን በመንገድ ላይ ይጐዘጒዙ ነበር አለ እንጂ። ❤ ቅዱስ ዮሐንስ ግን ለብቻው "ከኢየሩሳሌም ከሰሌን ዛፍ ላይ ዘንባባ ቆርጠው ያዙ" አለ። ሰሌንም በኢየሩሳሌም አልነበረም ጌታችን ሕፃን ሁኖ ሳለ ወደ ግብጽ በወረደ ጊዜ ከእናቱ ቡርክት ቅድስት ከሆነች ከእመቤታችን ድንግል ማርያም ጋር እስሙናይን ከሚባል አገር ደረሱ ከዚያም ሰሌን አገኙ። ጌታችንም ከሥርዋ ተነቅላ ሒዳ በደብረ ዘይት ላይ እንድትተከል አዘዛት ያንጊዜ ወደ አየር ወጥታ በረረች ሒዳም በዚያ በደብረ ዘይት ተተከለች ከእርስዋም ወስደው የክብር ባለቤት ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስን ተቀበሉት። ❤ ጌታችንም የሆሣዕናን ዑደት በአሳየ ጊዜ የአይሁድ ወገን ቅናት ይዟቸው በሚገድሉት ገንዘብ ምክንያት ፈለጉ። ለእርሱም ምስጋና ይሁን በእኛ ላይም ይቅርታው ቸርነቱ ይደረግልን ለዘላለሙ አሜን። + + + ❤ አባ ቄርሎስ፦ ይህም አባት የቤተ ክርስቲያንን ትምህርት በመማር ያደገና እጅግም አዋቂ ምሁር ነበር። ከእርሱ በፊት የነበረ ኤጲስቆጶስ አባ በኪኪሶስ በዐረፈ ጊዜ ይህን አባት መርጠው ለኢየሩሳሌም ኤጲስቆጶስ አድርገው ሾሙት። በተሾመም ጊዜ ከመነናውያንና ከአርዮሳውያን ተኲላዎች በመልካም አጠባበቅ ሕዝቡን ጠበቀ። ❤ የኤጲስቆጶሳት ጉባኤ በሰርድቄ በተሰበሰበ ጊዜ ይህ አባት ከዚያ ደርሶ አርዮሳውያንን ተከራክራቸው ምላሽ አሳጥቶም አውግዞ አሳደዳቸው አካክዮስንም ከቂሣርያ አገር ስብከቱ መንበር አሳደደው። አካክዮስም ወደ ታናሹ አርዮስዊ ወደ ሆነው ቆስጠንጢኖስ ሒዶ ከማኅበሩ ስለ ደረሰበት ውግዘትና ስደት ይልቁንም ከዚህ አባት ቄርሎስ የደረሰበትን ሁሉ በመናገር ከሰሰው። ስለዚህም አርዮሳዊ ንጉሥ ይህን አባት ከኢየሩሳሌም አሳደደው ሌሎችንም ብዙዎች ኤጲስቆጶሳትን ከአገረ ስብከቱ መንበራቸው አሳደዳቸው። ❤ ይህም አባት ቄርሎስ ወደ ተርሴስ ከተማ ሒዶ ከአገሩ ኤጲስቆጶስ ከስልዋኖስ ጋራ ተገናኘ። እርሱም ተራዳው ጥቂት ቀኖችም ከእርሱ ዘንድ አስቀመጠ። በሉክያኖስ ስብሰባ በሆነ ጊዜም ይህ አባት ከተሰበሰቡት ውስጥ አንዱ እርሱ ነው አካክዮስም ደግመው አወገዙት ረገሙትም ዳግመኛ ወደ ንጉሥ ሒዶ በዚህ በቅዱስ ቄርሎስ ነገር ሰራበት ንጉሡም ወታደሮች ልኮ ከዚያም ካለበት አሳደደው

❤ "በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። ❤ ❤ መጋቢት ፳፩ (21) ቀን። ❤ እንኳን የክብር ባለቤት ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከሙታን ለይቶ ወደ አስነሣው ወደ አልዓዛር ቤት ከደቀ መዛሙርቱ ጋራ ለሔደበት፣ አምላክ ለወለደች ለእመቤታች ለቅድስት ድንግል ማርያም ለወራዊ በዓሏ መታሰቢያና ለማቱሳላ ልጅ ለቅዱስ ላሜህ ለዕረፍቱ መታሰቢያ በዓሉ በሰላም አደረሰን። በተጨማሪ በዚች ቀን ከሚታሰቡት፦ ለከበሩ ሰማዕታት ከቅዱሳን ቴዎድሮስና ከጢሞቴዎስ ከመታሰቢያቸው ረድኤትና በረከትን ያሳትፈን። + + + ❤ በዚችም ዕለት የክብር ባለቤት ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከሙታን ለይቶ ወደ አስነሣው ወደ አልዓዛር ቤት ከቀደ መዛሙርቱ ጋራ ሔደ በዚያም ምሳ አዘጋጁለት ማርታም ምግብ በማቅረብ ታገለግላቸው ነበር። ሁለተኛዋ ማርያም ግን እግሮቹን ሽቱ እየቀባች በጸጒሩዋ ታሸው ነበር። ❤ ጌታችንም አመሰገናት "እርሷ ለመቀበሪያዬ ጠብቃዋለች" በማለት ስለ ቅርብ ሞቱ አመለከተ። ዳግመኛም "ድኆች ሁል ጊዜ ከእንተ ጋራ ይኖራሉ እኔ ግን ከእናንተ ጋራ አልኖርም" አለ በዚህም ተሰቅሎ የሚሞትበት ጊዜ ቅርብ መሆን ያመለክታል ለርሱም ክብር ከሃሊነት ገንዘቡ ስለሆነ ምስጋና ይገባዋል ለዘላለሙ አሜን። + + + ❤ በዚችም ቀን አልዓዛርን ሊገሉት የካህናት አለቆች ተማከሩ ገናና ስለሆነች ምልክት በእርሱ ምክንያት ብዙዎች በጌታችን የሚያምኑ ሁነዋልና። ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን ለዘላለሙ አሜን። + + + ❤ የማቱሳላ ልጅ ቅዱስ ላሜህ፦ እርሱም አንድ መቶ ሰማንያ ሁለት ዓመት ኑሮ ኖኅን ወለደው ከወለደውም በኋላ አምስት መቶ ስልሳ አምስት ዓመት ኖረ። በድምሩ ሰባት መቶ አርባ ሰባት ዓመት ኖረ። እግዚአብሔርንም አገልግሎት በሰላም ዐረፈ። የማቱሳላ ልጅ የቅዱስ ላሜህ የፈጣሪው በረከት ከእኛ ጋር ለዘላለሙ ይኑር አሜን። ምንጭ፦ የመጋቢት 21 ስንክሳር። +++ ❤ የዕለቱ የማኅሌት ምስባክ፦ "ሚጥ ገጸከ እምኃጢአትየ። ወደምስስ ሊተ ኵሎ አበሳየ። ልበ ንጹሕ ፍጥር ሊተ እግዚኦ"። መዝ 50፥9-10። የማሚነበበው ወንጌል ዮሐ 12፥1-12። + + + ❤ የዕለቱ ምስባክ፦ "ወትቀውም ንግሥት በየማንከ። በአልባሰ ወርቅ ዑጽፍት ወኊብርት። ስምዒ ወለትየ ወርእዪ ወአጽምዒ ዕዝነኪ"። መዝ 44፥9-10። የሚነበቡት ወንጌል ኤፌ 2፥13-ፍ.ም፣ 2ኛ ዮሐ 1፥1-8 እና የሐዋ ሥራ 7፥40-51። የሚነበበው ወንጌል ሉቃ1፥20-39። የሚቀደሰው ቅዳሴ ቅዳሴ እግዚእነ ወይም የእመቤታችን የማርያም ቅዳሴ ነው። መልካም የጾም ጊዜና በዓል። በሁላችንም ይሁንልን። ❤ በየቀኑ ይህን ቴሌግራም ላይ ማግት ከፈለጉ ከታች ያለውን ሊንክ ተጭነው ይቀላቀሉ። @sigewe https://t.me/eotcw

photo content